𝗔𝗵𝗹𝘂𝗹 𝗛𝗮𝗱𝗶𝘁𝗵 || አህሉል ሐዲስ
Статистикаረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “አላህ ፊቱን ያብራለት ንግግሬን ሰምቶ ላደረሰው (ላስተላለፈው) ሰው።” ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 189 https://t.me/AhlulHadithOfficial
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 14
- 1/48двое суток
- 16
- 1/72трое суток
- 17
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ማን ቀድሞ ይመልስ ! 🚀🚀 ትክክለኛውን መልስ የመለሰ add የሚለውን በመጫን ጠቃሚ ነገር ያገኛል ! ጥያቄ 👉 በቁርኣን ውስጥ ስማቸው ከሌሎች ነብያት በበለጠ ሁኔታ በብዛት የተጠቀሰው ነብይ ማን ናቸው?
ማን ቀድሞ ይመልስ ! 🚀🚀 ትክክለኛውን መልስ የመለሰ add የሚለውን በመጫን ጠቃሚ ነገር ያገኛል ! ጥያቄ 👉 ነብዩ ሙሀመድ ሰለላህ ወአለይሂ ወሰለም «በመልክም በፀባይክም እኔን ትመስላለህ» ያሉት ሰሀባ ማነው?
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲያላሁ ዐንሁማ) እንደተወራው፦ "የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአሹራን ቀን ጾመዋል፣ እንዲጾምም አዘዋል።" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ «የዓሹራእ ቀንን መጾም፤ ያለፈውን የአንድ ዓመት (ወንጀል) ማስተሰረያ እንዲሆን ከአላህ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ (እከጅላለሁ)።» (ሙስሊም ዘግበውታል) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "ከረመዳን በመቀጠል ከሁሉ በላይ በላጩ ፆም የአላህ ወር የሆነው ሙሀረም ነው።" (በሙስሊም ዘግበዉታል) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
📢 አስደሳች ዜና! ከዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የተርቢያ መዕከል 💎 ዳሩል ዒልም መርከዝ ለመጪዉ ክረምትና በጋ በአዳሪ መርሃግብር ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል። ☑️ የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦ 📍ጾታ፦ ለወንዶች ብቻ (አዳሪ) 📍 እድሜ፦ ከ10 - 20 ዓመት 📍 ጤንነት፦ ከማንኛውም በሽታ ነፃ የሆነ 📍 ስነ-ምግባር፦ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ የሆነ 📍 ፍላጎት፦ ለመቅራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው 📍ክፍያ፦ ወርሃዊ ክፍያን መክፈል የሚችል ☑️ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች፦ 📌 የቁርአን ሒፍዝ (በቃል መያዝ) 📌 የቁርአን ነዘር (ንባብ) እና ሙራጀዓ (ክለሳ) 📌 ቃዒደቱን ኑራኒያ እና የተጅዊድ ትምህርቶች 📌 የተለያዩ የዲን ኪታቦች ☎️ ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፡ +251911171786 | +251910034682 +251947224231 | +251970092357 በቴሌግራም ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈 በዋትስ አፕ ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈 የቴሌግራም አድራሻ፡ 🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial 🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial 🏢 አድራሻ: አንፎ 105 ከዘቢዳር ሆቴል ጀርባ
ከዑበይዲላህ ቢን ሚሕሰን አል-አንሷሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ፤ እርሳቸውም ከነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይዘው እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ መካከል በቤተሰቡ/በመኖሪያው ሰላማዊ ሆኖ የነጋለት፣ በአካሉ ጤነኛ የሆነ፣ የዕለቱ ቀለብ (ምግብ) ያለው ሰው፤ ዱንያ (ዓለም) ሙሉ በሙሉ የተሰጠችው ይመስላል። (ዱንያ ከነሙሉ ፀጋዋ ተጠቅልላ እንደተሰጠችው ይቆጠራል)።" (ቲርሚዚና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "የአያሙ አት-ተሽሪቅ ቀናት የመብያ፣ የመጠጫ እና አላህን (ሱብሓነሁ ወተዓላ) የማስታወሻ (የዚክር) ቀናት ናቸው።" (ሙስሊም ዘግበውታል) አያሙ አት-ተሽሪቅ ከዓረፋ እና ከዒድ አል-አድሓ ቀን ቀጥሎ ያሉ ሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሆኑ፣ እነሱም በሂጅራ አቆጣጠር የዙልሒጃ ወር 11ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ ቀናት ናቸው። በእነዚህ ቀናት የአላህን ጸጋዎች እየተመገቡና እየጠጡ እርሱን በዚክር ማመስገን ይወደዳል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
ከዐብደላህ ኢብኑ ዐምር (ረዲያላሁ ዐንሁማ) እንደተወራው ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "ኩራትና ማባከን (ብክነት) ሳይቀላቀልበት፤ ብሉ፣ ጠጡ፣ ሰደቃ ስጡ፣ እንዲሁም ልበሱ።" (ኢብኑ ማጃህ እና ኢማም አሕመድ የዘገቡት ሲሆን፣ ቡኻሪም በሰሒሓቸው ላይ በተዕሊቅ አስቀምጠውታል።) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
ዒድ ሙባረክ ! እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሓ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የደስታ፣ የጤና ፣ የመተሳሰብና የሰላም እንዲሆን እንመኛለን። አላህ ዱዓችሁን እና ምኞታችሁን ሁሉ የሚያሳካበት ፣ ቤታችሁም በበረከት የሚሞላበት ያድርግላችሁ። አህሉል ሐዲስ የቴሌግራም ቻናል = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ በዓረፋ ቀን ከእሳት ባሪያዎችን ነፃ ከሚያወጣበት ቀን ይበልጥ (ብዙ) ባሪያዎችን ነፃ የሚያወጣበት ሌላ ቀን የለም።" (ሙስሊም፡ 1348) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
ከአቡ ቀታዳህ (ረዲያላሁ ዐንሁ ) እንደተወራው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡ "የዐረፋ ቀንን መፆም ያለፈውን ዓመት እና የሚመጣውን ዓመት (ወንጀል) ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ።" (ሙስሊም ዘግበውታል) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
⚠️ የጥንቃቄ መልእክት! ብሔራዊ ባንክ የፋይዳ መታወቂያን ከባንክ አካውንት ጋር ለማስተሳሰር የሰጠው ጊዜ ማብቃቱን ተከትሎ፣ ሌቦች "ከብሔራዊ ባንክ ነው የምንደውለው፤ ሒሳብዎን ከፋይዳ ጋር ልናስተሳስር ነው፣ የፋይዳ ቁጥርዎንና አካውንትዎን ንገሩን" በማለት ዝርፊያ እየፈፀሙ ይገኛሉ። በመሆኑም በምንም መልኩ በስልክ ተደውሎ የዚህ አይነት ጥያቄ ስትጠየቁ መልስ ባለመስጠት ራሳችሁን ከዘረፋ እንድትጠብቁ እና አካውንታችሁ ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር ያልተያያዘ ከሆነ፣ ወደ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመሄድ ብቻ እንድታስተካክሉ ለማስታወስ እንወዳለን። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/FuadKemal https://t.me/FuadKemal
የዙልሒጃህ አስር ቀናት ታላቅነት ~ ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "በእነዚህ ቀናት — ማለትም በአስሩ (የዙልሒጃህ) ቀናት — ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ይልቅ አላህ ዘንድ ይበልጥ የተወደደ መልካም ስራ የሚሰራበት ሌላ ምንም ቀን የለም።" ሶሓቦችም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን (ከእነዚህ ቀናት ስራ አይበልጥም)?" ሲሉ ጠየቁ። እሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን አይበልጥም፤ በነፍሱና በገንዘቡ ወጥቶ፣ ከዚያም ምንም ነገር ሳይዝ የተመለሰ (በዚያው የሞተ) ሰው ቢሆን እንጂ።" (ምንጭ፦ ሱነን አቢ ዳውድ) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
ኡሙ ሰለማህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ “የዙልሒጃን ወር ጨረቃ ካያችሁ እና ከእናንተ መካከል አንዱ መስዋዕት (እርድ) ማቅረብ ከፈለገ፡ ከፀጉሩም ሆነ ከጥፍሩ (መቁረጥ) ይቆጠብ።” (ሙስሊም ዘግበውታል) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial
እንኳን ወደ ሐላል ገበያ በደህና መጡ! ~ በዚህ ቻናል ላይ አዳዲስና በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ ያገለገሉ፦ 🏠 የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን 🛠 የሥራ መሣሪያዎችን እና 📦 ልዩ ልዩ ንብረቶችን ያለ ምንም ደላላ፣ በቀጥታ ከሻጩ ጋር በመገናኘት በታማኝነት የሚገበያዩበት አስተማማኝ መድረክ ነው! 🛒 ገዢ ከሆኑ፦ ምርጥ ዕቃዎችን በቅናሽ ዋጋ ሳይቀደሙ ለማግኘት ቻናሉን በንቃት ይከታተሉ! 💰 ሻጭ ከሆኑ፦ የሚሸጡትን ዕቃ ፎቶ፣ ሙሉ መረጃና ዋጋ በ @ContactHalalGebeya በኩል ይላኩልን፣ ያለምንም ደላላ እራስዎ ይሸጣሉ! = ቻናሉን ለመቀላቀል፦ t.me/HalalGebeyaOfficial t.me/HalalGebeyaOfficial
видео или голосовое, без подписи
⏳ ነገ ሐሙስ ነው! ~ ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተወራው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፦ «ሥራዎች ሰኞና ሐሙስ (ወደ አላህ) ይቀርባሉ፤ እኔም ሥራዬ ጾመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ።» ብለዋልና የነገው የሐሙስ ጾም እንዳያመልጠን! ስራዎቻችን በጾም ታጅበው ወደ አላህ እንዲቀርቡ የቻልን እንጹም። አላህ ይወፍቀን! = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/AhlulHadithOfficial https://t.me/AhlulHadithOfficial