tgindex
Addis Intel

Addis Intelligence - about artificial intelligence, tools, and trends. tips, updates, and practical applications. Advertising manager:

Последний пост
31 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Технологии
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 724
0 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
27
20 постов
Вовлечённость
1,6%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
24
1/48двое суток
27
1/72трое суток
29

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 🏷 Moonshot AI አዲሱን Kimi K3.1 ሞዴል በኦገስት ወር (ነሀሴ) ውስጥ ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል 🔺በቅርቡ ከተለቀቀው Kimi K3 ቀጥሎ የሚመጣው ይህ አዲስ ስሪት የ Mythos-level አቅሙን እንደጠበቀ የሚቆይ ሲሆን በ AI ዘርፍ ውስጥ ከ Claude Fable 5 ጋር ያለውን ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ ያጠበዋል ተብሎ ይጠበቃል። 👉 ሲስተሙ አላስፈላጊ የ reasoning እርምጃዎችን በመቀነስ በከፍተኛ ፍጥነት እና በዝቅተኛ የ latency አገልግሎት ይሰጣል 👉 በ coding እና በ autonomous agent workflows ላይ ይበልጥ አስተማማኝ እና ፈጣን አፈጻጸም ይኖረዋል 👉 ሞዴሉ ክፍት (open-weight) ሆኖ የሚቀጥል በመሆኑ የከፍተኛ ደረጃ AI ቴክኖሎጂን ለሁሉም ተጠቃሚዎች በነጻ እና በቀላሉ accessible ይሆናል China Ai price😀 🤩 @AddisIntel

  • Google DeepMind የታዋቂውን AlphaFold ቡድን አባላት በተለያዩ የ AI እና የሳይንስ ፕሮጀክቶች ላይ በመመደብ ኦሪጂናል ቲሙን በትኗል ➡️ኩባንያው ትኩረቱን በ Gemini ወደሚመሩ የ AI ፕሮጀክቶች በማዞሩ የ AlphaFold ተመራማሪዎች ወደ Genomics፣ Enzyme design፣ Nuclear fusion እና Gemini ፕሮጀክቶች ተዛውረዋል። በተጨማሪም የተወሰኑት ተመራማሪዎች Alphabet ስር ወደሚገኘው Isomorphic Labs የተሸጋገሩ ሲሆን የኖቤል ተሸላሚው John Jumperን ጨምሮ አንዳንዶቹ ደግሞ ኩባንያውን ለቀው ወደ Anthropic ተቀላቅለዋል። ➡️ይህ የቡድን መበተን የ AlphaFold ፕሮጀክት ማብቂያ እንዳልሆነ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ዳታቤዝ ከ200 ሚሊዮን በላይ የፕሮቲን ስትራክቸሮችን ይዟል። በተጨማሪም AlphaFold 3 እና በ AI የሚመራው የመድኃኒት ግኝት ምርምር በ DeepMind እና Isomorphic Labs ስር ተጠናክሮ ቀጥሏል። 🤩 @AddisIntel

  • Mark Zuckerberg አሜሪካ የ AI ኤጀንሲዎችን ቁጥጥር በማጥበቅ የቴክኖሎጂውን እድገት ማዘግየት የለባትም ሲል ጥሪ አቀርቧል 🔺የ Meta ስራ አስፈፃሚ አዲሶቹን የ AI ሞዴሎች ለገበያ ከመልቀቅ በፊት ለ30 ቀናት ግምገማ እንዲያልፉ ማድረግ የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነት ወደኋላ ይጎትታል ሲሉ አበክረዋል። 🖱️Zuckerberg ክፍት የሆኑ Open-weight AI ሞዴሎችን በመደገፍ ቴክኖሎጂው በጥቂት ኩባንያዎች እጅ ብቻ መታጠር የለበትም ሲሉ ተከራክረዋል 🖱️የ AI ሞዴሎችን ለ Developers ክፍት ማድረግ ፈጣን ፈጠራን እንደሚያመጣ እና ገበያው ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል እንደሚያስችል ገልጸዋል 🖱️ይህ የ Meta አቋም ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ከሚፈልጉት OpenAI እና Anthropic ካሉ ኩባንያዎች ጋር ያጋጨዋል 🤩 @AddisIntel

  • TokenRouter የተባለው ፕሮቫይደር የ Kimi K3 ሞዴልን እስከ 50 ሚሊዮን Tokens በነጻ ማደልጀመሩን አስታወቀ በ 🙂Coding እና በ 🙂Agent ስራዎች ላይ ከፍተኛ አቅም ያለው Kimi K3 ከ Fable 5 እና GPT Sol 5.6 ጋር እኩል የሚወዳደር ሲሆን አሁን ላይ እነዚህን Tokens በነጻ ማግኘት ይቻላል። ለዚህ አገልግሎት API Key ለማውጣት የባንክ ካርድ ወይም የ Verification ሂደት አያስፈልግም። ⛓ Link - Free Token እዚህ ይውሰዱ

  • 🏷 አዲሱ የ Seedance 2.5 AI Video Generator ይፋ ሊደረግ መሆኑ ተገልጿል 📷ይህ አዲስ ስሪት በ AI የቪዲዮ ማምረቻ ዘርፍ ውስጥ ትልቅ እድገት ይዞ የሚመጣ ሲሆን ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበረውን Seedance 2.0 ስሪት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሻሽል ይሆናል። 🤩 @AddisIntel

  • ✴️ OpenAI ለ100,000 ተመራማሪዎች የ GPT-5.6 ሞዴሉን በነጻ የሚሰጥበትን አዲስ ፕሮግራም ይፋ አደረገ 👉ኩባንያው ChatGPT for Academic Researchers የተባለ አዲስ አሰራር የዘረጋ ሲሆን፣ ይህም ሳይንቲስቶች፣ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኢንጂነሮች የከፍተኛ ደረጃ AI ሞዴሎችን በነጻ እንዲጠቀሙ ዕድል ይሰጣል። 👉 አሰራሩ በመጀመሪያ ለ10,000 ተመራማሪዎች ክፍት የሚደረግ ሲሆን፣ እስከ 2027 ደግሞ ቁጥሩን ወደ 100,000 ለማሳደግ ታቅዷል። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉ ተመራማሪዎች የ GPT-5.6 ሞዴሎችን፣ የዳታ ሴኪዩሪቲ ጥበቃን፣ እስከ 4 ከሚደርሱ የቡድን አባላት ጋር አብሮ የመስራት ዕድልን እና የተለያዩ የስልጠና ድጋፎችን ያገኛሉ። 👉 ይህ እርምጃ ተመራማሪዎች በጽሁፍ እና በሰነድ ስራዎች የሚያባክኑትን ጊዜ በመቀነስ ትኩረታቸውን አዳዲስ ሳይንሳዊ ግኝቶች እና ምርምሮች ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል። 🤩 @AddisIntel

  • ✴️ አዲሱ Meta AI ከኢሜይል፣ ከካላንደር እና ከዌብሳይቶች ጋር በመገናኘት ሙሉ ዝግጅቶችን በራሱ ማቀድ የሚያስችልበትን አዲስ ፊቸር ይፋ ማድረጉን ገለጸ ➡️ በዚሁ መሰረት ኤአዩ የማህበረሰብ መረጃዎችን እና የክሪኤተሮችን ኮንቴንት በመጠቀም እንደ ልደት ያሉ ዝግጅቶችን የማቀድ አቅም ያለው ሲሆን፣ አገልግሎቱ በተመረጡ ሀገራት ውስጥ መለቀቅ መጀመሩን ኩባንያው አስታውቋል። 🔺 ሲስተሙ ለሚሰጣቸው ውሳኔዎች የጥቆማ ምንጮቹን በግልጽ የመለየት እና የማሳወቅ ሀላፊነት አለበት 🔺 የቦታ ምርጫ፣ የቲኬት ቆረጣ ወይም የፋይናንስ ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት ተጠቃሚው የየምንጮቹን ሚና አይቶ በራሱ ማረጋገጥ ይኖርበታል 🔺 ይህ አሰራር AI በራሱ የሰጣቸውን የውሳኔ ሃሳቦች እና ትእዛዞች ተጠቃሚው በቀላሉ እንዲቆጣጠር ያግዛል ➡️ይህ አሰራር የ AI ኤጀንቶች በራሳቸው የዕለት ተዕለት ውሳኔዎችን እና ክፍያዎችን ሲፈጽሙ የሚፈጠሩ ስህተቶችን ለመቀነስ እና የተጠቃሚዎችን ቁጥጥር ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይጫወታል። 🤩 @AddisIntel

  • 🔎 Google ከSuno ጋር የሚያደርገውን ውድድር በማፋጠን Lyria 3.5 የተባለ አዲስ የሙዚቃ ማምረቻ AI ሞዴል ይፋ አደርጓል 🎶አዲሱ ሞዴል በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰሩ የሙዚቃ ስራዎችን እጅግ በጣም ጥራት ባለው ድምፅ እና ቀደም ሲል በ AI ሙዚቃዎች ላይ ይታዩ የነበሩ አሰልቺ ድምፆች (Artifacts) በሌሉበት መልኩ ያቀርባል። 🔥 ሆኖም ሲስተሙ በሌሎች ቋንቋ የቃላት አነባበብ እና Stress ላይ አሁንም ቢሆን የተወሰኑ ክፍተቶች አሉበት። 🔥ይህ አዲስ የ Google ሞዴል በሙዚቃ አሰራር ዘርፍ ውስጥ በ AI የሚሰሩ ይዘቶችን ጥራት ወደ አዲስ ደረጃ የሚያሸጋግር ሲሆን ለክሪኤተሮችም ሰፊ እድል ይከፍታል። 🔗 Link ➕ Here 🤩 @AddisIntel

  • 🤖 ከ 300 በላይ ምርጥ የ AI Agents ስብስብን በአንድ ቦታ የያዘ አዲስ GitHub Repository ይህ ስብስብ ለተለያዩ ስራዎች የሚሆኑ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኤጀንቶችን በየዘርፋቸው መድቦ የያዘ ሲሆን እያንዳንዱ ኤጀንት አጭር ማብራሪያ፣ የአጫጫን መመሪያ እና ውጤታማ አጠቃቀም ላይ የሚያግዙ ቲፖችን አካትቷል። ✔️ ይህ ካታሎግ ለ Writing፣ Coding፣ Design፣ Analytics እና ለተለያዩ ስራዎች የሚሆኑ ቱሎችን በአንድ ቦታ ያቀርባል። ✔️ በተጨማሪም ለ Math፣ Economics፣ Sciences እና Language learning የሚሆኑ ኤጀንቶችን የያዘ ሲሆን እያንዳንዱን መሳሪያ በቀላሉ በመጫን የራስን የ AI Team ለመገንባት እና ስራዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ያስችላል። ✔️ ይህ መረጃ ተጠቃሚዎች ለስራቸው የሚሆን ትክክለኛ የ AI ኤጀንት በቀላሉ እንዲያገኙ እና በስራ ቦታ ላይ ምርታማነታቸውን እንዲጨምሩ ትልቅ እገዛ ያደርጋል። 🚀 Github 🤩 @AddisIntel

  • 🪐 Grok ተጠቃሚዎች ሃሳባቸውን በፅሁፍ ብቻ በመግለጽ ወዲያውኑ የሚሰሩ Web Apps እንዲገነቡ የሚያስችል Build Mode የተባለ አዲስ ፊቸር ይፋ አደርጓል 💡ይህ አሰራር በ Grok ዌብሳይት፣ በ iPhone እና በ Android አፕሊኬሽኖች ላይ የሚሰራ ሲሆን ተጠቃሚዎች የፈለጉትን አፕሊኬሽን አይዲያ ሲነግሩት ሲስተሙ በራሱ ሰርቶ በራሱ Domain Name ፐብሊሽ ያደርገዋል። 📷ሲስተሙ Subagents፣ የ Browser Tools እና በ Grok Imagine የተደገፈ Image Generation አቅም ያለው Grok Build የተባለ Coding Agent ይጠቀማል 📷በስራው የተዘጋጁ አፕሊኬሽኖችን በነጻ Domain ላይ ማስቀረት፣ Custom Domain ማገናኘት ወይም Source Code ወደ GitHub Export ማድረግ ይቻላል ⭐️ አገልግሎቱ ለ SuperGrok Heavy ተጠቃሚዎች ክፍት ሆኗል 🙂 በዚህ አሰራር የ Coding እውቀት የሌላቹ ሰዎች Dashboards Games እና Productivity Tools በቀላሉ መገንባት ትችላላቹ 🤩 @AddisIntel

  • ⚡️ ተጠቃሚዎች የ ChatGPT Agentን በመጠቀም ለማንኛውም ዌብሳይት የሚሰሩ Promo Codes የሚያገኙበት አዲስ መንገድ ይፋ ሆንዋል 👉 ይህ አሰራር የ ChatGPTን Agent ባህሪ በመጠቀም በኢንተርኔት ላይ ያሉ ኩፖኖችን በራሱ ፈልጎ በ Checkout ገጽ ላይ አንድ በአንድ በመሞከር የሚሰሩትን ብቻ ለተጠቃሚው ለይቶ ያቀርባል። 🌐 Agentው በመጀመሪያ የቅናሽ ኮዶችን በ Search Engine እና Coupon Sites ላይ ይፈልጋል 🏪 በመቀጠል ወደ ኦንላይን ሾፑ በመግባት እቃ Cart ውስጥ ይጨምራል 📝 ወደ Checkout ገጽ በመሄድ የተገኙትን ኮዶች በሙሉ በመሞከር የሚሰሩትን የቅናሽ መጠኖች ሪፖርት ያደርጋል 👉ይህ አሰራር ሰዎች በኦንላይን ሾፒንግ ወቅት የሚሰሩ Promo Codes ለማግኘት የሚያጠፉትን ጊዜ እና ድካም ሙሉ በሙሉ ያስቀራል። 🤩 @AddisIntel

  • Elon Musk አዲሱ ✴️Grok 4.6 ሞዴል በኦገስት 7 ይፋ እንደሚሆን እና በቅርቡ ደግሞ የበለጠ ግዙፍ Model እንደሚከተል አስታወቀ 🖱️እንደ Musk ገለፃ 1.5 Trillion Parameters ያለው Grok 4.6 በቅርብ ቀናት ውስጥ የሚለቀቅ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ 2.1 Trillion Parameters ያለው Grok 4.7 ይከተላል። ከዚህ በተጨማሪም SpaceX የ Cursorን Acquisition ማጠናቀቁን ተከትሎ በ Colossus 2 Cluster ላይ ከዜሮ የሰለጠነው Composer 3 የኮዲንግ ሞዴል በቅርቡ ይፋ ይሆናል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው። 🖱️ይህ አዲስ የ Composer 3 ሞዴል ከ Claude Opus 5 እና ከ GPT-5.6 Sol ጋር እኩል የሚወዳደር የ Coding Performance እጅግ በጣም በቅናሽ ዋጋ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። 🤩 @AddisIntel

  • 🏷 Moonshot AI የ Kimi-K3 ሞዴሉን በትንሽ መጠን በ 0.4 Billion Parameters ብቻ በማድረግ ለሁሉም ክፍት አደረገ 🔺በከፍተኛ አቅሙ ከ Opus እና ከ Fable ጋር የሚወዳደረው Kimi-K3 አሁን በትንሽ መጠን በመዘጋጀቱ ምንም አይነት ውድ ኮምፒውተር ወይም GPU ሳይስፈልግ በማንኛውም ደካማ ሲስተም ላይ መስራት ይችላል። 🔺ይህ አዲስ ስሪት በ አነስተኛ መጠን የተዘጋጀ በመሆኑ 8 GB RAM ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ ሙሉ በሙሉ በነጻ ይሰራል። በተጨማሪም በ Storage ላይ ከ 2 እስከ 4 GB ቦታ ብቻ የሚይዝ ሲሆን የ K3 ሞዴልን ዋና ዋና Architecture እና DNA ይዞ ስራዎችን ያከናውናል:: 😍 ይህ ለDevelopers Ai model በራሳቸው ኮምፒውተር ላይ በነጻ እና በፍጥነት እንዲሞክሩ ትልቅ እድል ይከፍታል share አድርጉላቸው 🔗 Link 🤩 @AddisIntel

  • 🔥 አንድ የOpenAI developer የCodex እና የChatGPT አጠቃቀም መንገዶችን ያካተተ website ይፋ አደረጓል ➡️ ይህ website የተለያዩ የተግባር ልምዶችን፣ ዝግጁ ፕሮምፕቶችን፣ መመሪያዎችን እና ጠቃሚ መሳሪያዎችን በአንድ ቦታ የያዘ የማህበራዊ ሚዲያ መሰል ገጽ አለው። ➡️ በተጨማሪም የAI ቴክኖሎጂዎችን በዕለት ተዕለት ስራ ላይ የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ትልቅ እገዛ ያደርጋል 🔗 Website link 🤩 @AddisIntel

  • 🔎 Google በአንድ ጊዜ ሶስት አዳዲስ የGemini AI 🏷 ሞዴሎችን ይፋ አደረጓል 👉 እነዚህ አዳዲስ ሞዴሎች የረጅም ኮንቴክስት ግንዛቤን እና የኮምፒውተር Vision አቅምን በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ገበያው ላይ ያሉ ተፎካካሪዎችን የሚበልጡ ሆነዋል። 👉 ኩባንያው Gemini 3.6 Flash፣ Gemini 3.5 Flash-Lite እና ለሳይበር ደህንነት የተሰራውን Gemini 3.5 Flash Cyber አስተዋውቋል 👉 አዲሶቹ ሞዴሎች ከብዙ ተፎካካሪዎች ጋር ሲነፃፀሩ በጣም ርካሽ ዋጋ ያላቸው ሲሆን ከGPT-5.6 በትንሹ ብቻ በዋጋ ይለያያሉ 👉 ዴቨሎፐሮች እና ተጠቃሚዎች የቪዥን እና የዳታ ፕሮሰሲንግ ስራዎችን በፍጥነት እና በቅናሽ ዋጋ ለማሰራት ይጠቀሙባቸዋል 🤩 @AddisIntel

  • ✴️ OpenAI ለChatGPT አዲስ Health mode ጨመረ 📌 ይህ አዲስ ፊቸር ChatGPT የህክምና መረጃዎችን እና የApple Watch ዳታዎችን በመጠቀም ለጤና ጥያቄዎች በገሃዳዊ ሜትሪክሶች የተደገፈ ምላሽ እንዲሰጥ ያስችለዋል። ➡️ ተጠቃሚዎች Apple Healthን እንዲሁም የOne Medical ወይም Function Health ሪኮርዶችን በማገናኘት የደም ምርመራዎችን፣ መድኃኒቶችን፣ የእንቅልፍ እና የእንቅስቃሴ ዳታዎችን ማጋራት ይችላሉ ➡️ ሲስተሙ የደም ምርመራዎችን ያወዳድራል የህክምና ቃላትን ያብራራል ወይም ከአለርጂ ነፃ የሆኑ ሬስቶራንቶችን ይጠቁማል ➡️ Free ተጠቃሚዎች ዶክተር የሚያስፈልግበትን ጊዜ የሚጠቁም GPT-5.5 Instant ሲያገኙ Paid ተጠቃሚዎች ደግሞ ለተወሳሰቡ የህክምና ጉዳዮች GPT-5.6 Solን ይጠቀማሉ 👥 @AddisIntel

  • 🙂 Moonshot AI የተባለው ኩባንያ አዲሱን Kimi K3 ሞዴል Open-source አድርጎ ለቋል 🖱️ይህ የቻይና ኩባንያ ቃል በገባው መሰረት Kimi K3 የተባለውን ከፍተኛ አቅም ያለው የAI ሞዴል ለሁሉም ክፍት ማድረጉን ይፋ አድርጓል። 🔺 ሞዴሉ በኮዲንግ እና በAI Agents ስራዎች ላይ ከFable 5 እና GPT-5.6 ጋር ተመሳሳይ አቅም ያለው ነው 🔺 ማንኛውም ሰው ሞዴሉን በርካሽ ፕሮቫይደር ላይ በመከራየት ወይም በራሱ ሰርቨር ላይ ሆስት አድርጎ መጠቀም ይችላል 🔺 ይህ እርምጃ ውድ በሆኑ SaaS ሰርቪሶች ላይ ጥገኝነት ያላቸውን startup አሰራር ሙሉ በሙሉ ሊቀይር ይችላል ➡️ ይህ open source የ AI ሞዴል መለቀቁ developers ኩባንያዎች በራሳቸው መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ሲስተሞች በቀላሉ እንዲገነቡ መንገድ ይከፍታል 👥 @AddisIntel 👥 @AddisIntel

  • ✴️ ChatGPT የሰራተኞችን የስራ ወሰን እና ሀላፊነት እያሰፋው መሆኑን አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ 🔹Axios እንደዘገበው የOpenAI አዲስ ጥናት ከ800,000 በላይ የአሜሪካ ኩባንያዎችን የቻት መልእክቶች በመመርመር ሰራተኞች ኤአይን እንዴት እንደሚጠቀሙበት አሳይቷል። ➡️ እንደ ኢሜይል መጻፍ እና መርሃ ግብር ማስተካከል ያሉ የተለመዱ ስራዎች ከተቀነሱ በኋላ 44% የሚሆኑት ጥያቄዎች የሌላ ሙያ መስክ ስራዎችን የሚያካትቱ ሆነው ተገኝተዋል ➡️ ይህ አሰራር ኩባንያዎች የሰራተኞቻቸውን የስራ ወሰን እንዲያሰፉ፣ ተጨማሪ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ እና የባለሙያዎችን የቁጥጥር ደረጃዎች እንዲዘረጉ ያስገድዳቸዋል ➡️ አጠቃላይ ሰራተኞች የባለሙያዎችን ስራ ለመሞከር እድል የሚያገኙ ሲሆን ውስብስብ ነገሮች ሲያጋጥሙ ብቻ ወደ ዋና ባለሙያዎች መምራት ይቻላል 📌 ይህ መረጃ ሰራተኞች ኤአይን ተግባራዊ እያደረጉበት ያለውን መንገድ የሚያሳይ እንጂ የስራ እድል መቀነስን ወይም የባለሙያዎችን መተካት የሚያረጋግጥ አይደለም 👥 @AddisIntel

  • 🤶 Anthropic free course የClaude Code ስልጠና ይፋ አደረገ 💻 ኩባንያው Claude Code በስራ ላይ እንዴት ውጤታማ በሆነ መንገድ እንደሚተገበር የሚያሳዩ እውነተኛ ሲናሪዮዎችን ያካተተ ነፃ ኮርስ ለቀቋል። 🖱️Claude Codeን ኮድ የሚጽፍ፣ ከGitHub ጋር የሚሰራ እና የተለመዱ ስራዎችን ኦቶሜት የሚያደርግ ሙሉ AI Agent እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ያስረዳል 🖱️ የHooks እና Skills አጠቃቀምን ጨምሮ ረጅም ስራዎችን በትንሽ የሰው ጣልቃገብነት እንዴት ማሰራት እንደሚቻል ያሰለጥናል 🖱️ ኮርሱ 15 አጫጭር ሌሰኖችን ያካተተ ሲሆን ሲጠናቀቅም ሰርተፊኬት ያሰጣል 🙂 ይህ እድል ዴቨሎፐሮች Claude Codeን በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራታቸው እንዲቆጣጠሩት እና በስራቸው ላይ በብቃት እንዲጠቀሙበት ያግዛል 🔗Link 👥 @AddisIntel

  • 🇨🇳 በቻይና በተካሄደው WAIC 2026 የዓለም አቀፍ AI ኮንፈረንስ ላይ የአዲሱ ትውልድ ትምህርት ቤት AI ጥቁር ሰሌዳ ይፋ ሆነ ➡️ይህ ዘመናዊ መሣሪያ ባህላዊውን የመማር ማስተማር ሂደት ሙሉ በሙሉ በመቀየር ትምህርትን የበለጠ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ያደርገዋል። 📷 በሰሌዳው ላይ የተጻፉ ነገሮችን በቀላሉ የመለየት እና ትምህርታዊ ይዘቶችን በራሱ የማደራጀት አቅም አለው 📷 ውስብስብ የሆኑ ርዕሶችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ታግዞ ለተማሪዎች በግልጽ ያብራራል 📷 መደበኛውን የክፍል ትምህርት ተማሪዎች በቀጥታ የሚሳተፉበት (Interactive) አሳታፊ ክፍለ-ጊዜ ያደርገዋል 🗒 የዚህ ዓይነት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታከለባቸው ሰሌዳዎች መስፋፋት ወደፊት ባህላዊውን የማስተማሪያ ዘዴ ሙሉ በሙሉ ሊተኩት ይችላሉ 👥 @AddisIntel

Addis Intel — tgindex