tgindex
AradaFm95.1-Sport

AradaFm95.1-Sport

Статистика
@AradaFm_Sportанглийский

This is AradaFm 95.1-Sport Official Telegram Channel

Последний пост
12:59
Последнее чтение
11:20
Постов за неделю
25
Всего постов
40
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
405
−1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
53
31 постов
Вовлечённость
13,1%
к подписчикам
Постов в день
3,6
всего 40
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
45
1/48двое суток
51
1/72трое суток
55

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የቀድሞ የባርሴሎና የመሃል ሜዳ ቴክኒሺያን ሰርጂዮ ቡስኬት በተለየ ሚና ወደ ባርሴሎና ተመልሷል ! ሰርጂዮ ቡስኬት የባርሴሎና ሁለተኛ ቡድን ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል። ባርሴሎና ከለቀቀ በኋላ በኢንተር ሚያሚ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር መጫወት ችሎ የነበረ ሲሆን በአሰልጣኝነት ሚና ግን ይሄ የመጀመሪያውን ሀላፊነቱ ነው AradaFm_Sport

  • ኖቫክ ጆኮቪች በ2028 ኦሊምፒክ መወዳደር እንደሚፈልግ ገለፀ ነሐሴ 10፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) የ24 ጊዜ የግራንድ ስላም አሸናፊው ኖቫክ ጆኮቪች ከሁለት ዓመታት በኋላ በሚደረገው ኦሊምፒክ የመወዳደር ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። የፊታችን ሀሙስ የሚወጣውን እና "Wolf in Winter" የተሰኘውን የሕይወት ታሪኩን የሚያትት ዶኩመንተሪ አስመልክቶ ለስፔኑ ስፖርት በሰጠው ቃለ ምልልስ ይህን ያለው። በሎስ አንጀለስ 2028 ኦሊምፒክ መወዳደር ህልሜ እና ግቤ ነው ከፍተኛ ፍላጎትም አለኝ ሲል ተናግሯል። በኦሊምፒኩ የመሳተፉ ነገር በሰውነቱ ሁኔታ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መሰረት ያደረገ መሆኑን በማንሳት በጥሩ ብቃት ለመድረስ ጠንክሮ እንደሚሰራ ገልጿል። ጆኮቪች አክሎም ከሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ ማግስት ራሱን ከፕሮፌሽናል የቴኒስ ተወዳዳሪነት እንደሚያገል ተናግሯል። AradaFm_Sport

  • ካሜሮን ማላዊን አሸንፋ የመጀመሪያዋን የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫን አሸንፈች! ካሜሮን በማላዊ ላይ ያልተጠበቀ የፍፃሜ ጨዋታ ድልን ለማስመዝገብ 45 ደቂቃዎች ብቻ ፈጅቶባታል። ቀድመው በማሪ ንጋህ ማንጋ ሁለት እና በፒኤስጂዋ ተጫዋች ናኦሚ ኤቶ አንድ ግቦች 3ለ0 በመምራት ወደ እረፍት አምርተው ጨዋታው ከእረፍት በፊት እንዲወሰን አድርገውታል።ከእረፍት መልስም ይህንኑ ውጤት በማስጠበቅ ወጥተዋል። ካሜሮን በ2004፣ 2014 እና 2016 ሶስት ግዜ የፍፃሜ ተፋላሚ ነበረች፣ ኢንዶሚቴብል ሊዮንሴሶች በመጨረሻ ግን ማላዊን 3ለ0 በማሸነፍ የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫን ዘውድ ደፍተዋል AradaFm_Sport

  • ሊቨርፑል ብራድሌይ ባርኮላን ለማስፈረም በድጋሚ ጥረቱን ቀጥሏል! ነሐሴ 10፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ባርኮላ የ23 አመቱ ተስፈኛ ተጫዋች ሚካ ጎድትስ፣ ማግሃነስ አክሊዮቼ እና ፈርናን ቶሬስ ወደ ፒኤስጂ መጥተዋል። የእነሱ መፈረም ባርኮላ በፔዤ ቤት ያለው የወደፊት ቄይታ ጥያቄ ውስጥ ወድቋል። ይህን አጋጣሚ ሊቨርፑል ለመጠቀም ከወኪሎቹ ጋር ውይይት እያደረገ ነው። ፒኤስጂ አሁንም ከባርኮላ ዝውውር 150 ሚሊዮን ዩሮ ይፈልጋል። አርሰናሎችም ቢሆን የተጫዋቹ ፈላጊ ናቸው ፈረንሳዊውን ተጫዋች ለማስፈረም ጥረት እይልደረጉ እንደነበር መረጃዎች ወጥተው ነበር። አሁን ግን የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጥያቄውን ገፍቶበታል። (ምንጭ፡ ዘ ስታንዳርድ/ኢኤስፒኤን) AradaFm_Sport

  • ክርስትያኖ ሮናልዶ ከወራት በኋላ ጫማውን ሊሰቅል እንደሚችል ተናገረ ነሐሴ 10፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) በእግር ኳስ ከታዩ ታላላቅ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ክርስትያኖ ሮናልዶ ጫማውን ለመስቀል መቃረቡን ተናግሯል። ከሰሞኑ ሰርጉን ያደረገው ሮናልዶ የዘንድሮው የውድድር ዘመን መጨረሻ ላይ ጫማውን ሊሰቅል እንደሚችል ገልጿል። የራሴን የሆነ አሻራ በእግር ኳስ ላይ አሳርፌ ማለፍ እፈልጋለሁ ያለው ፖርቹጋላዊው የወደፊት ሕይወቴን በምን መልኩ ማሳለፍ እንዳለብኝ አቅጃለሁ ብሏል። በአንድ ነገር ብቻ ማሳለፍ በቂ አይደለም ያለው ክርሰትያኖ ሮናልዶ 25 ዓመታት ከቆየሁበት እግር ኳስ መገለል ከባድ ነው ሲልም ተናግሯል። የ41 ዓመቱ ኮከብ በግብ ካስቀመጠው 1000 ግቦች ለመድረስ 24 ግቦች ብቻ ይቀሩታል። AradaFm_Sport

  • ዋልያዎቹ ከሴኔጋል ጋር በባህርዳር ስቴድዮም ይጫወታሉ! ነሐሴ 10፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ካፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሜዳው ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም እንዲያከናውን ጊዜያዊ ፈቃድ መሰጠቱን ተከትሎ ብሄራዊ ቡድናችን ጨዋታዎችን በሜዳው እንደሚያደርግ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል ። በዚህም መሰረት በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 10 ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ስታዲየም ማክሰኞ መስከረም 19/2019 ከቀኑ 10፡00 ላይ የሚያከናውን መሆኑን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል። AradaFm_Sport

  • አርሰናል ለ18ኛ ጊዜ የኮምዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ ነሐሴ 10፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) በ2026 የኮምዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ጨዋታ የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል ማንችስተር ሲቲን 3 ለ 0 አሸንፏል። ሪካርዶ ካላፍዮሪ (01') እና ካይ ሀቨርዝ (28') በመጀመሪያው አጋማሽ ማርቲን ኦዲጋርድ (48') ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ለ25ኛ ጊዜ በኮምዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ የተጫወተው አርሰናል 18ኛ ድሉ ሆኖም ተመዝግቧል። AradaFm_Sport

  • без подписи

  • መድፈኞቹ የመጀመሪያውን አጋማሽ 2 ለ 0 እየመሩ አጠናቀዋል ነሐሴ 10፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) በኮምዩኒቲ ሺልድ ጨዋታ አርሰናል ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 0 እየመራ አጋማሹን አጠናቋል። ጨዋታው በጀመረ 22ኛው ሰከንድ ላይ ጣልያናዊው ሪካርዶ ካላፍዮሪ የአርሰናልን ቀዳሚ ግብ አስቆጥሯል። ግቡ ከ58 ዓመታት በኋላ በኮምዩኒቲ ሺልድ ጨዋታ ከአንደኛው ደቂቃ በፊት የተቆጠረ ግብ ሆኗል። በ28ኛው ደቂቃ ደግሞ ጀርመናዊው ካይ ሀቨርዝ ከክሪስቶስ ዞሊስ የደረሰውን ኳስ በግንባር በመግጨት ሁለተኛውን ግብ አክሏል። የሊጉ ሻምፒዮን ውጤቱን አስጠብቆ ጨዋታውን በድል ካጠናቀቀ ለ18ኛ ጊዜ የኮምዩኒቲ ሺልድ አሸናፊ ይሆናል። AradaFm_Sport

  • አልጄርያ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች! ነሐሴ 9፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ አልጄርያ ሞሮኮን በመለያ ምቶች አሸንፋ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች በመደበኛ ጨዋታ 1ለ1 የተለያዩት ሁለቱ ቡድኖች አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች አልጄርያ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን ሻምፒዮን ለመሆን ማላዊ ከ ካሜሮን ይጫወታሉ AradaFm_Sport

  • ባየርኖች ለአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጁ የሚያደርጋቸውን የቴሌኮም ዋንጫ አሸንፈዋል! ነሐሴ 9፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) አርቢ ያልብዚንግን 3ለ1 ሲያሸንፍ ሉዊስ ዲያዝ በድጋሚ ጎል አስቆጥሯል፣ ይህም በቅድመ-ውድድር ዘመን ሁለት ጨዋታዎች 2 ጎሎችን አስቆጥሯል። ኢስማኤል ሳይባሪ የባየርን የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጎ ለሙሲያላ ጎል አመቻችቶ አቀብሏል ናትናኤል ብራውን ለባየርን የመጀመሪያውን ጎል አስቆጠረ የኮምፓኒ ቡድን የቴሌኮም ዋንጫን አሸንፎ ለሌላ የቡንደስሊጋ ዋንጫ ለመወዳደር ዝግጁ ነው። AradaFm_Sport

  • በወዳጅነት ጨዋታ ሩቡን አሞሪም ኤሲ ሚላን ይዘው የቀድሞ ቡድናቸውን 4ለ2 አሸንፈዋል ! ነሐሴ 9፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም ) ኤሲ ሚላንን ዩናይትድን 4ለ2 ሲያሸንፍ ሚላንን አሸናፊ ያደረጉ አራቱን ግቦች ቹኩዌዜ ፤ ሲሴ ፣ ጎንሳሎ ራሞስ እና ሉፍተስ ቼክ አስቆጥረዋል። የማንችስተር ዩናይትድን ሁለት ጎሎች ሀሪ ማጓየር እና ዶርጉ አግብተዋል። አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ኤሲ ሚላንን እየመሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን ገጥመው አሸንፈዋል። ዩናይትዶች የዛሬው የወዳጅነት ጨዋታ ባጠቃላይ ስድስተኛው ሲሆን ሁለት ድል ፣ ሁለት ሽንፈትና ሁለት አቻ ውጤቶችን አስመዝግበዋል። AradaFm_Sport

  • ቼልሲ በአቋም መለኪያ ጨዋታ ሪያል ሶሴዳድን አሸነፈ ነሐሴ 9፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) በአቋም መለኪያ ጨዋታ ሪያል ሶሴዳድን ያስተናገደው ቼልሲ 3 ለ 1 አሸንፏል። በጨዋታው አዲሱ ፈራሚ ሞርጋን ሮጀርስ አንድ ግብ ሲያስቆጥር ጆአኦ ፔድሮ ሁለቱን ቀሪ ግቦች አስቆጥሯል። የሪያል ሶሴዳድን ብቸኛ ግብ ጆን አራምቡሩ ከመረብ አሳርፏል። የዣቢ አሎንሶው ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹን ያጠናቀቀ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ፉልሀምን ይገጥማል። ሀብታሙ ምትኩ @Arada_Fm

  • የባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም ጊዜያዊ ፈቃድ አገኘ ነሐሴ 9፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) የባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ለማስተናገድ የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ። ለዓመታት በእድሳት ላይ የቆየው ስታድየሙ ከሰሞኑ በካፍ ገምጋሚ አካል ሲታይ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በውጤቱም ጊዜያዊ ፈቃድ ማግኘቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። ካፍ በስታዲየሙ የተመዘገቡ መሻሻሎችን በማድነቅ በላከው ደብዳቤ አሁንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ያልተጠናቀቁ ጉዳዮች እንዳሉ መግለፁም ተጠቅሷል። በዚህም የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ያሉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመስከረም ወር የሚያደርገውን ጨዋታ በስታድየሙ ማድረግ ይችላል። የባህርዳር ስታድየም በዕድሳት ምክንያት ላለፉት አምስት አመታት ምንም አይነት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን አለማስተናገዱ ይታወሳል። ሀብታሙ ምትኩ @Arada_Fm

  • የውድድር ዓመቱ ምርጥ ማልያ የየትኛው ክለብ ነው ? ነሐሴ 9፣ 2018 (አዲስ አበባ) የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊጀምር 6 ቀናቶች ብቻ ቀርተዋል። ዘ አትሌቲክ የፕሪሚየር ሊጉ 20 ክለቦች የመጀመሪያ ማልያን የውበት ደረጃቸውን የግሉን ምልከታ በማስቀመጥ አስፍሯል። በአንደኛነት የአዲስ አዳጊውን ኮቨንትሪ ሲቲን ማልያ ሲያስቀምጥ የሊቨርፑልን ማልያ የሁለተኛ ደረጃ ሰጥቶታል። በሶስተኝነት የማንችስተር ዩናይትድ ፤ በአራተኝነት የሰንደርላንድ ፤ በአምስተኝነት የኢፕስዊች ታወንን ፤ በስድስተኝነት የብራይተንን አስቀምጧል። የአርሰናል 7ኛ የቶተንሀም ሆትስፐርስ 8ኛ የአስቶን ቪላ 12ኛ ደረጃን ሲሰጣቸው የማንችስተር ሲቲን እና የቼልሲን ደግሞ 18ኛ እና 19ኛ ላይ ተቀምጠዋል። ሀብታሙ ምትኩ @Arada_Fm

  • 14 የእንግሊዝ ክለቦች የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ዛሬ ያደርጋሉ ነሐሴ 9፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና የሌሎችም ሊጎች ክለቦች የመጨረሻ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎቻቸውን ዛሬ ያደርጋሉ። በማይክል ካሪክ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ በቀድሞ አሰልጣኙ ሩበን አምሪም የሚመራው ኤሲ ሚላን ጋር ይጫወታል። በፖላንድ ሮክሎው የሚደረገው ጨዋታው ከቀን 11:45 ጀምሮ ይደረጋል። አስቀድሞ ከቀን 09:00 ጀምሮ ደግሞ የዣቢ አሎንሶው ቼልሲ ሪያል ሶሴዳድን ስታምፎርድ ብሪጅ ላይ ያስተናግዳል። ኢፕስዊች ታወን ከዩንየን በርሊን ፤ በርንማውዝ ከሜይንዝ 05 እንዲሁም አስቶንቪላ ከቦሩስያ ሞንቸግላድባክ ከ10:30 ጀምሮ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው። ብሬንትፎርድ ከፍራንክፈርት ፣ ብራይተን ከቦሎኛ ፣ ኤቨርተን ከሊል ፣ ሀል ሲቲ ከኒስ ፣ ሊድስ ዩናይትድ ከኦግስበርግ ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከባየር ሊቨርኩሰን ፣ ሰንደርላንድ ከሬንስ እንዲሁም ቶተንሀም ሆትስፐርስ ከሆፈንየም ከ11:00 ጀምሮ ይጫወታሉ። 12:00 ላይ ፉልሀም ስቱትጋርትን ሲገጥም ቦሩስያ ዶርትሙንድ ከሮማ 12:30 እንዲሁም ኢንተር ሚላን ከሪያል ቤቲስ ደግሞ ምሽት 02:30 ላይ ይገናኛሉ። ሀብታሙ ምትኩ @Arada_Fm

  • የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ግብ አስቆጣሪው ፒኤስጂን ተቀላቅሏል ነሐሴ 9፣ 2018(አራዳ ኤፍ ኤም) ስፔናዊው አጥቂ ፌራን ቶሬዝ በይፋ የፒኤስጂ ተጫዋች መሆኑ ተረጋግጧል። ያለፉትን አራት አመታት በባርሴሎና ያሳለፈው ተጫዋቹ በፓሪሱ ክለብ ለአምስት ዓመታት የሚያቆየውን ውልም በይፋ ፈርሟል። ስፔንን የዓለም አሸናፊ ያደረገችውን ብቸኛ ግብ ላስቆጠረው ተጫዋች ለዝውውሩ ፒኤስጂ 48.5 ሚልዮን ዩሮ ከፍሏል። የ26 ዓመቱ ተጫዋች በባርሴሎና ቆይታ የነበረው ቶሬዝ 3 የላሊጋ ጨምሮ 7 ታላላቅ ዋንጫዎችን አሸንፏል። ሀብታሙ ምትኩ @Arada_Fm

  • ስታምፎርድ ብሪጅ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ሊደረግበት ነው ነሐሴ 9፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) የምዕራብ ለንደኑ ክለቡ ቼልሲ በቀጣዩ የውድድር ዘመን የቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ባይሆንም ስታድየሙ ግን የውድድሩን ጨዋታዎች ሊያስተናግድ መሆኑ ተሰምቷል። ይህ ይሆናል የተባለው የዩክሬኑ ክለብ ሻካታር ዶኔስክ የቻምፒየንስ ሊግ የሜዳ ጨዋታዎቹን በስታምፎርድ ብሪጅ ለመጫወት መጠየቁን ተከትሎ ነው። ክራቨን ኮቴጅን እና ጂቴክ ኮሙኒቲ ስታድየሞችን በአማራጭነት ቢመለከቱም ተመልካች ከመያዝ አቅማቸው አንፃር ስታምፎርድ ብሪጅን ተመራጭ አድርገዋል ተብሏል። በሩስያ ዩክሬይን ጦርነት ምክንያት ሀገሩ ላይ ጨዋታዎችን ማድረግ ያልቻለው ለንደን ላይ ለመጫወት ያቀደው ሻክታር ከ32 ሺህ በላይ ዩክሬናውያንን በማሰብ መሆኑ ተገልጿል። ሀብታሙ ምትኩ @Arada_Fm

  • ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርድዮቪች ሚቾን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በይፋ ሾመ ነሐሴ 8፣ 2018(አራዳ ኤፍ ኤም) የ31 ጊዜ የሊግ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ ስኬታማ አሰልጣኙን ሰርድዮቪች ሚቾን በአምስት ዓመታት ውል ሹሟል። በሸራተን አዲስ ሆቴል በተደረገው መርሐግብር ላይ ከሰርብያዊው አሰልጣኝ በተጨማሪም ኢንስትራክተር ስዩም ከበደንም የቴክኒክ ዳይሬክተር በማድረግ ሹመት ሰጥቷል። በመድረኩ ላይ ሁለቱም በቀጣይ ሊሰሩ ያሰቧቸውን ዕቅዶች ያቀረቡ ሲሆን የክለቡን አካዳሚ በትክክለኛው መንገድ ከማዋቀር እስከ አፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ሻምፒዮንነት የሚደርስ ነው። ከ16 ዓመታት በኋላ ወደ ፈረሰኞቹ ቤት የተመለሱት አሰልጣኝ ሚቾ የአሰልጣኞች ስታፍ አባላታቸውንም በገለፃቸው ወቅት ያቀረቡ ሲሆን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ እና የአካል ብቃት እና የፐርፎርማንስ አሰልጣኝ አማካሪዎች መካተታቸው ተገልጿል። ክለቡ አዳዲስ ያስፈረማቸው ተጫዋቾችም በመርሐግብሩ ላይ የተዋወቁ ሲሆን በመጪው ማክሰኞ በይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ላይ የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅቱን ይጀምራል። በመስከረም ወር የመጀመሪያ ሳምንታት ላይም ወደ አንድ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር በመጓዝ እስከ ሶስት የሚደርሱ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች እንደሚያደርግ ተገልጿል። በተጨማሪም በመድረኩ ላይ ለ17 ዓመት በታች ቡድኑ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል። ሐብታሙ ምትኩ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical   Telegram:-https://t.me/Arada_Fm   Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm   @Arada_Fm

  • ዛሬ ሲቲ እስከ ምሽት የፈርናዴዝን የዝውውር ሂደት ማሳወቅ አለበት ቼልሲ ዛሬ ከምሽቱ 5 ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የዝውውር ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በሚል የኢንዞ ፈርናንዴዝ የሰዐት ገደብ አስቀምጧል ማንችስተር ሲቲዎች ለቀናት እና ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከኢንዞ ወኪሎች ጋር መደበኛ ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ቼልሲ የፈርናንዴዝ ትክክለኛ የውውር ዋጋ 120 ሚሊዮን ፓውንድ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። ሱቲዝኖቹ ይህንን ዋጋ ከፍለው እስከምሽት ዝውውሩን ይጨርሱት ይሆን? አብረን እናያለን AradaFm_Sport