tgindex
ምስባከ ማዕረጉ (Mairegu's Pulpit) ሰ ማ ይ ተ ና ፍ ቀ ሃ ል

ምስባከ ማዕረጉ (Mairegu's Pulpit) ሰ ማ ይ ተ ና ፍ ቀ ሃ ል

Статистика
@MareJesusанглийский

በሞቱ እመስለው ዘንድ እናፍቃለሁ!! ወደ ፊል 1:23 ✍️NAZARENE Holistic Gospel We love Jesus We miss Jesus He has promised us that he will not break his promise. Now is the time to look up.

Последний пост
21:34
Последнее чтение
17:58
Постов за неделю
11
Всего постов
37
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 533
−27 за 4 дн.
Сутки
−6
−0,13%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
193
35 постов
Вовлечённость
4,3%
к подписчикам
Постов в день
1,6
всего 37
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
95
1/48двое суток
108
1/72трое суток
117

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 21:349031

    ህመሜ ህመምህ ሰው የሰውን ጭንቀት ይጋራ ይሆናል፣ የሰውን እምባ ይጠርግ ይሆናል፣ የሰውን ለቅሶ ያግዝ ይሆናል፣ የሰውን ችግር ይረዳ ይሆናል፣ የሰውን ድካም ያግዝ ይሆናል፣ በእርግጥ እንዲህ ይሆናል አንዳንዴ ከጎናችን የሚሆኑ የሚያግዙን እለፍ ጊዜ ደግሞ ጀርባቸውን የሚሰጡን ይኖራሉ። ነገር ግን ማን በአንተ ቦታ ልሁን ይላል? ማን ያንተን ጭንቀት ልውሰድልህ ይላል? ማን ሞትህን እኔ ልሙት አንተ ኑር ይላል? ማን ግርፋትህን ልገረፍልህ አንተ አትቁሰል ይላል? ማንም አይልም። አንተ ግን የእኔን ህመም የወስድክልኝ ምትኬ ነህ። በእኔ ቦታ ሆንክ እንጂ ከጎኔ አልሆንክም። ከጎኔ ብትሆን እኔም በታመምኩ አንተም በታመምክ ነበር አንተ ግን ህመሜ ታመምክልኝ። ቁስልህ ጌጤ ሆኖ በኩራት የመኖሬ ምክንያት ሆነ። የኔ መሞት ገዶህ ከሰማያት የሳበህ ፍቅር ነው። የፍቅር ምሳሌ አይደለህም እራስህ ፍቅር ነህ። አንተን ስላመምህ ይመመኝ አልልም አንተ ግን አንተን እንዳያምህ እኔ ልታመምልህ ብለህ ግርፋቴን እና መመታቴን ለራሳህ አርገሃል። ህመምህ ፍቅርህን የሚናገር ስንኝ ነው። ችንካርህ መውደደህን የሚያስረዳ ሰንበር ነው። ያን ሁሉ መከራ የተቀበልከው እኔን ከዛ ሁሉ መከራ ለማዳን ነውና ተመስገን እልሃለሁ። እኔ ብገረፍ ትርፌ ቁስል እንጂ መዳን መች ይሆናል? እኔ ብቸነከር ቀሪዬ ህመም እንጂ መፈወስ አይሆንም። ይህን በራሴ መድረግ ስላልቻልኩኝ አንተ መፍትሔ ሆነህ ከሰማይ መጣህልኝ። አንተ ቆስለህ ሰው ሁሉ ዳነ አንተ ተመተህ ሰው ሁሉ ተፈወሰ። ጌታ ሆይ ተመስገን። “ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።” 1ኛ ጴጥሮስ 2፥24          ወንድማችሁ ማዕረጉ ደሳለኝ ነኝ https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus

  • ​"1 ቀን ብቻ ቀረው! አዎ... ነገ ይጀምራል! ​በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 'ሁለንተናዊ ተሃድሶ ለዳግም ምጽዓት' የአንድ ሳምንት ዝግ ስልጠና ነገ በይፋ ይጀምራል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ሀሳብ  አስተያየት አሎት? ✉️ ከታች በሚገኘው ሊንክ ይላኩልን ይደርሰናል። ╔════════════╗ @HHKCH_COMMENT @HHKCH_COMMENT @HHKCH_COMMENT ╚════════════╝

  • https://youtu.be/BhSLWKTIU20?si=LBReebpHbBLbMc8g ቅዱሳን ሰምታችሁ ተባረኩ🙏🥰

  • እግዚአብሔር እንደሚወደኝ አልጠራጠርም።ምንም እንኳን የመንገዱ እርዝመትና በየዕለቱ የሚገጥሙኝ ፈተናዎች ተስፋ ለማስቆረጥ ቢጥሩም አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ።ከወደደኝ ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ ነፍሱን አሳልፎ በመስጠት እስከ መስቀል ሞት ካፈቀረኝ አባቴ ጋር አንድ ቀን ፊት ለፊት እገናኛለሁ።እንደሚወድህ አንተም ታውቃለህ❤😭 https://t.me/MareJesus

  • 🔥😭😍የልቤ ልባዊ ጸሎት🔥😍😭 ከተጻፈው በላይ የሆንህ ፣ ከተዘመረልህም ይልቅ ድንቅነትህ የሚያበራ ፣ ከተሰበከው ጠልቀህ የምትኖር ፣ ከተቀደሰው ቅዳሴ በላይ መዓዛህ ልዩ የሆነ እግዚአብሔር አንተ ነህ ። የአቅማችንን ያህል እናመስግንህ እንጂ ይህ ልክህ ይህ መጠንህ አይደለም ። ምስጋናን የከንፈር ፍሬ ፣ መላ ሕይወታችንን የሚቃጠል መሥዋዕት ፣ በመጠን መኖራችንን የእህል ቊርባን ፣ ፍቅራችንን የኅብረት መሥዋዕት ፣ ንስሐችንን የኃጢአት መሥዋዕት ፣ ዓለም በቃኝ ማለታችንን የበደል መሥዋዕት አድርገን እናቀርብልህ ዘንድ እንወዳለን ። መሻት እንጂ አቅም የለንምና ካለ መቻል ታድነናለህ ። በፊትህ ሁሉም ነገር የተገለጠ ፣ የተራቆተና ባዶ የሆነ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የአሳባችንን ብክለት በመንፈስህ አየር አንተ ለውጠው ። በፊትህ እኛን ሁነን ስንመጣ የአንተ አድርገህ መልሰን ። ስንጀምር አንተ ፈጽምልን ፣ ስንፈጽምም ጅማሬአችንን እይልን ። የእኛ ጅምር ማለቅ ፣ የእኛ ፍጻሜ ደስታ የለውምና አንተ አግዘን። የሚበጀንን ባለ ማወቅ በሞት ሰፈር የሚንኖር ፣ እውቀት ተስኖን የእሳትን ውበት እንጂ ማቃጠል የማንለይ ልጆችህ ነንና አድገን እናሳርፍህ ዘንድ ሠርተህ ፈጽመን ። የምስጋናን ዘውድ ጭነህ ፣ በግርማ ተከበህ ፣ በራስህ ክብር ደምቀህ ትኖራለህ ። የሰጠኸው እንጂ የሰጠህ ፣ የሾምኸው እንጂ የሾመህ ማንም የለም ። እንደማትችል ዝምታህ ፣ እንደማይሰጥ መዘግየትህ ይደንቃል ። ልቤ እንደ መሰንቆ ሁኖ አንተን ቢያከብርህ ፣ ዓይኔ እንደ ዋሽንት ሁኖ አንተን ቢያስስህ ፣ እጄ እንደ በገና ሁኖ ንጉሥነትህን ቢተርክ እመኛለሁ ። ዝንጉዎችን በማስታወስ ፣ አላዋቂዎችን በአእምሮ የምትባርክ እኔ መሪያቸው ነኝና እባክህ አበርታኝ ። የሰጠኸኝን ሳላየው ሌላ ያምረኛል ፣ በምንጩ አጠገብ ቆሜ የጥማት ሲቃ ይተናነቀኛል ። የሌለኝን ከመስጠትህ በፊት ያለኝን አሳውቀኝ ። ጌታ ሆይ ስለበዛው ጤና የማመሰግንህ ከቶ መቼ ነው ። ፀሐይ ባሪያህ ሁና ሳይደክማት ታበራለች ፣ አንተ ግን የዓለም ብርሃን ባልካቸው ልጆችህ መብራትነት ትደሰታለህ ። በአንተ ዘንድ የተወደደ መሥዋዕት አቀርብልህ ዘንድ እጄን በትጋት፣ አፌን በምስጋና ፣ ልቤን በመወሰን ባርክ ። ሕዝቡ የአንተ ነውና እንደ ጎርፍ ወደ ጥፋት ሲሄድ መልሰው ። የምድር መሪዎች የሚመሩትን ንቀው የሚናገሩት ሁሉ ቀላል ንግግር ነው ። የፈጠርከውን ወገን አንተ አክብረው ። ተራራው ላይ ስወጣ ሁሉ ይታየኛል ። ወደ ተራራ ለመውጣት ግን ድካሜ ያሳስበኛል ። ያደከመኝ ተራራ ከፍታ እንደሚሆነኝ እባክህ አስረዳኝ ። ያልተገፋ ራስ ላይ አይወጣም ። የጎን ጦር የሌለበትም ስለ ዕድገት አያስብም ። ዛሬ የደረስኩበት ነገር ሁሉ ጠላቶቼ ላጥፋህ ሲሉ ያበሩኝ ነውና ጠላቶቼን ባርክልኝ ። ፈርዖንን አስነሥተህ እስራኤልን ለንስሐ የጋበዝህ ፣ የተመቻቸው ባሪያ ከመሆን ነጻነት ያላቸው ድሆች እንዲሆኑ ያነቃቃህ ፣ በክፉዎችም እየሠራህ ልጆችህን የምታበረታ አንተ ነህ ። የምስጋናህ ጤዛ ነፍሴን ያርሳት ፣ የክብርህ ጠል ይረፍብኝ ። ያነሰ ኑሮ ከመኖር ፣ ዝቅ ባለ አስተሳሰብ ዝቅ ከማለት ጠብቀኝ ። ዘመንን የማይብህ ዓይኔ ነህ ተመስገን ። ለዘላለሙ አሜን። https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 11 авг.73из cefethiopia

    🌟 ልጆችን በወንጌል የመድረስ ድንቅ ጉዞ፡ የ5-ቀን ክለብ (5-Day Club)! 🌟 ልጅነት የእውቀት ብርሃን የሚሰፍርበት፣ የወደፊት ሕይወትም መሠረት የሚጣልበት ውብ ዕድሜ ነው። ይህንን ወርቃማ ጊዜ በሰማያዊ እውነት ለመቅረጽ ልጆችን በወንጌል የመድረስ ህብረት (CEF) የሚያከናውነው አገልግሎት እጅግ የላቀ ነው። በአሁኑ ወቅትም ይህ ሕይወት የሚለውጥ የልጆች የወንጌል ማሠልጠኛ መርሃ ግብር በበርካታ የኢትዮጵያ ክልሎች በድምቀትና በታላቅ ስኬት እየተካሄደ ይገኛል። የ5-ቀን ክለብ (5-Day Club) ትልቁ ኃይል እና ፋይዳ ልጅ-ተኮር የወንጌል ማካፈል ስልት፡ ፕሮግራሙ ልጆችን በሚረዱት ማራኪ ቋንቋ፣ በምስላዊ ትምህርቶች፣ በመዝሙሮች እና በይነተገናኝ መንገዶች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲረዱ አድርጎ ያዘጋጃቸዋል። ለአዳጊ ወጣቶች የተሰጠ የተግባር መሪነት ዕድል፡ ወጣቶችና ሰልጣኞች ጥልቅ ሥልጠናዎችን ወስደው ወደ መሬት በመውረድ፣ ማህበረሰቡን የማገልገል እና ትውልድ የመቅረጽ አቅማቸውን በተግባር ያሳያሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችን የመድረስ ራዕይ፡ ከሥልጠናው ማጠናቀቂያ በኋላ እነዚህ አገልጋዮች በየአጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናቸው እና በየምስራች ቡድኖቻቸው (Good News Clubs) አማካኝነት ማራኪ የ5-ቀን ፕሮግራሞችን ያዘጋጃሉ። ይህ ትልቅ እና ሕይወት የሚለውጥ የእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ያለ እንቅፋት ተሳክቶ እንዲቀጥል፣ ሁላችሁም በጸሎት እና በማበረታታት ከሰልጣኞችና ከማኅበሩ ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን በፍቅር እናቀርባለን! 🙏 Facebook | Telegram | YouTube | website | TikTok sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯 Child Evangelism Fellowship እያንዳንዱን ልጆች | በእያንዳንዱ ቀን | በሁሉም ቦታ

  • በቃ ኢየሱስ ማለቴን ከማቆም ሞቴን እመርጣለሁ፣አፌን አላበላሽም፣በእርሱ አይደል እንደ ወደ አብ የቀረብኩት?ከኢየሱስ ጋር ኖሮ መሞት ያለ ኢየሱስ 1000 ዓመት ከመኖር ይልቅ የሚበልጥ ስኬት ነው።ከቄሳር ዙፋን ይልቅ የአንበሳ መንጋጋ ሚቾት ይሰጠኛል🙏 https://t.me/MareJesus

  • የሉቃስ ወንጌል 15:1-2 (AMH) •••••••••• ¹ ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። ² ፈሪሳውያንና ጻፎችም። ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ።

  • የእኔ አባት🥰 ያለ ትናንት ቀዳማዊ ያለ ዛሬ ማዕከላዊ ያለ ነገ ዳህራዊ ጥንቱን የሰራኸው አልፋ ፍጻሜውን ያበጀኧው ዖሜጋ ለዘመንህ ጥንት ለህይወትም ፍፃሜ የሌለህ አንተ ፊተኛው አንተ ኋለኛው አንተ መጀመሪያው አንተ መጨረሻ ዘላለማዊው ንጉሣችን በጣት ያልተሾምክ በጣት የማትሻር አጨብጭበን የማናነግስ አኩርፈን የማናወርድህ ግርማዊ ቀዳማዊ ኤልሻዳይ!! https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus

  • ከነሐሴ 10 እስከ 17 2018ዓ.ም ለመመዝገብ 0949591027 0931380080 ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ሀሳብ  አስተያየት አሎት? ✉️ ከታች በሚገኘው ሊንክ ይላኩልን ይደርሰናል። ╔════════════╗ @HHKCH_COMMENT @HHKCH_COMMENT @HHKCH_COMMENT ╚════════════╝

  • без подписи

  • без подписи

  • የእግዚአብሔርም ቃል #እየሰፋ_ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር #_እጅግ_እየበዛ_ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ። የሐዋርያት ሥራ 6:7 የጌታ ፀጋ እና ሠላም ይብዛላችሁ።እንደ እግዚአብሔር በጎ ፈቃድ የዓለም አዳኝ የሆነውን የዘላለሙን የምሥራች (ወንጌል) ለአሕዛብ (ለሰው ሁሉ) የማብሰር ጥር ለዳነ አማኝ ሁሉ የተሰጠ ኀላፊነት በመሆኑ፣ይኸንን መልካሙን የምሥራች ከሆሳዕና በመነሳት በሀላባ ከተማ የዘላለም አምላክ መንፈስ ቅዱስ በሠጠን መለኮታዊ እገዛ መሠረት ከሐምሌ 24-26 2018 ዓ.ም እያገለገልን ቆይተናል።በዚህም ቆይታ እግዚአብሔር አምላክ በብዙ ፀጋውን አብዝተውልን በተለያየ ኀይማኖት፣በሠይጣን እስራት ውስጥ ላሉት አብስረናል።እግዚአብሔርን አመስግኑልን...🙏 በቆይታችን፦ 1) በቤተክርስቲያን ውስጥ አምልኮ፣ፀሎት፣ቅዱስ ወንጌል መማር፣የቤተክርስቲያንቷን ምዕመን ማገልገል፣የልምድ ልውውጥ 2) የወንጌል ሥርጭት አገልግሎት በሀላባ ከተማ በሙሉ እና አከባቢ ማብሰር  በዚህም ቆይታ፦ 1) ወንጌል የሠማ፦ ወ=125 ሴት=125  ድምር=250 2) ተስፋ የሰጠ፦ ወ=10  ሴት=2    ድምር=12 3) ንስሐ የገቡ፦ ወ=1    ሴ=1   ድምር፦2 4) ያመነ፦  ወ=5   ሴት=3  ድምር፦ 8 የእግዚአብሔርን ቅዱስ ሥም ከፍ እናድርግ፣ ከቅዱሳን መልአክት ጋር...🙏 በእውነት እግዚአብሔር ቼር ነው። ዓለምን ለማዳን ኢየሱስን ወደ ዓለም በመላክ ሕዝቦችን ለመንግሥቱ በደሙ ዋጅቷልና። በሁሉ የረዳንን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ታላቅ አድርጉት። ደግሞም በተለያየ መንገድ በአገልግሎቱ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ የነበራችሁ እናንተ ሁላችሁም ብሩካን ናችሁ። በጣም እንወዳችኋለሁ !! https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus

  • #ዋናው_እኔ_ነኝ ብዙ የበደሉህ ዋኖች ይኖራሉ እንደ እኔ ግን አልበደለሁም፣ አንተን ያስከፉህ ቢሰለፉ ከፊት የምገኘው እኔ ነኝ፣ በኃጢአት ባህር መዋኘት ድሎት የሆናቸው ብዙ አሉ ዋናው ግን እኔ ነኝ፣ ልክ ባልሆነው ጎዳና የሚራመዱ አሉ መሪያቸው ግን እኔ ነኝ፣ አንተን በመቅረብ ፈንታ ጀርባ የሰጡህ አሉ እኔ ግን እብሳለሁ፣ ጌታዬ መድሃኒቴ ኢየሱስ አንተን የምትል ነፍሴ በስጋ ድካም ውስጥ ሳለ አለሁሽ ያልካት አንተ ነህ። እኔ መማርህ እንዴት ያለ ምህረት ነው። የምህረትህ ድልድልነት ለእያንዳንዱ መንገዴ መሸጋገሪያ ሆኖኛል። እኔን ለማዳን ወደዚች አለም የመጣ አስታዋሼ አንተ ነህ። ከነ ኃጢያቴ እንዳልጠፋ እኔ ባለሁበት ተገኝተህ ያገኘኸን ፈላጊዬ ነህ፣ በሞት ጥላ ውስጥ ያለሁትን በደምህ ድምጽ የጠራኸኝ ባለውለታዬ አንተ ነህ፣ በምድረበዳው ብቻዬን ስባዝን ና ወደ እኔ ያልከኝ አስጠጊዬ አንተ ነህ። እኔ ብቻ እንኳን በኃጢያት የጠፋው ብሆን የራስህ ጉዳይ ብለህ ከነበደሌ የማትተወኝ ለእኔ ብቻ እንኳን ብለህ ልትሞትልኝ የምትመጣ አፍቃሪዬ ነህ። ለእኔ ስትል ሰው የሆንክ አምላኬ ክርስቶስ ሆይ ክበር ተመስገን። እኔን ዋናውን ለማዳን ስትል ከሰው ተርታ ተገኝተህ በሰው ልክ የተመላለስክ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ተመስገን። ወደ ክብሬ ልትመልሰኝ ክብርህን እንደመቀመት ሳትቆጥር ከላይ ከሰማያት የመጣህልኝ አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ። እኔን ከማርከኝማ እኔን ይቅር ካልከኝማ ማንም ትምራለህ። እኔን ዋናውን ከተቀበልክማ መዳፍህ ሰፊ ነው ሁሉን ይቀበላል። ለእኔ ስለሆነው በጎነትህ ክብር ይሁንልህ። አሜን “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤” 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥15 ወንድማችሁ ማዕረጉ ነኝ https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus

  • የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ቢሆን የፊታችን ዕሁድ በዶዮገና ከተማ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር መልካምነቱን ያጠግበናል። https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus https://t.me/MareJesus