tgindex
KJUMJ Da'wah Center

KJUMJ Da'wah Center

Статистика

Official Page of KJUMJ Da'wah Structure Jimma University(kito campus JIT) *Inspiring the sunnah* Bot : @Daewa_comment_bot

Последний пост
14:29
Последнее чтение
08:44
Постов за неделю
10
Всего постов
40
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Образование
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
770
+1 за 4 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
218
38 постов
Вовлечённость
28,3%
к подписчикам
Постов в день
1,4
всего 40
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
116
1/48двое суток
132
1/72трое суток
143

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • የአላህ ቃል በማንም ቢነበብ ያምራል... ነገር ግን በአንዳንዶቹ ደግሞ ይለያል! 🎧

  • ⚠️በጣም የሚያስፈራ የቁርኣን አያህ፦ «وَعَصَيْتُم مِّن بَعْدِ مَا أَرَاكُم مَّا تُحِبُّونَ» (የምትወዱትን ካሳየኋችሁ በኋላ አመፃችሁ!) — [አል-ዒምራን፡ 152] በጭንቅ ቀን እጅህን ዘርግተህ"ያ አላህ! ይህን ብቻ ፈፅምልኝ እንጂ ከእንግዲህ ዳግመኛ አልመለስበትም፤ ቃል እገባልሃለሁ!" ብለህ ስትለምነው የነበረውን ቀን አስታውስ።ጌታህ አዘነልህ፤ የለመንከውን ሰጠህ፤ ልብህ የተመኘውን አሳየህ፤ ጭንቅህን ገፈፈልህ።ነገር ግን... ገና ከእጁ የተቀበልከው ጸጋ ሳይቀዘቅዝ፣ የታበሰው እንባህ ሳይደርቅ፣ በዚያው በሰጠህ ኃይል፣ ጤና እና ጸጋእርሱን መልሰህ አመፃከው! ያቺን የማልክባትን ወንጀል በጌታህ ፊት ደግመህ ተገበርካት።ከዚህ በላይ የሚያስፈራና የሚያሳፍር ታላቅ ክህደት አለን?! አንተ ከጌታህ 'የምትወደውን' ትቀበላለህ እርሱ ግን ከአንተ'ሚጠላውን' ያገኛል!

  • 🪷 ኢኽላስ ** ኢኽላስ የኢባዳዎች ሁሉ ማስዋቢያ ነው፤ኢኽላስ ትልቅ የቀልብ ስራ ነው፤ስራዎች ያለ ኢኽላስ ባዶ ናቸው፤ጣዕም አልባም ይሆናሉ፤ስራዎች ያለ ኢኽላስ ከምላስ እና አካል አያልፉም፤ቀልብ ላይ ጠብ የሚል እርካታም አያስገኙም፤ስራም እንደተበተነ አቧራ ይሆናል ድካም እና ልፋት ብቻ ሆኖ ይቀራል። ……ለስራዎቻችን የምናስቀድመው ኢኽላስ ትልቅ የቀልብ ስራ ነው።ኢኽላስ ስራችንን ከቆሻሻዎች አጽድቶ ንጹህ አድርጎ ለአላህ ማድረስ ነው፤የእውነት ለአላህ ብሎ መስራት ነው። ** ኢኽላስ ከትንሽ ስራ ጋር በርካቶችን ከፍ አድርጓል፤ኢኽላስን ማጣት ደግሞ ከብዙ ስራ ጋር በርካቶችን አዋርዷል ዝቅ አድርጓል። (አላህ ይጠብቀን) ** ኢብኑል ቀይም رحمه الله "ስራዎች በአፈጻጸማቸው እና ብዛታቸው አይበላለጡም፤ስራዎች የሚበላለጡት ቀልብ ውስጥ ባለው ነገር ነው፤ስራዎች አፈጻጸማቸው እና ሁኔታቸው አንድ ይሆን እና ከመብለጥ አንጻር ግን የሰማይ እና ምድር ያክል ልዩነት ይኖራቸዋል" ይላሉ ** አዎ ስራዎች ልብ ውስጥ ባለው እውነተኝነት ይበላለጣሉ! .........መልዕክተኛውﷺ እጅግ የሚወዷቸው የቅርብ ጓዳቸው አቡበከር رضي الله عنه እጅግ ታላቅ ሰው ነበሩ ደረጃቸውም ግዙፍ ነው። ** በክር ኢብኑ አብዲላህ ስላሰቸው ሲናገር እንዲህ ይላል "አቡበከር ለየት ያለ እና የበዛ ሰላትን እና ጾም ኖሮት አይደለም ከሁሉም የበለጠው እና የቀደመው ነገር ግን ቀልቡ ውስጥ በገባው ነገር ነው" ይላል ኢኽላስ ትልቁ የልብ ስራ ነው! اللهم أصلح فساد قلوبنا،وجعل أعمالنا خالصة لوجهك

  • 🌹 አላህ አንድን ባሪያውን ሲወደው . . . አላህ (سبحانه وتعالى) አንድን ባሪያውን ሲወደው፤ በልቡ ውስጥ ደግነትን፣ ቅንነትንና እዝነትን (ራህመትን) ያሰፍንለታል። ይህ የልብ ስጦታ ከማንኛውም ዓለማዊ ሀብት በላይ ትልቅ የጌታ በረከት ነው፤ ምክንያቱም በደግነት የታነጸ ልብ የሰላም ሁሉ መገኛ ነውና። በአላህ ውዴታ የተከበበ ባሪያ፤ በሰዎች ላይ በደልን (ዙልምን) አይፈጽምም፣ በትዕቢት አይታበይም፣ ቃል ኪዳን አያፈርስም፣ ተንኮልን አይሸርብም፣ እንዲሁም ታማኝነትን እንጂ ክህደትን በፍጹም አያውቅም። ስብዕናው በአላህ ፍርሃትና ውዴታ የተገራ ነውና። ** የአንድ ሰው እውነተኛ ታላቅነት የሚለካው ለፍጡራን በሚያሳየው ርኅራኄ ነው። ልብ በአላህ ብርሃን ሲታጠብ፣ ተግባር ሁሉ ይቃናል፤ ያኔ አላህ የሰዎችን ልብ ለዚያ ባሪያ ታዛዥና አፍቃሪ ያደርጋቸዋል። ** የመልካም ስነ-ምግባር ምንጭ የአላህ ውዴታ ምልክት ነው። አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ሲያምር፣ ይህም አላህ በውስጡ የዘራው የእዝነት ፍሬ ውጤት መሆኑን ያስገነዝባል። ** አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ለባሪያዎቹ ከሰጣቸው ትላልቅ ፀጋዎች መካከል በፍጥረታቱ እንዲወደዱ ማድረጉ ነው። 🌹አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ለሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) እንዲህ አላቸው :- { وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مني } سورة طه، الآية ٣٩. "ባንተ ላይም ከእኔ የኾነን መወደድ ጣልኩብህ።" ኢብኑ ከሲር ይህን የቁርአን አያህ ሲያብራሩ "አንድም ሰው ሙሳን አይመለከታቸውም የተመለከታቸው ሰው ሁሉ የወደዳቸው ቢሆን እንጂ" ብለዋል። ኢብኑ አል-ሙንከዲር ለአቢ ሐዚም እንዲህ አላቸው፦ ** ሰዎች ሲያገኙኝ በመልካም ነገር ዱዓ ያደርጉልኛል። እኔ አላውቃቸውም ከነርሱ ጋር በጋራ መልካም ተግባር ፈፅሜም አላውቅም። (ለነርሱም ያደረኩላቸው መልካም ነገር የለም) አቡ ሐዚምም እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ "ይህ የአላህ ችሮታ ነው።" { سَيَجْعَلُ لَهُمُ الرَّحْمَنُ وُدًّا } "አር-ረሕማን ለእነሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል።" ኢላሒ...! አንተ ከምትወዳቸውና በልባቸው ውስጥ ደግነትን ካሰፈርክላቸው ምርጥ ባሮችህ መካከል አድርገን። آمين يارب 🤲

  • без подписи

  • 📌 قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : (( لا تختصُّوا ليلةَ الجمعةِ بقيامٍ من بين اللَّيالي . ولا تخصُّوا يومَ الجمعةِ بصيامٍ من بينِ الأيَّامِ . إلَّا أنْ يكونَ في صومٍ يصومُهُ أحدُكُمْ )) - صحيح مسلم/1144 - 💎 شرح الحديث : يومُ الجمُعة خَيرُ الأيَّامِ، إلَّا أنَّ النبيَّ صلَّى اللهُ علَيهِ وسلَّمَ- كما في هذا الحديثِ - نَهى أن تُخَصَّ ليلتُه بقِيامٍ دُونَ غَيرِها مِن سائرِ لَيالي الأُسبُوعِ، وكذلكَ نَهَى صلَّى اللهُ علَيهِ وسلَّمَ أن يُخصَّ يومُه بصيامٍ مِن بَينِ سائرِ أيَّامِ الأُسبوعِ، إلَّا أنْ يَكونَ في صَومٍ يَصومُه أحدُكم، كأنْ يَكونَ صومُه مُرتبِطًا بكفَّارَةٍ مِنَ الكفَّاراتِ، أو نذْرٍ وقَعَ ميقاتُه يومَ الجُمُعةِ، وغيرِها ممَّا يَلزمُه صِيامُه، 📌 والمُرادُ بالتَّخصيصِ : هو إفرادُ اللَّيلَةِ بقِيامٍ، أو إفرادُ اليَومِ بصِيامٍ. (الدرر السنية / الموسوعة الحديثية/37169)

  • የአላህ መልዕክተኛ ወንጀለኞችን እንዴት ያርሙ ነበር? 🥀የአላህ መልዕክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከወንጀለኞች ጋር እጅግ አዛኝ ነበሩ። ምክንያቱም እነኚህ ወንጀለኞች የሰው ልጅ እንደመሆናቸው መጠን ነፍሳቸው ደክማ በዛ ወንጀል ላይ እንደወደቁ ስለሚያውቁና ወደ አላህ የሚያቃርባቸው አካል እንደሚያስፈልጋቸው ሰለተረዱ ነው። ✔️ ከአጋጣሚዎቻቸውም መካከል፦   1/ ኡማማተል ባሂሊ ባስተላለፈው ሀዲስ አንድ ወጣት ወደ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መጣና እንዲህ አላቸው፦ " አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ዝሙትን ይፍቀዱልኝ"  እንዲህ ሲል የአላህ መልዕክተኛ ባልደረቦች ተንጫጩ ወቀሱትም ።ከዛም የአላህ መልዕክተኛ "ወደኔ ተጠጋ" አሉት።ከዛም ይህ ወጣት ወደ ረሱል ተጠጋ። የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉት፦ "ይህን ተግባር ለእናትህ ትወደዋለህ? " ከዛም ወጣቱ " አላህ የርሶ ቤዛ ያደርገኝና በአላህ እምላለሁ አልወደውም " የአላህ መልዕክተኛ፦ " ሰዎችም እኮ ለእናቶቻቸው አይወዱትም " ቀጠሉ " ለሴት ልጅህስ ትወደዋለህ? " ወጣቱ፦ " አላህ የእርሶ ቤዛ ያድርገኝ በአላህ እምላለሁ አልወደውም " የአላህ መልዕክተኛ፦ " ሰዎችም አኮ ለሴት ልጆቻቸው አይወዱትም " ከዛም ለአክስትህ ለእህትህ እያሉ ቀጠሉ።በሁሉም ጊዜያት ታድያ ይህ ወጣት አይ የአላህ መልዕክተኛ አልወድም እያለ ይመልስ ነበር።ከዛም ረሱል እጃቸውን ደረቱ ላይ አደረጉና እንዲህ ብለው ዱኣ አደረጉለት፦ " ጌታዬ ሆይ!  ወንጀሉን ማርለት ልቡን አንፃለት ብልቱን ጠብቅልት " ይህ ወጣት ከዚህ በኃላ ዝሙት  እሱ ዘንድ እጅግ የተጠላ ሆነ!   ** የምንረዳው ቁም ነገር ፦የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሁሉም ሰው በላይ የአላህን ድንበሮች የሚጠባበቁ ሁነው ለእዚህ ወጣት ያደረጉትን ነገር ተመልክተናል።በእዝነትና በእርጋታ እንዲሁም በጥበብ የተሞላ ምላሽ ነበር የመለሱለት።እሱን ከመቆጣትና ከመጮኽ ይልቅ ድክመቱን ተረድተው በዘዴ ቀስ ብለው ያደረገው ድርጊት ትክክል እንዳልነበር አስተማሩት ከዛም ዱዓ አደረጉለት።     2/ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘመን አብደላህ የተባለ ሰው  ረሱልን ያስቃቸው ነበር። በሆነ አጋጣሚ መጠጥ በመጠጣቱ ረሱል ቅጣት አቋቋሙበት ከዛም በሌላ ጊዜ ደግሞ ጠጥቶ መጣና ተገረፈ።ከዛ አንድ ሰው ተነሳና " ጌታዬ ሆይ!  እርገመው! ስንት ጊዜ ነው የሚመጣው!? " ብሎ ሲረግመው ነብዩ ሰሙትና ፊታቸው ተቀያየረ " በአላህ እምላለሁ ከእሱ የማውቀው አላህና መልዕክተኛውን የሚወድ መሆኑን  እንጂ ሌላን አላውቅም " አሉ ** የምንረዳው ቁም ነገር ፦ አንድ አማኝ ወንጀለኛ እንኳን ቢሆን መልካም የሚባል ነገር ስለሚኖረው ሰዎች በወንጀሉ ሲያነውሩት እኛም የምናውቀውን መልካም ነገር በማንሳት ልናስቆም እንደሚገባን ነው ።                        3/ ሙአዊያህ ቢን አልሀከም ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ ይላል ፦ "ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር እየሰገድኩ ሳለ ከሰጋጆች መካከል ዘንድ ሰው ያስነጥሳል ። ከዛም ሙአውያህ ለሰጋጁ አካል "አላህ ይዘንልህ " ይለዋል። ሰጋጆች እንዲህ ስል በውግዘት አስተያየት ተመለከቱኝ ። ከዛም " ምን ሁናችሁ ነው ምንድን ነው ጉዳያችሁ እኔን የምትመለከቱኝ!?"  አልኳቸው።  ሰጋጆች ዝም ሊያሰኙኝ  ታፋቸውን ይመታሉ። ከዛ ሰላቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ዝም አልኩኝ ። እናቴም አባቴም ለአላህ መልዕክተኛ  ቤዛ ይሁንላቸው በአላህ እምላለሁ አልገላመጡኝም ፣ አልመቱኝም ፣ አልሰደቡኝምም " ከዛም የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለው አረሙት ፦ " ይች ሰላት እኮ ከሰዎች ንግግር አንዳችም አይሆንባትም። እሷ እኮ አላህን ለማጥራትና ለማላቅ እንዲሁም ቁርዓንን ለመቅራት ናት " ** የምንረዳው ቁም ነገር ፦ ባለማወቅ የሚሳታቱ ሰዎችን በለዘብተኝነት መመከር እንዳለብንና ፈጥነን ወደ ቁጣ ወይም ወደ እርምጃ መሄድ እንደሌለብን በዚህ ሀዲስ እንረዳለን።

  • без подписи

  • ሰላሁዲን አል አዩቢ  ይህን ስምና ስብዕና የምእራቡ ዓለም መስቀለኞች በሚገባ ያውቁታል፡፡ በታሪካቸው ውስጥ ላይረሱት በጉልህ የሚታይ ጀግና ነው፡፡ መስቀለኞቹ በተደጋጋሚ ኢስላማዊውን የሻም ምድር ድንበር ይጥሳሉ፡፡  በይተል መቅዲስን በእጃቸው አድርገው ይጫወቱበታል፡፡ በ583 ዓ.ሂ ወይም  እ.ኤ.አ በ1187 ይህ ፈርጣማና የዓላማ ሰው ሰላሁዲን ታዲያ ከግብፅ ምድር ተነስቶ ወደ ቁድስ ሲያመራ የመስቀላውያኑ ጦር ሒጢን የተባለ ቦታ ላይ ጠበቀው፡፡ በፍልሚያው የሰላሁዲን ጦር ድል ቀናው፡፡ ሉዚናንና ሮናልድ የተሰኙ የቁድስን ባለስልጣናት ማረከ፡፡ ከዚህ ፍልሚያ በኋላ ቁድስ ነፃ ወጣች፡፡ በሙስሊሞች እጅ ዳግም ከዑመር ጊዜ በኋላ ተመለሰች፡፡  ሰው ሰውን ሳይሆን ሃያሉን አምላክ መገዛት ጀመረ፡፡ ዛሬ የስርዓት አልባ ፅዮናውያን አይሁዶች መጫወቻና መፈንጫ ብትሆንም በወቅቱ ግን በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር ነበረች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዑመርም (ረዲየላሁ አንሁ) በዘመነ-ኺላፋቸው ነፃ አውጥተዋት ነበር፡፡ ሙስሊሞች ባለፈ ታሪካቸው ሽንፈትና ውርደትን ቀምሰው አያውቁም፡፡ ዛሬ ግን ኡማው ዲኑን ትቶ የሌሎች አጨብጫቢና አጃቢ ሲሆን መሰረታዊ ማንነቱ ኪሳራ ላይ ወደቀ፡፡ቢሆንም የሙስሊሙ እንቅልፍና መታለል ለጥቂት ጊዜ ነው፡፡ ንቃቱና ብርታቱ ግን ከአንዴ በኃላ መሸወድ አያውቀውም፡፡ ለዚህ ነው መልዕክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)  ‹‹ሙእሚን በአንድ ጉድጓድ ሁለቴ አይወድቅም›› ያሉት፡፡ የዚህች ኡማ ዳግም  ውልደት ሩቅ አይደለም፡፡ ለመወለድ ደግሞ የእርግዝናውንና የምጡን ህመም ማስተናገድ ይጠበቃል፡፡

  • ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنَّ اللَّهَ لَيَرْضى عَنِ العَبْدِ أَنْ يَأْكُلَ الأكْلَةَ فَيَحْمَدَهُ عَلَيْها، أَوْ يَشْرَبَ الشَّرْبَةَ فَيَحْمَدَهُ عَلَيْها﴾ “አላህ ከባሪያው ላይ ይወዳል ምግብን ከተመገበ በኃላ በሷ እንዲያመሰግነው። ወይም መጠጥንም ከጠጣ በኋላ በሷ እንዲያመሰግነው።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: (2734)

  • **ትልቁ ስህተታችን የራሳችንን ንፁህ ልብ በሰዎች ሁሉ ውስጥ ፍለጋ መሄዳችን ነው። በተለይ ቅን እና የዋህ ስንሆን፣ የምናሳየውን መልካምነትና የምንሰጠውን እውነተኛ ፍቅር ከሌሎችም በተመሳሳይ መልኩ እንደምናገኝ እንጠብቃለን። ነገር ግን ዓለም ሁሌም እንደ እኛ አይደለችም።   **  እራሳችሁን ለማንም Define አታድርጉ። ከማይረዷችሁ ሰዎች ጋር ጊዜያችሁን አታባክኑ። ደስታችሁንም፣ሀዘናችሁንም፣መከፋታችሁንም ሁሉንም ለአላህ ንገሩት ሳታወሩ፣ሳትጵፍ ይረዳችኋልና ። ** ከአላህ ጋር  አድርጉት ሁሉንም።      **የሚወድ ልብ ያላችሁ፣                                               ሰውን ለመውደድም የማትቸጋገሩ፣ ቀልባችሁ ንፁህ የሆነ፣ ውስጣችሁ ጥላቻ የሌለ ሁሉ እንኳን ደስስስስ አላችሁ ። **"ሙእሚን የሚወድም የሚወድድም/ በቀላሉ የሚለምድም የሚለመድም ነው። " ብለዋል ነቢያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ** መውደድ ወጪ አያስወጣም፣ አያለፋም። የሰውን ድካም የምትጋሩ፣ ሸክማቸውን የምታቀሉ፣ የቤት ሥራዎቻቸውን የምትካፈሉ፣ የማትከብዱ የማታካብዱ ቀለል ያለ ተግባቢ ሰው ሁኑ ይላል እስልምናችን። ** የጀነት መንገዱም ይኸው ነው።

  • مضتِ السنون كأنها أيامُ والعمرُ يمضي والأنامُ نيامُ والموتُ يدنو كل حينٍ خطوةً وأنا ومثلي أعيتِ الأحلامُ كنّا نُأَملُ بالشباب فقد مضى وأتى المشيبُ وظلّت الأوهامُ عامٌ أتى بالأمس أقبل نحونا واليوم يخلفُ بعده أعوامُ العام أضحى اليوم فينا جمعةً والجمعة الغرا لنا أيامُ وأنا ومثلي في الذنوب وما لنا زادٌ إذا هتف الرحيل مُقامُ فإلام نبقى في الذنوب أيا أخي والموت آتٍ والحياة حُطامُ وإلام نركض نحو عيشٍ زائلٍ هذا لعمري مؤسفٌ ومُلامُ

  • 🕋 አላህ ሱረቱል ተውባ መጨረሻ ላይ ስለ ሀቢቢ ﷺ አይነታነት በዚህ መልኩ ይገለፃል: لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ ** "ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ ፡፡"   عزيز عليه ما عنتم    * ችግራችን በእርሱ ላይ ፅኑ የሆነ * ሱረቱል ተውባ የአላህን ቁጣ የሚገልፅ ምዕራፍ ነው! በቢስሚላህ አይጀምርም። አስፈራሪ እና አስደንጋጭ አያዎችን አካቷል። ግን አላህ ምዕራፉን በሳቸው አዛኝነት ደመደመው! የሙዕሚኑ ችግር ችግራቸው የሆኑ መልዕክተኛ... ችግራችን፤ መከራችን የሚያስጨንቃቸው ፤ ታላቁን ጉዞ ሲያደርጉ እንኳን በቀን 55 ሰላት ሲወጀብብን ተጨንቀውልን እንዳይከብደን እና እንዳንቸገር ለማስቀነስ ጌታቸው ዘንድ የተመላለሱልን ነብይ ﷺ! ለሊቱን "ኡመቲ ኡመቲ" በማለት ከሳቸው በኃላ ለምንመጣው ኡመቶቹ የተጨነቁት መልዕክተኛ! ... ችግራችን፥ መከራችን፥ ጉዳታችን በሳቸው ላይ ጽኑ የሆኑት ውዳችን! ** በዚህን ያህል ደረጃ ነበር ለኛ የሚጨነቁት በሳቸው ላይ ሰለዋት ማብዛትን አንርሳ!!

  • ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል ! **የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡ “ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው *ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡ **የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ “ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” “የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” 🕰 “ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም ድርጊትህን እንጂ” “ አላህን ያዝ ሰበቡን አድርስ የተሻለ ነገር ታገኛለህ፤ኢንሻአላህ ፤ ሁሉም ነገር ከጥረት ጋር መሆኑን  አትዘንጋ ” ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

  • без подписи

  • **ሙስሊሞቹ 313 አካባቢ ብቻ ነበሩ ቁሳቁስና ትጥቅም የላቸውም ነበር። ቁረይሾች ደሞ 1000+ ሆነው በሙሉ አቅምና ትጥቅ "ዛሬ ሙስሊሞቹን እናጠፋቸዋለን" ብለው ወጥተዋል በኛ አእምሮ ሂሳብ ከሰራነው 313 vs 1000+ እጅግ ከባድ  ጭንቅ ያለበት ሰዓት ነበር። 🌹ረሱል (ﷺ) እና ሶሃቦች የአቅማቸው ጥረት ሁሉ ካደረጉ በኋላ፣ ረሱል (ﷺ) እጆቻቸውን ወደ ሰማይ ዘርግተው አላህ ድልን እንዲሰጣቸው በከፍተኛ ጭንቀት እና እምባ መለመን ጀመሩ፣**ሹፍ አኺ «تستغيثون» ማለት ዝም ብሎ ጸሎት ሳይሆን Emergency Call  ግራ ሲገባን መውጫ ቀዳዳ ስናጣ በዛች ሰዐት እርዳታን በመፈለግ ምናረገው ዱዐ ማለት ነው። 🕋 አላህም ጥሪያቸውን ሰማ ተቀበለውም"1,000 መላእክት"  ተላኩላቸው ውጊያውም በሙስሊሞች ድል ተጠናቀቀ። ** ወንድሜ... በህይወትህ ፈተናዎች በዝተውብህ፣ ችግሮች ከአቅምህ በላይ ሆነው ባስጨነቁህ ሰዓት የበድርን ጦርነት አስታውስ በአላህ ካመንክና ከታገልክ ፣ ከምርህና ከልብህ በየቂን አላህን ከጠራኸው  አላህ ፈጽሞ አይጥልህም፣ ባልጠረጠርከው መንገድ እርዳታ ይልክልሃል። ** በሰው አቅም የማይቻለው ነገር አላህ ጣልቃ ሲገባበት ታሪኩ በሙሉ ይቀየራል!! ኢንሻአላህ ❤️

  • °ᡣ𐭩 إِنها حَياة فَانِيـة فأعمل لِآخرَتك

  • без подписи

  • • عنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ : • قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : *《 لَا تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُقْبَضَ الْعِلْمُ ، وَتَكْثُرَ الزَّلَازِلُ ، وَيَتَقَارَبَ الزَّمَانُ ، وَتَظْهَرَ الْفِتَنُ ، وَيَكْثُرَ الْهَرْجُ ، وَهُوَ الْقَتْلُ الْقَتْلُ ، حَتَّى يَكْثُرَ فِيكُمْ الْمَالُ فَيَفِيضَ 》.* 📓📔 رواه البخاري (١٠٣٦) ومسلم (١٥٧)