- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- ещё не заходили
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- русский
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 32
- 1/48двое суток
- 36
- 1/72трое суток
- 39
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ቤተሰብ አንዴ ብቻ አንዴ🙏 ይሄን ካነበብክ ስልክህን 30 ሰከንድ አስቀምጥና አባትህን አውራው እባክህ እየፈለገህ ነው ያከብርሀል የማክበሩ ጥግም መለኮት እራሱን ወደሰው የመቀየር ከባድ ትግል አርጎልሀል አንተ እርጥብ ለጋበዘህ ጎደኛ ቀንህን ሙሉ እየሰጠህ አይደል🥺 ለአባትህስ 30 ደቂቃ ከበደህ ።😞 እሺ ሌላው ይቅርና አሁን ወደፀሎት ምክንያት አታብዛ ዝም በል።
ሉቃስ 21:29-31 29: ምሳሌንም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ “በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፤ 30: ሲያቈጠቍጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 31: እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች እወቁ።
የእግዚአብሔር ቸርነት በተደበቅክበት ወቅት እንኳን ፈልጎ ያገኝሃል፤ ሳታስበውም ትልቅ ቦታ ያደርስሃል። ዳዊት እግዚአብሔር ንጉሥ አድርጎ ሲመርጠው በግ ይጠብቅ ነበር። ዮሴፍም ወደ ቤተ መንግሥት ከመሄዱ በፊት እስር ቤት ነበር። አሁን ያለህበት ቦታ እግዚአብሔር ለወደፊት የሚያደርግልህን ነገር አይወሰነውም። ሰው አላየኝም ወይም ትኩረት አላገኘሁም ብለህ አትዘን። እግዚአብሔር ያለህበትን ቦታ በደንብ ያውቃል። በታማኝነት ማገልገልህን፣ በፀጥታ ማደግህንና በእሱ ጊዜ ማመንን ቀጥል። ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ፣ እሱ ከተክክለኛ ሰዎች ጋር የሚያገናኝበትን፣ ትክክለኛ በሮችን የሚከፍትበትንና የሚገባህ ቦታ ላይ የሚያስቀምጥበትን መንገድ ያውቃል። የእግዚአብሔርን መልካምነት ለማግኘት መሮጥ አይጠበቅብህም። ከእግዚአብሔር ጋር በታማኝነት ተመላለስ፤ ወደ ዓላማውም እንዲመራህ እመነው። “አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።” — መዝሙር 5፥12
📖 ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን – ክፍል 3 ዘጸአት 27 – መሠዊያው፣ አደባባዩ እና የዓለም ብርሃን ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ "መጻሕፍት... ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው።" (ዮሐንስ 5፥39) ዘጸአት 27 ሦስት ዋና ነገሮችን ያስተምራል፤ እነርሱም በክርስቶስ ፍጻሜያቸውን አገኙ። 1. የናሱ መሠዊያ (ቁ.1–8) ወደ መቅደሱ የሚመጣ ሰው መጀመሪያ የሚያገኘው መሠዊያውን ነበር። ኃጢአተኛ ያለ መሥዋዕት አይቀርብም ነበር። ይህ ክርስቶስን ያመለክታል፤ "ክርስቶስ ደግሞ ራሱን ስለ እኛ መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ።" (ኤፌሶን 5፥2) "በአንድ መሥዋዕት ለዘላለም ፍጹማን አደረገ።" (ዕብራውያን 10፥14) በብሉይ ኪዳን መሥዋዕት ደጋግሞ ይቀርብ ነበር፤ ክርስቶስ ግን አንድ ጊዜ ለዘላለም ራሱን አቀረበ። 2. የማደሪያው አደባባይ (ቁ.9–19) መቅደሱ አንድ መግቢያ ብቻ ነበረው። ይህ የሚያስተምረው፣ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ አንድ መንገድ ብቻ መኖሩን ነው። ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ "እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ አይመጣም።" (ዮሐንስ 14፥6) ወደ መቅደሱ አንድ በር እንደነበረ፣ ወደ አብም አንድ አዳኝ ብቻ አለ፤ እርሱም ክርስቶስ ነው። 3. የመቅረዙ ዘይት (ቁ.20–21) መቅረዙ ሁልጊዜ እንዲበራ ንጹሕ የወይራ ዘይት ይቀርብ ነበር። በአዲስ ኪዳን፣ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ።" (ዮሐንስ 8፥12) ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ነው፤ በእርሱ የሚያምን በጨለማ አይሄድም። የምዕራፉ ዋና መልእክት ዘጸአት 27 ሦስት ታላላቅ እውነቶችን ያስተምረናል፦ ✝️ መሠዊያው ክርስቶስ ፍጹም መሥዋዕታችን ነው። ✝️ አንዱ መግቢያ በሩ ክርስቶስ ብቸኛው የመዳን መንገድ ነው። ✝️ የሚበራው መቅረዝ ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ነው። ስለዚህ ዘጸአት 27 ወደ ክርስቶስ ያመለክተናል፤ በእርሱ መሥዋዕት እንድንድን፣ በእርሱ ብቻ ወደ አብ እንድንቀርብ፣ እና በብርሃኑ እንድንመላለስ ያስተምረናል። "ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድልን የሰጠን።" (1ኛ ቆሮንቶስ 15፥57)።
ጭብጨባ ይገባሀል👏👏👏👏😒
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው። — መጽሐፈ ምሳሌ 9:10 ምን ታፈጣለህ ዳይ ወደ ቸርች🤨
እግርህን አታንሳ🙌 "ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው"ነው የሚለው ብሂሉ!እኔ ግን እላለው "ሰውን ለመርዳት ሀብታም መሆን፣ሁሉ ያለውና የተረፈለት ሰው መሆን፣ስልጣንና ዝና ያለው ሰው መሆን አይጠበቅብህም"ሰውን ለመርዳት ቀዳሚውና ወሳኙ ነገር ልብ ነው።እነዚያ የተዘረዘሩቱ በሙሉ ተከታይ ነጥቦች ናቸው።ከሰዎች አንዳችን የፍቅር ምላሽ ጠብቀህ ልትረዳቸው ካሰብክ አንድ እርምጃ እግርህን አታንሳ።ለዚህ ደግሞ ኢየሱስ ፍቱን ምሳሌ ነው፤ይሁዳ አሳልፎ ለአይሁድ እንደሚሰጠውና በገንዘብ እንደሚሸጠው እያወቀ እግር ያጥባል(አንዳንዴ ዝም ማለት አለማወቅ እንዳይደለ እንገንዘብ🤔🙌) አምኖት ገንዘብ ያስይዘዘዋል።የይሁዳን ተንኮል እያወቀ ይወደው ነበር ከሌሎቹ ደቀመዛሙርት እኩል!ኢየሱስ ጥሩ ምላሽ ጠብቆ ሁሉን እንዳላደረገ እንዲሁ አንዳች መልካም ምላሽ ሳንጠብቅ ምናደርገውን ሁሉ በልግስና እናድርግ(ሁላችንም)።በመቀጠል ስናደርግ ደስስስስ እያለን እናድርግ🥰🥰
📖 ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን – ክፍል 2 ዘጸአት 26 – የመቅደሱ ድንኳን እና ክርስቶስ ኢየሱስ፦ "ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ በመጻሕፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተጻፈውን ተረጎመላቸው።" (ሉቃስ 24፥27) ስለዚህ ዘጸአት 26 ስለ ድንኳኑ ግንባታ ብቻ አይደለም፤ ክርስቶስን በምልክት ያሳያል። 1. ድንኳኑ – እግዚአብሔር ከሰው ጋር መኖሩ እግዚአብሔር በድንኳኑ ውስጥ በሕዝቡ መካከል ይኖር ነበር። በአዲስ ኪዳን ግን፦ "ቃሉም ሥጋ ሆነ፥ በመካከላችንም አደረ።" (ዮሐንስ 1፥14) ኢየሱስ እውነተኛው የእግዚአብሔር ማደሪያ ነው። 2. አራቱ መሸፈኛዎች ድንኳኑ በተለያዩ መሸፈኛዎች ተሸፍኖ ነበር። በውስጥ ያለው ውበት የክርስቶስን ቅድስናና ክብር ያመለክታል። ከውጭ ግን ቀላል ይመስል ነበር፤ እንዲሁም ኢየሱስ በሰው ዓይን ተራ ሰው መስሎ ታየ፣ በውስጡ ግን የእግዚአብሔር ሙላት ነበረ። 3. መጋረጃው (ቁጥር 31–33) ይህ የድንኳኑ ዋና ክፍል ነው። መጋረጃው ቅዱሱን ከቅድስተ ቅዱሳን ይለይ ነበር። ማንም በፈለገው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ፊት መግባት አይችልም ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀል ሲሞት፦ "የመቅደሱም መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ።" (ማቴዎስ 27፥51) ዕብራውያንም ይህን በግልጽ ይተረጉመዋል፦ "በመጋረጃውም፣ ይኸውም በሥጋው አዲስና ሕያው መንገድ ከፈተልን።" (ዕብራውያን 10፥20) ስለዚህ መጋረጃው የክርስቶስን ሥጋ ያመለክታል፤ በእርሱ ሞት ወደ አብ የሚያስገባ መንገድ ተከፈተ። 4. የቅድስተ ቅዱሳን ይህ የእግዚአብሔር መገኘት የሚገለጥበት ቦታ ነበር። ዛሬ ግን በክርስቶስ ምክንያት፣ "ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።" (ዕብራውያን 4፥16) ምክንያቱም ኢየሱስ ታላቁ ሊቀ ካህናችን ነው። የምዕራፉ ዋና መልእክት ዘጸአት 26 የሚያስተምረን፣ ሰው በራሱ ኃይል ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንደማይችል ነው። ነገር ግን ኢየሱስ በሞቱና በትንሣኤው መንገዱን ከፈተ፤ ዛሬ በእርሱ አምነን በድፍረት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን። "እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ አይመጣም።" (ዮሐንስ 14፥6)።ይቀጥላል ከአግዚአብሔር አባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ
без подписи
без подписи
ዛሬ(ክፍል 1) 📖 ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን "እናንተ መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ... እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው።" (ዮሐንስ 5፥39) "ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ በመጻሕፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተጻፈውን ተረጎመላቸው።" (ሉቃስ 24፥27) ዘጸአት 25 የመቅደሱን ዕቃዎች ብቻ የሚገልጽ ምዕራፍ አይደለም፤ በእነዚህ ሁሉ ውስጥ ክርስቶስ ተስሎ ይታያል። ✝️ መቅደሱ – እግዚአብሔር በሰዎች መካከል የሚኖርበት ምልክት፤ በአዲስ ኪዳን ይህ በኢየሱስ ተፈጸመ። ✝️ የቃል ኪዳኑ ታቦት – የእግዚአብሔርን ሕግ የያዘ፤ ክርስቶስ ደግሞ ሕጉን ፍጹም ፈጸመ። ✝️ የዕርቅ መክደኛው – በእንስሳት ደም የሚረጭበት ነበር፤ ክርስቶስ ግን በራሱ ደም አንድ ጊዜ ለዘላለም ቤዛነትን አገኘ። ✝️ የኅብስቱ ገበታ – "እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ" ያለውን ክርስቶስን ያመለክታል። ✝️ የወርቅ መቅረዝ – "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ያለውን ክርስቶስን ያሳያል። የብሉይ ኪዳን ጥላ ነበር፤ እውነቱ ግን በክርስቶስ ተገለጠ። "ሕጉ የሚመጣው መልካም ነገር ጥላ አለው..." (ዕብራውያን 10፥1) ይቀጥላል... (ክፍል 2፦ ዘጸአት 26 – መጋረጃው እና የክርስቶስ ሥጋ)
ደግመህ ደግመህ ባርከን Lighthouse Worship Channel @Yezema_Tube New bot @YezemaTube_bot ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
አባት ሆይ፥ ለመጽናት ጥንካሬን፡ አሁን ካለሁበት ሁኔታ ባሻገር ለማየት ደግሞ ተስፋን ስጠኝ። በተጨነቅሁና በተስፋ በቆረጥኩበት ቅጽበት፥ መጽናኛዬና መጠጊያዬ ሁነኝ። አንተ ፈዋሽ መሆንህን አውቃለሁና ጭንቀቴን፥ ፍርሃቴንና ህመሜን በእጆችህ ላይ አኖራለሁ። አሜን🙏🕊️
@Levinixbot | info
@Levinixbot | info
ቀ ሲ ሱ ፡ ከ እ ን ግ ዲ ህ ፡ አ ን ድ ፡ ሆ ና ች ኃ ል ፡ ባ ሉ ን ፡ ም ሽ ት ፤ እ ን ጀ ራ ፡ የ ፈ ታ ፡ ጠ በ ቃ ፡ ይ ፀ ል ይ ፡ ነ በ ር ... ✍🏽
The Kingdom Parables The kingdom of heaven is like treasure hidden in a field, which a man found and covered up; then in his joy he goes and sells all that he has and buys that field. Again, the kingdom of heaven is like a merchant in search of fine pearls, who, on finding one pearl of great value, went and sold all that he had and bought it. Of course there is an obvious point of the value of the Gospel here -- such that it exceeds the value of all our other posessions. But if we look a layer deeper, both valuabled have a hidden factor. The treasure is hidden in a field, and the pearl is hidden in an oyster. The point is that the Kingdom of God is hidden in the most ordinary and mundane things. And if we are to lay hold of it, we must liquidate our pride and purchase these ordinary assets.
без подписи
без подписи
без подписи