Ethio Sigma
Статистикаለአስተያየት እና ለማንኛውም ማስታወቂያ @li_ethio @Ybwaver ይሄ የኢትዮጵ የሲግማ ቻናል ነው በዚህ ቻናል 👇 አነቃቂ ንግግሮች እና ቪዲዮዎች ለአላማ እንዴት መታገል እንዳለብን እና ሌሎችንም ለማድረግ የሚረዱ ጹፉፎች ወደምንለቅበት ቻናል እንኳን ደና መጣችሁ 😈
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- Категория
- Криптовалюты (по похожим)
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 199
- 1/48двое суток
- 228
- 1/72трое суток
- 245
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
. Matrix . አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ደስ የሚል አስገራሚ ህይወት ተኝታችሁ በህልማችሁ ኑሩ ግን በፍፁም ከዛ ህልም አትነቁም እና ምረጡ ብትባሉ የመጀመሪያ ምርጫ ደስ የሚል ህይወት ነው አንተ መኖር የምትፈልገው ህይወት ነው ሁሉም ነገር እውነት ነው የሚመስልህ ግን ሁሉም ነገር ውሸት ህልም ነው ሰዎቹም የምትኖረውም ህይወት የሉም ተኝተሀል ህልም ነው ግን በፍፁም አትነቃም ያ ማለት ደግሞ እስካልነቃህ ድረስ ህልም መሆኑን እና አለመሆኑን አናቅም ለዛ ለኛ እውነት ነው ። ሁለተኛው እውነተኛ አለም ነው ግን አስቀያሚ ህይወት ነው ያለህ እዚህ የቱ ትመርጣለህ/ጫለሽ በውሸት አለም ውስጥ እውነት መስሎህ ደስ የሚል ህይወት መኖር ወይም በእውነት አለም ውስጥ አስቀያሚ ህይወት መኖር ? ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
ቦታህን እወቅ ..... አንድ አባት ከሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ልጁን እንዲህ ሲል ተናገረው "ይህ የእጅ ሰዓት አባቴ የሰጠኝ ነው፤ 200 ዓመታት ሆኖታል። ነገር ግን ላንተ ከመስጠቴ በፊት ሂድ እና ሰዓት ቤቶች ስንት ሊገዙህ እንደሚችሉ ጠይቀህ ና" አለው። ልጁም ጠይቆ መጣ እና "አሮጌ ስለሆነ 5 ብር እንገዛሃለን" እንዳሉት ነገረው። አባቱም ድጋሚ ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቆች ጋር ሄዶ እንዲጠይቅ ይነግረዋል። ልጁም ጠይቆ ይመጣ እና አሁንም ከ5 ብር በላይ እንደማይገዙት ይነግረዋል። "ሙዚየም ሄደህ ጠይቅ" ይለዋል አባቱ። ልጁም ጠይቆ ከመጣ በኋላ "አንድ ሚሊዮን ብር እንደሚገዙኝ ነገሩኝ" አለ። አባቱም "እንድታውቅ የፈለኩት የአንተንም ትክክለኛ ዋጋ (ቦታ) የሚሰጥህ ትክክለኛ ቦታ ላይ እንድትገኝ እንጂ የተሳሳተ ቦታ ላይ ሄደህ ሳይሳካልህ ሲቀር እንዳትናደድ ነው። ምንጊዜም ያንተን ዋጋ የሚያውቁ ብቻ ናቸው ክብርም አድናቆትም የሚሰጡህ ስለዚህ የተሳሳተ ቦታ ላይ አትገኝ!! ውድ እቃ ያለ ቦታው ርካሽ ነው::🫱🏻🫲🏼 ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
ሰዎች ብቻቸውን መሆን ይፈራሉ ፣ ነገር ግን እኛ ዋጋ ከሌላቸው ሰዎች ጋር ጊዜያችንን እንደገና እንዳናጠፋ እንፈራለን። ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
. ስኬት ምትክ ያስፈልገዋል . • አልኮል —> ውሃ • አለመሳካት -> መማር • ከመጠን በላይ ማሰብ -> ድርጊት • ተጠያቂነት -> ኃላፊነት • መርዛማ ጓደኞች —> አማካሪ • NETFLIX —> እንቅልፍ • አነቃቃ —> ዲሲፕሊን ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
አሁን ጀምር ! ከአሁን ጀምሮ ራስህ ላይ ብትሰራ በዚህ አለም የሚኖርህን ቀሪ ቆይታ ማሳመር ትችላለህ፤ ስለማትቀይራቸው ነገሮች አብዝተህ ማሰብ አቁም! ትናንትን መቀየር አትችልም፤ ዛሬን መጠንከር ከዛ ነገህን ማሳመር ትችላለህ። ወዳጄ ለምንም ነገር አልዘገየህም አጥብቀህ የምትፈልገውን ነገር አሁን ጀምረው! ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
የታላቁ እና የምንግዜም የእግርኳስ ንጉስ 🐐 ሊዮናል ሜሲ አድናቂዎች ቻናል ተከፍቷል ተቀላቀሉ 👉 @Leo_got_10 👉 @Leo_got_10
📌 መቼም ቢሆን እጅ አትስጥ ✓ በወደቅክ ቁጥር ተነስ ✓በተሳሳትክ ቁጥር አስተካክል። ✓ባልተሳካልህ ቁጥር እንደገና ሞክር። ✓ ህይወት ልታሳዝንህ በሞከረች ቁጥር በግድም ቢሆን ፈገግ በል፡፡ ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
አንድ ደራሲ 'የክፍለ ዘመናችን ትልቁ ግኝት ሰዎች አስተሳሰባቸውን በመቀየራቸው ብቻ ህይወታቸውን መቀየር መቻላቸው ነው' ብሏል። ከ 100 ዓመት በፊት ቢሆን የኖርነው ህይወታችን እንዲቀየር ወይ የነገስታት ዘር መሆን አለብን ወይ ደግሞ ወንድ ልጅ የግድ ጀግና መሆን አለበት፣ ሴት ልጅ ደግሞ ውብ መሆን አለባት ህይወቷን ለመቀየር። ይህ ዘመን ግን በአስተሳሰባችን ብቻ ራሳችንን ከፍም ዝቅም ማድረግ እንችላለን። ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
ተነስ አድርገው! ትናንሽ የምትላቸውን ተግባራት አትናቃቸው! 5 ደቂቃ መፀለዩ ወይ 10 ደቂቃ ስፖርት መስራቱ ቀላል ይመስላል፤ ግን ትልቁን ጋን የሚደግፈው ትንሹ ጠጠር ነው። ነገ አደርገዋለው ምን ችግር አለው አትበል! ቸልተኝነት ዋጋ ያስከፍልሀል፤ ስለዚህ ተነስና ያሰብከውን አድርግ! ከዛ የአይምሮ ሰላም ታገኛለህ። ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
መቼም አናቆምም! በየቀኑ በጥረትህ የምትገነባው እንጂ በድንገት ከሰማይ የሚወርድ ስኬት የለም። ራሳችንን ለማሳደግ ትናንሽ ነገሮችን በየጊዜው እየጨመርን ከሄድን ይሄን የምናነብ ሁሉ ከፍታው ላይ እንገናኛለን! እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በሂደት እንጂ በድንገት አይደለም! ስለዚህ የጀመርነውን በጠዋት መነሳት፣ ስፖርት፣ ማንበብ እና ገንዘብ ማስቀመጥ መቼም አናቆምም! ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
የትልቅ ስኬት መነሻ ጥልቅ ፍላጎት ነው! ይሄን ሁሌም በአይምሯችን ማሰብ አለብን፤ ብዙም ያልተቀጣጠለ እሳት ብዙ ሙቀት እንደማይሰጠን ሁሉ ደካማ ፍላጎትም ደካማ ውጤት ነው የሚሰጠን። ሁሌም የማይበርድ ፍላጎት የማይቋረጥ ፅኑ መሻት ያስፈልገናል። ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
ውሻ በሰፈሩ አንበሳ ነው ፣ አንበሳ ግን የትም አንበሳ ነው 😈 ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
ጥያቄው ትችላለህ ወይስ አትችልም አይደለም ! ዋናው ጥያቄ እየሞከርክ ነው ወይ የሚለው ነው!!!! እየሞከርክ እስከሆነ ድረስ ከብዙዎቹ ቁጭ ካሉት ሰዎች የተሻልክ ነህ 😈💪 ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
🇪🇹ወጣ ወጣ ወጣ 👏👏👏 💥 አፊኒ 2026 🍿 ✅ በአማርኛ ፊልም ቻናላችን ተለቋል 👉 https://t.me/Amahregna_film
ሰዎች ምክንያት እየፈለጉ ጥፋተኛ ካደረጉህ ሊርቁ እንደፈለጉ እየነገሩህ ነዉ ነቃ በል ! ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
ሰዎች ምክንያት እየፈለጉ ጥፋተኛ ካደረጉህ ሊርቁ እንደፈለጉ እየነገሩህ ነዉ ነቃ በል ! ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
በህይወትህ እነዚህ 3 ነገሮች ሁሌም መርሳት የለብህም !👇😈 1. ሰዎች አንተ ላይ ሊቀየሩብህ እና ሊከዱህ ይችላሉ ። 2. ሰዎች ይሄዳሉ ሰዎች ይመጣሉ። 3. አብዛኛው ሰው እስከመጨረሻው አብሮህ አይቆይም። ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
ራስን ማስቀደም ራስ ወዳድነት አይደለም! አስፈላጊ ነገር ነው! ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
የግንባር እንቅስቃሴ እና የውስጥ ምስጢር አንድ ሰው ቃላቱን በጥንቃቄ መርጦ ሊዋሽህ ይችላል፤ ነገር ግን ግንባሩ ላይ የሚታዩት መስመሮች እና ጡንቻዎች የውስጥ ጭንቀቱን፣ ፍርሃቱን ወይም ተንኮሉን አሳልፈው ይሰጣሉ። ግንባር የአንድ ሰው አእምሮ "ስክሪን" እንደመሆኑ መጠን፣ ግለሰቡ በንቃተ-ህሊናው ሊቆጣጠራቸው የማይችላቸውን ስሜቶች ፍንጭ ይሰጣል። በዳርክ ሳይኮሎጂ እና በሰዎች ማንነት ንባብ ውስጥ ስለ ግንባር ልታውቃቸው የሚገቡ 10 ነጥቦች፦ 1. የግንባር መስመሮች ድንገት መታየት (Sudden Furrowing): አንድ ሰው እያወራህ እያለ በድንገት ግንባሩ ላይ መስመሮች ከታዩ፣ የሚናገረው ነገር ከውስጥ ስሜቱ ጋር እየተጋጨ መሆኑን ያሳያል። ይህ ምናልባት ታሪኩን ለመፍጠር እየተጨነቀ መሆኑን ወይም ያቀደው ሴራ እንዳይነቃበት መፍራቱን ያመለክታል። 2. ቅንድብን ወደ ላይ መስቀል (Raised Eyebrows in Deception): ሰዎች ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ለማሳመን ሲጥሩ ወይም "የዋህ" ለመምሰል ሲፈልጉ ቅንድባቸውን ወደ ላይ ይሰቅላሉ። በዳርክ ሳይኮሎጂ ይህ "የማሳመኛ ስልት" (Persuasion Tactic) ተብሎ ይታወቃል፤ ግለሰቡ እውነቱን ሳይሆን አንተ እንድታምነው የሚፈልገውን ምስል እየሳለ መሆኑን ይጠቁማል። 3. ግንባርን መጥረግ ወይም መነካካት (The Forehead Rub): ውሸት በሚነገርበት ጊዜ አእምሮ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ስለሚገባ የግንባር ሙቀት ይጨምራል። ግለሰቡ ሳያውቀው ግንባሩን በጣቶቹ ሲያሽ ወይም ላቡን ሲጠርግ ካየኸው፣ ንቃተ-ህሊናው ከውጥረቱ ለመገላገል የሚያደርገው ጥረት ነው። 4. የግንባር ጡንቻዎች መወጠር (Micro-tension): አንድ ሰው ፈገግ እያለ ግንባሩ ግን የተወጠረ ከሆነ፣ ፈገግታው የውሸት (Masking) መሆኑን ማወቅ ትችላለህ። እውነተኛ ደስታ የግንባር ጡንቻዎችን ያዝናናል። 5. የ"አቀባባይ" ምልክት (The Flash of Recognition): አንድን መረጃ ደብቆ ሊያታልልህ የፈለገ ሰው፣ ያንን ጉዳይ ስታነሳበት ግንባሩ ላይ የሚታይ ቅፅበታዊ መኮማተር (Micro-expression) እውነቱን እንደሚያውቅ ያረጋግጥልሃል። 6. ግንባርን ወደ ፊት ማቅረብ (Intimidation Lean): በዳርክ ሳይኮሎጂ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ግንባራቸውን በትንሹ ወደ አንተ በማዘንበል የበላይነታቸውን ለማሳየት ይሞክራሉ። ይህ "የግዛት ምልክት" ሲሆን፣ አንተን ለማስፈራራት ወይም ሃሳብህን ለመቆጣጠር የሚጠቀሙበት መንገድ ነው። 7. በአንድ ወገን ብቻ የሚታይ መስመር (Asymmetrical Brow): አንድ ሰው ግንባሩን በአንድ ወገን ብቻ የሚሰበስብ ከሆነ፣ የሚናገረውን ነገር በራሱ እየተጠራጠረ መሆኑን ወይም አንተን ዝቅ አድርጎ እያየህ መሆኑን (Contempt) ያሳያል። 8. አይንን ከግንባር ጋር ማዋሃድ (The Focused Glare): ውሸታሞች ግንባራቸውን ሳያሸበሽቡ ትኩር ብለው ካዩህ፣ አእምሯቸው ሙሉ በሙሉ ውሸቱን "ፕሮሰስ" በማድረግ ላይ መሆኑንና ሌላ እንቅስቃሴ እንዳያሳዩ ራሳቸውን እየተቆጣጠሩ መሆኑን ይጠቁማል። 9. የጥያቄ ምልክት ግንባር (The Skeptical Brow): እያወራህ እያለ የግለሰቡ ግንባር ወደ መሃል ከተሰበሰበ፣ የሚነግርህ ነገር ቢኖርም በውስጡ ግን አንተን እየገመገመህ እና ቀጣይ ጥቃቱን እያሰላ መሆኑን መረዳት ትችላለህ። 10. ግንባርን መሸፈን (Protective Shielding): አንድ ሰው እያወራህ እጁን ግንባሩ ላይ ካስቀመጠ፣ እውነታውን ከመናገር ይልቅ ራሱን ከጥያቄህ እየተከላከለ መሆኑንና መረጃ እየደበቀ መሆኑን የሚያሳይ የ"ተከላካይነት" (Defensive) ባህሪ ነው። እነዚህን ጥቃቅን የግንባር እንቅስቃሴዎች ማስተዋል ስትጀምር፣ ሰዎች በንግግራቸው ሊገነቡት የሚፈልጉትን ግንብ አፍርሰህ ውስጣቸውን ማየት ትችላለህ። በዳርክ ሳይኮሎጂ አለም፣ ትልቁ እውነት ያለው ካልተነገሩ ምልክቶች ጀርባ ነው። ➡️ @Ethio_sigmaboy ➡️ @Ethio_sigmaboy
без подписи