ህዳሴ ሚዲያ ማዕከል Gidduugala Odeeffannoo Hiddaasee
Статистикаህዳሴ ሚዲያ ማዕከል Gidduugala Odeeffannoo Hiddaasee ይህ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 14 ትምህርት ጽ/ቤት የህዳሴ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የህዳሴ ሚዲያ ማዕከል የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/HSMC2016
- Последний пост
- 23 июл.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 811
- 1/48двое суток
- 929
- 1/72трое суток
- 1 002
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
በ2019 የትምህርት ዘመን በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ (ሀምሌ 9 /2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የትምህርት ቢሮ እና የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ በጋራ በወጣው የተማሪ ቅበላ መመሪያ መሰረት ለሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ በ2019 ዓ.ም ለማስተማር ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ ስለሆነም የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተማሪዎች በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 1. በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአማርኛ ወይም በአፋን ኦሮሞ ዘርፍ በመማር ላይ የነበሩ፤ 2. በ2018 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ ውጤት /Average/ 80% እና በላይ ያስመዘገቡ፤ 3. በ2018 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በአጠቃላይ ሳይንስ፤ በሒሳብ፤ በእንግሊዘኛ ትምህርት አይነቶች በእያንዳንዳቸው የፈተና ውጤት 80% እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ፤ 4. በ2018 ዓ.ም ከሚማሩበት ትምህርት ቤት ምንም ዓይነት የስነምግባር ግድፈት እንደሌለባቸው ደብዳቤ የሚያቀርቡ፤ 5. በትምህርት ቤታቸው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ ላይ መሳተፋቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ፤ 6. ተማሪዎች በ7ኛ ክፍል ውጤታቸው በአጠቃላይ ሳይንስ፤ በሒሳብ፤ በእንግሊዘኛ ትምህርት አይነቶች በእያንዳንዳቸው አማካኝ ውጤት 80% እና በላይ የሆነ፤ 7. በሳይንስ ሹርድ ካምፓስ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ መቀጠል የሚገፈልጉ፤ የምዝገባ ቀን፡- ከሐምሌ 13 ቀን እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ፤ መመዝገቢያ ሁኔታ፡- በበይነ መረብ (ONLINE) ሆኖ ማስፈንጠሪያ ሊንኩም https://bs.ministry.et የመግቢያ ፈተና ቀን 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በመሆኑ የፈተና ቦታና ሰዓት በቀጣይ በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡ ማሳሰቢያ፡- በምዝገባና በፈተና ወቅት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የመጣ አይስተናገድም፡፡ Beeksisa dorgommii barattoota Kutaa 9ffaa Kaampaasii Saayinsii Shardii (Science Shared Campus) Yuunivarsiitii Barnoota Kotteebee Bara Barnootaa 2019tiif: Akkaataa qajeelfama simannaa barattootaa Biiroo Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinneefi Yuunivarsiitii Barnoota Kotteebeetiin waliin qophaa'een, Kaampaasii Shardii Saayinsiitiif barattoota haara Kutaa 9ffaa bara barnootaa 2018 keessa qormaata magaalaa guutuu kutaa 8ffaa fudhatanii qabxii olaana galmeessisan dorgomsiisuun bara barnootaa 2019 keessa barsiisuuf qophiin xumurameera. Kanaafuu, barattoonni ulaagaalee armaan gadii guutan Kaampaasii Shardii Saayinsii keessatti dorgomuu ni danda’u: 1. Bara barnootaa 2018 keessa Bulchiinsa Magaalaa Finfinneetti damee Amaariffaa ykn Afaan Oromootiin barachaa kan turan; 2. Qormaata magaalaa guutuu daree 8ffaa bara barnootaa 2018 keessatti qabxii giddu-galeessaan (Average) 80% fi isaa ol kan galmeessisan; 3. Qormaata magaalaa guutuu daree 8ffaa bara barnootaa 2018 keessatti akaakuuwwan barnootaa Saayinsii Waliigalaa, Herrega, fi Ingiliffaa keessaa tokkoo tokkoon isaaniitiin qabxii qormaataa 80% fi isaa ol kan galmeessisan; 4. Mana barumsaa bara 2018 keessa barachaa turan irraa hanqinni amalaa (naamusa) tokkollee akka isaan irratti hin mul'atin xalayaa ragaa kan dhiyeeffatan; 5. Mana barumsaa isaanii keessatti kilaabii Saayinsiifi Teeknoolojii keessatti hirmaachuu isaaniitiif ragaa kan dhiyeeffatan; 6. Qabxii kutaa 7ffaa isaaniitiin akaakuuwwan barnootaa Saayinsii Waliigalaa, Herrega, fi Ingiliffaa keessaa tokkoo tokkoon isaaniitiin qabxii giddu-galeessaa 80% fi isaa ol kan qaban; 7. Mana barnoota Kaampaasii Saayinsii Shardii keessatti damee Saayinsii Umamaatiin (Natural Science) itti fufuu kan barbaadan; 8. Guyyaan Galmee: Adoolessa 13 hanga 17 bara 2018 A.L.H. tti gaggeeffama; 9. Haala Galmee: Toora interneetiitiin (ONLINE) yoo ta'u, liinkiin galmee: https://bs.ministry.et 10. Guyyaa Qormaata Seensaa: Barattoota dorgomtoota daree 9ffaatiif Adoolessa 24, 2018 A.L.H. ta'a. Iddoonii fi sa'atiin qormaataa beeksisaan kan ibsamu ta'a. Hubachiisa: Yeroo galmeefi qormaataa dursees ta'ee boodatti hafee kan keessummeeffamu hin jiru. ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Kanneen kutaa 9ffaaf dorgoman: o Qabxii barnoota kutaa 7ffaa giddugaleessaan 80% fi isaa ol kan qabu/du; o Barnoota Herregaa giddugaleessaan qabxii 80% fi isaa ol kan qabu/du; o Afaan Ingilizii giddugaleessaan qabxii 80% fi isaa ol kan qabu/du. Guyyaan galmee Adoolessa 13 hanga 17 bara 2018 A.L.Itti ni gaggeeffama. Haalli galmee: Galmeen karaa toora marsariitii (ONLINE) ni raawwatama. Liinkiin galmee: o Barattoota Mana B/Bultii Addaa Dhiirotaa Galaaniif: https://bs.ministry.et o Barattoota Mana B/Bultii Addaa Dubartootaa I/Mananiif: https://bs.ministry.et Qormaata seensaa: o Barattoota kutaa 9ffaaf Adoolessa 22 bara 2018 A.L.I o Barattoota kutaa 7ffaaf Adoolessa 23 bara 2018 A.L.I Bakki fi sa'atiin qormaataa beeksisa addaatiin ni himama. Hubachiisa: Guyyaa galmee fi qormaataa ifoomeen alatti barataan dhufu tajaajila kan hin arganne ta’uu isin hubachiifna. ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Addis Ababa Education Bureau: የ2019 የትምህርት ዘመን የአዳሪ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ቅበላ ውድድር ማስታወቂያ (ሀምሌ 9 /2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ የገላን የወንዶች እና የእቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በየዓመቱ 7ኛ እና 9ኛ ክፍልን በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል በከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በማወዳደር ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ በ2018 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተምረው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ 7ኛ እና 9ኛ ክፍል የተዘዋወሩ ተማሪዎች ለወንድ ተማሪ በገላን የወንዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሁም ለሴት ተማሪ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አወዳድሮ በ2019 ዓ.ም ቅበላ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ለመግባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 1. በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማስተማሪያ ቋንቋ በአማርኛ ወይም በአፋን ኦሮሞ በመማር ላይ የነበረ/ች፤ 2. በ2018 ዓ.ም በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ /Average/ ውጤት 80% እና በላይ፤ እንዲሁም በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ/Average/ ውጤት 80%ና በላይ ያስመዘገበ/ች 3. በ2018 ዓ.ም ከሚማሩበት ትምህርት ቤት ምንም ዓይነት የስነ-ምግባር ችግር እንደሌለባቸው ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤ 4. በትምህርት ቤቱ በልዩ ልዩ ተጓዳኝ ክበባት በንቃት ተሳታፊ የሆነ/ነች፤ 5. 7ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች የ5ኛ ክፍል ውጤት አማካኝ ውጤት 80% እና በላይ ሆኖ በሒሳብ ትምህርት ዓይነት አማካ 5. 7ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች የ5ኛ ክፍል ውጤት አማካኝ ውጤት 80% እና በላይ ሆኖ በሒሳብ ትምህርት ዓይነት አማካኝ ውጤት 80% እና በላይ እንዲሁም በእንግሊዘኛ ትምህርት ዓይነት በአማካኝ ውጤት 80% እና በላይ ያላቸው፤ 6. ለ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢ ተማሪዎች የ7ኛ ክፍል አማካኝ ውጤት 80% እና በላይ ሆኖ በሒሳብ ትምህርት ዓይነት አማካኝ ውጤት 80% እና በላይ እንዲሁም በእንግሊዘኛ ትምህርት ዓይነት በአማካኝ ውጤት 80% እና በላይ ሊሆን ይገባል፡፡ የምዝገባ ቀን · ከሐምሌ 13 ቀን እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፤ መመዝገቢያ ሁኔታ፡- · በበይነ መረብ (ONLINE) ሆኖ ማስፈንጠሪያ ሊንኩም Ø ለገላን ወንዶች አዳሪ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመልካች ተማሪዎች https://bs.ministry.et Ø ለእቴጌ መነን ልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመልካች ተማሪዎች https://bs.ministry.et · የመግቢያ ፈተና ቀን Ø 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በተጨማሪም 7ኛ ክፍል ለሚገቡ ተወዳዳሪ ተማሪዎች Ø ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም መግቢያ ፈተና ይሰጣል፡፡ በመሆኑም የፈተና ቦታና ሰዓት በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡ ማሳሰቢያ፡- በምዝገባና በፈተና ወቅት ቀድሞም እንዲሁም ዘግይቶ አይስተናገድም፡፡ Dorgommii Barattootaa Bara 2019 A.L.I Mana Barumsaa Bultii Addaa Seenanii Ilaala. Biiroon Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee Mana Barumsaa Sadarkaa Giddugaleessaa fi 2ffaa Manneen Barnootaa Bultii Addaa Dhiirotaa Galaan akkasumas Bultii Addaa Shamarranii Iteeggee Manan keessatti waggaa waggaadhaan barattoota kutaa 6ffaa fi 8ffaa qormaata sadarkaa magaalattiin qabxii olaanaa galmeessanii gara kutaa 7ffaa fi 9ffaatti ce'an dorgomsiisee fudhachuun barsiisaa jiraachuun isaa ni beekama. Haaluma kanaan, bara barnootaa 2018tti barattoonni Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee keessatti sirna barnoota Afaan Amaaraan yookiin Afaan Oromootiin kutaa 6ffaa fi 8ffaa baratanii bu'aa olaanaa galmeessuun gara kutaa 7ffaa fi 9ffaatti ce'an, dhiironni Mana Barumsaa Sadarkaa Giddugaleessaa fi 2ffaa Bultii Addaa Dhiirotaa Galaanitti, Shamarran immoo Mana Barumsaa Sadarkaa Giddugaleessaafi 2ffaa Bultii Addaa Shamarranii Iteeggee Mananitti dorgomanii bara barnootaa 2019tti barnoota isaanii hordofaniif simannaa ni taasisa. Kanaafuu, barattoonni ulaagaalee armaan gadii guutan mana barumsaa bultii addaa kana keessatti dorgomuu ni danda'u. Ulaagaaleen Galmee: Bara 2018 Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee keessatti sirna barnootaa Afaan Amaaraa yookiin Afaan Oromootiin barachaa kan ture/kan turte ta'uu. Bara 2018 keessa: o Qormaata sadarkaa magaalaa kutaa 6ffaa irratti giddugaleessaan (Average) 80% fi isaa ol galmeessuu; akkasumas o Qormaata sadarkaa magaalaa kutaa 8ffaa irratti giddugaleessaan 80% fi isaa ol galmeessuu. Mana barumsaa irraa xalayaa ragaa rakkoo naamusaa kamiyyuu akka hin qabne ibsu dhiyeessuu danda'uu. Gumiiwwan garaagaraa keessatti dammaqinaan hirmaachaa kan ture/te. Kanneen kutaa 7ffaaf dorgoman: o Qabxiin barnootaa kutaa 5ffaa giddugaleessaan 80% fi isaa ol ta'uu; o Barnoota Herregaa giddugaleessaan qabxii 80% fi isaa ol qabaachuu; o Afaan Ingilizii giddugaleessaan qabxii 80% fi isaa ol qabaachuutu irraa eegama.
видео или голосовое, без подписи
https://aa.ministry.et/#/result
видео или голосовое, без подписи
ቀን 01/06/2018ዓ.ም ለትምህርት ቤታችን ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለሁለተኛው ወሰነ ትምህርት በሠላም አደረሳችሁ እያልን የካቲት 02/2018 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምር መሆኑን አውቃችሁ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ በትምህርት ገበታችሁ ላይ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡ "መልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!" ትምህርት ቤቱ
እንኳን አደረሳችሁ!! ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ለት/ቤታችን መምህራን ፣ለተማሪዎቻችን፣ ለወላጆችና ለመላው የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!! የጥምቀት በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት በዓል እንደመሆኑ መጠን ሁላችንም በደስታ ልናከብረው ይገባል። ሆኖም ግን፣ ውድ ተማሪዎቻችን በአሁኑ ወቅት በፈተና ዝግጅት ላይ እንደምትገኙ መዘንጋት የለባችሁም። በዓሉን ስታከብሩ የሚከተሉትን ነጥቦች በልዩ ትኩረት እንድትተገብሩ ትምህርት ቤታችን ያሳስባል፦ • ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፦ በዓሉን ስናከብር ለፈተና ዝግጅት የምንጠቀምበትን ውድ ጊዜ መሸርሸር የለብንም። በዓላዊ ስሜት ተገፋፍታችሁ ከጥናት ሰዓታችሁ እንዳትዘናጉ። • ከመጠን ያለፈ መዝናናትን ማስወገድ፦ መዝናናት ያለ ቢሆንም፣ ከፈተናው በኋላ ሰፊ የእረፍት ጊዜ ስላላችሁ አሁን ግን ቅድሚያ ለትምህርታችሁ እንድትሰጡ ይገባል። • ለወላጆች፦ ልጆቻችሁ በበዓሉ ሰበብ ከትምህርታቸው እንዳይዘናጉና በቂ የጥናት ጊዜ እንዲኖራቸው አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንልን እየተመኘን፣ ተማሪዎቻችን በፈተናችሁ ውጤታማ እንድትሆኑ ብርቱ ጥረት እንድታደርጉ በድጋሚ እናሳስባለን። መልካም በዓል!!
видео или голосовое, без подписи
ሞዴል ፈተና መፈተን የሚያስገኛቸው ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው። 1. ያላችሁን እውቀት መመዘን እና ድክመታችሁን መለየት፡ ሞዴል ፈተናዎች በእጃችሁ ያለውን እውቀት ምን ያህል እንደሆነ ለመገምገምና የትኞቹ አካባቢዎች ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ያግዛሉ። ለምሳሌ፣ አንድን ሞዴል ፈተና ከሰራችሁ በኋላ በተወሰኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ደጋግማችሁ እንደተሳሳታችሁ ከተመለከታችሁ፣ በእነዚያ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ጥናት ማድረግ ትችላላችሁ። 2. ከፈተና ጥያቄዎች እና የፈተና ሁኔታ ጋር መለማመድ፡ ሞዴል ፈተናዎችን መለማመድ የፈተና ጥያቄዎችን ቅርፅና አቀራረብ እንድታውቁ ይረዳችኋል። በተጨማሪም፣ በፈተና ጊዜ ሊያጋጥሟችሁ የሚችሉትን ጭንቀቶች ለመቀነስና ከፈተናው ሁኔታ ጋር እንድትላመዱ ያደርጋል። 3. የፈተና ጊዜ አጠቃቀም ክህሎትን ማሳደግ፡ ሞዴል ፈተናዎችን ስትሰሩ፣ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ምን ያህል ጊዜ መመደብ እንዳለባችሁ ትማራላችሁ። ይህም በፈተናው ወቅት ጊዜያችሁን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት ይረዳችኋል። ለምሳሌ፣ በአንድ ጥያቄ ላይ ብዙ ጊዜ እንደምታጠፉ ከተመለከታችሁ፣ በቀጣይ ፈተናዎች ላይ ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም ስልት መንደፍ ትችላላችሁ። 4. በራስ መተማመንን መጨመር እና የፈተና ላይ ጭንቀትን መቀነስ፡ በተደጋጋሚ ሞዴል ፈተናዎችን መስራት በራስ መተማመናችሁን ይጨምራል እንዲሁም በፈተና ጊዜ የሚሰማችሁን ጭንቀት ይቀንሳል። በሞዴል ፈተናዎች ላይ ጥሩ ውጤት ስታገኙ፣ ለዋናው ፈተና የበለጠ በራስ መተማመን ይኖራችኋል። 5. የተማራችሁትን የማስታወስ እና የማስተዋል አቅምን መጨመር፡ ሞዴል ፈተናዎች የተማራችሁትን ነገር እንድታስታውሱና እንድትረዱ ያግዛሉ። ጥያቄዎችን ለመመለስ ስትሞክሩ፣ ቀደም ሲል ያጠኗችሁትን ርዕሰ ጉዳዮች በድጋሚ ታስታውሳላችሁ፣ ይህም ትምህርቱን በደንብ እንድትረዱት ያደርጋል። 6. የፈተና ጥያቄዎችን እና የተለያዩ የአጠያየቅ አይነቶችን ስልት ለማወቅ፡ ሞዴል ፈተናዎች የተለያዩ የጥያቄ አይነቶችን (ለምሳሌ፡ ምርጫ፣ እውነት ወይም ሐሰት፣ ወዘተ) እንድታውቁና ለእያንዳንዱ አይነት ጥያቄ እንዴት መልስ መስጠት እንዳለባችሁ እንድትረዱ ይረዳችኋል። 7. ትኩረት ማድረግ የሚያስፈልጉ ርዕሶችን እና አጠቃላይ ክለሳ ማድረግ ያለብንን ቦታዎች ለመለየት፡ ሞዴል ፈተናዎችን ከሰራችሁ በኋላ በየትኞቹ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደተሳሳታችሁ በመገምገም፣ በእነዚያ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ትኩረት ማድረግ ትችላላችሁ። ይህም ለፈተናው ስትዘጋጁ የትኞቹ አካባቢዎች ላይ ማተኮር እንዳለባችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል። በአጠቃላይ፣ ሞዴል ፈተናዎችን መፈተን እውቀታችሁን ለመገምገም፣ ለፈተናው ሁኔታ ለመለማመድ፣ ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም፣ በራስ መተማመናችሁን ለመጨመር እና ለዋናው ፈተና በተሻለ ሁኔታ ለመዘጋጀት ጠቃሚ ነው::
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
አዲስ ቲቪ
https://youtu.be/nvRuTcVxyNA
Education for generation: 👨👩👧በልጆች ህይወት ውስጥ የወላጆች ሚና👩👩👦👦 ክፍል አንድ 👉👉የልጆች ማንነት እና የወደፊት ህይወት ላይ ትልቅ ተፅእኖ ከሚያሳድሩ ተግባራት ውስጥ የወላጅነት ሚና/ parental role/ ዋንኛው ነው። ልጆች ወላጆች በሚያሳዩት አሉታዊ ይሁን አዎንታዊ ጠባይ ተጋላጭ ናቸው።United Kingdom departement of Education በተለያዩ ሀገራት ላይ ባደረገው ጥናት ጥሩ ያልሆነ/ ተገቢ ያልሆነ የወላጅነት ሚናዎች ሲል ግኝቱን አቅርቧል። በመሆኑም የወላጆች ሚና እንድንረዳ እና ንቁ ወላጅ እንድንሆን ስለሚያግዘን ከዚህ በታች አቅርበናል። የመጀመሪያው እንደሚከተለው ቀርቧል።👇👇 1.በቂ ትኩረት እና ጊዜ ለልጆች አለመስጠት 👉በስራ መጠመድ፣ ገንዘብ ለማግኘት መሮጥ 👉ከልጆች ርቆ ብዙ ጊዜ ማሳለፍ፣ 👉በስልክ/ በቲቪ መጠመድ 😔የልጆችን ጉዳይ ለቤት ሰራተኞች/ሞግዚቶች ሙሉ ሀላፊነት መስጠት። 👉👉አብዛኛውን ጊዜ ወላጆች " ዛሬ ከልጆቼ ጋር ፣ከቤተሰቤ ጋር ነው ቀኑን የማሳልፈው " ብለን እቤት ከሆንን ረዘም ላለ ሰዓት ወይ ተኝተናል አለዚያም በሞባይላችን/ በቲቪ ተጠምደናል። ልጆች ሲጫወቱ፣ሲጮሁ እንዳይረብሹን " ውጪ ተጫወቱ ቲቪ ልይበት" ልንል እንችላለን። እዚህ ጋር መገነዘብ ያለብን ነገር ለራሳችን ጊዜ አይኑረን አይደለም። ለራስ ጊዜ መስጠት በደንብ ያስፈልጋል ነገር ግን አላማው ከልጅ ጋር ማሳለፍ ከሆነ ማለፍ ያለበት ሙሉ ትኩረታችንን ለልጆቻችን በመስጠት፣አብሮ በመጫወት፣ በመዝናናት፣ እነሱን በማዳመጥ፣ የህይወት ክህሎቶችን በማስተማር መሆን ይኖርበታል። 👉👉ከልጆች ጋር በቂ ጊዜ ባለማሳለፋችን የተነሳ ልጆች ከወላጆች ሊያገኙት የሚገባውን ማህበረሰባዊ ክህሎት በተሳሳተ መንገድ ከውጪው አለም ይማሩታል።ይህ ደግሞ የወደፊት ህይወታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል።🙏🙏 ካነበብነው ይቀጥላል... 👨👨👧👧የልጆች አስተዳደግና የወላጆች ሚና 👨👨👧👧 ክፍል ሁለት ያለንን ልጅ ሳይሆን የምንፈልገውን ልጅ ለማሳደግ መፈለግ/Raising the child we want not the child we have/👇👇 ሁሉም ወላጅ ልጅ ከመወለዱ ቀደም ብሎ የሚፈልገውን ልጅ መሳል ይጀምራል "እኔ ልጄ እንዲሆን የምፈልገው……" በማለት ገደብ እንጥላለን። አንዳንዴ ከዚህም አልፎ ወደፊት ልጁ ሊኖረው ስለሚገባ ስራ እንወስናለን። አብዛኛውን ጊዜ ወላጆች እኛ ያጣነውን በልጆቻችን ለማግኘት እንሞክራለን። 👉ይህ ደግሞ ልጆቻችን ለተፈጠሩበት አላማ እንዳይኖሩ እና መክሊታቸውን እንዳያውቁ ያደርጋቸዋል። 👉ልጆቻችንን በማንነታቸው መቀበል ሳንችል ስንቀር እና እኛ ወደምንፈልገው ማንነት ስንገፋቸው ማንነታቸውን ያጡ፣ እኛ ደስ የሚለንን በማድረግ የሚኖሩ እና በራሳቸው ህይወት ሙሉነት የማይሰማቸው ይሆናሉ። ❤️❤️እንደወላጅ የእኛ ሀላፊነት ፈጣሪ የሰጣቸውን መክሊት እንዲያገኙት እና ለተፈጠሩበት አላማ እንዲኖሩ ማገዝ እና ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው።🙏🙏 ካነበብነው ሰናይ ሰንበት ይቀጥላል🙏