ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ Business and Economics©
СтатистикаDon't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
- Последний пост
- 18 апр.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Live stream started
💡 ብቁ ያልሆነ የቴክኒክ ባለሙያ የሚያስከትላቸው ችግሮች እና መፍትሄዎቹ በርካታ ፋብሪካዎች ውስጥ የስራ ሂደት ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች ከማሽኖች ባለፈ ብቁ ባልሆኑ የቴክኒክ ባለሙያዎች ምክንያት የሚፈጠሩ ናቸው። ይህም በብዛት የማይታወቅ ነገር ግን በምርት ሂደት፣ የእርስ በእርስ መተማመን እና የኢንቨስትመንት ትርፍ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርግ ችግር ነው 🚩 ኢንቨስተሮች መጠንቀቅ ያሉባቸው ምልክቶች ▪️ በግል ብቃት ማነስ የሚፈጠሩ ችግሮችን በማሽኖችና በማሽን አቅራቢዎች ላይ ማሳበብ ▪️ በ commissioning ወቅት አላስፈላጊ የሆኑ ቴክኒካዊ ቅሬታዎችን በማቅረብ ለወደፊት ለሚፈጠሩ ስህተቶች ሰበቦችን ለመፍጠር መሞከር ▪️ ባለቤቶች እና አመራሮች በቂ የቴክኒክ እውቀት በማይኖራቸው ሁኔታዎች ችግሮችን ለመቅረፍ ከመሞከር ይልቅ ጣት ለመጠቆም መሞከር ▪️ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ግብዓቶችን (low-grade preforms) በመጠቀም እና የጥራት ጉድለቶችን በመፍጠር የማሽነሪ ችግር እንደሆነ ማስመሰል ▪️ ችግር ፈቺ ከመሆን ይልቅ እንደ ተቆጣጣሪና አስተያየት ሰጪ መሆንን መምረጥ ▪️ ግልፅ የሆነን አሰራር ባለመተግበር ስህተቶችን ለመደበቅና ፍጹም መስሎ ለመታየት የሚደረግ ጥረት በሚገባ የሚሰሩ ማሽኖች ጥቅም ላይ ሲውሉ ብቁ ያልሆኑ የቴክኒክ ባለሙያዎች ይጋለጣሉ። ስለዚህም የሌሉ ችግሮችን መፍጠር፣ በቀላሉ የሚፈቱ ችግሮችን አክብዶ ማቅረብ እና ሃላፊነትን አለመቀበል የነዚህ ቴክኒሻኖች ምርጫ ይሆናሉ ⚠️ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ▪️ የምርት ሂደት መዘግየትና ማሽኖች ስራ የሚያቆሙበት ሰዓት መጨመር ▪️ ከማሽነሪ አቅራቢዎች ጋር ያለን ግንኙነት ማበላሸት ▪️ የተሳሳቱ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎችን እንድፈፅም ማድረግ ▪️ ሰራተኞች እንዳይማሩና ልምዳቸውን እንዳያሻሽሉ መገደብ ▪️ ትክክለኛውን የችግሮች መንስኤ እንዳንረዳ ማድረግ ❓ብቁ የሆነ የቴክኒክ ባለሙያ ምን ይመስላል? አንድ የቴክኒክ ባለሙያ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለበት ባይባልም ከታች የተዘረዘሩት ነገሮች ሊኖሩት ይገባል፡ ▪️ መሠረታዊ እና ጠንካራ የቴክኒክ እውቀት ▪️ የእውቀትና የቴክኒክ ክፍተት ሲኖር በሃቀኝነት መነጋገር ▪️ ለመማርና ለመሻሻል ፈቃደኝነትና ፍላጎት ያለው ▪️ መፍትሄ ላይ ያተኮረ እና አብሮ ለመሥራት ቀላል የሆነ ባለሙያ ▪️ በመወቃቀስ ሳይሆን የችግሮችን መሰረት ለማግኘት በመሞከር የሚያምን ▪️ ችግሮች በሚፈጠሩ ወቅት ግልፅ መሆንና ለመወያየት ዝግጁ ✅ ኢንቨስተሮችና ባለቤቶች የቴክኒክ ባለሙያ ከመቅጠራቸው በፊት መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች ▪️ የተረጋገጡ መሰረታዊ ልምዶች እና ክህሎቶች ▪️ ከቡድን ጋር የመስራት ችሎታና ጥሩ አመለካከት ▪️ ከማሽነሪ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር አብሮ የመስራት ፍቃደኝነት ▪️ ከመውቀስና ጣትን ከምጠቆም በፊት ችግሮችን የመመርመርና መፍትሄ ላይ የመድረስ ችሎታ 🤝 ትክክለኛው መንገድ/አሰራር ማቲክላይን ሐቀኝነት እና ግልጽነት አብሮ ለመስራትና ስኬታማ ፕሮጀክቶችን ለማስኬድ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያምናል ስለዚህም፡ ▪️ ቀጣይነት ያላቸውን የቴክኒክ ስልጠናዎች ለደምበኞቹ ባለሙያዎች በሰፊው ይሰጣል ▪️ በ commissioning ወቅት ከባለሙያዎች ቡድን ጋር በትብብር በመስራት ግልፅ የሆነ ርክክብ መኖሩን ያረጋግጣል ▪️ ችግሮችን ከመደበቅ ይልቅ ለመፍታት በሞሞከር ያምናል/ይሰራል ስኬታማ የምርት ሂደት የሚገነባው በጠንካራና ችግር ፈቺ በሆኑ ባለሙያዎች እንጂ ጣትን በመጠቋቆም አይደለም። ትክክለኛ የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ማሽኖችን እንደ መደበቂያና እንደ ሰበብ ሳይሆን እንደ ስኬት መሳሪያነት ይጠቀማል። --- 💡 Problems Caused by an Incompetent Technician (Fake Professional) and their solutions In bottling factories, serious production problems often don’t come from machines, they come from incompetent or unprofessional technical leadership. This situation is more common than it looks, and it can quietly damage performance, trust, and ROI. 🚩 Common Red Flags ▪️ Blaming equipment or suppliers to shift attention away from personal incompetence ▪️ Creating unnecessary technical complaints during commissioning to build future excuses ▪️ Pointing fingers instead of fixing problems, especially when owners or GMs lack technical knowledge ▪️ Using poor-quality inputs (like low-grade preforms) to “prove” machines are faulty ▪️ Acting as a critic rather than a problem-solver to maintain authority ▪️ Avoiding transparency, because real performance would expose past wrong decisions In reality, when machines run well, a fake professional risks being exposed, so problems are often manufactured, exaggerated, or misdirected. ⚠️ Why This Is Dangerous ▪️ Delays production and increases downtime ▪️ Damages relationships with suppliers ▪️ Leads to wrong investment decisions ▪️ Prevents teams from learning and improving ▪️ Masks the real root causes of inefficiency 🧩 What a Real Technical Professional Looks Like A good technician doesn’t need to know everything, but must be: ▪️ Strong in fundamental technical knowledge ▪️ Honest about limitations ▪️ Willing to learn and improve ▪️ Open to clear communication ▪️ Easy to work with and solution-oriented ▪️ Focused on facts, not blame ▪️ Transparent when issues arise ✅ What Investors & Owners Should Demand Before appointing a technical head, look beyond titles: ▪️ Proven basic experience and skills ▪️ Good attitude and teamwork ▪️ Openness to work with machine suppliers ▪️ Ability to diagnose, not accuse ▪️ Integrity over ego 🤝 The Right Way Forward At Maticline, we believe honesty and transparency are essential on both sides. We actively:
በነገራችን ላይ አንድ የሙሉ ሰዓት ስራው መማር ብቻ የሆነ ሰው በተማሪነት ጊዜው ስራ አጥም ሰራተኛም አይባልም! ነገር ግን ከትምህርት ቤት ወድቆ ከትምህርት ዓለም በወጣ ቅስፈት #ስራ_አጥ ቁጥር ውስጥ ይደመራል! #ለመረጃ፡ በ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ከ585,879 ተማሪዎች መካከል ያለፉት 48,929 ብቻ ናቸው! (536,950 ተማሪዎች ወድቀዋል)። Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
የንግድ ህግ በጠቅላላ ፅንሰ ሃሳብ ።።።።።።።።።።።።።።። ንግድ ከመጀመርህ በፊት እነዚህን ክኒኖች ዋጥ፦ 💊 ቤተሰብህም ቢሆን ማንም ለእዳህ ሀላፊነት እንደማይወስድልህ አስበህ ተዘጋጅ፦ ጓደኞችህ ስለሚያውቁህ ብቻ ከአንተ እንዲገዙ፣ ቤተሰብ እንዲያበረታታህ ወይም ችኮላህን እንዲያስተዋውቅ አትጠብቅ። አብዛኛዎቹ የመጀመሪያ ደንበኞችህ እንግዳዎች ይሆናሉ። እንግዶች ባልፈው ነገርህ ላይ ሳያተኩሩ ስለምታቀርበው ዋጋ ያስባሉ። እነሱ ችላ ሊሉህ የማይችሉትን ጥሩ ነገር በመገንባት ላይ አተኩር። 💊 በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ጠንክረህ ሰርተህም ላታተርፍ እንዲያውም ልትከስር ሁሉ ትችላለህ፦ በአብዛኛው ይህ የሚገጥምህ ንግድህ እስከሚረጋጋ ድረስ ነው። ነፃነት ነፃ አይደለም። ላብህን ትከፍልበታለህ። 💊 በንግድ ውስጥ የገንዘብ ችግሮች አሉ፦ በገንዘብ አያያዝህ ቸልተኛ ከሆንህ በንግድ ውስጥ ያልጠበቅኸው ከፍተኛ እዳ ሊመጣብህ ይችላል። የገንዘብ ፍሰት አስተዳደርን፣ በጀት ማውጣትን፣ ለታክስ መቆጠብ እና ትርፍን እንደ ደሞዝ የመመልከት ፍላጎትህን መቃወም መማር ያስገፈልግሃል። ገበያ የሚቀዘቅዝባቸው ወራት፣ ከደንበኞች የሚዘገዩ ክፍያዎችና ድንገተኛ ወጪዎች ይኖራሉ። ንግድ የገንዘብ አያያዝ ጥሩ ልምድ ይጠይቃል። 💊 የንግድ መክሊት በቂ አይደለም፤ መዋቅር (system) ያስፈልጋል፦ የንግድ ተሰጥኦና ጥሩ ሀሳቦች አሉኝ ልትል ትችላለህ። የአሰራር ሂደቶች፣ የስራ ፍተሻ ዝርዝሮች፣ የጊዜ መርሐግብር ዘዴዎችና ውክልናዎች ያስፈልጋሉ። እነዚህን ስትጠቀም በታመምህበት ወይም በእረፍት በወጣህበት ቀን ንግድህ አይፈርስም። ምርጥ ንግዶች በአዋቂነት ብቻ ሳይሆን በመዋቅር ጭምር ይሰራሉ። 💊 ንግድ የማንነትህን የእያንዳንዱን ክፍል ይፈታተናል። ባለጌ ደንበኞች፣ ስራህን አመሳስለው የሚሰሩ ሌሎች ነጋዴዎች፣ የገንዘብ እጥረት፣ የማይጠቅሙና ክፉ ሰራተኞች፣ የተበላሹ ሽርክናዎች፣ ከባድ ውሳኔዎችና ጥርጣሬዎች ይፈታተኑሃል። ንግድህን ለመገንባት እነዚህን የመፍታት ችሎታህን አዳብር። የበለጠ ጠንካራ፣ ብልህ፣ ስነስርዓትህ የተሞላ፣ ትኩረት ያለህና ስልታዊ መሆን ያስፈልግሃል። ንግድ መጀመር በህይወት ውስጥ ጠቃሚ ከሆኑት መንገዶች አንዱ ነው። ነገር ግን አቋራጭ መንገድ አይደለም፤ ውጣ ውረዶች እንዳሉት ማወቅ ያስፈልጋል። ይዘረጋል፣ ይሰብራል፣ ያድሳል። ንግድ እንደ ጦር ሜዳ እምነትህን ይፈትሻል። ከራስን መለወጥ የተወሰደ Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
4. የሥራ ዕቅድ የብሄራዊ ቁጠባችን 👇👇 ቀጣዮን https://t.me/Ermyas27 #Ethiopia #ShegerFM #TizitaZearada #Meri_Rass_Aman_Belay #ShegerShelf #Alemayehugelagay #Tereka #2022Andualemtesfaye #Ethiopia #Ethiopia #ShegerShelf #ዕንባእናኩነኔ #AndualemTesfaye #AlexAbrham #ShegerFM #Mekoya #EsheteAssefa #MohamedHamdanDagalo #Sudan #KidameChewata #ShegerMekoya #EsheteAssefa #JOHNSCOBELL #BashaAwalom #Spy #EddieChapman #Ethiopia #TizitaZeArada #HaileSelassie #HaggaiErlich Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
የባንኮች የብድር አሠጣጥ ሂደትና 7 መሠረታዊ የብድር መሥፈርቶች ================== የባንኮች የብድር መመሪያና ፖለሲ ከባንክ ባንክ የተለያየ እንደመሆኑ መጠን፣ የብድር አሰጣጥ ሂደቱም በተወሰነ መልኩ ከተቋም ተቋም የተለያየ ነው፡፡ ነገር ግን ባንኮች የብድር ማመልከቻ ከመቀበል ጀምሮ ደንበኛ ወይም ተበዳሪ የሚፈልገውን የብድር መጠን ለመፍቀድ እንዲሟላ የሚፈልጉት፣ የጋራ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም መስፈርቶች አሉ፡፡ አነዚህን መስፈርቶችና ጉዳዮች በሚገባ መገንዘብና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በሂደት ማሟላት የብድር ጥያቄ ውድቅ እንዳይሆን ከማገዝ ባለፈ፣ የሚፈለገውን የብድር መጠን ሳይቀናነስ ከባንኮች የማግኘት ዕድልን ያሰፋል፡፡ በተጨማሪም የብድር ጥያቄ ከቀረበ በኋላ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲሁም ቅድመ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምክንያት በመመላለስ የሚባክነውን የአበዳሪ ተቋሙንም ሆነ የደንበኛን ጊዜና ጉልበት ያድናል፡፡ ከሌሎች የብድር ተቋማት በተለየ ሁኔታ፣ ባንኮች ከተለያየ አቅጣጫ ሊመጣ የሚችል አደጋን (Risk) ለመለየትና ብድሩ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ (Credit Risk) ቀድሞ ለመከላከል፣ በርካታ ገንዘብ-ነክ እና ገንዘብ-ነክ ያልሆኑ የትንተና መሣሪያዎችንና ዘዴዎችን የሚጠቀሙ ሲሆን፣ የብድር ትንተና ጥልቀትና ስፋቱ እንደ ብድሩ ዓይነትና መጠን እንዲሁም ድርጅቱ እንደሚገኝበት ዘርፍ የተለያየ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የብድር ጥያቄው ለአዲስ ፕሮጀክት ወይም ለነባር ፕሮጀክት ማስፋፊያ በሚሆንበት ወቅት፣ ተበዳሪው ከሚያቀርበው የአዋጭነት ዝርዝር ጥናት በመነሳት ለሌሎች ብድሮች ከሚደረገው የመመዘኛ ትንተና በተለየ ሁኔታ ስለ ገበያ ሁኔታ፣ በፍላጎትና በአቅርቦት መካከል ስላለው ክፍተት፣ ስለ ዘርፉ የገበያ ፉክክር፣ ስለ ድርጅታዊ መዋቅሩና አስተዳደሩ፣ ስለ ቴክኒካል ጉዳዮች፣ ስለ ጥሬ ዕቃ አቅርቦት መኖር፣ ስለ ምርቱ ወጪና ዋጋ፣ ስለ ህጋዊነቱና ትርፋማነቱ፣ በአጠቃላይ ስለ ንግዱ አዋጭነትና ቀጣይነት ሠፊና ጥልቅ ጥናት ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም እንዲቀርቡ የሚፈለጉት ሰነዶች እንዲሁም እንዲሟሉ የሚጠበቁት መስፈርቶች ለባንኮች የብድር ትንተና ግብዓትነት የሚያገለግሉ ወይም የሚወሉ ናቸው፡፡ ሌላው አበዳሪ ተቋማት በብድር አሠጣጥ ሂደት ያላቸው የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ አነስተኛ የብድር ተቋማት በአብዛኛው፣ የሚሠጡአቸው ብድሮች ሙሉ በሙሉ በመያዣ (Collateral) እንዲሸፈኑ በማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ሂደት የሚከተሉ ሲሆን፣ ባንኮች በበኩላቸው የሚሠጡት ብድር ንብረትን በመያዝ ስጋቱ (Risk) እንዲሸፈን ቢፈልጉም፣ ዋና ትኩረታቸው ግን አስተማማኝ የገንዘብ ፍሰት (Cash Flow) መኖሩ ላይ ነው፡፡ ስለሆነም የተበዳሪውን የገንዘብ ፍሰት ትንበያን በመተንተን ተበዳሪው በየወቅቱ የሚኖረውን የመክፈል አቅም ይመዝናሉ፡፡ በአጠቃላይ ለባንኮች የብድር መያዣ፣ ከደንበኛው የመክፈል አቅምና ፍላጎት እንዲሁም የንግዱ አዋጭነት ቀጥሎ የሚመጣ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እንዲሁም በርካታ የብድር አገልግሎቶች የመኖራቸውን ያህል እያንዳንዱ የብድር አገልግሎት የራሱ የሆነ (Specific) ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎችን፣ መስፈርቶችንና ሰነዶችን ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም፣ ለዛሬ ንግድ ባንኮች በብድር አሠጣጥ ሂደት በመሠረታዊ ደረጃ ትኩረት የሚያደርጉበትን ጉዳዮች፣ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም የሚከተሉትን የብድር አሠጣጥ ሂደትን ብቻ ለመጠቃቀስ እንሞክራለን፡፡ 1。 የተበዳሪው ፀባይ ከብድር ክፍያው ጋር በተገናኘ ባንኮች መረዳት ከሚፈልጉት ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋነኛው የተበዳሪው የብድር ታሪክ (Credit history) ሲሆን፣ በዚህም ደንበኛው ከዚህ በፊት ምን ዓይነት የብድር ልምድ እንዳለው፣ ከየትኞቹ ተቋማት እንደተበደረ፣ ምን ዓይነት ብድር እንደወሰደ፣ የብድር ክፍያውን በወቅቱ ይፈፅም እንደነበረ፣ ከዚህ በፊት ተበድሮ ሙሉ በሙሉ የዘጋቸው ብድሮች መኖራቸውን ጭምር የሚዳሰስበት ሲሆን ይህንንም አሁን ላይ የእያንዳንዱ ተበዳሪ ዝርዝር መረጃ (Credit Information)፣ ከጋብቻ ሁኔታ ጀምሮ፣ ምን ዓይነት ብድር መያዣ እንዳቀረበ፣ የት ባንክ ላይ ምን ዓይነት ብድር እንደጠየቀና አሁን ላይ ምን ያህል ያልተከፈለ ቀሪ የብድር መጠን እንዳለበት፣ የብድሮቹ ጤነኝነት ጭምር በብሔራዊ ባንክ የብድር መረጃ ቋት ውስጥ ስለሚገኝ፣ ከብድሩ ጋር የሚነካኩትን ግለሶቦች (ያገባ ከሆነ የባለቤቱን እንዲሁም የብድር መያዣ ንብረቱን ዋቢ አድርጎ የሚያቀርብለትን ግለሰብ) የታክስ መለያ ቁጥር በመጠቀም መረጃዎችን ለማግኘት የሚችሉበት አሰራር በመኖሩ፣ ባንኮች ተበዳሪው ለብድር ብቁ መሆኑን (Creditworthiness) ለማረጋገጥ፣ መረጃዎቹን ለብድር ትንተና ግብዓት ይጠቀሙበታል፡፡ ስለዚህም እያንዳንዱ ከብድር ጋር የተገናኘ እንቅስቃሴ፣ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እና ተበዳሪው ቃል በገባውና ብድር ውል ላይ በሰፈረው መሠረት ክፍያዎችንና ግዴታዎችን በአግባቡ መፈጸም፣ ከማንኛውም አበዳሪ ተቋም ጋር በቀጣይ ለሚኖር የብድር ግንኑነት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ በርግጥ ከፀባይ ጋር በተገናኘ በዚህ ብቻ አይወሰንም፡፡ ሌሎች የተበዳሪው ግልጽነት፣ መረጃ የመስጠት ፍላጎት፣ የትብብር መንፈስ፣ ክህሎት፣ የግል ታሪክ እና ዝና ግምት ውስጥ ሊገቡ የሚችሉ ጉዳዮች ናቸው፡፡ 2。የብድር መያዣ ምንም እንኳን ባንኮች የሚከተሉት ገንዘብ ፍሰት ላይ ትኩረት ያደረገ (Cash-flow based lending) አካሄድ ነው ተብሎ ቢታሰብም፣ እስከተቻለ ድረስ የብድር መያዣን እንደ ሁለተኛና የመጨረሻ አማራጭ ሲገለገሉበት ይታያል፡፡ የብድር መያዣ፣ አንድ ተበዳሪ ለተበደረው ገንዘብ ዋስትና ወይም ብድሩ ስለመከፈሉ መተማመኛ ይሆን ዘንድ የሚያቀርበው ወይም የሚያስይዘው ንብረት ሲሆን ይህም በዋናነት ቤት፣ ህንፃ፣ ማሽን፣ መጋዘን፣ የማምረቻ ቦታ እንዲሁም መኪና ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህም ተበዳሪው በራሱ ስም የተመዘገበ ንብረትን በመያዣነት ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን በተጨማሪም ለሚበደረው ብድር ሌላ በሶስተኛ ወገን ተመዝግቦ የሚገኝ ንብረትን ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ባንኮች፣ የብድር መያዣው በማንና በምን ይዞታ ላይ እንደሚገኝ እንዲሁም አሁን ላይ በገንዘብ ምን ያህል ይገመታል የሚለውን ጥያቄ የተለያዩ የምህንድስና ባለሙያዎችን በመጠቀም ያስጠናሉ፡፡ ለዚህም ባንኮች ለእያንዳንዱ የብድር መያዣ ንብረት የራሳቸው የሆነ የሚመሩበት የግምት መመሪያ አላቸው፡፡ ከብድር መያዣ ጋር በተገናኘ ከባንኮቹ የግምት መመሪያ በተጨማሪ በብሔራዊ ባንክ በኩል የተቀመጠ ሁሉም ባንኮች የሚተዳደሩበት የበላይ የሆነ መመሪያም ይገኛል፡፡ ነገር ግን ንግዱ ከሚገባው በላይ አዋጪ ሆኖ በተገኘ ጊዜና ሁኔታ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች በበቂ ሁኔታ የተሟሉ ሆኖ ሲገኝ የባንኮችን ያለ መያዣ እስከማበደር ሊደርስ የሚችል የማበደር ፍላጎት (Appetite) ይከፍታል፡፡ 3。ካፒታል ካፒታል አንድ የሚጠቁመው ነገር የድርጅቱ ባለቤት ለንግዱ ወይም ለሥራው ያለውን ቁርጠኝነት እና በሥራው ያለውን መተማመን ሲሆን፣ ስለዚህም የድርጅት ካፒታል አስተማማኝና ሥራውን የሚመጥን ሆኖ እንዲገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ብር Vs የኬንያ ሽልንግ ===== የአንድ ሀገር ገንዘብ የምንዛሪ ዋጋ መቀነስ ሶስት ፋይዳዎች አሉት:: አንድ የኤክስፖርት ተዋዳዳሪነት እንድጨምር ያደርጋል፣ ሁለት የውጭ ኢንቨስትመንት ይስባል ሶስት ቱሪዝም እንድጨምር ያደርጋል:: ያንድ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ዋጋ #መቀነስ እንደት ኤክስፖርት ተዋዳዳሪነትን ይጨምራል፣ እንቨስትመንትን ይስባል? ቱሪዝም እንድጨምር ያደርጋል? 1. የኤክስፖርት ተወዳዳሪነት እድጨምር ያደርጋል የአንድ አገር የመገበያያ ገንዘብ ዋጋ ሲቀንስ የዛ ሀገር ምርትና አገልግሎቶች ለውጭ ገዥዎች ርካሽ ይሆናሉ:: ይህም ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን የሚያሳድግ በመሆኑ ኤክስፖርት ተኮር የሆኑ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ለአንድ አገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ ሚና ይኖረዋል:: 2. የውጭ ባለሀብቶችን ይስባል የአንድ አገር የገንዘብ ምንዛሪ ደካም ስሆን የውጭ ባለሀብት በጠንካራ ገንዘቡ ብዙ #ንብረት መግዛት ስለሚችል አገሪቱ ውስጥ ያሉ ንብረቶች ለውጭ ባለሀብቶች የበለጠ ሳቢ ሆነው ባለሀብትችን ይጠራሉ:: 3. የቱሪዝም ፍሰት ይበልጥ የጨመረ ይሆናል:: የአንድ ሀገር የገንዘብ ምንዛሪ ደካማ መሆን አገሪቱን የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ያሳድጋል። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት 3 ፋይዳዎች የአገር ውስጥ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንድጨምር ከማድረጉም በላይ ለበርኬታ ስራ አጥ ዜጎች በርካታ የስራ እድል ይፈጥራል:: ማስታወሻ:- ድሮ ጎመን ስንል የነበረው የኬንያ ሽንግል አሁን ላይ ወደ ምንቼትነት እየተቀየረ ያለ ስሆን 0.75 የኬንያ ሽንልግ ከኢትዮጵያ 1 ብር ጋር እኩል ወደ መሆን ተቃርቧል:: ለምሳሌ 50 የኬንያ ሽልንግ ይዞ #ኢትዮጵያ የገባ ኬንያዊ ቱሪስት እና 50 የኢትዮጵያ ብር የያዘ ኢትዮጵያዊ👇 ኢትዮጵያ ውስጥ ድንች በዳጣ የሚበላበት ቦታ ተያይዘው ቢሄዱ ኢትዮጵያዊው አንደ ስያዝ ኬንያዊው ሁለቴ አዞ ልበላ፤ ወይም ደግሞ ኢትዮጵያዊው የከፈለውን ከፍሎ መልስ ይዞ ልመለስ ይችላል:: Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
https://ethio.gxmgv.xyz/4rijIijw/c28cfffee2832c508666a71ae8?_t1754724928746&p=t
https://ethio.gxmgv.xyz/4rijIijw/c28cfffee2832c508666a71ae8?_t1754724874991&p=t
የ 10 አገራት የመገበያያ ገንዘብ በአሜሪካ ዶላር የዛሬ ሽያጭ (ምንዛሬ) ዋጋ ከዚህ እንደሚከተለው ነው፦ ⩩ 1| ኢትዮጵያ ➔ 1 dollar = 133.45 Birr (ብር¹) 2| ቬትናም ➔ 1 dollar = 26,021.47 dong 3| ኢንዶኔዥያ ➔ 1 dollar = 16,828.56 Rupiah 4| ማሌዥያ ➔ 1 dollar = 3,841.79 Rupiah 5| ኡጋንዳ ➔ 1 dollar = 3,665.60 Shilling 6| ታንዛኒያ ➔ 1 dollar = 2,686.67 Shilling 7| ናይጀሪያ ➔ 1 dollar = 1,608.72 Naira 8'| ደቡብ ኮሪያ ➔ 1 dollar = 1,440.83 won 9| ፓኪስታን ➔ 1 dollar = 280.95 Rupee 10| ኬንያ ➔ 1 dollar = 129.50 Shilling [ወዳጄ ልቤ!...] ➊ የኢትዮጵያ ብር የወደቀ ነው የሚሉህ የወደቁ ናቸው። የኢትዮጵያ ብር ከወደቀ የቬትናም፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ፣... ብር ምን ሊባል ነው? አስቀድሜ የጠቀስኳቸውን ሃገራት ጠቅል ሃገራዊ ምርት፣ የኢኮኖሚ ደረጃ፣ የገቢ መጠን፣... ወዘተ ትንሽ Browse አድርገህ አንብብ... ➋ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምርታማ አይደለም። 85% ህዝባችን በግብርና ላይ ተሰማርቷል ብለን ስናበቃ ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ስንዴ ስንገዛ ነበር። በአፍሪካ በቀንድ ከብት አንደኛ ነን ብለን ስናበቃ ስጋ ከኬንያ እንገዛለን። ሸራተን ሆቴል እና Sky light hote ስጋ የሚገዙት ከኬንያ ነው 🤔 መንግስት ምርት እናምርት፣ የከተማ ግብርና፣ የበጋ ስንዴ፣ የሌማት ትሩፋት፣... ወዘተረፈ የሚለው ምርትና ምርታማነታችንን ለማሳደግ የዳቦ ቅርጫታችንን ለመሙላት ነው። ዛሬም ዘይት ከውጭ ገዝተን እናስገባለን። ጫማ፣ ልብስ፣ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጸጉር ቅባት፣ መድሃኒት፣ የቤት ቁሳቁስ፣ ነዳጅ፣ አትክልትና ፍራፍሬ (ሽንኩርት ሳይቀር 😂)፣ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ ከእነመለዋወጫው፣ ማሽነሪ፣ ወዘተረፈ በውጭ ምንዛሬ ገዝተን የምናስገባ ጉዶ'ች ነን። [መፍትሄው] [ሀ] ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ ማምረት፣ [ለ] የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ብዙ ምርት ወደውጭ መሸጥ፣ [ሐ] ማምረት! ማምረት ! አሁንም በጥራትና በብዛት ማምረት ! 💰 ¹ - የዛሬ ዓመት 1 dollar እስከ 250 ብር ሊደርስ ይችላል።
የ 10 አገራት የመገበያያ ገንዘብ በአሜሪካ ዶላር የዛሬ ሽያጭ (ምንዛሬ) ዋጋ ከዚህ እንደሚከተለው ነው፦ ⩩ 1| ኢትዮጵያ ➔ 1 dollar = 133.45 Birr (ብር¹) 2| ቬትናም ➔ 1 dollar = 26,021.47 dong 3| ኢንዶኔዥያ ➔ 1 dollar = 16,828.56 Rupiah 4| ማሌዥያ ➔ 1 dollar = 3,841.79 Rupiah 5| ኡጋንዳ ➔ 1 dollar = 3,665.60 Shilling 6| ታንዛኒያ ➔ 1 dollar = 2,686.67 Shilling 7| ናይጀሪያ ➔ 1 dollar = 1,608.72 Naira 8'| ደቡብ ኮሪያ ➔ 1 dollar = 1,440.83 won 9| ፓኪስታን ➔ 1 dollar = 280.95 Rupee 10| ኬንያ ➔ 1 dollar = 129.50 Shilling [ወዳጄ ልቤ!...] ➊ የኢትዮጵያ ብር የወደቀ ነው የሚሉህ የወደቁ ናቸው። የኢትዮጵያ ብር ከወደቀ የቬትናም፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ፣... ብር ምን ሊባል ነው? አስቀድሜ የጠቀስኳቸውን ሃገራት ጠቅል ሃገራዊ ምርት፣ የኢኮኖሚ ደረጃ፣ የገቢ መጠን፣... ወዘተ ትንሽ Browse አድርገህ አንብብ... ➋ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምርታማ አይደለም። 85% ህዝባችን በግብርና ላይ ተሰማርቷል ብለን ስናበቃ ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ስንዴ ስንገዛ ነበር። በአፍሪካ በቀንድ ከብት አንደኛ ነን ብለን ስናበቃ ስጋ ከኬንያ እንገዛለን። ሸራተን ሆቴል እና Sky light hote ስጋ የሚገዙት ከኬንያ ነው 🤔 መንግስት ምርት እናምርት፣ የከተማ ግብርና፣ የበጋ ስንዴ፣ የሌማት ትሩፋት፣... ወዘተረፈ የሚለው ምርትና ምርታማነታችንን ለማሳደግ የዳቦ ቅርጫታችንን ለመሙላት ነው። ዛሬም ዘይት ከውጭ ገዝተን እናስገባለን። ጫማ፣ ልብስ፣ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጸጉር ቅባት፣ መድሃኒት፣ የቤት ቁሳቁስ፣ ነዳጅ፣ አትክልትና ፍራፍሬ (ሽንኩርት ሳይቀር 😂)፣ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ ከእነመለዋወጫው፣ ማሽነሪ፣ ወዘተረፈ በውጭ ምንዛሬ ገዝተን የምናስገባ ጉዶ'ች ነን። [መፍትሄው] [ሀ] ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ ማምረት፣ [ለ] የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ብዙ ምርት ወደውጭ መሸጥ፣ [ሐ] ማምረት! ማምረት ! አሁንም በጥራትና በብዛት ማምረት ! 💰 ¹ - የዛሬ ዓመት 1 dollar እስከ 250 ብር ሊደርስ ይችላል። Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
ግብፅ 2ኛ ኢትዮጵያ በ7ኛ ደረጃ ተቀመጠዋል በ2025 ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ምርት /GDP/ ያስመዘገቡ 10 የአፍሪካ ሀገራት በቀላል አገላለጽ፣ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ማለት አንድ አገር የሚያመርታቸው ነገሮች፣ ዕቃዎች፣ አገልግሎቶች፣ ሥራዎች፣ ዋጋ በአመት ውስጥ ሲሰላ የሚመጣው የብር መጠን ማለት ነው የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ከፍ ባለ መጠን የበለጠ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እየተካሄደ እንደሆነ ያሳያል ነገር ግን የሀብት መለኪያ ብቻ አይደለም የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ ኃይል፣ ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ፣ የኢንዱስትሪ አቅም እና ሌላው ቀርቶ እቃዎችን ወደ ውጭ የመላክ አቅምን ጭምር ያሳያል። ስለ አንድ ሀገር ኢኮኖሚ ጥንካሬ ስናወራ በመጀመሪያ ከሚነሱት ነገሮች አንዱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ነው። እንደ አይኤምኤፍ ዘገባ ከሆነ ደቡብ አፍሪካ በ2025 በ410.34 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት መጠን በአፍሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ሆናለች ግብፅ ደግሞ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርቷ 347.34 ቢሊየን ዶላር በመሆን ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ኢትዮጵያ በበኩሏ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት መጠኗ117.46 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት በ7ኛ ደረጃን አግኝታለች በአንድ ወቅት የአፍሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ባለቤት የነበረችው ናይጄሪያ ምንም እንኳን ሰፊ የህዝብ ቁጥር ቢኖራትም ወደ አራተኛ ወርዳለች፣ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት መጠኗ188.27 ቢሊዮን ዶላር ሆኗል የ10ሩ የአፍሪካ ሃገራት ደረጃ እንደሚከተለው ነው 1)- South Africa 🇿🇦- $410.34B 2)- Egypt 🇪🇬- $347.34B 3)- Algeria 🇩🇿-$268.89B 4)- Nigeria 🇳🇬-$188.27B 5)- Morocco 🇲🇦-$165.84B 6)- Kenya 🇰🇪-$ 131.67B 7)- Ethiopia 🇪🇹-$ 117.46B 8)- Angola🇦🇴-$113.34B 9)- Ivory Coast🇨🇮- $94.48B 10)- Ghana 🇬🇭-$88.33B Source: IMF Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
የራሽያ ኢኮኖሚ 28,000 ማዕቀብ ተቋቁሞ እንዴት አደገ? ኢኮኖሚው ለ3 ዓመት ጦርነት ውስጥ ሆኖ እጥፍ የGDP እና የፖለቲካ አጋርነት እድገት አስመዝግቧል! የራሽያ ኢኮኖሚ ( ፑቲን) በጦርነት እና በማዕቀብ ውስጥ ሆኖ ኢኮኖሚን የማሳደግ ምሳሌ ሆነዋል! ራሽያ ላለፉት 3 ዓመታት 28,000 ማዕቀብ ቢጣልባትም ኢኮኖሚዋ ማዕቀብ ከጣሉባት ሃገራት የተሻለ እድገት ማስመዝገቡን IMF እየመሰከረ ነው! Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
“120 ሚሊየን ህዝብ የምናስተዳድረው ከ64 ሺህ ግለሰቦችና ኩባንያዎች በምንሰበስበው ግብር ነው” - ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋር የምታደርገው ድርድር ከተሳካ 10 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ታገኛለች ብለዋል አል-ዐይን 2024/7/4 9:34 GMT ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የውጭ እዳ ጫና ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት አንጻር በ17.5 በመቶ መቀነሱን ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የፋይናንስ ሴክተር ፣ ግብርና፣ የገቢ እና ወጪ ምርት፣ የግብር አሰባሰብ እና ሌሎችም ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮችን ዳሰዋል። የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ካጎበጡ መሰረታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች መካከል አንዱ የሆነውን የውጭ እዳ ጫና በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት 6 አመታት 10 ቢሊየን ዶላር ለውጭ እዳ መከፈሉን አንስተዋል። መንግስታቸው የእዳ ጫናን ለማቃለል ወስዶታል ባሉት እርምጃ ከጥቅል ሀገራዊ ምርቱ የነበረውን ድርሻ ወደ 17.5 በመቶ ማውረድ ተችሏል ነው ያሉት። የግብር ገቢን በተመለከተ በበጀት አመቱ 529 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ በ11 ወራቱ 466 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ጠቅላይ ሚንስትሩ በምላሻቸው ተናግረዋል። “ከ64 ሺህ ኩባንያዎች እና ግለሰቦች በምናገኝው ገቢ የ120 ሚሊየን ህዝብ ጥያቄ ለመፍታት እየሰራን ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት አንጻር የምንሰበስበው ገቢ 7 በመቶ ብቻ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በቀጠናው ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አንጻር የምትሰበስበው ታክስ ዝቅተኛ ነው መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህን ማሻሻል እንደሚገባ አንስተዋል። መንግስት የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት በገቢ አሰባሰብ ላይ ያሉ አሰራሮችን ማሻሻል ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን፤ የታክስ ስወራ፣ ኮንትሮባንድ፣ የንግድ ማጭበርበር እና ሌሎችም ከገቢ ጋር የተገናኙ ክፈተቶች ከፍተኛ ተግዳሮቶች ናቸው ነው ያሉት። በወጭ እና በገቢ ምርቶች መካከል ያለው የንግድ ልዩነት አሁንም ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ኢትዮጵያ በአመት ከ7 ቢሊየን ዶላር በላይ ለእዳ ክፍያ፣ ለአፈር ማዳበርያ እና ለነዳጅ ወጪ ታደርጋለች ብለዋል። ሆኖም ሀገሪቱ ለውጭ ገበያ ከምታቀርባቸው ምርቶች የምታገኝው ገቢ 4 ቢሊየን ዶላር የማይሞላ ነው። በ11 ወራቱ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርት መተካት ተችሏል። ለአፈር ማዳበርያ እስከ 2 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚደረግ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ በአመት እስከ 15 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበርያ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ይገኛል ብለዋል። በግብርናው ዘርፍ በ2015/16 የምርት ዘመን 507 ሚሊየን ኩንታል የግብርና ምርት የተመረተ ሲሆን ይህም ከባለፈው የምርት ዘመን 100 ሚሊየን ኩንታል ብልጫ እንዳለው ነው የተገለጸው። ጠቅላይ ሚንስትሩ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል በተወሰደ እርምጃ መንግስት 10 ቢሊየን ብር ገቢ ማጣቱን ገልጸው፤ በዚህም የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ መቻሉን አመላክተዋል። የፋይናንስ ሴክተሩን አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ የውጭ ሀገራት ባንኮች በሀገር ውስጥ ገበያ የሚፈጥሩት ፉክክር እና የአሰራር መዘመን ታስቦበት በቅርቡ ገበያውን እንደሚቀላቀሉ አረጋግጠዋል። በአሁኑ ወቅት 32 የሀገር ውስጥ ባንኮች የሚገኙ ሲሆን ለሚመጣው ውድድር ለመዘጋጀት አቅማቸውን ሰበሰብ አድርገው ቢወሀዱ አሰራራቸውንም ቢከልሱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ወቅት 100 ሚሊየን የቁጠባ ሂሳብ እንዳለ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስታቸው ስልጣን ከመያዙ በፊት ከነበረው የቁጠባ ሂሳብ ከእጥፍ በላይ መጨመሩን ነው የገለጹት። የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ከ6 አመት በፊት ከነበረበት 86 ቢሊየን ዶላር ወደ 205 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል ፤ ዘንድሮ በኢኮኖሚ 7 ነጥብ 9 በመቶ እድገት እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው በሰጡት ማብራርያ አመላክተዋል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ችግርን ለመቅረፍ እና መንግስት የጀመረውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋር የሚደረገው ድርድር የቀጠለ ሲሆን ድርድሩ የሚሳካ ከሆነ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት 10 ቢሊዮን ዶላር ከተቋሙ እንደምታገኝ አንስተዋል። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ የቀጠለ ሲሆን በቀሪ ቆይታው በወቅታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራርያ የሚሰጡ ሲሆን በመጨረሻም ምክር ቤቱ የ2017 በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
የተባበሩት መንግስታት በዓለም ላይ ለ180 ሀገራት ገንዘቦች እውቅና ሰጥቷል፡፡ ገንዘብ አንድን ቁስ ለመግዛት ያለው አቅም እና ሌሎች ምንዛሬዎች ለሱ ያላቸው ፍላጎት ጠንካራ እና ደካማ ሊያስብለው ይችላል፡፡ በተጨማሪም በአንድ ሀገር ውስጥ ያለው የውጪ ምንዛሬ ክምችት፤ የዋጋ ንረት፤ የወለድ ምጣኔ፤ የኢኮኖሚ እድገት እና የማዕከላዊ ባንኮች የፖሊሲ ሁኔታ ምንዛሬውን ጠንካራ አልያም ደካማ ተብሎ እንዲፈረጅ ሊያደርገው ይችላል፡፡ 10 የዓለማችን ጠንካራ ምንዛሬዎች! ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ያላቸውን ዓለም አቀፍ የምንዛሬ መጠን በመመልከት ለመለካት ያህል…. 10ኛ. የአሜሪካ ዶላር (ጠንካራ የመገበያያ እና የውጪ ምንዛሬ ክምችት ገንዘብ ነው) 9ኛ. ይሮ (አንድ ይሮ በ1.08 ዶላር ይመነዘራል! የዓለም ሁለተኛው ግዙፍ መገበያያ እና የውጪ ምንዛሬ ክምችት የ19 አባል ሀገራት መገበያያ ገንዘብ ነው) 8ኛ. የሲዊዝ ፍራንክ (አንድየሲዊዝ ፍራንክ በ1.10 ዶላር ይመነዘራል! የተረጋጋ ምንዛሬ ከሚባሉት መካከል ሲሆን! የሲዊዘርላንድ እና ሊቺተንስቲን ገንዘብ ነው) 7ኛ. Cayman Islands (ካሪቢያን ደሴት) አንድ የካይማን ደሴት ዶላር በ1.20 ዶላር ይመነዘራል!) 68ሺ ነዋሪ ያለባት የእንግዚዝ ቅኝ ግዛት ነች! 6ኛ. ጅብራአልታር ፓውንድ (አንድ የጅብራአልታር ፓውንድ በ1.26 ዶላር ይመነዘራል!) 32ሺ ነዋሪ ያለባት የእንግዚዝ ቅኝ ግዛት ነች! 5ኛ. የእንግሊዝ ፓውንድ (አንድ የእንግሊዝ ፓውንድ በ1.26 ዶላር ይመነዘራል!) 4ኛ. የጆርዳን ዲናር (አንድ የጆርዳን ዲናር በ1.41 ዶላር ይመነዘራል!) የጆርዳን ዲናር በ1950 የፓለስቲን ፓውንድን ከለወጠ ጀምሮ በመንግስት ውሳኔ ምንዛሬውን ያስተዳድራል! 3ኛ. የኦማን ሪያል (አንድ የኦማን ሪያል በ2.60 ዶላር ይመነዘራል!) የኦማን ሪያል የህንድን ሩፒ መገበያያ አድርጎ ይጠቀም ነበር ነገር ግን ከፍተኛ የነዳጅ ሃብትን ተከትሎ ከለወጠ ጀምሮ በመንግስት ውሳኔ ምንዛሬውን ያስተዳድራል! 2ኛ. የባህሪን ዲናር (አንድ የባህሪን ዲናር በ2.65 ዶላር ይመነዘራል!) የባህሪን ዲናር የአሜሪከ ዶላርን ተጨማሪ መገበያያ አድርጎ ይጠቀም ነበር ነገር ግን ከፍተኛ የነዳጅ ሃብትን ተከትሎ ከለወጠ ጀምሮ በመንግስት ውሳኔ ምንዛሬውን ያስተዳድራል! 1ኛ. የኪዌት ዲናር (አንድ የኩዌት ዲናር በ3.25 ዶላር ይመነዘራል!) የኪዌት ዲናር በ1960 ከተዋወቀ ጀምሮ ሀገሪቷ ካላት ከፍተኛ የነዳጅ ሃብት ጠንካራ ኢኮኖሚ እና ከታክስ ጫና የሆነ የንግድ አማራጭ ከመሆኑ በተጨማሪ መንግስት በውሳኔ ምንዛሬውን ያስተዳድራል! በውሳኔ ጠንካራ ከሆነው #የኪዌት_ዲናር እና ፍጹም የተረጋጋ ምንዛሬ ከሆነው #የሲዊዝ_ፍራንክ እስከ የዓለም ተጽኖ ፈጣሪው #የአሜሪካ_ዶላር የምንዛሬውን ሁኔታ ብንመለከት የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ፤ የፖለቲካ መረጋጋት፤ የተፈጥሮ ሃብት (መጠቀም)፤ የዓለም አቀፉ ገበያ ለምንዛሬዎቹ ያላቸው ፍላጎት የየሀገራቱን ገንዘብ አቅም እና ደረጃ ይወስናል፡፡ Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
የባንክ ተበዳሪ ነዎት? ወይም ለመበደር አስበዋል? እነዚህ አዲስ መመሪያዎች ይመለከትዎታል https://l.kphx.net/s?d=7825560790572949687&extra=Q1RSWT1FVCZMTkc9YW0=&g=1fb6378cb8972698a7ce9b641f6cd997 (From Phoenix APP)
Share '2024 exam model for 12.pdf'
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጅታል የባንክ ሥርዓት በጊዜያዊነት መቋረጥን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ መግለጫ ***** መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጅታል የባንክ ሥርዓት ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት የባንኩ መደበኛ አገልግሎቶች ለተወሰኑ ሰዓታት መቋረጣቸዉ ይታወቃል፡፡ እንደሚታወቀው ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ባንኮች በሥርዓቶቻቸዉ ላይ በየጊዜዉ የደህንነት ፍተሻ እንዲሁም የማሻሻያ ሥራዎችን ያከናዉናሉ፡፡ በሥርዓቶቹ ላይ በሚከናወን ለዉጦችና ፍተሻዎችም የባንኮች አገልግሎት አልፎ አልፎ ሊቋረጥ ይችላል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትናንትናው ዕለት የተከሰተዉ የአገልግሎት መቋረጥ ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ችግሩ ከተከሰተበት ሰዓት አንስቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የባንኩን እና የደንበኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። በመሆኑም የባንኩ መደበኛ አገልግሎቶች በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲጀምሩና ባንኩ ወደተለመደው እንቅስቃሴው እንዲመለስ ማድረግ ተችሏል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተከሰተዉ የአገልግሎት መቋረጥ ባንኩ በመደበኛነት በሥርዓቶቹ ላይ በሚያደርገዉ ማሻሻያና ፍተሻ ምክንያት የተከሰተ እንጂ የባንኩን፣ የደንበኞቹን እንዲሁም አጠቃላይ የፋይናንስ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ክስተት አለመሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ በችግሩ ምክንያት የተከሰቱ የደንበኞች መጉላላትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳቶችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስፈላጊዉን ምርመራ በማድረግ ወደፊት ለህብረተሰቡ የሚያሳዉቅ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት የሚጠቀሟቸዉን ሥርዓቶች ደህንነታቻዉ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና የደንበኞችን ፍላጎት የሚያሟሉ ስለመሆናቸዉ በየጊዜዉ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ በሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የሚገኙ የፋይናንስ ሥርዓቶች ደህንነቸዉ የተጠበቀ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት የፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም መቀጠል ይችላል፡፡ የፋይናንስ ተቋማትም የሥርዓቶቻቸዉን ደህንነትና ቀልጣፋነት ይበልጥ ለማሳደግ የቴክኖሎጂ ተለዋዋጭ ባህርይ በማየት በቀጣይነት መሥራት እንደሚኖርባቸዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጥብቅ ለማሳሰብ ይወዳል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አጠቃላይ የፋይናንስ ሥርዓቱ ደህንነት የበለጠ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ እና የተረጋጋ ሆኖ እንዲቀጠል አስፈላጊ እርምጃዎችንና የአሠራር ሥርዓት ማሻሻያዎችን መዉሰዱን ይቀጥላል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
የህዝብን የህይወት ለውጥ ከነፍስ ወከፍ ገቢ ባሻገር ማሰብ ያስፈልጋል! (የIMF: World Happiness Report, 2023፡ Looking beyond GDP)…… ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) በአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ ያሉ በአንድ ዓመት ውስጥ ለፍጆታ የወጣ ወጪ (Consumption) ለኢንቨስመንት የወጣ ወጪ (Investment) የመንግስት ጠቅላላ ወጪ (Government Expenditure) እንዲሁም ከውጪ ምርት ለማስገባት የሚወጣን ወጪ (Import) ለውጪ ምርት በማቅረብ ከሚገኝ ገቢ (Export) በማቀናነስ ያሰላል፡፡ የዛሬ 50 ዓመት በወቅቱ የአሜሪካ ሴናተር የነበሩት ሮበረት በጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) ላይ ጠንከር ያለ ትችት አቀረቡ እሱም “ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) ህይወትን ጠቃሚ ከሚያደርጉት ምክንያቶች በስተቀር ሁሉንም ነገር ይለካል“(GDP measures everything...except that which makes life worthwhile) የዚህ አይነቱ ትችት ጠቅላላ ሀገራዊ ምርትን በተለየ ሁኔታ ማሰብ ያስፈልጋል የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ፖሊሲ አውጪዎች የአንድ ሀገርን ነዋሪዎችን የህይወት ለውጥ ሁኔታን በጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ከማየት ይልቅ ዜጎች በህይወታቸው ደስተኛ ስለመሆናቸው መለካት መጀመር አለባቸው ከሚለው አመክንዮ በመነሳት በየዓመቱ ከተለያዩ መለኪያዎች በመነሳት የዓለም የገንዘብ ድርጅት የዓለም ህዝቦች የደስተኝነት ደረጃ (World Happiness Report) ያወጣል፡፡ የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን ለጠቅላላ ህዝቦች ሲካፈል የነፍስ ወከፍ ገቢ ስሌትን ይሰጣል (GDP per capita) ይህ ቁጥር እየጨመረ በመጣ ቁጥር በኢኮኖሚ የተሻለ ሀገር ወይም የተሻለ ኑሮ የሚኖሩ ዜጎች ያላት ሀገር በሚል ሲሰላ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን የነፍስ ወከፍ ገቢ (Per Capita Income) ወይም ዜጎች በዓመት የሚያገኙት ገቢ መጠንን ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ብቻ ለመውሰድ ከሞመከር ዜጎች ያላቸው ማህበራዊ ድጋፍ፤ የጤና ሽፋን፤ በህይወት የመኖራቸው እድሜ ጣሪያ፤ የመኖር እና የመናገር ነጻነታቸው፤ ደግነታቸው/ልግስናቸው፤ አነስተኛ ሙስና መኖር፤ ወዘተ የዜጎች የኑሮ ደስተኝነት መለኪያ አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል በሚል ወደተግባር ሀገራት ገብተዋል፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት የዚህ ዓመት የዓለም ሀገራት ዜጎች ያላቸውን የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን እና የደስተኝነት ደረጃ ምን እንደሚመስል ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ባለፈ ማሰብ ያስፈልጋል በሚል ርዕስ (Looking Beyond GDP) ሪፖርት አውጥቷል (World Happiness Report, 2023) ፡፡ ዜጎቿን ደስተኛ በማድረግ ቀዳሚዋ ሀገር ፊንላንድ ስትሆን የመጨረሻዋ ሀገር ደግሞ አፍጋኒስታን ሆናለች፡፡ በዓለም ዜጎቻቸውን ደስተኛ ያደረጉ ሀገራት ከ1 እስከ 10 በደረጃ ፊንላንድ፤ ዴንማርክ፤ አይስላንድ፤ እስራኤል፤ ኔዘርላንድ፤ ሲዊዲን፤ ሲዊዘርላንድ፤ ሉግዘምበርግ፤ ኒውዚላንድ እና ኦስትሪያ ሲሆኑ፤ በዓለም የዜጎቻቸው የደስተኝነት ደረጃ የመጨረሻዎቹ ሀገራት ከ1 እስከ 10 በደረጃ አፍጋኒስታን፤ ሊባኖስ፤ ሴራሊዮን፤ ዛምቢያ፤ ኮንጎ፤ ቦትስዋና፤ ማላዊ፤ ኮሞሮስ፤ ታንዛኒያ፤ እና ዛምቢያ ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ዜጎቻቸው ደስተኛ ከሆኑባቸው ሀገራት 14ኛ የሆነችው ሃያሏ ሀገር አሜሪካ (ዜጎች 76ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ላይ ደርሰዋል) ስትሆን ከመጨረሻዎች ሀገራት 14ኛላይ ደግሞ የተቀመጠች ኢትዮጲያ (ዜጎች 1ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ላይ ደርሰዋል) ነች፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ሪፖርት ለማነጻጸር እየሞከረ ያለው በጠቅላላ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ የሆነችው ሉግዘምበርግ (120ሺ ዶላር በላይ የነፍስ ወከፍ ገቢ) ነገር ግን ዜጎቿ በደስተኝነት መለኪያ በዓለም 9ኛ ናቸው፡፡ ዜጎቿ በደስተኝነት መለኪያ አንደኛ የሆኑላት ሀገር ፊንላንድ በነፍስ ወከፍ ገቢ (48ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ) ሲታይ በዓለም ላይ ከ20ኛ በታች ነች፡፡ ስለዚህ የዓለም የገንዘብ ድርጅት አመክንዬ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (የነፍስ ወከፍ ገቢ) በዘለለ መመልከት ይገባል (ዜጎች ያላቸው ማህበራዊ ድጋፍ፤ የጤና ሽፋን፤ በህይወት የመኖራቸው እድሜ ጣሪያ፤ የመኖር እና የመናገር ነጻነታቸው፤ ደግነታቸው/ልግስናቸው፤ አነስተኛ ሙስና መኖር፤ ወዘተ) ለማለት ነው፡፡ የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን በኑሮ ደስተኝነትን አይፈጥርም (IMF, 2023)! የዜጎችን በኑሮ ያላቸውን ደስተኝነት ከGDP እና ከነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን ለይቶ መመልከት ይገባል (IMF: Looking beyond GDP)! በ2023 ጠንካራ ኢኮኖሚ ኖሯቸው ዜጎቻቸው በደስተኝነት መለኪያ ዝቅተኛ የሆኑ ሀገራት ዝርዝር! በ2023 ደካማ ኢኮኖሚ ኖሯቸው ዜጎቻቸው በደስተኝነት መለኪያ የተሻሉ ሀገራት ዝርዝር! የኢትዮጲያ ዜጎች በኑሮ ያላቸው የደስተኝነት ደረጃ ከመጨረሻዎቹ መካከል ነው! የዚህን የIMF: World Happiness Report, 2023 ሪፖርት ንጽጽር ለመመልከት የሚከተለውን የትንታኔ ቪዲዮ Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል አማራጮች የ2 ነጥብ 8 ትሪሊየን ብር ግብይት ተፈጽሟል ተባለ አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በዲጂታል አማራጮች የ2 ነጥብ 8 ትሪሊየን ብር ግብይት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ። የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ዲቪዥን የመርቸንትና የኤጀንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር ብሌን ኃይለሚካኤል÷ በስድስት ወራት የዲጅታል ግብይት እንቅስቃሴውን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡ አሁን ላይ ከ12 ሚሊየን በላይ የኤ.ቲ.ኤም ካርድ ተጠቃሚዎች፣ ከ9 ሚሊየን በላይ የሞባይል ባንኪንግና ከ20 ሚሊየን በላይ ሲቢኢ ብር ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡ የዲጂታል አማራጮችን የሚጠቀሙ የባንኩ ደንበኞች ቁጥር በየዓመቱ ከፍተኛ እድገት እያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በተያዘው በጀት አመት ስድስት ወራት ከ494 ሚሊየን በላይ ግብይቶች በዲጂታል አማራጮች ተከናውነው የ2 ነጥብ 8 ትሪሊየን ብር ግብይት መፈፀሙንም ነው የተናገሩት። ግብይቱ ከአምናው ተመሳሳይ ውቅት ጋር ሲነፃፀር የ35 በመቶ እንዲሁም በገንዘብ መጠን የ118 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ አዳዲስ የዲጅታል አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ ለማቅረበ መዘጋጀቱንም ዳይሬክተሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ የዲጂታል ባንኪንግ ደንበኞች ጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ሳይኖር በእጅ ስልክና በካርድ አማካኝነት አገልግሎት የሚያገኙበት ስርዓት መሆኑ ይታወቃል። Don't forget share and forward ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ በጎነት ነዉ በማናቸውም የኢኮኖሚኪስና ቢዝነስ ተያያዥ ጉዳዮች የምርምር ፕሮጀክትና የቢዝነስ እቅዶች እናማክራለን። ኢኮኖሚክስንና ተያያዥ ኮርሶችን በፈለጉት እርዕስ ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ online እናስተምራለን @SC2021bot 🇪🇹 @EconomistET🇪🇹 https://t.me/+cUVKDewqGixiN2Rk