tgindex
HU Awada Fellowship

HU Awada Fellowship

Статистика

ይህ channel HU Awada B&E college የክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት ነው:: የቀድሞ ኃጢአታችን የተሰረዘልን። አሁን የምንኖርበት ኃይልና ፀጋ የተሰጠን፣ ወደ ፊት ደግሞ በጌታ ፊት ልንኖር ሥፍራ የተዘጋጀልን ነን። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!!

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
50
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
529
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
145
40 постов
Вовлечённость
27,4%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 50
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
39
1/48двое суток
44
1/72трое суток
48

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • #Daily_verse @HU_awada_fellow

  • #Daily_verse @HU_awada_fellow

  • #Daily_verse @HU_awada_fellow

  • #Daily_verse @HU_awada_fellow

  • #Daily_verse #HUAWADA

  • #Daily_verse #HUAWADA

  • #Daily_verse #HUAWADA

  • #Daily_verse #HUAWADA

  • #Daily_verse #HUAWADA

  • ⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉        ሰላም ሰላም ውድ የፌሏችን ልጆች👋                                ⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉  👉🏻 የዛሬውን የ LCG ጥናታችን እንዳልረሳችሁ እርግጠኞች ነን፡፡        የዛሬ ጥናታችን የሚሆነው 👇🏻👇 1ኛ ተሰሎንቄ 2:13-20                             🕰 ዛሬ                       ማታ 3:00-4:00 📍TELEGRAM LIVE (LCG GROUP) ሁላችንም በጊዜ እንገናኝ!!!! የተወደዳችሁ ናችሁ🥰🥰 @HU_AWADA_Fellow #LCG #ዕሮብ_ና_እሁድ #3:00-4:00 #1ኛ_ተሰሎንቄ

  • #Daily_verse #HUAWADA

  • HU Awada Fellowship pinned «የዊሊያም ኬሪ አስገራሚ ታሪክ ዊሊያም ኬሪ በ18ኛው እና 19ኛው ክፍለ ዘመን (1761–1834) የኖረ እንግሊዛዊ ሲሆን፣በዓለም አቀፍ ደረጃ "የዘመናዊ ሚስዮን አባት" (The Father of Modern Missions) በመባል ይታወቃል። ኬሪ የተወለደው በድሃ ቤተሰብ ውስጥ ሲሆን፣ኑሮውን የሚመራው ጫማ በመጠገን (Shoemaker) ነበር።ይሁን እንጂ በውስጡ ከፍተኛ የሆነ የትምህርት ጥማት ነበረው።ጫማ…»

  • የዊሊያም ኬሪ አስገራሚ ታሪክ ዊሊያም ኬሪ በ18ኛው እና 19ኛው ክፍለ ዘመን (1761–1834) የኖረ እንግሊዛዊ ሲሆን፣በዓለም አቀፍ ደረጃ "የዘመናዊ ሚስዮን አባት" (The Father of Modern Missions) በመባል ይታወቃል። ኬሪ የተወለደው በድሃ ቤተሰብ ውስጥ ሲሆን፣ኑሮውን የሚመራው ጫማ በመጠገን (Shoemaker) ነበር።ይሁን እንጂ በውስጡ ከፍተኛ የሆነ የትምህርት ጥማት ነበረው።ጫማ እየጠገነ በተመሳሳይ ሰዓት መጽሐፍትን በማንበብ ላቲን፣ግሪክ፣ዕብራይስጥ፣ጣሊያንኛ፣ደች እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን በራሱ ጥረት በሚገባ አጠና። ኬሪ የዓለምን ካርታ እየተመለከተ ወንጌል ላልደረሰባቸው ሕዝቦች ትልቅ ሸክም ይሰማው ጀመር።በወቅቱ የነበሩ የሃይማኖት መሪዎች "እግዚአብሔር አሕዛብን ማዳን ከፈለገ ያለ እኛ እርዳታ ያደርገዋል" ብለው ራዕዩን ሲቃወሙት፣እርሱ ግን እንዲህ የሚል ታሪካዊ አባባል ተናገረ፡- ​"ከእግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን ጠብቅ፤ ለእግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን ለማድረግ ሞክር።" (Expect great things from God; attempt great things for God.) በ1793 ዓ.ም ኬሪ ቤተሰቡን ይዞ ወደ ሕንድ አገር ተጓዘ።በዚያም እጅግ ከባድ ፈተናዎች ገጠሙት። የገንዘብ እጥረት፣አደገኛ በሽታዎች፣የአንዱ ልጁ ሞት፣እንዲሁም የባለቤቱ የአእምሮ ጤና መታወክ ተደራረቡበት።ከዚህ ሁሉ መከራ ጋር ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ለዓመታት ሰርቷል።ለሰባት ዓመታት ያህል ሰብኮ አንድም ሰው ወደ እምነቱ አልመጣም ነበር፤ነገር ግን ወደ ኋላ አላለም። 📌ለታላቅ የሚስዮን ጥሪ የሚያነቃቃ ወሳኝ እና አንገብጋቢ ጥያቄ የኬሪን ታሪክ መሠረት በማድረግ፦ ❓ዛሬ በዕለት ተዕለት የተለመደ ኑሮህ ውስጥ (ልክ ኬሪ ጫማ እንደሚጠግነው) ተወስነህ ሳለህ፤ከእግዚአብሔር ታላቅ ነገርን ጠብቅ፣ለእርሱም ታላቅ ነገርን ለማድረግ ሞክር' በሚለው እውነት ታምነህ፣ነገ የብዙዎችን ሕይወት ሊለውጥ የሚችል መለኮታዊ ተልእኮ የመጀመሪያውን የእምነት እርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ የሚያስቀርህ ትልቁ ፍርሃትህ ምንድን ነው? ❓ኬሪ ጫማ በሚጠግንበት ጠበብ ያለች ክፍል ውስጥ ሆኖ የዓለምን ካርታ እየተመለከተ ያልተደረሱ ሕዝቦች ያሰብ ነበር።ዛሬ በምትሠራው የዕለት ተዕለት ሥራ ወይም ባገኘኸው አነስተኛ አጋጣሚ ውስጥ ሆነህ፣ከራስህ ወሰን አልፈህ ትልቅ አህጉራዊ ወይም ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር እያሰብክ ነው? ወይስ አሁን ያለህበት ሁኔታ ራዕይህን አጥቦታል?  ❓የሃይማኖት መሪዎች "አንተ ዝም በል፤እግዚአብሔር ያለ አንተም ማድረግ ይችላል" ሲሉት ኬሪ ግን አልተቀበላቸውም። በውስጥህ የተቀመጠውን ታላቅ ዓላማ "አይቻልም"፣"አቅም የለህም" ወይም "የአንተ ሥራ አይደለም" ብለው የሚገታቱህ ድምፆች ሲበዙ፣ድምፃቸውን ሰብረህ የመራመድ ቆራጥነት አለህ? ❓ለምትኖርለት ዓላማ ወይም ለጀመርከው መልካም ሥራ ላብህንና ጥረትህን አፍስሰህ ለረጅም ጊዜ ምንም ዓይነት ውጤት ባታይ፣ተስፋ ሳትቆርጥ እስከ መጨረሻው የመቆም እምነት እና ጽናት አለህ? ❓ዛሬ በሕይወትህ እግዚአብሔርን አምነህ ለመውሰድ የምትፈራው፣ነገር ግን ካደረግከው የብዙዎችን ሕይወት ሊለውጥ የሚችል "ታላቅ የእምነት እርምጃ" (Risk) ምንድን ነው? ❓ የአንተ መኖር እና መሰጠት ለአካባቢህ ማኅበረሰብ የሚያመጣው ተልዕኮዊ ለውጥ ምንድን ነው? ከእኔነት አልፈህ ለትውልድ የሚሻገር ምን አሻራ እየጣልክ ነው? 💫​እውነተኛ ሚስዮን (ጥሪ) ማለት የተቀመጥንበትን ምቾት ትታን የሌሎችን ሕይወት ለመለወጥ የሚደረግ ታላቅ ጉዞ ነው። 🧠 ሚሲዮናዊ አስተሳሰብ አላችሁ?     📢ሚሲዮናዊ ናችሁ? ✍...........

  • #Daily_verse #HUAWADA

  • #Daily_verse #HUAWADA

  • 2 авг.163из EvaSUE58

    ተስፋ| ክፍል 3 ዛሬም በማንኛቸውም ተግዳሮት በተሞሉ መንገዶች ውስጥ ብንሄድ ቃሉ ለልባችን ጠገን እና ብርታት ይሆነናልና ። ደግመን ለራሳችን  እናንብበው። "እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።” ብርታትና የልብ ጽናት ያለው እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ነው ። አብርሃም በዘመኑ ሁኔታዎችን በማየት ከማመን ልቡ በራደ እና በደከመ ጊዜ ፤ እግዚአብሔር ዳግመኛ የሚያበረታው የተስፋውን ቃል በማስታወስ ነበር ።  የአባታችን አብርሃም ብርታቱ  በእግዚአብሔር ተስፋ በማድረግ ላይ የተመሠረተ ነበር ። በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ማለት ነገሮች በእግዚአብሔር ጊዜ እንዲሆኑ መታመን ነው ። ልብ ከደከመ ሁሉም የሰውነት አካል ክፍሎች ሥራቸውን ያቆማሉ ። ልብ ከደከመ ውስጥ ይታወካል ። ውሰጥ ከታወከ ውጭም ይታወካል ። የውጭ ደኽና መሆን መሠረት የውስጥ ደኽና መሆን ነው ። ልብ እንደ መናገሻ ከተማ ነው ። መናገሻ ከተማ ከታወከ ሌሎች ሠላም አይሆኑም ።  መናገሻ ከተማ ሠላም እንዲሆን አሸባሪ ሳይሆን እውነተኛው ንጉሥ መንበረ ዙፋኑን መቆጣጠር አለበት ። ልባችን እግዚአብሔር የሚያርፍበት መንበረ ዙፋን ነው ።  ልባችን ከመታወክ እንዲያርፍ  ንጉሡን እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ በእምነት በልባችን ልናነግሠው ይገባል ። “ልቤ ተስፋ በቈረጠ ጊዜ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በድንጋይ ላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ።”  መዝሙር 61፥2 ... መሉውን ጽሑፉን ለማንበብ ሊንኩን ተጫኑት 👇👇 https://telegra.ph/%E1%89%B0%E1%88%B5%E1%8D%8B--%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%8D-3-08-01

  • #Daily_verse @HU_awada_fellow

  • Live ጀምሮዋል 👇👇👇👇 Hey! Join our video chat: https://t.me/+SK6c7m3XCwM0NGU0

  • ⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉        ሰላም ሰላም ውድ የፌሏችን ልጆች👋                                ⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉  1ኛ ተሰሎንቄ 2:4 ነገር ግን ወንጌልን አደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር የታመንን ሆነን እንዳገኘን መጠን፥ እንዲሁ እንናገራለን፥ ልባችንን የሚመረምር እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ እንደምናሰኝ አይደለም። 👉🏻 የዛሬውን ፕሮግራም እንዳልረሳችሁ እርግጠኞች ነን፡፡        የዛሬ ጥናታችን የሚሆነው 👇🏻👇 1ኛ ተሰሎንቄ 2:1-8                             🕰 ዛሬ                       ማታ 3:00-4:00 ሁላችንም በጊዜ እንገናኝ!!!! የተወደዳችሁ ናችሁ🥰🥰 @HU_AWADA_Fellow #LCG #ዕሮብ_ና_እሁድ #_3:00-4:00 #1ኛ_ተሰሎንቄ

  • #Daily_verse #HUAWADA