ኢትዮጵያ
Статистикаስለ ሀገራችን ታሪክ ፣ ባህል ፣ ጥንታዊ ቅርሶች ፣ ገዳማት ፣ መጎብኘት ስላለባቸው ስፍራዎች መረጃ ለማግኘት ካስፈለገ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ። ኢሉሚናቲን እናወግዛለን። የዚህ ቻናል አላማ ትውልዱ ሐይማኖቱንና ታሪኩን ያውቅ ዘንድ እና ሙሉ ትውልድ ይሆን ዘንድ ማገዝ ነው ። አንድነታችን ለህልዉናችን @HISCULHEROFETHIOPIA
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 22
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 3
- 1/48двое суток
- 3
- 1/72трое суток
- 3
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🕊 † እንኳን ለካህኑ ሰማዕት አባ ኦሪ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † † 🕊 ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ 🕊 † † ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ [በ፫ [3]ኛው መቶ ክ/ዘመን] ክርስቲያን መሆን ብቻውን ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ እረኛ ካህን ሆኖ መገኘት በጣም ከባድ ነበር:: ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና በሊቀ ጳጳሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም:: በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ:: ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል: ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም:: በጊዜው [በዘመነ ሰማዕታት] የነበሩ ካህናት የቤት ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ:: ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ ስጥኑፍ [የግብፅ አውራጃ ናት] መጻሕፍትን የተማሩ: ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ:: አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ ጥሪት [ምናኔ] ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን::" ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ:: ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር: በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል:: ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም ከበው ይነጋገሯቸው ነበር:: ሥጋውን ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ [ሰማዕትነት] በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና ከቤተ ክርስቲያን ወጡ:: በቀጥታ የሔዱትም ወደ ዐውደ ስምዕ [የምሥክርነት አደባባይ] ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "ክርስቶስ አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው::" ሲሉ በድፍረት ተናገሩ:: መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ አባ ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በኋላም ወደ ጨለማ እሥር ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ:: ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል:: በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል:: ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በኋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን አግኝተዋል:: በአክሊለ ጽድቅ ላይ አክሊለ ካህናትን: በአክሊለ ካህናትም ላይ አክሊለ ሰማዕታትን ደርበዋል:: † አምላከ ቅዱሳን በአባቶቻችን ጽናት ያጽናን:: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን:: 🕊 [ † ነሐሴ ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ [ሰማዕት] ፪. አባ ጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት] ፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ [ኢትዮጵያዊ] ፫. ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት [ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ] ፬. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን ፭. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ኢትዮጵያዊ] ፮. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ [ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት] † "ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" † [ ፩ቆሮ. ፲፥፲፬-፲፰ ] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🕊 † እንኳን ለካህኑ ሰማዕት ቅዱስ አልዓዛር እና ለቅዱሳን ቤተሰቡ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † † 🕊 ቅዱስ አልዓዛር ካህን 🕊 † † ይህ ቅዱስ የብሉይ ኪዳን ሰማዕታት ተብለው ከሚታወቁት ዋነኛው ነው:: የነበረበት ዘመንም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲሆን "ዓመተ መቃብያን/ ዘመነ ካህናት" ይባላል:: በወቅቱ ሰሎሜ የምትባል ደግ ሴት አግብቶ ይኖር የነበረው ቅዱስ አልዓዛር በኢየሩሳሌም ተወዳጅ ነበር:: ሐረገ ትውልዱ ከአሮን ወገን ነውና በክህነቱ ተግቶ ያገለግል ነበር:: በዚያ ላይ ሊቀ ካህንነትን በመመረጡ ሕዝቡን ይሠራ: ያስተምር: ያስተዳድር ነበር:: ቅዱስ አልዓዛር ከተባረከች ሚስቱ ሰሎሜ ፯ [7] ወንዶች ልጆችን አፍርቷል:: እነርሱንም በሥርዓት አሳድጐ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጐ ነበር:: በዚያው ዘመን በኢየሩሳሌም አካባቢ የሚኖሩ ፫ [3] እኩያን [ክፉ] ካህናት ነበሩ:: እነዚሁም ሕዝቡን ከማስቸገር: ፈጣሪን ከማሳዘን ቦዝነው አያውቁም ነበር:: የክፋታቸው መጨረሻ ግን የገዛ ሃገራቸውን ማጥፋት ሆነ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- ፫ [3] ቱም ተመካክረው የአልዓዛርን የሊቀ ካህንነት ቦታ ሊቀሙ ወስነው ወደ እርሱ ሔዱና እንዲህ አሉት:: "ሹመት በተርታ: ሥጋ በገበታ" ሲሆን ያምራልና እኛ በተራችን በወንበሩ ላይ እንቀመጥ::" እርሱ ግን "ሕዝቡን ጠይቃችሁ ተሾሙ" አላቸው:: እነርሱም ሕዝቡን ጠርተው "ሹመት ይገባናል" ቢሏቸው ሕዝቡ መልሶ "አልዓዛርን የሾመው እግዚአብሔር ነውና እናንተም ከፈጣሪ ጠይቃችሁ ተሾሙ" አሏቸው:: በዚህ ጊዜ ፫ [3]ቱ እኩያን ተቆጡ:: ምክንያቱም እግዚአብሔር እንደ ማይሰጣቸው ያውቃሉና:: ወዲያው ግን ፫ [3]ቱም ከአካባቢው ጠፉ:: ከኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ጨካኙ የግሪክ ንጉሥ አንጥያኮስ ሔዱ:: አንጥያኮስ ማለት "ቀኝ ዐይናችሁን ገብሩልኝ" የሚል ንጉሥ ነው:: እርሱን " ኢየሩሳሌም ባለቤት የላትምና ሒደህ ውረራት" አሉት:: "አጥሩ ጥብቅ ነው:: በምን እገባለሁ?" ቢላቸው "እኛ በመላ እናስገባሃለን" አሉት:: እርሱም ፪ መቶ ፵ ሺህ [240,000] ሠራዊት አስከትቶ ወረደ:: እነርሱ ቀድመው ወደ ኢየሩሳሌም ገብተው ያስወሩ ጀመር:: "እናንተ ሹመት ብትነሱንም እኛ ግን አንጥያኮስን ያህል ንጉሥ በእሥራኤል አምላክ አሳምነን መጣን" እያሉ ይሰብኩ ገቡ:: ቅዱስ አልዓዛር "አትስሟቸው:: በዚያም ላይ አሕዛብ የተቀደሰውን ምድር መርገጥ የለባቸውም" ብሎ ነበር:: ነገር ግን አንዳንድ ችኩሎች አይጠፉምና ፈጥነው የከተማዋን በር ከፈቱት:: ሠራዊቱን ደብቆ ትንሽ ራሱን የቆመ የመሰለው አንጥያኮስ በምክንያት: በክፋትና በመላ ሁሉን ሠራዊቱን አስገባ:: የሚገርመው በጊዜው የከተማዋ ሕዝብ ፲፪ [12] እልፍ ፻፳ ሺህ [120,000] ሲሆን ንጉሡ ያስገባው ሠራዊት ግን ፳፬ [24] እልፍ ፪ መቶ ፵ ሺህ [240,000] ሆኖ ተገኘ:: ወዲያው አንጥያኮስ ሕዝቡን ሰበሰበና አልዓዛርን ለብቻው ጠርቶ ተናገረው:: "አንተ አምላክህን እንደምትወድ ሰምቻለሁ:: አንተ የበጉን መስዋዕት በልተህ: ለስዕለ ኪሩብ ሰግደህ: ሕዝቡን ግን እሪያ [አሳማ] እንዲበላና ለጸፀሐይ እንዲሰግድ አድርግልኝ" አለው:: ቅዱስ አልዓዛር መለሰለት :- "እግዚአብሔር የሾመኝኮ በጐ ሃይማኖትን ላስተምር እንጂ ለክፋት አይደለም:: ለሕዝቤ የክፋት አብነት ፈጽሞ አልሆንም" አለው:: ያን ጊዜ ንጉሡ በቅዱሱ ላይ ተቆጣ:: "የምልህን ካላደረግህ ብዙ ግፍ ይደርስብሃል" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "የፈለግኸውን አድርግ" አለው:: በዚያን ጊዜ ንጉሡ የቅዱሱን ሚስትና ፯ [7] ልጆች እንዲያመጡለት አዘዘ:: ቅዱሱ እያየ ከፊቱ ላይ ፯ [7] ቱንም ልጆቹን በሰይፍ አስመታቸውና 7ቱም ወደቁ:: ለአንድ አባት ይህ የመጨረሻው መራራ ፈተና ነው:: አልዓዛር ግን ምን አንጀቱ በኀዘን ቢቃጠልም ከልጆቹ ለእግዚአብሔር አድልቷልና ቻለው ታገሠው:: በዚህ ለውጥ እንዳልመጣ ያየው ንጉሡ ሌላ ፍርድ ተናገረ:: ቅዱሱንና ሚስቱን [ሰሎሜን] በፈትል ጠቅልለው በሠም ነከሯቸው:: [ጧፍ እንደሚሠራበት መንገድ ማለት ነው::] አሁንም ግን ከአምልኮታቸው ፈቀቅ ባለማለታቸው ትልቅ ብረት ምጣድ ተጥዶ: ፪ [2] ቱም ከነነፍሳቸው እንዲቃጠሉ ተደረገ:: ቀጥሎም ሕዝቡን እንዲፈጁ አዋጅ ወጣ:: በከተማዋ ከነበረው ሕዝብ ፵ ሺህ [40,000] ያህሉ ተገደሉ:: ፵ ሺህ [40,000] ያህሉ ሲማረኩ ፵ ሺህ [40,000] ያህሉን ደግሞ ይሁዳ የሚባል አርበኛ በር ሰብሮ ይዟቸው ሸሸ:: "እንሾማለን: እንሸለማለን" ብለው ሕዝባቸውን ያስፈጁ እነዚያ ካህናትም እግዚአብሔር ፈርዶባቸው እነርሱም ተገደሉ:: ቅዱሱ የአልዓዛር ቤተሰብ ግን የክብርን አክሊል አግኝተዋል:: † የእሥራኤል አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር እንዲህ ካለው መከራ በኪነ ጥበቡ ይሰውረን:: ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን:: [ † ነሐሴ ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ አልዓዛር ካህን [ ሰማዕት ] ፪. ቅድስት ሰሎሜ ሰማዕት [ ሚስቱ ] ፫. ፯ "7ቱ" ቅዱሳን ሰማዕታት [ ልጆቹ ] ፬. ቅዱስ አሞን ሰማዕት [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ፪. ኪሩቤል [ አርባዕቱ እንስሳ ] ፫. አባ ብሶይ [ ቢሾይ ] ፬. አቡነ ኪሮስ ፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን ፮. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ ከ፲፪ [12] ቱ ሐዋርያት] † " አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ:: የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ:: ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት:: የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ:: የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት:: ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ:: የሚቀብራቸውም አጡ::" † [መዝ.፹፰፥፩] (78:1) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🕊 † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † † 🕊 ቁጽረታ [ጽንሰታ] ለማርያም 🕊 † ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ:: "ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ::" "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው::" [መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ.፩፥፱ ፣ መኃ.፬] ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል:: የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ [አሮን] የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር:: ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ:: እርሷ ደግሞ :- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: በሰባተኛው ቀን [ማለትም ነሐሴ ፯] መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: [ቅዳሴ ማርያም] † 🕊 ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 🕊 † ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ መታሰቢያ ናት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ይዟቸው ሔደ:: በዚያም ጌታ ከእነሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በእርስ ይከራከሩ ገቡ:: የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር:: የዋሃን [ገና ምሥጢርን ያልተረዱ] ነበሩና አንዱ ተነስቶ "ኤልያስ ነው": ሌላኛው "ሙሴ": ሦስተኛው "ኤርምያስ ነው" በሚል ተከራከሩ:: ቅዱስ ጴጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው "ሃሳባችንን አስታርቅልን:: ለአንተስ ማን ይመስልሃል?" አሉት:: አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው:: "እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን "እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው" አላቸው:: ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ:: ቸር አምላክ "ለምን ተጠራጠራችሁኝ" ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ:: "የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?" አላቸው:: እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ:: ጌታችን "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ጸጥ አሉ:: ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና:: በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነስቶ "አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው-አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ" አለው:: [ማቴ.፲፮፥፲፮] ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን "አንተ ዓለት ነህ" ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ:: ለቅዱስ ጴጥሮስም "መራሑተ መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ [ሥልጣን]" ተሰጠው:: ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ:: ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው:: ኢየሱስ ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ ማርያም: አካላዊ ቃል: ሥግው ቃል: ገባሬ ኩሉ: የሁሉ ፈጣሪ"ብለው ካላመኑ እንኳን ጽድቅ ክርስትናም የለም:: † 🕊 አፄ ናዖድ ጻድቅ 🕊 † ሃገራችን ኢትዮጵያ ምስፍና ከክህነት: ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯት:: ከእነዚህ አንዱ ደግሞ አፄ ናዖድ ናቸው:: ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ/ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ:: ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል:: ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት [ሰላም ለኪ: እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .] የደረሷት እርሳቸው ናቸው:: ትልቁን መልክአ ማርያምም ደርሰዋል:: ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው:: የጻድቁ ንጉሥ ሚስት [ማርያም ክብራ] : ልጆቻቸው [አፄ ልብነ ድንግልና ቡርክት ሮማነ ወርቅ] እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ:: ንጉሡ አፄ ናዖድ ከባለሟልነት የተነሳ ድንግል ማርያምን "እመቤቴ ስምንተኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?" አሏት:: እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው:: ንጉሡም አዝነው "እመቤቴ! ከዛ ዘመን አታድርሺኝ" አሏት:: በዚህ ምክንያት የስምንተኛው ሺህ ዘመን መስከረም 1 በ1500 ዓ/ም ሊገባ እርሳቸው ነሐሴ 7 ቀን በ1499 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የድንግል እናቱን ጣዕም: ፍቅር: የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖትና የአፄ ናዖድን በረከት ያሳድርብን:: 🕊 † ነሐሴ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም ፪.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር ፬.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ፭.አፄ ናዖድ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮጵያ] ፮.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ ፯.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት † ወርኀዊ በዓላት ፩.ሥሉስ ቅዱስ ፪.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፫.አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን አለቃ] ፬.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት ፭.አባ ባውላ ገዳማዊ ፮.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፯.ቅዱስ አግናጥዮስ † "መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::" † [መዝ.፹፮፥፩-፮] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🕊 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ † [ † እንኩዋን ለቅድስት እናታችን ማርያም መግደላዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ] † 🕊 ቅድስት ማርያም መግደላዊት 🕊 † ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ "መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት [ወንጌላውያን] ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ :- በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች በአንዱ [በመግደሎን] ተወልዳ ያደገች ናትና:: ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም ፯ [7] አጋንንት ተጠግተው ፯ [7] ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር:: በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት [ምንዝር ጌጥ] እና ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች:: በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም [ይቀበላል]: አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት አልዘገየችም:: ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን ፯ [7] የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ ሆነች:: ጌታም ከ፴፮ [36]ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ መርጦ ተከታዩ አደረጋት:: ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች:: እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው:: ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች:: ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ ነበረች:: [ዮሐ.፲፱፥፳፭] (19:25) ቅዱሳኑ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጌታን ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች:: እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን አልፈራችም:: ጌታችንም ከእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ አደላት:: በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም ፪ [2] መላእክትን [ሚካኤልና ገብርኤልን] ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም" አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት:: ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት:: "ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን ለደጋጉ ሐዋርያት ሰበከችላቸው:: ቅድስት ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሳኤ በሁዋላ ለ፵ [40] ቀን መጽሐፈ ኪዳንን ፤ ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ : በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም ልዩ አገልግሎት ነበራት:: ቅዱሱ እስጢፋኖስ ፰ [8] ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ መንፈስ ቅዱስ የሚባርከውን አጋፔ [የፍቅር ማዕድ] የምታዘጋጀው እርሷ ነበረች:: እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል:: እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ ቅዱስ መልአክ ወርዶ ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ ይመግባቸው ነበር:: እናታችን ማርያም መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች:: ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና ግርፋትን ታግሳለች:: በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ [ከአንዳንዶቹ በቀር] ያከብሯታል:: † 🕊 ቅድስት ኢየሉጣ ዘቂሣርያ 🕊 † በቀድሞው የግሪክ ግዛት [ቂሣርያ ውስጥ] በዘመነ ሰማዕታት አካባቢ የነበረችው ቅድስት ኢየሉጣ ክርስትናን የወረሰችው ከወላጆቿ ነው:: ገና ወጣት እያለች ወላጆቿ በማረፋቸው የሃብታቸው ወራሽ ሆነች:: ነገር ግን አንድ ክፉ ሰው መጥቶ ሃብቷን ነጠቃት:: በዚህ አዝና "የዳኛ ያለህ" ልትል ወደ ፍርድ ቤት ስትሔድ የጠበቃት ግን የሚገርም ነበር:: የተገፋችው እርሷ ተከሳሽ: ገፊው ደግሞ ከሳሽ ነበር:: የክሱ ጭብጥ ደግሞ "ክርስቲያን ነሽ" የሚል ነበር:: በወቅቱ በመኯንንቱ ፊት ክርስትናዋን ብትክድ በቀጥታ ሃብቷን ማግኘት ትችል ነበር:: እርሷ ግን ለአፍታ አሰበች:: "እንዴት ዘላለማዊ ሃብቴን [ሃይማኖቴን] በኃላፊው ንብረት እለውጣለሁ" ብላ ሁሉም እየሰሙ ጮክ ብላ "ክርስቲያን ነኝ" አለች:: ወዲያውም ሞት ተፈርዶባት ተገደለች:: ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ስለ ሰማዕታት በጻፈው ድርሳን ላይ በስፋት አመስግኗታል:: ለሴቶችም ታላቅ ምሳሌ ናት ብሏታል:: ቅዱሳት እናቶቻችንን ያጸና ቸር አምላካቸው እኛንም በሃይማኖትና በምግባር ያጽናን:: ከበረከታቸውም አብዝቶ ያድለን:: 🕊 [ † ነሐሴ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅድስት ማርያም መግደላዊት [ከ፴፮ [36]ቱ ቅዱሳት አንስት] ፪. ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕት [ ዘቂሣርያ ] ፫. አባ ዊጻ [ የታላቁ ሲኖዳ ደቀ መዝሙር ] [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም ፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል ፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ ፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ፯. ቅድስት ሰሎሜ ፰. አባ አርከ ሥሉስ ፱. አባ ጽጌ ድንግል ፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል " ጌታ ኢየሱስም :- "ማርያም" አላት:: እርሷ ዘወር ብላ በእብራይስጥ :- "ረቡኒ" አለችው:: ትርጉዋሜውም "መምሕር ሆይ!" ማለት ነው:: ጌታ ኢየሱስም :- "ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ:: ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሔደሽ . . . ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው" አላት:: መግደላዊት ማርያም መጥታ ጌታን እንዳየች ይሕንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች::" [ዮሐ.፳፥፲፮] (20:16) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🕊 † እንኩዋን ለጻድቃን ቅዱሳን አባ_አብርሃም : ቅዱስ ዮሐንስ እና አባ ፊልዾስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † † 🕊 አባ አብርሃም ክቡር ገዳማዊ ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ፬ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ ከዋክብት አንዱ ነው:: ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው:: ሠርግ ተደግሶ: ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ፲ ዓመታት ተቀመጠ:: በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ:: በቤት ውስጥ ከ፮ ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው:: አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን [፮ ዓመቷ ነበር] ለቤተ ዘመድ አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና ጸሎት ተወስኖ ለ፲ ዓመታት ቆየ:: ተጋድሎ በጀመረ በ፳ ዓመቱ እግዚአብሔር ለሌላ አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ አባ አብርሃምን አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው:: ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው:: ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ ውጪም ጣሉት:: እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት:: ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ እነሱ እየጸለየ ፲ ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት:: የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ [ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ] ወደ ጻድቁ መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም ለመኑት:: ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም በስመ ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ [ስብሐት ብጡል] መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ:: እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ ማርያ ያስብ ነበርና አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ:: ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ:: በዚህ ተስፋ ቆርጠው ፪ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ:: ይልቁኑ እርሷ [ማርያ] ሴተኛ አዳሪ ሆነች:: በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ:: ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት:: ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ:: በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: ማርያም ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ ኑሯል:: በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል:: † 🕊 ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ ይህ ቅዱስ የነበረው በዘመነ ሰማዕታት ቢሆንም እንደ ሰማዕታት ስቃይ አልደረሰበትም:: ክርስቲያኖችን እንዲገድሉና አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያቃጥሉ ከተመደቡ ወታደሮች አንዱ ነበረ:: ታዲያ እንዲገድላቸው የሚሰጡትን ክርስቲያኖች እየወሰደ ይደብቃቸው ነበር:: የመከራው ዘመን እስኪያልፍ ድረስም ይንከባከባቸው ነበር:: ሌሎች ወታደሮች እንዳይነቁበት ሁሌም "ክርስቲያኖችን በጣም እጠላለሁ" እያለ ያወራ ነበር:: እርሱ በሌሊት ሁሌም ለጸሎት ይተጋ ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር ኑሮም በዚህች ቀን በሰላም ዐርፏል:: † 🕊 አባ ፊልዾስ ዘደብረ ቢዘን ደብረ ቢዘን በቀድሞ የኢትዮዽያ ክፍለ ሃገር [አሁን ኤርትራ] ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ገዳም ነው:: ገዳሙ እመቤታችን ድንግል ማርያም በስደቷ ያረፈችበት: ጌታችን የባረከውና የመረጠው ቦታ ነው:: አባ ዮሐንስን: አባ ናርዶስንና ሌሎች ከዋክብት አበውን ያፈራ ሲሆን የአባ ፊልዾስን ያሕል ግን አልተገኘም:: ጻድቁ በግል የተጋድሎ ሕይወታቸው: ገዳሙን በአበ ምኔትነት በመምራታቸውና በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ምስጉን ነበሩ:: እርሳቸው ቅዱስ ሆነው አልበቃቸውምና ብዙ ቅዱሳንን ወልደዋል:: ይሕች ዕለትም የዕረፍታቸው መታሰቢያ ናት:: አምላከ ጻድቃን ገዳማትን ከመከራ ይጠብቅልን:: ከአባቶቻችን ቅዱሳን ጸጋ በረከትንም ይክፈለን:: [ † ነሐሴ ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ አባ አብርሃም ገዳማዊ ፪. ቅድስት ማርያ እህቱ ፫. ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ ፬. አባ ፊልዾስ ዘደብረ ቢዘን [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ፪. ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም ፫. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፬. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ ፭. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ ፮. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ] " በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ. . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" [፪ቆሮ.፲፩፥፳፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † ወለወላዲቱ ድንግል † ወለመስቀሉ ክቡር [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
видео или голосовое, без подписи
የእርዳታ ጥሪ እንድረስላት 🙏 የምትመለከቱዋት ወጣት ታዳጊ ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች በአጥንት ካንሰርን ህክምና ላይ ትገኛለች በሽታው ከታወቀ አንድ አመት ሆኗታል በበሽታው ምክንያትም የግራ እጇ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል ሆኖም ግን ኤልሮይ ተስፋ ሳትቆርጥ ህክምናዋን እየተከታተለች ነው አሁን ግን በሽታው ወደ ሳንባዋ በመሠራጨቱ የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማት በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ Heal Venture Medical and Surgical Center በ ICU ትገኛለች ሆኖም ግን በአሁን ሰአት ላይ የሆስፒታሉ ወጪ በቀን ከ50.000ብር ነው ከቤተሰብ ከአቅም በላይ ስለሆነ እናትም አባትም አጠገቧ ስለሌሉ ጓደኞቿ እያሳከሟት ነው.. እኛ ከጎኗ እንሁን 🥹❤️ CBE - 1000487578828 TeleBirr - 0911179293 Awash Bank - 013471629151800 ሁሉም አካውንት ስም - Rahel Aregay እህታችን ትፈልገናለች እንድረስላት 🙏
видео или голосовое, без подписи