tgindex
Gokazi

እንኳን ደና መጡ ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን! FOR ANY PROMOTION 📩 @GoKazi_Admin

Последний пост
5 июл. 2025 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
9
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
169 554
−519 за 3 дн.
Сутки
−273
−0,16%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
24,1 тыс
8 постов
Вовлечённость
14,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 9
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 5 июл. 2025 г.40,3 тыс23724

    የአለም ጤና ድርጅት ሀገራት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች ላይ ጭማሪ እንዲያደርጉ ጠየቀ። ድርጅቱ በምርቶቹ ላይ የሚደረገው የታክስ ጭማሪ የ50 ሚሊየን ሰዎችን ህይወት ያድናል ብሏል። የአለም ጤና ድርጅት በ2035 ሀገራት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች ላይ የሚጥሉትን ታክስ በ50 በመቶ ለመጨመር እንዲችሉ የሚገፋፋ ንቅናቄ ጀምሯል። ድርጅቱ '3 by35' ሲል የሰየመው ኢንሼቲቭ ገቢ ከማስገኘት በተጨማሪ መከላከል የሚቻሉ ገዳይ በሽታዎችን በመቀነስ የሚሊዮኖችን ህይወት ይታደጋል ብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የብዙሃኑን ህይወት እንደሚቀሙ በመጥቀስ እነዚህን ምርቶች ከመጠቀም በሚመጡት እንደ የልብ ህመም ፣ ካንሰር እና ሌሎችም  ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አሁን ላይ 75 በመቶ የሰው ልጅ የሞት ምክንያት እየሆኑ ነው ሲልም ገልጿል። የታክስ ጭማሪው የምርቶቹን ፍጆታ በመቀነስ ለመንግስታት ተጨማሪ ገቢ ያመጣል የሚለው ድርጅቱ ወደ ትግበራ ለመግባት ጊዜው አሁን ነው ብሏል። ንቅናቄው በሚቀጥሉት 10 አመታት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች የሚጣልን የኤክሳይዝ ታክስ በመጨመር 1 ትሪሊየን ዶላር ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን የተገኘው ገንዘብም ለሀገራት ልማት እና የጤና ተደራሽነት ይውላል ተብሏል። ከ2012-2022 ባሉት 10 አመታት 140 ሀገራት በምርቶቹ ላይ የታክስ ጭማሪ እንዳደረጉ ሲመላከት ደቡብ አፍሪካ እና ኮሎምቢያ በጥሩ ምሳሌነት ተነስተዋል። ድርጅቱ አንዳንድ ሃገራት እነዚህን ምርቶች ለሚያመርቱ ኢንዱስተሪዎች ማበረታቻ ይሰጣሉ በሚል ሲተች ሃገራቱ እንደዚህ አይነት ማበረታቻዎችን እንዲያነሱም ጠይቋል። ምንጭ CNN Sayefuz

  • 4 июл. 2025 г.22,7 тыс354

    ራሺያ ግዙፏን የማዕድን ስፍራ ተቆጣጠረች። በአውሮፓ ግዙፍ የሆነውን የሊቲየም ክምችት የሚገኝበትን ስፍራ በዶንባስክ ግዛት የሩሲያ ጦር ተቆጣጥሯል ። ወደ ፊት እየገሰገሰ የሚገኘው ጦሩ 74 ከመቶ የዶምባስክን ግዛት መቆጣጠር ችሏል ። ሼቭሼንኮ የተባለው ስራ በራሽያ ቁጥጥር ስር መዋሉ አሜሪካ ከኪዬቭ ጋር የገባችው የማዕድን ማውጣት ውል ‘ውሃ በላው’ ሊባል የተቃረበ ይመስላል ። ትራምፕ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባይደን በሞኝነት ለለገሱት በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በካሳ መልክ ማዕድን አውጥተው እንዲጠቀሙ ከዩክሬን ጋር መስማማታቸው ይታወሳል ። የኬዬቭ ሹማምንት አሜሪካ ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንድትሰጣቸው ቢማፀኑም ዋሺንግተን እንቢ ብላለች ። ይባስ ብሎ ለአሜሪካ ሊሰጥ የነበረውን የማዕድን ማውጫ ስፍራ አሁን የሩሲያ ጦር ተቆጣጥሮታል ። ሊቲየም ለኤሌትሪክ መኪና ባትሪ ማምረቻ ዋነኛ ግብዐት ነው ። ቻይና ይህን ምርት እየተጠቀመች የኤሌክትሪክ መኪናን በገፍ እያመረተች ነው ። አሜሪካ እና አውሮፓም የኬዬቭን ሊቲየም ማዕድን በገፍ ቋምጠውበታል : ይሁን እና ዋነኛውን ስፍራ ራሽያ ይዛዋለች ። ሌላኛው የማዕድን ማውጫ ለማዕከላዊ ዩክሬይን የቀረበ መሆኑ እፍይታ ነው ። ግን እንደ ሼቭሼንኮ አይሆንም ። ምንጭ BBC Sayefuz

  • 3 июл. 2025 г.19,2 тыс324

    2018 የበጀት ዓመት የኢኮኖሚ እድገት 7.1 በመቶ እንደሚሆን የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት/IMF ገመተ። በተመሳሳይ የዋጋ ግሽበቱ በ2017 በጀት አመት መጨረሻ ይሆናል ካለው 16.6 በመቶ በ2018 ወደ 12 በመቶ እንደሚወርድ ነው የተነበየው። የመንግስት ትንበያ እንደሚያሳየው በ2018 የኢኮኖሚ እድገቱ ወደ 8.9 በመቶ እንደሚደርስ ነው። የገቢ/ኢምፖርት መተባበቂያ ክምችት ወደ 2.1 ወራት ከፍ እንደሚል ገምቷል። ለ2017 የገመተው 1.7 ወር ነበር ይህም ከ2016 በጀት አመት አንፃር ከአንድ ወር በላይ ጭማሪ ነበረው። የውጭ እዳ ክምችት ከጥቅል ምርት አንፃር ወደ 26.6 በመቶ እንደሚርድ የተተነበየ ሲሆን የቀደመው አመት ትንበያ 30.4 በመቶ ነበር። ምንጭ : ኢዜአ Sayefuz

  • 3 июл. 2025 г.17 тыс536

    የሊቨርፑሉ አጥቂ ዲዮጎ ጆታ በስፔን በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ የሊቨርፑሉ አጥቂ ዲዮጎ ጆታ ከወንድሙ አንድሬ ጋር በስፔን በደረሰበት አሰቃቂ የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል። ምንጭ:[Marca] እና [goal.com] Sayefuz

  • 2 июл. 2025 г.17,7 тыс288

    " ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa6.ministry.et/#/result ወይም በ @emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ መመልከት ይችላሉ " - ትምህርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 79,034 ተማሪዎች መካከል 75,085 ተማሪዎች ማለትም 95 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን ገልጸዋል። ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከ1 እስከ 4 የሚሆኑት ከመንግስት ትምህርት ቤቶች መሆናቸው አመልክተዋል። " በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል ያለዉን የውጤት ልዩነት እጅግ እየተቀራረበ መጥቷል " ሲሉ ገልጸዋል። ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል። LINK ፦ https://aa6.ministry.et/#/result Telegram Bot : @MinistryResultQMTBOT ምንጭ : tikvahethiopia Sayefuz

  • 2 июл. 2025 г.21,1 тыс212

    በመዲናዋ በ7 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የኢንዱስትሪ መንደር። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ7 ቢሊየን ብር ወጪ ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ መንደር ለአገልግሎት ለማብቃት በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ፡፡ ከንቲባ አዳነች በአዲስ አበባ ከተማ በ7 ቢሊየን ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ መንደር ጎብኝተዋል፡፡ በዚህ ወቅትም የነዋሪዎችን ጥያቄ የምንመልሰው የሚታዩ ፣ የሚጨበጡ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 93 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የኢንዱስትሪ መንደሩ የመጀመሪያው ምዕራፍ ከ120 በላይ ሼዶች እንዳሉት አስረድተዋል፡፡ ሼዶቹ ለብረታብረት ሥራ፣ ለእንጨት ውጤቶች፣ ለጨርቃ ጨርቅ፣ ለፕላስቲክ እና ለኬሚካል ማምረቻነት፣ የምርት ማሳያ እና መሸጫ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸው። ሼዶቹ ለብረታብረት ሥራ፣ ለእንጨት ውጤቶች፣ ለጨርቃ ጨርቅ፣ ለፕላስቲክ እና ለኬሚካል ማምረቻነት፣ የምርት ማሳያ እና መሸጫ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸው። በተጨማሪም ሰፊ የሥራ ዕድልን ለመፍጠርና የኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ሚናው ጉልህ ነው ያሉት ከንቲባዋ÷ የግንባታው 2ኛ ምዕራፍ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ምርቶች የሚሆኑ ሼዶችን የያዘ ነው ብለዋል። ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በጥቂት ደቂቃ መድረስ የሚያስችል አዲሱ የአቃቂ ቦሌ ካርጎ መንገድ ላይ እና ምርት ማጓጓዝን ታሳቢ ያደረገና ስትራቴጂክ ስፍራ ላይ እንደሚገኝም የከንቲባ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ ምንጭ ፋና Sayefuz

  • 2 июл. 2025 г.25,8 тыс253

    5 ሚሊዩን ዶላር ያገኘው ኢትዮጵያዊው ስራ ፈጣሪ ። ቤተር አውት የተሰኘው ስታርትአፕ በአበልፃጊዎች ምርጡ የማረጋገጨ መሳሪያ እየተባለ እንደሚገኝ ተገልፃል። ነጻ መተግበሪያ የሚጠቀመው ሶፍትዌር አበልፃጊዎች የተጠቃሚዎች ማረጋገጫ የሚያስተዳድሩበትን መንገድ በማቅለሉ ተወዳጅ ሆኗል። ባለፈው ዓመት ወደ ሥራ የገባው የማረጋገጫ ማዕቀፍ በየሳምንቱ ከ150 በላይ ተጠቃሚዎች እንደሚጭኑት መስራቹ በረከት እንግዳ ተናግሯል። የዲጂታል ስርዓቱን ለብቻው በራሱ ጥረት እንዳበለፀገ የሚገልፀው በረከት፤ ዓለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቱ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን የሚበረታታ እንደሆነ አንስቷል። ምንጭ ቴክ ክራንክ Sayefuz

  • 2 июл. 2025 г.28,9 тыс837

    👉🏾በመዲናዋ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይፋ ሆነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት ወስነዋል። የፈተናው ውጤትም ይፋ ተደርጓል። በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል። በ2017 ዓ.ም 79,034 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ተገልጿል። ምንጭ : tikvahethiopia Sayefuz

  • Channel created

Gokazi — tgindex