tgindex
Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
141
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
24
22 постов
Вовлечённость
17,0%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
9
1/48двое суток
10
1/72трое суток
11

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የደቡብ አፍሪካ እና የዚምባብዌ ፕሬዝዳንቶች በካሪባ ሀይቅ የጀልባ መስመጥ አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ 🇿🇦 ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት የወጣ መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የ44 ሰዎችን ሕይወት በቀጠፈው በካሪባ ሀይቅ የጀልባ መስመጥ አደጋ ምክንያት ለዚምባብዌ ያላቸውን የጠነከረ አጋርነት ገልጸዋል። "ለተረፉት ፈጣን ምህረትን እንመኛለን፤ ለተጎዱ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች ድጋፍ ለመስጠት እና እፎይታን ለማስገኘት ሳይታክቱ ለሚሰሩ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም ክብር እንሰጣለን" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። 🇿🇼 የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦች አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ ለባለስልጣናት መመሪያ ሰጥተዋል። "የሚመለከታቸው አካላት በቦታው በመገኘት ለተጎጂዎች እና ለተረፉት ሰዎች ሙሉ የሕክምና፣ የቀብር እና የስነ-ልቦና ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ" ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስፈረዋል። 🔙 119 ሰዎችን ይዛ የነበረችው ጀልባ ማክሰኞ ዕለት በዚምባብዌ እና ዛምቢያ ድንበር በሚገኘው ካሪባ ሀይቅ ላይ ነበር የሰመጠችው። 📹 በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪዲዮ አደጋው ከመከሰቱ ጥቂት ቀደም ብሎ የነበረውን ሁኔታ እንደሚያሳይ ተነግሯል።

  • አሜሪካ እና ኢራን የነሐሴ 11 የጊዜ ገደብ ከመድረሱ በፊት የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማራዘም ተስማሙ የአናዶሉ ምንጮች እንደገለጹት ግን ሁለቱ ወገኖች ስምምነቱ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚራዘም እስካሁን አልወሰኑም፡፡ አሜሪካ እና ኢራን በኢስላማባድ የተደረሰውን የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማራዘም ‹‹መስማማታቸውን›› የፓኪስታን መንግሥት ምንጮች ነግረዉኛል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡ ስምምነቱ በነሐሴ 11 የሚያበቃ ነበር። ለሽምግልና ሂደቱ ቅርብ የሆኑ አንድ ምንጭ ‹‹ሁለቱም ወገኖች የጊዜ ገደቡን ለማራዘም ያላቸውን ፈቃድ ለአደራዳሪዎች ገልጸዋል››ብለዋል። ምንጩ አክለውም ‹‹ይሁን እንጂ ሁለቱ ወገኖች ስለ ጊዜ ርዝማኔ ለመወሰን መልዕክቶችን እየተለዋወጡ ነው›› ብለዋል። አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን አደራዳሪነት በሚያዝያ ወር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤በኋላም ሰኔ 10 የመግባቢያ ስምምነት በመፈረም ወደ መጨረሻ ስምምነት የሚያመራ ድርድር ጀምረው ነበር። ይሁን እንጂ ድርድሩ በደህንነት ዋስትናዎች እና በዓለም አቀፍ የኢነርጂ አቅርቦት እና ንግድ ስልታዊ በሆነው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ የነፃ መርከብ ጉዞ ዙሪያ በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል። በሰኔ 30 እና በሐምሌ 17 መካከል አሜሪካ እና ኢራን ወታደራዊ ጥቃቶችን ተለዋውጠዋል። ዋሽንግተን በኢራን ውስጥ በሚገኙ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ስታደርስ፤ ቴህራን ደግሞ በዮርዳኖስ፣ በባህሬን እና በኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት እና ቁሳቁሶች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ምላሽ ሰጥታለች። እስከዳር ግርማ

  • ሩሲያ ዩክሬን ሲቪሎች ላይ የፈጸመችውን የሽብር ጥቃት ኮነነች   "የኪየቭ አገዛዝ በተለያዩ የሩሲያ ክልሎች በሚገኙ ሲቪሎች ላይ በየዕለቱ የሚፈጽመውን አረመኔያዊ ድርጊት በመቀጠል፤ ሕፃናት፣ ሴቶችና አረጋውያንን ጨምሮ በሰዎች ሕይወትና አካል ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል" ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ገልጸዋል። ቃል አቀባይዋ ይህንን ያሉት እሑድ እና ሰኞ በቤልጎሮድ እና ኒዥኔካምስክ በሚገኙ የሲቪል ተቋማት ላይ የተፈጸሙትንና ታዳጊዎችን ጨምሮ በደርዘን ለሚቆጠሩ መጎዳት ምክንያት የሆኑትን የቅርብ ጊዜ የዩክሬን ድሮን ጥቃቶች በማስመልከት ነው። 📍 ዲፕሎማቷ ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች፦ 🔶 በጥቃቱ የተሳተፉ አካላት በሙሉ ተለይተው ከባድ ቅጣት ይቀጣሉ። 🔶 ሞስኮ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጥቃቶቹን አጥብቀው እንዲኮንኑ ትጠይቃለች። 🔶 ሩሲያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ዝምታ እንደ ተባባሪነት እና በሩሲያ ሕዝብ ላይ ለሚፈጸም ተጨማሪ ጥቃት እንደተሰጠ ማበረታቻ አድርጋ ትቆጥረዋለች።

  • ምዕራባዊ ጀርመን በሚገኘው አንድ የወታደራዊ ጦር ሰፈር አካባቢ ባለፈው ሐሙስ ምሽት ሁለት ድሮኖች መታየታቸውን ባለስልጣናት ዛሬ (ቅዳሜ) አስታወቁ። ክስተቱ በምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው የላይፕዚግ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ቦምብ የታጠቀ ድሮን ከተገኘ ከሁለት ቀናት በኋላ የታየ ነው ተብሏል። ድሮኑ ባለፈው ሐሙስ ምሽት 4:00 ሰዓት አካባቢ ከቤልጅየም ድንበር 35 ኪ/ሜ ርቆ በሚገኘው የጀርመን መኸርኒች ጦር ሰፈር አቅራቢያ ነው። ድሮኖቹ መታየታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ወዲያው የአካባቢው ፖሊስ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን የፖሊስ ቃል ዓቃባይ ተናግረዋል። የጀርመን መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት በመኸርኒች የሚገኘው ቡንደስቬር የጀርመን ጦር (ቡንደስቬር)ግቢ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት የመሳሪያዎች እና የወታደራዊ ቁሳቁሶች መለዋወጫ ክምችት ያለበት ከመሬት ስር የሚገኝ መጋዘን የሚገኝበት ስፍራ ነው። የጦር ሰፈሩ የአሜሪካን የፓትሪዮት የአየር መከላከያ ስርአቶችን የመጠገን ሃላፊነት ያላቸው ሰራተኞችም መቀመጫ ነው ተብሏል። በተለያዩ ቀናት ታዩ የተባሉ ድሮኖች ተመተው ይውደቁ ወይም ያምልጡ ዘ,ገባው ያለው ነገር የለም። ክስተቱን ተከትሎ ድሮኖች የኔቶ አየር ክልልን ሰብረው መግበታቸው አዲስ ስጋት ፈጥሯል። እንደ ጀርመን ያሉ የሕብረቱ ዋና ሃገ,ራት መሰል የደህንነት ስጋቶችን ለመቋቋም ምን ያህል ዝግጁ ናቸው የሚል ጥያቄም አስነስቷል። የጀርመን የመንግስት ባለስልጣናት ለድርጊቱ የትኛውንም የውጭ ሀገር በይፋ ባይወነጅሉም፣ አንዳንንድ ህግ አውጪዎች ግን ጣታቸውን በሩስያ ላይ ቀስረዋል። በበርሊን የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ትናንት አርብ የላይፕዚግ ክስተትን "የተቀናበረ ትንኮሳ" ሲል ውድቅ አድርጎታል። "ያለበቂ ማስረጃ በሩሲያ ላይ የሚቀርቡ ክሶች ሌላው ማሳያ" ነው ሲልም አጣጥሏል።

  • የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ለተጨማሪ ዉጊያ እየተዘጋጁ መሆናቸዉ ተነገረ‼️ የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለተጨማሪ ዉጊያ የሚያደርጉት ዝግጅት መቀጠሉን የተለያዩ ወገኖች አስታወቁ።የአዉሮጳ የሰላም ተቋም መገናኛ ዘዴዎችንና ሌሎች ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የመቀሌና የአዲስ አበባ ግንኙነት ይበልጥ እየተበላሸ ነዉ።ሁለቱ ወገኖች የሚያደርጉት የጦር ኃይል ንቅናቄም ሌላ ጦርነት ሊጫር ይችላል የሚለዉን ሥጋት አንሮታል።ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸዉን ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታችና ገንቢ በሆነ ዉይይት እንዲፈቱ ተቋሙ ጠይቋል። የአይን ምሥክሮች በበኩላቸዉ የትግራይ ኃይል የሚባለዉ የታጣቂዎች ስብስብ በርካታ ተዋጊዎችን ወደ ምዕራብ ትግራይ እያዘመተ ነዉ።እንደሚሉት የትግራይ ተዋጊዎች ትግራይ ክልልን ከአፋርና ከአማራ ክልሎች ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢም ምሽግ እየቆፈሩ መሆኑንም የዓይን ምሥክሮች አስታዉቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ባንፃሩ አማራና አፋር ክልሎች ከፍተኛ የወታደራዊ ንቅናቄ እያደረገ መሆኑን የዓይን ምሥክሮች ተናግረዋል። ከአፋር ክልል በደረሰን መረጃ መሠረት በክልሉ የዞን አራት ተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ተጨማሪ ወታደሮች ሠፍረዋል።ነዋሪዎቹ በሥም በዘረዘሯቸዉ ወረዳና ቀበሌዎች ወታደሮችን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀሱና ተጨማሪ ኃይል ማስሩ እስከ ትናንት ማታ ድረስ ቀጥሎ ነበር።

  • | ከሩሲያ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶች ቁጥር በ42.2% አደገ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ቀውስ ምክንያት፣ "ኢትዮጵያ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ደሴቶች፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ሞሮኮ እና አውሮፓ ምቹ መሸጋገሪያ ሆናለች።" ሲል የሩሲያ የጉዞ አንቀሳቃሾች ማኅበር ለሪያ ኖቮስቲ ገልጿል፡፡

  • ሆርሙዝ የተዘጋው ከኦማን ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት አይደለም ስትል ኢራን አስታወቀች   የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋኢ  እንደገለጹት፣ በጉዞ መስመር ላይ መስማማት እና በሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤ በኩል ደህንነቱ የተጠበቀ የመርከብ እንቅስቃሴን ማረጋገጥ፣ ይህንን የውሃ መስመር ለመክፈት አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎች ናቸው።ነገር ግን "ይህ ብቻውን በቂ አይደለም" ሲሉ ቃል አቀባዩ በቴህራን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።   "የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤ የተዘጋው በኢራን እና በኦማን መካከል በተፈጠረ የአመለካከት ልዩነት ምክንያት አይደለም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።"የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤ ችግር ውስጥ የገባው በአሜሪካ እና በጽዮናዊው አገዛዝ ወታደራዊ ጥቃት ምክንያት ነው።" ሲሉ ተናግረዋል፡፡አክለዉም የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደገለጹት፣ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚያካሂዱት ጦርነት በአንድ ሀገር ላይ ብቻ የሚደረግ ጦርነት አይደለም ብለዋል።   ባጋኢ፣ "ይህ በመላው ክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ሀገራት ደህንነት ላይ የሚካሄድ ጦርነት ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።"ባለፉት አምስት ወራት፣ በአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል መገኘት የተነሳ እንዲሁም በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ደቡባዊ ዳርቻ በሚገኙ ሀገራት ግዛት እና መሠረተ ልማቶች አጠቃቀም ምክንያት በክልሉ ላሉ ሀገራት ሁሉ አለመረጋጋት እና የደህንነት ስጋት መባባሱን በገሃድ ተመልክተናል" ብለዋል።"ስለሆነም፣ የክልሉ ሀገራት ይህ ሁኔታ እንዳይባባስ ለመከላከል ጥረት ማድረግ መፈለጋቸው ተፈጥሯዊ ነው።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በስምዖን ደረጄ

  • የሩሲያ ጦር የአፍሪካ ኮር የአየር ኃይል በማሊ ሞፕቲ ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የኤፍኤልኤ -ጂኒም* ጥምረት ካምፕ ደመሰሰ *ጃማት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊሚን (ጂኒም) የአዝዋድ ነጻ አውጪ ግንባር (ኤፍኤልኤ) አሸባሪዎች አጋር እና ከዓለም አቀፉ የሽብር ድርጅት አልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው ቡድን ነው።

  • 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል መርሀግብር በመካሄድ ላይ

  • ኢትዮጵያው ቢሊየነር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ክለብ ተመለሱ 📈 ቢሊየነሩ ከያዝነው የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ሀብታቸው የ19.7% ወይም 1.67 ቢሊየን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን የብሉምበርግ የቢሊየነሮች መለኪያ አመልክቷል።   🤩 ሀምሌ 25 ይፋ በሆነው የቅርብ ጊዜ ደረጃ፤ ሼሁ ከዓለም  375ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።   የስዊዲኑ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ 'ፕሪም' የአል-አሙዲ ዋና የሀብት ምንጭ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን በሳዑዲ አረቢያ እና በኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት፣ በንብረት፣ በግብርና፣ በኃይል እና በማዕድን ዘርፎች ኢንቨስትመንቶች እንዳሏቸውም የሚታወቅ ነው።   👉 ይህ አዲስ ምዕራፍ ሳዑዲ አረቢያ እ.ኤ.አ በ2017 ባካሄደችው የፀረ-ሙስና ዘመቻ፤ ከበርካታ የሳዑዲ መሳፍነት፣ ሚኒስትሮች እና ታዋቂ ነጋዴዎች ጋር መታሰራቸውን ተከትሎ በሀብታቸው ዙሪያ ከተፈጠረው አሻሚ ሁኔታ ማገገማቸውን ያመላከተ ነው።

  • ፑቲን በአየር ወለድ ኃይሎች ቀን ለሩሲያ አየር ወለድ ወታደሮች ክብር ሰጡ 🇷🇺 ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ አየር ወለድ ወታደሮችን በዓል አስመልክቶ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ጽናት እና ቁርጠኝነታቸውን አድንቀዋል። 💬 "የጠንካራ ስብዕና፣ የማይበገር መንፈስ እና የወንድማማችነት አንድነት ያላቸው —አንዱ ከሌላው ጎን ሁሌም የሚቆሙ ናቸው" ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል። የአየር ወለድ ኃይሎች ለሀገራዊ ደህንነት የሚያበረክቱትን ወሳኝ አስተዋፅኦ እንዲሁም በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ውጊያዎች ላይ ያሳዩትን ጀግንነት በተለየ አንስተዋል።

  • "300 ሰዎች ወደ ውኃው ገቡ፤ 150 ተረፉ፤ 150 ደግሞ ውኃ ውስጥ ሰምጠው ቀሩ" የስፔንን ድንበር ያቋረጠው ሞሮኳዊ ስደተኛ   ​"እዚህ የመጣነው ስፔን ድንበሯን ከፍታለች ተብለን ነው፤ ስንደርስ ግን ተዘግቶ አገኘነው። ሙቱ እያሉን ነው የሚመስለው" ሲል ተናግሯል።   ​ℹ️ በዕለተ ዓርብ ብቻ ከ48 ሺህ በላይ ስደተኞች ከሴኡታ ወደ ሞሮኮ የተመለሱ ሲሆን አጠቃላይ የተመላሾች ቁጥር ደግሞ ከ50 ሺህ እስከ 60 ሺህ እንደሚገመት የአከባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

  • የሩሲያ ኃይሎች ለዩክሬን ጦር አገልግሎት በሚሰጡ የዩክሬን ወደቦች እና መርከቦች ላይ ጥቃት እንደፈጸሙ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ ​ሚኒስቴሩ አክሎም የሚከተሉት ኢላማዎች መመታታቸውን አስታውቋል፦ ​◻️ በኦዴሳ ወደብ የሚገኙ የነዳጅ ማከማቻ ዲፖዎች፣ ​◻️ በኒኮላዬቭ ወደብ ለሰው አልባ ጀልባዎች አገልግሎት እንዲውል የተሻሻለ የባሕር ላይ ተጎታች መርከብ።

  • viral | ጉቦ በአደባባይ 🙋‍♂️ የትራፊክ ፖሊሱ በመንገደኞች መታየቱ ሳያሳስበው ጉቦ ሲሰበስብ በካሜራ ዕይታ ውስጥ ገብቷል፡፡ ከማኅበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘ ቪዲዮ

  • ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ:: የ"እግረኛው ሚዲያ" መስራችና ባለቤት የሆነው ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር የዋለው በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሆነ የታወቀ ሲሆን፣ ለእስሩ ምክንያት ከመከላከያ ሰራዊት አልባሳት (ዩኒፎርም) ጋር ተያይዞ ከቀረበው ዘገባ ጋር ሳይያያዝ እንዳልቀረ ምንጮቹ ጠቁመዋል። ጉርሻ page

  • የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ለመወያየት ዋሽንግተን ገቡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በዋይት ሀውስ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የሚገናኙ ሲሆን፥ በዋናነትም በኢራን ላይ የተከፈተው ጦርነት በአጀንዳነቱ ቀዳሚ ቦታ ይይዛል። ይህ ጉብኝት ሁለቱ ሀገራት በየካቲት ወር በቴህራን ላይ ጥቃት በመሰንዘር ጦርነቱን ከጀመሩ ወዲህ ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር የሚያደርጉት የመጀመሪያው ውይይት ነው። በተጨማሪም ጉብኝቱ በዌስት ባንክ የእስራኤል ወረራ እና እስራት በበረታበት እንዲሁም ከሶስት ወራት በኋላ በእስራኤል ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ላይ መሆኑ ትኩረት ስቧል። የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ኔታንያሁ ለምርጫው የትራምፕን ድጋፍ ለማግኘት እየጣሩ ነው። ኔታንያሁ ወደ አሜሪካ የመጡት በሐምሌ 11 ቀን በሞቱት የሪፐብሊካን ሴናተር ሊንድሴ ግራሃም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመገኘት ሲሆን፥ የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት ከትራምፕ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዘዋል። በውይይቱም ላይ ከኢራን ጦርነት በተጨማሪ በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል ስላለው ግጭት እንዲሁም የአብርሃም ስምምነትን ስለማስፋፋት እንደሚመክሩ ተገልጿል። ሆኖም የሁለቱ መሪዎች የውይይት ውጤት ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሎ አይጠበቅም ተብሏል። ሳራ ዮሐንስ

  • ኢራን ከአሜሪካ ጋር በድጋሚ ውይይት እንዲጀመር አልጠየኩም ስትል ተናገረች   የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኤስማኤል ባጋይ፣ ቴህራን ጦርነቱን ለማስቆም ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ድርድር እንደገና እንዲጀመር እንዳልጠየቀች ተናግረዋል።“ይህ የጦርነት አስተዳደር አይደለም። ተደጋጋሚ የጦር ወንጀሎች እና በእነሱ መኩራራት በጽዮናዊ አገዛዝ ተጽዕኖ ስር የፈጠሩትን አደጋ ለማምለጥ የተደረጉ ሙከራዎች ብቻ ናቸው፣ እናም ዋጋ እንደሚከፍሉ አይቀሬ ነው” ሲሉ ባጋይ በቴህራን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።   በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ መጥቷል፤ ዋሽንግተን ጥቃቶችን ስትፈጽም እና ቴህራን በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት እና መሳሪያዎች ላይ ኢላማ በማድረግ የአጸፋ ምላሽ ሰጥታለች።በሌላ በኩል ዩክሬን በካስፒያን ባሕር ላይ እየቀዘፈ የነበረ የኢራን የንግድ መርከብ ላይ የድሮን ጥቃት ከፈጸመች በኋላ አንድ ከፍተኛ የኢራን ሕግ አውጪ የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጥ ዝተዋል፡፡   በኢራን ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ጥቃት የአጸፋ ምላሽ አለው ያሉት የሕግ አውጪው ይህንን አሜሪካ እና እስራኤል ያውቃሉ ብለዋል።የኢራን ፓርላማ ብሔራዊ ደህንነት እና የውጭ ፖሊሲ ኮሚሽን ሰብሳቢ የሆኑት ኢብራሂም አዚዝ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልዕክት አሜሪካ እና እስራኤል “ማንኛውም በኢራን ላይ የሚፈጸም ጥቃት ምንጊዜም ዋጋ እንደሚያስከፍል ያውቃሉ። ይህ ደግሞ ዛሬም እውነት ነው” ብለዋል። በስምዖን ደረጄ

  • የእስራኤል ጦር በበርካታ የዌስት ባንክ ከተሞች ላይ ጥቃት ሰነዘረ በዌስት ባንክ ቢያንስ 20 ተጨማሪ ከተሞች ላይ ወረራ የተፈጸመ ሲሆን፣ ቤቶች ፈርሰዋል እንዲሁም በደርዘን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ታስረዋል ነዉ የተባለዉ። የእስራኤል ወታደሮች በተያዘችው ዌስት ባንክ እና ምስራቅ እየሩሳሌም የሚያደርጉትን ጥቃት አጠናክረው ቀጥለዋል። ቢያንስ 20 ከተሞችን እና መንደሮችን በመውረር፣ ቤቶችን በማፍረስ እና በደርዘን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንን በቁጥጥር ስር አውለዋል ነዉ የተባለዉ። የአልጀዚራ ዘጋቢዎች እንደዘገቡት፤ የእስራኤል ጦር ከናብሉስ በስተደቡብ በምትገኘው ቤይታ ከተማ የሚገኘውን የጀባል ሳልማን አካባቢ የወረረ ሲሆን፣ ከራማላ በስተምዕራብ በምትገኘው ኒሊን ከተማም የማፍረስ ስራዎችን አከናውኗል። አምስት ፍልስጤማውያንም በቁጥጥር ስር ውለዋል። ‹‹የእስራኤል ሰፋሪዎች በፍልስጤማውያን ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት በአብዛኛው በቤቶቻቸው፣ በምሽት በማስፈራራት ይቀጥላሉ›› አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ ሳራ ዮሐንስ

  • የጦርነትና የግጭት ሁኔታዎች ለጤና አገልግሎት አሰጣጥ ትልቅ ፈተና መሆናቸው ተጠቆመ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች እና ጦርነቶች ለጤና አገልግሎቱ ችግር መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር ነው ያስታወቀው። በተለይም የእናቶች እና ህፃናት ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት መፍጠራቸውን በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና ቤተሰብ ዕቅድና የአፍላ ወጣቶች ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር አለማየሁ ሁንዱማ ገልፀዋል። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የነበረው ጦርነትና አሁን ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶች የጤና ባለሙያዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው አገልግሎት እንዳይሰጡ ከማድረጋቸውም በላይ የግብዓትና የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት ምክንያት መሆናቸውን አንስተዋል። ዶክተር አለማየሁ እንዳሉት፥ ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች እናቶች ለሞትና ለከፍተኛ ስቃይ የሚዳረጉበት ዕድል ሰፊ በመሆኑ፥መንግስት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በተንቀሳቃሽ የጤና ቡድኖች አማካኝነት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ ይገኛል። በቀጣይም አገልግሎቱ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ ከአካባቢው አስተዳደሮች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ሊዲያ ደሳለኝ

  • ቬኔዙዌላ "ጂኦግራፊያዊ አድልዎን" በመጥቀስ ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት እንቅስቃሴ ጀመረች ​❌ ቬኔዙዌላ የሮም ስምምነትን ለመሻር እና ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት የወሰነችውን ውሳኔ ለተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በይፋ ማሳወቃቸውን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፌሊክስ ፕላሴንሲያ ጎንዛሌዝ በኤክስ ገፃቸው ገልጸዋል። ​❗️ካራካስ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በተለየ ሁኔታ የአፍሪካ እና የላቲን አሜሪካ ሀገራትን ኢላማ ያደርጋል ስትል የከሰሰች ሲሆን የፍርድ ቤቱ እርምጃዎች በቬኔዙዌላ እና በሰፊው ደቡባዊው ዓለም ላይ የተከፈቱ ሕጋዊ ጦርነት ነው ብላዋለች። ​"በዚህ ምክንያት በቬኔዙዌላ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የሚያስቀጥል እና ዓለም አቀፍ ፍትሕ ሊያስተካክለው የሚገባውን አለመመጣጠን የሚያባብሰውን ይህንን የሕግ መሣሪያነት አንቀበለውም። እውነተኛና ፍትሐዊ ለሆነ እንዲሁም የሕዝቦችን ሉዓላዊነት እና በራስ የመወሰን መብት ለሚያከብር ፍትሕ ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ እናረጋግጣለን።"