tgindex
Islamic History

Islamic History

Статистика

አሰላሙ አለይኩም ውዶቼ በዚህ ቻናል የተለያዩ ኢስላማዊ የሆኑ ታሪኮችን እናያለን።📚📚📚

Последний пост
2 нояб. 2024 г.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
80
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
96
21 постов
Вовлечённость
120,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • «ዱኒያ» «የሰው ልጅ አንዳንዴ አላህ"ﷻ"በሐብት፣ በመልካም ሚስት፣ በልጆች ሲያጣቅመውና በጤንነት ሲያቀማጥለው የጸጋን በሮች ሁሉ በከፈተለት ጊዜ ልክ አሏህ እንደወደደው አድርጎ ያስባል። فَأَمَّا ٱلۡإِنسَٰنُ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ رَبُّهُۥ فَأَكۡرَمَهُۥ وَنَعَّمَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَكۡرَمَنِ ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡ (89/15) «ሌላኛው ሰው ደግሞ ቤት፣ መኪና፣ ሀብት፣ሚስት ስለሌለው ብትኖርም ሀዘን ስትሆንበት፣ ልጆቹ አመጸኞች ሲሆኑበት ልክ አላህ እንደጠላው አድርጎ ያስባል። وَأَمَّآ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ فَقَدَرَ عَلَيۡهِ رِزۡقَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَهَٰنَنِ በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡ (89/ 16) « እውነታው ግን እነዚህ አይነት የሰው ልጆ አስተሳሰብና ለአላህ ውዴታ መመዘኛ የሰጡት ትርጉም ትክክል አይደለም። ለዚህም አላህ"ﷻ" ቀጥሎ { كَلَّا } ሲል ሁለቱንም የተዛባ አስተሳሰብ ውድቅ ደረገው። {"كَلَّا") በዐረብኛ ቋንቋ ከፊቷ የነበረን የተዛባ አስተሳሰብ ውድቅ አድራጊ ቃል ናት። "ማለትም ከላይ በመጣው ዐውድ መልእክቷ «እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ እንደምታስቡት አይደለም። የሀብትና ጸጋ ስፋት መስጠቱ የአላህ ውዴታን አይገልጽም። የሀብት ጥበትና የተጨናነቃ ሀያት የአሏህን አለመውደድ አይገልጽም። አላህ"ﷻ" ዱንያን ለሚወደውም፣ለማይወደውም፣ ለሙእሚንም፣ ለካፊርም፣ ይሠጠዋል» ማለቷ ነው። «የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ «ዱኒያ ከአላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ያክል ሚዛን ቢኖራት ኖሮ ካፊር አንዲትን ጉንጭ ውሃ ከእርሷ አይጎነጭም ነበር»። (ቲርሚዚይ፥ 2320) «የዱኒያ ነገር እንደዚህ ከሆነ፦ አንድ ሰው አላህ ጸጋ በረከቱን ቢከፍትለት፡በጤና ፣ በሀብት፣ በልጆች ቢንደላቀቅ በእርግጥ የአላህ (ፈድል) ችሮታ ነው። ግን ይህ ሰው ሙጅሪም ሁኖ ጌታውን እያመጸ አላህ"ﷻ" ጸጋና በረከት የሰጠኝ ስለወደደኝ ነው ብሎ ካሰበ መልሱ "ከልላ" ነው። «ሰዎች በኩፍር ላይ ሁነው የወንጀልን አይነት ሁሉ እየፈጸሙ አላህ በሀብትና በንግሥና ምስራቁንም ምዕራቡንም እንዲገዙ ሲፈቅድ በዚህ ጸጋ ብቻ አላህ ስለወደዳቸው መስሎ የሚታያቸው ይህንንም ጸጋ ለውዴታው ማስረጃ ሊያደርጉ ይችላሉ። መልሱ ግን አሁንም «አይደለም» ነው። «ይህ አይነት እውነታ በተጨባጭ ታሪክ ተፈጽሞ አልፏል። «ቃሩን»፦ አመጸኛ ከኃዲ ነው አላህ አይወደውም። ግን የሀብቱ ካዝና መክፈቻ ቁልፎች ብቻ በብዙ በግመሎች ይጫን ነበር። ግን አላህ እስከ ንብረቱ ወደ ምድር አሰጠመው። «ለነብዩ ሱለይማን(ዐሰ)»፦ አላህ ንግሥናንና ሀብትን ሰጥቷቸዋል ግን ይወዳቸዋል ምርጥ የአሏህ ባሪያ ታላቅ ነብይ ነበሩ። «ለፈርዖን»፦ አላህ ንግሥና ሀብትን ጸጋዎቹን ለግሶታል። ጸጋው ከአቅሙ በላይ ሁኖበት «እኔ ሃያሉ አምላክ» ነኝ ብሎ እስኪናገር ድረስ በጸጋ አቀማጥሎታል። ግን አይወደውም በክፉ ቅጣት ይዞታል። «ዱንያ የአሏህን ውዴታ መለኪያ መስፈርት በፍጹም ልትሆን አትችልም። ምክንያቱም የትንኝ ክንፍ ያክል እንኳ ሚዛን የላትምና። አላህ"ﷻ" እንዲወደው የፈለገ፦ ሙእሚን መሆን፣ የእርሱን ትእዛዝ ይጠብቃል፣ መልካምን ይሠራል፣ ለሠዎች ያዝናል፣ ሁሌ ለኽይር ስራ ሁሉ ተሽቀዳዳሚ ይሆናል። «በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡ (2/195) «አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡ (2/222) «በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀ ሰው አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል፡፡ (3/76) «አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡ (3/146) «አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና፡፡ (3/159) «አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡ (5/42) «በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና፡፡ (49/9) «አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ኾነው በመንገዱ (በሃይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል፡፡ (61/4) የአላህን ሐቅ ጠብቀው እሱ ከወደዳቸው ባሮቹ ያድርገን። ❐.በቴሌ ግራም፦ https://t.me/OusmanTe9

  • ሰውባን (ረ.ዐ) ነብዩን ከ ማንም በላይ እሚወዳቸው ሱሃባ ሰውባን (ረ.ዐ) ባርያ የነበረ ሰውና ነብዩ ﷺ ከባርነት ነፃ ያወጡት ሰው ነበር። ነብያችንን ከማንም በላይ እሚወዳቸው ሱሃባ በመባል ይታወቃል። ሰውባን ዘውትር ነብዩን ባያቸው ቁጥር በጣም ደስተኛ ስለሚሆን በ ቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ነብዩን ( ﷺ ) እያያቸው እራሱን ማስደስቱን የዘውትር ተግባሩ አደረገው። ሰውባን ዘውትር መትቶ ነብዩን (ﷺ ) መቶ በተመለከታቸው ግዜ የ ኢማን ደረጃው ከፍተኛ ምጥቀት ላይ ይደርሳል በተጓዳኝም ከተለያዩ ጭንቀቶች ና ከ ዱንያ ጭንቀቱ ይላቀቃል። አንድ ቀን ግን ሰውባን (ረ.ዐ) ነብዩን ሳያያቸው ቀረና በጣም ተናዶ ቆይቶ በመጨረሻም ነብዩን ( ﷺ) አያቸው። ከዛም ነብዩ (ﷺ) ሰውባንን አዩትና እንዲህ አሉት። ሰውባን ምነው ችግር አለ እንዴ ? ዛሬ የተናደድክ ትመስላለህ ? ብለው ጠየቁት። ከዛም ሰውባን ( ረ.ዐ) እንዲህ ሲል መለሰላቸው። " ያረሱለላህ ( ﷺ ) እኔ እርሶን በጣም እንደምወዶት ና በየቀኑ እርሶን በ አይኔ ማየት የተለየ ደስታን እንደሚሰጠኝና ፍሰሃን እንደሚያጎናፅፈኝ ያውቁ ኖሯል ? እርሶን በ አይኔ ማየት ለኔ ምን እንፈሆነ አያውቁም። እኔ እርሶን በአይኔ ባየሁ ግዜ በጣም ደስተኛ እሆናለሁ ነገር ግን እርሶን ሳላዮት ከቀረሁ ሞት ና አኺራ ትዝ ይለኛል። በ ውስጤም እንዲህ እያልኩ አወራለሁ። እርሶ ወደ አኺራ የሄዱ እለት ና አላህ ( ሱ.ወ) ወደ ራሱ የወሰዶት እለት ወደ ጀነት ሲገቡ ፣ ጀነት መግባት ብቻም ሳይሆን ደረጃው በጣም ከፍ ወዳለው ጀነት የገቡ እለት ከ ነብያት፣ ሹሃዳዖች ና ደጋጎች ጋር ስለሚሆኑ እኔ እርሶን አላገኞትም እናም ከዚህ በኃላ አላገኞትም ብዬ ሰጋለሁ ምክንያቱም እኔ ጀነት ብገባም እኔ እምገባው ጀነት እርሶ ከሚገቡት ጀነት በደረጃ ያነሰ ስለሚሆን እርሶን አላዮትም ድንገትም ጀነትም እማልገባ ልሆን እችላለሁ ይህ ከሆነ ደግሞ እርሶን ደግሜ አላዮትም። " ሰውባን ይህን ተናግሮ ጥቂትም አልቆየም ጅብሪል ( ዐ.ሰ) ወሀይ ይዞ ወረደ ተከታዩን የቁርዓን ዓያት ለ ነብዩ ( ሰ.ዐ) አወረደላቸው። ﻭَﻣَﻦ ﻳُﻄِﻊِ ﺍﻟﻠّﻪَ ﻭَﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝَ ﻓَﺄُﻭْﻟَﺌِﻚَ ﻣَﻊَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺃَﻧْﻌَﻢَ ﺍﻟﻠّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢ ﻣِّﻦَ ﺍﻟﻨَّﺒِﻴِّﻴﻦَ ﻭَﺍﻟﺼِّﺪِّﻳﻘِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟﺸُّﻬَﺪَﺍﺀ ﻭَﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤِﻴﻦَ ﻭَﺣَﺴُﻦَ ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺭَﻓِﻴﻘًﺎ ሱረቱ ኒሳዕ ከ 69-70 ያለው ዓየት በ ሰውባን ( ረ.ዐ) ምክንያት ነው የወረደችው። ሰውባንም ( ረ.ዐ) እቺ ዓያ በሱ ምክንያት መውረዷን ቡሽራውን ከነብዩ ( ﷺ ) ሲሰማ በጣም ተደስቶ ነበር ለሰዎችም እቺ ዓያ እኔ ለነብዩ ከነበረኝ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ በኔ ምክንያት ነበር የወረደችው እያለ ለ ጓደኞቹ ይናገር ነበር።

  • በአንድ ጊዜ የረሱል ባልደረባ የሆኑታ አቡበክር እና ነቡዬ ካዕባን ተደግፈው ሳለ ኡሙ ጀሚል ምትባል ሴት መጣች በእጅዋ ትልቅ ድንጋይ ይዛለች ለአቡበክር መጥታ ሙዘመም/ የተወገዘ ማለት ነው / የታለ አለች መልስ አልሰጣትም ባገኘው ይህን ድንጋይ አናቱ ለይ እጥልበት ነበር ብላ መጥፎ ግጥም ገጥማ ሄደች ይሄኔ የኔ ነቢይ አይንዋን አላህ ጋርድዋት ነው ያላየቺኝ አሉ እና በመቀጠል እንዲህ አሉ [ ሙዘመምን ይሰድቡታል እኔ ደሞ ሙሀመድ ነኝ የጌታዬ መልዕክተኛ ] በአንድ ጊዜ ኡመር ኢብኑ አብዱል አዚዝ በጨለማ እየሄዱ ነበር ጨለማ ስለነበር ሳያዪ አንድን ሰው በድንገት ረገጡት ሰውዬውም በንዴት አታይም አህያ ነህ እንዴ አላቸው ኡመርም [  no አህያ አይደለውም ኡመር ነኝ ብለውት ሄዱ ]

  • ብዙ ሰው ትኩረት ነፍጎታል። በተቃራኒው በማይረባ ነገር ተጠምዷል። መረጃው ያለው ሰው ትንሽ ስለሆነ ይመስለኛል። አመናችሁም አላመናችሁም ሰሞኑን በበርካታ ትምህርት ቤቶች ኒቃብ ተከልክሏል። የሚደርስላቸው ተቋምም ሆነ ድምፅ የሚሆናቸው ግለሰብ አጥተው በርካታ ኒቃቢስቶች ትምህርት ካቆሙ ሳምንት አልፏቸዋል። ለማን ቢነገር ይሻላል? መጅሊስ ይህን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ በቋሚነት ለምን አይፈታም? ምን እየተካሄደ ነው? ዛሬስ በምን እናመካኝ? እህቶቻችንን ስልታዊ በሆነ መልኩ ከትምህርት ገበታ ማገድ እስከ መቼ? ትኩረት ለኒቃቢስት ተማሪዎች! ኒቃቧንም ትለብሳለች፣ ትምህርቷንም ትማራለች። (ይህን መልዕክት በማሰራጨት ቢያንስ ሰዎች ዘንድ እየሆነ ስላለው ነገር መረጃው እንዲኖር እናድርግ። በዱዓችንም እናግዛቸው። || t.me/MuradTadesse

  • በረሱሉ ዘመን አንዲት እህትሽ በአዉድቅ በሽታ ትሰቃይ ነበር። ያቺ ሴትም የልብና የሰዉነት ሀኪም ወደሆኑት ወደ ረሱሉ በመምጣት ችግሯን ተናገረች። ረሱሉም ሁለት ምርጫ ሰጧት። አንድም ዱዓ አድርገዉላት ከበሽታዉ መዳን፣ አልያም በበሽታዉ ላይ ታግሳ ጀነትን ማግኘት። ሙዕሚኖች ዘንድ ከጀነት በላይ ዉድ ነገር አልነበረምና ታግሳ ጀነትን ማግኘትን መረጠች። ላኪን ሌላ ችግር አለ። እቺ እህትሽ አዉድቁ በሚጥልባት ወቅት የተወሰነ አካሏ ይገለጣል፣ ፀጉሯ የተወሰነዉ ክፍት ይሆናል። ይህ እንዲቀረፍላት ረሱሉ ዱዓ እንዲያረጉላት ጠየቀች። ረሱሉም ዱዓ አረጉላት። አይገርምም! እቺ ሴት ኮ አዉድቁ ጥሏት ሰዉነቷ ቢገለጥ እንደማትጠየቅ ታዉቃለች። ግን እቺ እህትሽ በክብሯ አትደራደርምና አዉድቅ ጥሏት እንኳን የትኛዉም የሰዉነቷ ክፍል እንዲታይ አትፈቅድም። እህቴ! አደራሽን በመሸፈኛሽ አትደራደሪ! በሂጃብሽ አትደራደሪ! ፀጉርሽን ለወንዶች ክፍት አታርጊ! አደራሽን ወንዶች በአይናቸዉ በልተዉ ሚጨርሱሽ ተራ ዕቃ እንዳትሆኚ! : እህቴ! አላህ ዘንድ ትራክሺያለሽና ራስሽን አታርክሺ! ያንን ዘመናችን ካመጣዉ ሂጃብ መሳይ ነገርም ተጠንቀቂ! ያን ከመሸፈን ይልቅ ሳቢ ሆኖ ምትጋጌጪበትን ሂጃብ ተጠንቀቂ! ያ ፀጉርሽን ሸፍኖ ሰዉነትሽን ወጥሮ ሚይዘዉ ልብስ ሂጃብ አይደለም። ሂጃብ ማለት ራስሽንም መላዉ አካላትሽንንም እኩል መሸፈን ሚችለዉ ነዉ። ያ አንገትን፣ ጭንን፣ እጅን የሚያሳየዉማ ዘመናዊ ሂጃብ እንጂ ሸሪዓዊ ሂጃብ አይደለም። ሰሀቢያት እህቶችሽ የሂጃባቸዉ ጉዳይ በጣም ያስጨንቃቸዉ ነበር። የሆነ ጊዜ ኡሙ ሰለማ የሴት ልጅ ከእግሯ በታች ልብሷን ምን ያህል ማርዘም እንዳለባት ረሱሉን ስትጠይቅ ረሱሉ አንድ ስንዝር እንደሚበቃ ነገሯት። እሷ ግን አንድ ስንዝር ሴት ልጅን ሙሉ በሙሉ መሸፈን አይችልም ብላ ተሟገተች። ረሱሉም አንድ ክርን እንዲያረጉና ከዚያ እንዳያስበልጡ ነገሯት። አጀብ! ኡሙ ሰለማ የዚህ ዘመን ወንዶች ልብስ አንድ ክርን ወደታች ረዝሞ፣ በታቃራኒዉ የሴቶቹ ደግሞ አንድ ስንዝር ወደላይ አጥሮ ብትመለከት ምንትል ይሆን? የሆነ ጊዜ ሀፍሳ ቢንት አብዱረህማን ኢብኑ አቡበክር ፊቷን የተወሰነ የሚያሳይ ስስ የፊት መሸፈኛ ልብስ ለብሳ አክስቷ አዒሻ ጋር መጣች። አዒሻም ተቆጥታ 'አላህ ሱረቱል ኑር ላይ ያወረደዉን አታዉቂም እንዴ?!' ብላ ልብሱን በጫጨቀችዉ። ኡሙና! የኛ ዘመን ሴቶችን ሂጃብ ብታዪ ምን ትዪ ይሆን! የሴት ሰሀቢያት ኮ አላህ ከነዉር ሁላ ካፀዳቸዉ ከረሱሉ ሳይቀር ይሸፋፈኑ ነበር። ከረሱሉ ከተሸፈኑማ ከሌላዉ ተራና ስሜቱን መቆጣጠር ከማይችል ከኛ ዘመን ወንድ መሸፈን ይበልጥ ዋጂብ መሆኑን ለማስረዳት ሰነድ መጥቀስ ያለብኝ አይመስለኝም። ይህ ትዉልድ አለቅጥ በሸህዋ የተፈተነ ትዉልድ ነዉ። አንቺ ቢያንስ ባለመገላለጥ ትዉልዱንም ራስሽንም ከፊትና ጠብቂ! ልክ እንደ ፋጢመቱ ዘህራዕ በህይወት እያለሽ አይደለም.. ሞተሽ እንኳን ሰዉነትሽ መገላለጡ የሚያሳስብሽ ጠንካራ ሴት ሁኚ! በአላህ እምላለሁ! ክብሯን ምትጠብቅን፣ ሂጃቧን ምታጠብቅን ሴት ማንም ተራ ወንድ አይቀርባትም። ይህ የምድር ህግ ነዉ! ዝንቦች ሁሌም ቆሻሻ ላይ ነዉ የሚያርፉት። ያቺ ብዙ ሰዉ ስለሚያወራትና ወንዶች ስለከበቧት  ዉብና እድለኛ አርጋ ራሷን የምታስብ ሴት ትገርመኛለች። እቺ ሚስኪን ሴት የአንድ ነገር ዋጋ ሲረክስ ፈላጊዉ እንደሚበዛ ዘነጋች እንዴ? በዕዉነታዉማ ዉዷም፣ ዉቧም፣ በዱንያም በአኼራም እድለኛዋ ያቺ በሂጃብ የተዋበችዉ የአላህን ትዕዛዝ የጠበቀች ሴት ናት።

  • ኡሙ_ሰለመህ “ምርጥ የሴት ጀግናና ድንቅ የኢስላም ጠበቃ!” የምእመናን እናት ኡሙ ሰለመህ በመጀመሪያ ያገበችው አቡ ሰለማን ነበር። ባልና ሚስቱ በጣም ይዋደዱ ነበር። በአንድ ወቅት ኡሙ ሰለመህ ለባለቤቷ እንዲህ አለችው፦   “ባል ሚስቱ እያለችም ሆነ ከሞተች በኋላ ሌላ ሴት የማያገባ ከሆነና ሚስትም ባሏ ከሞተ በኋላ እንደገና የማታገባ ከሆነ ባልና ሚስቱ ጀነት ውስጥም ባልና ሚስት ይሆናሉ ሲባል ሰምቻለሁ። እኔ ከሞትኩ በኋላ እንደማታገባ ቃል ግባልኝና እኔም ቀድመህኝ ከሞትክ ድጋሜ እንደማላገባ ቃሌን እሰጥሃለሁ” አለችው። አቡ ሰለመህ ግን ፦ “እኔ እንደምልሽ ታደርጊያለሽን? ብሎ ጠየቃት፡፡ እሷም “በእርግጥ” ብላ መለሰች፡፡ እሱም “ከሞትኩኝ በኋላ እንድታገቢ እፈልጋለሁ” አላት፡፡ ቀጥሎም “አላህ ሆይ! እኔ ከሞትኩ በኋላ ኡሙ ሰለመህ ከእኔ የተሻለ ሰው እንድታገባ አድርጋት፡፡ እሱም ምንም ዓይነት ችግር የማያስከትልባት ይሁን” ብሎ ዱዓ አደረገ።   አቡ ሰለመህ በሞተ ጊዜ ኡሙ ሰለመህ “ከአቡ ሰለመህ የሚበልጥ ማን አለ?” አለች፡፡ ብዙም አልቆየች፡፡ ነቢዩ አጯት፡፡   በመጀመሪያ ባልና ሚስቱ ወደ ሐበሻ ነበር የተሰደዱት፡፡ ከተመለሱም በኋላ እንደገና ወደ መዲና ተሰደዱ። ኡሙ ሰለመህ ሁኔታውን ስትገልጽ፦   “ባለቤቴ ወደ መዲና ለመሰደድ በወሰነ ጊዜ ዕቃዎቹን ግመሉ ላይ ጫነ። እኔና ልጃችን ግመሉን እንድንጋልብ አደረገ። እሱም ገመዱን በመያዝ ከከተማው እስክንወጣ ግመሉን መራ። የአባቴ ጐሣዎች (ባኑ ሙጊራ) ስንሄድ አዩንና መጥተው የግመሉን ገመድ ከአቡ ሰለመህ ነጥቀው “አንተ ወደፈለክበት መሄድ ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ልጃችን ካንተ ጋር ሄዳ እንድትጠፋ አንፈቅድም።” በማለት በግድ እኔና ልጄን ወደ ጐሣው ይዘውን ሄዱ። የባለቤቴ ጐሣዎችም (በኑ ዐብዱል አሰድ) ነገሩን ሲሰሙ ወደ በኑ ሙጊራ መጥተው ከፈለጋችሁ ልጃችሁን ልታቆዩዋት ትችላላችሁ። የጐሣችን የሆነውን ልጅ ግን ልታቆዩት አትችሉም። እናንተ ልጃችሁ ከባሏ ጋር መሄድ ከለከላችሁ፣ እኛስ ልጃችንን ከናንተ ጋር እንዲኖር እንዴት እንፈቅላችኋለን? በማለት ክርክር አነሱ። ልጄንም በግድ ወስደው ሄዱ። አቡ ሰለማ ወደ መዲና ገባ። በዚህ ዓይነት ሁኔታ እያንዳንዱ የቤተሰቡ አባላት ተለያዩ። በየቀኑ ወደ በረሃው እየሄድኩ ቀኑን ሙሉ አለቅስ ነበር። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከባለቤቴና ከልጄ ጋር ለአንድ ዓመት ያህል ተለያየሁ። ከአጐቶቼ ልጆች አንዱ ሁኔታዬ ስላሳዘነው ለጐሣዎቼ አባላት “ይህችን ሴት ከባሏና ልጇ ጋር ለያያችኋት፡፡ ምናለ ብትራሩላትና እንድትሄድ ብታደርጓት?” አላቸው። በዚህ በአጐቴ ልጅ ሰብአዊ ጥረት የተነሳ የበኑ ሙጊራ ጐሣዎች እንድሄድና ከባለቤቴና ከልጄ ጋር እንድገናኝ ተስማሙ። በኑ ዐብዱል አሰድም ልጄን ሰጡኝ። የተዘጋጀ ግመልም አገኘሁኝና ልጁን በእቅፌ አድርጌ ግመሉ ጀርባ ላይ በመቀመጥ ጉዞዬን ወደ መዲና ብቻዬን አቀናሁ። ገና አራት ማይሎች ሳልጓዝ ዑሥማን ኢብኑ ጦልሃን ‘ተንዓም’ ላይ አገኘሁትና “ወዴት ነው የምትሄጅው?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም ወደ ‘መዲና’ አልኩት፡፡ “የጉዞ ጓደኛ የለሽም?” ሲለኝ “አዎን ከአላህ በስተቀር ማንም አብሮኝ ያለ የለም’ አልኩት፡፡ የግመለን ገመድ ጨበጠና መምራት ጀመረ። በአላህ እምላለሁ! ከዑሥማን የበለጠ ጨዋ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም። መውረድ ሲኖርብኝ ግመሉ እንድንበረከክ ያደርግና እሱ ከቁጥቋጦ ጀርባ ይሆናል። ግመሉ ላይ መውጣት ስፈልግ አጠገቤ ያመጣውና እንዲንበረከክ ያደርገዋል። ከዚያም ገመዱን በመያዝ ግመሉን ይመራል። እንዲህ እያልን ቁባእ (ከመዲና ዳርቻ) ደረስን። አቡ ሰለመህ እዚያ እንደሚኖር ነገረኝ። ከዚያም ወደ ባለቤቴ እንድሄድ አሳየኝና እንደገና ወደ መካ ተመለሰ። በአላህ እምላለሁ! በዚያች አንድ ዓመት ውስጥ ያየሁት ስቃይ ማንም የሚችል የለም።”   ኡሙ ሰለመህ በአላህ ያላትን እምነትና መተማመን እንመልከት፡፡ ረጅምና አስቸጋሪ የሆነውን ጉዞ ብቻዋን ጀመረች፡፡ አላህም እንዴት እርዳታውን እንደላከላት እናስተውል። አላህ ለሚተማመኑበት ሰዎች እርዳታ ለመስጠት የፈለገውን ሰው እንደሚወክል ጥርጥር የለውም። የሰዎች ሁሉ ልብ በእጁ ነውና።   በሸሪዓ ሕግ ደረጃ ሴት ልጅ ብቻዋን ረዥም ጉዞ ማድረግ የተከለከለ ነው___ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ግዴታ የሆነ ስዴት ሲቀር

  • በጣም ትልቅ ፀጋ ዉስጥ ነን! """"""""""""""""""""""""""" ታዋቂው ዳዒ ዐምር ኻሊድ እንዲህ ይላል - በአንድ ወቅት ከሆኑ ወጣቶች ጋር ተቀማምጠን ሳለን እንደዋዛ የአላህን (ሱ.ወ.) ፀጋዎች መቁጠር ጀመርን፡፡ የትኛው ፀጋ እንደሚበልጥም አወጋን፡፡ ~ ከኛ መካከል አንዱ ‹ጤና ነው› ሲል ተናገረ፡፡ ~ ሌላኛው ‹ልጆች ናቸው› አለ፡፡ ሌላው ‹ማየትና መስማት መቻል ነው› አለ፡፡ ~ ‹ትልቁ ፀጋ እናቴ ናት› ያለም አለ፡፡ ~ እንዲሁ ‹ሀብት የሠጠኝ ጌታ በርግጥም ትልቁን ፀጋ ሠጠኝ› ያለም ነበር፡፡ ~ ‹እስልምና ነው› ያለም አለ፡፡ ~ ከመካከላችን አንድ የአሥራ ስምንት ዓመት ወጣት ግን አላህ (ሱ.ወ.) ከሠጠን ፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ ‹ጌታችን ጌታችን መሆኑ ነው፡፡› አለ፡፡ ትርጉሙ ምን ማለት ይሆን? ይህ ታዳጊ ወጣት በዚህች ዓለም ላይ ትልቁ ፀጋ ጉዳያችን ይዞ ያለው አላህ (ሱ.ወ.) መሆኑ ነው ማለቱ ነው፡፡ እሱ ነው ዋስትናችን፡፡ ልባችንን፣ እጃችንን፣ ግንባራችንን… ሁሉ ነገራችን ይዞ ወደ መልካም ነገርና ወደ ስኬት የሚመራን አላህ ነው፡፡ ትልቁ የአላህ ፀጋ አላህ አላህ መሆኑ፣ አላህም ጌታችን መሆኑ ነው፡፡ ጥራትና ልዕልና የተገባው ይሁን፡፡ በአላህ ጌትነት ወደድን፣ መልዕክተኛው ነቢያችን መሆናቸውን ወደድን፣ እስልምናን በሃይማኖት በኩል ወደድን፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) ለሚወደውም ለማይወደውም ሀብት ይሠጣል፡፡ አላህ ላመነበትም ለካደዉም ገንዘብ ይሠጣል፡፡ ጤና፣ ቤትና ንብረት ይሠጣል፡፡ እስልምናን ግን የሚሠጠው እርሱ ለወደደው ሰው ብቻ ነው፡፡ ወደ መንገዱ የሚመራው ራሱ የመረጠውን ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ሙስሊም መሆን መመረጥ ነው፡፡ ሙስሊም መሆን መብለጥ ነው፡፡ ሙስሊም መሆን መወደድ ነው፡፡ ባይወደን ኖሮ መቼ ይሠጠን ነበር፡፡ አላህ ወዶን እስልምናን ሠጠቶናልና ክብር ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ይሁን፡፡ አላህ እኔ፣ አንተና አንቺ ግን ሳንለምነው፣ ሳንማፀነው ፣ ሳንወተውተው ሙስሊም አደረገን። ለኢብራሂም (ዐ.ሰ.) አባት ፣ ለኑሕ (ዐ.ሰ.) ልጅ፣ ለሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) አጎት ያልሰጠውን ፀጋ ሠጠን፡፡ አላህ እስልምናን ሠጠን፡፡ አምላካችን ንፁህ የተፈጥሮ ሃይማኖትን ለገሰን፡፡ እንደ እስልምና ምን ገር የሆነ ሃይማኖት አለ፡፡ ለመረዳትም ሆነ ለትግበራ አይከብድም፡፡ ይህ በርግጥም ትልቅ ችሮታ ነው። አላህ የትላልቅ ችሮታዎች ባለቤት ነው። እርሱ ችሮታውን ለሚሻው ሰው ብቻ ይሠጣል። ነገርግን ብዙዎች አላህ የሠጣቸውን ፀጋ አያስተውሉም ፤ አያስተነትኑም ፤ አስተንትነውም አያመሰግኑምም፡፡ የእስልምና ፀጋ ከየትኛውም ፀጋ ሁሉ የላቀ ነው፡፡ ቢመዘን ቢለካ የትኛውም ፀጋ አይደርስበትም። ምስጋና ወደቀናው መንገድ ለመራን ጌታ ይሁን። እሱ ባይመራን ኖሮ  ባልተመራን ነበር። "እስልምናን ለሰጠን አላህ ምስጋና ይገባው" በሉ።

  • አቡ ሁረይራ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ ነቢዩ መስጊድ ውስጥ ተቀምጠው ከሰዎች ጋር በማውጋት ላይ እያሉ አንድ በደዊን መጣ። "ሰዓቲቱ መቼ ትከሰታለች ?" ሲልም ጠየቃቸው። መልዕክተኛው ወጋቸውን ቀጠሉ። አንዳንድ ሰዎች "ጥያቄውን ሰምተዋል፤ ስላላስደሰታቸው ነው" አሉ። ከፊሎቹ ደግሞ፦ "አልሰሙትም" ተባባሉ። መልዕክተኛው የጀመሩትን ወግ ሲያጠናቅቁ፦ "ስለ ሰዓቲቱ የጠየቀኝ ሰው የት አለ ?" አሉ። "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እዚህ ነኝ" አላቸው። "አደራ ስትጠፋ ሰዓቷን ተጠባባበቅ" አሉት። "አደራ የምትጠፋው እንዴት ነው ?" አላቸው። "ኃላፊነቶች ተገቢ ላልሆኑ ሰዎች በሚሰጡ ጊዜ ሰዓቷን ተጠባበቅ" አሉት። (ቡኻሪ) ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች 1/ ሰዓቷ ዓለም የምትጠፋበት የቂያማ ዕለት ናት። 2/ ከቂያማ ምልክቶች አንዱ የአደራ መጥፋት ነው። 3/ የአደራ መጥፋት ማለት በነቢዩ አተረጓጓም መሠረት ኃላፊነቶች አግባብ ላልሆኑ ሰዎች መሰጠታቸው ነው። 4/ ይህም ማለት መብቶች ይጨፈለቃሉ። ፊትናም ይነሳል። 5/ ኢብኑ ዑመር እንዳሉት፦ "ይህ ሐዲሥ በትምህርትም ሆነ በፈትዋ መስክ መሠረታዊ ተደርጎ ሊቀራ ይገባል።" 6/ በሌላ ሐዲሥ፦ "ከቂያማ ምልክቶች መካከል አንዱ እውቀት ከሕጻናት መፈለጉ ነው" የሚል እናገኛለን።

  • ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ አንድ ከገጠር የመጣ ኑሮው ያልሰመረለት(ድሃ) ግለሰብ ሰሃን ሙሉ ወይን #ስጦታ ያመጣላቸዋል። ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ስጦታውን ተቀብለው ወይኑን መብላት ጀመሩ...የመጀሪያውን ጎርሰው ፈገግ አሉ...ሁለተኛውንም ጎርሰው ፈገግ አሉ...ግለሰቡም እጅጉን #ተደሰተ...የነቢዩ ጓዶች(ሶሃቦች) ሁሌም ለነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ስጦታ ሲመጣላቸው ስለሚያካፍሏቸው ይህንን (ጣፋጭ) ወይን እንዲያካፍሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ...የአላህ መልእክተኛ ግን ሳያካፍሏቸው እያንዳንዱን የወይን ፍሬ እየበሉ እና ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተው ጨረሱ። ስጦታ አቅራቢው እጅግ በጣም ተደሰቶ...ስጦታውንም ስለወደዱለት አመስግኖ ሄደ። አንድ የነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጓድ(ሶሃባ) ጠጋ ብሎ ነቢዩን ጠየቃቸው ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ምነው ሳያካፍሉን?›› እሳቸውም ፈገግ ብለው መለሱ ‹‹ሰወዬው መደሰቱን አይታችኋል አይደል?? ወይኑን ስቀምሰው በጣም #ይመር ነበር...ባካፍላችሁ አንዳችሁ ግለሰቡን #የሚያስከፋ እና ደስታውን የሚያደፈርስበትን ነገር እንዳታሳዩት ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው ብለው መለሱላቸው።

  • 🍁"አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀምባቸው። ☝️የአላህ መልእክተኛ   .اللهم  صل وسلم علي نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين . እንድህ ብለዋል ⓵ ወጣትነትህን ከማርጀትክ በፊት ⓶ ጤንነትህን ከመታምህ በፊት ⓷ ሀብትህን ከመደህየትህ በፊት ⓸ ትርፍ ጌዜህን ከመጨናነቅህ በፊት ⓹ ህይወትህን ከመሞትህ በፊት

  • ☑️  ሼኸ ፈውዛን አላህ ይጠብቀዉና እንዲህ ይላሉ። 🌐 ከሰዎች መካከል (لا إله إلا الله) የምትለዋን ቃል እንዳይሉ ሸይጣን ያዘናጋቻቸው በጣም ብዙ ሰዎች አሉ። ➷☑️  ሼኸ ፈውዛን አላህ ይጠብቀዉና እንዲህ ይላሉ። 🌐 ከሰዎች መካከል (لا إله إلا الله) የምትለዋን ቃል እንዳይሉ ሸይጣን ያዘናጋቻቸው በጣም ብዙ ሰዎች አሉ። ➷አንዳንዴ ቢሆን እንጂ ሁሌም አይላትም ➷በዚህች ውድ ቃል አላህን አያወሳበትም ➷የውመል ቂያማ ሚዛንን የምትደፋ ከመሆኗም ጋር አይደጋግማትም ➷ ይህች ቃል ማለት በጣም ትልቅ የሆነች ንግግር ናት። ♦️ነገር ግን ትኩረት የሚሰጧት ➷በአዕምሯቸው ሚያስታውሷት፦ በምላሳቸው ያለማመዷት፦ የሚደጋግሟት  አላህ ኸይርን የወፈቃቸው በጣም ጥቂት የሆኑ አነስተኛ ሰዎች ብቻ ናቸው። 📚 تفسير كلمة التوحيد 👉ስለዚህ لا اله الا الله የምትለዋን ቃል ምላስህ ከማለት አይዘናጋ!! ◂ تفسير كلمة التوحيد 👉ስለዚህ لا اله الا الله የምትለዋን ቃል ምላስህ ከማለት አይዘናጋ!!

  • አዘጋጅና ፀሀፊ✍ ፦ ካሊድ (kalido ye umi) የዋሻው እግረኛ እንዴት ነው ሷሂቡ😍 ቁረይሾች ነብዩን ﷺ ለመግደል የመጨረሻ በዳይ ውሳኔ ላይ በደረሱበት ወቅት ጅብሪል የቁረይሾችን ሴራ በወህይ አሳወቃቸው። አላህ እንዲሰደዱ መፍቀዱንም አበሰራቸው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ በ14ኛው ዓመተ ነብይነት በወርሃ ሶፈር 27ኛው ሌሊት ማለትም ሴፕቴምበር 12/13_622 ቤታቸውን ለቀው ወደ ባልንጀራቸው አቡበክር ቤት ሄዱ። አቡበከር ከርሳቸው ዘንድ ለጉዞ ጓደኝነት ከማንም በላይ ታማኝ፣ ገንዘባቸውንም ለመሰዋት ዝግጁ ነበሩ። ከ አቡበክር ቤት በጓዳው በኩል በመውጣት ጎህ ሳይቀድ በፊት መካን በፍጥነት ለቀቁ። ቁረይሾች ለፍለጋ እንደሚሰማሩና መጀመሪያ የሚያስቡት ወደሰሜን አቅጣጫ የተዘረጋውን የመዲና ዋነኛ መንገድ መሆኑን ነቢዩ ﷺ በመረዳታቸው በስተደቡብ በኩል ወደ የመን የሚያደርሰውን መንገድ ይዘው ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ተጓዙ።በዚህ መንገድ 5 ማይሎች ያህል ተጉዘው "ሰውር" ከተባለው ተራራ ደረሱ። ትልቅና መንገዱም አስፈሪ፣ ድንጋያማና አስቸጋሪ ነው። በጉዞው ምክንያት የመልእክተኛው እግር ቆሰለ። ቁስላቸውን ለመደበቅ በእግራቸው ጫፍ ይጓዙ እንደነበር ይነገራል። ከጋራው ሲደርሱ አቡበክር ተሸከሟቸው። በከፍተኛ ድካምም ከተራራው ጫፍ ወዳለ ዋሻ አደረሷቸው። የዚህ ዋሻ ስም በታሪክ ጸሐፍት ዘንድ "ጋር ሰውር" (ሰውር ዋሻ) በመባል ይታወቃል። ከዋሻው አጠገብ ደርሰው ሊገቡ ሲሉ አቡበክር፦ "እኔ ከመግባቴ በፊት አይገቡም። አንዳች መጥፎ ነገር ቢኖር እንኳ እርስዎን ሳይሆን እኔን ይጉዳኝ።"በማለት ወደ ውስጥ ዘለቁ። ከጎኑ ሦስት ሽንቁሮች አዩ። ሽርጣቸውን በመቅደድ አንዱን ደፈኑት። ሁለቱን በእግሮቻቸው ደፈኗቸውና መልእክተኛውን "ይግቡ" አሏቸው። "የአላህ መልእክተኛ ﷺ ገቡና የአቡበክርን ጭን ተንተርሰው ጋደም አሉ። ወዲያውም እንቅልፍ አሸለባቸው። በዚህ መሀከል አቡበክርን እግራቸውን አንዳች ነገር ነደፋቸው። ነብዩ ﷺ ከእንቅልፍ እንዳይነቁ በመስጋት አልተንቀሳቀሱም ነበር። በስተመጨረሻም ከአይናቸው የሚወርደው እንባ ከነቢዩ ﷺ ፊት ላይ ሊያርፍ ቻለ። ነቢዩም፦ እንባው ቢያገኛቸው "አቡበክር ሆይ ምን አገኘህ?" በማለት ጠየቋቸው። "አንዳች ነገር ነደፈኝ፣ ወላጆቼ ለርስዎ መስዋእት ይሁኑ" አሉ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከተነደፉበት ቦታ ላይ ተፉላቸው። ሕመሙ ወዲያውኑ ለቀቃቸው። በዚህ ዋሻ ውስጥ ሦስት ሌሊቶችን ፣ማለትም ጁመዓ፣ ቅዳሜና እሁድ ሌሊት ፣አሳለፉ። አብደላህ ቢን አቡበክር ከነርሱ ጋር ያድር ነበር። አኢሻ እንዳሉት አብደላህ ብልህ ወጣት ነበር። ከነርሱ ጋር አድሮ ጎህ ከመቅደዱ በፊት ወደ መካ በመመለስ እዚያው ያደረ መስሎ ይተኛል። መካውያን የሚነጋገሯቸውን ጉዳዮች ሁሉ ይዞም መሸትሸት ሲል ወደነርሱ በመሄድ ያደርስላቸዋል። የአቡበክር አገልጋይ ዓሚር ቢን ፈሒራህ የሚታለቡ ፍየሎችን ምሽት ላይ ይወስድላቸዋል። እነርሱም በቂ ወተት ያገኛሉ። ጎህ ከመቅደዱ በፊትም ይዟቸው ይመለሳል። በነዚህ በሦስት ሌሊቶቹ ያለማቋረጥ ይህን ያደርግ ነበር። አሚር ፍየሎችን ይዞ አብደላህ ቢን አቡበክር እስከ መካ ድረስ በመከተል ኮቴውን ያጠፉለት ነበር። የአቡበክርና የነቢዩ መሰውር ያንገበገባቸው ቁረይሾች አስቸኳይ ስብሰባ በመቀመጥ ሁለቱን ለመያዝ የሚያስችላቸውን የትኛውንም መንገድ ለመጠቀም ወሰኑ። ወደ መካ የሚያደርሱ ጎዳናዎችን ሁሉ በጥብቅ የመሳሪያ ጥበቃ ስር አዋሉ። ሁለቱንም በሕይወት ወይም ገድሎ ወደ መካ ለሚያመጣ ማንኛውም ሰው ስለእያንዳንዳቸው መቶ ግመል ሽልማት ለመስጠት ቃል ገቡ። በዚህ ጊዜ ፈረሰኞች፣ እግረኞችና የኮቴ አዋቂዎች በፍለጋ ላይ ተሰማሩ። ጋራዎችን ፣ሸንተረሮችን ፣ሸለቆዎችንና ሜዳዎችን ሁሉ አሰሱ።ግና ድካማቸው ፍሬ አልያዘም። ያለ ውጤት ተመለሱ። ነገር ግን አሳዳጆች ከዋሻው በር ላይ መድረስ ችለው ነበር። ግና አላህ ፈቃዱን ፈጻሚ ነው። ቡኻሪ አነስን በመጥቀስ እንደዘገቡት አቡበክር እንዲህ ብለዋል፦ ከነቢዩ ﷺ ጋር ከዋሻው ውስጥ ነበርኩ። ራሴን ቀና ሳደርግ የሰዎችን እግሮች አየሁ። "የአላህ መልእክተኛ ሆይ፡ ከመካከላቸው አንዱ ወደ ታች ቢመለከት ያየናል።" አልኳቸው። "አቡበክር ሆይ ፣አይዞህ ፣ አላህ አብሮን አለ።" አሉ። በሌላ ዘገባም፦ "አቡበክር ሆይ ፡አላህ ሦስተኛ አብሯቸው ያለ ፡ሁለት ሰዎችን ምን ክፋት ያገኛቸዋል ብለህ ታስባለህ?" ብለዋል። በዚህ ጊዜ አላህ ነቢዩን ﷺበተአምር አዳናቸው። አሳዳጆቻቸው ከርሳቸው ለመድረስ ጥቂት እርምጃዎች ሲቀሯቸው ትተዋቸው ተመለሱ። ፍለጋው ጋብ ሲል በቁረይሾች የገነፈለው የብቀላ ስሜታቸው ሲሰክን የአላህ መልእክተኛ  ﷺእና ባልንጀራቸው ወደ መዲና ለመጓዝ ተዘጋጁ።

  • የመጀመሪያው የሀበሻ ስደት ተጽእኖው እና እንግልቱ በአራተኛው የነብይነት አመት መጨረሻ አካባቢ በጥቂቱ ተጀመረ። እያደር ግን ከቀን ከቀን ከወር ወር እየበረታና እየጠነከረ ሄደ። ከአምስተኛው ዓመት መሐከል ላይ ግን ጣሪያ ነክቶ መካ ውስጥ መኖር ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ደረሱ ። ከዚህ መከራ ሊታደጋቸው የሚችል ብልሐት ማፈላለግ የግድ ሆነ በዚህ ተጨባጭ መሐል ስደትን የሚጠቁመው እና የአላህ ምድር ሰፊ እንደሆነች የሚያሳየው የቁርአን መልእክት ተላለፈ ። ፤ قُلْ يَا عِبَادِ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۗ وَأَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةٌ ۗ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُمْ بِغَيْرِ حِسَابٍ እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ በዚህች ዓለም ውስጥ መልካም ተግባራትን የፈፀሙ በመጭው አለም መልካም እድል ተዘጋጅቶላቸዋል ። የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚያገኙት ያለገደብ ነው» በል {{አል ዙመር 10} } የሐበሻው ንጉስ አስሐመተ ነጃሺ ከርሱ ዘንድ ሰው የማይበደልበት ፍትሃዊ ንጉስ መሆኑን የአላህ መልክተኛ ((ﷺ)) ያውቁ ነበርና ሙስሊሞች ወደ ሀበሻ በመሰደድ በሐይማኖታቸው ሰበብ ይደርስባቸው ከነበረው ስቃይና መከራ እንዲያመልጡ አዘዙ። በነብይነት አምስተኛው አመት ረጀብ ወር ላይ የመጀመሪያ የሶሐቦች ስደተኛ ቡድን ወደ ሐበሻ ተሰደደ። አስራ ሁለት ወንዶችንና አራት ሴቶችን የያዘ ነበር ። የቡድኑ መሪ ዑስማን ቢን አፋን ሲሆን የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)) ሴት ልጅ ሩቂያ አብራ ነበረች ። የአላህ መልዕክተኛ ((ﷺ)) እርሷንና ባሏን ኡስማንን በማስመልከት ሲናገሩ እናንተ ከኢብራሂምና ከሉጥ በኃላ ለአላህ ብሎ በመሰደድ የመጀመሪያው ቤት ናችሁ። (ዛዱል ሚአድ 1/24) ስደተኞች ከመካ የወጡት ቁረይሾች እንዳያገኙዋቸው ጨለማን ተገን አድርገው ነበር ከዚያም ወደ ሸእባህ ወደብ አቀኑ አላህ ሁለት የንግድ መርከቦችን አዘጋጀላቸው በነርሱ አማካኝነት ወደ ሀበሻ ቀዘፉ ቁረይሾች መሰደዳቸውን ሲያውቁ ዱካቸውን ተከተሏቸው ግና ከባህር ዳርቻ ሲደርሱ ሄደው አገኟቸው ሙስሊሞች ሀበሻ ውስጥ ጥሩ አቀባበል ተደረገላቸው።

  • ነቢያት በጌታቸው ያላቸው መተማመን ~ 1⃣- ኑሕ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی لَغَفُورࣱ رَّحِیمࣱ} {ጌታዬ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው።} [ሁድ፡ 41] 2⃣- ሁድ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی عَلَىٰ كُلِّ شَیۡءٍ حَفِیظࣱ} {ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ጠባቂ ነው።} [ሁድ፡ 57] 3⃣- ሷሊሕ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی قَرِیبࣱ مُّجِیبࣱ} {ጌታዬ ቅርብ (ልመናን) ተቀባይ ነው።} [ሁድ፡ 61] 4⃣- ኢብራሂም ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی لَسَمِیعُ ٱلدُّعَاۤءِ} {ጌታዬ በእርግጥ ልመናን ሰሚ ነው።} [ኢብራሂም፡ 39] 5⃣- ሹዐይብ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی رَحِیمࣱ وَدُودࣱ} {ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነው።} [ሁድ፡ 90] 6⃣- ዩሱፍ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی لَطِیفࣱ لِّمَا یَشَاۤءُۚ} {ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው።} [ዩሱፍ፡ 100] 7⃣- ሙሳ ﷺ :- {إِنَّ مَعِیَ رَبِّی سَیَهۡدِینِ} {ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል።} [ሹዐራእ፡ 62] 8⃣- ሱለይማን ﷺ :- {فَإِنَّ رَبِّی غَنِیࣱّ كَرِیمࣱ} {ጌታዬ ተብቃቂ ቸር ነው።} [ነምል፡ 40] 📚 ምንጭ፦ [ፈራኢድ ወፈዋኢድ ሚነል ቁርኣኒል ከሪም]

  • አቡ ሰዒድ አል ኹድሪይ እንዳስተላለፉት ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፦ "ደጃል ሲመጣ ከአማኞች መካከል አንድ ሰው እርሱ ወዳለበት ይሔዳል። የደጃል ወታደሮችም ያገኙታል። ወደየት እየሔድክ ነው?" ሲሉም ይጠይቁታል። ''አዲስ ወደተነሳው ሰው እየሔድኩ ነው" ይላቸዋል። "በጌታችን አታምንምን?" ይሉታል። "ስለጌታችን ድብቅ ነገር የለም" ይላል። "ግደሉት" ይላሉ። ከፊሎችም ለከፊሎቹ፦ "ጌታችሁ ያለርሱ ፈቃድ ማንንም እንዳትገድሉ አልከለከላችሁምን?" ይሏቸዋል። አማኙን ሰው ወደ ደጃል ይወስዱታል። አማኙ ሰው ደጃልን ሲያይ፦ "ሰዎች ሆይ! ይህ የአላህ መልዕክተኛ የነገሩን ደጃል ነው" ይላል። "ደጃልም ያዙትና ፈንክቱት" በማለት ያዝዛል። ጀርባውና ሆዱ ይደበደባል። ደጃልም፦ "በኔ አታምንምን?" ሲል ይጠይቀዋል። "አንተ አስመሳይ መሲሕ ነህ" ሲል ሰውየው ይመልሳል። በመጋዝ እንዲሰነጠቅ ያዝዛል። በእግሮቹ መካከል ከሁለት ይሰነጥቀዋል። ደጃል በሁለቱ ክፋይ አካሎች መካከል ይሔድና "ቁም" ሲለው ሰውየው ቀጥ ይላል። "አሁንስ በኔ ታምናለህን?" ሲል ይጠይቀዋል። እንዲያውም ደጃል መሆንህን የበለጠ አወቅኩ ይለዋል። "ሰዎች ሆይ! ከኔ በኋላ በማንም ሰው ላይ ይህን ድርጊት አይፈጽምም" ይላል። ደጃል ሊያርደው ይይዘዋል። አላህም በአንገቱ ዙሪያ የነሐስ መከላከያ ያደርግለታል። እናም ሊያርደው አይችልም። እግርና እጁን ይይዝና ይወረውረዋል። ሰዎች እሳት ውስጥ እንደጣለው አድርገው ያስባሉ። ግና ያረፈው ጀነት ውስጥ ነው።   የአላህ መልዕክተኛ ቀጥለውም እንዲህ አሉ፦ "ይህ ከዓለማት ጌታ ዘንድ ትልቁ መስዋእትነት ነው።" (ሙስሊም)   ቡኻሪ የዚህን ሐዲሥ ከፊል መልዕክት ያዘለ ዘገባ አስፍረዋል። Umma Life https://ummalife.com/MuslimEthio

  • በዚያን ጊዜ ሴቶች ከወንድ ወንድሞቻቸው ባላነሰ ሁኔታ የመስዋዕትነት ስሜት ተሞልተው በአላህ መንገድ ከልባቸው ይታገሉ ነበር። ከዚህ አኳያ ማንኛውም ዓይነት አገልግሎት የማይቻል አልነበረም። #ኡሙ_ዘይድ_ስትናገር፦      "በኸይር ዘመቻ እኔ አና ሌሎች አምስት ሴቶች ጦር ሜዳ ደረስን። መልዕክተኛው የኛን መምጣት ስለሰሙ እንድንመጣ ላኩብን። #በቁጣም "እዚህ እንድትመጡ ማን ፈቀደላችሁ? ማን ነው እዚህ ያመጣችሁ?" አሉን። እኛም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እኛ ቁስለኛ ማከም እንችላለን። አንዳንድ መድሀኒቶችንም ይዘናል። ለሙጃሂዲኖች ቀስት በማቀበል ፥ ሲታመሙ በመንከባከብ እና ምግብ በማቅረብ እንረዳቸዋለን።" አልናቸው። መልዕክተኛውም እንድንቆይ #ፈቀዱልን።" ብላለች።     የዚያን ጊዜ ሴቶች በአሁኑ ጊዜ አሉ ከሚባሉ ወንዶች እንኳን የበለጠ ልበ ሙሉ ነበሩ። እስቲ እነዚህ በራሳቸው አነሳሽነት ጦር ሜዳ ሄደው በተለያዩ ስራዎች ለመካፈል ጥያቄ ያቀረቡትን ሴቶች ወኔ እንመልከት።     #ኡሙ_ሰልማ የሁነይንን ዘመቻ ነፍሰ ጡር ሆና ተካፈለች። ጩቤም ይዛ ነበር። መልዕክተኛው(ሶ.ዐ.ወ) "ይህንን ጩቤ ለምንድነው የያዝሽው?" ብለው ሲጠይቋት መልሷ "አጠገቤ የሚደርስ #ከሃዲን ሆድ እተረትርበታለሁ።" የሚል ነበር።    #በአሁድ ጦርነትም የቆሰሉ ተዋጊዎችን በመንከባከብ ተሳትፋለች። #አነስ(ረ.ዐ) ይህንን ሁኔታ ሲያረጋግጥ፦ #ዓኢሻና_ኡሙ_ሰልማ(ረ.ዐ) በጦር ሜዳው ወዲያ ወዲህ እየተሯሯጡ ውሃ ለቁስለኞች ሲያመላልሱ አይቻለሁ" ብሏል።

  • ዐውፍ ኢብኑ ማሊክ ኢብኑ ጡፈይል እንዳስተላለፉት ዐብደላህ ኢብኑ ዙበይር፣ ዓኢሻ የሰጠችውን ሽያጭ ወይም ስጦታ በማስመልከት፦ "በአላህ እምላለሁ! ዓኢሻ ይህን ነገር ካላቆመች በገንዘቧ በማዘዝ መብቷ ላይ ገደብ እጥልባታለሁ" ማለቱ ለዓኢሻ ተነገራት። "ይህን ተናገረ?" አለች። "አዎ" አሏት። "በአላህ እምላለሁ! ኢብኑ ዙበይርን መቼም ቢሆን አላናግረውም" አለች። ኢብኑ ዙበይር የዓኢሻ ቅያሜ በረዘመ ጊዜ አማላጅ ላከባት። "በአላህ እምላለሁ! አማላጅ አልቀበልም። ስለቴንም አላፈርስም።" አለች።   ኢብኑ ዙበይር ቅያሜዋ ሲረዝምበት ኢብኑ ሚስወር ኢብኑን መኽረማህን እና ዐብዱረሕማን ኢብኑ አል አስወድ ኢብኑ ዐብዲ የጉሥን አናገራቸው። "ከዓኢሻ ዘንድ እንድትወስዱኝ በአላህ ስም እለምናችኋለሁ፤ ምክንያቱም ከኔ ጋር ግንኙነት ማቋረጥ አግባብ አይደለም" አላቸው። ሚስወርና ዐብዱረሕማን ወደ ዓኢሻ ዘንድ ሔዱ። "አሰላሙ ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ፣ እንግባ?" አሏት። "ግቡ፣ ሁላችሁም ግቡ" አለች። ኢብኑ ዙበይር አብሯቸው እንዳልለ አላወቀችም። ኢብኑ ዙበይር ግርዶውን አልፎ ገባና ዓኢሻን ያዛት። እያለቀሰም ይማጸናት ጀመር። ሚስወር እና ዐብዱረሕማንም ይለምኗት ጀመር። በመጨረሻም አናገረችው። ይቅርታም አደረገችለት። "ነቢዩ  የፈጸምሽውን ዓይነት የተራዘመ ቅያሜ ከልክለዋል። ሙስሊም ወንድሙን ከሦስት ቀናት በላይ ማኩረፍና መቀየም የለበትም" አሏት። በዓኢሻ ላይ ተግሳጽና ወቀሳ ባበዙ ጊዜ እርሷም ምክንያቷን እያለቀሰች መናገር ጀመረች። "ስለት ገባሁ፤ ስለት ደግሞ ጥብቅ ነገር ነው። እነርሱ ግን ተግሳጻቸውን አላቆሙም። ኢብኑ ዙበይርን ለማናገር ስለቷን ስላፈረሰች አርባ ባሪያዎቿን ነጻ ለቀቀች። ከዚያ በኋላም ቢሆን ስለቷን እያወሳች መቅለሚያዋ በእንባ እስኪርስ ድረስ ታለቅስ ነበር። (ቡኻሪ) ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች 1/ ወንድምን በዓለማዊ ጉዳይ መቀየም ያለ ነው። ከሦስት ቀናት በላይ ግን ክልክል ነው። ዓኢሻ ከዚያ በላይ ኢብኑ ዙበይርን ያኮረፈችው በርሷ ዕይታ ኢብኑ ዙበይር በራሷ ንብረት ላይ እገዳ መጣሉ ሸሪዓውን መጣስ ነው ብላ ስላሰበች ነው። 2/ በወንጀል ነገር ስለት መፈጸምና መሙላት አይፈቀድም። እንዲህ ዓይነት ስለት የገባና ያፈረሰ ለስለቱ መፍረስ ማካካሻ ባሪያ ነጻ መልቀቅ ወይም አሥር ድሆችን ማብላት ወይም ማልበስ ይኖርበታል። ይህን ካልቻለ ሦስት ቀን መጾም ይኖርበታል።

  • ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ፦ "ባልሽ ሲመጣ ሰላምታ አቅርቢለት፡፡ የቤቱን በር የበለጠ እንዲያጸናም ንገሪው" አሏት፡፡ ኢስማዒል ሲመጣ፦ "የመጣ ሰው ነበረን?" ሲል ጠየቃት፡፡ 'አዎን፥ አንድ ያማረ ቁመና ያላቸው አዛውንት ወደኛ መጥተው ነበር' በማለት አዛውንቱን አወደሰች፡፡ 'ስላንተ ጠየቁኝ። ነገርኳቸው' ኑሯችን እንደት እንደሆነም ጠየቁኝ። በመልካም ሁኔታ ውስጥ መሆናችንን ነገርኳቸው'  ስትልም አከለች፡፡ 'ያዘዘሽ ነገር አለን? አላት፡፡ 'አዎን፥ ሰላምታ እንዳደርስህ ነግረውኛል። የቤትህን በር እንድታጸናም አዘውሃል ' አለች፡፡ 'አባቴ ነው። የቤቱ በር አንቺ ነሽ። እንድይዝሽ (እንዳልፈታሽ) ነው ያዘዘኝ ' አለ። ከዚያ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ቆዩና ከነርሱ ዘንድ መጡ። ኢስማዒል ከዘምዘም ውሃ አጠገብ ካለች አንዲት ዛፍ ሥር ሆኖ ቀስት እያበጃጀ ነበር። ሲያያቸው ተነሳና አባት ለልጁ ልጅም ለአባቱ የሚያደርገውን ዓይነት አቀባበል አንደኛው ለሌላኛው  አደረጉ። "ኢስማዒል ሆይ! አላህ አንድ ነገር አዞኛል" አሉት፡፡ "አምላክህ ያዘዘህን ነገር ፈጽም" አላቸው። 'ታግዘኛለህ ' አሉት፡፡ 'አግዝሃለሁ' አላቸው። 'እዚያ ቦታ ላይ ቤተ አምልኮ እንዳንጽ አላህ አዞኛል' አሉትና በዙሪያቸው ካለው መሬት ይበልጥ ከፍ ወዳለው አመለከቱ። ከዚያ ቦታ ላይም የቤቱን መሠረት ጣሉ። ኢስማዒል ድንጋይ ያመጣል። ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ያንጻሉ። ግንቡ ከፍ ሲል ይህንን (ጥቁሩን) ድንጋይ አስቀመጡና ከርሱ ላይ ሆነው ማነጻቸውን ቀጠሉ። ኢስማዒል (ዐ.ሰ) ድንጋይ ያቃብሉዋቸው ነበር። ሁለቱም ይህንን ሲያደርጉ፦ "ጌትችን ሆይ! ተቀበለን፤ አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና" እያሉ ነበር።   በሌላ ዘገባ እንደተመለከተው፦ "ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የኢስማዒልን እናት ይዘው ወጡ። ውሃ የያዘ ስልቻም ይዘዋል። የኢስማዒል እናት ከስልቻው ትጠጣ ነበር። ወተቱም ለልጇ ይፈስላት ነበር። መካ ሲደርሱ ከዛፍ ሥር አስቀመጧቸው። ከዚያም ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመለሱ። የኢስማዒል እናትም ተከትላ ከኋላቸው ጠራቻቸው፦ 'ኢብራሂም ሆይ! ለማን ትተህን ትሄዳለህ?' አለቻቸው። 'ለአላህ' አሏት፡፡ "ከሆነስ ተስማምቻለሁ' አለችና ተመለሰች፡፡ ከስልቻዋ ውሃ ትጠጣ ጀመር። ወተቷም ለልጇ ይፈስለታል። ውሃውም ሲያልቅባት አንዳች ሰው አገኝ እንደሆን ብላ በማሰብ ሄደች፡፡ ወደ ሶፋ ላይ ወጣች፡፡ አንድ ሰው ታገኝ እንደሆነ በማሰብ ዙሪያውን አየች፡፡ ማንም አላየችም። ከሸለቆው ስትደርስ እየሮጠች ወደ መርዋ ወጣች፡፡ ይህንንም አንድዙር ፈፀመች፡፡  ሕፃኑ የሆነውን ልይ በማለትም ወደርሱ ሄደችና ተመለከተችው። በነበረበት ሁኔታ ውስጥ ነበር። የሞት ትንፋሽ የሚተነፍስ ይመስል ነበር። ነፍሷ ልትረጋጋ አልቻለችም። ምናልባትም ሰው አገኝ እንደሁ በማለት ተመልሳ ሄደች፡፡ ሶፋ ላይ ወጣችና ተመለከተች፡፡ አንድም ሰው አላየችም። ሰባት ጊዜ ያህል ይህንን ፈፀመች፡፡ ልጁን ልሂድና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ልየው በማለትም አስባ እያለ አንድ ድምጽ ሰማች፡፡ 'መልካም ነገር ካለህ አሁኑ አድርገው' አለች፡፡ ጂብሪል ነበር። በተረከዙ መሬቱን ወጋው። ውሃ መነጨ። የኢስማዒል እናት ተደነቀች፡፡ ውሃውን ታፍስም ጀመር፣ በማለት ቀሪውን የሐዲሡን ክፍል አውስተዋል። (ቡኻሪ)   ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች 1/ የኢብራሂምና የኢስማዒል (ዐ.ሰ) ታሪክ ለተውሒድ የተደረገ ትግል፣ ለአላህ የታዛዥነትና የፍጹም ተገዥነት፣ የተስፋና የእምነት ሕይወት ተምሳሌትና ታሪክ ነው። 2/ የኢብራሂም (ዐ.ሰ) ሚስት ስሟ ሀጀር (ሀገር) ሲሆን የግብፁ ንጉሥ ለኢብራሂም (ዐ.ሰ) ባለቤት ለሳራ በአገልጋይነት ሰጣት፡፡ ኢብራሂምም (ዐ.ሰ) እርሷን አግብተው ኢስማዒልን ወለዱ። 3/ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ለኢስላም ሲሉ ከሀገራቸው ውስጥ ብዙ ስቃይ አሳልፈዋል። ከእሳት ላይ ተወርውረዋል። በመጨረሻም ሀገር ጥለው በመሰደድ መካ ውስጥ ቤተሰቦቻቸውን አስቀምጧል። 4/ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ልጅ ያገኙት በዕድሜያቸው መጨረሻ ላይ ነው። ተስፋ ሳይቆርጡ በዚያ ዕድሜያቸው አላህን መጠየቃቸው ሙእሚን ያለውን የተስፋ ስሜት ያሳያል። 5/ ሀጀር ውሃ ፍለጋ ከሶፋና መርዋ መሀል ሰባት ጊዜ ከሮጠች በኋላ ነበር አላህ ውሃን ያፈለቀላት፡፡ ይህ ድርጊቷ አንዳች ደግ ነገር ለማግኘት ተገቢውን ጥረት ማድረግ የግድ እንደሆነ ያስተምራል። 6/ ሀጀር ባሏ የአላህን ትዕዛዝ ሲፈፅም አጋዥ የምትሆን ሚስት ተምሳሌት ናት፡፡ "እርሱን ወድጄ ተቀብያለሁ" በማለት የሰጠችው መልስ ይህን ስብእናዋን ያጎላል። 7/ ነቢያት ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ለአላህ ሲሉ መሰዋታቸውን ከታሪካቸው እንማራለን። 8/ የኢስማዒል (ዐ.ሰ) የመጀመሪያው ባለቤት ሕይወትን ስታማርር እናያለን። ይህ ባሕሪይዋ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) አላስደሰተም። እንዲፈታት መከሩት፡፡ ፈታት፡፡ ሕይወትን ማማረር አግባብ አይደለም። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለውን ነገር መቀበል፣ ማስታወስና ማመስገን ተገቢ ነው። 9/ ኢስማዒል (ዐ.ሰ) ሚስታቸውን እንዲፈቱ ሁለተኛዋን ደግሞ አጥብቀው እንዲይዙ ከአባታቸው የተላለፈላቸውን ምክር ወዲያው ተግባራዊ ሲያደርጉት አይተናል። ልጅ የወላጆቹን ትእዛዝ ምን ያህል በፍጥነትና በፍቅር መተግበር እንዳለበት የኢስማዒል ድርጊቶች ትምህርት ይሰጡናል። 10/ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የመጀመሪያውን ሚስቱን እንዲተው ኢስማዒልን የነገሩት ለሕይወት ያላትን አሉታዊ እይታ ስላልወደዱትና ይህን ጸለምተኛ ስሜት ወደ ልጃቸው እንዳታጋባበት ስለሠጉ ነው። 11/ ኢብራሂም እና ኢስማዒል (ዐ.ሰ) ከዕባን መነጻቸውን ይህ ታሪክ ይነግረናል። 12/ አባትና ልጅ ከዕባን እየገነቡ ያደረጉት ዱዓ የነርሱን ለአላህ መተናነስ ያመለክታል። በጎ ሥራ ሠሩ። ከዚያ በኋላ እንዲቀበላቸው ተማጸኑት፡፡ በምንሠራቸው በጎ ሥራዎች መኩራራት የለብንም። መሥራታችን አንድ ነገር ሆኖ አላህ እንዲቀበለንም ዱዓ ያስፈልጋል። Umma Life https://ummalife.com/MuslimEthio ቴሌግራም/ telegram/  https://t.me/ethiomuslim_1

  • ኢብኑ ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ "ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የኢስማዒልን እናትና ልጇን (ወደ መካ ምድር) አመጣቸው። ልጇ ጡት በሚጠባበት ዕድሜ ላይ ነበር። ከአላህ ቤት ዘንድ ከአንዲት ዛፍ አጠገብ ከመስጊዱ የላይኛው ገጽታ በኩል ከዘምዘም ምንጭ በላይ አስቀመጧት፡፡ ያን ጊዜ መካ ውስጥ አንድም ሰው አልነበረም። ውሃም አልነበረበትም። ከዚያም ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ተመልሰው ሄዱ። የኢስማዒል እናት እየተከተለች፦ "ኢብራሂም ሆይ! አጫዋችም ሆነ ምንም ነገር በሌለበት ሸለቆ ውስጥ ብቻችንን ትተህን የት ነው የምትሄደው?" አለቻቸው። ደጋግማ ይህንኑ ጠየቀቻቸው። ወደርሷ አልዞሩም። 'ይህን እንድታደርግ ያዘዘህ አላህ ነውን?' አለች፡፡ ''አዎን'' አሏት፡፡ ''እርሱ ካዘዘህ እንዲሁ አይተወንም (ለክፉ አይሰጠንም)'' አለችና ተመለሰች፡፡ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ጉዟቸውን ቀጠሉ። ማንም ሊያያቸው ከማይችልበት በተራራ መሐል ካለ መንገድ ላይ ሲደርሱ፥ ፊታቸውን በማዞርና እጃቸውን ወደ ላይ በማንሳት የሚከተለውን ዱዓ አደረጉ፦   "ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት (በካዕባ) አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ፤ ጌታችን ሆይ! ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ (አስቀመጥኳቸው)፤ ከሰዎችም ልቦችን ወደነሱ የሚናፍቁ አድርግ፤ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው። (ኢብራሂም፡ 37)   የኢስማዒል እናት ኢስማዒልን ታጠባ ጀመር። ዕቃው ውስጥ ከቀራት ውሃም ለርሷም ለኢስማዒልም ታጠጣ ጀመር። ዕቃዋ ውስጥ ያለው ውሃ ሲያልቅ እርሷም ልጇም ተጠሙ። ልጇ (ጥም ጠንቶበት) ሲወራጭ አየችው። የግዷን ውሃ ፍለጋ ሄደች፡፡ በምድር ካሉ ተራሮች መሐል ለርሷ ቅርብ 'ሶፋ' የተባለው ተራራ ነበር። ከርሱ ላይ ወጣችና ምናልባትም አንድ ሰው አይ እንደሁ በማለት ወደ ሸለቆው ተመለከተች፡፡ አንድም ሰው አላየችም። ከ'ሶፋ' ወረደች፡፡ ከሸለቆው ስትደርስ የቀሚሷን አንድ ጎን ከፍ አደረገችና አቅሟን ሁሉ በመጠቀም ትሮጥ ጀመር። ሸለቆውን አልፋ 'መርዋ' ከተባለው ቦታ ደረሰች፡፡ እርሱ ላይም ቆማ አንድ ሰው አይ እንደሁ በማለት ወደ ሸለቆው ተመለከተች፡፡ አንድም ሰው አላየችም። ይህንኑ ሰባት ጊዜ ደጋግማ ፈፀመች፡፡"   ኢብኑ ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዳሉት ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፦ "ለዚህም ነው ሰዎች በሐጅ ወቅት በሶፋና በመርዋ መካከል የሚሮጡት በማለት ተናግረዋል።   "መርዋ' ላይ ለመጨረሻ ጊዜ በሮጠች ጊዜ ድምጽ ሰማች፡፡ የበለጠ ትኩረት ሰጥታ ስታዳምጥ ድምጹ ዳግም ተሰማት፡፡ 'ድምጽህን አሰምተሃል። ውሃ ካለህ ስጠኝ አለች፡፡ ወዲያውም ዘምዘም ከተባለው ቦታ ላይ መልኣክ ቆሞ ተመለከተች፡፡ በተረከዙ ወይም በክንፉ መሬቱን ይጭራል። ወዲያውም ውሃ ፈለቀ። በእጇ ማቆሪያ አበጀችለት፡፡ ውሃውንም እየዘገነች ከዕቃዋ ውስጥ ትከት ጀመር። በዘገነችው ቁጥር ብዛቱ ይጨምራል።   በሌላ ዘገባ እንደተወሳውም፦ "የዘገነችውን ያህል መጠን ይጨምራል።"   ኢብኑ ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፦ "የኢስማዒልን እናት አላህ ይዘንላት፡፡ ውሃውን ባትዘግነው ኖሮ ዘምዘም ትልቅ ወንዝ ይሆን ነበር።" ብለዋል። "ለራሷ ጠጣች፡፡ ልጇንም አጠጣች፡፡ መልአኩም፦ "አይዟችሁ! ችግር ይገጥመናል ብላችሁ አትፍሩ። እዚህ ቦታ ላይ ልጅና አባቱ የሚያንጹት የአላህ ቤት አለ። አላህ ቤተሰቦቹን ከንቱ አይተውም" አላት፡፡   ቤቱ ከጉብታ ላይ ነበር። ጎርፍ ይመጣና በቀኛና በግራ በኩል ይሸረሽረዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የጁርሁም ጎሣ ሰዎች በ"ከዳእ" መንገድ በኩል መጡ። (ጁርሁም የዐረብ ጎሣ ነው) ከመካ በታች በኩልም ሰፈሩ። በውሃ ዙሪያ የምትሽከረከር ወፍም ተመለከቱ። 'ይህ ወፍ የሚዞረው ውሃ ባለበት አካባቢ ነው። በዚህ ሸለቆ ውስጥ ደግሞ ውሃ የለም።' አሉ። ጉዳዩን ያጣሩ ዘንድ አንድ ወይም ሁለት ሰዎችን ላኩ። ሰዎች ሲሄዱ ውሃ አገኙ። ተመለሱና ነገሯቸው። ወደ ውሃው ሄዱ። የኢስማዒል እናት እና ልጇ ኢስማዒል ከውሃው አጠገብ ተቀምጧል። ካንቺ ዘንድ እንድንቀመጥ ትፈቅጃለሽን?' አሏት፡፡ 'አዎ፥ ውሃውን ግን መጠቀም አትችሉም ' አለች፡፡ 'ይሁን' በማለት ተስማሙ።"     ኢብኑ ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዳሉት ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚከተለውን አክለዋል፦ "የኢስማዒል እናት ሁኔታው አስደሰታት፡፡ ከሰዎች ጋር መሆንን ትወድ ነበር። ከዚያ ቦታ ላይ ሰፈሩ። ወደ ቤተሰቦቻቸውም መልክት ላኩ። እነርሱም ከነርሱ ጋር ሰፈሩ። በርካታ ቤተሰቦችም ተፈጠሩ። ይህ ልጅ አደገ። ዐረበኛን ከነርሱ ተማረ። ሲያድግ ከሁሉም ዘንድ ተወዳጅ ልጅ ሆነ። ከመሐላቸው አንዲት ሴት ልጅ አጋቡት፡፡ የኢስማዒል እናት ሞተች፡፡   ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ትተዋቸው የሄዱ ቤተሰቦቻቸውን ፍለጋ ኢስማዒል ካገባ በኋላ መጡ። እንደደረሱ ኢስማዒልን አጡት፡፡ ሚስቱን የት እንደሄደ ጠየቋት፡፡ 'ለኛ ምግብ ፍለጋ (ወይም አደን) ወጥቷል።' አለቻቸው። ስለ አኗኗራቸውም ጠየቋት። 'ችግር ውስጥ ነን ' በማለት ስሞታ ነገረቻቸው። 'ባልሽ ሲመጣ ሰላምታ አቅርቢለት፡፡ የቤቱን በርም እንዲቀይር ንገሪው ' አሏት፡፡ ኢስማዒል ሲመጣ ያልተለመደ ነገር የተከሰተ ዓይነት ስሜት ተሰማው። 'የመጣ ሰው ነበርን?' ሲል ሚስቱን ጠየቃት፡፡ 'አዎ፥ እንዲህ ያለ አዛውንት መጥተው ነበር። ስላንተ ጠየቁኝ፥ ችግር ውስጥ መሆናችንን ነገርኳቸው ' አለች፡፡ 'አንዳች ያዘዙሽ ነገር አለን?' አላት፡፡ 'አዎን፥ ሰላምታ እንዳደርስልህ ነግረውኛል። የቤትህን በርም እንድትቀይር አዘውሃል' አለች፡፡ 'አባቴ ነው፣ እንድፈታሽ ነው ያዘዘኝ። ወደ ቤተሰቦችሽ ሂጂ' አላት፡፡ ፈታትም። ሌላ ሴትም አገባ። ኢብራሂም (ዐ.ሰ) አላህ የፈቀደውን ያህል ጊዜ ቆይተው ተመልሰው መጡ። ኢስማዒልን አላገኙትም። ከሚስቱ ዘንድ ገቡና ስለርሱ ጠየቋት፡፡ 'ምግብ ልፈልግልን ወጥቷል' አለች፡፡ 'እንዴት ናችሁ? ' አሏት፡፡ ስለኑሮዋቸው ጠየቋት፡፡ 'በጥሩ ሁኔታ ውስጥ ነን ' አለች፡፡ ለአላህም ምስጋና አቀረበች፡፡ 'ምግባችሁ ምንድን ነው?' አሏት፡፡ 'ሥጋ' አለች፡፡ 'የምትጠጡትስ?' አሏት፡፡ 'ውሃ' አለች፡፡ እሳቸውም፦ "አላህ ሆይ! በሥጋና በውሃ ውስጥ በረከትን አድርግላቸው ' አሉ ዱዓ አደረጉ።"          ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፥ ያኔ አዝርዕት አልነበራቸውም። ቢኖራቸው ኖሮ አላህ እንዲባርክላቸው ዱዓ ያደርጉላቸው ነበር። እነዚህ ሁለቱ ሥጋና ውሃ መካ ውስጥ ላሉ ሰዎች ካልሆነ በቀር ሌሎች አዘውትረው ሲመገቧቸው አይስማሙም።   በሌላ ዘገባ እንደተወሳው፥ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) መጡና፦ "ኢስማዒል የታለ? አሉ። 'አደን ሄዷል' አለች፡፡ 'አረፍ ይበሉና ይብሉ፥ ይጠጡ' አለች፡፡ ምግባችሁና መጠጣችሁ ምንድን ነው?' አሏት፡፡ 'ምግባችን ሥጋ ነው፤ መጠጣችን ውሃ ነው ' አለች፡፡ 'አላህ ሆይ! ምግብና መጠጣቸውን ባርክላቸው።' ሲሉ ዱዓ አደረጉ።" አበልቃሲም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "የኢብራሂም (ዐ.ሰ) ዱዓ በረከት" ሲሉ ተደምጧል።

  • የሱብሒ ሶላት ሱንና ትልቅ ትኩረት ከተሠጣቸው ሱንናዎች መካከል አንዷ ናት፡፡ «በዚህች ዓለም እና በዉስጧ ካሉት ነገሮች ሁሉ ብልጫ አላት!» ብለዋል ረሱላችን።በጉዞም ሆነ በአገር እያሉ ይህቺን ሱንና አልተዉም፡፡ የምትሰገደው ሁለት ረከዐህ ነው፡፡ ረከዓዎቹ ቀለል ያሉ ናቸው፡፡ በመጀመርያው ረከዐህ «ቁል ያ አዩሀል ካፊሩን»ን በሁለተኛው «ቁል ሁወላሁ አሐድ»ን ማንበብ ይወደዳል። ከሱንናው በኋላ በቀኝ ጎን ጥቂት ጋደም ማለት ሌላው የረሳነው ሱንና ነው፡፡ ከግዴታ ሶላቱ በኋላ ተቀምጦ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ አላህን ማውሳት መቻል እንዴት ያለ መታደል ነው በረቢ!፡፡ የሱብሒን በረካ ለመቋደስ በግዜ መተኛት! = t.me/AbuSufiyan_Albenan