ABU ABDULHALIM
Статистика- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 78
- 1/48двое суток
- 89
- 1/72трое суток
- 96
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
👌⭕️ሚስቱን ቤት እንድትረጋ አድርጎ ቋሚ ስራ ባይኖረውም የቀን ስራም ቢሆን ተሯሮጦ እየሰራ እቤት ተሸፋፍና እንድትቀመጥ አድርጎ ቤቱን ለማስተዳደር በሚተጋ ታታሪ ወንድ ላይ የአላህ እዝነት ይስፈን!!! 👇👇🔻🔻👇👇 https://t.me/daewaselefiya_desse https://t.me/daewaselefiya_desse https://t.me/boruselasa_22
👌 👉 #ያጋጠመህ መከራ ወይም #ፈተና ለአንተ ጉዳት ብቻ #ሳይሆን ጥቅምም እንደሚሆን #ተረዳ !! -------------------------------------------- 👌👉 ታላቁ ኢማም አል-ሐሰን ል-በስሪ { رحمه الله تعالى } እንድህ ይላሉ :- "لاَ تَكْرَهُوا النَّوَائِبَ الْمُقْلِقَةَ، وَالأَحْدَاثَ الْمُغْمِمَةَ، فَرُبَّ أَمْرٍ تَكْرَهُهُ فِيهِ نَجَاتُكَ، وَرُبَّ أَمْرٍ تُحِبُّهُ فِيهِ عَطَبُكَ." تفسير القرطبي من سورة البقرة الآية-- ٢١٦-- ------------------------ "👌 👉 #የሚያስጨንቁ መከራዎችንና የሚያሳዝኑ ክስተቶችን አትጥሏቸው ! ! የምትጠላው ነገር ውስጥ ያንተ #መዳን { ደኅንነት } ሊኖርበት ይችላል ፤ #የምትወደው ነገር ውስጥ ደግሞ ያንተ #ጥፋት ሊኖርበት ይችላል !! ------------------------- 👌 👉 እኛ ሰዎች የምናየው የነገሮችን ውጫዊና የአሁኑን ገጽታ ብቻ ነው ። አንድ ነገር #ሲያጋጥመን ወይም ሲቀርብን { ሲያጋጥመን } "#መልካም ነው" ብለን እንመኛለን ፤ ሲጎድልብን { ስናጣው } ደግሞ እንደ #ጉዳት እንቆጥረዋለን ። ነገር ግን ነገሮችን በሙሉ ስዕላቸውና #በመጨረሻ ውጤታቸው የሚያውቀው ልዕለ ሃያሉ ጌታ الله ብቻ ነው ። ----------------------- 👌 👉 አንድ ሰው #የሚያስፈራው ወይም የሚያስጨንቀው ፈተና {ሙሲባ} #ሲደርስበት ማለትም :- የተመኘው ነገር ሳይሳካ ሲቀር ፣ ንብረት ወይም የሚወደው ነገር ሲጎድል በወቅቱ #ጥፋት ሊመስለው ይችላል !! እውነታው ግን ምናልባትም ከትልቅ ጥፋትና አደጋ ውስጥ እንዳይገባ መንገዱን የቀየረለት ጌታ ያንን ነገር ከእሱ በማራቅ ወይም ፍላጎቱን ባለማገኘቱ ሊሆን ይችላል !! ይህ የሚሆነው ግን በالله ላይ ያለው እምነትና ሠዎችን ከመጎዳት የራቀ የሆነ ጊዜ ነው !! 0 ------------------------- 0 👌 👉 በተቃራኒው ደግሞ እጅግ አጥብቀን የምንመኘውና የምንወደው ነገር ማለትም ሀብት ፣ ስልጣን፣ ወይም የትኛውም ዱንያዊ ስኬት ከተሳካልን በኋላ ለአኼራችን ወይም ለዱንያችን ውድቀትና ጥፋት ምክንያት ሊሆን እንደሚችልም መገንዘብና መረዳት ይኖርብናል !! 0 ----------------------- 0 👌 👉 እንደ አጠቃላይ የታላቁ ኢማም ንግግር በህይወታችን ውስጥ ምንም ዓይነት ያልተጠበቀና የሚያስዝን ነገር ቢከሰት እንኳ "الله በእኔ ላይ የወሰነው ነገር ሁልጊዜም ለእኔ የተሻለው ነው" ብለን በውሳኔው እንድንረካ ወይም የ الله ን ውሳኔ ወደን እንድንቀበል እና ልባችንን ሙሉ በሙሉ በ الله ጥበብና እቅድ ላይ እንድናስጠጋ ያስተምረናል !! 0 ----------------------- 0 አላህ ከፈተና ከመከራ ና ከችግር ይጠብቀን !! #ወንድማችሁ አቡ ማሂ #አብደልከሪም { ደሴ } 👌 👉 https://t.me/Abumahiasselefi/10039
ወንድምህን ጠቃሚ እንጂ ጎጂ አትሁነው !! 👌 👉 ታላቁ ታቢዕይ የህያ ኢብኑ ሙዓዝ { ر حمه الله تعالى } እንድህ ይላል :- « لِيَكُنْ حَظُّ الْمُؤْمِنِ مِنْكَ ثَلَاثَةً: إِنْ لَمْ تَنْفَعْهُ فَلَا تَضُرَّهُ، وَإِنْ لَمْ تُفْرِحْهُ فَلَا تَحْزُنْهُ، وَإِنْ لَمْ تَمْدَحْهُ فَلَا تَذُمَّهُ.» { جامع العلوم والحكم وسير أعلام النبلاء } «አንድ አማኝ ወንድምህ ከአንተ የሚያገኘው ድርሻ ሦስት ነገሮች ይሁኑ !! ----------------------------- 1. ካልጠቀመከው አትጎዳው 2. ካላስደሰትከው አታሳዝነው / አታስከፋው / 3. ካላወደስከው (ካላመሰገንከው) አትማው (አትነቅፈው) { جامع العلوم والحكم وسير أعلام النبلاء } ----------------------- 👌 👉 #ይህ የታላቁ ቴብዕይ የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ ምክር በሰው ልጅ #ማህበራዊ ህይወት ውስጥ ትልቅ ሰላምን የሚያሰፍን « ትልቅ ምክር » ነው። #ምናልባትም በሰዎች መካከል በሚኖር ግንኙነት ውስጥ ሰው ሁሉ መልካም ላይሰጥህ ወይም ላይጠቅምህ ይችላል፤ ነገር ግን ቢያንስ ከጉዳቱ መጠበቅ ትልቅ በጎነት ነው። ---------------------- 👌 👉 #ታላቁ ኢማም ምክራቸውን #በሦስት ምሶሶዎች ላይ ትኩረት አድርገው መክረውናል !! ------------------------ 1ኛ :- ወንድሞቻችን / ለእህቶቻችን / መጥቀም ካልቻልን ለወንድሞች /ለእህቶች / ጉዳት መሆን እንደለለብን በአትኩረት ተናግረዋል !! ------------------------- 👌 👉 በሰው ህይወት ውስጥ እጅህን ዘርግተህ መርዳት ካልቻልክ እግርህን አስጠግተህ እንዳይወድቅ ድጋፍ ሁነው ይህንንም ካልቻልክ በእግርህ ጠልፈህ እንዳትጥለው ጥንቃቄን መውሠድ ይገባሃል !! ወንድምህን /እህትሽን / ለመርዳት አቅምህ /ሽ/ካልፈቀደ መስጠትህ ይቅርበት/ባት/ና الله የሠጣነውን ለመቀማት አትቋምጥ /ጭ/ !! -------------------- 2ኛ :- ለወንድምህ /ለእህትህ / ደስታ መሆን ካልቻልክ ሐዘን አትሁን፡ የሰዎችን የከበደ ትከሻ በፈገግታና በማስደሰት ማቃለል ካልቻልክ፡ በክፉ ንግግርህና ድርጊትህ የልባቸውን ስብራት አትደገመው ልባቸውን በደስታ አድምቃቸው እንጂ አታጨልማቸው !! ----------------------- 3ኛ: - #ወንድምህ በዋለልህ ውለታ #ማመስገን ካልቻልክ #ባልሠራውና ባልገመተው ነገር አትማው ስሙን አታበላሽበት !! ----------------------- 👌 👉 ሰው በሰራው በጎ ነገር ልትቀርበውና ልታደንቀው ባትችል እንኳን በጀርባው ሁነህ አትስደበው ስሙንም አታጉድፈው !! የሰዎችን ነውር ከምትከታተል የራስህን ጉድለት ለማስተካከል ታገል ይህ ለአንተ ትልቅ ስኬት ይሆንሃል !! ------------------- 👌 👉 #ሀቢቢ :- ሰዎችን መጥቀም የደግነት ከፍተኛው ማዕረግ ነው ፤ ነገር ግን ሰዎችን አለመጎዳት ደግሞ የራሱ የሆነ ትልቅ በጎ አድራጎት ነው። ሰዎች ከአንተ መልካም ነገርን ካላገኙ ቢያንስ ከአንተ ሰላምና እፎይታን ያግኙ አትበድላቸው አታቁስላቸው !! --------------------https://t.me/WerebaboBistima_SelefyochChannel
⭕️👌ሴትን ልጅ ከማፍቀርህ በፊት መጀመሪያ እሷን ማክበረን ተማር ምክንያቱም ካከበርካት እሷን ለመጉዳት የምታስብበት ግዜ አይኖርህም ዘላለም እንዳፈቀርካት ትኖራለህ እንጂ‼️ https://t.me/abuanes53 https://t.me/abuanes53
без подписи
без подписи
ነገረ ዶሪህ የዚህን ዶሪህ በር ሌባ ሰርቆት ሲሄድ የአካባቢዉ ሰዎች አሳደዉ ያዙትና፣ የሸይኹን የቀብር በር ለምን ሰረቅክ? ብለዉ ሲጠይቁት። አይ በሩን እራሱ {ሸይኹ} ነዉ የሰጠኝ አላቸዉ። እርሱ {ሸይኹ} የሞተ ሁኖ ሳለ እንዴት ይሰጥሀል? አሉት። {ታዲያ} የሞተ ሁኖ ሳለ እንዴት ልጅና ሲሳይ እንድሰጣችሁ ወደርሱ ትመጣላችሁ? አላቸዉ። ሁሉም ዋለሉ {መልስ አጡ} https://t.me/jamadegollo https://t.me/jamadegollo
https://t.me/nassiru_ddin https://t.me/nassiru_ddin
💥 በህይወት ውስጥ ካሉ ነገሮች ሁሉ እጅግ ውቡ ነገር ቢኖር፥ 👌 ከልቡ የሚወድህና የሚያከብርህ እውነተኛ ሰው ማግኘት ነው። 💥እውነተኛ ወዳጅ ማለት ምን አይነት ነው? 👉 ስትርቅ የሚፈልግህ፣ 👉መራቅህ ሲረዝም የሚናፍቅህ፣ 👉ናፍቆቱ ሲበዛ ስለ አንተ ደህንነት የሚጠይቅና የሚከታተል፣ 👉ዱንያ ብታጠምደው የማይረሳህ፣ 👉ቀናቶች ቢነዱት ጥሎህ የማይጠፋ ነው! 💥ህይወት ምንም ያህል ብትከብድበት እንኳ ፈፅሞ የማይደገፍ ፅኑ ምርኩዝ ይሆንልሃል። 💥ጊዜ የማይቀይረው፣ ሁኔታዎች የማይበግሩት፣ በደስታህም ሆነ በችግርህ ጊዜ ውዴታውን የሚጠብቅ፣ በልቡ ውስጥ ማንም የማይጋራው ልዩ ቦታ የሚሰጥህ ሰው ነው። 💥ስብራትህን አይቶ የሚደብቅልህ፣ ሳይነግረው ፍላጎትህን አውቆ የሚሞላልህ፣ 💥እናም ሚስጥርህን በደረቱ ውስጥ እንዳለች ታማኝ አደራ ጠብቆ የሚይዝልህ እርሱ ነው፤ እውነተኛው ጓደኛ ማለት! 👌እንዲህ አይነት ሰውን ካገኘኸው አጥብቀህ ያዘው፤ ምክንያቱም አንዳንድ ነፍሶች በህይወት ውስጥ ዳግም አይደገሙምና! https://t.me/dewaselefiyaGOHA https://t.me/abujuhyfa https://t.me/WerebaboBistima_SelefyochChannel https://t.me/AbujeferHarbu
የዛንለት ምንሊውጠኝ ነው ..? 🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻 🔴🔴👉 የሰው ልጅ ሆይ ባለፎቅ ብትሆን ባለዘመናዊ መኪናና ባላብዙ አሽከር ብትሆን ባለብዙ ሰራዊት እንድሁም ቆንጆ ብትሆን ምጡቅ ተናጋሪ ብትሆን የአገር ሽማግሌ ዓሊም ብትሆን ተወዳጅ ዳዒ ጠቅላይ ሚኒስቴር ብትሆን ታላቅ ጀኔራል ስፔሻሊስት ዶክተር ብትሆን መድሐኒት አዋቂ ከዚች ቀብር አታመልጥ መጨረሻህ ይህ ነው ያውም ቀባሪ ባለበት ስፍራ ከሞትክ ያውም አስከሬንህ ከተገኘ በቃ ይህ ነው መጨረሻዬ መጨረሻህ መጨረሻችን ። - 🔴➢ የዘለልክባት መሬት የተንጠባረርክባት መሬት ዝምድና የተቆራረጥክባት መሬት ሽርክን ያግበሰበስክባት መሬት ነገ ትጫንካለች ። ሽታህ እንዳያስቸግር አርቀው ቆፍረው በጠባብ ለህድ ውስጥ አስገብተው እንደዚህ ያለብሱካል ። = 🔴👉 የአደም ልጅ ሆይ ቆም ብለህ አስብ የተፈጠርክበትን አላማ አትርሳ اللهን በብቸኝነት ተገዛ ነብይህን ተከተል ካጠፋህ ተውበት አድርግ ። ሽርክን ራቅ, አትኩራ, አትበድል, ዝሙትን ራቅ, አታጭበርብር, አትስረቅ, አራጣ አትብላ, ባጠቃላይ ወንጀልን ራቅቅቅ... ❗️ == ከወንጀል ለመቆጠብ ሞትን አስታውስ ""عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَكْثِرُوا ذِكْرَ هَاذِمِ اللَّذَّاتِ ". يَعْنِي الْمَوْتَ الترمذي والنسائي "ጥፍጥና ቆራጭ የሆነውን ሞት አስታውሱ አዎ..ራሳችንን እንድንፈትሽ ይህችን ዓለም እንደምንሰናበታት ባስታወስን ቁጥር ከሐራም እንርቃለን በዒባዳ ላይ እንጠነክራለን.. 🔺➣👇 https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse
🍂ብዙ ሰው አኸራውን የረሳው #ስሜትን_መከተል እና #በረጅም_ምኞት ነው ወላሁል ሙስተዓን አላህ ይጠብቀን 🤲 ሞት ትንሽ ትልቅ ሳይል እየወሰደ እያዬን ለምንድነው የምንዘነጋው ነገ ብቻ ነው የሚታየን ስንቶቻችን ነን ድንገተኛውን ሞት የዘነጋነው አላህ ልብ ይስጠን 🤲💦💧
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ውድ ወንድምና እህቶች እንደት ናችሁ ዛሬም እንደተለመደው ከተለያዩ ኡስታዛችንና ከውዱ ሸይኻችን ጋ ፏፏፏፏፏ ብለን ጣፋጭ የሆኑ ምክሮችን የምንሠማበት ቀን ነው ዳዕዋ የሚጀመረው ከምሽቱ በኢትዮ 3:00 ተጨማሪ መልእክት يقول النبي ﷺ من لا يشكر الناس لا يشكر الله አደራዋን ሰምታችሁ እንደ እናት አዛኝ በሆነችው በእህታች ሽኝት ላይ የተገኛችሁ ውድ ሰለፍዮች جزاكم الله خيرا እሷን በማጣታችን ውስጤ ቢያዝንም የሽኝቱን ሁኔታ ስሰማ ግን በጣም ነው የተደሰትኩት በሰለፍዮች መተዛዘን በየትም ቦታ ያላችሁ የውዱ ሸይኻችን ፍሬወች አላህ ይጠብቃችሁ መጨረሻችንን አላህ ያሳምርልን قال رسول الله ﷺ أتاني جبريل ، فقال : "يا محمد عش ماشئت فإنك ميت، وأحبِب من شئت فإنك مفارقه، واعمل ما شئت فإنك مَجْزِيٌّ به، واعلم أن شرف المؤمن قيامه بالليل، وعِزُّه استغناؤه عن الناس" ማሳሰቢያ ሌለኛው አደራዋ ደግሞ ወንድም እህቶቾ ዱአ እንዳደርጉላት ነው ጦሳ ላይ ስትገቡ ዱአ እንዳደርጉልኝ ንገሩልኝ ነበር ያለችው በየትኛውም አለም ላይ ያላችሁ እናት አባት እህት ወንድሞች አደራ ዱአ እናድርግላት وعَن أبي هريرة أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ ذَكَرَ يَوْمَ الجُمُعَةِ، فَقَالَ: فِيه سَاعَةٌ لا يُوَافِقها عَبْدٌ مُسلِمٌ، وَهُو قَائِمٌ يُصَلِّي يسأَلُ اللَّه شَيْئًا، إِلاَّ أَعْطَاهُ إِيَّاه وَأَشَارَ بِيدِهِ يُقَلِّلُهَا، متفقٌ عليه. ሰአቱ እስከሚደርስ በየሶሻል ሚድያወች ሸር ማድረግ አይርሱ ሸር ሽር ሽር https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse
ውዷ እህታችን ልባችን ተክዟል አይናችንም እንባ አዝሏል ምንም በአካል ባለውቅሺ በሰለፍዮች ልብ ውስጥ ያለሺን ቦታ ሳውቀው የባሱኑ ከፋኚ ለዲንሺ ያለሺ ቦታና መልካምነትሺ ሰለፍዮችን በንባ ተሞልተዋል አላህ መልካም ስራሺን ሁሉ ይቀበልሺ አንች ከስራሺ ጋር ተገናኚተሻል ቀብርሺን አላህ ያስፋልሺ ብርሀን አላህ ያድርግልሺ የኛንም መጨረሻ አላህ ያሳምርልን በመጨረሻይቱም ሀገር በጨነቱ ጨፌ አላህ ይሰብስበን በምንም መልኩ የማይተዋወቁ በመንሀጂ ሰለፍ በእስልምና ያዋደደ ያግባባን ጌታ ምስጋና በአይነቱ በይዘቱ ይገባው
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ✍️ اللهم ارحمها واغفرلها وعافها واعف عنها وأكرم نزلها ووسع مدخلها واغسلها بالماء والثلج والبرد ونقها من الذنوب والخطايا كما ينقى الثوب الابيض من الدنس اللهم أبدلها داراً خيراً من دارها وأهلاً خيراً من أهلها واجعل الجنة دارها ومستقرها. https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse
ውዷ እህታችን የአንች የዱኒያ አጀል ደርሶ በአደራሽ መሰረት የምትወጃቸው ውድ ሰለፍዮች ባማረና በሚያስደስት ሽኝት ሸኝተውሻል። አዛኙ ጌታችን الله በአማረ መስተንግዶ ይቀበልሽ ፣ ማረፊሽን ጀነተል ፊርደውስ ያድርግልሽ እህታችን ‼ ሰለፍዮች በአደራ ጊዜ ስትሰባሰቡ ቃላችሁን ስትሞሉ አቤት ደስስስስ ስትሉ ጀሊሉ አጅራችንን እጥፍ ድርብ አድርጎ ይመንዳን። በቀጣይ የማንኛችን ተራ መሆኑን አናውቅምና ደእዋችን ላይ መተዛዘን መደጋገፍ ላይ ወንድማማችነት ላይ ተጋግዘን ቀልባችንን በኢማን አርጥበን በሱና እንደተዋብን መጨረሻችንን الله አሳምሮ እያስፈለገችን እየሳሳንላት እየወደድናት ከተለየችን እህታችን ጋር ልእለ ሀያሉ ጌታ በጀነት ያገናኘን የእኛ ውድ እህታችንዋ‼
اِنا لله واِنا اِليه راجعون
السلام عليكم ورحمةالله وبركاته መልእክት ለሁሉም ሰለፍዮች 👉إنا لله وإنا إليه راجعون 🔥 👉 #እህታችን #ሀያት_ኩታበር ወደ ማይቀረው ሃገር ሂዳለችና ነገ በጧት #በኩታበር ከተማ #በመገኘት ሽኝኝት እንድናደርግላት !! #ሁላችንም መቃብር ቦታ #በመገኘት #እህታችንን የመሸኘት #ግደታ አለብን !! #አደራም ብላችኋለች ‼ إنا لله ما أخذ وله ما أعطى وكل شيء عنده بأجل مسمى إن العين تدمع والقلب يحزن ولا نقول إلا ما يرضي ربنا የመቃብር ቦታው #ኩታበር ከተማ ነው‼ #ማሳሰቢያ :- እህታችን الله ይዘንላትና #ለዳዕዋ ሠለፍያ አቅሟ በቻለው ያክል ስትጠቅም ና #እህቶቿንም ሆነ #ወንድሞቿን ስታገዝ ስታጠናክር የነበረች ጠንካራ እህታችን ነች ‼️ --------- 🔥 👉 #ይህቺ እህታችን ገና #ህመም ላይ ባለችበት ሠኣት ጀምራ #መልካምን ሽኝኝት እንድታደርጉላትና #ሱናን በጠበቀ መልኩ ወደ الله #እንድንሸኛት በተደጋጋሚ #ወስያ ልካለች !! 📱https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse
السلام وعليكم ورحمة الله وبركاته #በደሴና በአካባቢዋ #ያላችሁ ወንድሞች አንድም #ወንድም ሊቀር አይገባውም !! #እህታችን በህይወት #እያለች አደራችሁን #መልካምን ሽኝኝት #አድርጉልኝ ብላ ተማፅናችኋለች !! #ሁላችንምም አደራችንን #ለመወጣት ወደ ኋላ ማለት የለብንም !! እህታችንን الله መልካም መቀበልን ይቀበላት !! #እህታችን በደሴና በአካባቢዋ ላሉ #ሠለፍዮች አንድ እህት ብቻ አይደለችም !! የሠለፍዮች አንድ ተቋም ነበረች !!
👌 እህታችን ሐያት የዓቂዳ ደዕዋ በኩታበርና በአካባቢው እንድሰራጭ ከፍተኛ ትግል ያደረገች ለብዙዎችም ሰበብ የሆነች ምርጥ እህታችን ናት ። ለሰለፍዮች እንደናትም እንደ ታላቅ እህትም ሆና ስታግዝ ስታቀራ ስትታገል የነበረች ጀግና እህታችን ነበረች ። 👌ዛሬ ግዜው ደረሰና በዙል_ሒጃ 11_12_1447 ሒጅሪያ ከዚህ ዓለም ወደማይቀረው ዓለም ሔዳለች ። الله ቀብሯን ያስፋላት ስራዋን ይቀበላት ጀነትን ይግጠማት ፊርደውስን ይሸልማት ...! 👌ሐያት አንድ ሰው ብትሆንም ለደዕዋ ሰለፍያ ግን ተቋም ነበረች ። አዛኝ እንስፍስፍ ለደዕዋ ወንድሞች ሞራል የምትገነባ ለእህቶቿ አዛኝ ነበረች ። ገና ደዕዋ ሰለፍያ ዳዴ ሲልና ግብግብ በበዛበት ጊዜ ጀምራ በቆራጥነት የታገለች የሱናዋ አርበኛ ነበረች ... ነገር ግን ሞት እያለ .... ------ https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse/15653
без подписи