tgindex
D

Death Chronicle

Статистика
@AmharaChronicleанглийский

#አማራ ሁሉንም በመልኩ ሠራ! የአማራ ታሪክ ባህል ፍልስፍና ጥበብ ሀገረ መንግስት ምስረታ እንዲሁም ኢትዮጽያ ወቅታዊ ክስተቶች ከአምሐራ ተጋድሎ ጋር በ#AmharaChronicle #The Amhara Chronicle https://t.me/AmharaChronicle X.twitter https://x.com/AmharaChronicle?t=AaAT-oWLCsny48aIX-DPvw&s=35

Последний пост
3 нояб.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
103
0 за 4 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
145
21 постов
Вовлечённость
140,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://youtu.be/IiZ7Yjp5u88?si=GXxeUTMm35I5tWqJ

  • ሀገርም ቤተክርስቲያንም ፈተና ላይ ከወደቀች በእርግጥም ሠነባብታለች። በዚህ ፈተና በሞላበት አለም ውስጥ ምእመን ቤተክርስቲያንን መጠጊያ ቢያደርግ ማይችልበት ሠአት ላይ ነው። ውጊያው መንፈሳዊ ውጊያ ነው። ይህን ለምን እደሚያደርጉት የሚያውቁት እዛ አካባቢ ያሉ ሰዎች ናቸው። ምን አልባትም ቤተክርስቲያ በሀሳዊያን በመናፍቃን ከተወረረች ቆየች አሁን ምመኑን ከየትኛውም የቤተክርስቴያን አገልግሎት ለመነጠል ምንም ነገር ያደርጋሉ። ጋዜጠኛ መስከረም የታዘበችውን ተነፈሰች እዛው አካባቢ ያሉ አባቶች ቢጠየቁ ስንት ጉድ በወጣ ነበር። በቤታችሁ ለመገልገል ክፈሉ? በየትኛው መመሪያስ ነው ይሄን ያህል የሚያስከፍሉን? (በጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው) አንድ ወዳጄ ከሰሞኑን አግብቶ ስንጫወት የሰርግ ወጭ ነገር ተነሳ። አንድ ወጭ ላይ አስደገምሁት አረጋገጠልኝ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ በሥርዓተ ቤ/ክ ለማግባት 10,000 ብር ተጠይቆ ከፍሏል። አስቡት ወጣቱ ጠፋ ምናምን የሚል አስተዳደር እንደእግዚአብሔር ቃል ራሴን ጠብቄ ኑሬያለሁ አሁን በክብር በቤቴ በስጋ ወደሙ ልሞሸር ይገባል ብሎ ሲመጣ ትክፍላለህ ሲባል። በዚህ ስገረም አንዱ እንዲህ አለኝ እኔ እንዳውም ላገባ ስል ቤ/ ክ አጥቼ ብዙ ለፋሁ አለኝ። ለምን? ስለው ብትከፍልም ብዙ ሰርግ አለብን ሥርዓቱን አንፈጽምም እያሉ አንድ ቦታ ባለቤቴን ስለሚያውቋት እሽ አሉን አለኝ። ተመልከቱ ወጣቱ ቤተ ክርስቲያኔ ብሎ ሲመጣ ሰው በዛብን ሲባል? ደሞ ወዲህ የእግዚአብሔር ልጅነትን ለማግኘት ክርስትና ለማስነሳት ሲመጡ ይህን ያህል ብር ክፈሉ ሲባሉ…. ልጅነትን በገንዘብ? አንዲት ደሃ ወልዳ ልታስጠምቅና ከክርስቲያንም ሕብረት ልትጨምር ስትሄድ ክፈይ ስትባል…😭 እውነት ነው አገልግሎቱ ገንዘብ ያስፈልገዋል። ነገር ግን ከመንግስት ቀጥላ ከፍተኛ ገቢ አላት የምትባልና ብዙ የሰው ኃይል የምታስተዳድር ቤ/ክ ለልጅነት ጥምቀት እና ወጣቱ ዓለምን ትቶ ለራሱን ጠብቆ ወደ መቅደስ ሲመጣ እንደመሸለም ማስከፈል ምን ማለት ነው? ለሰርግ ከፍለን፣ ለጥምቀተ ክርስትና ከፍለን፣ ለሙት ዓመት መታሰቢያ ከፍለን፣ ለቀብር ቦታ ከፍለን፣ በጸሎት አስቡኝ ለማለት ከፍልን እንችለዋለን? ደግሞ ከአጥቢያ አጥቢያ ያለው የክፍያ መጠን ልዩነት እኮ አንዱ ቀጥታ ገነት ሚያስገባ የሌላው ደግሞ ማያስገባ ነው ሚመስለው። ሙዳዬ ምፅዋቱ ለማን ነው ሚዞረው? ታቦት ቁሞ ለማን ነው ሚለመነው? ለአገልግሎት እያላችሁ አይደል? እስኪያለውን ገንዘብ ሀቅን ይዛችሁ አከፋፍሉት ለገጠር ለከተማ ይበቃል እኮ! እኛ በተቀደሰችውና ፍጽምት በሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን ለሰከንድ አንገት ደፍተን አናውቅም። በምድርም በሰማይም አለኝታችን ናትና! በአስተዳደራዊ ጉዳይ ግን በስንቱ እንሸማቀቅ!! ይህን ጉዳይስ ቅዱስ ሲኖዶስ ያውቀዋል? ለቅዳሴው ሳያስከፍሉን አንድ በሉን! ...

  • ቆይ ግን ይሄን ሕዝብ ምን አድርግ ነው ሚሉት😭 እንዴት አንድ አባት ላጠፋነው ጥፋት መቀሌ ድረስ መጣችሁ አልገጠማችሁንም በሚመስል በልበ ሙሉነት ይከስሳል?! እንቅልፉን የተኛው ማን ነው?

  • እመኑኝ ይህ ሰው የእስራኤሉን ሞሳድ (MOSAD) ያስከነዳል! ደጋግመን እንናገራለን ከዚህ ሰው ውጭ ኢትዮጽያን ማሰብ ይከብደል። ከዚህ ሰው ውጭ አማራን ማሰብ ይከብዳል። ካለዚህ ሰው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን ማሰብም ይጨንቃል። ይህ ሰው በዚህ ዘመን ባይፈጠርስ ኖሮ ብሎ ማሠብ ደግሞ ከሁሉም የከፋ ነው! በዘመን መካከል የተገኘ: ብቻውን ይታገል ዘንድ ብቻውን በፅናት ይቆም ዘንድ ህዝብ ሀገር ሐይማኖት ማቅ በለበሱ ጊዜ ማዕበሉ ጨርሶ እንዳያጠፋቸው በፅናት ይታገሉ ዘንድ እግዚአብሔር ጠባቂ አድርጎ የላከው የዘመናችን እንዲሁም የ ትውልዳችን ጀግና። በታሪክ ማህደር እንደ ጥንተ አባቶቻችን ልናሞካሸው ስሙን በክብር መዝገብ ልንሰድረው ስራው በደማቅ ቀለም ሊፃፍ በዚህች ሰአት ክብረ ወሰን እየሰባበረ የተገለፀ የዘመናችን መሪ ቅዱስ አቢዮተኛ! ሁለት አስርት አመታት እና በላይ የማይዋዠቅ አቋም: በእውቀት በፅናት እና በእውነት በአስር ጊዜ ለክተህ አንድ ጌዜ ቁረጥ መርህ እውነትን የሰበከ: የዘመን ሁሉ ሰንኮፎችን ወደ ጥልቁ ባህር እየወረወረ የሚገሰግስ አብሪ ኮከብ! ጠላት በውስጥ እና ከውጭ ሀገርን ለማፍረስ አንቅልፍ አጠው በሚለፍፉበትና በሚቅበዘበዙበት ጊዜ ሀገርን ከመፍረስ ለማዳን በውችንፍር መሀል ህዝብ ጣሩ በበዛበት ጊዜ ፈጥኖ የተገኘ የዘመናችን ሙሴ። መከራን ይቀበል ዘንድ ከሚወዳት ሀገሩና እናት ቤተክርስቲያን እቅፍ ተለይቶ የተሰደደ አምላኩን ይዞ ምሎ ተገዝቶ እውነትን እያመሠጠረ ከግፉአን ፊት ከወደቁ የምድር ላይ ጥቁር መላእክት ፊት ከዲያቢሎስ ከወረሱት የጥልቁ አለም ሃሳብ አራማጆች ፊት አንድ ብቻውን በፅናትና በጥበብ የቆመ የማይቻለውን ለሰማይ ለምድር የከበደውን ሁሉ ያፈራረሰ ጀግና። ያልተዜመለት ከያኒያን ያልተቀኙለት ሊቃውንት ቅኔ ያላወረዱለት ጨለማን ገሸሸ እያደረገ የሚገሰግስ የንጋት ላይ ኮከብ። ይህ ሰው ተአምር ነው። ይህ ሰው ድንቅ ነው። ይህ ሰው ጥበብ ነው። ይህ ሰው ምስጢር ነው። ሲያሻው ቃል ተናጋሪ ሲያሻው የጦር መሪ ሲያሻው ቃል አቀባይ ሲያሻው አቃቤ ህግ ሲያሻው ደህንነት ነው። ሐሳዊ ነቢያት እንደጦር ይፈሩታል ሐሳዊ መሪዎች ብእሩን ሲያነሳ አንደበቱን ሲከፍት ያርበተብታቸዋል። ድኩማን መሀይም የዘር ፖለቲክስ አራማጆች አምርረው ይረግሙታል። ጆፌ አሞራ ለቃቃሚ የዶለር ቀበኞች ሆድ አንጂ ማሰቢያ የሌላቸው ድኩማን የዲያቢሎስ ባለሟል የሰው ደም ነጋዴዎች አምርረው ይፀየፉታል። እንክርዳዱን ከስንዴ እየለየ በገሞራ መካከል በኩራት የሚረማመድ ለሐገር ለወገን ሲል የበረታ ለዝና ለኃብትም ያይደለ ላሳደገችው አምጣ ለወለደችው በፈጠረችው ባወረሰችው ጥበብ ልክ መሠዋዕት ሊከፍልላት የአምላኩን ቃል ከፊት እያስቀደመ ለእውነት የቆመ ትጉህ ገበሬ። እንዲህም ይላል: በኩራት "አንድ ለናቱ ሺህ ለጠላቱ" ጠላትና ባንዳን ድራሹን ያጠፋ አንደ መብረቅ እያስገመገመ: እንደ ሚሳኤል እየተወነጨፈ ድባቅ የሚመታ ከማማው ላይ ሳይወረድ አመታትን በከፍታ በፅናት ከፍ ብሎ የበረረ የኛ ትውልድ ጀግና የዘመናችን ዳዊት። የአለም ሚዲያወች ቢጨመቁ አንኳ የዚህን ሰው ያክል ምሉእነት የላቸውም። እመኑኝ ይህ ሰው ብቻውን ከኔቶ (NETO) ይልቃል። እመኑኝ ይህ ሰው ከአሜሪካው ሲአይኤ (CIA) በብዙ ይርቃል። እመኑኝ ይህ ሰው የእስራኤሉን ሞሳድ (MOSAD) ያስከነዳል......... #Underrated ይላሉ ፈረንጆቹ🤗🤗🤗 ምን ማለት ኖ🤔 ከዘመኑ የቀደመ የኛ ትውልድ አብሪ ኮከብ እንደ ነብይ ትንቢት ተናጋሪ! ይህ ሰው ማነው ካላችሁ #ዘመድኩን በቀለ ነው! ብእርህ አይንጠፍ! ፀሎትህ እና ብርታትህ ለጠላቶችህ የገሀነም እሳት ይሁንባቸው:: ሀሳባቸውን እቅዳቸውን ሽባ ያድርግባቸው!! "አምሐራ ሁሉን በመልኩ ሰራ!" #The Amhara Chronicle https://t.me/AmharaChronicle 08/06/2017 ዓ.ም

  • без подписи

  • በመጨረሻም በነባር የሚዲያ ጋፈሮች የተከዳው የአምሐራ ፋኖ ትግል አዲስ ንፁህ ታማኝ እውነተኞች የሳይበር ለይ ተዋጊዎችን ያዋልድ ዘንድ ግድ የሚልበት ደረጃ ላይ መሆኑን እንገንዘብ። ምሁራን ደፈር ማለት ያስፈልግ ከሆነም አሁን ነው። አምሐራ የሆነ ሁሉ መሽኮርመሙን ማቆም አለበት። "አምሐራ ሁሉን በመልኩ ሰራ!" #The Amhara Chronicle https://t.me/AmharaChronicle 06/06/2017 ዓ.ም

  • የአምሐራ ፋኖ ትግል ነባርና አዲስ የሚዲያ ሌቦችን ፈጠረ እንጂ የሕዝብ ችግር እና ሰቆቃ ገብቷቸው ከጎኑ የቆሙ የሚዲያ ታጋዮችን መፍጠር አልቻለም። አንድ ለእናቱ ብቸኛው እንደ ሚዲያ ተቋም መረጃ ቴሌቪዥን እንዲሁም ዘመድቁን በቀለ ለአመታት በብቸኝነት ለዚህ ገራገር የዋህ ለተራበ አጉራሽ ህዝብ ሞትና ስደቱን መገፋቱን በብቸኝነት ድምፅ በመሆን ለአመታት ዋስ ጠበቃ በመሆን ለብዙ ታጋዮች እንደ መነሳሻ በመሆን በታማኝነት አገልግለዋል። የዘመድኩንን ወንጭፍ መቋቋም ያቃታቸው ርካሽ ወሮበሎች ጋጥወጦች አስመሳይ የደም ነጋዴዎች ግን የክፋት መዝገባቸው መገለጥ ሲጀምር ለአምሐራ ብቻ አደለም በስርአቱ ገፈት ቀማሽ ለነበረው የኢትዮጽያ ህዝብ በሙሉ ከፊት በመቅደም የስቃይ ድምፆችን ያስተጋባን ተቋም በ24 ሰአት ውስጥ ፍርስርሡን ሊያወጡት ችለዋል። ለዚህም በግልፅ እንደታየው የእነ አስረስ ማረ ጥምር የፖለቲካ ጋፈሮች የአገው ሸንጎ፣ ፋፍዴኖች እንዲሁም የተለያዩ ሚዲያወች: አዲስ ድምፅ በዋነኝነት እና እዛው መረጃ ቴሌቪዥን በነበሩ የግል ጥቅም ተጋሪወች ለመረጃ ቴሌቪዥን ከአምሐራ ህዝብ አይንና ጆሮ መራቅ ዋነኛኞች ናቸው። ሁሉም ነገር መጥራቱ ግን አይቀርም ሁሌም ቢሆን ንጋት አለ። ሁሉም የአጁን ያገኛል። ይህ ትግል ብዙ ሌቦችን የገለጠበት ነው። ይህ ትግል መሬት ላይ ጀግኖች እንደፈጠረ ሁሉ አየር ላይ በተቃራኒው ሺህ ባንዳወችን ፈጥሯል። ሺህ መሀይም የደም ነጋዴ የጥቅም ተጋሪዎችን ወልዷል። ለኦፖርቺኒስቶሽ ለማተሪያሊስቶች የአማራ ፋኖ ትግል እንደ ሎተሪ ነው የሆነላቸው። ይህ ክፉ ቀን በዘመናት መካከል በአንድ ማህበረሠብ ወይም ሀገር ውስጥ ሊከሰት እንደሚችል በመረዳት ቀድመው የተዘጋጁበት እንደሆነ መረዳት ይቻላል። እነዚህ ምንደኞች አውርቶ አዳሪ አጭበርባሪ ሸለፈቶች ጊዜውን ይዋጁ ዘንድ እንደ መርህ በመቁጠር በህዝብ ደምና አጥንት ላይ እየተሳለቁ ይህን አጋጣሚ የገቢ ምንጫቸው በማድረግ የክህደት ጥግን በአማራ ሕዝብ ላይ አሳይተውበታል። የፋኖ ትግል እንደ አድረሽ ፈረስ የሚቆጥሩት ፖለቲከኞችና የሚዲያ ሰዎች እልፍ ናቸው። ደደቦች ስለሆኑ ሁሉም እንደነሡ ስለሚመስላቸው ሲበዛ ዥልጦች ናቸው። ስለነዚህ ከንቱዎች የሀገሬን እጣ ፈንታ እና የህዝብን መፃኢ እድል ሳስብ እየሆነ ያለው ነገረ መመልከትም ያንገበግባል። አሁን አምሐራ እንደ ህዝብ የተጠላ ፍፁም የሆነ አምሐራዊ ማንነት ነው። እስከ አለም ዳርቻ የተጠላ ማንነት ስለሆነ እንዲጠፋ ተፈረዶበታል። በስሙ የተከፈተው የውሸት ዶሴ ተገልጦም አያልቅም። ይህን ዶሴ የሚቀድ አምሐራ ነኝ የሚል ታማኝ ኤሊት ደግሞ አንድም አልተገኘም ። አንድም! የ አምሐራ ፋኖ አንድ ዘመድኩን በቀለ እና የፈጠረው አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔርን ብቻ ይዞ እየተዋጋ ነው። እውነታው ይሄ ነው! ሁሉም በሚባል ደረጃ ነባር የትግሉ ፋና ወጊ ነን የሚሉ ነባር ጋዜጠኞች ሚዲያወች ሁሉ ተጠልፈው ለሆዳቸው ተገርደው በጎጥ በመደር ተወሽቀው ወድቀዋል። እንታገልለታለን የሚሉትን የአምሐራ cause ዘንግተውት አይደለም ይልቁንም የጥቅም ተጋሪ ለመሆን በጎጥና በጓደኛ የግምባር ሰራዊት በመፍጠር የተነሱበትን አላማ ወደ ጎን በመተው ሕዝብን ለዳግም መከራ እንዲጋለጥ አድርገዋል። የአምሐራ ሕዝብ መሬት ላይ እየተዋደቀ ባለበት ሰአት የመረጃ ግንኙነቱን አየር ላይ ለሚገኙ ከአምሐራ ሕዝብ ጎን ነን ለሚሉ የሳይበር ሰራዊቶች በመተው በፍፁም እምነት ነበር የተንቀሳቀሰው። በዚህም ምክንያት አዳዲስ የትግል ሚዲያወችና ሳይበር ኤሊቶች ትግሉን እንዳይቀለቀሉ የራሱ የሆነ ተፅእኖ ነበረው። ህዝብ ጆሮ የሚደርሡ ከህዝብ ጋር እንዲሁም መሬት ላይ እየተዋደቀ ከሚገኘው የፋኖ ሰራዊት ጋር በቀጥታ ይገናኙ የነበሩ ሚዲያወችና ጋዜጠኞች እምነታቸውን በልተዋል። አሁን በልበ ሙሉነት አምሐራዊ መሰረት ያላቸው ሚዲያዎችና የሕዝብ ብሶት የተሰማቸው ፖለቲከኞች አሉ ብሎ መናገር አይቻልም። ይህ መላ አምሐራ ህዝብ ያልተገነዘበው ጉዳይ ነው። ሁሉም ነባር ሚዲያወችና ግለሰቦች መሬት ላይ እስከ ቀራኒዮ ድረስ ከሚታገሉት ጀግኖች ውጭ አምሐራነት ቅንጣት ታክል አያሳስባቸውም። በዚህ ሰአት ለአምሐራ ፋኖ ትግል ከዘመድኩን በቀለ ውጭ ዋስ ጠበቃ የሚሆን ሰው ማግኘት አይቻልም። ይኽ ሕዝብ ምን እንደበደለ አናቅም ያጀገነው ሁሉ ይክደዋል። ምን ያክል ቢደራጁ ነው ያስብላል። የደም ሀረጋቸው አንድ እስኪመስል ድረስ ከፍ ያደረጋቸው ሁሉ በአይን ጥቅሻ መርዛቸውን ሲተፉ መመልከት እና በሰፈር ሲወሸቁ ማየት የተለመደ ሆኗል። ዘመድኩን በቀለ ከቅድመ ብልፅግና እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ የከፈለውን መስዋእትነት ማንም አልከፈለም። በዚህ ሰአት ታዲያ አንድ ዘመድኩን በቀለ በልዩነት ያስፈልግ ነበርና ለአምሐራ ሕዝብ የተሰጠ ጠባቂ አድርገን እንቆጥረዋለን። ጎጠኛ ሰፈርተኞች የጥቅም ተጋሪዎች የግለሰብ ጋሻ ጃግሬዎች አቋራጭ መንገድ ወንበር ናፋቂወች እና የዶላር ቀማኞች ይህን እውነት መቀበል አይሆንላቸውም። ምናልባትም የፋኖ ትግል በዘመድኩን እጅም እንዳለ አምናለሁ። ከሸዋ እስከ ወሎ እሰከ ጎንደር አሁን ላይ ጎጃም ውስጥ የተሰገሰጉ ከርከሮዎችን እየለቀመ አንድ በአንድ እየለቀመ እያሰጣቸውም ይገኛል። ይኸን ማድረግ የሚቻለው ከሚታየው ቸነፈር ከሚነፍሰው አውሎ ንፍስ ከሚዘንበው በረዶ ከሚነደው እሳት አንፃር ይኼን ማድረግ የሚቻለው በዘመድኩን በቀለ ብቻ ነው። ይሄን መሬት ላይ ከሚዋደቁ የነቁ ፋኖዎች ውጭ ብዛኛው የአማራ ህዝብ አይገነዘበውም። "ምናልባት ዘመድኩን በቀለን ለመረዳት ተሰጥኦ ሊያስፈልግም ይችል ይሆናል!" ለዛም ነው ብዙዎች አምርረው የሚጠሉት። የጠላት አይኖች ከአምሐራ ፋኖ ትግል በላይ ዘመድኩን በቀለ ላይ ነው! ይኸም የሆነው በምክንያት ነው። ተሰጥኦ ላለው ሰው ብቻ ይገባዋል። በእርግጥም ዘመድኩን በቀለን ለመረዳት ከዘመድኩን በቀለ ብእሮች ጋ አመታትን በደስታም በሐዘንም አብሮ መዝለቅን ይጠይቃል። እንዲህም ተሁኖ ታዲያ በዚህ አድካሚ ጉዞ ውስጥ ይህን አውቆ አበድ መሳይ ጉምቱ እንድ ዘመድኩን ለመረዳት መጀመሪያ ሰው መሆንንም ይጠይቃል። ጅቦች ሲያልፉ ዘመድኩን በቀለ መጮህ ነበረበት ባለቤቶቹም ይነቁ ዘንድም ግድ ነበር: ክላሽ እና ጎራዴ ይታጠቁ ዘንድም ግድ ነበር: ድንጋይም ይሁን ቆንጨራ ያዘጋጁ ዘንድ ጩኸቱ እስፈለጊ ነበር። ይህ የዘመድኩን በቀለና የአምሐራ ህዝብ የመንፈስ ቁርኝት ነው! ይኽ አጥር በማንም ላይሰበር በፍፁም መንፈሳዊ መስተጋብር የተጋመደ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ የአምሐራ ሕዝብ ከኦሮሙማው እና ከትግራዩ ህውሀት አረመኔነት በላይ በእነ እስክንድር ጀሌዎቹ ሀይል መከራው በሺህ ተባዝቶ ሲቃውን በሰማን ነበር። በዚህ ሰአት ጎጃም እያሳለፈው የሚገኘው መከራ ለዚህ ትልቅ ማስረጃ ነው። ሌላኛው እስክድር አስረስ በሚባል ገፀባህሪ አማካኝነት የጎጃም ፋኖም ሆነ የጎጃም ህዝብ ህይወት መስቅልቅሉ እየወጣ ነው። ምናልባትም ዘመድኩን እንደሚለው ግን ማንቁርቱን ተይዞ ከኡጋንዳ እስከ አሜሪካ ከ ተደራጀው ወንበዴ ስብስብ ጋር ለፍርድ መቅረቡ አይቀርም። በዚህ ፈታኝ ጊዜ አዳዲስ የትግሉ ቱርፋት የፈጠራቸው አምሐራዊ ደም የተዋሐዳቸው እስከ ቀራኒዮ ከህዝብ ጎን የሚቆሙ አዳዲስ የሳይበር ሰራዊቶችን ማዋለድ ግድ ይለናል።በቲክቶክ የሚመራ የአማራ ትግል የለም። በነ ሞጣ ቀራኒዮ በእነ ቤተልሔም ዳኛቸው እና መሰል የቲክቶክ አራዊቶች ስር ተወሽቆ የአባቶቻችን ዙፋን መናፈቅ ቂልነት ነው።

  • без подписи

  • የለማ። በስንቱ ይካዳል ይህ ህዝብ። ይህ ወያኔ ህውኀት ናፋቂው የሰሊጥ ናፋቂው የሰሊጥ አርበኛ በብልፅግና ጥርቡ ሙላት #አድህኖ መሪነት በተሰራው ድብቅ ተልዕኮ ኢትዮ 251 እንደ ሚዲያ በእንዝህላልነት አርበኛ ውባንተን ለአንድ ወገን ድብቅ አላማ ማስፈፀሚያነት ተላልፎ እንዲሰጥ እና ዋጋ እንዲከፍል ትልቁን ሚና ተጫውተዋል።ከዛን ጊዜ በኋላ በተለየ ሁኔታ ስለተከሰቱ ሀያሌ የፖለቲካል ኮንስፖይሬሴ አካሔዶች የአምሐራን ህዝብ መከራ ሲያበዙበት በግልፅም የተለያዩ የግል ፍላጎት አራማጆች የእከካቸው ማራገፊያ ሲያደርጉት እየተመለከቱ በዝምታ በማለፍ እና የህዝብ ስቃይ ህመሙ በግልፅ እንዳይሠማ የውሸት ደመሠሠውና ማረከው በሚል ማዘናጊያ ዜናዎችን በማሰራጨት በሕዝብ ላይና መሬት ላይ ባሉ ጀግኖች ትግል ላይ አፊዘዋል። ግርም የሚለው አንድም ቀን በግልፅ ስለ ጠላፊውና ጭምብላሙ እስክንድር ነጋና ጄሌዎቹ በስተትም ከተሰሩት የክህደት ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴን ሴናርዮ ለማሳየት አለመዠሞከራቸውን ስንመለከት አብዝተን እንድንጠራጠርና ከውስጥም ከውጭም ከተገለጡ ጠላቶቻችን መሐል ለይይተን እንደማናየቸው ሊገነዘቡ ይገባል። አምሐራው ይሔን መጠየቅ ይጀምራል። የአንድን ግለሰብ ፍላጎት አላማ እና ፖለቲካል እሳቤ ከህዝብ ፍላጎት ጋር ጨፍልቆ እኩል ማወዳደርና ባላንስ ለማድረግ መሞከር ነውርም ነው። ይቀጥላል....... #The Amhara Chronicle https://t.me/AmharaChronicle 01/06/2017 ዓ.ም

  • ከዚህ ከገጠመን ጦርነት በላይ የአምሐራ ተወላጅ ነን ትግሉ ይመለከተናል በሚሉ በአንድም በሌላ ህዝቡ አምኖ በተቀበላቸው የሚዲያ እና መሬት ላይ በሚገኙ ከሀዲ ባንዳዎች ምክንያት ክፉ ጊዜ እያስተናገድን ነው። በትክክልም ለአምስት አስርት አመታት በተግባር የተጠነሰሰው የጄኖሳይዳል ሙከራ አሁን ላይ አምሐራን የማጥፋት ፕሮጀክት ፋፃሜ ላይ መድረሡን እየተመለከትነ ነው። ትናንት የአምሐራ ትግል የት ይደርሳል ተብሎ በመላ ኢትዮጵያ ሁሉ በጉጉት ሲጠብ የነበረ ትግል እዛው የአምሐራ ህዝብ መሐል በተወለዱ የዲቃላ ልጆችና አምሐራም ሁነው ለከርሳቸው በተገረዱ ድልብ መሀይም የአምሐራነት ስነ ልቦና የሌላቸው ቅልብ ብአዴናውያን አማካኝነት ትግሉ የከፋ ፍጅት እያደረሠብን ይገኛል። ባለፉት አስርት አመታት ብቻ እንኳ ይህ እንቅስቃሴ ለሁሉም በተገለፀበት ሁኔታ ነገር ግን የተቀረው አምሐራ ምን እንደተደገሰለት ባልተረዳበት ሁኔታ ጥቂት የማይባሉ የአምሓራ ሆዳም ውክሎችና ምሁራንና ግለሰቦች መጪው የአምሐራ እጣፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል መረዳቱ መገንዘቡ እያላቸው በማንያገባኛል ተዕቢት ለሆዳቸው ተኝተው የተገረዱ በመሆናቸው ብቻ ዛሬ ህዝቡ ለገባበት እና እያስተናገደ በሚገኝበት ሞትና መሳደድ መንገድ ጠራጊዎች ነበሩ። በዚህ ሰአት ለገጠመን መከራ መሳደድ እና የውሻ ሞት: ከቀበሌ ሚኒሻ እስከ ላይኛው የመንግስ እርከን የስልጣን ተዋረድ የነበሩ የነበሩ የወያኔ ህውሀት ጥርብ የተሐድሶ አቀንቃኞች እስከ ብልፅግና አጨብጫቢ ሹመኛ ቂል ሐሞት የለሽ አጎንባሾች-የአምሐራነት :ምንሊካዊነት ÷ የቴዎድሮሳዊነት፣ የበላይዬነት መንፈስ ለሰከንድ ያልተዋሐዳቸው ፣ አገልጋይነትና ታማኝነት እንደ ገብርየ እና እንደሽፈራው የአምሐራነት ስነልቦና ያልተላበሳቸው: የአፄነት ክብር ልባቸዉ የማይናፍቅ አምሐራዊ ስብዕና አደብዛዦች: የአንድን በአለም ላይ ሁሉ ስሙ እንደ ጊዮን ወንዝ ገዝፎ ከፍ ብሎ የሚዘከርን ህዝብ አምሐራዊ ሳይኮሎጂካል Mind Set የሠበሩና ያዋረዱ በመሆናቸው በምድር በሰማይ ፍርዳቸውን መቀበላቸው አይቀርም። ፍፁምም እናምናለን። ለዚህም ነው ለይተን ካወቅነው ጠላታችን በላይ ከውስጣችን የመሸገው ባንዳው አምሐራ ስቃያችን ያከበደው። የትናንት ጄሌ ቅልብተኛ ወያኔ ወብልፅግና ፍራሽ አዳሽ አልጋ አንጣፊ መሀይም ዲቃሎች ሞታችን መከራችን ሊያራዝሙት ከጀግኖች ጎራ እንደ ጀግና ተመስለው ገብተው Behind the curtain እንደ መሪ እየተጫወቱ ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን የሚያምነውን የሚጠብቀውን የፋኖ ትግል: እናት ልጇን የገበረችለትን የፋኖ ትግል: አባት ለልጁ በሬውን ሸጦ የገዛውን ጓንዴና ምንሽር ወልውሎ ዝናሩን አስታጥቆ ድል ሳያደርግ እንዳይመለስ መርቆ የሸኘበትን የፋኖ ትግል ጠልፈው መከራችንን ሺህ ጊዜ ሌያባዙብን ከፊት ለፊት እየተራመዱ የክፋት መንገድ ራጊ ሆነው ዳግም በፈሰሰው ደማችን ላይ ሲዘባበቱ መመልከት..... አወይ አምሐራ ስንቱን ቻልከው! ከባድ የጣር ጊዜ ላይ ነው አምሐራ። እርግማኑ እንደቀጠለ ነው። ከምንም በላይ አንድ እውነተኛ የህዝብ አገልጋይ የሚዲያ ሰራዊቱን የሚመራ በ እውነትና በመርህ የአምሐራን Cause ተረድቶ በድፍረት መረጃን የሚተነትን ምሁርና ጋዜጠኛ አለማግኘታችን ምንስ ብንበድል ነው?! የተደበቀ ያለየለትም ለፍልፈው የወጡ የአየር ላይ አጋንቶችንም በጊዜ አሳይቶናል ። የህዝብ ዕንባ ተረስቶ ሞትና መሳደዱ በእሳት መቃጠሉ በርሀብ አለንጋ መገረፉ ተንቆ ለግል ፍላጎታቸው ብቻ እንደ አድራሽ ፈረስ ቆጥረውን ሲቅበዘበዙ በየሚዲያው ሲያመነዥኩ የኋላ የኋላ አምላክ በጥበቡ ዳዊትን አስነስቶ ድብቅ ክፉ ስራቸውን የገለጠበት ቅዱስ ትግል ነው። እነዚህ ክፉ የአየር ላይ እና በምድር ላይ የተሰገሰጉ አጋንቶች በሆዳቸው ተስበው የተከሉት ክፉ ተንኮል ተሳክቶላቸው ፍሬም አፍርተው በተለይ የጎጃም ፋኖ ውስጥ አጠቃላይ የአምሐራ ህዝብ ላይ ፈንጅ ቀብረው መቀባጀራቸው አልቀረም። በዚህ የፋኖ ትግል እንደ ነቢያት ተናጋሪ የነበሩትን እንደ ቅዱስ የተቆጠሩትን የፋኖ ፌክ ታጋዮችን ሁሉ ገላልጦ እንደ ወደቁ መላእክት በአየር በምድር በታትኖ ያጋለጠ ነው። ከዚህም በኋላ የአማራ ህዝብ በልጆቹ ሊኮራበት የሚችል የሳይበሩን ጦርነት የሚመራ የሚዲያ ጄኔራል ማግኘት ተስኖታል። 60 ሚሊዮን በላይ ለሆነ ህዝብ አንድ ታማኝ አገልጋይ ማጣት ያንገበግባል ...😭😭😭 የቀደሙት ፊት አውራሪዎች የአሁኖች ጭምብል አውላቂ የዶላር እርዝራዥ ከሀዲ ባንዳዎች የኢትዮ 360 /Ethio360/ ሚዲያና አባላት- ሀብታሙ አያሌው/ቀንድ አውጣ/ እና ጀሌዎቹ እነ እየሩሳሌም /ያፈሰሰችው እምባዋ ሳይቀር የአምሐራን ሴቶች ሁሉ የካደች/ ብሩቅ ይባስ ግን ደጀ ሰላም አካባቢ ያለ መለኩሴ በሉት የሚክድ አይመስልም የዋህ ነው-ሀብታሙ አያሌው ማደንዘዣ የሱዳን ጭስ እንደቀባው ይታማል😁፣ አዲስ ድምፅ ሚዲያ አበበ እስክስታ በለው ግን ከእውቀት ነፃ ነው። ድሮም እኮ ደደብ እንደሆነ ፊቱ ያስፎግራል ግን ትወናው ከባድ ስለነበር እየተቅለሰለሰ አምሐራውን ጋጥ ያደረገ ክፉ ሰው ነው። እንዲሁም ሌሎች በ መረጃ Tv አየር ሰዐት ተጠቃሚ የነበሩ በሙሉ / ዘመድኩን ነጭ ነጯን አያካትትም/ የቀድሞው ኢትዮ ኒውስ /Ethio News/ በለጠ ካሳ or Current affaires ሚለው ነገርም አለው- በእውነት አሁን ይሄ ሰው ምኑ ጋዜጠኛ ይመስላል ከባንዳነት ከጎጠኝነት የተሻለ እንዴት አታግሎ ያታግላል። ሌላኛው ዋሜራ ሚዲያ/Wamera Media/ ነው። ግርማ ካሳ ከዘመዴ ጋ ይግበባሉ። ኦሮሞ ነውም ይባላል አምሐራ ትግል ሾተላይ በመሆን አገልግሎቱን ጀምሯል: ዘመዴ እያስተነፈሰው ነው። ምናላቸው ስማቸው ከእነ ሀብታሙ አያሌው ጋር ስራቸው ትግል መጥለፍ ሆኖ ሳለ በምን ምክንያት ተጣሉ? የእስክንድር እንደራሴዎች ጣና ቴሌቪዥን። ኢትዮ 251 ሚድያ /Ethio 251 Media / ሙሉጌታ አንበርብር እና ጓደኞቹ ህብረት ስራ ማህበር /እነ ጓድ'ን ግን በምን ተቀይመሐቸው ነው አልገባንም ሁሉም ጠፉብን እኮ። ነው ወይስ እራስህን እንደ ታማኝ የአምሐራ ትግል አቀንቃኝ ነኝ ብለህ ታስባለህ? ሙሉጌታ አንበርብ ሁሉም ሰው የሆነ ነገር ካንተ ይጠብቃል። መንግስትን ብቻ እየተቸህ በአምሐራ ፋኖ በውስጥ ትግል ውስጥ የክፉ መሪወችን መከፋፈል ስራ ባላንስ ለማድረግ ከና አካቴውም እያወቅህ ግን ባላንስ ለማድረግ ምትሔድበትን መንገድ ፅዩፍ መሆኑን ልታውቅ ይገባል። ይህ ደግሞ ለትግሉ አንዳች ነገር አይፈይድለትም። የትግሉ መጨረሻ ላይ ሚና ነበረኝ አስቡኝ ለማለት ይጠቅምህም እንደሆነ እናያለን። Ethio 251 ሚዲያ እነ ሙሉጌታ አንበርብር በአምሐራ ፋኖ ትግል ውስጥ በውስጥ ባንዳ ተላላኪ መሪወች የሚከናወኑ እያንዳንዷን ተንኮል ክፋት ነውር አበጥረው ያውቃሉ ወይም መረጃው አላቸው። ይሔን ግን ለህዝቡ እና በትግል ላይ ላሉ እውነተኛ መሪወችና የፋኖ ታጋዮች ሴራውን ወደ ሚዲያ ማውጣትና ለህዝብ ማሳወቅ አይፈልጉም። ይህ ትልቅ ክህደት ነው። ይህ ከፋፋይ ሴራ እንዳይገለጥ በየቀኑ አሰደማሚ ምናልባትም ማደናገሪያ የጀብድ ታሪክ ሲግቱን ይውላሉ ይኼ ነውር ነው። በአርበኛ ውባንተ ላይ የተሰራው ሴራ እንደ ሚዲያ Ethio 251 የመጀመሪያ ሀላፊነቱን ይወስዳል ነገ መጠየቁም አይቀርም። በይቅርታም የሠሩት ዶክመንተሪ ለጊዜውም ቢሆን እንጂ ነገ ቀን ሲመጣ በትክክልም ይጠየቁበታል። ያ የሰሊጥ ነጋዴ የህዋት ቅጥረኛ የብልፅግና ሸውከኛ ሙላት አድኖን ከተቋሙ መባረሩ ለኀጥያታችሁ ስርየት ካሰጠም እናያለን። እውነት ፍርድ

  • መጠየቅ እንጀምር። ሙሉጌታ አንበርብር አሁን ደግሞ አጋፋሪ ብለህ ተሰብሥበህ መጣህ። ስንተኛ ጓዶችህ ናቸው? ከህዝብ ጎን ምትቆምበት ሰአት አሁን ነው። የጓደኛ ማሊያም መቀያየር አላማረብህም። መናህ ከወዴት ነው ብድፍረት ሚጠይቅህ አልነበረም አሁን ግን ደፈር ብለን ልንጠይቅህ ይገባል!

  • የሚደነግግ ህግስ አለወይ?ሶስተኛ፦ በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ቋሪትና ደጋ ዳሞት ላሉየሽብር ቡድን አስተባባሪዎች በስልክ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም በመደወል መከላከያን ማጥቃት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በማሳወቅ እንዲመቱት ትዕዛዝ ሰጥቷል የሚል ነው። አቃቤ ህግ ለዚህ ክሴ አስረጅ የሚሆን አንዳችም ማስረጃ አላቀረበም። የተደወለበትና የጥሪ ተቀባይ ስልክ ቁጥሮች እንዲሁም የትዕዛዝ ተቀባይ ግለሰቦች ማንነት አልቀረበም። በቀረበ የማስረጃ ዝርዝር ላይም በተሰጠው ትዕዛዝ መነሻነት በቋሪትና ደጋዳሞት ወረዳዎች የተጎዱ ሰዎችና ንብረት ዝርዝርም አልቀረበም። የፍሬ ነገር ክርክር ሲደረግ የማቀርበው እንደተጠበቀ ሆኖ የወቅቱ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የፌደራል መንግስት የፀጥታ ኃይሉን ወደ ክልሉ እንዲገባ የጠየቁት ሐምሌ 27/2015 ዓ.ም ነው። የመከላከያ ሰራዊት ወደ ደጋ ዳሞትና ቋሪት መግባት የሚችለውም ርዕሰ መስተዳደሩ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ በመሆኑ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም አቃቤ ህግ በክሱ ርምጃ ይወሰድበት ብለሃል ያለውን መከላከያ በምን አግባብ ቋሪትና ደጋዳሞት ሊገባ ቻለ የሚል ከባድ የህገ መንግስታዊነት ጥያቄ የሚያስነሳ  ነው። የተከበረው ችሎት፤ ክቡራን ዳኞች፤ አቃቤ ህግ በስልክ ትዕዛዝ ሰጥቷል በሚል የሁለት ግለሰቦች ንግግር የያዘ ድምፅ አዳምጨዋለሁ። አቃቤ ህግ በስሜ በተመዘገበ የታወቀ ስልክ ቁጥር ስለመደወሌ፣ የደወልኩበትን ስልክ ቁጥር እና አስተባባሪ ነው ያለውን ግለሰብ ስም አላቀረበም። ለመሆኑ በማስረጃነት ያቀረበው የድምፅ ቅጅ የኔ ስለመሆኑ በምን አረጋገጠ? በምን መሳሪያ መረመረው? ኢትዮጵያ የድምፅ አሻራ መመርመሪያ መሳሪያና በዚህ መስክ የሰለጠነ ባለሙያ የላትም። የት አስመርምሮት? ምን ያህል ፐርሰንት ከእኔ የትኛው ኦሪጅናል ድምፅ ተነፃፅሮ ምስስሎሽ ተገኘበት? እንደ አገርስ የድምፅ ምስስስሎሽ መቁረጫው መቶኛው(cut -off percentage) ምን ያህል ሲሆን ነው ህጋዊ ውጤት የሚኖረው? እነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆነው እና የቀረበው የድምፅ ማሰረጃ የእኔ አይደለም እንጅ፤ ቢሆን እንኳን ወንጀል የሚያቋቁም አንዳችም የህግ ጥሰት ግን አላገኘሁበትም። በመጨረሻም፦ አቃቤ ህግ ያቀረበው የፀና ፈቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ መያዝ ጉዳይ ህጋዊ ፈቃድ ያለኝ፣ የፈቃድ ደብተሩንም ለ8 ወራት ይዘውት ቆይተው የመለሱልኝና ማቅረብ የምችል መሆኔን ለችሎቱ አስታውቃለሁ። አቶ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬ. @tikus_tikusuan

  • የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬ በችሎት የተናገሩት! በአቃቢ ህግ በክስነት የቀረቡ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ለተከበረው ችሎት ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት ክቡራን ዳኞች እንዳቀርብ ትፈቅዱልኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ። አንደኛ፦ እኔ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬ ዛሬ በዚህ ችሎት በተከሳሽነት የቆምኩት፤ ለ550 ቀናትም በግፍና ችካኔ እገታ ውስጥ የምገኘው ለአንዲት ደቂቃ እንኳን በጥፋተኝነት የሚያስቀጣ አንዳችም የወንጀል ድርጊትን የሚያቋቁም የህግ መተላለፍ ስለፈፀምኩ አይደለም። ይልቁንም የአማራ ህዝብ የሚያነሳቸውን የህልውና ጥያቄዎች በይፋ በማቅረቤ፤ በህዝቤ ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል በማስረጃ በመመሞገቴ፣ የገዠውን ፓርቲ አፈናና የመንግስት አሰራሮችንና አመራሮችን ብልሹነትና ዘረፋ በመታገሌና በማጋለጤ ነው። ያደረግኋቸው ትግሎችና ማጋለጦች በሙሉ በህጋዊ መድረኮችና አማራጮች ያደረግኋቸው ናቸው። ራሴው ጭምር በኮሚቴ አባልነት ተሳትፌባቸው የተረጋገጡ አማራውን በጅምላ የመግደል፣ማፈናቀልና ማሳደድ ዘር ተኮር ጥቃት ሪፖርቶች፣ የኢትዮጵያ ሰባዊ መብት ኮሚሽን በተለያዩ ጊዚያት ያወጣቸውን ሪፖርቶች እንዲሁም ልዩ ልዩ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሰባዊ መብት ተቋማት ያወጧቸውን ሪፖርቶች በመያዝ መንግስትና ገዘው ፓርቲ ብልሹ አሰራሮችንና አመራሮችን እንዲያስተካክል ታግያለሁ። ይህንንም በቀጥታ የሬድዮና የቴሌቪዠን ስርጭት ባገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ያደረግሁት ነው። በምክር ቤቱ በመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነቴ በነበረኝ ኃላፊነትም በፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የተከናወኑ የኦዲት ሪፓርቶችን መሰረት በማድረግም የከፋ ችግር ያለባቸውን ተቋማት አሰራራቸውን፣ አደረጃጀታቸውን እና አመራራቸውን እንዲያሻሽሉ የመገምገም ስራ ሰርቻለሁ። ተደጋጋሚ የአመራር ብልሹነት ያሳዩ አካላትም የወንጀልና ፍትኃብሔር ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ክስ እንዲመሰረት ፍትህ ሚኒስቴርን አዝዣላሁ። በምክር ቤት አባልነቴም ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በአሰራራቸው የፋይናንስ ግልፀኝነትና ህጋዊነትን እንዲከተሉና እንዲያረጋግጡ እንዲሁም ኦዲት ለመደረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቂያለሁ። እነዚህን ጥያቄዎች እንዳልጠይቅ አንዳንድ አመራሮች በግል በኢመደበኛ ሁኔታ ለማግባባት ሞክረዋል። አንዳንዶቹም ሊያስገድሉኝ፣ ሊያሳስሩኝና አንዳች አይነት ጉዳት ሊያደርስቡኝ እንደሚችሉ ጭምር ነገረውኛል፤ መልዕክትም አድርሰውኛል። ይህ ሁሉ የሆነው ያጎደልኩት ስነ- ምግባር አልያም የተላለፍኩት ወንጀል ስለነበር አልነበረም። ይልቁንም ያደረግሁት ሁሉ በህዝብ እንደራሴነቴ ህዝብና ህግ የጣለብኝን ግዴታ እና ኃላፊነት ነው የተወጣሁት። ያደረግሁት ሁሉ የሚያሸልም እንጅ የሚያስነቅፍ አልነበረም። እጅግ ሲከፋም አሁን ባለሁበት ሁኔታ የግፍ ሰለባ የሚያደርገኝ መሆን አልነበረበትም። የተከበረው ችሎት፤ ክቡራን ዳኞች፤ ቀደም ብዬ እንዳወሳሁት ለ550 ቀናት በአስከፊ ሁኔታ የተሰቃየሁት፤ ለቀጣይ ለማይታወቁ የሰቆቃ ሌሊቶችም በአገታ የምቆየው አንዳችም ወንጀል ስለፈፀምኩ አይደለም። ማን እንዳሰረኝ፣ ለምን እንደሰረኝ አውቃለሁ። እውነታውን ፈጣሪ፣ ህዝቡም ያውቃል። ሁለተኛ፦ እኔ አማራ የሆንኩት አማራ ሆኘ ስለተወለድኩ ነው። የአማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ የሆንኩትም ፈቅጀ፣ መርጨና ወድጄ ነው።በየትኛውም ቦታና ሁኔታ ለአማራነቴ ጥብቅና መቆምም ተፈጥሯዊ ግዴታዬ ነው። በዚህም በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ ስርዓታዊ፣ ተቋማዊ ህገመንግስታዊ ሁለንተናዊ በደሎችና መገፋቶችን ለማስቆምና የህዝባችንን ዘላቂ መብቶች፣ ፍላጎቶችና ጥቅሞችን ለማስከበር የአማራ ህዝብ የህልውና ጥያቄዎች ናቸው ብሎ በለያቸው የፓለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አጀንዳዎች ላይ ፕሮግራምና ፖሊሲ በመቅረፅ እንዲሁም የመመስረቻ ማንፌስቶ በማዘጋጀት ከትግል ጓዶቼ ጋር በመሆን በምርጫ ቦርድ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰኜ ፓርቲ አቋቁሚያለሁ። በ6ኛው ዙር አገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫም 5 የፓርላማና 13 የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን አሸንፈናል። ባነኘነው ወንበርና በመራጮች ድምፅ ብዛትም የኢትዮጵያ ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ ነው። እኔም የህዝብ እንደራሴ የሆንሁት ገዠውን ፓርቲ ጨምሮ ከተፎካካሩ ሌሎች 8 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወዳድሬ አሸንፌ ነው። በምርጫ ማንፌስቷችን፣ በመመስረቻ ጽሑፋችን በልዩ ልዩ መድረኮች ባካሄድናቸው የምርጫ ክርክሮች ጭምር የህዝባችንን እሴቶች እንደምንጠብቅ፣ የአማራ ብሔርተኝነት የማደራጃና የርዕዮተ-ዓለም ማዕቀፋችን እንደሆነ እንዲሁም ህዝቡ መርጦን መንግስት ከሆን የህዝባችንን የህልውና ጥያቄዎች እንደምንመልስ ተከራክረናል፣ ቃል ገብተናል። አማራዊ እሴታችን ለእኛ ቅዱስ ነው። እኛነታችን ከደምና ስጋ ብቻ ሳይሆን ከአማራዊ እሴት ጭምር የተሰራ ነው። በዚህም ደስተኞች ነን። ይሁንና አቃቤ ህግ ባቀረበው የፖለቲካ ውንጀላ ሰነድ ላይ ''አማራ ርስቱን ተቀምቷል፤ አገሪቱ በአማራ እሴት መመራት አለባት'' የሚል የርዕዮተዓላማዊ አቋም መያዛችን ክስ ሆኖ ቀርቧል። የተከበረው ችሎት፤ ክቡራን ዳኞች፤ ''የአማራ ህዝብ የህዝብና ግዛት አንድነትና ኢ-ተነጣጣይነት ተገርስሷል'' የሚለው እውነት እኔ ብቻ ሳልሆን መላው አማራና በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚጋሩት ኃቅ፣ ፓርቲዬ አብንም በመመስረቻ ሰነዱና በምርጫ ማንፌስቶው በግልፅ ያሰፈረው፣ ያሁኑ የአማራ ብልፅግና የቀድሞው አዴፓ በ12 መደበኛ ጉባኤው ተገቢነቱን አምኖ የሚታገልለት የአማራ ጥያቄ መሆኑን በይፋዊ መግለጫ ጭምር የተቀበለው ነው። የፌደራል መንግስቱም የአማራ ህዝብን ጨምሮ በሌሎችም ብሔረሰቦች የሚቀርቡ የማንነትና ወሰን ጉዳዮችን እልባት ለመስጠት ኮሚሽን እስከ ማቋቋም መድረሱ፣ አሁን በስራ ላይ ባለው  አገራዊ ምክክር ኮሚሽንም እንዲፈቱ ከተያዙ ቁልፍ አገራዊ አጀንዳዎች አንደኛው መሆኑን ወስዶታል። ታዲያ እንዴት ክስ ሆኖ እኛ ላይ በልዪነት ሊቀርብ ቻለ? እሴትን በተመለከተ ለችሎቱ ለማስገንዘብ ያህል፦ እሴት ማለት የጋራ የሆነ ማህበረሰባዊ የነገሮች ምልከታ ሆኖ የማህበረሰብ አባላት በግልና በጋራ የሚያከናውኗቸውን የየዕለት ተግባራትና እሳቤዎች ጥሩነት አልያም መጥፎነት እንዲሁም ተገቢነቴና ኢ-ተገቢነት መለያ መርኋቸው ነው። የአማራ እሴት ማለት የማንነቱ መገለጫዎች የሆኑት ለአብነትም አማኝነት፣ለጋስነት፣ ሩህሩህነት፣ ይቅርባይነት፣ደግነት መልካምነት፣ ኃቀኝነት፣ጀግንነት፣ ሰውዳድነት፣ ሰው አክባሪነት፣ ግልፅነት፣ ትሁትነት፣ እንግዳ ተቀባይነት፣ ቀናዒነት፣ አርበኝነት፣ ህግ አክባሪነት፣ ፍትኃዊነት፣ርቱአዊነት፣ ታማኝነት፣አስተዋይነት፣ ጥበበኝነት፣ገርነ፣ ትዕግስተኝነት፣መንፈሰ ጠንካራነት ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህ የአማራ ህዝብ እሴቶችአማራነታችንን የገነቡ የስነ ልቦና ውቅሮች ናቸው። አቃቤ ህግ አንዳችም ማስረጃ ማቅረብ አይችልም እንጅ ኢትዮጵያ በእነዚህ የአማራ እሴቶች ብቻ መመራት ይኖርባታል'' የሚል አቋም ብይዝ እንኳን ጉዳዩ የፖለቲካ ሙግትና ውይይት፤ ክርክርና ድርድር አጀንዳ እንዲሁም ለመራጭ ዜጎች ይሁንታ የሚቀርብ የምርጫ ኮረጆ ጉዳይ እንጂ በወንጀለኝነት የሚያስጠይቅ አይደለም። ይህ የአቃቤ ህግ ክስ ግን መንግስት ከአማራና ከአማራነት የፀዳች ኢትዮጵያ ነው ወይ የሚፈልገው የሚል ሙግት ያስነሳል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከአማራና አማራነት በስተቀር እንዲሆኑ

  • без подписи

  • без подписи

  • Can We Condemn That Act of Killing?!😭

  • ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈትን ተከትሎ ምን ውሳኔ አሳለፈ ? የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ከዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራር አካላት ጋር የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ውይይት ማካሄዱን ገልጿል። ውይይቱ በተለይ ቤተሰቦቹ ሊደገፉ በሚችሉባቸውና ሃኪሙ በህይዎት ዘመኑ ያከናወናቸው ልዩ ሙያዊ አስተዋጽኦችን መዘከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ዶ/ር አንዱአለም ምንም እንኳን የተሰጠውን ጸጋ ሳይሰስት በመጠቀም ለበርካቶች የዘርፉ ባለሙያዎችና በሙያው ላገለገላቸው በርካታ ህሙማን የቅን አገልጋይነት ተምሳሌት የነበረ እንቁ ባለሙያ ቢሆንም ገና በ37 ዓመቱ የተቀጠፈ በመሆኑ ለህጻናት ልጆቹና ቤተሰቡ ትቶ ያለፈው ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሌለው መሆኑ ተገልጿል። የቀረቡለትን በርካታ ዓለምአቀፍ የስራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገኑን ለማገልገል ቆርጦ የነበረ ባለሙያ ከመሆኑም በላይ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ክፍል የነበረውን ልዩ አበርክቶና የቀዶ ጥገና ክፍሉን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሻሻል እየጣረ የነበረ እና እውን ለማድረግ ጫፍ ላይ ደርሶ ያለፈ መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የነበረውን ሞያዊ አቅም ተጠቅሞ ራሱን ለተገልጋዮች በቅንነት ሰጥቶ ያለፈ ታላቅ ባለሙያ እንደነበረ የስራ ባልደረቦቹ ፣ተማሪዎቹ እና አገልግሎቱን ያገኙ ደምበኞቹ የሚመሰክሩለት ድንቅ ሃኪም የነበረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል። በመሆኑም ፦ ➡ የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤ ➡ ባለቤቱ ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤ ➡ ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሰራው እሱ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈቱ ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረ በመሆኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስሙ ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤ ➡ የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምለት፤ ➡ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስሙ BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም፤ ➡ ለ40ኛ ቀኑ መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶ/ር አንዱአለም የህይዎት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል። ውሳኔው ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡ #BDU @tikvahethiopia

  • #የሳይበሩ አለም መሪዎች! 5. መምህር ነዋይ ካሳሁን 4. መምህር ሳሙኤል(ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ) 3. መምህር ፋንታሁን ዋቄ 2. ዲ/ን ዮርዳኖስ 1. መምህር ዘመድኩን በቀለ ( ይህ ቆቱ ጥጋበኛ ቢሆንም በልዩነት እንመጣበታለን😂😂😂) በዚህ ሰአት የኢትዮጵያን ሪሊጂየስ ኤንድ ፖለቲካል ላንድስኬፕ: በዋንኝነት አማራ የገጠመውን መከራ በመረዳትና የተጋረጠበትን የጀኖሳይድ ሴናርዮ በመተንተን ፈር ቀዳጅ ሆነው ከፊት የተገኙ የተዋህዶ ልጆች ናቸው! እነዚህ ግለሰቦች ቤተክርስቲያን አምጣ የወለደቻቸው ምስጉን ሀቀኛና እውነትን የተጋፈጡ: በልዩነት የተኛውን የሚያነቁ: የመንግስትን ነውረኝነት÷ባለጌነት: ጥርቅም መናፍቅ የጎሳ ቡድንተኛ መናፍቅ የሐይማኖት አባቶች (ነውር ጌጡ ሆነው ፋራ ሠገጤ ሆነው ሲነቃባቸውም እፍረት የሌላቸው አይናቸውን በጨው አጥበው  በመንግስት ወታደር እየተጠበቁ የምእመንን ስቃይ ቢያራዝሙትም) እነዚህን ሰንኮፎች መግቢያ መውጫ በመሳጣት የሚያደርጉትን ተጋድሎ ሁሉም በአፅንኦት ሊመለከተው ይገባል። ከስር ከስር መከታተልም አስፈላጊ ነው።  እንደ ሀገር እንቅልፍ ላይ መሆናችን እርግጥ ነው እንደ ሀገር ዳንኪራ ላይ ነን ጦርነት ያጎሳቆለን አንመስልም እረሀብ ያጠቃን አንመስልም ሀገር ለመጥፋትና ለመበታተን ጣር ላይ መሆኗ ተዘንግቷል። ሠቆቃ ከሞላው የኑሮ ውድነት አንገቱን አስደፍቶት በየቤቱ ጥሻ ከወደቀው በላይ ምድሪቱ ላይ ጊዜ ያበቀላቸው አረሞች ድሎትና ደስታ ሀዘናችንን መከራችን ያስረሡ ዘንድ ግድ ነበርና በአግራሞት ከመመልከት የተሻለ አልነበረም። በዚህም የተነሳ ብርቱ የማህበረሰብ አንቂ ሰዎቻችን መልእክታቸው ለማዳረስ እንቅፋት ሲሆንባቸው እንመለከታለን። ሁሉም ስካር ላይ ነው:  የጠገበውና በቤቱ መከራ የገባው እኩል እብደት ላይ ነው: ሚለያቸው የሚያስተናግዱት pain ብቻ ነው። በዚህ ልክ አቅላችን ስተናል እውነት ትህትና ምግባር አፈርድሜ በልተዋል። ማይክ የጨበጠ ሁሉ ህዝቡን ይግጠዋል በዐት ዘግተው የተቀመጡ ሊቃውንት አባቶች ተዋርደዋል። ነገርየው በፀሎት ብቻ የሚለቅም አይደለም አባቶችን ጭምር እንደ ዳዊት ወንጭፍ የሚያነሱበትም ደረጃ መድረሡን ልብ ልንለው ይገባ እንደሆነ ለደቂቃ ማሰብ ሳያስፈልግ አልቀረም። #The Amhara Chronicle https://t.me/AmharaChronicle

  • без подписи

  • без подписи