ካሪዝማ የትርጉም ፣ የፅህፈት እና የህግ ማማከር አገልግሎት
Статистикаካሪዝማ የትርጉም፣ የፅህፈት እና የህግ ማማከር አገልግሎት ላለፋት አመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ነው።
- Последний пост
- 7 мая
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በሰዎች የባንክ አካውንት ያስተላለፋትን ገንዘብ እንዲመለስሎ መጠየቅ ይችላሉ ??? 👉 በመርህ ደረጃ ሊከፍል የማይገባውን ገንዘብ ከከፈሉ ፣ ግለሰቡ ገንዘቡን እንዲመልስሎ መጠየቅ ይችላሉ .... የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 2164..... 👉 ይሁን እንጂ ገንዘቡን ያስተላለፉት የግለሰቡን ስም እና አካውንት ቁጥር በመፃፍ በባንክ ከሆነ ገንዘቡን አስበዉበት በራስዎ ፈቃድ እንዳልኩት የሚያስቆጥር በመሆኑ ገንዘቡ እንዲመለስሎት የመጠየቅ መብት አይኖሮትም ። ⚫️ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 26 ዕትሙ በሰ/መ/ቁ 175660 በሰጠው የህግ ትርጉም መሠረት ። 👉 ነገር ግን ገንዘቡን የግለሰቡን አካውንት እና ስም በመፃፍ በባንክ የላኩት በገንዘብ በተቀባዩ ተጭበርብረዉ ፣ ተገደው እና መሰል ድርጊት ተፈፅሞዎበት ከሆነ ይህንኑ በበቂ በማስረጃ ማስረዳት ከቻሉ ገንዘቡ እንዲመለስሎ የመጠየቅ ሙሉ መብት ይኖሮታል።.
በወንጀል ጉዳዮች ላይ በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል አይነቶችን በዝርዝር የሚያሳይ እና ጠቃሚ መረጃ የያዘ ነው። #በወንጀል_ጉዳዮች_ላይ_የእርቅ_አፈፃፀም_ሂደት_እና_አይነቶች በመርህ ደረጃ ወንጀል የመንግስትን እና የህዝብን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ክስ የሚመሰረተው በመንግስት ዐቃቤ ህግ አማካይነት ነው። ሆኖም አንዳንድ የወንጀል አይነቶች በግል ተበዳይ እና በከሳሽ መካከል በሚደረግ እርቅ እንዲያልቁ በህግ ተፈቅዶላቸዋል። ይህ አሰራር ጉዳዩ ወደ ረጅም የፍርድ ቤት ሂደት እንዳይገባ በመርዳት ለሁለቱም ወገኖች ጊዜን እና ወጪን ይቆጥባል። በተጨማሪም በማህበረሰቡ ውስጥ ሰላማዊ መፍትሄዎችን በማምጣት ማህበራዊ ትስስሮችን ያጠናክራል። #ለምን_በወንጀል_ጉዳዮች_ላይ_እርቅ_ይፈቀዳል? ✔️ #የወንጀሉ_ክብደት_አነስተኛ_ሲሆን: የእርቅ አፈፃፀም የሚፈቀደው በአንጻራዊነት ክብደታቸው ዝቅተኛ በሆኑ እና በግለሰቦች መካከል በሚፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ነው። እነዚህ ወንጀሎች በመንግስት ወይም በህዝብ ላይ ከባድ ጉዳት የማያስከትሉ በመሆኑ ጉዳዩ በግል ስምምነት እንዲያልቅ ይፈቀዳል። ✔️ #የግል_አቤቱታን_መሰረት_ሲያደርግ: አንዳንድ የወንጀል አይነቶች የሚመሰረቱት በተበዳዩ አካል የግል አቤቱታ ላይ ብቻ ነው። አቤቱታው ከተነሳ በኋላም ቢሆን ተበዳዩ እርቅ ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆነ ክሱ ሊቋረጥ ይችላል። #በእርቅ ማለቅየሚችሉበት የወንጀል አይነቶች ምሳሌዎች በ2004 ዓ.ም. በወጣው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ እና የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መመሪያ ቁጥር 22/2010 መሰረት፣ በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል አይነቶች በግልፅ ተደንግገዋል። ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው። #ቀላል_የአካል_ጉዳት: #ታስቦ_የሚፈጸም_ቀላል_የአካል_ጉዳት (አንቀጽ 556(1)): ይህ ወንጀል በቀላሉ ጉዳት ለማድረስ አስቦ የተፈፀመ ሲሆን፣ ጉዳቱ ብዙም ከባድ ካልሆነ በእርቅ ሊፈታ ይችላል። #በቸልተኝነት_የሚፈጸም_ቀላል_የአካል_ጉዳት (አንቀጽ 559(3)): በቸልተኝነት ወይም በጥንቃቄ ጉድለት የተፈጠረ የአካል ጉዳትም ከዚህ ውስጥ ይመደባል። #ከስነ-ምግባር_ጋር_የተያያዙ_ወንጀሎች: #የዛቻ_ወንጀል (አንቀጽ 580): የአንድን ሰው ሰላም እና ደህንነት በሚያናጋ መልኩ የሚፈፀም ማስፈራራት ወይም ዛቻ። #የስድብና_ማዋረድ (አንቀጽ 615) እና_የስም_ማጥፋት (አንቀጽ 618): እነዚህ ወንጀሎች የአንድን ሰው ክብር እና መልካም ስም የሚጎዱ ድርጊቶች ናቸው። #አመንዝራነት (አንቀጽ 652): ይህ ወንጀል የሚካሄደው የግል አቤቱታ ሲቀርብ ብቻ ነው። #ንብረት-ነክ_ወንጀሎች: በቤተዘመድ_ንብረት_ላይ_የተፈጸሙ_ወንጀሎች (አንቀጽ 664): በቤተሰብ አባላት መካከል የሚፈጠሩ የንብረት ጉዳዮች። #በሰው_ንብረት_ላይ_ጉዳት_ማድረስ (አንቀጽ 689): የሌላን ሰው ንብረት ማበላሸት። #አግኝቶ_መደበቅ (አንቀጽ 679) #እና_በሌላ_ሰው_ሀብት_ያለአግባብ_መጠቀም (አንቀጽ 678): እነዚህ ወንጀሎች የተፈቀደውን የሀብት አጠቃቀም ገደብ ያለፈ ድርጊቶችን ያመለክታሉ። የእርቅ_አፈፃፀም_ሂደት በወንጀል ጉዳዮች ላይ እርቅ የሚፈፀምበት ሂደት #በጠቅላይ_ዐቃቤ_ህግ_መመሪያ_ቁጥር 22/2010 በዝርዝር ተቀምጧል። ይህ መመሪያ ጉዳዩ እንዴት እንደሚመራ፣ ተበዳዩ ምን መብቶች እንዳሉት እና እርቅ ሲደረግ ምን አይነት ጥንቃቄዎች መወሰድ እንዳለባቸው ይገልጻል። ዋና ዋናዎቹ የእርቅ ሂደት ደረጃዎች የሚከተሉት ናቸው። #የእርቅ_ጥያቄ_መቅረብ: እርቅ ማድረግ የሚፈልገው ወገን (ተበዳይ ወይም ተከሳሽ) ለዐቃቤ ህግ ወይም ለፍርድ ቤት የጽሁፍ ጥያቄ ያቀርባል። #የጉዳዩ_መገምገም: ዐቃቤ ህግ የቀረበለትን ጥያቄ ይመረምራል። ጉዳዩ በእርቅ ሊያልፍ የሚችል ከሆነ እና ከህዝብ ጥቅም ጋር የማይጋጭ ከሆነ፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ይሸጋገራል። #የእርቅ_ስምምነት_መፈረም: ሁለቱም ወገኖች በእርቅ ስምምነት ላይ ከደረሱ፣ ስምምነቱን በጽሁፍ አዘጋጅተው ይፈርማሉ። ይህ ስምምነት ተከሳሹ ለተበዳዩ ሊያደርግ የሚችለውን ካሳ ወይም ሌላ ስምምነት ሊያካትት ይችላል። #የክሱ_መቋረጥ: በስምምነቱ መሰረት ዐቃቤ ህግ ወይም ፍርድ ቤቱ ክሱን ያቋርጠዋል፣ በዚህም ጉዳዩ ይዘጋል። ይህ አሰራር ወንጀልን ከመቅጣት ባለፈ ሰላማዊ መፍትሄዎችን በማበረታታት ለፍትህ ስርአቱ ያለውን አስተዋፅኦ ያሳያል። ይሁን እንጂ፣ ሁሉም ወንጀሎች በእርቅ ሊያልቁ እንደማይችሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ከባድ ወንጀሎች (ለምሳሌ፣ ግድያ፣ ዝርፊያ፣ ከባድ የአካል ጉዳት) በመንግስት እና በህዝብ ላይ ከባድ ጉዳት ስለሚያስከትሉ፣ በህግ ጥብቅ በሆነ እና ከበድ ባለ ቅጣት የሚጠይቁ ናቸው።
👉ተጨማሪ መመዘኛዎች፣ #ተአማኒነት እና ጥንቃቄ: አንድ ምስክር የሚሰጠው ቃል ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በጥንቃቄ መታየት አለበት። በወንጀል ጉዳዮች ላይ ምስክሩ በፖሊስ ወይም በሌላ አካል ተጽዕኖ ስር መውደቁን፣ ወይም ምስክርነቱ የተሰጠው ከጥቅም ወይም ከጥላቻ አንጻር መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለምሳሌ፣ የፖሊስ ምስክሮች ቃላቸውን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። #የምስክሩ ማንነት: ምስክሩ የፖሊስ ሰርጎ ገብ፣ የአደንዛዥ ዕፅ ሱስ ያለበት ወይም የአእምሮ ችግር ያለበት ከሆነ ቃሉ በጥንቃቄ መፈተሽ አለበት። #የምስክሩ ቀጥተኛነት: "በዓይኔ አየሁ" ወይም "በጆሮዬ ሰማሁ" የሚሉ ምስክሮች ቃላቸው ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር መጣጣሙን በከፍተኛ ጥንቃቄ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በወንጀል ጉዳይ ላይ፣ በቀጥታ ምስክርነት ላይ ብቻ ተመርኩዞ ውሳኔ መስጠት አደገኛ ነው። ለፍትሐብሄር (ሲቪል) ጉዳዮች የምስክር ቃል ምዘና በፍትሐብሄር ጉዳዮች ላይ ማስረጃን የመመዘን መስፈርት ከወንጀል ጉዳዮች ያነሰ ነው። ✅የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሚመሰረተው በበለጠ ማስረጃ የበላይነት (Preponderance of the Evidence) መርህ ላይ ነው። ይህ ማለት፣ አንድ ማስረጃ ከሌላው ማስረጃ የተሻለ እምነት የሚጣልበት ከሆነ፣ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በዛ ማስረጃ ላይ ይመሰረታል። ተጨማሪ መመዘኛዎች: #የምስክሩ ተነሳሽነት: የምስክሩን የግል ጥቅም ወይም ወገንተኝነት መገምገም በፍትሐብሄር ጉዳዮች ላይ ቁልፍ ነው። ለምሳሌ፣ አንድ ሰው የቤተሰብ አባልን ንብረት ለመውረስ በሚደረግ ክርክር ላይ ሲመሰክር፣ ቃሉ በጥንቃቄ መመዘን አለበት። #የምስክሮች ብዛት: በፍትሐብሄር ጉዳዮች ላይ የዓይን ምስክሮች ቁጥር ለውሳኔው ክብደት ሊሰጠው ይችላል። ብዙ ምስክሮች አንድ አይነት ነገር ሲመሰክሩ፣ ፍርድ ቤቱ የዚያን ማስረጃ ተአማኒነት ከፍ አድርጎ ሊመለከተው ይችላል። #የግንኙነት አይነት: የምስክሩ ከፓርቲዎቹ ጋር ያለው ዝምድና፣ የንግድ ግንኙነት ወይም የጓደኝነት ግንኙነት ቃሉን ለመመዘን ያገለግላል። ለምሳሌ፣ በገንዘብ ክርክር ላይ የባለ ዕዳው የቅርብ ጓደኛ የሆነ ምስክር ቃሉን በጥንቃቄ መፈተሽ ተገቢ ነው። ስለሆነም፣ ምንም እንኳን የምስክር ቃልን የመመዘን መሰረታዊ መርሆች ለወንጀል እና ለፍትሐብሄር ጉዳዮች ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ በወንጀል ጉዳዮች ላይ ያለው የሕግ መስፈርት (ያለ ምንም ጥርጥር) ከፍ ያለ በመሆኑ፣ የምስክሮች ቃል የበለጠ ጥብቅ በሆነ ማጣሪያ ውስጥ ያልፋል። በፍትሐብሄር ጉዳዮች ላይ ግን (በበለጠ ማስረጃ የበላይነት) መርህ ላይ ተመርኩዞ፣ የምስክር ቃሉ አሳማኝ እና ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር የሚጣጣም መሆኑን ማየት በቂ ሊሆን ይችላል።
የምስክሮች ቃል ትክክለኛነት መመዘኛ መንገዶች በፍርድ ቤት ክርክሮች ውስጥ የሰዎች ምስክርነት ወሳኝ ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል። ሆኖም፣ አንድ ምስክር የሚሰጠው ቃል ምን ያህል ትክክለኛና ተዓማኒ እንደሆነ መለየት የዳኝነት ሂደት ከባድ ፈተና ነው። ብዙውን ጊዜ ዳኞች ምስክሮቹ ከከሳሽ ወይም ከተከሳሽ ጋር ባላቸው ዝምድና ወይም ጠብ ላይ ብቻ ተመስርተው ውሳኔ ሲሰጡ ይታያል። ይህ አካሄድ ግን የምስክር ቃሉን ሙሉ በሙሉ የሚመዝን አይደለም። የምስክርነት ቃል ትክክለኛነትን ለመመዘን እና ሚዛናዊ ውሳኔ ለመስጠት ዳኞች በርካታ ጉዳዮችን በዝርዝር ማጤን አለባቸው። ከታች የተዘረዘሩት ነጥቦች የምስክር ቃልን ለመገምገም የሚረዱ ዋና ዋና መመዘኛዎች ናቸው። 1. ዕድልና አጋጣሚ (Opportunity and Occasion) አንድ ምስክር ስለሆነ ድርጊት ሲመሰክር፣ በመጀመሪያ እሱን ለማየት፣ ለመስማት ወይም ለማወቅ የቻለበትን ሁኔታ መገምገም ያስፈልጋል። የዚህ መመዘኛ ዋና ጥያቄዎች፡ #ምስክሩ ድርጊቱ በተፈጸመበት ጊዜና ቦታ ለምን እዚያ ሊገኝ ቻለ? #ድርጊቱ ሲፈጸም እሱን ያስተዋለበት አጋጣሚ ምን ያህል ተጨባጭ ነው? ለምሳሌ፣ አንድ ምስክር ወንጀል የተፈፀመው ሌሊት ላይ በጨለማ እንደሆነ ቢመሰክር፣ በዛ ሰዓትና ቦታ ለማየት ምን ያህል ዕድል ነበረው? የምስክሩ ቃል በአጋጣሚው ላይ የሚሰጠው ማብራሪያ ምክንያታዊ ካልሆነ፣ የቃሉ ተዓማኒነት አጠያያቂ ሊሆን ይችላል። ይህ መመዘኛ ምስክሩ ያየውን ወይም የሰማውን በትክክል ለመለየት የሚያስችል በቂ ጊዜ፣ ቦታ እና አካላዊ ሁኔታ እንደነበረው ለማረጋገጥ ይረዳል። 2. ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ የምስክርነት ቃል ምዘና ቀጥተኛ ማስረጃ ማለት ምስክሩ "በገዛ ዓይኔ አየሁ" ወይም "በገዛ ጆሮዬ ሰማሁ" የሚለው አይነት ነው። ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ ደግሞ ምስክሩ በሌላ ሰው የሰማውን ወይም ያየውን የሚያብራራበት ነው። ብዙ ጊዜ ቀጥተኛ ማስረጃ የተሻለ ነው ብሎ ማሰብ የተለመደ ነው። ሆኖም፣ ይህ አመለካከት ሁልጊዜ ትክክል ላይሆን ይችላል። የዓይን ምስክር ከግል ፍላጎት፣ ጥላቻ፣ ወይም ከዝምድና የተነሳ የተዛባ ቃል ሊሰጥ ይችላል። ለምሳሌ፣ አንድ "የአይን ምስክር" ወንድሙን ለመከላከል ሲል ውሸት ሊመሰክር ይችላል። በሌላ በኩል፣ ቀጥተኛ ያልሆነ ምስክር (ለምሳሌ፣ ስለአካባቢው ሁኔታ የሚመሰክር ገለልተኛ ሰው) ቃሉ ከተጨማሪ ማስረጃዎች ጋር ሲታይ የበለጠ እምነት የሚጣልበት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ፣ የምስክርነት ቃል ጥራት የሚለካው ቀጥተኛ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ሳይሆን፣ ከሌሎች ማስረጃዎች እና ሁኔታዎች ጋር ተደምሮ በሚያሳየው የአስረጅነት ብቃት ነው። 3. የምስክሮች ቃል አንድነትና ልዩነት ብዙ ምስክሮች ሲሰሙ የሁሉም ቃል እርስ በእርስ መጣጣም አለበት ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን፣ በምስክሮች ቃል መካከል ልዩነት መኖሩ ሁልጊዜ እውነትን መናገር ያቆማሉ ማለት አይደለም። ምክንያቱም፡ #የግንዛቤ ልዩነት: ሰዎች የተለያየ የማስተዋል እና የማስታወስ ችሎታ አላቸው። ሁለት ሰዎች አንድን ክስተት ቢመለከቱ እንኳን የሚያስታውሱት ነገር የተለያየ ሊሆን ይችላል። #የቃላት ምርጫ: ሰዎች አንድን ነገር ለመግለጽ የሚጠቀሙበት የቃላት አገላለጽ ሊለያይ ይችላል። ስለዚህ፣ ፍርድ ቤቶች በቃላት መካከል ያለው ልዩነት ጉልህና መሰረታዊ መሆን አለመሆኑን ማየት አለባቸው። ለምሳሌ፣ አንድ ሰው "ሰዓቱ ከሰዓት 10 አካባቢ ነበር" ሲል፣ ሌላው ደግሞ "ከ10:30 በፊት ነበር" ቢል፣ ይህ ልዩነት ጉልህ አይደለም። ነገር ግን አንዱ ምስክር "ሰዎቹ ሁለቱ ነበሩ" ብሎ ሌላው "አምስት ሰዎች ነበሩ" ቢል፣ ልዩነቱ መሰረታዊ ነው። በተቃራኒው፣ ምስክሮች የሚሰጡት ቃል ተመሳሳይ መሆኑ ሁልጊዜ እውነት መሆኑን አያረጋግጥም። የሁሉም ምስክሮች ቃል ቃል በቃል ቢመሳሰል፣ የተቀናጀ (scripted) ሊሆን ይችላል ብሎ ጥርጣሬን ይፈጥራል። ስለዚህ የምስክሮች ቃል ቢመሳሰልም እንኳ እያንዳንዳቸው በሚሰጡት ማብራሪያ እና አያያዥነት ላይ መመስረት ተገቢ ነው። 4. ጥቅም ያላቸው ምስክሮች የምስክርነት ቃል ምዘና አንድ ምስክር ከከሳሽ ወይም ከተከሳሽ ጋር ዝምድና፣ ጠብ፣ ወይም የጥቅም ግንኙነት ሲኖረው፣ ቃሉን በጥንቃቄ መመዘን ያስፈልጋል። ይህ ማለት ግን ሁልጊዜ ይዋሻል ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ግንኙነቱ የጎላ ቢሆንም ምስክሩ እውነተኛውን ነገር ሊመሰክር ይችላል። ፍርድ ቤቶች አንድ ምስክር የሚመሰክረው ለጥቅም ወይም ለጥላቻ የተነሳ መሆኑን ለመለየት የሚከተሉትን ማጤን አለባቸው፡ #ምስክሩ ጉዳዩን ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት በማሰብ የተጋነነ ወይም የተቀነባበረ መረጃ ሰጥቶ እንደሆነ። #ምስክሩ ለመመስከር የተነሳበት ትክክለኛ ምክንያት ምን እንደሆነ። ለምሳሌ፣ አንድ ምስክር በቤተሰብ አባል ላይ ስለተፈጸመ ወንጀል ሲመሰክር፣ ቃሉ በስሜት የተሞላ እና የተጋነነ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን፣ ለተጋራ ጥቅም ማስረጃ ለማቅረብ ሲል የሚመሰክር ምስክር፣ እውነቱን ሊያጣቅስ ይችላል። 5. ልዩ መደብ ያላቸው ምስክሮች ቃል ምዘና አንዳንድ የምስክሮች ቡድኖች እንደየሁኔታቸው ተጨማሪ ጥንቃቄ የሚሹ ናቸው። #ህጻናት: የህጻናት ምስክርነት ብዙውን ጊዜ እውነተኛ እንደሆነ ቢታሰብም፣ ከሌሎች ተፅእኖዎች ስር የመውደቅ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው። በተጨማሪም የማስታወስ ችሎታቸው በእድሜያቸው ምክንያት አጠያያቂ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ፣ የህጻናት ቃል ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ተነጻጽሮ በጥንቃቄ መመዘን አለበት። #አዛውንቶች: የእድሜ መግፋት ከማስታወስ ችሎታ መዳከም ጋር ተያይዞ ችግር ሊፈጥር ይችላል። ስለዚህ፣ የአዛውንቶች ምስክርነት ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ተደግፎ መታየት ይኖርበታል። #የሙያ ምስክሮች (ኤክስፐርቶች): የሙያ ምስክሮች በሙያዊ አስተያየታቸው ምክንያት ተዓማኒነት ያላቸው ቢሆኑም፣ ቃላቸው እንደ ፍጹም እውነት ሊወሰድ አይገባም። ዳኞች የኤክስፐርቱን ሙያዊ ደረጃ፣ ልምድ፣ ገለልተኝነት እና አስተያየቱን የሰጠበትን ምንጭ ማጣራት አለባቸው። ለምሳሌ፣ የአንድን ጉዳይ አወሳሰን ለማገዝ የመጣ ባለሙያ ቃሉ የራሱን ወይም የሌላውን ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን ማጤን ያስፈልጋል። የምስክሮችን ቃል በትክክል ለመመዘን፣ ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በማነጻጸር እና በመተንተን የተሻለ እና እውነተኛ ውሳኔ ላይ መድረስ ይቻላል። ለወንጀል እና ለፍትሐብሄር ጉዳዮች የምስክሮች ቃል ምዘና የምስክሮች ቃል ለወንጀል እና ለፍትሐብሄር (ሲቪል) ጉዳዮች ወሳኝ ማስረጃ ነው። ሆኖም፣ ሁለቱ የሕግ ዘርፎች የራሳቸው ልዩ ባህሪያት ስላሏቸው፣ የምስክር ቃልን የመመዘን ሂደትም ይለያያል። ለወንጀል ጉዳዮች የምስክር ቃል ምዘና በወንጀል ጉዳዮች ላይ የመንግስት ጠበቃ (ዐቃቤ ሕግ) የተከሰሰውን ሰው ጥፋተኛ መሆኑን ያለ ምንም ጥርጥር (Beyond a Reasonable Doubt) ማረጋገጥ አለበት። ይህ ማለት፣ የምስክሮች ቃል በጣም በጥንቃቄ እና በከፍተኛ ጥርጣሬ መፈተሽ አለበት።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በክረምት በከፊል የሚሰጡ የዳኝነት አገልግሎቶች የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 38 ንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት ከመደበኛ የፍርድ ቤት የስራ ጊዜ ውጭ አስቸኳይ ጉዳዮች እንደሚስተናገዱ ይገልጻል፡፡ በዚህም መሰረት መሰረታዊ የመብት ጥሰት የሚያስከትሉ በባህሪያቸው ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱ የስራ ጊዜ እስኪጀመር አፋጣኝነታቸው ታይቶ ዉሳኔ ካልተሰጠባቸው የመብት መጣስን ሊያስከትል የሚችሉ እና ሊካስ የማይችል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮችን አይቶ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑባቸው ጊዜ ማለትም ከነሃሴ 01 ቀን እስከ መስከረም 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ በተረኛ ችሎት በወንጀል እና በፍታብሄር ጉዳዮች መደበኛ የፍርድ ቤት የስራ ጊዜን የማይጠብቁ ጉዳዮች አስቸኳይ ጉዳዮች ሲቀርቡ የሚታዩ ይሆናል በዚሁ መሰረት፡- በፍታብሄር ከሚቀርቡ ጉዳዮች ፡- ➢ አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች ➢ የልጅ ቀለብ ➢ አካል ነጻ ለማውጣት ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ➢ እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ➢ ሰራተኞች በአሰሪዎቻቸው ላይ የሚያቀርቡት የደመወዝ ክፍያ የሚመለከቱ አፈጻጸም ጉዳዮች ➢ ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዞች ጋር ተያይዞ አስቸኳይ የማህተም አገልግሎት ጥያቄዎች (ለእግድ, መጥሪያ ለማድረስ..) ➢ አንገብጋቢ እና ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ መጠበቅ የማይችሉ በተረኛ ችሎቱ ዳኛ የሚወሰኑ ሌሎች የፍታብሄር ጉዳዮች በወንጀል ከሚቀርቡ ጉዳዮች፡- ➢ ዋስትና ➢ አመክሮ ➢ አርቲዲ (እስረኛ ያለባቸው የሚቀርቡ የወንጀል መዛግብት ) ➢ በተሰብሮ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ➢ ጊዜ ቀጠሮ(አራዳ ምድብ ችሎት) ➢ ለመሰየም የሚቀርብ አቤቱታ ➢ እስረኛ ያለባቸው መዝገቦች ➢ አንገብጋቢ እና ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ መጠበቅ የማይችሉ በተረኛ ችሎቱ ዳኛ የሚወሰኑ ሌሎች የወንጀል ጉዳዮች ባጠቃላይ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆንባቸው ጊዜያት መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ የማይጠብቁ ጊዜ የማይሰጡ እና አጣዳፊ የሆኑ የወንጀል እና የፍታብሄር ጉዳዮች በተረኛ ችሎት የሚስተናገዱ መሆኑን በማረጋገጥ ሁሉም የፍርድ ቤቱ ማህበረሰብ እንዲሁም ተገልጋዩ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲወጣ እናሳውቃለን፡፡
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи