✨KB Orthodox✝️
Статистикаኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶችና መዝሙሮችን ያገኛሉ✝️ ሌላኛውን ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 @KB_Creatives
- Последний пост
- 5 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 75
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 109
- 1/48двое суток
- 124
- 1/72трое суток
- 134
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
መናገር ባለብህ ሰአት ብቻ ተናገር ... "አስተውል ከአይሁድ ጫጫታ ይልቅ የክርስቶስ ዝምታ ነው ጲላጦስን ያስጨነቀው" አስተዋይ ግን ዝም ይላል(ምሳሌ 11:12) ✝@KB_ORTHODOX✨
‛‛ለሌሎች ይቅርታን ስትሰጥ፣ ለራስህ ሰላምን ትሰጣለህ።’’ ✍🏻አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝@KB_ORTHODOX✨
✨እግዚአብሔርን ፈርታችሁ..... ሥራ ስትሠሩ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ሥሩ : ስትናገሩም እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ተናገሩ :ስታገቡም እግዚአብሔርን ፈርታችሁ አግቡ : ስትነግዱ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ነግዱ : መንገድ ስትሔዱም እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ሂዱ : ስታስተዳድሩም እግዚአብሔርን ፈርታችሁ አስተዳድሩ ። 🗣አባ ገብረ ኪዳን ✝@KB_ORTHODOX✨
‛‛እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለሁኝ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አንተ አድነኝ።’’ ✍️አባ እንጦንስ ✝@KB_ORTHODOX✨
‛‛እግዚአብሔር ድካምህን እንደሚያውቅና እስካሁን ድረስ እንደሚወድህ እርግጠኛ ሁን! በኃጢአት ውስጥ ብትሆንም እግዚአብሔር ሊያድንህ፣ ወደ እርሱ ሊያቀርብህና ወደ ቀደመ ደረጃህ ሊመልስህ እንደሚሠራ እመን።’’ ✍️አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ✝@KB_ORTHODOX✨
በወዳጅነት ብዙ አመታትን የዘለቁ ወዳጆችን ካየህ ስንት ጊዜ ይቅር ተባብለው ይሆን እዚህ የደረሱት ማለትን አትዘንጋ። ✍️ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ✝@KB_ORTHODOX✨
"ሰው ቢጠላችሁ፣ ሰው ቢሸሻችሁ፣ ስታጡ ጓደኛም ቢከዳችሁ፣ ምንም ብትሆኑ ፤ ማለዳም ተነስታችሁ ገንዘብ ብታጡ፣ ስራም ብታጡ ቢቸግራችሁ ፣ ዳኛም ባይፈርድላችሁ፤ ዝም ብላችሁ አንድ ቃል በሉ ... 'እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው' ። ✝@KB_ORTHODOX✨
"ምላስህን መግራት የጀመርክ ቀን፣ የነፍስህን ደጅ መቆለፍ ጀምረሃል። ከመናገርህ በፊት ቃላትህን በፍቅርና በእውነት ሚዛን ላይ መዝን። በቁጣ የተነገረ ቃል የጥፋት ዘር ነው፤ በትዕግሥት የተነገረ ቃል ግን የፈውስ ሥር ነው።" ምንጭ፦ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ "የመጀመሪያውና ሁለተኛው የቆሮንቶስ መልእክት ትርጓሜ" ✝@KB_ORTHODOX✨
‛‛ከመናደድህ በፊት ቁጣ ምን ያህል ኃጢአት እንደሆነ አስብ።’’ ✍️አባ ዶሮቴዎስ ✝@KB_ORTHODOX✨
"ዓይኖችህን በማዕበሉ ላይ ሳይሆን ነፋስን በሚያዝዘው አምላክ ላይ አኑራቸው። እምነት ማለት ፍርሃት አለመኖር አይደለም፤ በፍርሃትህ መካከል የእግዚአብሔር መገኘት ነው እንጂ።" "Do not let your eyes be fixed on the storm, but on the One who commands the wind. Faith is not the absence of fear, but the presence of God in the midst of your fear." ምንጭ፦ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፣ "ስለ፣ ፈተናዎች" የተሰጠ ትምህርት (በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል የተሰጠ ስብከት፣ ካይሮ) ✝@KB_ORTHODOX✨
‛‛የዚህ ዓለም ኑሮ እንደ ሕልም ነው፤ በዚህ ሕይወት የሚከናወኑት ነገሮች ሁሉ ጥላ ናቸው።’’ ✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ✝@KB_ORTHODOX✨
‛‛የዋህ ልብ የእግዚአብሔር ማረፊያ ነው።’’ ✍️ቅዱስ ኔክታሪዮስ ዘኤጂና ✝@KB_ORTHODOX✨
‛‛እውነት በራሷ ትቆማለች፤ ምንም እንኳ የሚረዷት ባይኖሩ አሸናፊ ናት።’’ ✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ✝@KB_ORTHODOX✨
✝ እንኳን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት መሸጋገሪያ ለሆነችው ዕለት ሰኔ 25 በሰላም አደረሳችሁ ! ቅድስት ቤተ ክርስቲያ] ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በአራት ዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች ። እሊሕም ዘመናት መጸው [ጽጌ] ፣ ዘመነ ሐጋይ [በጋ] ፣ ዘመነ ጸደይ [በልግ] እና ዘመነ ክረምት ናቸው ። ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ከማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል ። በተለይ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሽሽታችሁ [ስደታችሁ] በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" ብሎናልና [ማቴ.፳፬፥፳] (24:20) አብዝተን ልንጸልይ ይገባናል ። በዘመነ ክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ የለበትምና ፍሬ ምግባር ሣናፈራ ሞት እንዳይመጣ ፤ አንድም ክረምት የዝናብና የጭቃ ጊዜ በመሆኑ እንኩዋንስ ለስደት ለኑሮም አይመችም ። አበው ስለ ዝናም ሲያስተምሩ ዝናም ወደ መሬት ሲወርድ አንድ ጊዜ ዠቅ ብሎ በሙላ አለመውረዱ መከራ በመጠን በአቅም ለመሰጠቱ ምሳሌ ነው ይሉናል ። ከሰኔ 25 - መስከረም 25 በሚቆየው ወርኃ ክረምት በልዩነት የመከራ ወቅት ምሳሌ ነውና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጸልይ :- "በዝንቱ ፡ ክረምት ፡ በመዋዕሊነ ፡ እንበለ ፡ ፍሬ ፡ እንዘ ፡ በቆጽል ፡ ኀሎነ ፡ ናስተበቁዐከ ፡ እግዚኦ ፡ ኢይኩን ፡ ጉያነ ።"... #ትርጉም [ ክረምት ፡ በተባለ ፡ በእኛ እድሜ ፡ ፍሬ ፡ ሳናፈራ ፡ በቅጠል ፡ /ያለ ፡ መልካም ፡ ሥራ/ ፡ ሳለን : አቤቱ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስደትን ፡ አታምጣብን ፡፡ ] ስለ ዝናም ጸልዩ ! ✝@KB_ORTHODOX✨
✝ የማኅበራዊ ሚዲያ ፈተና በአሁን ሰዓት የአዳም ዘር መብሉ ፣ መጠጡ ፣ ወሬውም ሆነ ሁለመናው ማኅበራዊ ሚዲያ እየሆነ መጥቷል። ፌስቡክ ፣ ኢንስተግራም ፣ ዩቱብ ፣ ቲክቶክ በቀላሉ ስለሚከፈቱ ከትንሽ እስከ ትልቁ ከፍቶ ይዝናናል ። ሰው ፎቶውን ፣ የበላውን የጠጣውን ፣ ያየውን ፣ የሰማውን ይለጥፋል ፣ ይሰድባል ፣ ያመሰግናል ፣ ይረግማል ይመርቃል። ከሁሉም መተግበሪያዎች ጀርባ ግን ምን እንዳለ የሚያውቁ ጥቂቶች ብቻ ይመስሉኛል። ማኅበራዊ ሚዲያ በአግባቡ ካልተያወ በነገው ትውልድ ላይ ትልቅ ሱስ የሚሆን እየሆነም ያለ ይመስለኛል ። የሰው ልጆችን አኗኗር በእጅጉ ይቀይራል ፣ ጤንነት ይቃወሳል ፣ አንገትና ጀርባ በልጅነት ይጎብጣል ፣ አይን ያለጊዜው ይደብዝዛል ፣ ነገ ላይ ቀጥ ብሎ መሄድ ተረስቶ ዛሬ "የእጅ መታጠብ ቀን" እንደ ሚባለው " ከቲክቶክ ነጻ ቀን" ተብሎ ቢከበር ደስ ይለኛል ። ሰው ከሰው ጋር ንግግር ቀንሶ ከግዑዝ ነገር ጋር ያወራል ማሰብ ማሰላሰል ያቆማል። የሰው የመመራመር አቅም በእጅጉ ይጎዳል። እውቀቱ ተሰብስቦና ተሸብቦ ከኢንተርኔት ብቻ ይሆናል መጽሐፍ ማገላበጥ ጌጥ ይሆናል። በጊዜው ወላጅ ራሱንና ልጁን ያርም ይዘጋጅ ካልሆነ ጣጣው ቀላል አይሆንም ለዛሬ አንድ ነገር ብቻ ልጠቁም። ቲክቶክም ሆነ ፌስቡክ የራሳቸው የሚሰሩበት ስልት (algorithm) አላቸው። ሰዎችን በጾታ ፣ በሀገር ፣ በእድሜ በመሳሰሉት ነገር ይከፍሏቸዋል። ለምሳሌ ቲክቶክ ባለቤቱ ቻይና ውስጥ ያለ ነው ይባላል ። ስለሆነም ታላላቅ የወጣት ስኬት ፣ የፈጠራ ክህሎት ፣ ስፓርታዊ ውድድር ፣ አስገራሚ የሳይንስ ግኝት ፣ የሒሳብ ውድድር ፣ ሥራ ፈጣሪነት ፣ ወጣቶች ለራሳቸው ስኬት ሲሰሩ የሚያሳይ ሲለጠፍ ቲክቶክ ወደ ከፈቱ የቻይና ወጣቶች ይሄዳል። እንድንደቅ (እንድንደነዘዝ) የምንፈለገው እኛ ደግሞ ጦርነት ፣ ግድያ ፣ ሥራ አጥነት ፣ የራቁት ዳንስ ፣ ሴትና ወንድ በአጸያፊ መልኩ ሲገናኙ ፣ ስድብ ፣ ሎተሪ ቆርጦ ስለወጣለት ሰው ፣ ፕራንክ ሲደራረጉ ፣ ሰዎች መጠጥ ቤት ተቀምጠው ፣ ባል ሚስትን ሲያታልል….. እንደ ጉድ ወደ እኛ ይከማቻል ይፈሳል ። አንድም የምናየው ተከታታይ ቪዲዮ የእኛን ማንነት እስከ ማሳወቅ ይደርሳል ። በዚህ የመጣ አይናችን እና ጭንቅላታችን ዞሮ እንተኛለን። ይህ አይነት ነገር ደጋግሞ የሚመጣብህ ከሆነ መጫወቻና ቁሻሻ መጣያ ሆነሃል ። ኒውክለር ሳይተኮስ አንተን መግደል ማለት ይሄ ነው ። አንተ የምታየውን ዝባዝንኬ የቻይና ወጣት አያይም ። የቻይና አሊጎሪዝምና የአሜሪካ አሊጎሪዝም ይለያያል ለአፍሪካ ደግሞ አስበው ። ስለሆነም ሰፊ ማሰላሰል ይፈልጋል ። ስልክ እያየን ስንሄድ ፣ ስንነዳ የምንጋጭ ብዙ ነን ። ይህችን ለጥቆማ የጻፍኳት ናት ፈተናው ግን ቀላል አይሆንም እናስብበት ለማለት ነው።
*<<በልቤ በር ቆመህ እያንኳኳህ የምትጠብቀኝ እኔ ማነኝ ?* ጌታ ሆይ የሚያስቆይ አመል ኖሮኝ ነው የጠበከኝ ? ምኔን አይተህ ነው የታገስከኝ ? የፈጠርከኝ እኔ ፣ ሁሉ ነገሬ ያንተ ሲሆን ሁሉን መስጠት ሲገባኝ ትንሿን ትኩረቴን ነሳሁህ ! የሰጠኸኝን ጉልበት ላንተ ማድረግ አቃተኝ ! የሰጠኸኝን ጊዜ እኔ ግን ትንሿን ለአንተ ማካፈል አልቻልኩም ! ታድያ ለምን ? የእውነት ለምን ብለህ እስካሁን ከደጄ ቆመሀል ? መሄጃ ሳይኖርህ እኮ አይደለም ከልቤ የቆምከው አንተ እኮ ታላቅ ነህ ታድያ እኔ ስር ምን ትሰራለህ ? *ፍቅር !* አዎ ከእኔ ጋር ከፍቅር ውጪ ምን አለህ ? ምግባር የለኝ ፣ እምነት የለኝ ፣ አንተን የሚፈልግ ልብ የለኝ ... ጌታ ሆይ እስክከፍትልህ አትጠብቅ በተዘጋ በር የገባህ አንተ በተቆለፈውም ልቤ ሳታስፈቅደኝ ግባ ! እኔ ለ እኔ መሆን አልቻልኩምና እኔነቴን ገዝተህ የአንተ አድርገኝ !
‛‛መውደቅ አዳማዊ ነው። ወድቆ አለመነሳት ግን ዲያቢሎሳዊ ነው።’’ ✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
‛‛ትዕቢት የኃጢአት ሁሉ ሥር ናት፤ ትህትና ደግሞ የጽድቅ ሁሉ መሠረት ናት።’ (✍️ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰላልዊ) ✝@KB_ORTHODOX✨
"ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን።" (ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ) ✝@KB_ORTHODOX✨
ሰሙነ ሕማማት 👉 ሐሙስ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ እግር ይባላል። በዚህም ምሳሌ ካህናት አባቶቻችን በእለተ ሐሙስ በእውቀት፣ በእድሜ፣ በክብር፣ በስልጣል ትልቅ ነኝ ሳይሉ ከዲያቆናት እስከ ምዕመናን ድረስ ዝቅ ብለው እግር በማጠብ ክርስቶስን በተግባር ይሰብካሉ። የምስጢር ቀን ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። ✝@KB_ORTHODOX✨