tgindex
🌙Guiding Moon™

🌙Guiding Moon™

Статистика

#قال_الله_تعالى_﴿ وَذَكِّرۡ فَإِنَّ ٱلذِّكۡرَىٰ تَنفَعُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴾ [ الذاريات: 55] “አስታውስ፤ ያንተ ማስታወስ ለአማኞች ትጠቅማለችና”✨ 🕌 🌿አሰላሙ አለይኩም ኑ እንማማር✨ የተለያዩ እውነተኛ ታሪኮች #Hadis #Quran #Dua #IQuote & other islamic contentochn ያገኛሉ ከእናንተ የሚጠበቀው #join ማለት ነው❕

Последний пост
15 янв.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
70
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
23
21 постов
Вовлечённость
32,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ከረመዷን በፊት… ~ 🕐እንደ ንፋስ በሚከንፈው የዘመን ፍጥነት ውስጥ ሆነን፣ የናፍቆት እና የራህመት ወር የሆነው ረመዳን ከደጃችን ሊደርስ እነሆ ሁለት ወራት ከሁለት ቀናት አከባቢ ብቻ ቀሩት። ነገር ግን በጊዜው እሩጫ ልክ እነዚህን ቀናት እንደ ሁለት ሳምንታት ብንቆጥራቸው ማጋነን አይሆንም። ወዳጄ ሆይ! የረመዳንን ጨረቃ መጠበቅ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ዋናው ቁምነገር ከወሩ ትሩፋት ለመቋደስ ነፍስያን አሁን ላይ ማዘጋጀት ነው። ያልታረሰ መሬት ዝናብ ቢዘንብበትም ምርቱ እንደማይሰምር ሁሉ፣ ከወዲሁ በኢባዳ ያልረጠበች ልብም ረመዳንን በአግባቡ ማስተናገድ ይከብዳታል። ስለሆነም ከዛሬ ጀምረን ራሳችንን እንፈትሽ። የቀን ተቀን ውሎአችንን በቁርኣን ድምቀት እናጅበው፤ ሌሊቱን ከእንቅልፍ በመስረቅ ለጌታችን በሚደረግ ዱዓ እና የለይል ሶላት እናድምቀው። የሶሻል ሚዲያ ጫጫታን ቀንሰን፣ ከፈጣሪያችን ጋር የምናደርገውን ቆይታ እናብዛ። ዛሬ ላይ ልባችንን ካላለዘብናት፣ ነገ ረመዳን ሲመጣ የኢባዳው ጣዕም ሊርቀን ይችላል። የረመዳን ስኬት መሰረቱ የሚጣለው ዛሬ ነው። ስለዚህ ከወዲሁ ፕሮግራማችንን አስተካክለን፣ ልባችንን አፅድተን ያን የከበረ እንግዳ እንጠብቀው። አላህ ለዚያች ለከበረች ወር በሰላም ያድርሰን! ©qelbachn1

  • የኢልም ንያ በአራት ነገራቶች ላይ ይሽከረከራል። ①) መሀይምነትን ከራስ ማስወገድ ②) መሀይምነት ከፍጥረታቱ ማስወገድ ③) ባወቁት ነገር መስራት ④) ከመጥፋት መጠበቅና ህያው ማድረግ ናቸው። 📚 [البَيِّنَةُ للشَّيْخِ صَالِحُ العُصَيْمِيّ(ص٣)] እውቀት ስትፈልግ አላማህና ፍላጎትህ እነዚህ አራት ነገሮች ይሁኑ።

  • ﴿وَاذْكُر رَّبَّكَ كَثِيرًا وَسَبِّحْ بِالْعَشِيِّ وَالْإِبْكَارِ﴾. «سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ ، أشْهَدُ أنْ لَا إلَهَ إلَّا أنْتَ ، تَبَارَكْتَ وَتَعَالَيْتَ ، أسْتَغْفِرُكَ وَأتُوبُ إلَيْكَ ، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِكَ».

  • የሰላት አርካኖች 14 ናቸው እነሱም 1-ለሚችል ቀጥ ብሎ መቆም 2 - ተክቢረተል ኢኸራም(የመክፈቻ ተክቢራ) 3 - ንይ’ያህ ማድረግ፡፡ 4 - ፋቲሓን መቅራት፡፡ 5 - ሩኩዕ 6 - ከሩኩዕ ቀና ብሎ መቆም (እዕትዳል)፡፡ 7 - በሰባቱ አካላት ሱጁድ መውረድ፡፡ 8 - በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ፡፡ 9 - ለመጨረሻው ተሸሁድ መቀመጥ፡፡ 10 - የመጨረሻውን ተሸሁድ መቅራት፡፡ 11 - በመጨረሻው ተሸሁድ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶላት ማውረድ፡፡ 12 - ሰላምታ (ተስሊም)፡፡ 13 - በሁሉም ማእዘናት ውስጥ የእርጋታ (ጡመእኒና) መኖር፡፡ 14 - የማእዘናቱን ቅደም ተከተል መጠበቅ ናቸው

  • ⛓️የዘመናችንን ሁኔታ በትክክል ሲገልጽ በጣም የሚያዛዝን ልብ የሚያደማ  ነው፡- "ሁሉም ነገር በጣም የሚያሳዝን ነው፣ ነገር ግን ማንም ግድ የሚሰጠው (የሚጨነቅ) የለም..." የሴቶች የላላ ሂጃብ ጠባብ ልብሶች የተገለጠ አካል የተለቃለቀ ፊት (ሜካፕ) ጮክ ያሉ ሳቆች ስሜት ቀስቃሽ ሽቶዎች የንግግር ድፍረት ይሄን ሁሉ በሚስቱ በእህቱ በልጁ በእናቱ ላይ እያዬ ምንም አይመስለውም ወንዱ። ሴቷም በሚገርም ሁኔታ 🔸 ይህን ሁሉ እያደረገች "ምን ትመኛለሽ?" ብለህ ብትጠይቃት... 🔸 " ጀነትን መግባት እመኛለሁ" ትላለች። ⁉️ ❗እናተ ሙስሊም ሴቶች ሆይ! ይህ እኮ ያማል!  እውነት ጀነት በዚህ መንገድ ትገኛለች እንዴ?በጭራሽ አትገኝም ⚠️ ይህ ፀያፍ ተግባር በየቤቱ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚታይ ሆኗል ⚠️ ሴት ልጅ የሰውነት ቅርፅና እብጠቷንን በሚያሳይ ፒጃማ በቤቷ ውስጥ ትንቀሳቀሳለች... በአባቷ፣ በወንድሞቿ፣ በአጎቶቿና (ነገሩን በሚረዱ) ወንዶች ልጆቿም ፊት ሳይቀር... ከዚያም አንዳንዴ በሱሪ፣ አንዳንዴ በአጭር ቀሚስ እግሮቿን ገልጣ ትቀይረዋለች። ሱሪው ረጅም ቢሆን እንኳን አንዳንዶች ጭኖቻቸውን እስኪያሳይ ድረስ ያስጠብቡታል (ይወጥሩታል)❗❗❗ በጣም ከመወጠሩ የተነሳ 👌 ልክ ራቁቷን ያለች ይመስላል። ላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ (ከአላህ ውጪ ድጋፍም ሆነ ኃይል የለም)...❗❗❗ 🔸 አንድ ሰው ይህንን ድርጊት ከተቃወመና ከጠየቀ ልክ እንግዳ ጥያቄ እንደጠየቀ ሰው በትኩረት ታይሻለች... "ይሄ እኮ አባቴ ነው... ወንድሜ ነው... አጎቴ ነው" ትላለች❗ "በነሱ ፊት መልበስ ምን ችግር አለው ትላለች?!" 🔸 ውዷ እህቴ ሆይ! እንዴት ዳሌሽንና ጭኖችሽን ወጥሮ የያዘ ልብስ ለብሰሽ በቅርብ ዘመዶችሽ (መሀረሞችሽ) ፊት ትወጫለሽ?......⁉️ ወይንም እግርሽና ደረትሽ ተገልጦ! 🔸 እነሱም እኮ ወንዶች ናቸው፤ ወንዶች ዘንድ ያለው ስሜትና ፈተና እነሱም ጋር አለ። ወደ ውጭ ስትወጭ በደንብ ለብሰሽ የምትወጭው ፀሀይ እንዳታቃጥልሽ ፈርተሽ እኮ ነው ከቤት የምትወጪው⁉️.... ታዲያ ለእሳት እንዳይጋለጥ የተገለጠ አካልሽን መሸፈን አይበልጥም?🔥 🟤 በክፍሎች ውስጥ ያለ ክስተት ከባድ ክስተት በእናቷና በእህቷ ፊት ልብሷን ትቀይራለች... ከአካሏ መታየት የሌለበትን እያሳየች... ሀራም መሆኑን ሳትገነዘብ... ኃፍረት (ሀያዕ) ሳይሰማት። 🔸 የድርጊቱን አደገኛነት ካስታወስሻት... አይኖቿን በገረሜታ ፈጣ ወደ አንቺ በማየት... "እናቴ እኮ ናት.. እህቴ እኮ ናት..❗ በመካከላችን የሚደበቅ ነገር የለም" ትላለች❗ 📚 የዑለማዎች (የሊቃውንት) ፈትዋዎች ሴት ልጅ የሰውነት መወላገጃዎቿን (አውራዋን) የሚገልጥ ልብስ ከባሏ ውጪ በማንም ፊት እንድትለብስ ወይም እንድትቀይር አይፈቅዱም🚫። 🟤አንድት እህት ስትናገር እንዲህ ትላለች:::::: አንዲት የስራ ባልደረባዬ እንደነገረችኝ... ባለቤቷ ለሰላሳ ዓመታት በፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ሲሰራ... በስራ ዘመኑ ሁሉ ከቅርብ የሥጋ ዘመድ (መሀረም) የሚደርስ የትንኮሳ አቤቱታ ቀርቦለት አያውቅም ነበር... 🚫 ባለፉት ሶስት ዓመታት ሲቀር! ⁉️ ጉዳዩን ሲመረምር ተከሳሽ የሆኑት ዘመዶች ለዚህ ነገር የገፋፋቸውና ወንጀሉን እንዲፈጽሙ ያደረጋቸው የሴት ዘመዶቻቸው አለባበስ መሆኑን ተናገሩ ይለናል❗ 🟤::::: ሌላዋ ደግሞ እንዲህ ትላለች "ባለቤቴ አንድ ቀን ከቤተሰቦቹ ዘንድ መጥቶ ፊቱ ላይ የሀዘን ምልክት ይታይ ነበር፤ ምክንያቱን ብጠይቀው አልመለሰልኝም አልነግረኝ አለ❗ 🔸 ደጋግሜ ስጠይቀው እንዲህ አለኝ፡- 'ሥነ-ልቦናዬ ደክሟል... እህቶቼና ልጆቻቸው በሚለብሱት ልብስ ምክንያት አለኝ። 🔸 እመክራቸዋለሁ ግን ፋይዳ የለውም አይሰሙም፤ ወላሂ እርዳታ የሚጠየቀው ከአላህ ብቻ ነው አለኝ። ⛔ እህቶቼና ልጆቻቸው በጠባብ፣ የሰውነት ቅርፅ በሚያሳይ ወይም በተገለጠ ልብስ፤ ደረታቸው ወጥቶ፣ እግራቸው ተገልጦ፣ ሱሪያቸው ተወጥሮ እንዴት ይሆናል⁉️ 🔸 ሴት ልጅ እኮ ናት በአካል ውስጥ ያለን የስሜት እሳት የምታቀጣጥለው... ያኔ አእምሮ ይጠፋል... ⁉️ ይህ በወንድም ላይ ከሆነ፣ የባል ወንድም ወይም ጎረቤት ቢሆንስ....." 🔸 ልብን የሚያደሙ ስንት ታሪኮች አሉ... ሴቷ በቸልተኝነቷ የምታደርሰውን አታውቅም። ውድ እህቶቼ ሆይ! ውስጥንም ውጭንም የሚሸፍነው የሀያዕ (የአክብሮት/የእፍረት) ልብስ ምንኛ ያምርብሻል! 🚫 ተጠንቀቂ! አንቺ በተዘናጋሽበት ልብስ ምክንያት ለሚፈጸም ፀያፍ ተግባር ወይም ለሚሰበሰብ ኃጢአት ሰበብ እንዳትሆኚ 🔸 በምዕራቡ ዓለም የተስፋፋው የዝሙትና የትንኮሳ ወንጀል ከቀን ወደ ቀን እየተራቆተ በመጣው በዚህ አለባበስ ምክንያት እንጂ በሌላ አይደለም። 🟤:::::: እህቶቼ ሆይ... እነዚህ በነፍሴ ውስጥ የተመላለሱ እውነታዎች... እና ከደረቴ የወጡ ቃተቶች ናቸው... ብዕሬ የጻፈውም ያለውን እውነታ ነው። 🔸 መልእክቱን ስላረዘምኩኝ ይቅርታ፣ ጉዳዩ ትኩረት ስለሚሻ ነው። አላህ እንዲጠቅማችሁና እኔም የፈለኩት ቦታ እንዲደርስ እለምነዋለሁ። 🔸 ጀግና ሁኚ! አላህ በዱኒያም በአኼራም በመልካም እንዲተካሽ ነፍስሽን ታገያት (ጂሃድ አድርጊ)። 🔸 ይሄንን መልዕክት በሴቶች መካከል አሰራጪው፤ በማህበረሰብሽ ውስጥ ጠቃሚ ሁኚ፤ የአንድን ሰው ልብ ያንኳኳ ይሆናል። እንደ "መልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል" ቁጠሪው። ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለእናንተም በዱኒያና በአኼራ መመራትንና መሸፈንን ጻፍልን። 🗯️ "ጌታዬ ሆይ! በቅርቢቱ ሕይወት ሥራቸው የጠፋባቸውና እነሱ ሥራን እንደሚያሳምሩ የሚያስቡ ከሆኑት አታድርገን።" 🗯️ አላህ ይጠብቅሽ እኛንም ይጠብቀን አሚን ✍አቡ ሒበቲላህ ሑሰይን

  • HADITH   "አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "ሶደቃ (ምጽዋት)ገንዘብ አታጎድልም። አላህ ባሪያውን በይቅርባይነት ክብርን እንጅ አያክልለትም። አንድ ሰው ለአላህ ሲል አይተናነስም። አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጅ።" (ሙስሊም ዘግበውታል)

  • *❌❌የልብ ቅርፅ ❌❌*  ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ المزة القلب 👈👈❌❌❤لا يجوز لأنه تشبه بالكفار️ *ልብ ቅርፅን መጠቀም የተከለከለና የተወገዘ  ነገር ነው በኩፋሮች መመሳሰል ነውና።* *የማይሳሳት የለምና እኔም ይህን ነገር ተጠቀረሜው ነበር ስለሆነም ተመልሻለሁ።* *የሰው ልጅ ሆኖ የማይሳሳት የለም ነገር ግን የአንድ ነገር ጥፋትና ችግር ሲነገረው መመለስ ለአላህና ለመልዕክተኛው ተገዥነት ነው።* *ታላቁ አሊም ሼኽ ሷሊህ አል ፈውዛን እንድህ ይላሉ* يقول ‏العلامة صالح الفوزان حفظه الله: ‏ ‏«انظروا إلى سعة فضل الله أنهم عصوا الله وخالفوا أمره لكن لما تابوا تاب الله عليه وأحبهم» ‏ ‏[أسباب محبة الله للعبد] *የአሏህን ትሩፋትና ቼርነት ተመልከት አላህን አመፁት ከትእዛዙም አፈነገጡ ነገር ግን ሲመለሱ ሲፀፀቱ አላህ ምህረቱን ለገሳቸው ወደዳቸውም።* *ነብዩም እንድህ ሲሉ ተመላሽን አሞግሰዋል* كل بني آدم خطاء وخير الخطائين التوابين. *የሰው ልጆች ሁሉ ተሳሳቾች ናቸው ከተሳሳቾች ሁሉ መልካሙና ጥሩው ግን ተመላሾቹ ናቸው ይሉናል የአላህ ነብይ።* ‏لا يجوز استعمال رمز القلب👈❌❌ (❤) قال الشيخ ابن باز رحمه الله : " أنه رمز للعشق المحرم ورمز للألهه الاغريقية" اللجنة الدائمة للأفتاء [20950] ⭕ تذكير بخصوص بعض الرموز المستخدمة في برنامج          الواتس أب                              فلابد يا أخي المسلم ويا أختي المسلمة أن نتنبه لخطورة حرب اليهود والنصارى وملل الكفر على الإسلام وأهله ،و مما ينبه عليه هو وجود هذه الرموز الخبيثة المتدوَالة في برنامج الواتس آب وهي مخالفة لدِينِنا الإسلامي الحنيف وعقيدتنا التي هي رأس مالنا ..كثير منا يَستعملها في بعض رسائِلِه وهو لا يعلم معناها ولا يعلم مدى خطورتَها علي عقيدتِنا فعَلى سبيل المثال لا الحَصْر : *ወንድሞችእናእህቶች ልንነቃ ይገባል ይህ ድርጊት ከኩፋሮች የመጣ ነው ቀጥታ ከአቂዳ ጋር ግንኙነት አለው ስለዚህም ከዲናችን ጋር የሚቃረን ነገር መጠቀምን እንጠንቀቅ።* *ለምሳሌ አንዳን ነገሮችን እንመልከት* 1⃣ هذه👈❌❌ ✳ ❇ 💠✨⚓ ترمز للديانة النصرانية وهي أشكالٌ مِن الصُّلْبان . *ይህ ምልክት የክርስትና የመስቀል ምልክት ነው።* 2⃣ وأمَّا هذا👈❌❌❌ 💖 فرمْـزٌ على أنَّ الصليب في القلب . *ይህ ምልክት ደግሞ መስቀል ከልቤ ውስጥ ነው እወደዋለሁ ማለት ነው።* 3⃣ وأمَّا هاذان الرمزان👈👈❌👌 ⛪ 💒 فهما للكنيسة وأنها في القلب. *እነዚህ ሁለት ምልክቶች ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ምልክት ነው ይህም ማለት ቤተክርስትያን ከልቤ ውስጥ ነው ማለት ነው።* 4⃣ وأمَّا هذه👈❌❌ 🙏 فتحيةٌ في الديانة البوذية عُبَّاد بُوذا . ✅✅✅✅ 5⃣ وأمَّا هذا🗿فرمْـزٌ َلِوَثَن أو صنم . *ይህ ደግሞ የጣኦት ምልክት ነው።* 6⃣ وأمَّا هذه 👈👈❌❌♦ ♣ ♥  فهي لأوراق اليانصيب . 7⃣ وأمَّا هذا 🔯 فرمْز للصهيونية اليهودية . 8⃣ وأمَّا هذه👈👈❌❌ 🍻🍺 دعاية لشَرَابٌ الخَمْر . *እነዚህ ምልክቶች ደግሞ የአስካሪ መጠጥ ምልክቶች ናቸው።* 9⃣ وهذا 🎄 يرمُز لِِتَزُيين الأشجار في بعض الأعياد النصرانية وما يسمى [الكريسمس] . 🔟 وهذه لِآلآت الموسيقى المُحرَّمة👈❌❌ 🎺 🎸 🎻  🎼 🎶🎵🎷 *እነዚህም ምልክቶች የሙዚቃ መሳሪያ ምልክቶች ናቸው።* 1⃣1⃣ وهذه ♍ لفظ الجلالة بالمقلوب اقلبو الجهاز. *ይህ ደግሞ እጅግ የሚገርምና ከሁሉም እስልምና ላይ ለመጫወት ሆን ብለው የሰሩት ነው።* *ይህማ ካልሆነ እንደት የአላህን ስም ገልብጠው ይፅፋሉ!!?* *ይህ ከላይ የምትመለከቱት ምልክት የአሏህን ስም ገልብጠው ፅፈው ነው።* 2⃣1⃣ وهذه 👐  🙌  ليست للدعاء لاحظ أصابع الإبهام للداخل و ليس إشارة للدعاء الله أعلم بمقصودها.. 3⃣1⃣ وهذه رموز عبدة الشيطان كما يسمون أنفسهم ♈♉♋♌♑♓. *ይህ የሰይጣን አምላኪዎች ምልክት ነው።* وغيرها كثير  ... وكثيرون منا لا يعلمون والله المستعان . *እናም ሌላም ሌላም ከዲናችን ጋር ሊቃረን የሚችሉ ነገሮችን አይሁዶች አዘጋጅተው አቅርበውልናል።* *ለምሳሌ እስቲከሮች ✅✅* 👉❌❌❌❌❌😂😘😭😜☺️🙊👻🤡👿👽😹☠🧑‍🍳👨‍🌾👮‍♀👮🧕👳‍♂👳👨‍👧‍👧🦊🐻 *እና ወዘተ እንጠንቀቅ✅✅✅*   *በጌታዬ ይሁንብኝ ይህን አንድ ሙስሊም ሊጠቀመው* *አይገባም።።።።* ❞ከራሴው  ጀምሮ  አላህ  ይዘንልን    የዘጋነው  ኢሞጅ   የቱን  ያክል መዘዝ  እዳለው  በማስረጃ  ከላይ  አንብቡት

  • ⛔️ እራስህን አታሙኝ !!   ዓለም ላይ ያለን መጽሐፍ አንብበህ ቁርኣንን ለማንበብ ጊዜ ካጣህ እመነኝ አንተ ትልቅ ክስረት ውስጥ ነህ!!!    በቤትህ የሚገኘው ቁርኣን ላይ አቧራን ካስተዋለወክ፣በልብህ ላይ የተከመረው አቧራ በርክቷል ማለት ነው!!!   ስለ ማንኛውም ነገር ግንዛቤን ከፈለግክ፣ከቁርኣን ጋር ያለህን ትስስር አጥብቅ !!! በጊዜህና በስራህ ውስጥ በረከት ካጣህ የልብ ድርቀትና ፅልመት ከተሰማህ ጭንቀት፣ውጥረት፣ሐዘን ከወረረህ ቆም በልና ከቁርኣን ጋር ያለህን ግንኙነት ፈትሽ! « ልባችን ቢፀዳ ኖሮ፣ከአላህ ንግግር ባልጠገበ ነበር ወዳጅ ከወዳጁ ንግግር እንዴት ይጠግባል !! » ዑስማን ቢን ዐፍ’ፋን (رضي الله عنه) አል–ጀዋቡል–ካፊ #አላህ_ያግራልና!🖤 @strong_iman

  • يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِّنَ الظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ الظَّنِّ إِثْمٌ ۖ وَلَا تَجَسَّسُوا وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡ ነውርንም አትከታተሉ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡

  • Imagine ስምህ ከነ አባትህ ስም ተጠርቶ ለነቢ ሰለዋቱ ረቢ ወተስሊማቱሁ አለይህ ሰላምታህ ሲቀርብላቸውና መልስ ሲሰጡህ 🥺🥹🥰 አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም ❤️❤️

  • ወንጀልን የሚያሰርዙ ስራዎች ምንድን ናቸው? - ትልልቅ ወንጀሎችን መራቅ። - መልካም ስራዎችን መስራት። - መልካም ስራዎችን ማስከተል። - በብርድ ሰአት ውዱእ ማድረግ። - አምስት አውቃት ሶላቶች። - ወደ መስጂድ መሄድ። - የጁሙዓ ሶላት። - የረመዷን ፆም። - ንፁህ ተውበት። • ንፁህ ተውበት ምንድን ነው? ሶስት መስፈርቶችን ያሟላ ትክክለኛ ተውበት ነው። እነሱም፦ 1- ከወንጀሉ መላቀቅ። 2- በመስራቱ መፀፀት እና 3- ወደ ወንጀሉ አለመመ፞ለስ ናቸው። • ወንጀሉ በሌላ ግለሰብ ላይ ከሆነ የተፈፀመው፣ ይቅር ማስባል ግዴታ ነው። ካልሆነ የቂያም ቀን ይጠየቃል። • በግለሰብ ደረጃ ተውበት የሚቋረጠው መቼ ነው? የሞት ስካር ሲመጣ ነው። «አላህ: ያንድን ባሪያ ተውበት፣ ነፍሱ ጉሮሮው ላይ እስካልደረሰች ድረስ ይቀበለዋል።» [ሶሒሑል ጃሚዕ (1903)] ተውበት ሙሉ በሙሉ የሚቋረጠው መቼ ነው? ፀሃይ በምእራብ በኩል ስትወጣ ነው። • የተውሒድ ሰው ሁኖ በትልልቅ ወንጀሎች ላይ የሞተ ሰው ሑክሙ ምንድን ነው? የተውሒድ ባለቤት የሆኑ ወንጀለኞች ሶስት ክፍል ናቸው። አንደኛ፦ መልካም ስራቸው ከመጥፎ ስራቸው የበለጠላቸው ናቸው። እነዚህ ጀነት ይገባሉ። እሳት በፍፁም አትነካቸውም። ሁለተኛ፦ መልካም ስራቸው እና መጥፎ ስራቸው እኩል የሆነባቸው ናቸው። እነዚህ “አስሓቡል አዕራፍ” የሚባሉት ናቸው። አላህ የሻውን ያክል በጀነት እና በጀሃነም መካከል ይቆያሉ፣ ከዚያም ጀነት እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል። ሶስተኛ፦ መጥፎ ስራቸው ከመልካም ስራቸው የበለጠባቸው ናቸው። እነዚህ በወንጀላቸው ልክ ጀሃነም ይገባሉ። ከዚያም በነብያችን ﷺ ፣ በሌሎች ነብያት፣ በወሊዮች፣ በመላእክት እና በሌሎችም ሸፋዓ ከእሳት ውስጥ ይወጣሉ፣ ጀነትም ይገባሉ። የእሳት ቅጣት ከባድ ነው። የሰው ልጅ ለአንድ ደቂቃ እንኳ መቋቋም አይችልም። ስለዚህ መልካም ስራዎቻቸው ከሚበልጡላቸው ሰዎች እንሁን። መታደልም በአላህ ነው

  • " ጀነት ዉስጥ ጥላዋ ብቻ ሀምሳ ዓመት የሚያስኬድ አንዲት ዛፍ አለች" አሉ። " የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ለማነው የተዘጋጀችው?" አሏቸው። "ኢስቲግፋር ለሚያበዙት ነው።" አሏቸው። አስተግፊሩሏህ በሉ። ኢስቲግፋርን አብዙ።

  • 🎖#አቡ_በክር አስ-ሲድ-ዲቅ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል ☞ለሞት ጓጓ፤ ሕይወትን ይሰጥሀልና፡ ☞ነፍስን አሳምር፤ ሰዎች ላንተ ያሳምሩልሀልና። ☞በልብ ድርቀት እንጂ እንባ አልደረቀም፡፡ ☞በኃጢአቶች ብዛት እንጂ ቀልቦች አልደረቁም፡፡ ብለዋል 🎖 #ዑመር አል-ፋሩቅ (ረ.ዐ) ይህን ብለዋል ☞ሚስጥሩን የደበቀ ሰው አማራጩ በእጁ ነው። ☞ሦስት ነገሮች በወንድምህ ደረት ውስጥ ውዴታሀን ያፀኑልሀል፦ ➊በሰላምታ መጀመር፣ ➋ለርሱ መጅሊስን ማስፋትና ➌ እርሱ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ በሆኑ ስሞች እርሱን መጥራት ብለዋል 🎖#ዑስማን ቢን አፋን እንዲህ ብለዋል፡- አራት ነገሮች ውጪአቸው ሲታይ ትሩፋት ሲሆን ውስጣቸው ሲታይ ደግሞ ግዴታ ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ➊ ከደጋግ ሰዎች ጋር መቀላቀል ትሩፋት ሲሆን ነገር ግን በነርሱ መመራት ግዴታ ነዉ፡፡ ➋ ቁርአንን ማንበብ ትሩፋት ሲሆን ነገር ግን በርሱ መሥራት ግዴታ ነው። ➌ ቀብርን መጎብኘት ትሩፋት ሲሆን ለርሱ መሰናዳት ለቀብር መዘጋጀት ግን ግዴታ ነው። ➍ የታመመን ሰው መጠየቅ ትሩፋት ሲሆን ተግሳፅን መውሰድ ግን ግዴታ ነው። ብለዋል፡፡ 🎖 #ዐሊይ_ቢን_አቢ_ጣሊብ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- ☞ የታገለ ሰው አሸነፈ፡፡ ንፉግ የሆነ ሰውም ተዋረደ፡፡ ከሰዎች ሁሉ በጣም ቸሩም ይሰጠኛል ብሎ ከርሱ ለማይከጅል ሰው የሰጠው ነው። ☞ ዓመቱ የተለያየ ሆኖ ሲዞር አይቻለሁ ....... ሀዘንም ሆነ ደስታ አይዘወትርም፡፡ ☞ ንጉሣን በርሱ ውስጥ ቤተ መንግስትን ገንብተዋል ....ንጉሳን ሆነ ቤተ-መንግስቱ ግን ኋላ ቀሪዎች አልሆኑም። ☞አንዳች ጥቅም ለማግኘት ሲል የወደደህ ሰዉ ያንን ጥቅም ሲያጣብህ ወዲያዉኑ ተሰላችቶ ይተዉሀል ☞ይቺ አለም ህልም ናት፡ መጭዉ አለም ንቃት ነዉ፡፡እኛ ደግሞ በመካከላቸዉ በህልም ቅዠት ዉስጥ እንገኛለን ☞የማጣትም ሆነ የመጎዳት ዋናዉ ምክንያት ግዴለሽነት ባህሪ ነዉ ☞አላህ ዘንድ ያለዉን ደረጃ ለማወቅ የፈለገ ሰዉ እርሱ ለአላህ ብሎ የሚያደርገዉን ነገር ይመልከት ☞አንዳንድ ጊዜ የማግኘት ተስፋ ወደ ማጣት፡የማትረፍ ተስፋ ወደ መክሰር ያመጣል ☞ልማድ ጠንካራ ሀይል ነዉ በድብቅ አንድን ነገር የለመደ ሰዉ በአደባባይ ያጋልጠዋል ☞የዋህ ብሎ ማለት አንድ ጉድጓድ ወስጥ ሁለቴ የወደቀ ነዉ ☞በእሱና በአላህ መካከል ያለዉን ነገር ያስተካከለ አላህ በርሱና በሰዎች መካከል ያለዉን ነገር ያስተካክልለታል ☞በራስ ስራ መኮፈስ ራስን በራስ የሚደረግ ምቀኝነት ነዉ ☞አላህ የሰጠዉን ነገርወዶ የተቀበለ ባላገኘዉ ነገር አያዝንም ☞ምላስ አዉሬ ነዉ መረን ከለቀቀ ይናከሳል ሁሉንም አላህ ቀብራቸዉን ኑር ያድርግላቸዉ!

  • • ﴿فَٱذۡكُرُونِیۤ أَذۡكُرۡكُمۡ﴾. - «سُبْحَانَ اللهِ». - «الحَمْدُ للهِ». - «لَا إلَهَ إلَّا اللهُ». - «اللهُ أكْبَرُ». - «لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ». - «لَا إلَهَ إلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ». - «رَبِّ اغْفِرْ لِي وَتُبْ عَلَيَّ إنَّكَ أنْتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ».

  • ✍     አላህ በተከበረው ቃሉ በአንዲት ምዕራፍ ውስጥ ስለ ሁለት ደካሞች ይነግረናል፦ 📖{وَخُلِقَ الْإِنسَانُ ضَعِيفًا}    {ሰው ደካማ ተደርጎ ተፈጠረ።}                [አል_ኒሳእ:²⁸] 📖{إِنَّ كَيْدَ الشَّيْطَانِ كَانَ ضَعِيفًا} {የሸይጧን ተንኮል ደካማ ነው።}               [አል_ኒሳእ:⁷⁶]     ሁለት ደካማዎች ቢፋለሙ ከሁለት አንዳቸው አጋዥ ካላገኙ በስተቀር አንዱ ሌላውን መርታት አይችልም።    በጠላትህ ላይ አሸናፊ ትሆን ዘንዳ ሁሌም በአላህ ታገዝ!!

  • ✍️የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ (ረሒመሁል'ሏህ) እንዲህ ይላሉ:- የልብ መድኃኒት 5 ነገሮች ናቸው:- 1᎐ ቁርዓንን አስተንትኖ መቅራት፣ 2᎐ ሆድን ማስራብ፣ 3᎐ ለሊት ለሰላት መቆም፣ 4᎐ በለሊት ወደ አሏህ መተናነስ፣ 5᎐ ከደጋግ (ሷሊሕ) ሰዎች ጋር ማዘውተር። ምንጭ:-📚ዘሙ ቀስወቲል ቀል ገፅ (3 )

  • ‏- سُبحان الله . ‏- الحمدلله . ‏- لا إله إلا الله . ‏- اللهُ أكبر . ‏- سُبحان الله و بحمدهِ . ‏- سُبحان الله العظيم . ‏- استغفر الله و أتوبُ إليه . ‏- لا حول و لا قوة إلا بالله . ‏- اللهُم صلِ على نبينا محمد . ‏- لا إله الا الله محمد رسول الله .🦋

  • ▫️ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «አንድ ሰው ለሌላ ሰው "አላህን ፍራ!" ብሎ ሲገስፀው፤ ‘ስለኔ አያገባህም ስለራስህ አስብ‘ ብሎ የሚሰጠው ምላሽ አላህ ዘንድ ከተጠሉ ንግግሮች ነው» ☂📗 ሲልሲለቱ ሰሂሀህ 2598☂

  • [ ሞት ...] ስመ ጥሩ የሻፊዒይ መዝሀብ ሊቅ ኢማም አል ሙዘኒይ እንዲህ ይላሉ:– "ኢማም አሽ ሻፊዒይ ለሞት በዳረጋቸው ህመም ላይ በነበሩበት ወቅት ልጠይቃቸው ገብቼ እንዴት አነጉ?ስል ጠየቅኳቸው፤እሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱልኝ "ከቅርቢቷ ዓለም የምጓዝ፣ወንድሞቼን የምለይ፣የሞትን ፅዋ የምጎነጭ፣ወደ አላህ የምቀርብ ሆኜ አነጋሁ፤በአላህ እምላለው ሩሔ የጀነት ነች ላባስራት፣ወይስ የጀሀነም ነች ላርዳት የማውቀው ነገር የለም" ይህንን መራርና በጫንቃችን ተሸክመን የምንኖረውን እውነታ መዘንጋት፣ከአላህም ጋር ሆነ ከፍጡራን ጋር ለሚኖረን መስተጋብርና ትስስር ብልሹነት ዋነኛ ምክንያት ነው፤ለዚህም ነው ሰዪዳችን (ዐለይሂ ሶለዋቱላሂ ወሰላሙህ) "ጥፍጥናን ቆራጭ የሆነን ሞት አስታውሱ"በማለት አበክረው አደራ ማለታቸው፤በእያንዳዱ ቅፅበት ሟች መሆንን መዘከር የእውነተኛ አማኞኝ መገለጫ ነው፤ሞትን በረሳን ቁጥር እርምጃችን አላህ ከመዳፈር አኳያ ይሆናል።ዋነኛው ነገርም አዋዋይን መምረጥ ግድ ይለናል ምክንያቱም ሞትን ረስቶ በዱንያ ፍቅር ከሰከረ ሰው ጋር ከዋልክ ምናለፋህ ቀስ በቀስ አንተም በዱንያ መስከር አይቀርም የውሎህ መበላሸት ለቀልብህ መድረቅ ምክንያት ነውና ውሎህን አስተካክል። ሟቾች ነን! ያ ረብ! እዝነትህን🖤

  • ለነዛ የማያልፉ መስለውን ልባችንን ሲያስጨንቁን ለነበሩ አሁን ላይ በአላህ እርዳታ ላሳለፍናቸው ጊዜያቶች በሙሉ   💚     الْحَمْدُ لِلَّهِ 🤲

🌙Guiding Moon™ — tgindex