- Последний пост
- 11 дек. 2024 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ለገሰ ሥዩም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን መገደላቸው ተሰማ❗️ ከፖሊስ አዛዡ በተጨማሪ የወረዳው የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ሲሳይ በሻዳ ተመትተው ጫንጮ ሆስፒታል መግባታቸውን ሰምተናል፡፡ በጥቃቱ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አንድ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል በድምሩ አራት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ዋዜማ ማረጋገጧን ገልፃለች። አማጺ ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን ጠዋት 3 ሰዓት አካባቢ ልዩ ስሙ ሮብ ገበያ በተባለ ስፍራ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ ፖሊስ አዛዡና የጸጥታ ኃይሎቹ ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊው ወደ ጫንጮ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተገልጿል። አማጺ ቡድኑ <<የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለናል>> በማለት ቀድመው ማሳወቃቸውን ተከትሎ አመራሮቹና የጸጥታ ኃይሎቹ ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ተጠቁሟል። ሆኖም በስፍራው ሲደርሱ በአማጺ ቡድኑ በኩል በተከፈተባቸው ድንገተኛ የእሩምታ ተኩስ የፖሊስ አዛዡና የጸጥታ አባላቱ ሕይወታቸው ማለፉን ምንጮች ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ አመራሮቹ ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ፓትሮል ተሽከርካሪ አቃጥለው ከጥቅም ውጪ ማድረጋቸውንም ተሰምቷል። ድርጊቱ የተፈጸመው የክልሉ መንግሥት በቅርቡ ከአማጺ ቡድኑ አንድ ክንፍ ጋር አደረኩት ባለው የሠላም ስምምነት በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እየገቡ እንደሆነ እየተገለጸ ባለበት ወቅት ነው። ዘገባው የዋዜማ ራዲዮ ነው። https://t.me/Ethiojournal11
ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት። አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ነው የሾመው። ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል። " ጊዜያዊ አስታዳደሩ በተቋቋመበት ህግ እና አሰራር መሰረት ወደ ስራ ገብቻለሁ አሁን ላይ በፅ/ቤት ስራ ርክክብ እያደረኩ ነው " ብለዋል። ዛሬ ደግሞ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ዓዲግራት ከተማ በተካሄደ የም/ቤት ጉባኤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩትን ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አቶ ረዳኢ ሹመቱን አረጋግጠዋል። " TPLF ተወዳድሮ በተመረጠበት ትግራይ እስካሁን ያለው የTPLF ም/ቤት አባላት ናቸው ፤ እኔም እንደ TPLF አንድ አካል ተወካይ ሆኜ ነው የቀረብኩት " ሲሉ ሹመቱ በም/ቤት እንደፀደቀላቸው ተናግረዋል። አቶ ዓለም ስለ ረዳኢ ሹመት የማውቀው የለም ብለዋል። " በምክር ቤት ስለተደረገው ሹመት በማህበራዊ መገናኛ ነው ያየሁት በይፋ በመንግሥት መዋቅር አልሰማሁም " ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ረዳዒ ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ሹመት ምንም ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል። " ሹመት እንደተሰጠው ሰምቻለሁ ያው ትግራይም ኢትዮጵያም ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አካሄዳችን የአንድ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አስተዳደር የራሱ ምክር ቤት አለው ምክር ቤቱ ነው ከንቲባም ፣ የወረዳ አስታዳዳሪም ፣ ካቢኔም የሚያፀድቀው በዚህ ም/ቤት ያላለፈው ከንቲባ ወይም አስተዳዳሪ የመሆን እድል የለውም " ብለዋል። " እንደ ድርጅት ከምክር ቤት ውጭ ከመጣ ተቀባይነት አለው ብዬ አላምንም እንደ ህወሓት አቋማችን ይሄው ነው " ያሉት ረዳኢ ከምክር ቤት ውጭ ማንም ሰው ደብዳቤ እየፃፈ የሚሾመው ተቀባይነት የለም ሲሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሰጠውን ሹመት አጣጥለዋል። ትላንት በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ የወረዳና የከተማ ም/ ቤቶች አብላጫው መቀመጫ በህወሓት በመያዙ ከባለፈው ጉባኤ በኃላ የአመራር ማስተካከያ እያደረግን ነው ብለው ነበር። የጊዛያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመመራው ቡድን ጊዜያዊ አስታዳደሩን ስራ አላሰራ እንዳለና የወረዳና የከተሞች ም/ቤቶችን በመጠቀም በመንግሥት የተመደቡ አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ መሆኑን ይህም መፈንቅለ መንግሥት እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል። የዚህ መረጃ ባለቤት ቪኦኤ ሬድዮ ነው። https://t.me/Ethiojournal11
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከሄዝቦላህ ጋር የተጀመረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳብ "በመርህ ደረጃ" መቀበላቸው ተሰማ! እሁድ ምሽት ከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት የፀጥታ ምክክር ሀሳቡን በ "በመርህ ደረጃ" ማፅደቃቸውን ሲኤንኤን ጉዳዩን ያውቃሉ ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል፡፡በዛሬው እለት ለሊባኖስ መንግስት ይተላለፋል ተብሎ በሚጠበቀው የስምምነት ሰነድ ላይ እስራኤል ያላትን የሀሳብ ልዩነቶች እንደምታንጸባርቅ ነው የተነገረው፡፡ ምንም እንኳን ቴልአቪቭ እንዲስተካከሉ የምትፈልጋቸው የሰነዱ ሀሳቦች ካልተስተካከሉ ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ መቀበሏን ማረጋገጫ ባይሆንም ከበርካታ ወራት በኋላ ለስምምነት የቀረበው ሰነድ ይህኛው እንደሆነ ተገልጿል፡፡የተኩስ አቁም ስምምነት ለፊርማ ከመቅረቡ በፊትም በሀገሪቱ የካቢኔ ምክር ቤት መጽደቅ ይኖርበታል፡፡ ”በቀጠናው የአሜሪካ ልዩ ልዑክ አሞስ ሆይስተን ባለፈው ሳምንት በቤይሩት ባደረጉት ንግግር “በእስራኤል እና በሄዝቦላህ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ለፍጻሜ ቀርቧል፤ ነገር ግን ለስኬታማነቱ የሁለቱን ተደራዳሪዎች በጎ ፈቃድ ይፈልጋል” ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የሊባኖሱ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ እና የፓርላማ አፈጉባዔው ናቢህ በሪ ከሄዝቦላህ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ገንቢ እና ክፍተቶቹን ማጥበብ የሚያስችል ውይይት አካሄድዋል ነው ያሉት፡፡ልዩ ልኡኩ አሞስ ሆይስተን በድርድሩ የመጨረሻ ሂደቶች ዙርያ ለመምከር በመጪው ረቡዕ ወደ ሊባኖስ እንደሚያቀኑም ተዘግቧል፡፡በአሜሪካ የሚደገፈው የሰላም ስምምነት ሀሳብ ለ60 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም በማስተግበር ዘላቂ የሆነ ጦርነት ማስቆምን ተፈጻሚ ማደረግ አላማው አድርጓል፡፡(alain) https://t.me/Ethiojournal11
Update 11 ሞት ከ40 በላይ ጉዳት‼ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ ወረዳ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ታውቋል። 📌አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው። 📌የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሥራ ሒደት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ዘውዴ በአደጋው እስካሁን የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል ብለዋል። 📌በተጨማሪም በ40 ሰዎች ላይ ከባድ እና 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። 📌ዛሬ ጠዋት 2:30 ላይ በተከሰተው አደጋ የተጎዱ ሰዎች በሰንዳፋ ሆስፒታል ሕክምና እተከታተሉ እንደሚገኙም አመልክተዋል ሲል ፋና መረጃውን አጋርቶ ተመልክተናል።ለሟች ቤተሰቦች መፅናናቱን ይስጥልን:ጉዳት የደረሰባችሁም አላህ ምህረቱን ያቅርብላችሁ:https://t.me/Ethiojournal11
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#Update " ተገደን እንጂ ወደን የገባነው ጦርነት የለም ፤ በDDR አሰራር ወደ ህዝባችን ለመቀላቀል ፍቃደኞች ነን ሁሌም ምርጫችን ሰላም ነው " - ተመላሽ ታጣቂዎች የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የዲሞብላይዜሽን እና መልሶ ማቋቋምያ ስነ-ሰርዓት በትግራይ መቐለ በይፋ ተጀምሯል። ቅዳሜ ህዳር 14/2017 ዓ.ም በይፋ በተከናወነው የዲሞብላይዜሽን እና መልሶ ማቋቋምያ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓተ የክልሉ እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎች ተገኝተው ነበር። የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በDDR የሚታቀፉ የትግራይን ጨምሮ በስድስት የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ ታጣቂዎች በሁለት ዓመት ውስጥ ዴሞብላይዝ በማድረግ ወደ ህዝቡ እንዲቀላቀሉ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ተገልጿል። የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ምን አሉ ? ትጥቅ መፍታትና ዴሞብላይዜሽን (DDR) ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነቶች ዋነኛ እና ጎልቶ የሚጠቀስ ነጥብ ቢሆንም በሃብት እጦት ምክንያት መዘግየቱ ተናግረዋል። በትግራይ ጦርነት የተሳተፉ 274,800 ታጣቂዎች በDDR ዴሞብላይዝ ሆነው በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ህዝብ ይቀላቀላሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፦ 👉 በአንድኛ ዙር 75 ሺህ 👉 በሁለተኛ 100 ሺህ 👉 በሦስታና ዙር 53 ሺህ 800 👉 በአራተኛ ዙር 46 ሺህ እንደሆነ አብራርተዋል። በተካሄደው እጅግ አሰቃቂ ደም አፋሳሽ ጦርነት " በርካታ ህይወት ተቀጥፈዋል ፣ አካል ጎድሏል የሀገር እና የህዝብ ሃብት ወድመዋል " ያሉት አቶ ተመስገን ይህ እንዳይደገም እንደ ሀገር እና ህዝብ በቁርጠኝነት መስራት አለብን ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል። የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳን ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? DDR ቀድሞ መደረግ የነበረበት ቢሆንም፤ ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆን ሃብት ለማሰባሰብ ነው የዘገየው ፤ የዘገየም ቢሆን ዛሬ መጀመሩ ለሰላም ያለው ትርጉም ትልቅ ነው ብለዋል። ተፈናቃዮች ባልተለመለሱበት፣ የትግራይ ሉኣላዊ ግዛቶች ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ባሉ የሀገር ውስጥና የውጭ ታጣቂዎች ተይዞ ባለበት ወቅት DDR መጀመሩ ከስጋት ወጪ ሆኖ እየተፈፀመ ባይሆንም ሁኔታዎች እየተስተካከሉ ይሄዳሉ ከሚል ተስፋ ድጋፋችን መስጠት እንቀጥላለን ሲሉ ገልጸዋል። የDDR መተግበር የትግራይ ሰላም መቀጠል ከሀገር ሰላም መፅናት ተያይዞ መታየትና መፈፀም እንዳለበት የፌደራል መንግስት እና ለጋሾች ትኩረት አደርገው ደጋፋቸው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅብረዋል። የተሰናባች ታጣቂዎች ተወካይ ነጋሽ ገ/ዮሃንሰ ምን አሉ ? " ተገደን እንጂ ወደን የገባነው ጦርነት የለም ፤ ስለሆነም የነበረው ችግር በጠረጴዛ ውይይት መፍታት ከተቻለ ትጥቅ አንግበን የምንኖርበት ፍላጎት ስለሌለን በDDR አሰራር ወደ ህዝባችን ለመቀላቀል ፍቃደኞች ነን " ብለዋል። ታጣቂዎች " የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ምርጫችን ሰላም ነው የተሟላ ሰላም እንዲሰፍን አሁንም ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጪ በትግራይ መሬት ያሉ ታጣቂዎች ለቀው እንዲወጡ ለፌደራል መንግስት እና ለአደራዳሪዎች እንጠይቃለን " ሲሉ ተናግረዋል። " ለቀድሞ ታጣቂዎች ለማቋቋምያ የተመደበው በቂ ስላልሆነ ቀጣይ የሆነ ድጋፍ እንሻለን " በማለትም ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራሮች ተገኝተው ነበር። #TikvahEthiopiaFamilyMekelle Photo Credit - DW @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
" አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የተሰጠ ውክልና የለም " - ሚኒስቴሩ " ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል " በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች እየተላለፉ እንደሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳውቋል። እየተለለፉ ባሉት ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች ህብረተሰቡ ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየተዳረገ መሆኑን አመልክቷል። በመሆኑ " መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራሁ ነው " ብሏል። በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን አሳውቋል። ሚኒስቴሩ ፥ " ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን " ብሏል። የሁለትየሽ ስምምነት የተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት በ lmis.gov.et ላይ መመልከት እንደሚቻል ገልጿል። @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
#ኢትዮጵያ " ' ወደ ውጪ እንልካችኋለን ' በሚል ምክንያት ' ተጭበርብረናል ፣ ተዘርፈናል ' እያሉ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሰዎች ተበራክተዋል " - የአ/አ ፍትህ ቢሮ አሁን አሁን በኢትዮጵያ በርካታ ሰዎች በተለይም ወጣቶች ወደ ውጭ ሀገራት የመሄድ ፍላጎታቸው እየተበራከተ መጥቷል። እኚህ ወጣቶች ከሀገር ለመውጣት የተለያዩ ሙከራዎችንም ሲያደርጉ ይታያል። የውጭ ጉዞ ለማድረግ ከሚሞክሩባቸው አንዱ መንገድ ደግሞ በደላሎች ፣ በጉዞ ወኪሎች እና በሌሎችም አማካኝነት ነው። ወጣቶች በትምህርት ፣ በስራ እንዲሁም በጉብኝነት አማካኝነት ነው ከሀገር ለመውጣት የሚጥሩት። የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ፣ አፍላ የሆነ የወጣትነት እድሜያቸው ሳያልፍ አንዳች ነገር አፍርተው ቤተሰብ መስርተው ጥሩ ኑሮ ለመኖር ፤ ከድህነት ለመላቀቅ ሲሉ በሚሞክሯቸው የውጭ ሀገር እድሎች ግን ምንም ርህራሄ በሌላቸው አጨበርባሪዎች ሲታለሉም ይታያል። የወጣቶቹን ፍላጎት እያየ ገንዘባቸውን የሚበላቸው ፣ አውሮፓና አሜሪካ ብሎ ሌላ የወንጀልና ደህንነት የሌለው ቀጠና የሚልካቸው ደላላ፣ ወኪል እየበዛ መጥቷል። በመዲናችን አዲስ አበባ ህገወጥ ስራን የሚሰሩ የጉዞ ወኪሎች መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ለአሃዱ በሰጠው ቃል ፤ በየጊዜው የውጪ ሀገር የጉዞ ወኪልና አማካሪ ድርጅቶች እንዲሁም ደላሎች " ወደ ውጪ እንልካችኋለን " በሚል ምክንያት ' ተጭበርብረናል፣ ተዘርፈናል ' እያሉ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሰዎች መበራከታቸውን አስታውቋል፡፡ እነዚህ ቅሬታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸው ተመላክቷል። " እነዚህን ቅሬታዎች ተሰምተዉ ዝም የሚባልበት አግባብ የለም " ያለው ቢሮ በቀጥታ ለአዲስ አበባ እና ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በመላክ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እየሰራሁ ነው ብሏል። " በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ሰዎች ፍላጎት መበራከቱን ተከትሎ፤ ዜጎች ከሕግ ውጪ በሚሰሩ ድርጅቶችና ደላሎች አማካኝነት ረብጣ ገንዘባቸውን መጭበርበራቸው እየተባባሰ ይገኛል " ነው ያለው። በብዙዎች ጥቆማና ቅሬታ መሰረት፤ ከዚህ ቀደም ከ40 በላይ ሕገ-ወጥ ሥራን በመስራት የተሰማሩ የውጪ ሀገር የጉዞ ወኪሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ቢሮው አመልክቷል። ፍትህ ቢሮ ፤ " ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ ወደ ውጪ ለመውጣት ሲፈልግ፤ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሕጋዊ የሆኑ ወኪሎችን ለይቶ ስላሰራጨ፤ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ማግኘት ይችላል " ብሏል። አልያም በአካል ቀርቦ መረጃ እንዲያገኝ ለአሃዱ በሰጠው ቃል አሳስቧል። #ኢትዮጵያ #የውጭሀገራትጉዞ #ወጣቶች @tikvahethiopia
ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተባለ በሰዓት ከ12 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛል የተባለው ይህ አዲስ ሚሳኤል ለመምታት አስቸጋሪ እንደሆነም ተገልጿል ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተብሏል።፡ አሜሪካ እና ሌሎች የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን መስጠታቸውን ተከትሎ ኪቭ ሞስኮን ከሰሞኑ አጥቅታለች፡፡ ይህን ተከትሎ ሩሲያ “ኦሬሽኒክ” በተሰኘ አዲስ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ዩክሬንን መታለች፡፡ እንደ ሩሲያ መከላከያ መግለጫ ከሆነ ወደ ዩክሬን የተተኮሰው “ኦሬሽኒክ” ሚሳኤል በዲንፒሮ የሚገኘውን የሚሳኤል ማምረቻ እና የጦር መሳሪያ መጋዝንን አጥቅቷል፡፡ የአሜሪካ ጦር በዚህ ሚሳኤል ዙሪያ እንደገለጸው ሚሳኤሉ አዲስ እና አህጉር አቋራጭ፣ የኑክሌር አረር መሸከም የሚችል ነው ብሏል፡፡ ሩሲያ ሚሳኤሉን የተኮሰችው ለሙከራ ጭምር እንደሆነ ያሳወቀው የአሜሪካ ጦር ሚሳኤሉ በቀጣይ የመሻሻል አቅም እንዳለው እና ሞስኮ ይህንን ሚሳኤል በብዛት ሊኖራት እንደሚችልም ገልጿል ሩሲያ ወደ ዩክሬን አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል መተኮሷ የተነገረው የብሪታንያ ጦር በበኩሉ የሩሲያ አዲሱ ሚሳኤል አውሮፓን ኢላማ ለማድረግ ተብሎ የተሰራ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ከደቡባዊ ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተተኮሰው ይህ ሚሳኤል ብሪታንያ ለመድረስ 19 ደቂቃ፣ ጀርመን ለመድረስ 14 እንዲሁም ፖላንድ ለመድረስ 8 ደቂቃዎች በቂ መሆናቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በ40 ደቂቃዎች ውስጥ በአሜሪካ ያሉ ኢላማዎችን መምታት እንደሚችልም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ T.me/ethio_mereja ኢትዮ-መረጃ
የአባቷን ገዳይ ለመያዝ የፖሊስ አባል የሆነችው እንስት ከ25 አመታት በኋላ ገዳዩን በቁጥጥር ስር አዋለች!! የአባቷን ገዳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስን የተቀላቀለችው ብራዚላዊት እንስት ከ25 አመታት በኋላ ገዳዩን በቁጥጥር ስር አውላለች፡፡ ጥር 16፣ 1999 ከዛሬ 25 አመት በፊት ቦአ ቪስታ በተባለ የብራዚል ከተማ ውስጥ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ጊቫልዶ ጆሴ ቪሴንቴ የተባለው ሰው በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ያልፋል፡፡ሬይሙንዶ አልቬስ የተባለው ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ ሟቹ የነበረበትን 150 ሪልስ የብራዚል ገንዘብ መልስልኝ በሚል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ግጭት ያድጋል፡፡ቀጥሎም ገዳዩ መጠጥ ቤቱን ትቶ ከወጣ ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ ሽጉጥ ታጥቆ በመምጣት የአምስት ልጆች አባት የሆነውን ጊቫልዶ ቬሴንቶ ጭንቅላቱ ላይ ተኩሶ ገድሏል፡፡ በወቅቱ በአፋጣኝ ከአካባቢው የተሰወረው ገዳይ በስሙ የፖሊስ ማደኛ ቢወጣበትም ፖሊስ የተለያዩ ክትትል እና ማጣርያዎችን ቢያደርግም ሊይዘው አልቻለም፡፡ በጊዜው የ9 አመት እና የቤተሰቡ የመጀመርያ ልጅ የሆነችው ታዳጊ ለአመታት በፍትህ ማጣት ሲብሰለሰሉ የኖሩ ቤተሰቦቿ ሁኔታ በአዕምሯ ውስጥ ተቀርጾ አደገች፡፡ ጂስሊየን ሲልቫ ዴዲውስ የተባለችው ብራዚላዊት የአባቷን ሞት ተከትሎ አምስት ልጆችን ለማሳደግ ሀላፊነት የወደቀባትን እናቷን ለማገዝ የተለያዩ ስራዎችን ሰርታለች፡፡ ሆኖም ጎን ለጎን ትምህርቷን መከታተል እና የምንግዜም ህልሟ የሆነውን የአባቷን ገዳይ ለፍትህ የማቅረብ ጉዳይ ዘንግታ አታውቅም፡፡ በ8 አመቷ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከተመረቀች በኋላ ህግ በማጥናት ለ7 አመታት ጠበቃ ሆና አገልግላለች፡፡ በ2022 የጥብቅና ስራዋን በመተው የአባቷን ገዳይ ለመያዝ ፖሊስን ተቀላቀለች፡፡ በፖሊስ አባልነት የግድያ ወንጀል ምርመራዎችን በማጣራትም የአባቷ ገዳይ ላይ መድረስ ችላለች፡፡ጎሜዝ የተባለው የአባቷ ገዳይ በ2013 በሌላ የነፍስ ማጥፋት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ 12 አመታትን ታስሮ እንደወጣ ካወቀች በኋላ የሚገኝበትን ቦታ አፈላልጋ በማወቅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገዋለች፡፡ ጂስሊየን ሲልቫ ዴዲውስ የአባቷ ገዳይ ወደ ሚገኝበት የእርሻ ስፍራ ከሄደች በኋላ የዛሬ 25 አመት በፈጸመው ወንጀል በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን እርሷም የሟቹ የጓደኛው አባት መሆኗን ነግራው ወደ እስር ቤት ይዛው ሄዳለች፡፡ እንስቷ የገዳዩን መያዝ በቁጥጥር ሰር ያዋለቸውም እርሷ እንደሆነች ለቤተሰቦቿ ስትነግራቸው የተሰማቸው ስሜት ሁሌም ከአዕምሮዋ እንደማይጠፋ ተናግራለች፡፡(ምንጭ፣ አልአይን)
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#ኮሬ 🛑 “ አሁንም ግድያው እንደቀጠለ ነው። ዛሬም 3 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል” - ኮሬ ዞን 🔵 “ ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል” - በፌደራል ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮሬ ህዝብ ተወካይ ዛሬ (ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም) ሦስት ንጹሐን ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች መገዳላቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮሬ ዞን አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። “ ችግሩን ማስቆም የሚችል መንግሥት አካል አልተገኘም ” ያሉት አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ በዞኑ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ አካል፣ በሁለተኛው ዙር የመኸር ወቅት ብቻ 11 ሰዎች ሲገደሉ አራት ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጸዋል። “ ጉዳቱ የደረሰባቸው ቀበሌዎች ዳኖ፣ ጎልቤ፣ ጋሙሌ፣ ኬረዳ፣ ሻሮ ናቸው። በአጠቃላይ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በታጣቂዎች ተዘርፏል ” ነው ያሉት። በአካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የሚፈጸመው ግድያ ለምን ይሆን መቋጫ ያጣው ? ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ያቀረብንላቸው በፌደራል ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ የህዝብ ተወካይ አምዛዬ አወቀ (ዶ/ር) ምላሽ ተሰጥተዋል። “ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ምንም መቋጫ አላገኘም። እኛም በተደጋጋሚ ለመንግስት አመልክተናል። ግን ምንም መፍትሄ የለም። በየቀኑ ግድያ እንሰማለን ” ብለዋል። “ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እኛም ሁሉም በዬቦታው እየጮኸ ነው ግን መፍትሄ የለም። ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነው ” ሲሉም አክለዋል። የኮሬን ህዝብ የወከሉት በፌደራል ደረጃ እንደመሆንዎ ለመንግስት ቅርብ ነዎትና ጉዳዩን በግልጽ ለመንግስት አንስታችሁ ነበር? ከሆነስ የመንግስት ምላሽ ምንድን ነው? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ፦ “ በየጊዜው ነው የሚነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ በተገኙበት ጊዜ ኦፊሻሊ ጥያቄ ሁሉ አንስቼ ነበር በ2016 ዓ/ም። ‘ሁኔታውን ለማርገብ የተወሰነ የመከላከያ ኃይል ይላካልና ሁኔታው ይረጋጋል’ ብለው ነበር። ከዚያ በኋላ የተወሰነ ኃይል ሂዶ ነበር። እሱም አሁን በአገሪቱ ባለው ሁኔታ ይመስለኛል ተቀነሰ። ከዚያ በኋላ ግን ሁኔታው እየተባባሰ ነው የሄደው። ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ህዝቡ በዬቀኑ ይዘረፋል። መንገድም የለም። የዲላ ህዝብ ጋር ነው የኮሬ ዞን የሚገናኘው ይሄ መንገድም ከተዘጋ ዘጠኝ ዓመት ሆኖታል። ይሄን ሁሉ በማመልከታቸም አመልክተናል። ሽማግሌዎች ወጥተው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ ለሰላም ሚኒስቴር አመልክተዋል፤ ለክልሉ መንግስት በዬጊዜው የሚቀርብ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል ” ሲሉ መልሰዋል። ስለዚህ የመፍትሄው ጉዳይ ምንም እየተሰራበት አይደለም ማለት ነው ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ ምንም መፍትሄ የለም ” የሚል ነው። “ አንዳንድ ጊዜ ‘እርቅ ተደርጓል’ ይባላል፤ አምና እርቅም ለማድረግ ተሰብስበው የነበሩት የብልጽና ፓርቲ ኃላፊም ጭምር የተገደሉበት ሁኔታ አለ። መንግስት የራሱ ፓርቲ አባል ሲገደል እንኳ ገዳዮች እነማን ናቸው ብሎ ተከታትሎ ሊያቀርብ አልቻለም ” ሲሉም ተናግረዋል። በመሆኑም መንግስት፣ ሚዲያዎችም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ህዝቡን እንዲታደጉ በህዝቡ ስም ጥሪ አስተላልፈዋል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#ሰበርዜና ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በርዕሰ ብሄርነት እንደማይቀጥሉ ታወቀ! ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጥቅምት ላይ የሚጠናቀቀውን የስራ ዘመናቸውን ተከትሎ በርዕሰ ብሄርነት መቀጠል እንደማይፈልጉ መስማቱን መሠረት ሚድያ ዘግቧል። ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ለበርካታ ወራት በስራ ድርሻቸው ዙርያ በሚፈፀሙ አንዳንድ ድርጊቶች እና ከስራ አስፈፃሚው አካል ጋር ባላቸው ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ደስተኛ እንዳልነበሩ ሰምተናል። በመጪው ሳምንት የመጀመርያ ቀናት ይህን ያለመቀጠል ውሳኔያቸውን ለስራ አስፈፃሚው አካል ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዛሬው እለት በኤክስ (ትዊተር) አካውንታቸው ላይ "እነ ጥላሁን ገሠሠ: ቴዲ አፍሮ: አሊ ቢራ:ማህሙድ አህመድ..ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው::"የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው:መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው"ይላል ማህሙድ "ዝምታ ነው መልሴ"ን ሲያዜም::ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" የሚል ፅሁፍ አስፍረው ነበር። ይህን ተከትሎ የፕሬዝደንት ፅ/ቤት ሀላፊው አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ "የፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ኦፊሴላዊ አካውንት አለ፣ እኛ አስተያየት መስጠት የምንችለው በእሱ ዙርያ ነው። የተባለው ፅሁፍ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም" በማለት ለኢትዮጵያ ቼክ ምላሽ ሰጥተው ነበር። ይህ ፅሁፍ አሁን ድረስ የፕሬዝደንቷ የኤክክስ አካውንት ላይ ይገኛል። ምንጭ ፣ መሰረት ሚዲያ
видео или голосовое, без подписи