tgindex
Selam comparative Religion Student

Selam comparative Religion Student

Статистика

እንሸ አላህ በዝህ ቻናል የተለያዩ በንፅፅር ዙርያ ያሉት ነገራት እና የመፅሓፍ ቅዱስ ጥናት ምደረግበት ይሆናል በሰለፍይ ወንድማችን አብድሰላም مقارنة الأديان

Последний пост
3 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
98
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
35
21 постов
Вовлечённость
35,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
11
1/48двое суток
12
1/72трое суток
13

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • Channel name was changed to «Selam comparative Religion Student»

  • 2 авг.11из Abi_Abik

    ወንጀል ምን ያህል ሕይወታችን ሊያጨልም ይችላል??? ብዙ ሰዎች.......   ጉዳያቸው ሲሰናከልባቸው "የሰው ዐይን ነው" ይላሉ።    ሪዝቃቸው ሲጣበብባቸው "የምቀኛ ሴራ ነው" ይላሉ።    ሀሳብ ጭንቀት ሲበዛባቸው "ይህማ ድግምት ነው" ይላሉ።    በጣም ጥቂቶች ናቸው; ቆም ብለው "የእኔና የጌታዬ ግንኙነት ሊያበላሹ የሚችሉ ተውበት ያላረኩባቸው ምን ያህል ወንጀሎች አሉብኝ??" ብለው ከነፍሳቸው ጋ ሂሳብ የሚሰሩት። ቁርኣን ከፍተህ ብታነበው.........    ስንት ህዝቦች ናቸው አላህ ያጠፋቸው??    ስንት ከተሞች ናቸው አላህ ያወደማቸው??    ስንት ህዝቦች ናቸው በጎርፍ፣ በጩኸት፣ በነፋስ፣ በማስመጥ፣ ሌሎቹ ወደ ሌላ ፍጥረት በመቀየር ሌሎቹ ከሰማይ ድንጋይ በማዝነብ ያጠፋቸው???     የእነዚህ ሁሉ የመጥፊያ ሰበብ ምን ነበር??? ቁርኣን ይነግርሃል....... ﴿فَأَخَذَهُمُ اللَّهُ بِذُنُوبِهِمْ﴾ {አላህ በወንጀላቸው (ሰበብ) ያዛቸው።} ﴿فَأَهْلَكْنَاهُمْ بِذُنُوبِهِمْ﴾. {በወንጀላቸው (ሰበብ) አጠፋናቸው።} ወንጀል፦ ለአፍታ ተፅፎ ከዝያም የሚሰረዝ ክስተት አይደለም; ወንጀል ማለት የሚከረፋ ሽታ ያለው አለርጂክ ነው። ወንጀል........     የዕድሜህ በረካ ይወስድብሃል!!     ከልብህ ላይ የዒባዳ ጥፍጥና ያስወግድብሃል!!     ሰላት ያከብድብህና እርጋታም ይሁን ሰኪና ይነሳሃል!!     ከቁርኣን ያራርቅሃል!!        ልብህ ያደርቅብሃል!!        የሪዝቅ በር ይዘጋብሃል!!       ብዙ ፀጋዎች ቢኖሩህ እንኳ ጭንቀት ይለቅብሃል!! ይህ ሲባል .......     የመከራ ሁሉ መንስኤው ወንጀል ነው ማለት አይደለም። አላህለባሪያው ደረጃውን ከፍ ሊያደርግለት አሊያም ወንጀሉን ሊምረው ሲል ሊፈትነው ይችላል። ሆኖም........    ወንጀላችን ምን ሊያስከትልብን እንደሚችል አላህ በቁርኣኑ የነገረን ማስጠንቀቂያዎች መርሳት የለብንም።     የሆነ ሰዓት ይኑርህ......     ለብቻህ ተነጥለህ እያንዳንዱ ወንጀልህን እየዘረዘርክ ከነፍስህ ጋ የምትተሳሰብበት።    እንደ ተውበት ያለ: የኸይር በር የሚከፍት; እንደ እስቲግፋር ያለ: መከራን የሚያነሳ አንድም ነገር የለም!! hamdu

  • ለነብዩ ሙሀመድ ወህይ እንዴት መጠላቸዉ!! بسم الله الرحمان الرحيم 🍭እንደምታወቀዉ ጠላት ከዱሮም ጀምሮ እስከ ዛሬ አንተን ወይም ድንህን ምያጠፋ መንገድ ካጣ ወደ ስድብና ወደ ትችት ይሄዳል ካፍሮች እስልምና እየተስፋፋ መሄዱን ስያዩ ምያረጉት ስጠፋቸዉ ያለ የሌላዉን ለማንቋሸሽ ይጠቅመናል ያሉትን በማምጣት ተያይዟሉ ከነዛም ዉስጥ 1 ነብዩ ሙሀመድን ሃርስ ብን ሂሻም ምባል ሰዉዬ ወህይ/ግልጠተ መለኮት እንዴት ነዉ ምመጣልህ ብሎ በጠየቃ ግዜ እንድ ኣሉ ኣንዳንዴ በደዉል ድምፅ አምሳያ ይመጣልኛል ኤሄም በኔ ለይ በጣም የበረታ ነዉ ከዛም ወህዩ ይቆረጥና ያለኝን በልቤ እዛለሁ ኣንዳንዴ ደሞ መልኣኩ ጅብርል በሰዉ ተመስሎ ይመጣና ያናግረኛል ብሏል ። ሀድሱን ኣዕሻ በሰህህ አል ቡካር 2ኛ ሀድስ ለይ ዘግባለች እናም በሌላ ቦታ ነብዩ ሙሀመድ ራሳቸዉ የደዉል ድምፅ እንደምጠላ ያሱ ድምፅ ያለበትን ቦታ መላዕክት እንደማይገቡ ተናግሯሉ ሀድሱን ሙስልም ዘግበዉታል 👉እናማ ጥያቄያችን ነብዩ ሙሃመድ የደዉል ድምፅ እንደምጠላ ተናግረዉ ለርሳቸዉም ደሞ የመጠላቸዉ በሱ ድምፅ ነዉና ታድያ ለርሳቸዉ የመጠዉ ትክክል አይደለም ማለት ነዉ?? ይላሉ👇 በመጀመርያ ሀድሱ በቅጡ ባለመረዳትና ባለማያት የምመጣ ነዉ ሀድሱ ምንድነው ምለዉ ሀድሱን እንይ (مثل صلصلة الجرس) በደዉል ድምፅ አምሳያ) ታድያ የቱጋ ነዉ በደዉል ድምፅ ይመጣል ያሉት እች مثل የምትለዉ ቃል (ምስል/አምሳያ) የምትለዉን ፍች ትሰጠናለች ታድያ ነብዩ ያሉት በሱ ድምፅ አምሳያ ኣሉ እንጅ በሱ ድምፅ ኣላሉም ✍እችን مثل የምትለዉ ቃል ከፍል መመሳሰልን እንጅ ሙሉ በሙሉ መመሳሰልን አታስዝም ታድያ ይህ ድምፅስ ምንድነው ከተባላ *የመላአኩ ጅብርል ክንፍ ድምፅ ነዉ) በማለት ኡለማኦች እንዳስቀመጡት ታላቁ ልቅ እብን ሀጀር በፈትሁ አል ባር 1/25 ኤሄንን ሀድስ ስያብራሩ ያስቀምጣሉ አክለዉም እንድ ይላሉ (እንዴት ይመሳሰላል መላዕኩ ያረገዉ ነገር መላዕክት ከምሸሹት ነገር ጋር?) ብባል መልሱ; ኣንድ ነገር ከኣንድ ነገር መመሳሰሉ ያ ነገር ሙሉ በሙሉ መመሳሰልን አያስዝም ይላሉ ቀጥለዉ እዝጋ የተፈለገዉ አይነቱን መግለፅ ነዉ ይላሉ ✋ታድያ እዝጋ የተፈለገዉ ሁኔታዉ መግለፅ እንጅ በፍፁም ከደዉል ድምፅ ነዉ የምለዉን ኤሄ ሀድስ አያስዝም ከምያስዋሹት ነገር ሁሉ አምላካችን አሏህ ጠራ ወሏሁ አዕለም ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏህ ወበረካቱሁ

  • без подписи

  • قال الله (ويل لكل همزة لمزة) الآيه يقول عبد الله الن عباس (هم مشاؤون باالنميمة المفرقون ببن الأحبة.. #(ለሀሜተኛ ለዘላፍ ሁሉ ወዮለት)# እችን ኣያ በማስመልከት አብደሏህ እብን መስዑድ እንድ ይላሉ; እነሱም ሀሜትን ይዘዉ ምራመዱ ናቸዉ በሁለት ወዳጆች መሀከል ምያለያዩ ናቸዉ። 👉ይላሉ በህርግጥም አሏህ ለንደዝህ አይነት ሰዉ በእሳት እንደምቀጠዉ ዝቷል. የሰዎችን ወሬ ከመመላለስህ በፍት አንተ ማን ነህ አንተ ከንደዝህ አይነት ሰዉ ርቀሃልን መጀመርያ በራስህ ለይ ስራ። 🍭ብዙዎቻችን ቁርሳችን ሰዎችን ማማት በሆና ግዜ ለይ ነዉ ያለነዉ በሰዎች ጉዳይ በማያስገበህ ነገር አትግበ አንተ በራስህ ለይ በስራህ ለይ ብዝ ሆን ሰዎች ስለአንተ ብያወሩህ ብያሙህ አንተን ምጎዳ ነገር የለዉም ብጠቅምህ እንጅ አንተ ብታማቸዉ ግን ትጎዳለህ።

  • 26 мая37из abumuazhusenedris

    ዐረፋ ተራራ ቁሞ የዋለ ሰው ምላሱን በዚክር ተግቶ ያላወሰው። አይኖቹን በለቅሶ በእንባ ያራሰው ደስ ይበልህ እያልኩ ደስታየ ይድረሰው። ተራረውን ሳስብ የህዝቡን ተማፅኖ እጁን ሲዘረጋ ጌታውን ተማምኖ። ካላህ ውጭ ያለውን እርግፍ አርጎ ጥሎ ለአዛኙ ጌታ ሐጃውን ነጥሎ። አንዱ ጤና ስጠኝ አንዱ ልጅ እያለ አንዱ ዱንያ ስጠኝ ሌላው እድሜ እያለ። ሁሉም በየሐጃው ኢላሂ እያለ ዘጠነኛውን ቀን ዐረፋ ላይ ዋለ። ሲመሽ ሙዝደለፋ ለማደር ተጓዙ ተኝተው ያድራሉ እንድህ ነው ትዛዙ። ግን ፈጅርንም ሰግደው መሽዐሩ ላይ ቆሙ ብርሀኑ እስኪፈካ በዱዓ ተመሙ። መቸም ቦታው ሲመች መሽዐረል ሐራሙ እኛም ለወደፊት ያድርሰን ከሪሙ። ጫር ጫር ይጨረስ እንዴ አቡ ሙአዝ

  • Aselamu aleykum werhmetulahi weberekatu Hustaz ይህን ጥያቄ 🚩ለነብዩ ሙሐመድ መገለጥ(ወህይ) እንዴት ይሰጥ ነበር? በሐዲስ ውስጥ የተገለጸው አስገራሚ መግለጫ ቁርአን ስለ ሰይጣን ሲናገር:- ሱራ 15:34:- (አላህ) አለው «ከርሷም ውጣ፡፡ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና፡፡» ስለ ተረገመው እርግማን ደግሞ tafsir ibn kathir ሲናገር:- ተፍሲር ኢብን ካሲር ሱረቱል…

  • Aselamu aleykum werhmetulahi weberekatu Hustaz ይህን ጥያቄ 🚩ለነብዩ ሙሐመድ መገለጥ(ወህይ) እንዴት ይሰጥ ነበር? በሐዲስ ውስጥ የተገለጸው አስገራሚ መግለጫ ቁርአን ስለ ሰይጣን ሲናገር:- ሱራ 15:34:- (አላህ) አለው «ከርሷም ውጣ፡፡ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና፡፡» ስለ ተረገመው እርግማን ደግሞ tafsir ibn kathir ሲናገር:- ተፍሲር ኢብን ካሲር ሱረቱል አል-ሒጅር 15 ፡ 34-37:- ሳኢድ ቢን ጁቤይር ሲናገር አላህ ኢብሊስን (ሰይጣንን) በረገመው ጊዜ መልኩ ከመላዕክት ወደተለየ መልክ ተቀየረ፣ ድምጹም እንደ ደወል ድምጽ ሆነ፡፡ በዚህም ምድር ላይ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የሚሰማ ማንኛውም የደወል ድምጽ የዛው የሰይጣን ድምጽ አካል ነው፡፡ ይህ በእንዲ እንዳለ በአንድ ወቅት ነብዩ ሙሐመድ እንዴት መገለጥ እንደሚመጣላቸው ሲጠየቁ የመለሱት:- ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 1፣ 1 ፡ 2 :- አል-ሃሪስ ቢነ ሂሻም ነቢዩን እንዲሀ ሲል ጠየቃቸው፡- ራእዩ ሲወርድ የሚመጣለዎት በምን ሁኔታ ነው? እርሳቸው ሲመልሱም መልአኩ አንዳንድ ጊዜ የደወል ድምጽ በሚመስል ድምጽ እየተናገረ ይመጣል፤ ይህ ዐይነቱ የራእዩ አወራረድ ለእኔ በጣም ከባዱ ልቋቋመው የማልችለው ዐይነት ነው፡፡ ትቶኝ ከሄደ በኋላ መልአኩ የነገረኝን አስታውሰዋለሁ፡፡ አንዳንዴ መልአኩ ሰው በመምሰል ወደ እኔ ይመጣና ያናግረኛል እኔም ምን እንዳለኝ እረዳለሁ አስታውሰዋለሁም፡፡ አኢሻ አክላም ራእዩ በእርሳቸው ላይ በወረደ ጊዜ በከባድ ብርድ ሰዓት ግንባራቸው ላብ በላብ ይሆናል፡፡ ✨ሊመለሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች:- 1. ድምጹ ከሰይጣን ድምጽ ጋር እንዴት ሊመሳሰል ቻለ? ሰይጣን አላህ ሲረግመው መልኩና ድምጹ ሲቀየር ድምጹ የተቀየረው እንደ ደወል ድምጽ ወደሚመስል ድምጽ ነበር፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ራዕዩ ወደ እርሳቸው እንዴት እንደሚመጣላቸው ተጠይቀው ሲመልሱ መልአኩ የደወል ድምጽ በሚመስል ድምጽ እንደሚያናግራቸው ተናግረዋል፡፡ እንዲያውም ከላይ እንዳነበብነው ማንኛውም በምድር ላይ ያለ የደወል ድምጽ የሰይጣን ድምጽ አካል እንደሆነ አስረግጠው ነግረውናል፡፡ እንግዲህ እርሳቸው መጀመሪያ እንደ ገመቱት ሰይጣን ካልሆነ በስተቀር ገብርኤል ለምን ብሎ የሰይጣንን ድምጽ ተውሶ ሊያናግራቸው ይችላል? 2. እንደ ደውል ድምጽ የሚመስለው የሰይጣን ድምጽ የመባረክ ፍሬ ሳይሆን የእርግማን ፍሬ ነው፡፡ ይህን የእርግማን ፍሬ የሆነውን መጠቀም ደግሞ ለአላህ በመገዛት ላለ መልአክ የሚመጥን አይሆንም፡፡ የዋሻው እንግዳ ገብርኤል ከነበር የራሱን ድምጽ መጠቀም ትቶ የተረገመውን የሰይጣንን ዐይነት ለመጠቀም የተገደደው ለምንድን ነው? መልአኩ ገብርኤል ለመሆኑ ታማኙ ማስረጃስ የትኛው ነው? 3. መልአኩ ገብርኤል ተልኮ ወደ ሰዎች ሲመጣ ነቢዩ ሙሐመድ የመጀመሪያ አይደሉም፤ በሱረቱል መርየም ላይ ዘካርያስንና ማርያምን እንዳነጋገረ እናነባለን፡፡ ያኔ ያነጋግር የነበረው በተረጋጋና አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ ሲሆን፣ ነቢዩ ሙሐመድን ግን የሚሞቱ ከዛ ቀን በኋላ ፀሐይን የማያዩ እስኪመስላቸው በማሰቃየት ነበር፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ላይ ባሕሪው የተቀየረው ለምንድን ነው? 4. ይህ የዋሻው እንግዳ በሱረቱል አል-አለቅ 96 ቁጥር ሁለት ላይ ‹ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)› ብሎ አንብቦላቸዋል፡፡ ይህ ቁርአን ውስጥ ከተጠቀሱት የጽንስ እድገት ደረጃዎች መካከል ሁለተኛው ደረጃ ነው፡፡ ይህንን ሲናገር እንዲህ የሚባል የጽንስ የእድገት ደረጃ እንደሌለና ከሳይንስ ጋር እንደሚጋጭ አያውቅም ነበርን? አላህስ ቢሆን ስለ ፍጥረቱ ምንም ዐይነት ዕውቀት የለውምን? አላህ ሁሉን አዋቂ ከሆነ ደግሞ እንዲህ ዐይነት ስህተት የፈጸመው የሂራ ዋሻ የነቢዩ እንግዳ ማን ነበር? 5. ኢማም ሙስሊም ነቢዩ እንዲህ ብለው መናገራቸውን ዘግበዋል፤ ሐዲሱ የተላለፈው በአቡ ሁሬይራ ነበር፡- "የትንሳኤ ቀን እየተቃረበ ሲሄድ የአማኞች ራዕይ ሐሰተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ እውነተኛ ራዕይ የሚያይ በንግግሩ እውነተኛ የሆነ ሰው ብቻ ነው፡፡ የሙስሊም ራዕይ አርባ አምስት እጁ ትንቢታዊ ነው፡፡ ሦስት ዐይነት ራእዮች አሉ፣ አንዱ ምልካም ራዕይ ከአላህ የሆነ ነው፡፡ ሁለተኛው አስጨናቂ የሆነ ክፉ ራእይ ከሰይጣን የሆነና ሦስተኛው ከራሱ ከሰው አሳብ የሚወጣ ነው፡፡ …" ብለዋል፡፡ የነቢዩ የሂራ ዋሻው ራእይ ደግሞ ብዙ ስቃይ ያለበትና በሐሰቶች የተጨናነቀ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ታዲያ ያን የመሰለ እንግልትና ጭንቅ ከበዛባቸውና መልእክቱም ሐሰተኛ ከሆነ የዋሻው እንግዳቸው መልአኩ ገብርኤል ነበር እንዴት ሊባል ይችላል?

  • ማንም መጥቶ ሊሰብካችሁ አይገባም መንገድ ላይ ወይም ስራ ላይ ሆናችሁ የሆነ ክርስቲያን ቢገጥማችሁ እናም ሊሰብካችሁ ቢሞክር እነዚህን ማስታገሻ ክትባት ከትቧቸው። አይከብዱም ቀላል ሆነው ለማንም ማስታገሻ መድኃኒት ናቸው በቃላችሁ  ያዟቸው። ኢየሱስ ያድናል ተቀበሉ ከተባላችሁ የሚከተለውን በሉ ኢየሱስ ራሱ በጨነቀው ሰዓት የሚያድነው ሲፈልግ ነበር እሱ ራሱ አዳኝ ያስፈልገዋል። “አሁን ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ነገር ግን ስለዚህ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ።”   — ዮሐንስ 12፥27 ኢየሱስ አድነኝ እያለ ወዝ በወዝ ሆኖ ዱዓ ያደረገበትንም  ጨምሩላቸው። “በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ።”   — ሉቃስ 22፥44 ኢየሱስ ሞቶ ተነስቷል ሞትን ድል አደረገ ከተባላችሁ የሚከተለውን በሉ አምላኬን መቃብር ውስጥ አልፈልግም መቃብር የሚገቡት ሙታን ፍጡራን ብቻ ናቸው። አምላኬ የሞት እና ህይወት ፈጣሪ እንጂ ሟች አይደለም። በባይብል እንኳን ኢየሱስን ሞቶ እንዳይበሰብስ አምላክ ነው ያስነሳው። ባያስነሳው በስብሶ ይቀር ነበር ይላል። ³⁰ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤ …  “እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል።”   — ሐዋርያት 13፥34 ብስብስ ነገር አላመልክም ብላችሁ ደግሞ ድብድብ ውስጥ እንዳትገቡ። ኢየሱስ ይህን አደረገ እንዲህ ተዓምር ሰራ ከተባላችሁ የሚከተለውን በሉ መልክተኛ ነብይ ስለሆነ አምላክ ተዓምር እንዲያሳይ ይሰጠዋል። የሚያደርገው በራሱ አይደለም በአምላክ ሀይል ነው። “እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።”   — ዮሐንስ 5፥30 “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤”   — ሐዋርያት 2፥22 አምላክ ተዓምር እና ምልክት በእርሱ በኩል ማለትም በኢየሱስ በኩል አደረገ ይላል እንጂ ኢየሱስ በጭራሽ ከራሱ ማድረግ አይችልም። ኢየሱስ አምላክ ነው ከተባላችሁ የሚከተለውን በሉ - እኔ አምላክ ነኝ - እኔ ፈጣሪ ነኝ - እኔ መለኮት ነኝ ያለበት ካለ እንዲያሳዩ ጠይቋቸው !!! ከሌለ በቃ ...... አያይዛችሁ ግን ይህን ንገሯቸው ኢየሱስ ከአምላክ የሚሰማ ሰው ነበር። “ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።”      ዮሐንስ  8፥40 ኢየሱስ ወደ አምላክ ለሊት ሙሉ ሲፀልይ ያድር እንደነበር “በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።”       ሉቃስ 6፥12 ኢየሱስ በስተመጨረሻም ወደዛው ያመልከው ወደነበረው አምላክ እንደሄደ ንገሯቸው “ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።”    ዮሐንስ 20፥17 🌀🌀🌀🌀🌀🌀 በእነዚህ ነጥቦች ባታሳምኗቸው እንኳን ቢያንስ እነሱ አይሰብኳችሁም። አላህ ሒዳያ ይስጣቸው ለእኛም ፅናቱን ይስጠን!!

  • 1 апр.42из mahircomp123

    📖 ➿😀ወንድም:- Nejashi➿

  • 25 февр.64из AbuImranAselefy

    ሀቢቢ 👇 👉 ስኬትህ የሚጀምረው አላህን ማመፅህ ያሳሰበህ ቀን ነው። 👉 እድለቢስነት የሚጀምረው ደግሞ በወንጀል መርካት ሲጀመር ነው። ሰው በሰራው ግፍ ከተደሰተ የውድቀት ገደል መንገከባለል መጀመሩን ይወቅ! 📝 አቡ ዒምራን ♻️ ✅ 💬 👇 https://t.me/AbuImranAselefy/11875

  • 17 февр.63из AbuYehyaAselefy

    📢📢📢 ሰበር ዜና እንኳን ለ1447 ኛው የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ =======> 🌙 የረመዷን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ እሮብ የካቲት 11, 2018 E.C. (February 18 , 2025 G.C.) የረመዷን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል። 🔎 ዛሬ ተራዊህ የምንሰግድ ይሆናል። አልሃምዱሊላህ! 👉 የዘመናት ጌታ ቀናትን በሰው ልጆች መካከል ይቀያይራል። አምናና ዘንድሮ በብዙዎች ቤት የተለያየ ነው። አምና ከባሏ ጋር የፆመች… ከ ሚስቱ፣ ቤተሰቡ ጋር የፆመ ዘንድሮ ብቻዉን የሚፆም ብዙ አለ፣ አምና ብቻዉን የፆመ ዘንድሮ አጋር አግኝቶ የሚፆምም እንዲሁ አለ። አምና ረመዷን በአንድ ሱፍራ አብረውን ያፈጠሩ፣ ዛሬ ከመሬት በታች የሚገኙ ብዙ ወዳጆቻችን አሉ። 🔎 ረመዷንን በዓመት አንድ ወር ብቻ ነው፣ በአግባቡ እንጠቀምበት። አሥራ አንድ ወራት ያበላሸነዉን አንድ ወርሃ ረመዷን ያስተካክልናል።ረመዷን የለውጥ ወር ነው፣ የተዘበራረቀ ሕይወታችንን መስመር ያስይዝልናል።  ከአላህ የተሰጠን ችሮታ ነውና ዕድሉን በአግባቡ እንጠቀምበት። ዒባዳ ላይ እንጠናከር፣ በዱዓ ላይ እንበራታ። 📱👇👇👇 https://t.me/AbuYehyaAselefy https://t.me/AbuYehyaAselefy https://t.me/AbuYehyaAselefy

  • 17 февр.43из Abdul_halim_ibnu_shayk

    || ሰበር በቱመይር ጨረቃዋ ታድናለች ነገ ረመዷን መሆኑ ተረጋግጧል !!

  • 17 февр.42из Mistre_ahbashe

    አንዳንድ ቻናሎች ረመዷን ነገ መሆኑ ተረጋግጧል እያላችሁ አትሰክሱ እስካሁን ባለው አልተገለፀም እንደውም አብዛኛ ሀገሮች ሀሙስ መሆኑን ገልጿሉ ሳዑዲን እየተጠባበቅን ነው እሷ ከ 9:00 በኋላ ነው መከታተል ምትጀምረው 11: 30 ወይም 12:00 ያየችውን ትናገራለች በአሏህ ፍቃድ እኔም ታማኝ መረጃ ላደርሳችሁ ዝግጁ ነኝ ይከታተሉ 👇👇 https://t.me/Mistre_ahbashe/5879?single

  • 13 февр.34из Mistre_ahbashe

    ጀምበር (ፀሐይ) ከወጣችበት ቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ ምርጡ ቀን.... የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "በርግጥ አላህ ይህንን ቀን (የጁሙዐን ቀን) የሙስሊሞች ክብረበዓል አድርጎታል። ወደ ጁሙዐ ሶለት የሚመጣ፣ገላውን ይታጠብ፣ ሽቶ ካለው ይቀባ እንዲሁ የጥርስ መፋቂያንም ይጠቀም። [ኢብኑ ማጀህ:1098፣ሶሂሕ አት-ተርጊብ 1/298] አል-ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላሁ ተዓላ) እንዲህ ይላሉ፦ "የጁሙዐ ሶላት ሙስሊሞች በጀመዐ (በሕብረት) ከሚሰግዱት ትልቁ ነው...." (ዛድ አል-መዓድ 1/364-365) በጁሙዐ ሌሊትና በጁሙዐ ቀን ከሚወደዱ ተግባራት መካካል በመልእክተኛው (ﷺ) ላይ ሶላዋት ማውረድ ነው።  መልእክተኛው (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "በኔ ላይ በጁሙዐ ቀን እና በጁሙዐ ሌሊት (ሐሙስ ምሽት) ላይ ሶለዋት አብዙ። [(ዛድ አል-መዓድ 2/420)] ቀጥታ በሐዲስ እንደመጣው መልእክተኛው (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "በኔ ላይ በገፍ (በብዛት) ሶለዋትን በጁሙዐ ቀን እና በጁሙዐ ሌሊት (ሐሙስ ምሽት)  ላይ አብዙ። በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶለዋትን ያወረደ፣ አላህ በሱ ላይ 10 ጊዜ ያወርድበታል። (ሶሂሕ አል-ጃሚዕ:1209) ውዱ የአላህ ነብይ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "ከሶላቶች ሁሉ ምርጡ ሶላት በጁሙዐ እለት በጀመዐ የሚሰገደው የፈጅር ሶላት ነው ።"(አስ-ሶሂሓ:1566) አውስ ቢን አውስ አስ-ሰቀፊ ( ረሂመሁላሁ ተዓላ) የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አለ፦ ❝...በጁሙዓ ቀን በትክክል የታጠበ፣ ከዚያም ወደ ኹጥባ በጊዜ የሄደ፣ በመጓጓዣ ሳይሆን በእግር የሄደ፣ ኢማሙ (ኸጢቡ) አጠገብ ቀርቦ የተቀመጠ፣ የሚያዳምጥና የማያወራ...የሆነ ሰው አመቱን ሙሉ እንደፆመና እንደሰገደ ይቆጠርለታል።❞ ሐዲሱን፡ ኢማሙ አሕመድ፣አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል/ ሸይኽ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል (ሶሂህ አል-ጃሚዕ አስ-ሰጊር ቁጥር: 6405) አል-ሙላ አል-ቃሪዕ ይህንን ሐዲስ አስመልክተው ማብራሪያ ሲሰጡ የሚከተለውን አሉ፦ ❝...ዐለማዎች እንዲህ አሉ: 'ከመልእክተኛ (ﷺ) ሐዲሶች በአጠቃላይ ከዚህኛው ሐዲስ የበለጠ አጅር (ምንዳ) ያለው የበለጠ ምናውቀው የለም።'❞ [ሙርቃት አል-መፋቲህ ሸርህ ሚሽካት አል-መሳቢህ፣ (3/484)] https://t.me/+T8MoT_By-xRlZWQ0 አል-ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ “የጁሙዐ ቀን ከሳምንት ይስተካከላል፣ ረመዷን ደግሞ ከአመት ይስተካከላል እንዲሁም ሐጅ ከሙሉ ሕይወት የሚስተካከል ነው።” [(ዛድ አል-መዓድ (1398)] ➝ በጁሙዐ እለት ከሚወደዱ ተግባራቶች መካከል አንዱ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ) ነው፡ መልእክተኛው (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "በጁሙዐ እለት ሱረቱል ከሕፍን ያነበበ፣እስከ ቀጣይኛው ጁሙዐ ድረስ ብርሃንን (ኑርን) ይላበሳል።" [ሶሒህ ጃሚዕ አስ-ሰጊር 2/6470] ሌለኛው በጁሙዐ እለት ከሚወደዱ ተግባራት መካከል ዱዐ ነው። መልእክተኛው (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "በጁሙዐ እለት አንዲት ሰዓት አለች ማንኛውም ሙስሊም ዱዓ ካደረገ፣ ዱዓው ተቀባይነት አለው።" [ቡኻሪ:5295፣ ሙስሊም:852] አል-ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) አንዲህ አለ፦ "በጁሙዐ እለት፣ የአሱር ሶላት የመረሻዋ ሰዓት ላይ የሚደረገው ዱዓ ተቀባይነት ያገኛል።" [ዛድ አል-መዓድ: 1/104] አክለውም አል-ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ «በጁሙዐ እለት ዱዓ ኢስቲጃባ የሚሆንበት ሰዓት ልክ እንደ ለይለቱል ቀድር አይነት ነች።» [ዛደል መዓድ: 1/398] ሌለኛው ከጁሙዐ ቀን ቱሩፋቶች መካከል ታላላቅ ወንጀሎች ሲቀሩ ጥቃቅን ወንጀሎች ይታበሳሉ። [አስ-ሲልሲለህ አስ- ሶሒሐህ: 3623] መልእክተኛው (ﷺ) እንዲህ ብለዋል አላህ ዘንድ ምርጡ ቀን የጁሙዐ ቀን ነው። [ሶሂሕ አል-ጃሚዕ:1098፣ሲልሲለህ አስ- ሶሒሐህ:1502] ታላቁ ሶሃባ ዐብዱሏህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የሚከተለውን ብለዋል፦ «የሁሉም ቀናቶች መሪ ጁሙዐ ሲሆን፣ የወራቶች መሪ ደግሞ የረመዷን ወር ነው።» [መሰነፍ ኢብን አቢ ሸይበህ:5552] ሌለኛው ከጁሙዐ ቀን አዳቦች መካከል ኹጥባን በትኩረት ማድመጥ ይሻል። ታላቁ ታቢዒይ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር (ረሂመሁላህ) የሚከተለውን ይላሉ፦ "ኸጥባ እየሰማሁ ወሬን ከማውራት አናቴን በጅራፍ ብገርፍ እኔ ዘንድ እጅግ የተወደደ ነው። [ጦበቃት ኢብኔ ሰ'ዐድ 6/260] አሽ-ሸይኽ ዐብዱል-ዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) የሚከተለውን አሉ፦ "በኹጠበህ ሰዓት ሰላምታን መመለስ አልተደነገገም፤ይልቁንስ ዝም ማለት ነው።" [መጅሙዑል ፈታዋ 12/339] ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ፦ "የጁሙዐ ኹጠባ  እየተደረገ ሰላምታን ማቅረብ አይፈቀድም፤ እንዲሁም ለሰላምታ ምላሽ መስጠት እርም ነው።" [ፈታዋ 16/100] ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ፦ «ከጁሙዐ ሕግጋቶች መካከል ኢማሙ ኹጠባ እያደረገ ሳለ አለመናገር ነው።» [አል-ሙለኸስ አል-ፊቅህ 1/198)] በተጨማሪም ሸይኹ እንዲህ አሉ፦ "...ኢማሙ ኹጠባ እያደረገ ከመጣ ሁለት ረከዓዎችን ሳይሰግድ መቀመጥ የለበትም።» [አል-ሙለኸስ አል-ፊቅህ 1/198)] ✍  Translated by: Abu Hafsah ˢʰᵃʳᵉ ᵗʰᵉ ᵏʰᵃʸʳ | ʲᵒⁱⁿ https://t.me/semirEnglish https://t.me/+T8MoT_By-xRlZWQ0 https://t.me/+T8MoT_By-xRlZWQ0

  • 12 февр.26из Abdul_halim_ibnu_shayk

    || ሴቶች ከወንዶች የሚለዩባቸው ህግጋቶች ! በአብዘሃኛው አሕካም ሴቶች ከወንዶች ጋር ተመሳሳይ ፍርድን ይጋራሉ። በጥቂት አሕካሞች ደግሞ ከወንዶች ለየት ያለ ፍርድን ያስተናግዳሉ። ከወንዶች ከተነጠሉባቸው አሕካሞች መካከል... ٠ የሴት ልጅ ሽንት (በህፃንነቷ) ውኃን በማፍሰስ ብቻ አይጠራም፤ የግድ እንደ አዋቂ ሽንት እሽት ተደርጎ መታጠብ አለበት። ٠ከሸናች ቡኃላ ለኢስቲንጃእ (ለውኃ) ፋንታ ኢስቲጅማር ማድረግ (ድንጋይነ መሰል ነገር መጠቀም) አይቻልላትም። ٠ ግርዛቷ ዋጂብ (ግዴታ) አይደለም፤ በወንዶች ሲሆን ዋጂብ ይሆናል። (መዐል ኺላፍ...) ٠ፀጉሯን መላጨት ሐራም ይሆንባታል። ٠ሴቶች አቅመ መጠን መድረሳቸውን ከሚያሳዩ ምልክቶች “ሐይድ ማየትና፤ ማርገዝ” የሚጠቀሱ ሲሆን፤ እነዚህ በወንዶች አይታዩም። ٠ፈፅሞ አዛን ማለት አትችልም። ٠ ለወንዶች ኢቃማ ማድረግም አትችልም፤ ለግሏ ከሆነ ቢቻልላትም። ٠በሶላት ውስጥ ሆነ ከሶላት ውጪ ድብቅ ገላዋ (ዐውራዋ) ከወንዶች አውራ የተለየ ነው። ይኸውም... - አጅነቢዮች አጠገብ (ሶላትው ውስጥ ሆነ ከሶላት ውጪ) ሙሉ ሰውነቷን መሸፈን ግዴቴዋ ነው። - አጅነቢዮች ከሌሉ በሶላት ውስጥ ፊቷንና መዳፎቿን መክፈት ትችላለች። ٠ ፉሉሓ መግባት ሐራም ይሆንባታል። (የተጠላ ብቻ ነው ሐራምነት አይደርስ ያሉ እንዳሉ አይዘነጋም) ለወንዶች ከሆነ ሽርጥ አድርገው ከሆነ የተፈቀደ ነው። ٠ አጅነቢዮች ካሉ ሶላት ላይ ድምጿን ግልፅ (ጀሕር) አድርጋ መስገድ አትችልም። ٠በሶጁድና በሩኩዕ ሳዓት ሰውነቷን ሰብሰብ ታደርጋለች። ለወንዶች ሲሆን እጆቻቸውን ከሰውነታቸው ማራራቅ ነው የሚገባቸው። ٠ በሶላት የሆነ ነገር ቢያጋጥማት እጆቿን ታማታለች፤ ለወንዶች ሲሆን ተስቢሕ ማድረግ ነው የተደነገገው። ٠ ሶላተል'ጀማዓ (የሕብረት ሶላት) ዋጂብ አይሆንባትም፤ ያለ ባሏን ፍቃድ መገኘትም አትችልም ፤ በቤት መስገዷ ለሷ የተሻለ ነው። ٠ ጁሙዓም ዋጂብ አይሆንባትም። ٠ ፈጽሞ ''ኹጥባ'' ማድረግ አትችልም። ٠ ለወንዶችንና ለወንዳ ገረዶችን ኢማም መሆን አትችልም። ٠ ሴቶችን ኢማም ኹና ስታሰገድ መሃላቸው ትቆማለች፤ ወንድ ሲሆን ከፊት ለፊት ትንሽ ወጣ ብሎ የሚቆም ሆኖ ሳለ ። ٠ ሐር'ን መልበስና ማንጠፍ ትችላለች ። ٠ የወርቅ ጌጥ (ሃብል...ቀለበት) መጠቀም ትችላለች። ٠ በዒድ ተክቢራና በሐጅ ተልቢያ ድምጿን ከፍ አታደርግም ٠ሙታ ስትከፈን በአምስት ልብሶች ብትከፈን የተሻለ ነው፤ ለወንዶች የተሻለው ሶስት ልብስ ሆኖ ሳለ። ٠ ሶላተል ጀናዛ ሲሰገድባት አሰጋጅ ኢማሙ መሃሉዋ (በመቀመጫዋ ቲዪዪ) ይቆማል፤ ለወንዶች ከራስ ጌያቸው አጠገብ ። ٠ ጀናዛ መሸከም አትችልም፤ሞቿ ሴትም ብትሆን እንኳን። ٠ በጦር ሜዳ ከሙርክ ድርሻ የላትም፤ ጉርሻ እንጂ። ٠ በንብረት ነክና ወንዶች በማያውቁዋቸው ነገራት ላይ እንጂ ምስክርነቷ ተቀባይነት የለውም። ٠ የሁለት ሴቶች ምስክር ከ አንድ ወንድ ምስክርነት ጋር ይስተካከላል። ٠ ያለ መሕረሙዋ መንገድ መግባት አትችልም፤ ለሐጅም ቢሆን እንኳን ። ٠ በሐጅ ወቅት የተሳፋን ነገር መልበስ ትችላለች። ٠ ወንዶችን ተጋፍታ ሐጀረል አስወድ'ን መሳም አይደነገግላትም። ٠ በጠዋፍ ወቅት ዱብ ዱብ (ሮጥ ማለት) አይቻልላትም። ٠በሐጅ ወቅት ጸጉሯን አትላጭም፤ ይልቁን ከሁሉም ጉንጉን የትንሿን ጣት አንጓ ያኬል ብቻ ታሳጥራለች። ٠ በዐቂቃ ወቅት አንድ በግ/ፊየል ይታረድላታል። ٠ በኒካሕ ሰዓት ወሊይ ሆና መዳር አትችልም ፤ የሌላን ሰው ኒካሕም ተወክላ መቀበል አትችልም። ٠ ከሴቶች ጋር የፈረስና የግመል እሽቅድድም ማድረግ አይፈቀድም። (አንድ ወንድ ከባለቤቱ ጋር አጅነቢይ በሌለበት በእግርም ሆነ በፈረስ ቢወዳደር ይቻልለታል) ٠ ከውርስ ድርሻዋ የወንዶች ግማሽ ነው። ٠ ቃዲ (የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኛ) መሆን አትችልም ። ٠ ወተቱዋ (ማጥባቷ) እርም የማድረግ አቅም አለው። ٠ በሚከተሉት ነገራቶች ከወንዶች ትቀደማለች.. - በሞግዚትነት (ልጆች የማሳደግ ሐላፍትና በመውሰድ) - ከሙዝደለፋ ወደ ሚና በመሔድ - ሶላት ካበቃ ቡኃላ ከመስጂድ በመውጣት - ወጪ በሚደረግበት ወቅት ٠ ቂሳሳን መተግበር አትችልም። (አትገድልም ፤ አትገርፍሞ ፤ አትወግርም። ٠ ጂሓድ አይወጅብባትም ٠ ዚሚያ (ከሙስሊሞች ተስማምተው የሚኖሩ አይሑድና ነሳራዎች ዚሚይ ይባላሉ) ከሆነች ጂዝያ (ግብር) የለባትም። ٠ ጦር ሜዳ ላይ የካፊር ሴቶች አይገደሉም፤ ሙስሊሞች እስካልተጋደሉ። ٠ ከትዳር ቡኃላ በዚና ወድቃ ስትወገር ጉርጓ ተቆፍሮላት ነው መሆን ያለበት፤ ከወንዶች በተቃራኒ። ٠ በሐድ የምትገረፍም ከሆነ ተቀምጣ ነው መሆን ያለበት ፤ ወንድ ከሆነ ቆሞ ። ٠ ከሴቶች ነቢይ የለም ። በነዚህና በመሣሠሉ ህግጋቶች ሴቶች ከወንዶች ይለያሉ። ወሏሁ አዕለም ! https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk/3162

  • 12 февр.23из Multeqa_Ahlissuneh

    ⛔️ ማስጠንቀቂያ ለሴቶች! — "አንዳንድ የኢኽዋንና የሙመዪዓ ተላላኪዎች እና በሰለፊያ ስም ነጋዲዎች ውስጥ ለውጥ እየተሽሎኮሎኩ ሴቶችን አድ እያደረጉ በውስጥ እያዋሩ፣ ያልሆነ ሊንክ እየላኩ ነውና ሴቶች ጥንቃቄ እንድታደርጉ።" — "ሴቶችን አድ ከሚያደርጉ ሰዎች አላማ መሃከል፦ ሴቶችን ለማባለግና ዱርዬ ለማድረግ፣ ከትክክለኛው መንሀጅና ዐቂዳ ለማውጣት፣ የሰለፊያ ፕሮፋይል አድርጎ ለዲኑ እንደተጨነቀ አስመስሎ ቀስበቀስ አግቢኝ ብሎ ብሯን ለመብላት፣ ስልኩን ሃክ አድርጎ ለመጭበርበርና ቆሻሻ ቪዲዮዎችን ለመላክ፣ ሌሎችም ምክንያቶች አድ የሚያደርጉ አሉ።" 🔥 "እህት! ጥንቃቄ አድርጊ፣ ራስሽን ከረከሰ ሰው ጋር ሆነሽ አታርክሺ፣ በጭራሽ አድ አትመልሺ፣ የሱና ቻናል ነው ሼር አድርጊልኝ ላለ ሁሉ አትቀበይ፣ እስከአሁን የነበርሽበት ሞኝነት ይብቃሽ።" https://t.me/Multeqa_Ahlissuneh https://t.me/Multeqa_Ahlissuneh

  • 10 февр.22из UstazAbuzarhassenAbutolha

    ♦️| ጥርት ያለ ሰለፊይ ሁን! 🎙 ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ || የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha

  • 4 февр.32из Mukamil_Hussan

    ዕውቀት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ “ዒልም” عِلْم‎ ማለት “ዕውቀት” ማለት ሲሆን “ጀህል” جَهْل ማለት ደግሞ “መሃይምነት” ማለት ነው። ዕውቀት የእምነት መሠረት ነው፥ ያለ ዕውቀት በጭፍንነት የምንከተለው ነገር ጥፋት ነው፦ 17፥36 *"ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና"*፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ዕውቀት ለማግኘት ደግሞ ማንበብ ጉልህ ሚና አለው። አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ብሎ አዟቸዋል፦ 96፥1 *”አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም”*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ “ኢቅራ” ትእዛዛዊ ግስ ሲሆን ቁርኣን ሲጀምር የሚነበበው “ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም” ነው፥ ከአንድ ሱራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው እና የሚጀምረው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው” በሚል ነው፦ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሱራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏} “ቱነዘለ ዐለይሂ” تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ማለትም “ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” እኛ እንድናነበው የወረደ ነው፦ 29፥45 ከመጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ 18፥27 ከጌታህም መጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّك ቁርኣንን በማንበብ የሚገኘው ዕውቀት "ነቅል" ይባላል፥ "ነቅል" نَقْل የሚለው ቃል "ነቀለ"نَقَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከአላህ በነቢይ የሚተላለፍ ዕውቀት ነው። አምላካችን አላህ ቁርኣንን በነቢዩ ዐሳወቀ፥ "ዐለመ" عَلَّمَ ማለት "ዐሳወቀ" ማለት ነው። አላህ የማናውቀውን ሁሉ በቁርኣን ስላሳወቀን፥ እርሱ ዘንድ በላጩ ነገር ቁርኣንን ዐውቆ ማሳወቅ ነው፦ 55፥2 *"ቁርኣንን አስተማረ"*፡፡ عَلَّمَ الْقُرْآنَ 4፥113 *አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 49 ዑስማን"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከእናንተ በላጩ ቁርኣንን ዐውቆ ያሳወቀ ነው"*። نْ عُثْمَانَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُكُمْ مَنْ تَعَلَّمَ الْقُرْآنَ وَعَلَّمَهُ በመቀጠል አሁንም አምላካችን አላህ "አንብብ" የሚል ለሁለተኛ ጊዜ ያዛል፥ አላህ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ በቀለም ያሳወቀው ቸር ጌታ ነው፦ 96፥3 *"አንብብ! ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን"*። اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ 96፥4 *"ያ በብርዕ ያስተማረ"*፡፡ ٱلَّذِى عَلَّمَ بِٱلْقَلَمِ 96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ "ቀለም" قَلَم የሚለው ቃል "ቀለመ" قَلَمَ‎ ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ብዕር" ማለት ነው። በቀለም ዕውቀት በማንበብ የምናገኘው ዕውቀት "ዐቅል" ይባላል፥ "ዐቅል" عَقْل የሚለው ቃል "ዐቀለ"عَقَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን በቀለም የሚተላለፍ ዕውቀት ነው። አምላካችን አላህ ሰውን ሲፈጥረው ቋንቋ መናገርን ዐሳወቀው፥ "ዐለመ" عَلَّمَ ማለት አሁንም "ዐሳወቀ" ማለት ነው፦ 55፥3 *"ሰውን ፈጠረ"*፡፡ خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ 55፥4 *መናገርን አስተማረው*፡፡ عَلَّمَهُ الْبَيَانَ 2፥31 *አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው*፡፡ وَعَلَّمَ ءَادَمَ ٱلْأَسْمَآءَ كُلَّهَا አምላካችን አላህ ለኣደም የነገርን ስም ዐሳወቀው፥ ይህንን ዕውቀት በማንበብ መፈለግ የሁሉም ሙሥሊም ግዴታ ነው፥ "አንብብ" የሚለው ትእዛዝ ቀዳማይ ተደራሲነቱ ለነቢያችን"ﷺ" ቢሆንም ደኃራይ ተደራሲነቱ ለመላው የሰው ዘር በሙሉ ነው፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 229 አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"*" አሉ፦ *"ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው"*።  عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ እውነት ነው፤ ዕውቀትን በማንበብ ማግኘት ይቻላል፥ ቀጣዩ ይህንን ዕውቀት በጥበብ መጠቀም ነው። ጥበብን የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጦታል፦ 2፥269 *ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብንም የሚሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠ*፡፡ የአእምሮዎች ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡ يُؤْتِى ٱلْحِكْمَةَ مَن يَشَآءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ ٱلْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِىَ خَيْرًۭا كَثِيرًۭا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ ይህ ሁሉ የሚሆነው አላህ የሻ እንደሆነ ነው፥ አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል። ይህ ዲን የነቅል ዕውቀት እሳቤ ሆነ የዐቅል ዕውቀት እሳቤ አቅፏል፥ አላህ መልካም የሻለት ሰው ዱኑን ያስገነዝበዋል፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 57, ሐዲስ 25 ሙዓዊያህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ መልካም የሻለት ሰው ዱኑን ያስገነዝበዋል"*። أَنَّهُ سَمِعَ مُعَاوِيَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ يُرِدِ اللَّهُ بِهِ خَيْرًا يُفَقِّهْهُ فِي الدِّينِ، አምላካችን አላህ እርሱ በቁርኣኑ የገለጠውን ዲኑል ኢሥላምን ያስገንዝበን! አሚን። ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም

  • 4 февр.26из kedmiya_letewuhid_ste

    🔵ቀጥታ ስርጭት ቀጣይ ✨كتاب التوحيد لشيخ صالح بن فوزان                   ╰┈➢ ገ          ╰┈➢ ባ                  ╰┈➢ገ                      ╰┈➢ ባ                               ╰┈➢ በሉ 📚 🎙 ┈──── ••⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ ╰┈➢ በኡስታዝ አቡ ሀሳን ሙሀመድ አል-ኪርማኒይ https://t.me/kedmiya_letewuhid_ste?livestream=8b68d2aa5e80632d3a