- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 219
- 1/48двое суток
- 250
- 1/72трое суток
- 270
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
"በችኮላና በጥድፊያ" የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ተመላክቷል። 👉 አንዳንድ መመሪያና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የማይገመገሙ መሆኑ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። 👉 ህጎች በወጡ በሳምንት እና በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸውም እንዳሉም ተገልጿል። (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) በኢትዮጵያ የህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎች፣ የአዋጅ መሻሮችና መጣረሶች እየታዩ መሆኑን፣ ይህንንም መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ፖሊሲም ሆነ ወጥ የህግ ማዕቀፍ በሀገሪቱ አለመኖሩን ፌደራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አመለከተ። ጥናቱ "የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም በሀገሪቱ ያለውን የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም የአተገባበር ስርዓት ከረጅምና ከአጭር ጊዜ እቅዶች እንዲሁም ከቦትስዋና፣ ከጋናና ከደቡብ አፍሪካ ተሞክሮዎች አንጻር በመመርመር የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ነው። ህግ የማህበረሰብንና የመንግስትን መስተጋብር የሚመራ መሳሪያ እንደመሆኑ ተለዋዋጭነት ባህሪው ቢሆንም፣ የሚወጡ ህጎች ጥራት፣ ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተገማችነትና ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ጥናቱ ያስቀምጣል። ከ2010 ዓ.ም ወዲህ የተካሄደው የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በርካታ ህጎች የመውጣታቸውን ያህል፣ በችኮላና በጥድፊያ የሚወጡ ህጎች የህግ አወጣጥ ስርዓቱ የተረጋጋ እንዳይሆን፣ በህዝብና በባለሙያዎች ያልተመከረበት እንዲሆን እንዳደረጉት ጥናቱ ጠቁሟል። ይህም ባለሀብቶች የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ውሳኔ እንዳይወስኑ፣ ዜጎችም ስለ መብትና ግዴታቸው ያላቸው ግንዛቤ አናሳ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተመላክቷል። ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ አዋጆችን ሙሉ በሙሉ መመርመሩን ገልጿል። ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት፣ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በስድስት ተያያዥ ተቋማዊ ምሶሶዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን የለየው ጥናቱ እነሱም የህገ መንግስት የበላይነት በተግባር መረጋገጥ፣ ውጤታማ የስልጣን ክፍፍልና ሚዛን፣ ጠንካራ የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓት፣ በሙያ የታገዘ የረቂቅ ዝግጅት ተቋም፣ ትርጉም ያለው የህዝብ ተሳትፎ፣ እና ገለልተኛ የዳኝነት ቁጥጥር ናቸው። ኢትዮጵያን በተመለከተ ግን ሀገሪቱ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋትን የተመለከተ ፖሊሲ እንደሌላት፤ ጠቅላላ የህግ አወጣጥ ስርዓትን የሚመራ ፖሊሲም እንደሌለ፤ የሚወጡ ህጎችም በአብዛኛው በጸደቁ ፖሊሲዎች ላይ ከመመስረት ይልቅ የአስፈጻሚውን ጊዜያዊ ፍላጎት የሚያንጸባርቁ ሆነው መገኘታቸውን ለይቷል። በህግ ማዕቀፍ ረገድም ኢፌዲሪ ህገ መንግስት፣ ደንብ ቁጥር 6/2008፣ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና ሌሎች ሰነዶች ቢኖሩም፣ ከማርቀቅ እስከ አፈጻጸምና ክትትል ድረስ ያለውን ሂደት በአንድ ወጥነት የሚገዛ ማዕቀፍ አለመኖሩ ተጠቁሟል፤ ያለው አሰራርም በተበታተኑና በተበጣጠሱ መመሪያዎች ላይ የተመሰረተ ነው። በአተገባበር ደረጃም ከተለዩ ክፍተቶችም ውስጥ :- - ተደጋጋሚ የአዋጅ ማሻሻያዎች (ለምሳሌ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኤክሳይዝ ታክስ አዋጆች በወጡ በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸው መሆኑ) ፣ - ሰፊ የአዋጅ መሻሮች (ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 ብቻውን 18 አዋጆችንና 35 ደንቦችን መሻሩ)፣ - ተደራሽ ያልሆኑ መመሪያዎች ፣ - ተቃራኒ ይዘት ያላቸው አዋጆች መውጣት፣ - ከበላይ ህጎችና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች መኖር (በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰልን በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የያዘ ድንጋጌ በመሆኑ ማክሰኞ ወጥቶ በሳምንቱ ማክሰኞ ማሻሻያ የተደረገበት ሂደት መኖሩ) - የበታች ህጎች ያለ ተገቢ ግምገማ መውጣት ( በተለይ ታክስ አካባቢ ይሄ ችግር በአደገኛ ሁኔታ መስተዋሉ) - አዋጆች በተግባር ያለመፈጸም ይገኙበታል። ከጥንካሬ አኳያም የተለያዩ ግኝቶችን ያስቀመጠው ጥናቱ ባለ ሶስት ደረጃ የምርመራና የንባብ ሂደት፣ የፍትህ ሚኒስቴር ማጣራት ሚና፣ የህግ ማዕከልና አማካሪዎች መኖር፣ እንዲሁም በቅርቡ የተቋቋመው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ማሻሻያና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ እንደ አዎንታዊ እርምጃዎች ተጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የባለሙያ እጥረት፣ የተቋማት አለመናበብ፣ የአመራር ትኩረት ማነስ እና ወጥ የህግ ይረቀቅልኝ ስርዓት አለመኖር እንደ ዋና ዋና ድክመቶች ተለይተዋል። ጥናቱ ከጋና፣ ከደቡብ አፍሪካና ከቦትስዋና ተሞክሮ በመነሳት ፦ ° ፍርድ ቤቶች ግልጽ የህገ መንግስት ተጣጣሚነት የመተርጎም ስልጣን እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ° የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓትን ማጠናከር፣ ° ሙያዊ የረቂቅ ዝግጅት አቅምን ማጎልበት፣ ° የህዝብና የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ተወካዮች ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ፣ ° ህግ ማውጣትን ከፖለቲካ ፍጥጫ ነጻ ማድረግ፣ ° የተጠቃለለ ፖሊሲና ሁሉን አቀፍ ህግ ማዘጋጀት፣ ° ገለልተኛ የህግ ኮሚሽን ማቋቋም፣ ° በዩኒቨርሲቲዎች የሌጂስሌቲቭ ድራፍቲንግ ስልጠናና ካሪኩለም ማዘጋጀት፣ ° የህግ አወጣጥ ሉዓላዊነትን ከውጭ ተጽእኖ መጠበቅ፣ እንዲሁም የበታች ህጎችን ከአዋጅ ጋር ተጣጥመው መውጣታቸውን የሚከታተል ስርዓት መዘርጋት የሚሉ ምክረሃሳቦችን አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
#የግብር_ጉዳይ የኢትዮጵያ የፌደራል #ጠበቆች ማህበር ዝማኔ ኩነት ወይም Update on Current Affairs በሚል ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መደብዳቤ ማህበሩ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር የጠበቆች ግብር አከፋፈልና ከሙያው ልዩ ባህርይ ጋርየተጣጣመ የግብር ማዕቀፍ እንዲኖር በተከታታይ ውይይቶች ማድረጉን አስታውቋል። በእነዚህ ውይይቶች በተደረሰው መግባባት እና በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 በተደነገገው መሰረት ሊዘጋጅ የሚገባውን እና የባለሙያዎች የተቀናሽ ወጪ መመሪያ ለማዘጋጀት የሚረዳውን የፖሊሲ ግብዓት ሰነድ ማህበሩ የጥናት ቡድን በመመደብ ባለፉት አራት ወራት ሲሰራ ቆይቶ ስራውን አጠናቆ ሰነዱን ለገንዘብ ሚኒስቴር አስረክቧል ብሏል። ከዚያም በላይ ማህበራችን ጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ክትትል እያደረገ ይገኛል ብሏል። በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአዋጁ መሰረት የተቀናሽ ወጪ መመሪያው ጸድቆ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ ጠበቆች አመታዊ ገቢያቸውን በህጉ መሰረት በሚያሳውቁበት ወቅት ወጪያቸው ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር እንዲያዝላቸው የሚጠይቅ ደብዳቤ በማስገባት ውጤቱን በመከታተል ላይ ይገኛል ብሏል። ማህበሩ የጠበቆችን ሙያ ልዩ ባህርይ የሚያንጸባርቅ ፣ ፍትሃዊ ፣ ግልጽ እና ተገማች የግብር ማዕቀፍ እንዲኖር ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር የጀመረውን ስራ በቀጣይነት አጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ፣ እንዲሁም የመመሪያውን ዝግጅትና አፈጻጸም በቅርብ በመከታተል ለአባላቱ ተገቢውን መረጃ በየጊዜው ያደርሳል ብሏል። የሚበረታታና የሚደገፍ ጥረት ሲሆን ውጤቱ ደግሞ በጉጉት የሚጠበቅ ነው🙏🙏🙏 የሕግ ቤት
#ለመረጃ፡ ጥሬ ገንዘብ ያላቸው ግለሰቦችና ተቋማት ገንዘባቸውን በማዋጣት በጋራ በተቋቋመ ፈንድ አማካኝነት በተለያዩ የትርፍ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ የሚያስችል “የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ” ረቂቅ መመሪያን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ተዘጋጅቷል ሰነዱን በማንበብ አስተያየት መስጠት ለምትፈልጉ ከላይ ተቀምጧል!
без подписи
ለተከታታይ አምስት (5) ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነው። ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናትና ከዚያ በላይ ከስራ የቀረ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውልን ማቋረጥ የሚያስችል አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰበር መዝገብ ቁጥር 249795 ላይ አንድ ሰራተኛ በተከታታይ ከአምስት (5) ቀናት በላይ ከሥራ ከቀረ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ጠቅሶ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ ነበር። ሆኖም ሰበር ሰሚ ችሎቱ አሁን ላይ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ከስራ ማሰናበት የለበትም የሚለውን የሕግ ትርጉም ሽሮታል። በምትኩ ከእረፍቶችና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውሉን ማቋረጥ ይቻላል በሚል ትርጉም ተሰጥቷል። ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው። ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
👉 ቃብድ ✍️ ቃብድ ማለት ተዋዋይ ወገኖች ውላቸው እንዲጸናላቸው ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት እና ሽያጩን ለማረጋገጥ አንዱ ወገን ለሌላኛው የሚሰጠው የማስያዣ ገንዘብ ነው። በኢትዮጵያ የውል ሕግ ሥርዓት ውስጥ ቃብድ ከመደበኛ የውል አፈጻጸም ለየት ያሉ የሕግ ውጤቶች አሉት። 1. የቃብድ የሕግ ውጤት በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885 እንደ ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885(1) እና (2) ድንጋጌ፣ በቃብድ የታሰረ የሽያጭ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለየው በሚከተሉት ነጥቦች ነው፦ ተቃራኒ ስምምነት እስካልተደረገ ድረስ፣ ቃብድ የሰጠው ወገን የሰጠውን ቃብድ በመተው፣ ቃብድ የተቀበለው ወገን ደግሞ የተቀበለውን ቃብድ እጥፍ አድርጎ በመመለስ ውሉን በፈቃዳቸው ማፍረስ ይችላሉ። በቃብድ የታሰረ ውል እንደ ሌሎች መደበኛ ውሎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1776 መሠረት በግዴታ እንዲፈጸም በሕግ አይገደድም። ይልቁንም ተዋዋዮቹ ቃብዱን በመተው ወይም እጥፍ በመመለስ ከውሉ የመውጣት የመውጫ ቀዳዳ ይሰጣቸዋል። የቅድመ ክፍያ እና የቃብድ ልዩነት 👇👇👇✍️✍️✍️ ተከራካሪዎች የከፈሉት ገንዘብ ቃብድ ሳይሆን ለሽያጭ ዋጋው ማሟያ የተደረገ የቅድመ ክፍያ ከሆነ፣ የቃብድ ሕግ እጥፍ መመለስ ወይም ትቶ መቅረት ተፈጻሚ አይሆንም። ቃብድ ለተዋዋይ ወገኖች ውሉን የመተው መብት የሚሰጥ ቢሆንም፣ የሚከፈለው ገንዘብ ቃብድ መሆኑንም ወይም የቅድመ ክፍያ መሆኑ በግልጽ መታወቅ አለበት። ከጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service
#ethiotelecom ኢትዮ ቴሌኮም በኦንላይን ሰነዶችን ለማረጋገጥ የሚያስችል የዲጂታል ፊርማ አገልግሎት አስጀምሯል። ኢትዮ ቴሌኮም ተገልጋዮች በአካል ሳይገኙ ሰነዶችን በዲጂታል መንገድ እንዲፈርሙና ህጋዊ ማረጋገጫ እንዲያገኙ የሚያስችለውን "ቴሌሳይን" (teleSign) የተሰኘ ሶሉሽን በይፋ ስራ አስጀምሯል። - ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ - ከፍትህ ሚኒስቴር - ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በመተባበር የቀረበው ይህ ሲስተም፣ ተገልጋዮች ካሉበት ሆነው የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን እንዲያገኙ ለማስቻል ያለመ ነው። በተለይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአካል ኤምባሲ ወይም የውክልና መስጫ ቢሮዎች ሳይገኙ የህጋዊ ውክልና ለመስጠትና ለተለያዩ ጉዳዮች የሚገጥማቸውን የጊዜና የጉዞ ወጪ ችግር ለመቅረፍ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። "ቴሌሳይን" ዜጎች ካሉበት ሆነው የሰነድ ማረጋገጥ፣ የውክልና ስልጣን እና የጠበቃ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል። በዲጂታል መንገድ ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል የውክልና ስልጣን አንዱ ሲሆን፤ ይህም የዲያስፖራው ማህበረሰብም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች በአካል ኤምባሲ ወይም ቢሮ ሳይገኙ የውክልና ስልጣን ለመስጠትም ሆነ ለማንሳት ያስችላል። በተጨማሪም ድርጅቶችና ዜጎች ማንኛውንም ህጋዊ ሰነድ ካሉበት ቦታ ሆነው በዲጂታል መንገድ እንዲያረጋግጡ የሚያስችል የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎትን ያካተተ ሲሆን፤ የህግ ባለሙያዎችም የጠበቃ ፈቃድ ለማውጣትና ለማደስ የሚጠቀሙበት የተቀናጀና ወረቀት-አልባ አሠራር በሶሉሽኑውስጥ መካተቱ ተነግሯል። ይህ የዲጂታል ፊርማ መድረክ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ የቪዲዮ ማንነት ማረጋገጫን የሚጠቀም ሲሆን፣ ከብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር በመናበብም የፊርማውን ትክክለኛነት ያረጋግጣል። ተገልጋዮች በቴሌብር አማካኝነት ክፍያቸውን ፈጽመው በቀን 24 ሰዓት አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ ይህም ቀደም ሲል ለቀናት ይወስድ የነበረውን አሰራር ወደ ጥቂት ደቂቃዎች ዝቅ እንደሚያደርገው ተገልጿል። አገልግሎቱ በኢትዮጵያ አዋጅ ቁጥር 1072 ለዲጂታል ፊርማ ከተቀመጠው ህጋዊ ማዕቀፍና ከዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች ጋር የተጣጣመ በመሆኑ በህግ ፊት ሙሉ ተቀባይነት እንዳለው ይፋ በማድረጊያ ስነስርዓቱ ወቅት ተነግሯል። ተገልጋዮች የቴሌሳይን የሞባይል መተግበሪያን ወይም telesign.et የተሰኘውን የኩባንያውን ድረ-ገጽ በመጠቀም የዲጂታል ፊርማ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።. @tikvahethiopia
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи