Faruk Tech and Lang Learning🌍🌍
Статистика- Последний пост
- 19 июн.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ዛሬ ጁምዐ ነው ❗️ በነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋት አውርደዋል ⁉️ .
🔳DAILY HADITH🔳 "ዓነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) "ሟችን ሶስት ነገሮች ይከተሉታል ፥ ቤተሰብ ፣ ገንዘብ፣ ስራው። ሁለቱ ሲመለሱ አንዱ ከእርሱ ጋር ይቀራል። ቤተስብና ገንዘብ ሲመለሱ ስራው ይቀራል (አብሮ መቃብር ይወርዳል) ብለዋል (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
.🔅ተውሂድ ከማንኛውም አምልኮ በፊት መታወቅ ያለበትና ወደ እርሱ ጥሪ ሊደረግለት የሚገባው ወሳኝ ነጥብ ነው ። የአላህ መልእክተኛ /ﷺ/ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ሙዓዝ የተባለውን ሱሃቢ "የመን" ወደ ተባለ አገር ላስተማሪነት ሲልኩት፦ «إِنَّكَ تَأْتِي قَوْمًا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ، فَادْعُهُمْ إِلَى شَهَادَةِ أَنَّ لا إِلَهَ إِلا اللهُ وَأَنِّي رَسُولُ الله" “ መጽሐፍ የተሰጣቸውን ሰዎች ታገኛለህ ስለዚህ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት ጌታ አለመኖሩንና እኔ የአላህ መልእክተኛ መሆኔን አስተምራቸው ” አሉት።
በሐጅ ጉዞ ላይ የታየው እጅግ አስደሳች ቅፅበት! 🕋 እቅፍ ድግፍ! 😍 የጸጥታ ጥበቃ ስራ ላይ የነበረው ሳውዲያዊ ወታደር በሐጅ ስነ-ስርዓት ላይ እናቱን በድንገት አግኝቶ የተቃቀፈበት ምስል በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እያስለቀሰና እያስደሰተ ይገኛል። ስራ፣ ሀላፊነት እና ቦታ ሳይገድበው ለእናቱ የሰጠው ይፋዊ ፍቅር ለሁላችንም ትልቅ ትምህርት ነው። ለእናትዎ ያለዎትን ፍቅር በኮሜንት ይግለጹላት! ❤️👇 #Hajj #Mother #Love #Trending
اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته ወንድም እህቶቼ እንደት ናችሁ 🌙🌙 ዒድ ሙባረክ 🌙🌙 عيد مبارك كل عام وانتم بخير 💫✨💫💫✨💫💫✨ تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال ✨✨✨✨✨✨✨✨ اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ، لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ، وللَّهِ الحمد መልካም በዓል ይሁንላችሁ عيد مبارك
🌻 ዒድ ሙባረክ 💐 እንኳን ለ1447ኛው ዒድ አል-ፈጥር በዓል በሠላም አደረሰን። 🌸 تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 人 ★* 。 • ˚* ˚ 🌙 . (_ _) * ዒድ * ★ . ┃口┃ * mubark * . ┃口┃★ * ***. . *˛• . ┃口┃★ * •★ 。•˛˚˛* . ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ * . ┃口┃ .-:'''"''''"''.-. . ┃口┃ (_(_(_()_)_)_) ┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃ . ┃. ┃_┃∩∩∩∩∩∩┃ . 三_三三三三三 🌷አላህ መልካም ሥራችንን ሁሉ ይቀበለን! ጥፋታችንንም ይቅር ይበለን። የደስታ የሰላም እና የተባረከ ዒድ ይሁንልን!! 💫 ዒድኩም ሙባረክ እንኳን አደረሳቹ 💫
🌙ዛሬ…❷❼ኛው ለይል🌙 ---------------------------- ከሽ ወራት በላይ የተሰጣት ፀጋ፡ ሰማንያ ሶስት አመት የአንድ ሌሊት ዋጋ፡ ታዲያ ይህን ሰምቶ ማነው የማይተጋ፡ ያመመው ካልሆነ ውስጡ የተናጋ፡ 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي የዛሬዋ ሌሊት ልዩ ግምት አላት፡ በታሪክ ሰምተናል ብዙ ሲባልላት፡ ይነቃቃል ዑማው የኢስላም ገበሬ፡ ልዩ ነው ስሜቱ ይባንናል ዛሬ፡ 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي በሁሉም አቅጣጫ መስጂዱ ይሞላል፡ እውነትም ይሔ ቀን ሲር አለው ያስብላል፡ ብቻ ለሁላችን አሏህ ይወፍቀን፡ በሁለቱም ሀገር አሏህ ይታረቀን፡ 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي መሳጂዶች ሁሉ በሰጋጆች ደምቀው፡ የጀሊሉ ባሮች በዱዓዕ ተጨንቀው፡ ያ አሏህ እባክህ ብለው ሲማፀኑ፡ ልዩ ነው ድባቡ ወጣቱም ህፃኑ፡ 💫በ❷❼ኛው ለይል የእንቅልፍ ሰራዊቶች ስራ ፈትተው ያድራሉ። 💫በ❷❼ኛው ለይል ፍራሾች እና አልጋዎች የዓመት ዕረፍታቸውን ያገኛሉ። 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي 👉በዚህ ለይል ምድር በሙስሊሞች ዒባዳ የተለዬ ካባ ታጠልቃለች ተብሎ ይታሰባል። 👉ሰማይ በመላዒካዎች ዝውውር ደምቀው እንደ ሚያነጉ ይጠበቃል!! 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي ⚫️ሌሊቷ ከከባድ ቅዝቃዜ እና ከከባድ ሙቀት ነፃ ሆና በሰላምና በዕርጋታ እንደ ምታነጋ ትጠበቃለች። ያ አሏህ ያ ረቢ ያ ጀባር ግጠመን አሚን። 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي 🌙ዛሬ ማለት፦ 👉የረመዷን ❷❼ኛው ሌሊት ነው። ከሁሉም ሌሊቶች በበለጠ ለይለተል ቀድር የሚከጀልበት ሌሊት ነው። 🖊ከቀደምቶቻችን……… "ወላሂ ለይለተል ቀድር በ❷❼ኛው ሌሊት ነው" ብለው የሚምሉ ነበሩ። 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي 🌙ለይለተል ቀድር ማለት፦ አላህ የዓመቱ ውሳኔ የሚወስንባት; መላኢካዎች ጅብሪልን ጨምሮ የሚወርዱባት; ጎህ እስከ ሚቀድ ድረስ ሙሉ ሌሊቱ ሰላም የሚሆንባት ሌሊት ናት!! 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي 👉🌙ለይለተል ቀድር ማለት፦ ቁርኣን የወረደባት ሌሊት ናት; አላህ በተከበረው ንግግሩ "የተባረከች ሌሊት" ብሎ የሰየማት ሌሊት ናት!! 👉🌙ለይለተል ቀድር ማለት፦ ስለሷ በተነገረው አምኖና ምንዳዋን ከጅሎ እየሰገደ ያነጋ የሆነ ሰው ያሳለፈውን ወንጀሉ የሚታበስለት ሌሊት ናት!! 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي 👉🌙ለይለተል ቀድር ማለት፦ ከ1000 ወራት ወይም ከ83 ዓመታት የበለጠ ደረጃ ያላት ሌሊት ናት!! ምን አይነት ለሌት ነች ምን አይነት ተዓምር፡ ምን አይነት ፀጋ ነች የበረከት ክምር፡ ፀጋዋ ተነግሮ መቼ ይዘለቃል፡ ከነገረን በላይ ሚስጥሯን ማን ያውቃል!? 👉ታድያ ዛሬም የሚተኛ ሰው ይኖራል⁉️ ⭕️መደጋገም ያለብን ዱዓዕ‼️⭕️ 🤲اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي 🤲አላህ ለሁላችን ለይለተል-ቀድርን ይወፍቀን አሚን🤲
رمضان 25🌙 ዱንያ የዉድድር ሜዳ ናት። አሯሯጩ ሳይሆን የጨረሰው ነው ሚሽለመው። ያቋረጠው ሳይሆን በጽናት ያጠናቀቀው ነው ትልቅ ስኬት የሚጎናፀፈው። ከረጅም ሩጫ በኋላ ተወዳዳሪዎች ይዳከማሉ። ወደ መዳረሻው እየቀረቡ በመጡ ቁጥር በርካቶች ይንጠባጠባሉ። የሥራዎች ፍፃሜያቸው ነዉና ሚታየው ብልሆች ግን ስለ ፍፃሚያቸው ነው የሚጨነቁት። ከዛሬው ድካም ይልቅ የነገን እርካታ ነው አሻግረው የሚያዩት። ስለሆነም ጽኑ ናቸው፣ ብርቱ ናቸው፣ ጠንካሮች ናቸው፣ ትጉሃን ናቸው። 👉ረመዷን አሁንም አለ። ከረመዷን በጥሩ ዉጤት ለመውጣት ማለቂያው አካባቢ መበርታት አስፈላጊ ነው። የዉድድር ፈረሶች ለማሽነፍ ያለ የሌለ ሀይላቸዉን የሚጠቀሙት በመጨረሻ ዙር ላይ ነው። በዉድድሩ መጨረሻ አካባቢ ከሚሳነፉት እንዳንሆን እንጠንቀቅ። አላህ ረመዷናቸው ተቀባይነታቸው አግኝቶ፣ ኻቲማቸው አምሮ፣ ዉጤታቸው ሰምሮ ረመዷንን ከሚሰናበቱት ያድርገን። እስከመጨረሻው መስመር ድረስ በርቱ።
🌙 ረመዳንና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞቹ 1⃣9⃣ ✍️የሁሉ ነገር ጅማሬ ፍፃሜ አለው። ረመዳንንም ለመጨረስ እየተንደረደርን ነው። ታዲያ ፍፃሜው ምን መመስል አለበት የሚለውን ለማወቅ በዚህ ጊዜ የሚፈፀመውን የታላቁን ነቢይ (ﷺ) ተግባር መመልከት የግድ ነው ከእናታችን አዒሻ (ረ.ዐ) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፦ ﴿كان رسولُ اللهِﷺ إذا دخَل العَشْرُ الأواخرُ مِن رمضانَ أيقَظ أهلَه وشدَّ المِئزرَ وأحيا اللَّيلَ﴾ “ነቢዩ (ﷺ) የመጨረሻዎቹ የረመዷን ወር አስር ቀናት ሲገቡ ሌሊቱን በሙሉ በሰላትና በፀሎት ያሣልፉ ነበር ቤተሰቦቻቸውንም ለኢባዳ ይቀሰቀሱና ወገባቸውን ታጥቀው ለኢባዳ ይነሣሱ ነበር።” 📚ኢብኑ ሂባን ሶሂህ ብለውታል: 3436
የጾመኛ ደስታዎች =========== አቡሁረይራ [ረዐ] እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «አላህ እንዲህ አለ: — የአደም ልጅ ሁሉም ስራ ለርሱ ነው፤ ጾም ሲቀር። እርሱ ግን ለኔ ነው። እኔም እመነዳበታለሁ። ጾም ጋሻ ነው። የእያንዳንዳችሁ የጾም ቀናችሁ ሲሆን የወሲብ ወሬ አያውራ፤ አይጩኽ። አንድ ሰው ከተሳደበው ወይም ከተጋደለው እኔ ጾመኛ ሰው ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ የጾመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሽቶ የበለጠ ተወዳጅ ነው። ጾመኛ የሚደሰትባቸው ሁለት ደስታዎች አሉት። ሲያፈጥር ይደሰታል። ጌታውን ሲገናኝም በመጾሙ ይደሰታል።» ሹዐቡል‐ኢማን ገፅ 265 .
በረመዳን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች ⛔️ ሰላት ሳይሰግዱ መፆም፣ ⛔️ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሰሑርን አስቀድሞ በመመገብ ሱብሕ ሳይሰግዱ መተኛት፣ ⛔️ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም (ሙሰልሰላት) ማሳለፍ፣ ⛔️ረመዷንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣ ⛔️ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሰላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣ ⛔️ተራዊሕ ላይ በየአራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐ እና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣ ⛔️ የተራዊሕ ኢማሞች በጣም ረጅም የቁኑት ዱዓእ ማድረግ፣ ⛔️መግሪብ ሰላት ሲጠናቀቅ ስርአት በሌለው መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣… አለ) ⛔️ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ" እያሉ መዞር፣ (10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣ ⛔️ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣ ⛔️እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣ ⛔️ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያስፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣ ⛔️ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣ ⛔️ሴቶች ሽቶ ተቀብተው ለተራዊሕ መውጣት፣ ⛔️በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች በየ ጎዳናውና በየካፌው አላስፈላጊ መዝረክረክ፣ ⛔️ሃሜት፣ ⛔️ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣ ⛔️ቀኑን በካርታ፣ በዳማ እና መሰል አጉል ነገሮች ማሳለፍ፣ ⛔️ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ⛔️የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣ ⛔️በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርኣን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።) ⛔️ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ ተሰብስበው እያወሩ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣ ⛔️አንዳንድ አካባቢዎች የዒሻእ ሰላትን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣ ⛔️አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣ ⛔️አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማስገደድ፣ ወዘተ ✍ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
видео или голосовое, без подписи
Goranto seeco 👐 #Sheer/ሼር Neh Abay Meqe Toobokoy 🙏 Tamaa gubal fooca/Taswiir akak tablen toobokoyti #Ibraahim_Hayshum_ibraahim deqsita Addis Ababal baritto baritak sugeh yani buxak 3 ayroh bayeh geytimam kee taham fanah buxa mari goranat kaak yanim takkay immay kaa tubleeh, kay xaagu le matanaay, elle baritak sugeh yan Addis Ababah magaalak lih sugeh yan buxa marak sabti ayro buxak gexe giira xaagi kaak waytimaah, aqaxal(Konnabak) buxa mara kee ahli inkih shoklit yanin meqe toobokoy. kaa yuble mari yenek aw kay xaagu le mari yenik tamaa gubal tan nebroh/silkih neh heetton. 😞 📱 0946184635 🫴 📱 0914938923🫴
ምርጥ ጉደኛ ይሰጣቹሁ የ አለማት ጌታ(አሏህ) ለብዙ ዘመን አብሯችሁ የኖረ መልካም የሚመኝላችሁ ፣ የማይፎካከራችሁ ፣ የማይመቀኛችሁ ፣ ቅርባችሁ የሆነ ፣ ችግራችሁ እና ውድቀታችሁ የሚጨንቀው ፣ ስኬታችሁና ደስታችሁ ሀሴት የሚጭርበት … ጓደኛ ካላችሁ አጥብቃችሁ ያዙ ። ወላሂ ትልቅ ኒዕማ ነው ። የቱንም ያህል ብርቱ ብትሆኑ ለብቻ መቆም ከባድ ነው ፣ አድካሚ ፣ አሰልቺ ነው ። ነብያችን ﷺ እንኳ ጓደኛ ነበራቸው ። ስለ አባበክር ረድየላሁ ዐንሁ ሲናገሩ “ የሁላችሁንም ውለታ መልሰናል የአባበክርን ሲቀር “ ብለዋል ። የነብዩን ﷺ ተልዕኮ ማገዝ ላይ የአባበክር ሚና ቀላል አልነበረም ። የጓደኞቻችሁን ጥፋቶች እለፉ ፣ በመነጋገር እና መከባበርም ተራረሙ ። ብቸኝነት የሚያመፃድቅ ነገር አይደለም ! ©️
ለብዙ ዘመን አብሯችሁ የኖረ መልካም የሚመኝላችሁ ፣ የማይፎካከራችሁ ፣ የማይመቀኛችሁ ፣ ቅርባችሁ የሆነ ፣ ችግራችሁ እና ውድቀታችሁ የሚጨንቀው ፣ ስኬታችሁና ደስታችሁ ሀሴት የሚጭርበት … ጓደኛ ካላችሁ አጥብቃችሁ ያዙ ። ወላሂ ትልቅ ኒዕማ ነው ። የቱንም ያህል ብርቱ ብትሆኑ ለብቻ መቆም ከባድ ነው ፣ አድካሚ ፣ አሰልቺ ነው ። ነብያችን ﷺ እንኳ ጓደኛ ነበራቸው ። ስለ አባበክር ረድየላሁ ዐንሁ ሲናገሩ “ የሁላችሁንም ውለታ መልሰናል የአባበክርን ሲቀር “ ብለዋል ። የነብዩን ﷺ ተልዕኮ ማገዝ ላይ የአባበክር ሚና ቀላል አልነበረም ። የጓደኞቻችሁን ጥፋቶች እለፉ ፣ በመነጋገር እና መከባበርም ተራረሙ ። ብቸኝነት የሚያመፃድቅ ነገር አይደለም ! ©️
የምሽት ስንቅ ዛሬ የጁሙዓ ሌሊት ነዉ፣ በዚህ ታላቅ ምሽት በነቢዩ (ﷺ) ላይ ሶለዋት ማውረድን እናብዛ። ከመተኛታችን በፊትም የመኝታ ዝክሮችን በማለት አላህን እያስታወስን እንተኛ። ለማስታወስ ያህል፦ የሶለዋት ትርፍ፦ በነቢዩ ላይ አንዴ ሶለዋት ላወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድበታል። اللهم صل وسلم على نبينا محمد. የመኝታ ዚክር፦ አያተል ኩርሲይን፣ የመጨረሻዎቹን ሶስት ሱራዎች (ኢኽላስ፣ ፈለቅ፣ ናስ) እና "ቢስሚካ ረቢ ወዳዕቱ ጀንቢ..." የሚሉትን ዚክሮች ማለት የሌሊት ጥበቃ ያስገኛል። አላህ በሰላም ያሳድረን! መንገደኛ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
👉ያለመውለድ ችግር (መካንነት) 10 ዋና ዋና ምክንያቶች👇 ጥንዶች ጋብቻ ከፈፀሙ በኋላ በቀጣዩ የህይወት ምዕራፍቸው የሚጠብቁት ነገር ልጅ መውለድ ነው። አንድ ሴት ምንም የመውለድ ችግር ሳይኖርባት እና የወሊድ መከላከያ ሳትጠቀም በአንድ ወር ውስጥ የማርገዝ እድሏ 20% ሲሆን 6 ወር ውስጥ 60% እንዲሁም በ1 ዓመት 85% ነው። ለሁለት አመት ቢሞክሩ ደግሞ 95% የማርገዝ እድል አላቸው። 15% የሚሆኑ ጥንዶት በአንድ አመት ውስጥ ምንም አይነት የወሊድ መከላከያ ሳይጠቀሙ ቋሚ የግብረስጋ ግንኙነት እያደረጉ የማርገዝ ችግር ያጋጥማቸዋል። ይህም መካንነት ወይም ያለመውለድ ችግር አጋጥሟቸዋል ተብሎ ህክምና ይጀመርላቸዋል። የሴቷ እድሜ ከ35 አመት በላይ ከሆነ ለ6ወር ሙከራ አድርጋ እርግዝና ካልተፈጠረ የመካንነት ህክምና መጀመር አለባት። መውለድ ያለመቻል እጅግ በርካታ ምክንያቶች ሲኖሩት አንዳንዶቹ ወደ 20% የሚሆኑት ይህ ነው የሚባል ምክንያት የላቸውም። ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ዋናዋናዎቹ ምክንያቶች እነሆ 1. ከወንድ በኩል የሚኖር መካንነት (male factor infertility) እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት 20% የሚሆነው ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ከወንድ በኩል የሚኖር ነው።ይህም በጭንቅላት ውስጥ የሚመረት ሆርምሞን ማነስ, በዘር ፍሬ ላይ የሚያጋጥም ሰፐርም የማምረት ችግር (primary testicular defect in spermatogenesis), የወንድ የዘር ትቦ መዘጋት, እንዲሁም ምክንያቱ የማይታወቅ የወንድ መካንነት (idiopathic male infertility) ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከ70-80% የሚሆነው በወንዶች በኩል የሚያጋጥም መካንነት በዘር ፍሬ (testes) በተለያዩ ምክንያቶች ዘር ያለማምረት ችግር የሚመጣ ነው። ይህም በዘር (genetics) ፣ በኢንፌክሽን ፣ በአደጋ፣ ጨረር መጋለጥ፣ ለሙቀት መጋለጥ እንዲሁም የሆርሞን ማነስ ምክንያት ሊሆን ይችላል። 2.በሴቶች ላይ እንቁላል የመለቀቅ ችግር (ovulatory dysfunction) 25% የሚሆነው ያለመውለድ ችግር (መካንነት) ምክንያት የእንቁላል ያለመለቀቅ ችግር ነው። አንዲት ሴት ስትወለድ ከ1-2 ሚሊየን የሚጠጉ እንቁላሎች በኦቫሪ ውስጥ ይኖራሉ። አነዚህ እንቁላሎች እድሜዋ አየጨመረ ሲሄድ እየቀነሱ ይመጣሉ። እርግዝና እንዲፈጠር እንቁላል ከኦቫሪ ወደ ማህፀን ግድግዳ መለቀቅ አለበት ይህ የመለቀቅ ሂደት በተለያየ ሆርሞኖች ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው። የእነዚህ ሆርሞኖች መዛባት እንቁላል እንዳይለቀቅ ሊያደርጉ ይችላሉ። PCOS ፣ ከአንጎል የሚመነጭ ሆርሞን ማነስ፣የፕሮላክቲን መብዛት ፣ የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ/መብዛት እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ። 3.የማህፀን ቱቦ መዘጋት በግራና በቀኝ በኩል የሚገኙ እንቁላል አስተላላፊ ትቦዎች በተለያየ ምክንያት ሊዘጉ ይችላሉ። በሰርጀሪ፣ በኢንፌክሽን፣ ከማህፀን ውጭ በሚያጋጥም እርግዝና እንዲሁም በሆድ እቃ ውስጥ በሚያጋጥም ጠባሳና መጣበቅ ሊዘጋ ይችላል። 4.በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚያድግ እጢ በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚፈጠር እጢ እንቁላልና ስፐርም ሴል እንዳይገናኙ እንዲሁም እርግዝና ከተፈጠረ በኋላም ምቹ ሁኔታ እንዳይኖር ሊያደርጉ ይችላሉ። 5.የማህፀን አፈጣጠር ችግር በተፈጥሮ ለሁለት የተከፈለ ማህፀን (septated uterus) ተደጋጋሚ ውርጃ እንዲኖር እንዲሁም ምንም ማህፀን ያለመፈጠር ችግር የመካንነት ችግር ሊያመጡ ይችላሉ። 6.ኢንዶሜትሪዮሲስ (endometriosis) ጠባሳና መጣበቅን በመፍጠር የማህፀን ትቦ እንዲዘጋ እንዲሁም በኦቫሪ ውስጥ እጢ (endometrioma) በመፈጠር የእንቁላል ማምረት ሂደትን በማወክ መካንነትን ሊያመጣ ይችላል። 7.የዘረ መል (chromosome) ችግር Turner syndrome, down syndrome, Kallman syndrome, የተባሉ የዘረመል ችግሮች ያለመውለድ ችግር ያመጣሉ። 8.ምክንያቱ የማይታወቅ (unexplained infertility) ብዙ ምርመራዎች ተደርገውም ምንም ምክንያት ላይገኝ ይችላል።ይህም 20% የሚሆኑት ያለመውለድ ችግር ያለባቸው ጥንዶች ላይ ያጋጥማል። 9.የግብረ ስጋ ግንኙነት አደራረግ ችግር እርግዝና እንዲፈጠር እርግዝና የሚፈጠርበትን የወር አበባ ኡደት ጊዜ ጠብቆ የማድረግ ችግር፣ ማለስለሻ ጄሎችን መጠቀም ያለማርገዝ እድልን ይጨምራሉ። እንቁላል የሚለቀቅበትን ወቅት ጠብቆ (Fertile period) ተደጋጋሚ ግንኙነት ማድረግ የማርገዝ እድልን ይጨምራል። 10.እድሜና የአኗኗር ሁኔታ የሴቶች እድሜ ሲጨምር የእንቁላል መጠን እየቀነሰ ይሄዳል። በተጨማሪም ሲጋራ ማጨስ፣ለተለያዪ ኬሚካሎች መጋለጥ፣ ለጨረር መጋለጥ፣ የክብደት መጨመር፣ ጭንቀት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል መውሰድ ለመካንነት ያጋልጣል። ዶ/ር በላይ አለሙ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ለማማከር ☎️ +251977297156 ይደውሉ። ቴሌግራም ይቀላቀሉ: t.me/Wellwoman2 Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1 @HakimEthio
ጁሙዓን የት ሃገር፣ የት መስጅድ ሰገዳችሁ? ኹጥባው ስለምን ነበር? ለሌሎችም እንዲጠቅም ከሰማችሁት ውስጥ የኹጥባውን ጭብጥ በአጭር አስፍሩት።