የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግሽ ዓባይ ግቢ የተማሪዎች ሕብረት
СтатистикаWe are the Gish Abay Campus Students' Union, dedicated to fostering a vibrant and supportive community for all students at Bahir Dar University. Our mission is to empower students through information sharing, collaboration and engagement in campus life.
- Последний пост
- 17 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 66
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Образование
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 796
- 1/48двое суток
- 912
- 1/72трое суток
- 983
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
#NGAT አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket ለማግኘት የኢሜይል አድራሻችሁን መጎብኘት አትዘንጉ። ትምህርታዊ መረጃ™ ✅ ✅ ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ 🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers 🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
ጸሐይ ካልወጣች፣ አምፖሉ ካልበራ፣ ሻማው ካልተለኮሰ፣ ጭለማ ይሰለጥንብናል። ተማሪ ካልተማረ፣ ካላነበበ፣ ካልጻፈ ደንቁሮ ነው የሚቀረው። ገበሬ አርሶ፣ መልካም ዘር ካልዘራበት መሬቱ አረም ይበቅልበታል። መልካም ዘር ቢዘራ እንኳን አረም መብቀሉ አይቀርም። ከመዝራት ባላነሰ አረሙም መታረም አለበት።አረሙ ከየት መጣ? እንጃ! አላውቅም ግን የተፈጥሮ ህግ እንዲህ ነው። የሰው ልጅ አእምሮም እንዲሁ ነው። ካላነበበ፣ ካልጠየቀ፣ ካልተማረ የሃሳብ አረም ጭንቅላቱን ይወረዋል። ክፋት የሚሰለጥነውም መልካም ሰዎች ምንም ሳያደርጉ ከተቀመጡ ነው።አስተውሉ! ጨለማ የብርሃን አለመኖር ነው! ክፋት የመልካም አለመኖር ነው። ድንቁርና የእውቀት አለመኖር ነው። አሉታዊ ነገሮች ሁሉ በራሳቸው ያሉ ነገሮች ሳይሆኑ የበጎ ነገሮች አለመኖር ነው። የእግዜር ህግ አይጠየቅም። ሰው መልካም እንዲሆንለት መጣር አለበት። በጎ እንዲሳካለት መድከም አለበት። እጁን አጣጥፎ ከተቀመጠ ክፋት ይሰለጥናል፤ ጨለማ ይበረታል።
📢 የወደፊት ሕይወታችሁን የሚወስነው የ Department ምርጫ! ❗️ይሄን ሳታውቁ ውሳኔ እንዳትወስኑ! ------------------------------------ ✨ ይህ የመጀመሪያውና ዋነኛው ጥያቄ ነው! አንድን የትምህርት መስክ ስንመርጥ ለዚያ የትምህርት መስክ ፍቅር...... Read More 📨 @keleme_2013
#እናሳታውሳችሁ #NGAT የNGAT ምዝገባ ጊዜ እስከ ረቡዕ, ሀምሌ 29/ 2018 ዓም ድረስ ተራዝሟል። የNGAT መመዝገቢያ Link https://ngat.ethernet.edu.et በ2019 ዓም የድህረ ምረቃ ትምህርታችሁን በመንግስት እና በግል ኮሌጆች ለመከታተል ፍላጎቱ ካላችሁ የNGAT ማለፊያ ውጤት ግደታ ስለሆነ ምዝገባው እንዳያልፋችሁ አሁኑኑ ተመዝገቡ እና ለፈተና ተዘጋጁ። 👉የNGAT የፈተና ጊዜ እስካሁን አልተወሰነም ከMOE መረጃው ሲወጣ ተከታትለን እናሳውቃለን! 👉የፈተናው ጊዜ ድንገት ስለሆነ የሚነገረው ከአሁኑ ተዘጋጁ ፈተናው በጠቅላላ እውቀት የሚሰራ ስለሆነ በደንብ ጊዜ ሰጥቶ መዘጋጀት ይጠይቃል። ቻናላችንም እንደ ባለፉት 4/5 ዓመታት በ1000ዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች እንድያልፉ ከጎናቸው ነበርን አሁንም በዌብሳይት ለNGAT/GAT የሚሆኑ ሞደል ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል በደንብ ተለማመዱ። የGAT/NGAT ሞደል ጥያቄዎችን ከነማብራሪያቸው ለማገኘት ዌብሳይታችን ይቀላቀሉ👇 https://www.gatexam.com/exams ያለፉ 6 ዓመታትን ሞደል ጥያቄዎችን ሁሉንም በአንድ ላይ ከነማብራሪያቸው በቅናሽ ለማገኘት👇 https://www.gatexam.com/packages NB: ዌብሳይታችን ላይ Purchase አድርጋችሁ ትክክለኛ Transaction No ማስገባታችሁን እና Pending ማለቱን አረጋግጡ‼️
📢 Announcement 5th Round of NGAT Training Elevate Your Performance for the National Graduate Admission Test! The College of Science and the Faculty of Humanities at Bahir Dar University are officially opening registration for the 5th Round of GAT Training. This intensive two-day program is designed to equip postgraduate applicants with the skills needed to excel in the upcoming national exams. 🗓️ Key Details Dates: August 03–04, 2026 (Hamle 27–28, 2018 E.C.) Mode: Hybrid (Choose between Online or Face-to-Face) Fee: 300 Birr 🧠 Training Focus Areas Verbal Reasoning: Master reading comprehension and vocabulary. Quantitative Reasoning: Tackle arithmetic, algebra, geometry, and data. Analytical Writing: Refine your critical thinking and structured expression. 📍 How to Join 1. Payment & Registration Bank: Commercial Bank of Ethiopia (CBE) Account Name: Human Rights and Legal Aid, BDU Account Number: 1000012881968 Reference: 5th Round NGAT Training Register Here: Online Registration Form (Note: Please attach your payment receipt to the form.) 2. Attendance Options Face-to-Face Venues (Peda Campus): College of Science: Smart Room 401 Faculty of Humanities: NEL-1 Online Session Links: English Session (Google Meet) Mathematics Session (Google Meet) 📞 Need More Information? Feel free to contact our coordinators: 👉 Dr Ayenew Guadu: 0967 610 008 👉 Dr Minbale : 0911562519 Don't miss this opportunity to prepare with experts from the Departments of Mathematics and English! Best regards, The Training Coordination Team, Bahir Dar University Open the link to register https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdUBEDSA4MbiJ1OqGUypIZeh5ZSLDDD78zgGfi6eVvVcvI_Dg/viewform?fbclid=IwdGRzaAPYfo9jbGNrA9h-gGV4dG4DYWVtAjExAHNydGMGYXBwX2lkDDM1MDY4NTUzMTcyOAABHmovko5P2OGjIuoi9JAx0HU14md-RiK2ermDilsAnb3JfdCS2KmHprIVEdiw_aem_dnvC0WJ9e7nrg0pu7IgwKQ&sfnsn=wa
~ የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የሚሰጠውን መደበኛ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና /National Graduate Admission Test/ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ፈተናውን ለመውሰድ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች በሙሉ ምዝገባ የሚካሄደው እስከ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ከታች በተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ ገብታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለፈተናውም አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን። የፈተና መስጫ ጊዜው ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡ የመመዝገቢያ ሊንክ፡- https://ngat.ethernet.edu.et #ማሳሰቢያ:- ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ። የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር (ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) መሆኑን አውቃችሁ በቴሌ ብር በኩል በምዝገባው ወቅት የሚፈጸም ይሆናል። ምዝገባው የሚከናወነው በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን የመፈተኛ ጣቢያውን በሚመለከት ግን ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢ ቁጥሩ ታይቶ በስታንዳርዱ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡ የግሽ ዓባይ ግቢ ተማሪዎች ህብረት
~ #NGAT አንዳንድ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የድህረ ምረቃ (ማስተርስና PhD) መግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ የጀመረ መሆኑን ቢያሳውቁም አሁን ላይ ግን የመመዝገቢያ ሊንኩ እየሰራ አለመሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም ምዝገባው በቅርቡ የሚጀምር ስለሆነ የምዝገባው ቀን በይፋ ሲገለፅ የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ፈተናው በመጭው ሐምሌ 29/30 እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ቀደም ብሎ ማሳወቁ ይታወሳል። የግሽ ዓባይ ግቢ ተማሪዎች ህብረት
~ በመልካም ሀሳብ የሰው አስተሳሰብ ይገነባል፤ በተለወጠ አስተሳሰብ ደግሞ የላቀ እና የተሟላ ስብዕና ያለው ሰው ይታነፃል፤ የላቀ እና የተሟላ ስብዕና ያዳበሩ ሰዎች ተባብረው ጠንካራ እና ዘላቂ የሆኑ ሀገር ተሸካሚ ተቋማትን ይፈጥራሉ። ጠንካራ እና ከብልሹ አሰራር ነፃ የሆኑ ተቋማት ደግሞ የበለፀገች እና ሉዓላዊነቷ የተከበረ ሀገር ይፈጥራሉ። እውነተኛ ለውጥ ከአስተሳሰብ ይጀምራል። ሀገር ለመለወጥ ዋና መሰረቱ በተለወጡ ግለሰቦችና በሚለውጡ ሀሳቦች የታነፁ ማህበራዊ ተቋማት ሲገነቡ ነው። የሀሳብ እና የሞራል መሪዎች በብዛት ተፈጥረው ሀሳብ የሚያሸንበት እና ሰው በሰውነቱ የሚከበርበት ማህረሰብ መፍጠር ለሁሉም ነገር መሰረት ነው። ለዚህም ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ። ሀገር ወዳድነት፣ ስራ ፈጠራ፣ የትምህርት ጥራት፣ መልካም አስተዳደርና ዲሲፕሊን ከዚህ ትውልድ ይጠበቃል። Asian Tigers የሚባሉት ፈጣን እድገት ያስመዘገቡት የሩቅ ምስራቅና የደቡብ ምስራቅ ኤስያ ሀገራት ባለፉት ጥቂት አስርት አመታት ያስመዘገቡት ታሪካዊ እድገት ለዚህ ማሳያ ነው። መልካም የዕረፍት ጊዜ ይሁንላችሁ የግሽ ዓባይ ግቢ ተማሪዎች ህብረት
~ ዲሲፕሊን! ''በምታልሙት ሕልም እና በእጃችሁ ሊገባ በሚገባው እውነታ መካከል ያለው ርቀት መጠሪያ ስሙ ዲሲፕሊን ይባላል። ዲሲፕሊን የሌለው ሕልም፣ በምንም ያህል ተነሳሽነት (motivation) ቢጀመርም ከቅዠት ቀጠና አልፎ የመሄድ አቅም የለው፡፡ ዲሲፕሊን ማለት አንድን ማድረግ ያለብኝን ነገር ስሜቴ ቢፈቅድም ባይፈቅድም መደረግ ስላለበት ብቻ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ማንኛውም ችሎታና ብቃት ከዲሲፕሊን ውጪ ከንቱ ነው፡፡ ምክንያቱም ዲሲፕሊን ከሌለኝ ምንም እንኳ የማድረጉ ብቃት ቢኖረኝና በነገሩ ባምንበትም ያንን ነገር ማድረግ ያስቸግረኛል፡፡ በሌላ አባባል ዲሲፕሊን ከሌለኝ መልካም ልማድን ለማዳበር ፈጽሞ አልችልም። ሕይወቴን በዲሲፕሊን ካልመራሁ የምተገብረውን ነገር የሚወስንልኝ ያመንኩበት መርህ ሳይሆን የእለቱ “ሙድ” ይሆናል፡፡ ይህ እንዳይሆን ራሳችንን ለመምራት ጤናማ የሆነን ዲሲፕሊን ማዳበር የግድ ነው።'' Paulo Coelho መልካም ምሽት የግሽ ዓባይ ግቢ ተማሪዎች ህብረት
~ Dear students; who are in transition from first to second year While you enjoy your summer break, we urge you to think ahead and prepare yourself for the next task: choosing your major department when you return to campus. To help you make the best decision, we recommend you to use some portion of your free time to do these essential things. First, reflect on your natural talents, academic strengths and career goals to find a field that truly fits you. Second, research different departments to understand their course requirements, knowledge you will acquire and the job opportunities they offer thereafter. Nowadays, knowledge is free. You can google, search on you tube or ask other social media platforms so that you can easily access relevant informations about the department that you are interested in. Third, consult senior students or professionals in those fields to get real, honest advice about what to expect. By spending just a small part of your vacation on this reflection and preparation, you can fully enjoy your summer while ensuring you return to campus ready to make a confident choice that sets you up for a successful future. Bon ete! Gishabay Campus Students Union
~ Discipline Discipline is the most important ingredient of success that gets us to the finish line. In university, the biggest challenge we face isn't just the difficulty of the books or the exams that we take, it’s managing our own time, distractions and choices. Discipline is not about punishing ourself nor living a silent life. It is simply choosing what we need most over what we want now. When the excitement fades, life gets tireful and the exams get tough, it is our daily discipline and habits that will carry us through. Therefore, we have to master our days, protect our focus and build our future. Bon ete! Gishabay Campus Students' Union
~ Dear students, This summer vacation is the most important opportunity for you to strike a perfect balance between recharging your energy and reinventing yourself. After a busy academic year in Bahir Dar, the first thing should be to rest your mind catch up on rest, dive into hobbies and spend quality time with family and friends. However, the best thing you should do is a touch of self-improvement. Use this free time to learn practical skills like editing, developing soft skills, new language, or financial literacy and take on a short internship, or volunteer for a cause you care about. By mixing financial vacation with a little personal growth, you will return to campus in the fall feeling completely refreshed, highly motivated and a step ahead of the next academic year. Bon ete!! Gishabay Campus Students' Union
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግሽ ዓባይ ግቢ የተማሪዎች ሕብረት pinned «~ ለአመታት የለፋችሁበት፣ የደስታና እንቅልፍ ጊዜያችሁን ቀንሳችሁ፤ ከእድሜያችሁ ቀንሳችሁ ቀንና ሌሊት አምብባችሁ፤ አሳይመንት፣ የአጋማሽ ፈተና እንድሁም የማጠቃለያ ፈተና እየወሰዳችሁ፣ እያለፋችሁ እዚህ ደርሳችኋል።... ለ12 ዓመታት ገደማ የቀን ቤታችን ትምህርት ቤት ነበር። ላለፉት አራትና አምስት ዓመታት ደግሞ ቀንና ማታ... በቃ ሙሉ ቤታችን ዩኒቨርሲቲ ነበር። አድስ ማህበረሰብ፣ አድስ ጓደኛ፣ አድስ…»
~ ለአመታት የለፋችሁበት፣ የደስታና እንቅልፍ ጊዜያችሁን ቀንሳችሁ፤ ከእድሜያችሁ ቀንሳችሁ ቀንና ሌሊት አምብባችሁ፤ አሳይመንት፣ የአጋማሽ ፈተና እንድሁም የማጠቃለያ ፈተና እየወሰዳችሁ፣ እያለፋችሁ እዚህ ደርሳችኋል።... ለ12 ዓመታት ገደማ የቀን ቤታችን ትምህርት ቤት ነበር። ላለፉት አራትና አምስት ዓመታት ደግሞ ቀንና ማታ... በቃ ሙሉ ቤታችን ዩኒቨርሲቲ ነበር። አድስ ማህበረሰብ፣ አድስ ጓደኛ፣ አድስ ትምህርት፣ አድስ አካባቢ፤ ሁሉም ነገር አድስ...። ሁሉም ነገር አለፈ። ...አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲያችንን እያመሰገንን ወደ አድስ የሂወት ምዕራፍ መሸጋገር ግድ ይለናል። ሁሉንም ነገር ያስተማረን፣ የምንወደው የትምህርትና የሂወት ቤታችን ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በላይ ከአህጉራችን አፍሪካ ብሎም ከዓለም ስመ-ጥር የትምህርት ተቋም ሆኖ እንድቀጥል ምኞቴ ነው። ተመራቂ ጓደኞቼ በሙሉ በድጋሜ ሀገራችሁንና ቤተሰቦቻችሁን የምታገለግሉበት መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ። መልካም ጉዞ Au revoir🙌 Bonne carriére! ተማሪ ያለው ከተማው (ወንድማችሁ🥺) የግሽ ዓባይ ግቢ ተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
~ ውድ ተመራቂ ተማሪዎች መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ። የግሽ ዓባይ ግቢ ተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
~ ለተመራቂ የተ/ህብረት ስራ አስፈፃሚዎች ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: እንኳን ደስ አላችሁ! Congratulations! :::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: ውድ ጓደኞቼ፤ ዛሬ የደስታችሁ ቀን ብቻ ሳይሆን፣ ከትምህርታችሁ ጎን ለጎን ለተማሪው ማህበረሰብ ሌት ተቀን ስትደክሙ የነበራችሁበት ያ ያላሰለሰ ጥረትና ታታሪነት በድል ያበቃበት ታላቅ ዕለት ነው። ይህ ማዕረግና የዛሬው ውጤት በግሽ ዓባይ ግቢ የዘራችሁት መልካም ስራ፣ የጽናትና የከባድ ድካማችሁ እውነተኛ ፍሬ ነው። በዚህ የጋራ ጉዞአችን ውስጥ ያካፈላችሁን ልምድና ያሳያችሁት መደጋገፍ ለእኛ ትልቅ መመሪያችን ነው። ጓደኝነታችን ከስራ ባለፈ፣ በፈተና ውስጥ መፅናናትን ያስተማረን እውነተኛ ስጦታችን ነበር። በህብረታችን ውስጥ ያኖራችሁት ውብ አሻራ መቼም አይረሳም። በሄዳችሁበት የህይወት መስክ ሁሉ ስኬት፣ ሰላምና ደስታ አብሯችሁ ይሁን! :::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: ጓደኝነታችሁ ኩራታችን፣ ታታሪነታችሁ ደግሞ መመሪያችን ነው!!! :::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: C O N G R A T U L A T I O N S !!! ሰኔ 2018 ዓ.ም(June 2026) በሪሁን እንደሻው የተ/ህብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ ተጠሪ
без подписи
без подписи
без подписи