tgindex
ጊዜን መሸከም

ጊዜን መሸከም

Статистика
Последний пост
11 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
171
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
228
23 постов
Вовлечённость
133,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
31
1/48двое суток
35
1/72трое суток
38

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • አብዝቼ ከምወደውና እጅግ ከማደንቀው ታላቁ ቃኚ (ገጣሚ) በዕውቀቱ ሥዩም ጋር እና ከቃኚ ውብአረገ አድምጥ የዘራፊው ማስታወሻ ጋር

  • “መጽሐፍ ማንበብ ያቆመ ማኅበረሰብ ይሞታል!” ደራሲ ሬ ብራድበሪ በጭራሽ ኮሌጅ አልገባም። ወጣትነቱን በሎስ አንጀለስ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ያገኘውን መጽሐፍ ሁሉ እያነበበ በማሳለፍ፣ “ከመጻሕፍት ክምችቶች ተመርቄያለሁ” ብሎ እስከመናገር ደርሷል። እሱ ቤተ መጻሕፍትን ብቸኛው እውነተኛ ዩኒቨርሲቲ እንደሆነ ያምን ነበር—የሰው ልጅ ነፍስ በቀለምና በወረቀት ላይ ተቀርጾ የተጠበቀበት ቦታ። ብራድበሪ ፦ “አንድ ባህል የሚሞተው ሰዎች ማንበብ ሲያቆሙ ነው።” በሚለው ዝነኛ አባባሉ ይታወቃል፡፡ ይህ በመንግሥት ሳንሱር ዙሪያ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ሳይሆን፣ በገዛ ፈቃድ ስለሚደረግ አዕምሮን የማሽመድመድ አደጋ የተነገረ ነው። ብራድበሪ ወደ ፈጣንና ጥልቀት ወደሌላቸው የመዝናኛ ዓይነቶች በተጓዝን ቁጥር፣ ለጥልቅ አስተሳሰብ የሚያስፈልገውን ትዕግሥት እናጣለን ብሎ ይሰጋ ነበር። ለእሱ፣ መጽሐፍ ሕያው ነገር ነው—አንድን ሥልጣኔ በጤናማ አስተሳሰብ ጠብቆ የሚያቆይ፣ በዘመናት መካከል የሚደረግ ውይይት ነው። ያ ውይይት ሲቋረጥ ግን፣ ባህሉ ራሱ መደርመስና መክሰም ይጀምራል። ምንጭ አዲስ አድማስ

  • без подписи

  • በህይወት የደከመ፣ በመሆንና ጊዜን በመሸከም የተሰላቸ መንፈሱ ሞትን ሁሉ እንዳስመኘው ይነግረናል። ደጋግሞ ሞትን ሊጎነጭ ሞክሮ በፍርሃቱ እንደተወው እንዲህ ይናዘዝልናል። “ወደ የትኛው አድማስ ብሰደድ ሕመሜን እሸሸው ይሆን? መከራዬን እንዴት ላመልጠው እችላለሁ? እኔ እንጃ! ምናልባት ደፋር ከሆንሁ ሞቴ ከነዚህ ሁሉ መከራዎች ሊሸሽገኝ የሚችል ዓለሙ የሚሸሸው ስርቻ ይመስለኛል። ሆኖም ወደ ሞት የተጓዝሁባቸው መንገዶች ሁሉ ከታዛው ሲደርሱ በፍርሃት ክብ መንገድ ዳግም ከህይወት ደጅ ያደርሱኛል።’’ ለዚህም ነው ርዕሱን የሞት መልስ ቅኝቶች ለማለት የወደድነው። ፍርሃቱ ባይሸብበው ሞቶ ነበርና። ሞትን ሞክሮ ወይም በመሞት ላይ ወስኖ የተመሰለን እንዴት አልሞተም ይሉታል? አንድ ሰው ቁርጠ ሃልዮ ከደረሰ ያሰበውን ድርጊት አድርጎታልና። አንድም አንድ ደራሲ ስራውን ካቀረበ በኋላ ደራሲው ሞቷል ይባላልና። ጊዜን መሸከም ከምንምነት ተነስቶ በመሆን አልፎ ወደ ምንምነት የመንደርደርን የህይወት አዙሪት የፈከረበት ስራ ነው። ምንምነቱ ባለው የተፈጥሮ የመሆን ሀቅም ወደ ህይወት አደገ። ያ ህይወትም በመውጣትና መውረድ እሽኮለሌ ተንፏቅቆ ወደ ምንምነት ይደርሳል። እስኪ ይሄን የምንምነት መንገድ ሰፋ አድርገን እንየው። 1. በመጀመሪያ ምንም ነበር የህይወትን ጽንስ ለመረዳት የማይቃትት የለም። ህይወት እንዴት ተጀመረ? ይሄ ሁሉ መሆን ከየት ተነሳ? አስገኝው ማን ነው? ለመሆኑ ከመፈጠራችን በፊት ምን ነበር? ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ይሄን ጥያቄውን “ለምን አልፈጠርህም እስክትፈጥር ድረስ?” ሲል ይጠይቃል። ከሳይንህ እስከ ሃይማኖት ብሎም እስከ ሚት ድረስ ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ያልምከረ የለም። ብዙዎች ግን ከመሆን በፊት ምንምነት ነበር ይላሉ። ምንምነት ባዶነት ወይም ኦናነት ማለት አይደለም። ምንምነት ማለት መሆንን የመሆን ጉልበት የታጠቀ የፍጥረት ሁሉ የመጀመሪያ ወይም የጋራ መልክ ነው ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ቁጥር 2 ላይ “ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ።” በማለት አንዳችም አልነበረም በሚለው ቃል ምንምነትን ሊነግረን ይሞክራል። ጊዜን መሸከምም ተመሳሳይ መልክ አላት። የህይወትን ውል ለመፍታት ከጽንፈ ዓለሙ ጥንስስ ለመነሳትና ሀዘንና መከራ ብሎም ሞት የህይወት አይነተኛ መልኮች ናቸው የሚል መሰረት ለማስያዝ ይቃትታል። ምንምነትን በኦናነት ብሎም በጨለማነት ይመነዝረዋል። ያ ምንምነት መልኩ ጥቁርና በፈጣሪውም ልቦና ውስጥ ይም ህይወት ይሁን የማለት ቁዘማ ነበር ይለናል። - - - ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 8 የተወሰደ! ሙሉውን የቴሌግራም ገጻችንን በመቀላቀል ያንብቡ!

  • ወይ መገጣጠም ደሞ #የመጽሐፍት_ቀን ነው አሉ😊 የዚህ ዘመን የሥነ ጽሑፍ ወዳጅ፣ በተለይ የእኔ #ትውልዶች ምልክቶቻችሁን ንገሩን ቢባሉ፣ ምልክታችን ብለው ከሚጠቅሷቸው መካከል #ዲጅታል_መጽሔቶችን ተጠቃሽ ያደርጋሉ ብየ ዐስባለሁ። ከእነዚህ መካከል ደሞ #ባይራ_ዲጅታል_መጽሔት ከግንባር ቀደሞቹ የምትሰለፍ #ታላላቆች ነን ብለው ሐሳብን የትውልድ መልክ ሊያደርጉ የተነሡ ዕውቀትም ትጋትም ሲደመር ብዙ ቅንነት የሞላቸው ልጆች የመሠረቷት ናት። ምናልባት የምታምኑኝ ካላችሁ እምነቴን ሳላጎድል ከምጋብዛችሁ የሥነ ጽሑፍ በአጠቃላይ ነገረ ኪን መጽሔት ጋብዘን ብትሉኝ #ባንራታ እላችኋለሁ፤ ተቀላቀሉ። በ"ጊዜን መሸከም" መድበለ ቅኚት ( የግጥም መድበል እንደማለት) ወንድም ውብአረገ አድምጥ የራሱን ፍካሬያዊ ዳሰሳ አድርጓል ገብታችሁ ኮምኩሙ። ደሞ ውቤን ዝም ብላችሁ በብዙ ጠብቁት። በቃ በብዙ... በዚህ ሊንክ ይገቡ https://t.me/Bayradigital ውብአረገ አድምጥ ልዑልሰገድ አስማማው @ብርሃን ደርበው Yonas Hailemarkos እና ምክትል አዘጋጇ (ይቅርታ ስም ዘንግቼ ነው🙏) ወንድማዊም ክነታዊም አክብሮቴን መውደዴን ውስዱ💜🙏 እንዲሁም አምደኞች Yonas Tadesse Berhe Yodit Amanuel @ፍሬው ማሩፍ Zufan Kifle ፋሲካው ጌታቸው ዓለማየሁ ታየ እና ያልጠቅስኳችሁ ደስ ትሉኛላችሁ🙏 በርቱልን ──✵❂✵── የሞት መልስ ቅኝቶች! መንደርደሪያ… ሞት በአጀባው የታደለ ነው ያስብላል። በዘመናት የተነሱ ከያንያንና ጸሐፍት ስለ ሞት እልፍ ብለዋል። አንዳንዶቹ ሞት የማይቀለበስ ናዳ መሆኑ ህይወታቸውን ውል አልባ አድርጎባቸው እየታመሙ ጽፈዋል። አንዳንዶቹ በሩቅ እያዩ እንዳልናቁት፤ ፊት ለፊት ሲታገኙት ደግሞ መሸሸጊያ ሲቸግራቸው ተመልክተናል። ከሞቱ በፊት ስለ ሞትና መለኮት፣ ብሎም ስለ ህይወት ውዳሴና ስለ ሞትም ህያውነት በብዙ ከጻፉ ሰዎች ውስጥ አንደኛው ታላቁ የህንድ ባለቅኔ ራቢንድራናት ታጉር ነው። ታጉር ደራሲ፣ ገጣሚ፣ የሙዚቃ አዘጋጅና ጸሐፌ ተውኔት ነው። የ1913 እ.አ.አ የስነ ጽሑፍ ኖቤል ሽልማት አሸናፊ ነው። ታጉር ያረፈው እ.አ.አ በነሐሴ 07፣ 1941 ዓ.ም ነው። የመጨረሻ ግጥሙን የጻፈው ከመሞቱ ከሰባት ቀን በፊት እ.አ.አ ሀምሌ 31፣ 1941 ዓ.ም ነው። ታሞ አልጋ ላይ ሆኖ ሞቱን እየጠበቀ የጻፋቸው ግጥሞቹ ታጉር ካረፈ በኋላ Shesh Lekha በሚል ርዕስ ታትመዋል። ወደ 15 የሚሆኑ ግጥሞች ናቸው። ምንም ርዕስ አልተሰጣቸውም። ግጥሞቹ እንደ ሌሎቹ የታጉር ስራዎች ውበትና ቋንቋ ላይ አይምነሸነሹም። በችኮላና ፊት ለፊት እየተወረወሩ በስሜታቸው ግን የሚናደፉ ግጥሞች ናቸው። በእነዚህ ግጥሞቹ ውስጥ ህይወት፣ ሞትና መለኮት ደጋግመው ተነስተዋል። በተለይ እያንዣበበት ካለው ሞት ጋር ፊት ለፊት መጋፈጡ ቁጡ ያደረገው ይመስላል። ከሞት በኋላ ያለውን ዘላለማዊ ህይወት መጎናጸፍ በሚቃጣው ድምጸት ይቀኛል። በአንደኛው ግጥሙ እንዲህ ይላል May mortal bonds decay May the great universe embrace me And in my heart know without fear The great unknown. ይሄን ግጥም በደምሳሳው እንዲህ መተርጎም ይቻላል። (ምናልባት ያስተሳሰሩን ሙት ሰንሰለቶች ይበጠሳሉ ያቅፈኝ ይሆናል ይህ ሰፊ ህዋ ጽንፈ ዓለም ሁሉ ያለ አንዳች ፍርሃት ያላንድ ዋሾ ቃል ታላቁን ምስጢር ይህ ልቤ ያውቃል።) በዚህ ግጥሙ ታጉር ስለ አይመረመሬውና አይታወቄው ታላቅ የሞት ዓለም በእርግጠኝነት አውቃለሁ እያለን ነው። ሞት ባይመረመረም ለታጉር ነፍስ ግን ቅርብ ነውና። እንዲሁም በሌላ ግጥሙ Death like Rahu Casts shadows only But cannot sap life’s divine ambrosia: Entrapped by this material world This I know for sure ይሄንና በመሳሰሉት ግጥሞች ስለሞት፣ ስለማይታወቀው ዘለዓለማዊ እውነት ይቃትት ነበር። Dr Sultana Jahan ታጉርና ሩሚ ሞት ላይ ያላቸውን አተታይ ባተተበት ጽሑፉ Radice (1987) እና Bhattacharya (2006) የሚባሉ ደራሲዎችን እማኝ አድርጎ እንዲህ ይለናል። “Tagore’s approach to death in Shesh Lekha is deeply meditative, tender, and accepting, rooted in Hindu Vedantic thought, particularly the Upanishadic concept of the eternal soul (Atman) and its union with Brahman (the Supreme Reality). Tagore perceives death not as annihilation but as a return to cosmic unity, a continuation rather than a cessation of existence. His philosophy resonates with the Hindu belief in the cyclic nature of life, death, and rebirth (samsara).” ታጉር ሞትን እንደ መጥፋት አይመለከተውም። በጥንታዊ የቬዳ አስተሳሰብና በአፕናሻድ ፈትለ ነገር የመንፈስን ዘለዓለማዊነትና ከታላቁ እውነት ጋር ያላትን ስሙር ህብረት ይፈክራል። ለታጉር ሞት መበስበስ አይደለም። ሞት ከጽንፈ ዓለሙ ጋር ህብረትን ፈጥሮ እያረገዱ የመቀጠል እንጂ አፈርና ትቢያ ሆኖ መቅረት አይደለም። ስለዚህም ሞቱ ላይ ይመሰጥበታል። ያላየውን እውነት በነቃ መንፈስ ሊቀበለው ይታትራል። ግጥሞቹን በፍጥነት ከህሊናው ዲብ እያስፈተለከ በቀጥተኛ ድምጸት ያወርዳቸዋል። የቸኮለ የመንፈስ መንገደኛ በቃል ልሳኑ ይወረወራቸው የመጨረሻ ትንፋሾች ናቸው። ጊዜን መሸከም ጊዜ በረርክ በረርክ ግና ምን አተረፍክ ግና ምን አጎደልክ እንዲል ታላቁ ደበበ ሰይፉ የዘውዴ አለልኝ ግጥሞችም በጊዜ ሚዛን ውስጥ እየተሰፈሩ ለመትመም መሆንን መሸከም የገደዳቸው ናቸው። የዘውዴን ግጥሞች ለመረዳት ራሱ ገጣሚው እንደ መግቢያ፣ እንደ ቀዳሚ ቃል ብሎም በየመጽሐፉ መካከል እንደ መክፈያ ያስቀመጣቸው ማብራሪያዎች ከበቂ በላይ ናቸው። እንዲያውም ሌላ ለማሰብም እድል አይሰጡም ማለት ይቻላል። ራሱ የራሱን ስራ ሂሶታል ቢባል ያስሄዳል። ለአብነት እንይ ቢባል እንኳን ግጥሞቹን በጥሪአችው አማካኝነት በቀለማትና በሙዚቃ ምሳሪያዎች ከፋፍሏቸዋል። ጥቁር፣ ስማያዊ፣ ሐምራዊና ነጭ ሲል ስይሟቸዋል። እንዲሁም በድምጸታቸው አማካኝነት በዋሽንት፣ በክራር እንዲሁም በነጋሪት መስሏቸዋል። ምን ማለት እንደሆነና ትርጓሜአቸውንም አስቀምጧል። የግጥሞቹን መንፈስ ብሎም ገፊ ምክንያት በአንዳንድ ምልክቶች አማካኝነት ግን የራሳችንን ብያኔ መስጠት እንችላለን። ከቀዳሚ ቃሉ ጀምሮ በግጥሞቹ ቀለም ሳይቀር የሚስተዋል አንዳች ደብዛዛ ብርሃን አለና እሱን እንከተል። “ምስጋና አይደለም የደበዘዘ መተጣጣት ነው” ሲል በቀዳሚ ቃሉ ባስቀመጠው ጽሑፍ ላይ ሆነን የግጥሞችን መንፈስ ለመገርመም ብንሞክር ቃል ገደፋችሁ አንባልም። በቀዳሚ ቃሉ “ራሴን ከማጥፋት ውጭ ሌላ ማምለጫ እንድሌለኝ ተረድቻለሁ። ሆኖም ሞቴ ከሕይወት የተሻለ ላይሆን ይችላል።” ይለናል

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ሕይወት ቢራቢሮ ናት..?                       ... ወይስ የወንዝ አበባ?          (በነገራችን ላይ "የነፍስ  ዕንባ" መጽሐፌ፣ የምታሳዛነኝና የሀገሬን ሰዎች ልብ ያየሁባት መጽሐፌ ናት።)         የህይወት ትርጉሙ ራዕዩና ህልሙ ብርታቱ ድካሙ ውልደቱ ወይ ሞቱ የአልፋና ዖሜጋው፣ አቆጣጠር ስዓቱ እንዴት ተጀምሮ፣ እንዴት ነው እሚጨረስ? ጅምር ከፍጻሜው... በምንድን ነው እሚለይ? መስፈሪያ ሚዛኑስ? የመኖር ትርጉሙ? የመሞት ጉዳቱስ ህብረቱ ምንድን ነው? ግንጥል ልዩነቱስ? እንደ ቢራቢሮ፣ "ውበትን ፍለጋ" ሲታትሩ መሞት? ሳይመሽ ወይ ሳይነጋ? ውበትን አፍቅሮ መኖርን ዘክሮ ውበት ባዩ ቁጥር፣ እሾሁን ሳይፈሩ መወጋት በፍቅሩ? ለአድናቆት የላኩት፣ የመቅሰም ቀስት ዙሮ ፍላጻው እራስን... ወግቶ ማለያየት? ከ... ወደዱት ተፈጥሮ? በኩራዝ ወጋገን፣ ተማርኮ በብርሃን ዘለው ያቀፏት ለት፣ ማጣት ህልውናን? መውጣት ከማህበሩ? መሰረዝ ከአጀንዳው?... ወደ ሞት መገስገስ ተፋቶ ሕይወትን? ወይስ? ከወንዝ ዳር በቅሎ፣ እንደ ፈካ አበባ ሁሉን እየሳቡ፣ በውበት ሙሃባ በተፈጥሮ ግርማ ያየን ሁሉ ማቅለጥ፣ እንደ ሌሊት ሻማ? ሁሌ ሲደነቁ ሲወደሱ መኖር? ለግሩም ተፈጥሮ፣ ዘላለም መዘመር? ሁሌ ስለፍካት ሌት ቀን ስለውበት እንደ ሀምሌ ዝናም፣ ማጉረፍ እልፍ ቃላት? ነውስ? የራስ ውበት እንደ ወጥመድ ሁኖ፣ ሰጥቶ ባዕድ አድናቆት ፍቅራቸው አፍርቶ፣ የዘላለምን ሞት እንደ ፅጌ ረዳ... መቀጠፍ መቆረጥ? ያለ ዕድሜ መቀጨት? ተሸቶ በወረት... ከቆሻሻ መጣል የጠወለጉ ዕለት? ሳያፈሩ መድረቅ? ሳያረጁ መውደቅ? ቀን ሳይደርስ መክሰም? በባድ እጅ ተቀጥፎ፣ መለየት ከዚህ ዓለም? ነውስ? ልክ እንደ ጂረቱ፣ እንደ ወንዝ ፏፏቴው መኖር አለመኖር፣ ትርጉም የማይገባው? እራሱን የማይጠቅም? መፈጠር ስለ ሰው? በተመሩት መፍሰስ? ቀን አይቶ መደፍረስ? ጊዜ ሲጥል መንጠፍ? በአጠቡት አሸዋ፣ አልጌ እላዩ ማንጠፍ? መኖሩ ስለ ሰው ማበሩ ለሌላው ፍካት ልምላሜው የሚታይ ለባዳው ለእራሱ እማይገባው? ትርጉሙ ምንድን ነው? አንድምታው ተፈጥሮ የሚሰጠው ትምህርት? ፍችው ተመስጥሮ ሕይወት ቢራቢሮ ናት?፣ ወይስ ወንዝ አበባ? አብናኝ  ነፋስ ነው? ወይስ በናኝ ላባ? ሕይወት የሀዘን ስላቅ? ወይስ የሀሴት እንባ? ሕይወት ማለት ምን ነው? ከየት ነው? እሚወጣ፣ የት ነው? የሚገባ ሲፈልጉት መንደፍ? ነው? ሲፈልግ ማለፍ? መቃጠል በእሳት ክንፍ? ወይስ እንደ አበባ... በውሃ ለምልሞ አልፎ ሀጁን ማቀፍ ሕይወት ቢራቢሮ ናት?፣ ወይስ (የ)ወንዝ አበባ? መውጫ መሰላሉ.... መፍቻው ቁልፍ የቱ ነው?.... አንድምታ ትርጉሙን የሕይወትን አምባ፡፡ @highlight

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • #የአባቶቼን ታሪክ #የአድዋን የድል ዕለት ሳከብር፣ እንደ አንድ ሀገሩን #እንደተቀማ ብኩን ትውልድ ኾኜ ነው💔 ዋ! አንቺ አድዋ "ሀገር አልባ ባላገር" - ኾንኩልሽ ብኩን ተቅበዝባዥ ባንዲራዬን ስከተላት ትርቃለች - እንደ በርሃ ሚራዥ። አንቺ የምድበዳ ምኩራብ ከመሰዊያሽ እንዳይጠፋ፣ እንዳይከስም እሳቱ ምን ቢታጠን መዳን ይኾን፣ ለረከሰ ነፃነቱ? ረመጥ ነው እሳት፣ የሚያንገበግብ ቁስል በስምሽ እየማሉ - አንድምታሽን መወንጀል። ናፈቅሽኝ አንቺ ሀገሬ፣ ታመምኩልሽ እናትዓለም የሚቀብርሽ እድር እንጅ፣ የሚያድንሽ ምሁር የለም። @አብይ ወሬ Zewdie Alelgn Aragew

  • ቤተሰቦይ 👋 ባይራ ዲጅታል መጽሔትን እያነበባችሁ ነወይ ሸጋ ሸጋ ሐሳብ ይዛ መጥታለች https://t.me/Bayradigital

  • ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 8 ነገ ምሽት ይጠብቁን!! Stay tuned💚💛❤️ ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!

  • እናቷ #ገበያ እን ደሔደችና ስትመጣ ከረሜላና ብስኩት ይዛልሽ ትመጣለች ብለን ያታለልናት ሕፃን፣ በግቢው ከስጡ ሰር ከወፏ ጋር ስትጫዎት ነበር። ድንገት ወፏ በረረች፣ ምን እንዳለቻት እንጃ "ወዮ ወዮ ወዮ እናቴ" እያለች አለቀሰች። የእናቷን መሞት ነገረቻት መሰለኝ💔

  • без подписи

  • አድዋ እና የካቲት ወር #አድዋ እና ኪነ ጥበብ አድዋና አዝማሪዎች! አዝማሪ ሀሰን አማኑ በአድዋ ጦርነት ወቅት ከአርባኞች ጀርባ ወኔ በመስጠት አዝማሪዎች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል:: ከስር የምትመለከቱት ወሎዬ አዝማሪ ሀሰን አማኑ ይባላሉ። አይነ ስውር ነበሩ። ሐሰን አማኑ በመሳፍንቱም፣ በነገሥታቱም እጅግ የታወቁ እና የተከበሩ አዝማሪ ነበሩ፡፡ በአድዋ ጦርነት ወቅት ጦር ሜዳ ድረስ በመሄድ በግጥም እየሸለሉ እና እየፎከሩ ጦረኞችን ሲያጀግኑ የነበሩ ሰው ነበሩ። ሐሰን አማኑ ማየት የተሳናቸው አዝማሪ ናቸው፡፡ ውልደታቸው #ከወሎ ነወ። ስለእሳቸው ታሪክ የተጻፈ መጽሐፍ እስካሁን አላገኘሁም፤ ከግጥሞቻቸው በስተቀር። ሐሰን አማኑ በመሳፍንቱም፣ በነገሥታቱም እጅግ የታወቁ እና የተከበሩ አዝማሪ ነበሩ፡፡ በዋናነት የንጉሥ ሚካኤል አዝማሪ ቢሆኑም በዐጼ ዮሐንስም በዐጼ ምኒልክም ዘንድ እንዲሁ ተወዳጅ ነበሩ፡፡ እንደ ሌሎች አዝማሪዎች ሁሉ ሀሰን አማኑም በሰላሙ ጊዜ ያዝናናሉ፤ በጦርነትም ጊዜ ያበረታታሉ፣የጀግንነትን ሥራ የፈጸሙትንም ያሞግሳሉ፣በሞት ጊዜም ያጽናናሉ፡፡ ሸዋ ነው ሲሉት፣ ዓድዋ የታየው፤ ሺናሻ መላሽ፣ ወንዱ አባ ዳኘው። ወዳጁም ሣቀ፣ ጠላቱም ከሳ፤ ተንቀሳቀሰ ዳኘው ተነሣ፤ አራቱም አህጉር፣ ለሱ እጅ ነሣ። (ዝክረ ነገር፤ ገጽ 880) በተመሣሣይ መልኩም፣ ከዓድዋ ጋር በተያያዘ ስለወሎው ንጉሥ ሚካኤልና ስለታላቁ ጀግና ፊታውራሪ ገበየሁ (አባ ጎራው) ሐሰን አማኑ የሚከተሉትን የሙገሳ ግጥሞች ተቀኝቷል። ስለንጉሥ ሚካኤል እንዲህ አሉ፦ ማን በነገረው ለጣሊያን ደርሶ፤ ሚካኤል መጣ ረመጥ ለብሶ። (ዝክረ ነገር፤ ገጽ 883) (መጪው "ሚካኤል" ሰውም መልአክም ነው። ሰው ሲሆን፣ ንጉሥ ሚካኤል ነው። መልአኩ ሚካኤል ሲሆን ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስን አትጊና አጽኚም ነው።) ስለፊታውራሪ ገበየሁ የተገጠሙት ሁለት መንቶዎች ግን በስፋት የሚታወቁ ናቸው። የነዚህም ገጣሚ ሐሰን አማኑ ነው። ታጭዶ ሲወቃ፣ ዐድዋ ላይ ገብስ፤ አናፋው ዘልቆ፣ (ጎራው) በመትረየስ። ዐድዋ ሥላሴን፣ ጥሊያን አረከሰው፤ ገበየሁ በሞቴ፣ ግባና ቀድሰው። (ዝክረ ነገር፤ ገጽ 885) ማጣቀሻ:- ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል፣ዝክረ ነገር፣አዲስ አበባ፣1962፡፡ ከነገረ መጻሕፍት ዓድዋ (፲፩) ------------ አዝማሪዎች እና አደዋ ---------------------------- ፪.አዝማሪ ሀሰን አማኑ ---------------------- ስለ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ደግሞ አዝማሪ ሀሰን አማኑ እንዲህ ብሎ ነበረ። "ጣልያን ገጠመ ከዳኛው ሙግት አግቦ አስመሰለው በሠራው ጥይት ። አሁን ማን አለ በዚህ ዓለም ጣልያን አስደንጋጭ ቀን ሲጨልም ። ግብሩ ሰፊ ነው ጠጁ ባሕር የዳኘው ጌታ ያበሻ ባሕር። አይኮረተም እጁ የዘናው ወንዱ ምኒልክ ዝንታለም ይቅናው። ወዳጁም ሣቀ ጠላቱም ከሳ ተንቀሳቀሰ ዳኘው ተነሳ አራቱ አህጉር ለሱ እጅ ነሣ። ፈረሱ ዳኘው ሚስቱ ጣይቱ ምጥዋ ወርዳ ቀዳች ወጥ ቤቱ። ምንጭ፦ኢትዮጵያ የድህረ ገፅ