tgindex
Amhara development Assocation-Head Office

Amhara development Assocation-Head Office

Статистика

Amhara Developmet Assocation/ADA/

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
9
Всего постов
28
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 010
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
 
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
375
23 постов
Вовлечённость
18,7%
к подписчикам
Постов в день
1,3
всего 28
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ከጎዳና ሕይዎት እስከ አልማ የብቁ ወጣት የሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊነት_ የአካል ጉዳተኛው ወጣት የሕይዎት ጉዞ -------/////------_- ​አንዳንዶች በሕይወት አጋጣሚ በሚገጥማቸው ፈተና ተስፋ ቆርጠው ሲቀሩ፣ ሌሎች ደግሞ እሾሁን ወደ አበባ፣ ፈተናውን ደግሞ ወደ ስኬት መሰላል ይቀይሩታል። በደብረ ታቦር ከተማ የተወለደው ወጣት አገኘሁ ደሳለኝ እሾሁን ወደ አበባ፣ ፈተናውን ደግሞ ወደ ስኬት መሰላል ከቀየሩት ወገን ነው።​ ሕይወት ላዘጋጀችው ውድድር ገና በልጅነቱ ነበር የተሰለፈው። በወቅቱ በነበረው የአካል ጉዳት ምክንያት እንግዳ ወደ ቤት ሲመጣ ይደብቁት የነበረበት፣ ለትምህርትም ኾነ ለሥራ አይኾንም ተብሎ የተገፋበት፣ በባሕር ዳር ጎዳናዎች ላይ እስከ መተኛት የደረሰበት መራራ እና አሰቃቂ ጊዜያትን እንዳሳለፈ ይናገራል። ​ነገር ግን ወጣት አገኘሁ ለእነዚህ ችግሮች ሁሉ አልተንበረከከም። ​"አካል ጉዳተኝነት አለመቻል አይደለም፤ ከሰው እጅ መጠበቅን ትተን ሠርተን ለሌሎች መትረፍ እንችላለን" የሚል የማይንበረከክ መንፈስን ሰንቆ ተነሳ። ከጎዳና ሕይወት እስከ ሊስትሮነት፣ ከኮብልስቶን ሥራ እስከ ልብስ ስፌት የላቡን ጠብታ እየገበረ የጽናት መንገድን ተጓዘ። ​ዛሬ አገኘሁ በሥራው ውጤታማ ኾኖ በራሱ ጥረት የልብስ ስፌት ማሽኖችን በመግዛት የራሱን ሱቅ ከፍቶ እየሠራ ነው። ከዚህ ባሻገር ለሁለት ወጣቶች የቋሚ ሥራ ዕድል ፈጥሯል። ​ለ12 ተማሪዎችም የትምህርት ቤት ደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በነጻ ሰፍቶ በመስጠት ትልቅ የሰብዓዊነት አርዓያነቱን አሳይቷል። ወጣቱ ​በቅርቡ አሚኮ ከአልማ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የብቁ ወጣት የሥራ ፈጠራ ውድድር ላይ በልብስ ስፌት ዘርፍ ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ተክቶ በመሥራት የተሻለ ጥንካሬ ያለው ምርት በማቅረብ አሸናፊ መኾንም ችሏል። ወጣት አገኘሁ አሸናፊ ኾኖ ሲወጣ በበላይነት ያሸነፈው ተወዳዳሪዎቹን ብቻ አልነበረም ከፊት ለፊቱ ተደቅነው የነበሩትን የሕይወት መሰናክሎች፣ የሰዎችን አሉታዊ አመለካከት እና የጎዳናውን አስቸጋሪ ሕይወት ጭምር ነው እንጂ። ​ዛሬ ላይ በሠራው ሥራ አሸናፊ ኾኖ በመድረክ ላይ ሲቆም የስኬቱ ምስጢር እጁ ላይ ያለው ሀብት ሳይኾን በውስጡ የነበረው የማያወላውል ዕምነት እና ጠንካራ ሥነ ልቦና መኾኑን አስመስክሯል። ​አገኘሁ ዛሬም ሕልሙ አልቆመም፤ ሥራውን የበለጠ በማስፋት ለብዙዎች ሥራ መፍጠር እና የሕይወት ታሪኩን ለሌሎች አስተማሪ በሚኾን መልኩ በፊልም ሠርቶ ማቅረብ ይፈልጋል። ​ዕውነትም ተስፋ አለመቁረጥ አሸናፊ ያደርጋል። ​ #አልማ #አሚኮ #አልማ 08_12_2018_ዓ.ም በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052 ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/@aamharadevelopment ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK ቲክቶክ:tiktok.com/@amhara.devt.assoc ዌብሳይት: www.ada.org.et ሺህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺህ! ‎

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ከጎዳና ሕይዎት እስከ አልማ የብቁ ወጣት የሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊነት_   የአካል ጉዳተኛው ወጣት የሕይዎት ጉዞ

  • አማራ ልማት ማህበር ደሴ ኮምቦልቻ ልማት ጽ/ቤት እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ ልማት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ። --------///////------- የአማራ ልማት ማህበር ደሴ ኮምቦልቻ ልማት ጽ/ት ቤት እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትምህርት፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። ‎የመግባቢያ ሰነዱ ዓላማ የሁለቱን ተቋማት የሰው ኃይል፣ ዕውቀት፣ ሙያዊ ልምድና የምርምር አቅም በማቀናጀት ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠቅሙ የትምህርት፣ የምርምርና የልማት ሥራዎችን በጋራ ማከናወን፣ እንዲሁም የማህበረሰቡን ችግሮች በዕውቀትና በምርምር ለመፍታት የጋራ ሥራን ማጠናከር ነው። ‎ በስምምነቱ ላይ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አወል ሰይድ እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው ከአልማ ጋር ለረጅም ዓመታት በመተባበር ሲሠራ ቆይቷል። አሁን የተፈረመው ሰነድ ደግሞ ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያደርሳል። በጥናትና ምርምር በመታገዝ ለህብረተሰቡ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ሥራ በማቀናጀት ለመከወን መስማማታቸውን አስረድተዋል። ‎አልማ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኝና ረጅም የሥራ ታሪክ ያለው ተቋም በመሆኑ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮው መሠረት እንደ አልማ ያሉ በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራቱ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ገልጸዋል። ‎ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ የመግባቢያ ሰነዱን መፈራረም ብቻ በቂ እንዳልሆነ ጠቁመው፤ ስምምነቱ ከፊርማ በኋላ ወደ ተጨባጭ ተግባር ወርዶ በማህበረሰቡ ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ዩኒቨርሲቲው በየዘርፉ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና አጋርነት ትብብር ጽሕፈት ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አስረሴ ሞላ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸው ተግባራት መማር ማስተማር፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መሆናቸውን ጠቁመዋል። የአልማ ድርሻ ደግሞ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አስረሴ፣ ሥራዎቹን በማቀናጀት ለህብረተሰቡ በተደራጀ መንገድ አገልግሎት ለመስጠት ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ደሴ ኮምቦልቻ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ አድማሴ እንደገለጹት፣ አልማ በትምህርት፣ በጤናና በሥራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ሲሆን ሥራዎቹን ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በማያያዝ የህብረተሰቡን ችግር በዘላቂነትና በተቀናጀ መልኩ ለመቅረፍ ያለመ ነው። የመግባቢያ ሰነዱ ይህንን አላማ ለማሳካት የሚያስችል መሠረት እንደሚጥል አመልክተዋል። እስከ አሁንም ሁለቱም ተቋማት ለህብረተሰቡ ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል። ዛሬ የተፈረመው ስምምነት ወደ ተግባር ሲተረጎም ህብረተሰቡ የበለጠ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት እንደሚቻል የተናገሩት የአልማ ደሴ ኮምቦልቻ ልማት ጽሕፈት ቤት ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የሀገር ሽማግሌ አቶ ጫኔ መንገሻ ናቸው። ‎የመግባቢያ ሰነዱን ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አወል ሰዒድ እና የአልማ ደሴ-ኮምቦልቻ ልማት ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ አድማሴ የተፈራረሙ ሲሆን ተቋማቱ በቀጣይ የጋራ ዕቅዶችን በማውጣትና በተግባር በማዋል የትብብር ሥራውን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተገልጿል።መረጃው የወሎ ዩኒቨርስቲና የደሴ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡ #አልማ #ወሎዩኒቨርስቲ #አልማ _06_12_2018_ዓ.ም በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052 ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/@aamharadevelopment ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK ቲክቶክ:tiktok.com/@amhara.devt.assoc ዌብሳይት: www.ada.org.et ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!

  • አማራ ልማት ማህበር ደሴ ኮምቦልቻ ልማት ጽ/ቤት እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ ልማት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

  • አማራ ልማት ማህበር በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከወላጆቻቸው ለተጠፋፉና ለተነጣጠሉ ህፃናቶች ድጋፍ አደረገ። -----------///////--------- አማራ ልማት ማህበር የጎንደርና አካባቢው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳና ከተማ በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከወላጆቻቸው ለተጠፋፉና ለተነጣጠሉ ህፃናቶች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። የጎንደርና አካባቢው አልማ ልማት ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዘውዴ አማራ ልማት ማህበር አልማ በመደበኛው በርካታ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀው ከመደበኛ ስራዎቹ ባሻገር ከዩኒሴፍ ጋር በመቀናጀት እንደ ዞን በደባርቅ እና በዳባት ወረዳዎች በ20 ቀበሌዎች በህፃናት ጥበቃ ላይ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም መስፈርቱን መሰረት ተደርጎ የተለዩና ድጋፍ የሚሹ 524 የሚሆኑ ህፃናትን የተለያየ ድጋፍ መደረግ መቻሉን ገልፀዋል። እየተሰራ ባለው ስራ ህፃናትን ወደ ትምህርት ገበታቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው የቆዩትን ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። አልማ ከአጋር አካላትና ተቋማት ጋር በመተባበር በርካታ ተግባራቶችን እያከናወነ መሆኑን ያመላከቱት ዳይሬክተሩ የሚገኝን ሃብት በአግባቡ በመጠቀምና ለሚፈለገው አላማ በማዋል ማህበረሰቡን ማገልገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የደባርቅ ወረዳና ከተማ አልማ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አበረ መንደር አጠቃላይ በወረዳና በከተማ አስተዳደሩ አልማ ዩኒሴፍ ከዚህ በፊት በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት መማር ላልቻሉ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ለ262 ህፃናት መማር እንዲችሉና የተሟላ የቤተሰብ እንክብካቤ ለመፍጠር 3 ሚሊዮን 26 ሺህ 886 ብር በሆነ ወጭ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልፀው በዛሬው ቀንም በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከወላጆቻቸው የተጠፋፉና የተነጣጠሉ 56 ህፃናቶችን በመለየት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል። በዛሬው ድጋፍ ከአልማ ዩኒሴፍ በተገኘ 865 ሺህ ብር ወጭ በወረዳ እና በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ በ10 ቀበሌዎች ለተለዩ ህፃናት ድጋፍ አድርገናል ያሉት ሃላፊው አልማ ከዚህ በተጨማሪ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በኑሮ ዘይቤ ማሻሻያ እንዲሁም ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። የአልማ ዩኒሴፍ ሶሻል ወርከር የሆኑት ወይዘሪት ሜሮን ታረቀኝ አልማ ዩኒሴፍ በኢኮኖሚ እጥረት መማር ያልቻሉ ፣ በተለያየ ምክንያ ወላጃቸውን ያጡና የተነጣጠሉ ህፃናትን ቤት ለቤት ተከታትሎ ጥናት በማድረግና የመለየት ስራ በመሰራት እንዲሁም ቅድሚያ መሰጠት ያለባቸውን ቅድሚያ በመስጠት ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም በተለያየ ምክንያት ለተበታተኑ፣ ለተጠፋፉ ህፃናት እንደ ብርድ ልብስ፣ ፍርናሽ ከነ ትራቱ፣ ሳሙና፣ የመማሪያ ደብተር፣ እስክብሪቶ፣ እርሳስ፣ ፖርሳ እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንደተደረጉ ገልፀዋል። የደባርቅ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበባው አዛናው፣ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ማሩ አዲስ፣ የደባርቅ ወረዳ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ስመኝ እና ሌሎች አጋር አካላት በድጋፉ ተገኝተዋል።መረጃው የደባርቅ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡ #አልማ #UNICEF #አልማ _05_12_2018_ዓ.ም በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052 ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/@aamharadevelopment ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK ቲክቶክ:tiktok.com/@amhara.devt.assoc ዌብሳይት: www.ada.org.et ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!

  • አማራ ልማት ማህበር በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከወላጆቻቸው ለተጠፋፉና ለተነጣጠሉ ህፃናቶች ድጋፍ አደረገ።

  • የማህበሩን 2019 በጀት ዓመት  እቅድን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን ማጠናቀቅ ይገባል ፡፡አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ------------////////--------- የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ከሐምሌ 28 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሁለት ቀናት በዋናው መሥሪያ ቤት በተካሄደው የምክክር መድረክ፣ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን በስፋት በመገምገም የአዲሱን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ  አስተዋውቋል።   በውይይቱ ላይ የዋና መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ 11 የዞን አልማ  ልማት ጽህፈት ቤቶች የተወጣጡ የማኔጅመንት አባላት እና የተሸለ ተሞክሮ ያላቸው የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።   በመድረኩ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ያቀረቡት ስትራቴጅክና ኢኖቬሽን ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበረ መኩሪያ ማህበሩ የሚጠቅመው ትልቅ እቅድ በማቀድ የሚቻለውን ሁሉ ጥረት በማድረግ የማህበረሰቡን ሰፊ የማህበራዊ ልማት ችግር መፍታት እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡ በ2019 በጀት አመት ከአባላት ሃብት የማሰባሰብ እቅድ በገንዘብ፣ በአይነት፣ ሙያና ጉልበት ከ4ነጥብ 3ቢሊዩን ብር የልማት ሀብት መታቀዱን ገልጸው ይህም እቅድ  እጅግ የተለጠጠ ሰፊ እርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን ያሳያል ብለዋል ፡፡ ከዳያስፖራ ከ34ሚሊዩን ዶላር በላይ  እንዲሁም ከአጋር አካላት በዶላር 55 ሚሊዮን ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸዋል ፡፡   ከአባላት በተሰበሰበ ሃብት ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት   483 መማሪ ክፍል፣ 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት 1,247 መማሪያ ክፍል እንዲሁም 2ኛ ደረጃ 321 መማሪያ ክፍል በድምሩ 2,051 መማሪያ ክፍል ለመገንባት ታቅዷል ያሉት ም/ዋና ስራ አስፈጻሚው የጤና ተቋማት የግምባታ እቅድን በተመለከተ መሰረታዊ ጤና ኬላ 27 ብሎክ፣ አጠቃላይ ጤና ጣቢያ 11 ብሎክ  በድምሩ 38 የጤና ተቋማት በበጀት አመቱ እንደሚገነቡ ተናግረዋል ፡፡ የቴክኒክ ኮሌጅ ወርክሾፕ ግንባታን በተመለከተ 8 ወርክሾፖችንና 2 ሸዶችን የመገንባት እቅድ የተያዘ መሆኑን ገልጸው ይህን የተለጠጠ እቅድ እውን ለማድረግ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን ከወዲሁ መጀመር፣ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ በማግባባት  ተሳታፊ ማድረግ፣ የማህበሩን አባላት፣ደጋፊዎች ፣ አጋር አካላትን እና  ዲያስፖራውን መሰረት ያደረገ  ፕሮጀክትን ለመተግበር  የህዝብ ንቅናቄ መፍጠር ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡ የ2019 በጀት አመት እቅድ ላይ የዋና መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ 11 የዞን አልማ  ልማት ጽህፈት ቤቶች የተወጣጡ የማኔጅመንት አባላት እና  ተሞክሮ ለማቅረብ የተገኙ የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ጋር በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል ፡፡ የ2019 በጀት አመት እቅድን  አስመልክቶ ማጠቃለያ  የሰጡት የአልማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ የ2019 በጀት ዓመት  እቅድ በላቀ ደረጃ ለመፈጸም ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን ማጠናቀቅ ፣ ባለፈው ዓመት የታዩ ክፍተቶችን ማረም የዚህ ዓመት ዋና ትኩረት ይሆናል ብለዋል ። የመደጋገፍ ባህልን በማዳበር  ከዋናው መ/ቤት  እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ያለው የክትትል እና የድጋፍ ሥርዓት (Teamwork) መጠናከር ፣በስራ ላይ የሚታዩ የአመለካከት ክፍተቶችን ለመቅረፍ የማያቋርጥ ግንዛቤ ፈጠራ ስራ ፣አዲስ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ከሞላ ጎደል ጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ቢሆኑም ተጨማሪ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚገባ ገልጸዋል ። ወጪ ቆጣቢ፣ ውጤታማ እና ተቋማዊ ግቦችን ማሳካት የሚችል የአሠራር ማዕቀፍ መዘርጋት እንደሚገባም አመላክተዋል ፡፡ የለውጥ መሪ (Transformational Leadership) መሆን፣ ለውጥን በብቃት መምራት እና የተቋሙን ተቋማዊ አቅም ማሳደግ ፣የሰዎችን አመለካከት፣ አሰራር እና ቴክኖሎጂ አቀናጅቶ መሄድ  የአመራሩ  ዋና ትኩረት መሆን እንዳለበት  አሳስበዋል ። ማህበሩ በ2019 በጀት ዓመት የዲጂታል ሽግግርን ማዕከል ያደረገ አሰራርን መተግበር፣ የአፈጻጸም ጥራትን ማረጋገጥ፣ የተቋሙን ብራንድ መገንባት እና አዳዲስ የገቢ ማመንጫ አማራጮችን በመጠቀም የፋይናንስ አቅምን በዘላቂነት ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተመላክቷል ። በመድረኩ ማጠቃለያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የዞን አልማ ልማት ልማት ጽህፈት ቤቶች  በተቋም ደረጃ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤቶች  ፣ከ1ኛ-3ኛ ለወጡ ለወረዳ አልማ  ልማት ጽ/ቤቶች ማበረታቻ ሽልማት እና የምስክር ወረቀቶች ተበርክቷዋል። በተጨማሪም የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤቶች ውስጥ በሴት ሥራ አስኪያጆች 1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ፣አዲስ አባል በማፍራት ግንባር ቀደም ለሆኑ ሰራተኞች ከ1ኛ-5ኛ ለወጡ የማበረታቻ እና የምስክር ወረቀቶች  ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። #አልማ #7ኛው_የአልማ_ሳምንት_2018ዓ.ም #አልማ _29_11_2018_ዓ.ም በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052 ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/@aamharadevelopment ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK ቲክቶክ:tiktok.com/@amhara.devt.assoc ዌብሳይት: www.ada.org.et ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!

  • የማህበሩን 2019 በጀት ዓመት  እቅድን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን ማጠናቀቅ ይገባል ፡፡አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи