ጠቃሚ መጻሕፍት - Beneficial Books
Статистикаለመጭው ትውልድ እንሠራለን ! እጅግ ጠቃሚ መጻሕፍትን እንጠቁማለን! የመጻሕፍት ዳሰሳ እናደርጋለን፤ አዳዲስ ሐሳቦችን እናቀርባለን፤ መጻሕፍቶችን በሶፍት ኮፒ እናቀርባለን! ከእናንተ ከቤተሰቦቻችን የሚጠበቀው ማንበብና አዳዲስ ሰዎችን Add ማድረግ ብቻ ነው።
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 13
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 17
- 1/48двое суток
- 19
- 1/72трое суток
- 21
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ዋካ መጻሕፍት ~ Waka Books ~~~~~~ የተለያዩ መጽሐፍትን ፣ የጥናት ወረቀቶችን ፣ የደራሲያን አጫጭር እና ረጃጅም ጽሁፎች በቀላሉ የሚያስቀምጡበት እና የሚያገኙበት ፤ በነጻነት የሚሸጡበት እና የሚገዙበት ዌብ ሳይት ነው። ዋካ ቡክስ መጽሐፍትን እና የድርሰት ሥራዎችን ሁሉ በቀላሉ የሚያገኙበት እና የሚጠቀሙበት ዘመኑን የመሰለ ግዙፍ ፕላት ፎርም ነው ። ዊብ ሳይቱን እየገባቸው Log in በማድረግ የምትፈልጉትን አገልግሎት ተጠቀሙ ። ~~ Hard copy መጸሐፍ የምትሸጡም ሆነ የምትገዙ እየገባችሁ እርስ በርሳችሁ በራሳችሁ አድራሻ መገበያየት ትችላላችሁ ። ሌላው የማይገኙ መጽሐፍትን መሸጥ የምትፈልጉ በዌብ ሳይቱ በኩል ተነጋግራችሁ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው Takos Coffee ውስጥ ማስቀመጥ እና መሸጥ ትችላላችሁ ።የዋካ ቡክስ መጽሐፍትን ከፈለጋችሁ እዚያው ታገኙታላችሁ። በተረፈ Wakabooks ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በapplication እየመጣ ነው። እየገባችሁ log in በማድረግ በነጻ ተጠቃሚ ይሁኑ።http://www.wakabooks.com
ሀገርን መውደድ በዘውግ ( በብሔር ) ተኮር ፌደራሊዝም ~~ ሀገር እንዴት ይወደዳል? ይህ ገለጻ (Presentation) ጊዜውን የዋጀ እጅግ ተገቢ እና ወሳኝ ሲሆን አቀራረቡም ሆነ ውይይቱ እጅግ የሞቀ ነው ። ይህ ወሳኝ ገለጻና የሞቀ ውይይት በተከታታይ የሚቀርብ ስለሆነ እንድትከታተሉት እየጠየቅን ዩቱቡንም #subscribe #shares በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። https://youtu.be/dHQtj8uF9Fg?si=maNcIU0ITIqHb-VC
❝ ተሰጥኦን ፍለጋ ❞ ስለ ተሰጥኦ ምንነት እና ለሥኬት ያለው አይተኬ ሚና ከበርካታ ንባቦቹ እና ከሕይወት ዘመን ተሞክሮዎቹ ቀምሮ ለትውልዱ ያቀርባል ። አቅራቢው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ዘነበ ወላ ነገ በቀን 3/12/ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ላይ በዐውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ ላይ በወመዘክር አዳራሽ በመገኘት ተሰጥኦ ያለውን ሁለንተናዊ ፋይዳ ለኢትዮጵያውያን ይናገራል ። በሰዓቱ በመገት ይከታተሉ ይወያዩ ።
ነገር ይቀይርልኛል” ብላ በምትተማመንበት በምናሴ ትነጠቃለች። ተአምር በሚያስብለው በጡት ወተት ምክንያት ለሕይወቷ ትርጉም ለመስጠት ትታትራለች። የጡት ወተቷን ምርምር በማድረግ ለትልቅ ዓለምአቀፍ በጎ ተፅዕኖ ታደርጋለች ተብላ የተቆጠረችው ሥዕለማርያም የዓለም አቀፍ መሳለቂያና ትችት ምንጭ ትኾንባታለች። ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው ድግግሞሽ ነው። ይህ ደግሞ በሳርተር የተገለጸውን “existence without essence”-ን ያሳያል። የህላዌነት መሠረታዊ ሐሳብ ነጻነት ነው፤ ግን ነጻነት ፍርሃትን ይወልዳል። ሄላም ለአሮን ፍቅሯን መናገር ትችላለች፤ ነገር ግን ዝምታን መርጣለች። የግራጫው መዝገቡ፣ የእንጀራ እናቱ የምታደርስበትን በደል እንደሚያውቀው ሁሉ ሄላምም ክብካብና ዘበናይ የሚያደርሱባትን አድሎ ታውቃለች፤ ግን ለረዥም ጊዜ ዝም ብላለች። ሄላም፣ ሙዚቃዋን ካጣች በኋላ ወደ ባንዱ ሄዳ መጋፈጥ ትችላለች፤ ነገር ግን አትሄድም … ይህ በሳርተርኛ bad faith ነው። የሄላም ምርጫ ዝምታ ኾነ እንጂ ደካማ ናት ማለት አይደለም። “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል ዝምታ ነው ያላት። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዝምታዋ፣ የለመደችውን ግፍ ከማታውቀው ዐዲስ ግፍ የመምረጥ ኹኔታ ነው። ዐዳዲስ ግፎችን ለመሸሽ በዝምታ አላዋቂነት ዛጎል ውስጥ የመደበቅ ብቃት ነው። የለመደችውን ግፍ የመከላከል አቅም ስላላት ባለመደችው ግፍ እንዳያጠፏት ሠግታ በውስጣዊ ንቃተ ሕሊና የዘየደችው ብልሃት ሊኾን ይችላል። ዝምታዋ የመቆየቷ ምሥጢር ነው። ደበበ ቀዝቃዛ ገለልተኛ ነኝ የሚለው ሰው ለመኖር ሲል ሳይታወቀው ስሜቱን የሚቆጣጠርበት መንገድን ለማስታወስ ነው። “የስንብት ቀለማት” ገጸባሕርይ የኾነው ዮሴፍም ብዙ ነገር ያውቃል፤ ግን ዝም ይላል … ፊያሜታ ቂል መስሏት ትዘባርቃለች … እሱ ግን “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል የዝምታ መልስ ይመልስላታል። እሷ ግን ዝምታው አይገባትም። የ“ቀዳዳ”ው ደበበ እና “የስንብት …” ዮሴፍ ቀዳዳውን አይሞሉትም፤ እያዩት ይኖራሉ። ዶነሮች ጥሩ ፈንድ ሲለቁ ፊያሜታ ፕሮጀክቱን ለአሳምነው ትሰጠውና ዮሴፍን “ምን ዶነሮች እኮ ጠፉ ትለዋለች” … ዝም ይላል፤ ይታዘባል። ቃል መሣሪያ ነበር፤ በዘመነ ደበበ፣ በዘመነ ዮሴፍ፣ በዘመነ ሄላም እና በዘመነ መዝገቡ ዱባለ ግን ቃል አደገኛ ኾኗል፤ ዝምታ ኹነኛ መጠጊያ ነው … ይህ ከደርግ በኋላ የተፈጠረ “traumatized literary silence” ማሳያ ነው። ስለኾነም ተራኪዎቹ (ደበበ፣ መዝገቡ፣ ዮሴፍ እና ሄላም) ለምን ዝም አሉ ሳይኾን "ዝምታን የሚያመነጭ ሥርዓት ምን ይኾን?" ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። ግለሰብ ዝም ሲል፤ ሕዝብ በጸጥታ ይዋጣል፤ የዚያኔ የተማከለው ኃይል አፍ ያወጣል። የአዳምን ዐዲሱን መጽሐፍ "በንባብ ይለቅ" ብለን መርቀናል። ቢኒያም አቡራ ሐምሌ 25 / 2018 ዓ.ም
ይገኛል። በሌላኛው የድኅረ-ቅኝ-ግዛት ኂስ (postcolonial criticism) መዝሙረ ሄላምን ስንመለከት መጀመሪያ ላይ “ፈረንጅ ሲያደንቀኝና ሲገረምብኝ የሰሙ የአገሬ ደነዞች በየተራ “ካላስ የኔ ጎሳ ናት” … እያሉ መሻማት ጀመሩ ትላለች - ሄላም። በኋላ ደግሞ በተነዛባት አጓጉል ወሬ … የሄላምን ጡት ንቀው፣ አንጓጥጠው፣ አባረዋት ሲያበቁ የፈረንጅ የዱቄት ወተትን ይመርጣሉ። ይህ በባሕላዊ ማንነትና በዘመናዊነት መካከል የሚዋልል ማኅበረሰብን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የድኅረ-ቅኝ-ግዛት አካል ነው። በሌሎቹ የአዳም ሥራዎች ውስጥ ድኅረ-ቅኝ-ግዛት አተያይ በቋንቋና በኪነ-ጥበብ ምርጫ ውስጥ እንዴት እንደሚንፀባረቅ ያሳያል። በመዝሙረ ሄላም ላይ ደግሞ ምዕራባዊው ዓለም ለአገር በቀል መፍትኼ-ሥራይ የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ መኾኑንና የኢኮኖሚ ብዝበዛው አሁንም በረቂቅ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል። እዚህ ላይ ሥዕለማርያም የተባለችዋን ገጸባሕርይ እና በውጭ ሀገራት የተነዙ ወሬዎችን ስንጨማምር ደግሞ የበለጠ ብዙ ለማለት ያስችላል። መዝሙረ ሄላም ላይ እጅግ ብዙ ማኅበረሰባዊ ኂስ እናገኛለን። ለአብነት ያህል አንድ ሁለቱን እንቃኝ። “መዝሙረ ሄላም” ላይ ማኅበረሰቡ በችላ-ባይነት አልያም በኾን ተብሎነት ልጆቹን ምን ያህል ተጠቂ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መልክ ተንጸባርቆበታል ማለት ይቻላል። ጋሽ ክብካብና ዘመናይ ኾን ብለው ቴዲና ሄላም ላይ የሚያደርሱትን፣ ተክለማርያም የወላጁን(የዘሪቱን) ችላ-ባይነት ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ማኅበረሰቡ ልጆችን “የነገ ተስፋዎች” ይላል፤ ነገር ግን ዛሬያቸው ላይ አይሠራም። ማኅበረሰብ የመማጸኛ ከተማዎችን ወደ ተጨማሪ ግፍ መሥሪያ ቦታዎች እንደሚቀይር በአዳም መጻሕፍት ላይ በብዛት እንመለከታለን። “ይወስዳል መንገድ …” ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ማርታ ለደበበ በምትሰጠው ፍቅር ሳቢያ የሚሠራበትን ግፍ የምታስረሳ ብትኾንም ማኅበረሰቡ ግን ተጨማሪ ግፍ የሚሠራበት መሣሪያ ኾናለች። የስንብት ቀለማት ላይ ምኒልክ ከዚያ ሁሉ እስርና እንግልት በኋላ፣ “በፊያሜታ አርፋለሁ” ብሎ ቤቷ ሲሄድ ተጨማሪ ሕመም በጆሮው በኩል ጭንቅላቱ ላይ ይሻጥበታል። መዝሙረ ሄላም ላይም፣ ሄላም “ሙዚቃዬን ከሕዝብ ጆሮ ያደርስልኛል … ያሳርፈኛል …” ብላ የተመካችበት ምናሴ እንጦሮጦስ ይጨምራታል። ማኅበረሰባችን የመስቀል ተ ሠላጢን ግብር እንዳለው፣ ከላይ አሳልሞ ከታች በአንካሴው ጉድጓድ እንደሚምስ ያሳያል። ይህም የመልእክትን ወጭት ሰብሮ የወጣ ጥበባዊ አጻጻፍ ነው። በፈጣጣው የቀረበ የትችት ኮሶ አይደለም። ድንቅ ነው! መዝሙረ ሄላም ላይ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸባሕርያት የተወሰኑት (አሮን፣ ቃል፣ ምናሴ፣ ሄላም) ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ። auto-fiction ዓይነት አጻጻፍ ባለው የአሮን አተራረክ ውስጥ አሮን “system observer” መኾኑን እንገነዘባለን። ሥርዓቱን ያያል፣ ዘማቹን ያስተውላል፣ ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ችግሩን ይመለከታል፣ ይጽፋል። አሮን የተገፋ ታሪክ ድምፅ ነው፤ ንቃት አለው፣ ግን የታሪክ ሂደትን የሚቀይር ኃይል የለውም፤ ስለዚህም ያ ሁሉ የጻፈውን ጽሑፍን ያጣል። የንቃት ችግር የለበትም፤ የማኅበራዊ ንቃት ድምፅነቱን ከዘመነ አባት ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ ተመልክተናል። ግን ደግሞ ይህ ብቻውን የቆመ ነጠላ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማኅበራዊ ተሳትፎ የለበትም። ቃል የተሰኘችው ገጸባሕርይም እንደ አሮን ናት፤ ንቃት ያላት፣ system observer ናት። ማኅበራዊ ንቃት ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ካላገዘው ግንጥል ጌጥ ነው። ቃልና አሮን ንቃት አላቸው፤ ግን ንቃታቸውን ተግባር አላገዘውም፤ ንቃቱን የሚተገብር አደረጃጀት የላቸውም። ስለዚህ ዕጣ-ፈንታቸው ውድቀት ይኾናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ይህን የድግግሞሽ አዙሪት መዝሙረ ሄላም ላይ ደራሲ አዳም ረታ በሰላ ብዕር አስቀምጧል። የደራሲና የአርታኢ ትስስር በተንጸባረቀበት በሄላም አተራረክ ውስጥ ምናሴ የተሰኘ ገጸባሕርይ እናገኛለን። ምናሴ የ-false collective consciousness ትእምርት ነው። ምናሴዎች ለሥልጣን ይሠራሉ፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ ያስባሉ፤ ነገር ግን የሥርዓቱ የመጠቀሚያ መሣሪያ (system functionary) ናቸው። ምናሴዎች የኦልቪቴዎች ጥይት ናቸው። ምናሴዎች የሔላምዎች ስኬት ሳይኾን የገዛ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ምናሴ በሌላ መነጽር ብናየው የመንግሥት ቢሮክራት የመካከለኛው መደብ ውክል ነው። ሀገሩ ከንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊ ሥርዓት ቢቀየርም፤ ከወታደራዊ ሥርዓት ወደ ሌላ ሥርዓት ቢለወጥም ምናሴያውያን ግን አይቀየሩም። ሥርዓት ይቀየራል - ምናሴያውያን አይቀየሩም፣ ትእዛዝ ይፈጽማሉ፣ ይከድራሉ። ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካል-ታሪክ ውስጥ የተደጋገመ፣ ግን ደግሞ ያልተስተዋለ እውነት ነው። ሄላም የወታደር ልጅ ናት፤ እንዲያሳድጋት በአደራ የተሰጠው ቤተሰብ የሚበድላት። የሷ ዓይነት ዕጣ ከደረሰው እንደ ወንድሟ ከምታየው ቴዲ ከሚባል ልጅ ጋር ታድጋለች። መጀመሪያ የሚልዮን፣ የኋላ ኋላ የምናሴ ፍቅረኛ የምትኾን ድምፀ-መረዋ ሴት ናት። ሁሉ ነገሯን ባጣችበት ወቅት ጡቷ ተአምር ያመርታል። በመዝሙረ ሄላም ላይ የሄላም የጡት ወተት የአንዳች ነገር ውክል ይመስለኛል። ሻዕቢያ ለታጋይ ወጣቶች ማሳደጊያ ፈልጓት ሊሰርቃት መፈለጉ በቀላሉ የሚዘለል ነገር ነው? ወተት እና ጡት በመጀመሪያ እይታ የሕፃናት ትዝታ፣ የእናትነት ምሥል፣ የእምነት እና የጾታ መነሳሳት የተዋሃዱበትም አይደል? ወተት ሕይወት ነው? የመጀመሪያ ምግብ፣ ከእናት ወደ ልጅ የሚፈስም አይደል? በክርስቲያናዊ ምልክት ንጹሕነትን አይወክልም? ወተት ከ“ቅዱስ” ወደ “ሥጋዊ” የሚያስተላልፍ ድልድይ ነው ማለት እንችል ይኾን? የሄላምን ጡት የጠባ ታማሚ ልጅ እንዴት ጤናማ ሊኾን ቻለ? የምን ትእምርት ነው? ሄላም ከብዙ ወንድ ጋር የወጣች እንደመኾኗ ለዚህ ሰናይ ግብር ለምን የሷ ጡት ተመረጠ? ሌላው፣ መዝሙረ ሄላም ላይ ኦልቬቲን እናገኛታለን። ኦልቬቲ የግራጫ ቃጭልዋ። መዝገቡ ንፋስ መውጫ ሳለ፣ ባልንጀራው ኤልያስ የብልግና ሀሁ ሊያስተምረው እፊቱ ያቆማት ቀይ ሰሌዳ ነበረች ኦልቬቲ። መዝሙረ ሄላም ላይ ምናሴን እና ቤተሰቡን የምታሾር ዐውራ ገጸባሕርይ ኾና ትከሰታለች። መዝሙረ ሄላም እና ግራጫ ቃጭሎች በጋለሞታይቱ በኦልቬቲ ብቻ ሳይኾን በዘመነ እንድርያስ እና በመዝገቡ ዱባለም ይገናኛሉ። ነጋ ዳቦ ጋጋሪውም በ-typological space መዝሙረ ሄላም ላይ እናገኘዋለን። መዝሙረ ሄላምን ከህላዌነት (Existentialism) አንጻር እንመልከተው። ሄላም ትርጉም በማይሰጥ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደምትኖር እናነባለን። የሀገሯ ዳር ድንበር እንዳይነካ አባት ብታዋጣም አሳዳጊዎቿ ግን የወላጅን ፍቅር አዋጥተው አይለግሷትም። ወርቅ አበድራ ጠጠር ትነፈጋለች። ዕቃ ለማገዝ ቤቷ ድረስ ለመጣው ሚልዮን ልቧን ትሰጣለች። ሀና የሸነቆረችውን ክፍተት ለሞላችበት ውለታዋ ክፍያ ይኾን ዘንድ ሚልዮን ለሄላም የወለፈንዴ ቡጢ ያሳርፍባታል። ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት ባስ ውስጥ ካገኘችው ሄኖክ ጋር ብትሞክርም የበለጠ የሕይወት ትርጉም ይዛባባታል። የወታደር ልጅ መኾኗ ሄላምነቷን በዜሮ ያባዘዋል። የመጨረሻው ስንብትም ከሄኖክ ጓደኛ አፎት በሚወጣ ሰይፍ መቀላት ይኾናል። ከሄኖክ ጓደኛ ጀርባ የሚውለበለበው ባንዲራ ደግሞ የሄኖክ ሸሚዝ መኾኑ ደግሞ ቁስሉን እንደ አቡሰዲቅ ያደርገዋል። ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ያለውን የሙዚቃ ሥራዋን፣ “ትርጉም ወዳለው
መዝሙረ ሄላም ላይ የተደረገ አጭር ኂሳዊ ንባብ ከቢኒያም አቡራ አዳም ረታ ታሪክን ከነገሥታት፣ ከመሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ባበጀው ድልድል ውስጥ ‹ላዕላይ› ከሚባሉት ደረጃዎች አንጻር አያስመለክተንም። ታሪካዊ ከሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተዘነጉትን ጥቃቅን የታሪክ ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ይመርጣል። ይወስዳል መንገድ ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ፍንዳታውን ከሚሞት ዘመድ፣ ከሚደነግጥ ለማኝ፣ ከሚሰነጠቅ የወፍ እንቁላል፣ ከሚፈስ የእናት ወተት ጋር Micro-Macro Connection በመፍጠር የትልቁ ቀዳዳ መፈጠርን ከሚጢጢዬ ሽንቁሮች ጋር ያስተሳስርልናል። እንዲህ ያሉ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕሪያትን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጻሕፍቱ ውስጥ በተለያየ መጠን እናገኛለን። Adam Reta አዳም ረታ "መዝሙረ ሄላም" በተሰኘው በዐዲሱ መጽሐፉ ላይም በኢትዮጵያ ታሪካዊ-ፖለቲካዊ አጋጣሚ ውስጥ እንደ ዐውራ የሚታዩትን የእድገት በኅብረት ዘመቻን እንደነ-አሮን፣ እንደነቃል … ባሉ ገጸባሕርያት በኩል፣ የሰባ ሰባቱን ድርቅ በሄላም ጡት በኩል፣ “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ” እየተባለ ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጋር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በሡልጣን በኩል፣ የከተማ መሬት ዐዋጅን በተለያዩ ግለሰቦች በኩል … እናያለን። በዚህም የታሪክን ትልቅ ካርታ ለመረዳት የተረሱና የጠለሉ ታሪኮችን ይመረምራል። ስለዚህ ነቁጣዊ ማኅበራዊ ክስተቶችን ወደ ታሪክ ምኩራብ በማምጣት ከትልቁ የታሪክ ምሥል ጎን ያስተያያል። ይህ ደግሞ የኒው ሂስቶሪሲዝም ኹነኛ ማጠንጠኛ ነው። ልክ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ባለው “የመንግሥቱ ጊዜ” በሚለው ድርሰት ውስጥ፣ ትልቁን “የታኅሣሥ ግርግር”ን እንደ መቼት አምጥቶ የተጻፈውና የተተኮረው ግን ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ላይ ነው። ስለግርማሜ ንዋይ፣ ስለኮሌኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሰለጄነራል ሙልጌታ ቡሊ አይደለም የሚያትተው። ስለአንድ ብላቴና ከእንቅልፍ መነሳት፣ ስለገበጣ ጨዋታ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕፃናትን አሰብስቦ ‹ኪራላይሶን› የሚያስብል ካሕን፣ ስለመንደር ውስጥ ሐሜቶች፣ ስለግለሰቦች ፍርሃት፣ በአጋጣሚ ስላየው አስደናቂ አሞራ … ያወጋል። የታሪክ አጋጣሚ አምጥቶ በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች ላይ ስለሚረብበው የታሪክ መንፈስ ያትታል። ልክ እንደዚሁ መዝሙረ ሄላም ላይም ጽሑፉ ታሪክን አያብራራም፤ ነገር ግን ታሪክ እንዴት በሰው ልብ ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል። በዚህ ኹነተ-ደቂቅ (micro-event) ምክንያት በዘመኑ ላይ ያገነገነውን ባሕላዊ እምነትን፣ የሥልጣን መዋቅርን፣ የወል ግንዛቤን አጨንቁረን እንድንመለከት ያስችለናል። ከመንግሥት ሼልፍ ላይ ሳይኾን ከግለሰብ ጀርባ ላይ የተወሰደው የአዳም የአጻጻፍ መንገድ ከኒው ሂስቶሪስዝም ጽንሰ-ሐሳቦች ጋር በአንድ መም ላይ የሚሄዱ ናቸው። መዝሙረ ሄላም የተሰኘው ዐዲሱ የአዳም ረታ መጽሐፍ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕርያትን ይጋራል። አንዳንድ ነገሮችን በዓይን መመልከት ባይቻልም በግብሩ (ቁስ ላይ በሚያደርገው ግፊት) ግን ይታወቃል። በመዝሙረ ሄላም መጽሐፍ ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን በቀጥታ ማየት ባንችልም ቅሉ እነርሱን የሚያሳይልንን ነገሮች ግን እንቃኛለን። ዘማች ወጣት ተማሪዎችን እናያለን፤ መንግሥትን፣ ሕግንና ኃይልን ግን በቀጥታ አንመለከትም። የተማከለ ኃይል አናይም ግን የገጸባሕርያቱ የፍርሃት ምንጭ ከተማከለ ኃይል ጋር የተያያዘ ቀጭን መስመር መኖሩን እናያለን። መንግሥትም ቢኾን በቀጥታ አይገባም፤ ነገር ግን ፍርሃት እንደ ሥርዓት ዘዋሪ (system driver) ይኾናል። እንደ ሚሸል ፉኮ አገላለጽ ኃይል ከተማከለ ሥርዓት የሚመነጭ ሳይኾን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በፍርሃት፣ በልማድ፣ በንግግር … ሊከሰት የሚችል ሂደት አይደል? መዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ “circulation of social energy” ቀርቧል። መዝሙረ ሄላም ላይ መረጃ ከመንግሥት አይመጣም፤ ከግለሰብ እንጂ። የከተማ መሬት ዐዋጅም ኾነ የተማሪዎች ዘመቻ በገጸባሕርያቱ ወሬ ውስጥ ነው የሚንቀረቀበው። ይህ የመረጃ ሥርዓት ኃይል ማን እንዳለው ማን እንደሌለው ያሳያል። እንግዲህ ይህ በፉኮኛ micro-power መኾኑ ነው። በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ ወሬ እንጂ እንደ ሰነድ አይቀርብም። ወሬ የፍርሃት ቤንዚን ነው … ፍርሃት ደግሞ በዝምታ መሸበብን ይፈጥራል … የዝምታ አፈ-ሙቅ ደግሞ ኃይለኛው እንዳይታይ ያደርጋል … የተደራጀው ኃይል ጥፋትን ሊያደርስ ባሰበ ቁጥር የወሬ ቤንዚን ይጨምራል። ሰዎች በዕቅብተ-ንግግር ራሳቸውን ሲሸብቡ ደርዝ ያለው ሙግት ይኮሰምናል፣ ንግግር ሲጠፋ ያልታወቀ አደጋ ይከሰታል፣ ፍርሃትም ይጨምራል። ያልታወቀ አደጋ ደግሞ ከታወቀ አካል ይመጣል። ስለዚህ ጥንስሱ የሚጀምረው ከወሬ እንደኾነ ያስመለክተናል። አዳም በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክን እንደ “circulation of social energy” ሲያቀርብ ፕሬዝዳንት፣ ጀነራል፣ ፕሮፌሰር የኾኑ ታሪክ ከላዕላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች አያስፈልጉትም። በአንጻሩ ሄላም ለማን እንደሳመችው ተደርጎ ብርሃኔ ያስወራው ወሬ፣ የሄላም አባት ወታደር በመኾኑ ምክንያት በካሱ፣ በሄኖክ እናት የተነዛው ወሬ እና ሄላም ከሄኖክ ጋር የተቆራረጠችበት መንገድ እንዲሁም የሄላምን የጡት ወተት በተመለከተ የተነዛው ወሬን ይጠቀማል። መዝሙረ ሄላምን ከድኅረ-ቅኝ-አገዛዝ የኂስ መንገድ አንጻር እንመልከተው። እውን ቅኝ-ግዛት ተረት ኾኖ ቀርቷል? በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነልቦና ረገድ የቅኝ አገዛዝ ዳናው ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል? አዳም በመዝሙረ ሄላም ጽሑፍ ውስጥ ከቅኝ-ግዛት በተወረሰ መዋቅር ምክንያት የተሰናከለን ሕይወት ሊያስመለክተን ይኾን? “ከተሞች ከቅኝ ግዛት በኋላ ሁለት ዓይነት መልክ ይኖራቸዋል፤ ለጥቂቱ የተድላ፣ ለተቀረው ደግሞ የአሳር መንደር ይኾናሉ” ይላል ፍራንዝ ፋኖን። በመዝሙረ ሄላም ላይ እና “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት” የተሰኘው ድርሰት ላይም ይህንን ነው የምንመለከተው። “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ጽሑፎች መካከል “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላ ሞት” አንዱ ነው። የቢሾፍቱ ልጆች ሆቴሉን ያዩታል፤ ግን አይገቡበትም። ሆቴሉ የሀገራቸው መሬት ላይ ነው፤ እነርሱ ግን ከሆቴሉ ውጭ ናቸው። መናፈሻው ውስጥ አንዲት የፈረንጅ ልጅ ጠግባ ለልጆቹ እንደ ውሻ ዳቦ ትወረውርላቸዋለች። አፈር ላይ የወደቀን ዳቦ አራግፈው ይመገባሉ። በገዛ ሐይቃቸው ዳር ላይ ናቸው፤ ሌሎች ግን በጀልባ እየተንሸራሸሩ ይንፈላሰሳሉ። ለፈረንጆቹ ያደረው ሞገስ የላንድሮቨር ተፈናጣጭ ኾኗል። ሌሎቹ ግን ከመኪናው ውጪ ናቸው። ሞገስ እንደ እነርሱ ሕጻን ቢኾንም ለፈረንጅ በማሸርገዱ የትምህርት ቤቱ ባለቤት ሲመስል ሌሎች ልጆች ግን በገዛ መምህራቸው ይብጠለጠላሉ። የቢሾፍቱ ልጆች፣ ነጻ በተባለች ሀገር እየኖሩ በቅኝ ግዛት ጥላ ይተዳደራሉ። የቢሾፍቱ ልጆች በገዛ መንደራቸው አካሉ በማይታይ የቅኝ ግዛት እጅ ይገፋሉ። ሞገስ አይናገርም፤ የሚናገርለት አለ። ልክ የቢሾፍቱ ልጆች ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንደምናገኘው ሁሉ “የስንብት ቀለማት” ላይም በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንመለከታለን። እንደ ዘድሬክ፣ ሳተርን፣ ከተስፋዬ ወደ አሸናፊ የተቀየሩ የድሎት ምሥሎች እና የእነምትክ ጉልት፣ የእትየ እልልታ የጉርሻ መሸጫ መስኮት ያሉ የእጦት ሥዕል እናገኛለን። መዝሙረ ሄላም ላይም እንዲህ ያለ በአንድ ከተማ ላይ የሁለት ምሥሎች አደባባይ እጀግ ብዙ ቦታ
የሀገር ግንባታ ! ጽንሰ ሃሳብ እና ትግበራ ! ~~~~~~ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጅሶ በዐውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ ላይ በመቅረብ የኢትዮጵያ የታላላቅ አሳቢያንን ብቃት የሚፈትነውን የምንጊዜም አንገብጋቢ ጉዳያችን ላይ ምሁራዊ ጥናታቸውን እጅግ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ አቅርበዋል ። ምሁራዊ ኃቀኝነትን ከተጋነነ ንዑሳን ብሔርተኝነት እና ሀገራዊ ብሔርተኝነት ተረክ ጋር አስታርቀው የተጓዙበት ርቀት አሁን ኢትዮጵያ ካለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር አጻር ምሳሌ የሚሆኑ ምሁር መሆናቸውን ታዳሚያን ገልጸዋል ። ~~~~~ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ የሀገር ግንባታን ጽንሰ ሃሳብ እና እድገት የዓለምን ታሪክን ንቡር ጠቅሰው ከአብራሩ በኋላ የኢትዮጵያንም የሀገር ግንባታ ሙከራ በተወሰነ ደረጃ ለማየት ሞክረዋል ። ከታዳሚያን በርካታ አድናቆት ፣ ጥያቄ ፣ አስተያየት የቀረበላቸው ሲሆን ለተጠየቁት ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል ።በዚህ መድረክ ላይ ጥያቄ ለመጠየቅ በርካታ ታዳሚያን እጃቸውን ያወጡ ቢሆንም ከአለው ጊዜ አንጻር የተወሰኑትን ብቻ ልናስተናግድ ተገደናል ። በዚህ አጋጣሚ የአገር ጉዳይ ገዷችሁ ፣የእረፍት ጊዜአችሁን ሰውታችሁ መጥታችሁ፤ ጥያቄዎቻችሁን እና ምልከታችሁን ከጊዜ አንጻር ያልተቀበልናችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን በዐውደ ፋጎስ ስም ይቀርታ እንጠይቃለን ። ሙሉ ቀረጻውን በዐውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ ላይ እስክናቀርበው ድረስ ዩቱብ ቻናሉን Subscribe ያድርጉ ። https://youtu.be/yudM5aX1mV0?si=QFSwB6VQYZ3zcGO9 የዐውደ ፋጎስ ነጻ የሃሳብ ዐደባባይን ማገዝ የምትፈልጉ በውስጥ አናግሩን ። በእውነት እና በቅንነት የትውልድ ንቃት በሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ በነጻ እንሰራለን ።
89ኛው ዙር የዐውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ ~~~~~~ ርእስ :- ❝የሀገር ግንባታ : ከጽንሰ ሃሳብ እስከ ትግበራ❞ አቅራቢ :- ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ( የምሥራቅ አፍሪካ ፖሊሲ ጥናት መሥራች እና የቀድሞ ምክትል ዳይሬክተር ፤ ለበርካታ ዓመታት በትምህርት እና በምርምር ፖለቲኮ - አካዳሚ ጽሁፎችን ሲያበረክቱ የኖሩ ፣ በዩኒቨርስቲ በመምህርነት ያስተማሩ፣ ብሔርተኝነት የሚል ዳጎስ ያለ መጽሐፍ የጻፉ እና በተለያዬ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ላይ ያገለገሉ አካዳሚክ የፖለቲካ ሰው ናቸው) ቀን :- እሁድ ሐምሌ 19/ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ቦታ :- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዘክር እና ቤተ መጻሕፍት ( ወመዘክር ) አዳራሽ ። ከቻሉ የዶ/ር ብርሃኑ የጻፏቸውን በርካታ አርቲክሎችን እና ብርሔርተኝነት የሚለውን መጽሐፍ አንብበው ቢመጡ የተሻለ ነው ።በጊዜው በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የነጻ ሃሳብ አራማጅ ምሁራን ይገኛሉ ። ይኸን የሃሳብ ዐደባባይ subscribe ያድርጉ። https://youtu.be/qBXYbg8i5UQ?si=43ECTh8NaZ315d1z
ደ*ደብ መሆን ያምረኛል! ~~ ቢሮው እንደገባን በታላቅ ፍቅርና አክብሮት ተቀበለን ፣ ስልኩን አንስቶ ደወለና ጥሩ ፒዛ እና ጥብስ አምጡልን አለ ። ጥብስ አልቋል አሉት ። በቃ ያለውን ፒዛና ቀይወጥ ይሁን ብሎ ትኩስ ነገርም በምርጫችን አዘዘልን። በኢትዮጵያ ባህል እየቆረሰ ይህችን ጨርሷት እያለ በቢሮው መገበን ። ቢሮው ያምራል ። ልጁም ደስ ይላል ። ፍጹም ነጻነት በተሞላበት መልኩ ፣ የእውቀትም ፣ የሀብትም ፣ የደረጃም ልዩነት ሳይኖረን በነጻነት እያወጋን ጨዋታችንን አደራነው።በነጻነት ስላችሁ በሙሉ ነጻነት አይደለም ። የምንጠብቃቸው ሰው ሰራሽ ሕጎች አሉ ።ግን መንፈሳችን እየተነቃቃ ይሄድ ነበር። በቁሳዊው ዓለም እና በመንፈሳዊው ዓለም መካከል እዚያም እዚህ እየረገጥን ተንቦጫረቅን ። ድሮስ ማነው በጠራ መንገድ የሄደው ? ካላስመሰለ በስተቀር። አንዱ ጓደኛችን በጎ ምግባር ለመስራት ገንዘብ ያስፈልጋል አለ ። አክሎም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሀብታም መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላታል የሚለውን እና መሰል ጥቅሶች አልቀበልም ብሎ ለምሳሌ ከ6ቱ ቃላተ ወንጌል ሦስቱ በመስጠት የሚገኙ ናቸው ከሌለህ ምን ትሰጣለህ ? ብሎ አብራራ። ሁላችንም ገንዘብ አስፈላጊ እንደሆነ እየተወያየን ሳለ ድንገት ዘለን ወደ ሌላ ርእስ ውስጥ ገብተን ነጎድን። ወጣቱ ጋባዣችን ዩኒቨርስቲና ከዩኒቨርስቲ ከወጣ በኋላ ያሳለፋቸውን አስገራሚ የተጋድሎ ትዝታ አወጋን ። ለአመነበት እውነት ባለው የእውቀት ልክ የሄደበትን ርቀትን ተረከልን ። ያ ሁሉ የእውቀት እና የሕይወት ተጋድሎ ግን ክብርም ሆነ ንብረት እንዳላመጣለት በተመስጦ ነገረን ።ለእውነት በቆመ ጊዜ ከገዛ ወገኖቹ የመጣበትን ፈተናም አጫወተን ። ያነበባቸው መጽሐፍት እና በሕይዎት ያሉ አርአያዎቹ ግን በጽናት እንዲቆም እንዳደረጉት እኛን በሚያስተምር መልኩ መሰከረልን ። እንዲህ አለን ' ወዲህ ነፍሴ እንደ በፊቱ መጽሐፍ አንበብ ፣ ተመራመር ፣ተመሰጥ ፣ በመንፈስ ክነፍ ፣ለእውነት እና ለፍትህ ዘብ ቁም ጠበቃ ሁን ይለኛል ፤ ወዲያ ደግሞ በዚህ ዓለም ላይ ገንዘብ ኑሮህ ዝናህ ናኝቶ ለቤተሰብህ ኑር ይለኛል ... አንዳንድ የሚዲያ ስራ ልሰራ ስሞክር ፣ ሞራል ፣ ሥነ ምግባር ፣ የማኅበረሰብና የሃይማኖት ኃላፊነት ፣ ይሉኝታ ፣ ሀገራዊ ኃላፊነት እየመጣብኝ አቸገራለሁ ። አንዳንድ ጊዜ ብዙ ኃላፊነት እንዳይሰማኝ ደ*ደብ ደፋር መሆን ያምረኛል' አለን ። ይኸ የኢትዮጵያ ዓለም ለሞራል ፣ ለሕግ ፣ ለሃይማኖት ፣ ለእውነት ለሚጠነቀቁት ሳይሆን የአስመሳዮች እና የሰነፍ ደፋሮች ነው አለን። በጸጋው ማሞ
ስለ ሊቅ አፅቁ በዐውደ ፋጎስ የቀረበ ምርጥ ጥናት ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ስለ ሊቅ አፅቁ ሕይወት፣ አስደናቂ ስብእና እና አበርክቶዎች በዲ. አሻግሬ አምጤ በመረጃዎች ላይ በመመስረት እጅግ በተመጠነ ፤ ውብ በሆነ አቀራረብ ፤ ትህትና በተሞላበት ምሁራዊ አገላለጽ ፤ አዳዲስ ምልከታዎችን ባሳዬ መልኩ ጥናቱን አቅርቧል ። የመድረኩ ታዳሚያን ባልተለመደ መልኩ በመደነቅ እና በመገረም ለአቅራቢው ከፍተኛ አክብሮት እና ምሥጋና በማቅረብ በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎችን አቅርበዋል ። እንደ ዲ. አሻግሬ ያሉ በመረጃ እና በንጹህ ኅሊና የሚተነትኑ ከአድሏዊነት ነጻ የሆኑ ሰዎች ኢትዮጵያ ያስፈልጓተልም በማለት አስተያየት ተሰጥቷል። የቀረበው ጽሑፍ ከሊቁ አርቆ አሳቢነት ባሻገር የዘመኑን የጎንደርን እና የኢትዮጵያን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ፣ የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ እንቅስቃሴ የሚያስቀኝ ነበር ። እንደነዚህ ያሉ ተራማጅ ሊቅን ለትውልዱ ማስተዋወቅ ለዝመና እና ለአገር ግንባታ ያላቸው ሚና ላቅ ያለ መሆኑን ከታዳሚያን ተገልጿል ። የዐውደ ፋጎስ የሃሳብ ዐደባባይ ውሎ እንደምንጊዜውም ውብ ነበር ። ሙሉውን እስከምንለቅላችሁ ድረስ ይኸን ልዩ የዐውደ ፋጎስን የዩቱብ ቻናል Subscribe እያደረጋችሁ !https://youtu.be/yudM5aX1mV0?si=kWztD8qAw1B_-OAS
без подписи
без подписи
без подписи