tgindex

መዳን የፈለገ መንሐጀ ሰለፍን ይከተል

Статистика
Последний пост
24 июн.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
104
−1 за 1 дн.
Сутки
−1
−0,95%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
31
21 постов
Вовлечённость
29,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 24 июн.21из saleFiy_hune

    ☞  ፈትዋ )                          ➢ ልጆች ምን አይነት ኪታቦችን እንዲቀሩ ይመክራሉ ? 🎙በሸይኽ አብዱል ሐሚድ {ሐፊዘሁሏህ} https://t.me/saleFiy_hune https://t.me/saleFiy_hune

  • 18 июн.25из abuzekeryamuhamed

    💡ሸይኽ ከተማሪዎቹ ጋር! አንድ አስተማሪ ከተማሪዎቹ ጋር ማሳየት ያለበት ማንነት። ~ መከባበር ~ መተዛዘን ~ መመካከር 💺 በዶክተር ሸይኽ ሁሰይን አስ'ሲልጢይ ሐፊዘሁላህ https://t.me/HussinAssilty https://t.me/HussinAssilty

  • 26 мая39из fewaedabibekr

    📮ክፍለ ሀገር ለዝያራ ስንሔድ እንዴት መሆን አለበት  🔖 በሚል ርዕስ የተደረገ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ የጁሙዐ ኹጥባ ትርጉም። 📌ሙሐደራው ላይ ከተወሱ ነጥቦች⤵️ 👉አስሩ ቀናቶች በላጭነት 👉በእነዚህ አስሩ ቀናቶች በላጭ ከመሆናቸውምጋ ወደ ክፍለሀገር ሲወጣ የሚፈፀሙ ሙንከራቶች፤ ⭕️ወደ ክፍለሀገር ስንሄድና እዛም ሄደን በምን ሁኔታ ነው ማሳለፍ ያለብን 🎙️ በኡስታዝ አቡ በክር ዐብዱረሕማን ቢን ሸምስ አላህ ይጠብቀው። 📅 ጁሙዐ 14/09/2018E.C 🕌መስጂደል አሳር 📎https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/20628

  • 🚫 ደም ይነጅሳልን? | የፊቅህ ትምህርት 🎙 ኡስታዝ ዶ/ር ሸምሱ በብዙዎቻችን ዘንድ ጥያቄ የሚነሳበትን 'ደም ይነጅሳልን?' የሚለውን ነጥብ በሰፊው ያብራሩልናል። ስለ ነጃሳ አይነቶች እና ስለ ጠሃራ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ድንቅ የፊቅህ ትምህርት ነው። እስከ መጨረሻው ተከታተሉት። 👇👇 https://youtu.be/7rToWE2gzqw?si=KxAiNzMFEuVpAEHl

  • 4 мая40из Abumuseab

    አዲስ ረድ (ምላሽ) የኢኽዋን፣ የአህባሽና የሱፍያ ጥምር ከሆነው  መጅሊስ ጋር በተቀላቀሉት ሸይኽ አብዱልከሪም አህመድ አምቡዬ ላይ ሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን - ሀፊዞሁሏህ - ሸሪአዊ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ የሰጡት ብይን:: 🔷ሸይኻችን ሸይኽ ሐሰን ገላው (ሀፊዘሁላህ) በሸይኽ ዐ/ከሪም ላይ ምላሽ ለመስጠት ካበቃቸው የሸይኽ ዐ/ከሪም ተግባር 👇👇 https://t.me/IbnShifa/6565?single

  • 3 мая29из Abuhemewiya

    🟢ሰለፊይ የመሆን ማረጋገጫ 🟢تحقيق السلفية والسنية قال العلامة ربيع بن هادي المدخلي رحمه الله "فلا تتحقق السلفية والسنية في أحد حتى يفارق أهل البدع والتحزب قلباً وقالبا ويلتزم بما كان عليه السلف الصالح ظاهرا وباطنا، عقيدة ومنهجا، قولا وعملا، عبادة وأخلاقا" مجموعة الردود  376 አሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊይ አሉ: የሚከተሉት ነጥቦች እስከሚረጋገጡ ድረስ በአንድ አካል ላይ ሰለፊይነት እና ሱኒይነት አይረጋገጥም። ✏️የቢድዐህ እና የቡድንተኝነት ባልተቤቶችን በቀልቡም በአካሉም እስከሚርቃቸው ድረስ። ✏️ሳሊህ ቀደምት (ሰለፍ አሳሊህ) የነበሩበትን በውጭም ፣ በውስጥ ፣ በእምነት (በዐቂዳህ) ፣ በመንሃጅ ፣ በንግግርም በተግባር ፣ በዒባዳም በስነምግባር አጥብቆ እስከምይዝ ድረስ። http://t.me/Abuhemewiya

  • 3 мая24из IbnShifa

    መንሀጀ-ሠለፍን እንዴት ተረዳሀው/ሽው?! ……  …… መንሀጀ-ሰለፍን በትክክል እንገንዘብ!! 🔹 መንሀጀ-ሠለፍን በትክክል ከተረዳን የሁሉንም ነገር ልክና ድንበር እናውቀዋለን። መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን) እና ባልደረቦቻቸውን ጨምሮ እነሱንም በትክክል የተከተሉ የደጋግ ቀደምቶች መንገድ ማለት ነው። መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- አንዳንዶች እንደሚያስቡት ልክ እንደ ሌሎች የጥመት አንጃዎች ራሱን የቻለ አንጃ ሳይሆን ትክክለኛ (ንፁህ) ያልተበረዘው እስልምና ማለት ነው። ትክክለኛውና (ንፁህ) እስልምና ማለት ደጋግ ቀደምቶች ባመኑበት መልኩ ማመን ነው!። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:- فَإِنْ آمَنُوا بِمِثْلِ مَا آمَنتُم بِهِ فَقَدِ اهْتَدَوا ۖ وَّإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا هُمْ فِي شِقَاقٍ ۖ فَسَيَكْفِيكَهُمُ اللَّهُ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ «በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱንም አላህ ይበቃሃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡» አል_በቀረህ 137 ትክክለኛ ሠለፊይ ማለት ደግሞ:- እነዚሁ ደጋግ ቀደምቶች ባመኑበት መልኩ አምኖ በአካሄድም ሆነ በአኽላቅ፣ ከከሀዲዎችና ከጥመት አንጃዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነትም ሆነ በሌላ ደጋግ ቀደምቶችን በመልካም ሁኔታ ተከትሎ መጓዝ ማለት ነው። ሠለፊይነት ማለት:- የመልካም ቀደምቶችን መንገድ ለራስህ ዝንባሌ በሚመችህ መልኩ ሳታሰናዳው አጥብቀህ በመልካም ሁኔታ መከተል ነው። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:- وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ «ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡» አል_ተውበህ 100 መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- የፖለቲካው ሁኔታ ሲቀያየር የምትቀያይረው ማለት አይደለም!! መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- የአንድ ሰሞን የግርግር አቋም አይደለም!!። መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- በዱኒያዊ ጉዳይ ከተወሰኑ የጥመት አንጃዎች (የቢድዐ) ሰዎች ጋር ስትገናኝ ለዱኒያዊ ጥቅም አልያም አንዳች ለዲን ይጠቅማል ብለህ ምታስበው ነገር እንዳይቀርብህ ብለህ በማላላትም ይሁን በማጥበቅ የምትቀያይረው አቋም ሳይሆን የትም ሆነህ በየትኛውም ሁኔታህ እስከ እለተ ሞትህ አጥብቀህ የምትይዘው የማይቀያየር የደጋግ ቀደምቶች መንገድ ነው። መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ከሆኑ ግለሰቦች ጋር በዱኒያዊ ጥቅምም ይሁን በስነ-ምግባር ስላልተጣጣምክ ለመወነጃጀል ያህል የምትጠቀምበት አይደለም!! መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ቢደላህም ቢቸግርህ፣ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር በዱኒያዊ ጥቅማ ጥቅምም ሆነ በሌላ ብትጋጭም ሆነ ብትዋደድ፣ እስከ እለተ ሞትህ በክራንቻ ጥርስህ አጥብቀህ የምትይዘው የደጋግ ቀደምቶች መንገድ የሆነው ንፁህ እስልምና ነው!! መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ሞቅ ሲልህ ምታወልቀው ሲበርድህ አንስተህ የምትለብሰው ጃኬት አይደለም!! ይልቅ ሞቅታህም መቀዝቀዝህም ትክክል ይሁን አይሁን የምትለካበት ትክክለኛው መነፅር ነው። ስትቀዘቅዝ ለምን ቀዘቀዝኩ? ብለህ እንደ ሸሪዓ ራስህን የምትገመግምበት መንገድ ነው። ሞቅ ሲልህ ደግሞ ይህ እንደ ሸሪዓ (እንደ ቀደምቶች አቋም) ተገቢ ነው አይደለም? ብለህ ራስህን ፈትሸህ ምታስተካክልበት ምንጊዜም ሊለይህ የማይገባ የደጋግ ቀደምቶች መንገድ እንጂ ሞቀኝ ብለህ አውጥተህ የምታስቀምጠው ልብስ አይደለም!! ሠለፊይ (ሱኒይ) የሆነ ሰው የማይሳሳት ፍፁም አይደለም!!። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ:- “ሰለፊይ ነው ብዬ ፂሙን አስረዝሞ፣ ሱሪውን አሳጥሮ፣ እንዲህ ሲያደርግ አይቼ ሰለፊይነት አስጠላኝ… ኒቃቧን ለብሳ እንዲህ አድርጋ እንዲህ ስትል… ደግሞ በዛ ላይ ቀሪኣ ነች (የቀራች ናት) ከዛ በኋላ አስጠሉኝ…” ወዘተ ይላሉ። ሆነ ብለውም ይሁን አይሁን እንዲህ መሰል ፀያፍ ቃላቶችን በሰለፊይ ወንድምና እህቶች ላይ ከምላሳቸው የሚያወጡ ሰዎች አሉ። እንዲህ የሚሉ ሰዎች ሶስት ነገሮችን ዘንግተዋል:- 1ኛ, ዲናችን የሚለካው በቁርኣንና በሀዲስ እንጂ በሰዎች እንዳልሆነ ዘንግተዋል። 2ኛ, እነዚህ ኢስላማዊ ምልክት የሚታይባቸውን ሰዎች ሰው መሆናቸውን ዘንግተው ልክ ምንም የማይስቱ እንደ መላኢካ (ፍፁም) አድርጎ መሳል አለ። 3ኛ, አንዳንዴም እነዚህ ሰዎች ጥፋት ነው ብለው የሚያስቡት ነገር በሆነ ባህል ተፅእኖ ወድቀው ስህተት መስሎ የታያቸው ነገር ግን ደግሞ እንደ ሸሪዓ ችግር የሌለው ነገር በመሆኑ ሌሎች ቀለል አድርገው ተግብረውት ይሆናል። የሆነው ሆኖ ብቻ ግን አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ሰለፊይ የሆነ ሰው ፍፁም አይደለም!! ይሳሳታል ከስህተቱ ግን ቶሎ ይመለሳል። እንዲሁም መንሀጀ ሰለፍ በሰዎች ሳይሆን የሚለካው ሰዎች ናቸው በመንሀጀ ሰለፍ የሚለኩት!! ፈተናዎች በሚደራረቡበት ጊዜ እና የጥመት አንጃዎች ማእበል በሚበረታበት ወቅት እውቀት ያለው እንኳን ከመንሀጀ ሰለፍ ሲንገዳገድ ካየህ በጭላንጭል እውቀት መንሀጀ ሰለፍን የያዙ ሰዎች እንዴት ይሆኑ ይሆን?! ብለህ እንድታስብ ያደርግሃል። መንሀጀ ሠለፍን በትክክለኛ እውቀትና በትክክለኛ ማስረጃ በሚገባ ተገንዝቦ መያዝ ግዴታ ነው!! አለያ ግን ልክ ባህሩ በማእበል ሲናወጥ የጀልባዎች ሁኔታ እንደሚያሳስበው ሁሉ፣ በትክክለኛ እውቀት መንሀጀ ሰለፍን አጥብቀው ያልያዙ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ ነው!! ሳጠቃልል ሠለፊነት ማለት:- ቁርኣን እና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መገንዘብ ማለት ነው። እንዲሁም ደጋግ ቀደምቶች በተጓዙበት መጓዝና በቆሙበት መቆም ነው። ✍🏻ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

  • 🌙 የጁምዓ ቀን ህግጋትና ሱና 🎙 በሸይኽ አብዱልሐሚድ 👇 https://youtu.be/bVeoH9KvivU?si=23K5HWgHULSnI52U

  • ‏قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله : المسبحة من شعار الصوفية وأنت أصابعك تكفي . 📚شرح إغاثة اللهفان 08-11-1436هـ

  • 12 апр.39из IbnShifa

    የኢራን መሪዎች እጅ በሱኒዮች ደም የተጨማለቁ ናቸው!! ——— ይህን አንብባችሁ ዐረቢኛ ምትችሉ ከቪዲዮው አድምጣችሁ ፍረዱ!! https://t.me/IbnShifa/6578 ➣ ሶሪያ ውስጥ አምባገነንና አ_ራ_ጅና ጨፍ_ጫፊ ለነበረው ለሺዓው መሪ በሻር አል'አሰድ ለማገዝ ከኢራን ወደ ሶሪያ ለሚላኩ ወታደሮች እንደሚከተለው ነበር በመሪዎቻቸው (በሸይኾቻቸው) የሞራል ቅስቀሳ ሲደረግላቸው የነበረው:- “እናንተ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ሆይ! እንድናሳውቃችሁ የምንፈልገው ነገር ቢኖር:- እናንተ አሁን የምትጓዙት የተቀደሰ ወደሆነው ውጊያ (ጦርነት) ነው፣ እናንተ አሁን ወደ ሶሪያ ሻም አገር አህሉሱናዎችን ለመግደል ነው ምትጓዙት። አዎ እናንተ አሁን ከበኒ ዑመያዎች ጠንካራ የሆነን ቡድንም ልትዋጉ ነው ምትሄዱት። እናንተ ሺዓዎች የኢራን፣የአፍጋኒስታንና የሂዝቦላ ሺዓዎች፣ አዎ እናንተ የሉብናን የፍሊስጢን ሺዓዎች ወደ ሻም (ሶሪያ) የተቀደሰ ጦርነት ለማካሄድ ነው ምትጓዙት። አዎን እናንተን አሁን እያዘጋጀን ያለነው ሄዳችሁ (የሱኒዮችን) መስጂድ በማውደም የሁሰይንን (ቦታዎች) ልትገነቡ ነው። እስኪ ከአህሉሱናዎች ወንዶች ካሉ ፊት ለፊት ይውጡ፣ እኛ ለእነሱ ሚዳው ላይ ዝግጁ ነን፣ ከአህሉሱናዎች ውስጥ ከመስጂዶቻቸው መከላከል የሚፈልጉ ወንዶች ካሉ፣ ከሶሃቦች መከላከል የሚፈልጉ ካሉ፣ ሀያ ወደ ጦር ሜዳው ይግቡ፣ እናንተ ወዳጆች ሆይ! አሁን የምንዘጋጀው እነዚያን ለመግደል ነው። እነዚያ (ሱኒዮች) ዱኒያ ወጥራቸዋለች፣ በመቀመጥ ተወጥረዋል፣ ውዶች አሁን ጊዜያችን ነው። ከወታደሩ አቤት ሆይ!… አቤት ሆይ!… አለ። የሶሪያውያን ሰቆቃና ውድመት የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፣ በሶሪያ ህፃናት ላይ ኬሚካል ተኩሰው አየሩን በክለው እየተሰቃቱ ሲሞቱ የዓለም ህዝብ ልብ ነው የደማው። አገራቸውን ለቀው የተሰቃዩት ለሞትና እንግልት የዳረጓቸው እነዚህ ጨፍጫፊዎች ናቸው። እነዚህን ጨፍጫፊዎች ነው እንግዲ የሀገራችን ኢኽዋኖች ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አሳቢና እንደ ጀግና አድርገው የሚያስተዋውቁት። እነዚህ የኢራን ሺዓ መሪዎች ናቸው ኢራቅንና ሌሎች ሙስሊም አገራትን ተመካክረው ሲወሩና ሲጨፈጭፉ ከዛሬ ጊዜያዊ ጠላቶቻቸው ከአይ ሁ_ዶ _ች ጋር ወዳጅ የነበሩት። ኢራኖች ይህን አላማቸውን ለማሳካትም በተለያየ አገር አማፂያንን ያስታጥቃሉ፣ በሶሪያና በሉብናን ሂዝቦላን፣ በኢራቅ ሀሽደ'ሸዕቢይ፣ በየመን ሁሲይን በፍልጤም ሀማስንና መሰሎችን አደራጅተው አስታጥቀዋል። = ጥበበኛው አምላካችን አላህ በትላንት ወዳጆቻቸው እጅ የሞትን ጠዓምና የጦርነትን ፈተና እና መራራ ጠዕም እንዲቀምሱ ሰበብ አድርጓል!! ይህ የአላህ ህግ ነው!! በዳይ ዟሊምን ከጊዜ በኋላም ቢሆን የበደሉን ክፉ ምሬት ያቀምሰዋል። ሺዓዎች (ራፊዷዎች) በስመ ኢስላም የሙሊሞችና የኢስላም ጠላቶች ናቸው!! የሶሃቦች የነቢዩ ﷺ ባልደረቦች ጠላቶ ናቸው!! አትሸወዱ! አሁን በፖለቲካ ስለተጋጩ እንጂ የአይ_ሁ_ዶ ች ወዳጆች ናቸው!! ታዲያ ለኢስላምና ለሙስሊሙ ምን አስቀሩ? ለዚያም ነው የኢስላም ሊቃውንት ሙስሊም አይደሉም ከሃ_ዲ_ዎች ናቸው!! ብለው ብይን የሰጡት። ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

  • 12 апр.31из IbnShifa

    የኢራን መሪዎች እጅ በሱኒዮች ደም የተጨማለቁ ናቸው!! ——— ይህን አንብባችሁ ዐረቢኛ ምትችሉ ከቪዲዮው አድምጣችሁ ፍረዱ!! ↘️↘️ https://t.me/IbnShifa/6579 https://t.me/IbnShifa/6579

  • 2 апр.34из AbuImranAselefy

    💬 ለሸሪዓ እውቀት ፈላጊዎች በሙሉ 👉 ​የሸሪዓ እውቀትን መፈለግ ወደ አላህ ከሚያቃርቡ ታላላቅ ተግባራት እና ከላቁ አምልኮቶች አንዱ ነው። በዚህም ባሪያው ጌታውን ያውቃል፣ በግልጽ ማስረጃም ያመልከዋል፣ ከራሱና ከሌሎችም ላይ መሀይምነትን ያስወግዳል። የቀደምት ሊቃውንት (ሰለፎች) በእውቀት መድረኮች ላይ በመገኘት ትልቅ ትኩረት ይሰጡ ነበር። በሷም ላለው ትልቅ ኸይር እና ትልቅ ደረጃ ትዕግስት ያደርጋሉ። 👉 ​ከዚህ በመነሳት፣ እናንተ የእውቀት ፈላጊዎች ሆይ!  ዘርፍ እጅግ ጠቃሚና ሁሉንም አጠቃላይ የሆኑት "ኩቱቡ ሲታህ" (ስድስቱ መጽሐፍት) መሆናቸውን ላሳውቃችሁ እወዳለሁ። እነሱም፦ ₁ ​ሶሒሕ አል-ቡኻሪ ² ​ሶሒሕ ሙስሊም ³ ​ሱነን አቢ ዳውድ ⁴ ​ጃሚዕ አት-ቲርሚዚ ⁵ ​ሱነን አን-ነሳኢ ⁶ ​ሱነን ኢብኑ ማጃህ ​"እያንዳንዱ ኪታብ ተለይቶ የሚያወቅበት ባህርያት አሉት፤ ◈ የፊቅህ ግንዛቤን (ጥልቀት) የሚፈልግ ሰው 'ሶሒሕ አል-ቡኻሪን' አጥብቆ ይያዝ። ◈ በሐዲስ ሰንሰለት ላይ ጥቂት አስተያየቶችን (ወይም አጠር ያሉ ዘገባዎችን) የሚመርጥ ደግሞ 'ሶሒሕ ሙስሊምን' ይያዝ። ◈ በሐዲስ ዘርፍ ላይ ሰፋ ያለ እውቀትን የፈለገ በ 'ጃሚዕ አት-ቲርሚዚ'ን ይያዝ። ◈ የአሕካም (የሕግጋት) ሐዲሶችን የፈለገ ደግሞ መዳረሻው 'ሱነን አቢ ዳውድ' ነው። ◈ በምዕራፎች አደራጃጀትና በፊቅህ አርእስቶች ውበት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ደግሞ ይህንን በ 'ሱነን አን-ነሳኢ' ውስጥ ያገኘዋል። 👉 እያንዳንዱ መጽሐፍ የቀደምትም ሆኑ የዘመኑ ሊቃውንት ትኩረት የሰጡባቸው የራሳቸው የሆኑ ልዩ ጠቀሜታዎች አሏቸው። ​"ለዚህም ሲባል፣ በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኘው ሰላም መስጂድ እንድትገኙ ለደርስ ተጋብዛችኋል። 🕌 ​የመማሪያ ቦታ፦ ኮምቦልቻ፣ ሰላም መስጂድ። 🎤 ​አስተማሪ፦ ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (አቡ ዓብዱሰላም)። 📚 ​ትምህርቱ፡ ስድስቱ የሐዲስ መጽሐፍት (ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ እና ኢብኑ ማጃህ)። 💬 ሸይኹ "እናንተ የእውቀት ፈላጊዎች ሆይ! ኑ እነዚህን 6 ኪታቦች ኪታቦች አብረን እንማር" በማለት ጥሪ አቅርበውላችኋል። 👉 ​ተማሪው ሊያሟላቸው የሚገቡ ቅድመ-ሁኔታዎች፦ ◦ በመጀመሪያ ​የአረብኛ ሰዋሰው (ነህው) የአልፊያ ኢብኑ ማሊክን ያህል ወይም የቀረበ ያክል የተማረ (እውቀት ያለው) ከሶርፍም እንደዚሁ የተወሰነ እውቀት ያለው መሆን ◦ ​ሁለተኛ ደግሞ ከፊቅህም እውቀትም ድርሻ ሊኖረው ይገባል። ይህም በታወቁ መዝሃቦች ወይም በዘመኑ የፊቅህ መጽሐፍት ላይ ግንዛቤ ያለው መሆን! ​◦ ሶስተኛ አጫጭር የዓቂዳ እና የመንሐጅ ኪታቦችን የቀራ መሆን! ​◦ አራተኛ ደረሶች ትምህርቱን አብረው ጀምረው አብረው የሚጨርሱ መሆን አለባቸው። 💬 በእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መሰረት — በአላህ ፈቃድ — እነዚህ መጻሕፍት በአንድ ዓመት ተኩል ወይም በሁለት ዓመታት ውስጥ ተጠንተው እንዲጠናቀቁ ይጠበቃል። 👉 ​ሊዘነጋ የማይገባው ትልቁ ቁምነገር፦ የስድስቱ ኪታቦች (ኩቱቡ ሲታህ) ንባብ በቀጥታ አይጀመርም። ይልቁንም ተማሪው ስለ ሐዲሥ እና ስለ ሐዲሥ ደረጃዎች ለመረዳት ብቁ ይሆን ዘንድ፤ ከእነሱ በፊት (ሙስጠለሐል ሐዲሥ) ኪታቦች ጥናት ሊቀደም ይገባል። ◈ በመጀመሪያ በ'አል-መንዙማህ አል-በይቁኒያህ'ን፤ እንደ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) አይነት ጠቃሚ ማብራሪያዎች ጋር ይጀምራል። ◈ በመቀጠል በሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር (አላህ ይዘንላቸውና) 'ኑዝሀቱ-ነዘር ፊ ሸርሒ ኑኽበቲል ፊከር' መጽሐፍ ይቀጥላል። ◈ እንዲሁም በዚህ ዘርፍ (ፈን) እውቀቱ እንዲሰርጽና የሚማረውን የነቢዩን ሱና በማስተዋል እንዲረዳ፤ በ'አልፊያህ አስ-ሱዩጢ'፣ ወይም በኢብኑ ከሲር 'አል-ባዒሥ አል-ሐሢሥ'፣ ወይም በ'አልፊያህ አል-ዒራቂ' ይቀራል።" ​"እዚህ ጋር በአንድ ነገር ላይ ማሳሰቢያ መስጠት እወዳለሁ፤ እሱም፦ ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (አላህ ይጠብቃቸውና) ሲያስተምሯቸው የነበሩት የፊቅህ ኪታቦች ትምህርት እንደተለመደው ኢንሻአላህ የሚቀጥሉ መሆኑን ነው። ስለዚህ በሐነፊ መዝሀብ ጥልቅ እውቀትን መቅሰም የሚፈልግ ሰው እነዚህን ትምህርቶች ለመከታተልና ከሸይኹ ለመቅሰም ይጓጓ (ይበርታ)።" ​"በተጨማሪም የተከበሩት ሸይኽ አቡ ጦልሃ (ሸይኽ አቡ ዘር ቢን ሀሰን አል-ወሎውይ አል-ኮንቦልሺይ — አላህ ይጠብቃቸው) ወደሚሰጧቸው ትምህርቶች እንድትገኙ ተጋብዛችኋል። እሳቸውም በሰላም መስጂድ በመግሪብ እና በዒሻእ መካከል፣ እንዲሁም በእሁድ ቀን የቀን ክፍለ ጊዜ ያስተምራሉ።" 👉 እነዚህ በሸይኩ የሚሰጡት የትምህርት ዘርፎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ (1) ሰፋ ያሉ የዐቂዳ እና መንሐጅ ኪታቦች። (2) የቅዱስ ቁርኣን ተፍሲር (ትንታኔ)፤ እንደ ኢብኑ ከሲር እና ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጦበሪ ባሉ ታዋቂ የተፍሲር መጻሕፍት ላይ በመመርኮዝ። (3) ኡሱል አት-ተፍሲር (የቁርኣን ትንታኔ መሠረታዊ መመሪያዎች)። (4) ኡሱል አል-ፊቅህ (የእስልምና ሕግጋት መሠረታዊ መመሪያዎች)። (5) አል-ቀዋዒድ አል-ፊቅሂያህ (የፊቅህ ፈን መርሆዎች)። (6) ሙስጦላህ አል-ሐዲስ (የሐዲስ ጥናት መመሪያዎች) እና ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ የትምህርት ዘርፎች። ​“አላህ በዚህ ሥራ ላይ በረካውን እንዲያሰፍንበት፣ ጠቃሚም እንዲያደርገው፣ ለእርሱ ብቻ የተሰራ (ኢኽላስ ያለበት) እና ጽናትንም እንዲለግሰን እንለምነዋለን።” ​“የአላህ ሰላት፣ ሰላምና በረካ በነቢዩ ﷺ ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይውረድ።” ​“ሸዋል 13፣ 1447” ​“በአቡ መንሱር ሙሐመድ ሐያት አል-ወለውይ አል-ሀረዊይ የተጻፈ።” https://t.me/AbuImranAselefy/12034

  • 📌 የደዕዋ ኘሮግራም እሁድ ሸዋል 17 1447 ሙዞ አቤላሞ ነስር መስጂድ ልዩ የሆነ የሙሓደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ 🗓መጋቢት 27 2018 ⏰ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ 🌙 ለሴቶች በቂ ቦታ አለን 🎙ተጋባዥ እንግዶች፦ ዶክተር ሸምሱ ኡስታዝ ኑራዲስ ወንድም ሐይደር ወንድም አቡ አፍናን 🕌 አድራሻ፦ ኢሌ ጤና-ጣቢያ ወደ ግራ ገባ ብሎ ☎️ ለበለጠ መረጃ፦ 0941651853

  • 🛡️ የ AI ዓለም ጉድ🛡️ ውድ የሱና ቤተሰቦች፤ የቴክኖሎጂው ፍጥነት ከምንገምተው በላይ እየረቀቀ ነው። እስኪ እነዚህን 3 አስገራሚ እውነታዎች ተመልከቱ፦ 1️⃣ የሞዴሎች ብዛት፦ በአሁኑ ሰዓት በዓለም ላይ ከ1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) በላይ የ AI ሞዴሎች አሉ። እንደ Hugging Face ባሉ መድረኮች ላይ ብቻ በየቀኑ አዳዲስና የተለያዩ ሥራዎችን የሚሠሩ "ሰው ሠራሽ አእምሮዎች" ይፈጠራሉ! 🚀 2️⃣ የመረጃ ጥልቀት፦ እነዚህ ሞዴሎች በሰው ልጅ ታሪክ የተጻፉ መጻሕፍትን በሙሉ በሰከንዶች ውስጥ አንብበው የመተንተን አቅም አላቸው። ነገር ግን የቱ "ሐቅ" የቱ "ባጢል" መሆኑን መለየት ስለማይችሉ፣ እኛ በሰለፍያ መርህ መረጃዎችን ማጣራት አለብን። 🔍 "إِنَّ هَذَا الْعِلْمَ دِينٌ فَانْظُرُوا عَمَّنْ تَأْخُذُونَ دِينَكُمْ" "ይህ እውቀት ዲን ነው፤ በመሆኑም ዲናችሁን ከማን እንደምትቀበሉ ተመልከቱ!" 🔍 3️⃣ ወሳኝ ምርጫ፦ AI የሰውን ልጅ አይተካም፤ ነገር ግን AIን የሚጠቀም ሰው የማይጠቀመውን ሰው በቀላሉ ይተካዋል! ለዚህም ነው ቴክኖሎጂውን መልመድ ለሁላችንም "አማራጭ" ሳይሆን "ግዴታ" የሆነው። 💡 የአቡ አይመን መልእክት ዓለም በአንድ ሚሊዮን የ AI ሞዴሎች ብትሞላም፣ እኛ ግን በአንድ ጥራት ባለው የሰለፍያ መርህ ላይ ቆመን ቴክኖሎጂውን ለዲናችንና ለዱንያችን ስኬት እንጠቀምበታለን!። ✍️ አቡ አይመን (Software Developer) 💻

  • 30 мар.29из jj_app_developer

    📱 አድስ አፕሊኬሽን ተለቀቀ       〰〰〰〰〰〰〰        ↪️ ሙሀደራዎች🎙 ➩ 🎙በ ኡስታዝ Dr. ሸምሱ አለህ ይጠብቃቸው ለሌሎች ሼር በማድረግ ላልደረሳቸው እናዳርስ! ✅  መሰል  ቂራአት እና ሙሀደራወች ለማሰራት የሚከተልውን አድራሻ ይጠቀሙ👇👇👇👇 @JJ_selfy_app_developer ✅ ከነ ሊንኩንም ሼር ማረግን አትርሱ       👇👇👇👇👇 https://t.me/jj_app_developer

  • 10 мар.451из Abumuseab

    የጎዳና ላይ ኢፍጣር Vs መውሊድ ...ቢደዓ ቢደዓ አጀማመሩ ብዙ ግዜ እንደ ከባድ ነገር ላይሆን ይችላል እንደው አንዳንዱ ቢደዓዎች አንዳንድ ለዲን ካላቸው ዕውቀት ማነስም ቀለል ተደርገው  እስልምናን ከመውደድ አኳያ ሊፈበርኳቸው ይችላል ችግሩ በግዜው የነበሩ ስለ ዲን ግንዛቤ ከማጣት አኳያ መፈብረካቸው ብቻ ሳይሆን ሺርክን አፍቃሪ ተውሒድን የማያውቅ ትውልድ እየተፈጠረ ሲሄድ  ኮሃላ የሚመጣው ትውልድ ቁርዓን ሀዲስ ካማለት ይልቅ አባቶቼን ብሎ ሙጭጭ ማለት ይጀምራል የዚህኔ አባቶቹ ባለማወቅ እየሰሩት የነበሩት ሺርክና ቢደዓም እንደ ትልቅ ዒባዳ ይቆጠራል ። ይህን ሺርክና ቢደዓ ለማጥፋት ከሱም ለመመለስ ሌሎች እውቀት ያላቸው የሞት ሽረት መክፈል ይጠበቅባቸዋል የሞት ሽረት የሚያህል መስዋዕትነትንም ከፍለው ማጥፋቱ ላይሳካላቸው ይችላል በሌላ በኩል ደግሞ ዕውቀት ከማጣት ሳይሆን ዕውቀቱ እያላቸውም ቢደዓ መጥፎና ውግዝ ነገር መሆኑን እያወቁም ከዱኑ ሌላን ነገር እያስቀደሙ ወይ ላስልጣናቸው ማቆያ በሚል ተልካሻ ምክንያት አልያ እኛስ ከእነ እገሌ በምን እናንሳለን በሚል ውሃ የማይደፋ ፉክክር እያመጡ እንደቀልድ በዲኑ ላይ አድስ መጤን ሲፈበርኩ አልያ የፈበረኩትን ሲያግዙ ይስተዋላል ይህም ምናልባት እንደ ኑህ አለይሂ ሰላም ግዜ ሰዎች በግዜ ያሉ ሰዎች ዘንዳ ምንም ላይሆን አልያ ዲን ነው ተብሎ ላይያዝ ይችላል ነገር ግን ግዜያት በነጎዱ ቁጥር እነዚህ ተግባራት ሙሉ ለሙሉ አቅጣጫቸውን መቀየራቸው ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው ለዚህም እንደ ማሳያ ለማንሳት የፈለኩት የጎዳና ላይ ኢፍጣርን ነው የጎዳና ላይ ኢፍጣር ምናልባት ዛሬ ምንም ላይመስለን እንደቀልድ የጀመርነው ከሌሎች ጋር በገባነው ፉክክር ሊሆን ይችላል ልክ እንደ መውሊድ ሰዎች የመውሊድ ሰዎች መውሊድን ሲጀምሩት በዚሁ መልኩ ነበር "ናሳራዎች የዒሳን ዓለይሂ ሰላም ካከበሩ እኛስ ነቢዩ ሙሀመድን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ከሁሉም በላይ እንወዳቸው ዬለ ? ስለዚህ ይበልጥ የሳቸውን የውልደት ቀን ልናከብር ይገባል " በማለት ነበር በፉክክር ገብተው የጀመሩት ይሃው ዛሬ ምን ያህል ፈሳድን ሺርክንና ቢደዓን እያስፋፋ እንደሆነ እሙን ነው ። የጎዳና ላይ ኢፍጣሩም ከዚህ በምንም አይተናነስም እንደው ይክፋ እንጂ ። ግዜያት በሄዱ ቁጥር ዲኑ እየተረሳ ጅህልና እየተስፋፋ ነው የሚሄደው " ሰዎች መሀይምን መሪ አድርገው ይይዛሉ " እንዳሉት ውዱ ነቢይ የዲን ዕውቀት እየተረሳ ሲሄድ ደሞ ዲን ያልሆነውም ዲን ተደርጎ እንደ ዒባዳ ይያዛል ስለዚህ ዛሬ እንደቀልድ የተጀመረው የጎዳና ላይ ኢፍጣይ ነጌ እንደ ትልቅ ዒባዳ ነው የሚያዘው እንደው እንደ ዒባዳ መያዙን ብቻ ሳይሆን መስቀል አደባባይን ሌላ ለየት ያለች የአምልኮ ቦታ ተደርጋ እንዳትያዝም ያስፈራል የኑህን አለይሂ ሰላም ህዝቦችን ሰይጣን መጥቶ " አባቶቻችሁ እኮ እነዚህን ሀውልት በከንቱ አልሰሯቸውም እኮ ዝናብ ሲጠፋቸው ርሃብ ሲበረታባቸው እነሱን ነበር ወጥተው የሚለምኑት " እንዳላቸው ሁላ ሳይጣን ተኝቶ አይተኛም ነጌም ለመጪው ትውልድ መጥቶ " እነዝያ አባቶቻችሁ ለከንቱ ይመስላቹሃል አደባባይ ወጥተው የሚያፈጥሩት ? ... " ብሎ የሽንገላ ና ማታለያ ወሬውን አምጥቶ መጪውን ትውልድ ላለማጥመሙ ምንም አሳማኝ ነገር ዬለንም ። በርግጥ እውነቱን እናውራ ከተባለ አሁን እራሱ ጎዳና ላይ ወጥቼ በማፍጠሬ ሌላ አጅር አገኝበታለሁ የሚል ዬለም ማለት አያስደፍርም እንደ ዲኑ ክፍል የሚቆጥረ ዲንን ያልተማረው ወጣፍ በገፍ መኖሩ አያጠራጥርም። ስለዚህ ውድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሆይ እውነት ዲንህን የምታስብ ከሆነ እንዲህ ያሉ ኹረፋቶችን ከዲን ያልሆኑ ዲንን የሚያበላሹ ቆሻሻዎችን እራስህም ራቅ ሌሎች በቅርብህ ያሉትንም እንዲርቁ አድርግ ። አላህ ሀቅን በሀቅነቱ ያሳየን የምንከተለውም ያድርገን ባጢልን በባጢልነቱ ያሳየን የምንርቀውም ያድርገን አሚን !!! ✍አቡ መስዐብ ጅብሪል ሱልጣን ✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!! https://t.me/Abumuseab

  • 👆👆👆 الرد على الشيخ أبي عمار محمد بن عبدالله باموسى فى كتابه زغل الدعوة والدعاة آدم الزبير النيجيري https://t.me/Abumuseab/5829

  • 10 мар.41из Rightpathstudent

    🟢አጭር የግጥም መልዕክት 👉"ለጎዳናው ኢፍጣር ሰዎች" ስሙ ተከሽኖ መልካም ቢመስልም፣ ከቢድዓ ሸክምነት አይወጣም መቼም፣ ድሮም ዛሬም ቢሆን ዲኑን አይወክልም፣ ዲናችን ሙሉ ነው ጭማሪ አይፈልግም፣ በሆነ ባልሆነው እያሳበባችሁ፣ አላዋቂውን ህዝብ እያጃጃላችሁ፣ ለመውሊድ ሰደቃን እንዳላከካችሁ፣ በነቢይ ውዴታ እንዳታለላችሁ፣ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ምነው አማራችሁ?! የማን ፈለግ ይሆን ማንስ አዘዛችሁ?! አመትን በሙሉ ጠብቆ ማክበርን "የጎዳናው መውሊድ "ውጤቱ ምን ይሆን?! የመውሊዱ ጣጣ ሳይለቀው ኡማውን በከንቱ ፈልሰፋ አትበርዙ ዲኑን ባንድነት ሙገታ አትበታትኑን የሀቅ ውዴታ ይሁን በተግባራችን አቁሙ ተብሏል "አዲሱን መውሊድን" ከፊትና ጠብቆ በሱናህ ይግደለን።✍✍ ➣ይህ ተግባር የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሳይሆን የጎዳና ላይ ዚና መፍጠሪያ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ➥ከፊት ያለን ሰዎች አሏህን እንፍራ። ➥ለፈሳድ(በዋናነት ለዝሙት መዳረሻ ፣አጅነቢይ ወንድ ና ሴት መደባለቅ(ኢክቲላጥ) ወዘተ... ) መስፋፋት በር ከፋቾች አንሁን። ➥የኡማው አደራ አለብን!የፈተናን በር አንክፈት!የጠላት መጫወቻ አንሁን። ➥ዲን የተገነባው በማስረጃ(በደሊል) እንጂ በጭፍን ስሜት አይደለም! ➣አሏህ ከተጠቃሚዎች ያድርገን🤲 || የቴሌግራም ቻናላችን👇👇👇👇 https://t.me/abuziyad876534 ጆይን በሉ then-----------ሼር

  • 7 мар.30из hussenabass123

    حكم التهنئة بقوله: مبروك أو كل عام وأنتم بخير ❂❂❂❂❂❂❂ السؤال ❂❂❂❂❂❂❂ ما حكم التهنئة في أول الشهر بقوله: مبروك أو كل عام وأنتم بخير، فهل هي من السنة أم لا؟ الجواب الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على نبينا محمد وعلى آله وأصحابه أجمعين، التهنئة بشهر رمضان لا بأس بها، وهي عادة معروفة عند الناس يتخذونها من باب الدعاء، يدعو بعضهم لبعض بهذا ولا بأس به، وقد ذكر بعض أهل العلم أن النبي صلى الله عليه وسلم كان يبشر أصحابه برمضان، يقول: (أتاكم رمضان) مبشرا لهم به، ولكن كلمة: (كل عام وأنتم بخير) هذه يظهر لي أنهم يريدون الدعاء بهذا، يعني جعلك الله في كل عام بخير، لكن لو قالوا كلمة أحسن من هذا وأخص، مثل أن يقول: بارك الله لك في الشهر وأعانك فيه على طاعته، وما أشبه ذلك لكان هذا أحسن من (كل عام وأنتم بخير) . https://t.me/hussenabass123

  • 7 мар.25из hussenabass123

    👉 ከቢድዓ ባለቤቶች ማስጠንቀቅ አድርሱልኝማ ከቢድዓ ባለቤቶች ማስጠንቀቅን ትተው ኢኽዋንጋራ ለሚርመጠመጡት ሁለተኛ ኢኽዋን ሙመይዓ ማለት ነው ኢንቢህ https://t.me/hussenabass123

መዳን የፈለገ መንሐጀ ሰለፍን ይከተል — tgindex