tgindex
⚖️🇪🇹 የሕግ ምክር /Legal Advice/📝📢

⚖️🇪🇹 የሕግ ምክር /Legal Advice/📝📢

Статистика
@MeserlawyerангНиКскиК

ለማንኛውንም የህግ ጉዳዮች👇👇 LawyerYemesrach LL.B LL.M in Human Rights Law ⚖️ ☎️0911-98-20-12 /0920-88-92-64☎️

Последний пост
12:17
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
7
Всего постов
27
Тип
открытый
Язык
ангНиКскиК
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
144
+4 Са 3 дн.
Сутки
+1
+0,70%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
29
25 постов
Вовлечённость
20,1%
к подписчикам
Постов в день
1,0
всогО 27
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
14
1/48двое суток
16
1/72трое суток
17

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ተጠርጣሪ በመረጠው የግል ሕክምና ተቋም የመታከም መብት ===////===== * በወ/መ/ሼ/ሼ/ሕ/ቁ.184 መሠረት የትዕዛዝ ይግባኝ የሌለ ስለመሆኑ የተደነገገ ቢሆንም የተሰጠው ትዕዛዝ ወደፊት በዋናው ጉዳይ ላይ ከሚቀርበው ይግባኝ ጋር ተጠቃሎ ሊቀርብ የማይችልና ውጤቱም የሚቀለበስ ካልሆነ በጊዜያዊ ትዕዛዝ ላይ የተሰጠ ይግባኝ ነው በሚል ተቃውሞ የማይቀርብበትና በይግባኝ የሚታይ ስለመሆኑ፤ * ለእስረኞች የሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው በማረሚያ ቤት ውስጥ በተዘጋጀ የጤና ተቋም ቢሆንም በሕግ ጥላ ሾር የሚገኝ ተጠርጣሪ በጤና ተቋሙ ለመታከም እምነት የሌለው በመሆኑ በመረጠው የግል የሕክምና ተቋም አገልግሎት እንዲያገኝ በጠየቅ ጊዜ ይህንን ለማከናወን የፀጥታ ስጋት ቢኖርም መንግስት ጸጥታ እና ደሕንነትን በማስጠበቅ ተጠርጣሪው ህክምናውን እንዲያገኝ ሊያመቻች የሚገባ ስለመሆኑ፤ የሰ/መ/ቁ 203051 (የካቲት 22ቀን 2013ዓ.ም)ቅፅ 25

  • https://youtu.be/6heRNGgavDM?si=oLLe5PkBxWS2ZYpZ

  • የኢትዮጵያ መንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ! 1. የምዝገባ ሂደት ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ከተቀጠረ በ60 ቀናት ውስጥ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የጡረታ ምዝገባ ማድረግ አለበት። 2. የጡረታ መዋጮ ● ለሲቪል ሰራተኞች: ከሰራተኛው 7%፣ ከመንግስት 11% ሲሆን፣ በድምሩ 18% ይሆናል። ● ለፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት: ከሰራተኛው 7%፣ ከመንግስት 25% ሲሆን፣ በድምሩ 32% ነው። 3. ለጡረታ የሚያበቁ ምክንያቶች ● በእድሜ ምክንያት (60 ዓመት ሲሞላ) ● በራስ ፍቃድ ● በጤና ጉድለት ● በስራ ላይ በደረሰ የአካል ጉዳት ● በሞት 4. የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈልባቸው ሁኔታዎች ● በእርጅና ● በህመም ● ወደ ውጭ አገር በመሄድ ● በትምህርት ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ ● በእስራት ምክንያት 5. የጡረታ አበል በይርጋ የሚዘጋበት ጊዜ ● የጡረታ ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነ የጡረታ አበል ሳይወሰድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ፣ አይከፈልም። ነገር ግን፣ ከዚያ በኋላ ጥያቄ ካቀረበ፣ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ክፍያው ይቀጥላል። ○ የሟች ጡረታ (ዳራጎት) ሳይጠየቅ ወይም ለ3 ዓመት ሳይወሰድ ከቆየ፣ በይርጋ ይዘጋል። 6. በእድሜ ምክንያት ለሚወጣ ሰራተኛ የጡረታ ስሌት ● የጡረታ አበል የሚሰላው በመጨረሻዎቹ 36 ወራት (3 ዓመት) አማካይ ደመወዝ ላይ ተመስርቶ ነው። ● ከመጀመሪያው የቅጥር ቀን እስከ 10 ዓመት ያለው አገልግሎት በ30% ይባዛል። ● ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት በ1.25% ይባዛል። ○ ለምሳሌ: 28 ዓመት ያገለገለ ሰራተኛ ስሌት፡- ● (10 ዓመት × 30%) + (18 ዓመት × 1.25%) = 30% + 22.5% = 52.5% ● የመጨረሻ 36 ወራት አማካይ ደመወዝ 5,000 ብር ከሆነ፣ የጡረታ አበሉ 52.5% × 5,000 ብር = 2,625 ብር ይሆናል። 7. የቅጥር ቀንና ወር ሲታጣ የቅጥር ዘመን ብቻ በህይወት ታሪክ ከተሞላ፣ የጡረታ ቀንና ወር በሚከተለው መልኩ ይያዛል፡- ● በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ይወሰዳል። ● በግሪጎሪያን (እ.ኤ.አ) አቆጣጠር ከሆነ ታህሳስ 31 ተብሎ ይወሰዳል። 8. በራስ ፈቃድ ጡረታ መውጣት ● አንድ ሰራተኛ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን እና የ25 ዓመት የአገልግሎት ዘመን ሲኖረው በራሱ ፍላጎት ጡረታ መውጣት ይችላል። ● ለፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት ግን ጡረታ ከሚወጡበት እድሜ 5 ዓመት ቀድመው መውጣት ይችላሉ። 9. የሟች ጡረታ ወራሾች ● የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ወይም የአካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ ከ21 ዓመት በታች መሆን አለባቸው። ● የሟች እናትና አባትም ወራሾች ይሆናሉ። 10. ለጡረታ አበል ማስፈፀሚያ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ● የህይወት ታሪክ ቅጽ (ጡ1 እና ጡ2) ● የሙከራ እና የቋሚ ቅጥር ደብዳቤዎች ● የጡረታ መለያ ቁጥር ● የ36 ወራት ደመወዝ መረጃ ● የዝውውር፣ የደረጃ እድገት እና የደመወዝ ለውጥ ደብዳቤዎች ● የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ ● የባለጡረታው ወይም የወራሽ ፎቶግራፍ

  • የሕሊና/የአእምሮ ሕመም እና የወንጀል ኃላፊነት (በወንጀል ሕግ አንቀጽ 48 እና 49)፦ አንድ ተከሳሽ በፈጸመው የወንጀል ድርጊት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ኃላፊ የማይሆነው (የአእምሮ ሕመምተኛ ነው የሚባለው) ድርጊቱን በፈጸመበት ወቅት በሕመም ምክንያት የድርጊቱን አደገኝነት ማወቅ ወይም ራሱን መቆጣጠር ያልቻለ መሆኑ በህክምና ማስረጃ ሲረጋገጥ ብቻ ነው የሰበር በመዝገብ ቁጥር 225975 ላይ የሰጠው ውሳኔ ። የህክምና ማስረጃዎች እና የባለሙያ ምስክርነት አቀራረብ (በወንጀል ሕግ አንቀጽ 51/3)፦ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸው የህክምና ምርመራ ውጤት ያልተሟላ ወይም አጠራጣሪ ሆኖ ሲያገኙት፣ የህክምና ምርመራው እንደገና ተደርጎ በትክክል ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ መስጠት አለባቸው። የህክምና ውጤቱ በራሱ በቂ ሆኖ ባልቀረበበት ሁኔታ፣ ፍርድ ቤቶች በሳይንሳዊ መንገድ የተደረሰበትን የህክምና መደምደሚያ ትተው የህክምና እውቀት በሌላቸው የሰው ምስክሮች ቃል ላይ ብቻ በመመስረት ተከሳሹን "በከፊል ኃላፊ ነው" ወይም "የአእምሮ ሕመምተኛ ነው" ብለው መደምደማቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው። የስር ፍርድ ቤቶች ስህተት፦ በተከሳሹ (ተጠሪ) ላይ የተደረጉ የህክምና ምርመራዎች ተከሳሹ በአሁኑ ወቅት የከበደ የአእምሮ ሕመም እንደሌለበትና ድርጊቱን በፈጸመበት ወቅትም የአእምሮ ሁኔታው ምን ይመስል እንደነበር የማያሳዩ ባሉበት ሁኔታ፣ የስር ፍርድ ቤቶች የህክምና ምርመራው እንደገና ተጣርቶ እንዲቀርብ ሳይታዘዝ ተከሳሹን "በከፊል ኃላፊ" በማለት ቅጣቱን ማቃለላቸው አግባብ አይደለም ተብሏል።

  • https://youtu.be/WxsiZzQkDgA?si=ViU3u8XRXriO56b1

  • йоС пОдписи

  • https://youtu.be/vr6Xfld9vQg?si=TlVyl4mCT7LcpDhI

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • 7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ የሰበር ውሳኔ፤ መዝገብ ቁጥር 246230 ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 186946 የተሰጠው ውሳኔ ‘‘በአንድ ቦታ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቢኖራቸው አንደኛው ቤት ቢሰራ ሌላኛው ወገን በይዞታዬ ላይ እየተቃወምኩኝ ቤት ሾለሰል ያፍርስልኝ በማለት መጠየቅ የማይችል መሆኑን’’ የሚገልጸው ውሳኔ ተለውጧል፡፡ 7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት መዝገብ ቁጥር 246230 “በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ186946 በሚያዝያ 26/2013 ዓ.ም የተሰጠው አስገዳጅ ትርጉም እና ሌሎች መዝገቦች ላይ የተያዘዉ ተመሳሳይ አቋም ተለውጦ፤ በአንድ ባለይዞታ ሊመዘገብ የሚገባን የከተማ ይዞታ ከአንድ በላይ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ ለተለያዩ ሰዎች ተደርቦ ተሰጥቶ ሲገኝ ለቦታው ባለመብትነት ቅድሚያ የሚሰጠው መጀመሪያ ያስመዘገበው ሰው ነው’’ በሚል ተተርጉመዋል፡፡

  • በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1196(1) መሠረት በሕጋዊ መንገድ የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው ሰው የንብረቱ ባለቤት ለመሆኑ የሕግ ግምት የሚወሰድ በመሆኑ፣ ይህ ግምት ሊፈርስ የሚችለው ካርታው ከሕግ ውጪ መሰጠቱ ወይም ሰነዱን የመስጠት ሥልጣን በሌለው አካል የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ በሰው ምስክርነት ወይም ገንዘብ አውጥቻለሁ በሚል ክርክር ብቻ ሊፈርስ አይችልም። ​በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 (1 እና 2) መሠረትም የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጠበቀው በሕጋዊ መንገድ በተያዘ ይዞታ ላይ ሲሆን ብቻ ነው። በመሆኑም በጋብቻ ውስጥ ባልና ሚስት በወላጅ ስም በተመዘገበ ይዞታ ላይ ገንዘብና ጉልበት በማፍሰስ ቤት ቢገነቡ እንኳ፣ ይዞታውም ሆነ በይዞታው ላይ የተገነባው ቤት የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ሊሆን አይችልም። ​በቤቱ ግንባታ ላይ በትዳር ዘመን በባልና ሚስት የተደረገ የገንዘብ ወጪ ወይም አስተዋጽኦ ካለ፣ ግምቱን ከመጠየቅ ውጪ በሌላ ሰው ስም ባለው ይዞታ ላይ ያረፈውን ቤት የጋራ ንብረታችን ነው ብለው የክፍፍል ጥያቄ ማቅረብ አይችሉም። ​ስለሆነም፣ በጋብቻ ውስጥ በወላጆች ስም ባለው መሬት ላይ የሚገነባ ቤት የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ሳይሆን የባለይዞታው ንብረት እንደሆነ የሚቆጠር ሲሆን፣ በፍቺ ጊዜ የትዳር አጋሮች መብት የሚጠበቀው ያወጡትን ገንዘብ በድርሻቸው ተመላሽ እንዲደረግላቸው በመጠየቅ እንጂ የንብረቱን/የቤቱን ክፍፍል በመጠየቅ አይደለም። ​የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ አቶ ብርሃኑ ከበደ እና ም/ኢ/ር ጥሩነሽ ዱባለ፣ መዝገብ ቁጥር 132 (ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም)

  • በፍርድ ቤት #እግድ የተጣለበትን የማይቀሳቀስ ንብረት (ቤት) የገዛ ሰው፣ ውሉ በመንግሥት አካል ዘንድ ስለተመዘገበ ብቻ "ተገቢውን ጥንቃቄ ያደረገ መልካም እምነት ያለው ገዢ" (prudent purchaser) ተብሎ በሕግ ጥበቃ ሊደረግለትና የንብረቱ ባለቤት ሊሆን አይችልም። 🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄 🎯የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 186626 ላይ የሰጠው ውሳኔ ። የውሳኔው ዋና ዋና ነጥቦች፦ 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 #የገዢው #የማጣራት #ግዴታ፦ ማንኛውም የማይቀሳቀስ ንብረት የሚገዛ ሰው ውል ከመዋዋሉና ከመመዝገቡ በፊት፣ በንብረቱ መዝገብ ላይ የፍርድ ቤት እግድ፣ የዕዳ ወይም የቀደመ የሦስተኛ ወገን መብት መኖር አለመኖሩን የመርመርና የማጣራት የሕግ ግዴታ አለበት። #የምዝገባ #ገደብ፦ ውል ባለሥልጣን ፊት መመዝገቡ ወይም መጽደቁ ብቻውን፣ በሕግ የተጣለን እግድ ወይም የትዳር አጋርን ፈቃድ ማጣት የሚያስቀር/የሚያጸና ሕጋዊ ሽፋን ሊሆን አይችልም። #ውጤት፦ ገዢው አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሳያደርግ እግድ ያለበትን ንብረት ቢገዛ፣ ውሉ ሕጋዊ ውጤት አይኖረውም ውድቅ ይሆናል)፤ የንብረቱም ባለቤት መሆን አይችልም።

  • https://youtu.be/UPM0SPLmVHA?si=AaXJdhGmmZmXm4jf

  • በወንጀል ህግ አንቀፅ 63(1) መሠረት ዋሥትና ለመከልከል ተከሳሽ የተከሰሰበት አንቀፅ በሞት ወይም ከ15 ዓመት በላይ የሚያሥቀጣ ከሆነ እና ጉዳት የደረሠበት ሠው የሞተ እንደሆነ የሚሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው ✍️ቅፅ 24 👉ሠ/መ/ቁ 182266

  • ⚖️ የሰበር ውሳኔ | የሰ.መ.ቁ. 227120 ታህሳስ 27/2015 #ዋና_ፍሬ_ነገር ከእምነት ተቋም (ፀበል) የተሰጠ የፀበል መቆየት ማስረጃ በሕግ ከታወቀ የሕክምና ተቋም የተሰጠ የሕክምና ማስረጃን አይተካም። ስለዚህ፣ ከተፈቀደው የሕክምና እረፍት በኋላ ከሥራ ለመቅረት የቀረበ የፀበል ማስረጃ በቂ ሕጋዊ ምክንያት ስላልሆነ፣ ከ5 ተከታታይ ቀናት በላይ ያለፈቃድ ከሥራ መቅረት ሕጋዊ ስንብትን ያስከትላል። ✅ ውሳኔ: የሰራተኛዋ ስንብት ሕጋዊ ነው፤ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔም በሰበር ጸንቷል። --------------------—-------------

  • ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 15 ዓመት የሆኑ ወጣት አጥፊዎች ከባድ ወንጀል ቢፈጽሙ እንኳ ወደ ጠባይ ማረሚያ ተቋም እንጂ ወደ እስር ቤት ሊላኩ አይገባም። ከ9 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ደግሞ ምንም ዓይነት ድርጊት ቢፈጽሙ በወንጀል አይጠየቁም። የጉዳዩ ይዘት በአጭሩ፦ ተከሳሹ የ14 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ በ8 ዓመት ሕፃን ላይ የግብረ-ሰዶም ወንጀል በመፈጸም ተከሷል። ተከሳሹ የፈጸመው ድርጊት ከ15 እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ከባድ ወንጀል ቢሆንም፣ ተከሳሹ ወጣት አጥፊ በመሆኑ ቅጣቱ ከ10 ዓመት እስራት ሊበልጥ አይገባም። የቅጣት አፈጻጸሙን በተመለከተ፤ ተከሳሹ በጠባይ ማረሚያ ተቋም እንዲቆይ ወይም ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎች እንዲወሰዱበት መደረግ አለበት። በክልሉ የጠባይ ማረሚያ ተቋም ከሌለ፣ ተከሳሹ በእናቱ ጥበቃ ሼር ሆኖ በፖሊስ ክትትል እንዲደረግበት መታዘዝ ይኖርበታል እንጂ ወደ እስር ቤት መላክ እንደሌለበት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቶበታል። የስበር/መ/ቁጥር 136262

  • ‎የመጀመሪያውና በአዋጁ አንቀጽ 288(1) ሼር የተደነገገው “ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ” የማረጋገጫ ደረጃ ከዓቃቤ ሕግ የሚጠበቅ የማስረዳት ግዴታ ነው። በዚህም መሠረት ዓቃቤ ሕግ ክስ ያቀረበበትን ወንጀል በተመለከተ የሐሳብ (Mens Rea) እና የድርጊት (Actus Reus) ክፍሎችን፣ እንዲሁም እንደ ጭብጥ የተያዙና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ነጥቦች መሟላታቸውን “ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ” በሆነ ደረጃ የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለበት በሕጉ በግልጽ ተመልክቷል። ‎የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ እንደ ጭብጥ የተያዘውን ነጥብ ወይም ከጭብጡ ጋር ተያያዥነት ያለውን ፍሬ ነገር፣ በአጠቃላይ ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል መፈጸሙን አረጋግጧል የሚባለው ወይም ተከሳሹ እንዲከላከል የሚታዘዘው ከላይ በተጠቀሰው “ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ” በሚለው ሚዛን ማስረጃው በቂ ሆኖ ሲገኝ ብቻ እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 288(2) ላይ በግልጽ ሰፍሯል። ፍርድ ቤትም የዓቃቤ ሕግን ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወይም ሊያስከስሰው/ሊያስቀጣው የሚችልን ወንጀል (በቀድሞው ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 113(1) መሠረት) መፈጸሙን የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ ካረጋገጠ ብቻ ተከሳሹ ሊከላከላቸው የሚገባ ነጥቦችን ለይቶ በመግለጽ የመከላከያ ማስረጃውን እንዲያቀርብ የማዘዝ ግዴታ እንዳለበት በአዋጁ አንቀጽ 289(2) ሼር ከቀድሞው ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 142 በበለጠ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ተደንግጓል። ‎በሌላ በኩል ተከሳሹ ወንጀሉን መፈጸሙን በተመለከተ በዓቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ወይም በዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ላይ “ምክንያታዊ ጥርጣሬ መፍጠር” ከቻለ ብቻ ተከላክሏል ተብሎ በነፃ እንዲሰናበት እንደሚወሰን በአዋጁ አንቀጽ 293(1) ሼር ተደንግጎል። ይህም ማለት የመከላከያ ማስረጃው የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ሚዛን ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በታች መሆኑን ማሳየት አለበት ማለት ነው። ይህንን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 212950 (ቅጽ 28) እና 51706 (ቅጽ 10) ላይ የሰጠውን ትርጉም አዲሱ የማስረጃ ሕግ የተቀበለው ይመስላል። ስለዚህ “ምክንያታዊ ጥርጣሬን መፍጠር” የሚለው የመከላከያ ማስረጃ ደረጃ አሁን በግልጽ በአዋጅ ቁጥር 1410/2018 አንቀጽ 293(1) ሼር መደንገጉን እንረዳለን። ‎በመጨረሻም ሦስተኛውና “የማስረጃ ብልጫ” (Preponderance) የተባለው ደረጃ በአዋጁ አንቀጽ 293(2) ሼር የተደነገገ ሲሆን፣ ይህም ለኢትዮጵያ የወነጀል ፍትህ ሥርዓትና አሠራር ሙሉ በሙሉ አዲስ ነው። ይህም ከሌሎች አገራት ተሞክሮ የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል ከረቂቁ መገመት ቢቻልም፣ ቋሚ ኮሚቴው በረቂቁ ላይ በሰጠው ትንተና ላይ ስለዚህ አንቀጽ [293(2)] ምንም አለማለቱ ምናልባትም በመጨረሻው በምክር ቤቱ በጸደቀውና በነጋሪት ጋዜጣ በሚታተመው ሕግ ውስጥ ላይካተት ይችላል የሚል ጥርጣሬን ይፈጥራል። ‎ይህ የማረጋገጫ ደረጃ የተከሳሽን የመከላከያ ማስረጃ ምዘና የሚመለከት ሲሆን፣ ይህም ተፈፃሚት የሚኖረው ተከሳሹ የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን መብቱን ጠብቆ ስያምን ብቻ ነው። ለምሳሌ ተከሳሹ የነፍስ ግድያ ወንጀል መፈጸሙን አምኖ ነገር ግን የፈጸመው ራሱን ለመከላከል እንደሆነ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 78 መሠረት ከተከራከረ፣ ራስን ለመከላከል የሚያስችሉ የሕግ መሥፈርቶች መሟላታቸውን በመከላከያ ማስረጃው ማሳየት አለበት። ‎ይህም ተከሳሹ እንደ ፍትሐ ብሔር ክርክር ባለ የማረጋገጫ ደረጃ ማረጋገጥ እንዳለበት በአዋጁ አንቀጽ 293(2) ሼር የተደነገገ ሲሆን፣ “እንደ ፍትሐ ብሔር ክርክር” ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሌላ ሕግ በግልጽ እስካልተደነገገ ድረስ “የማስረጃ ብልጫ” (Preponderance) ደረጃን ያመለክታል። ‎ባጠቃላይ ይህ አዲስ አዋጅ በወንጀል ጉዳይ ማስረጃ ማረጋገጫ ደረጃ ረገድ በርካታ አዳዲስና ግልጽ ነገሮችን ይዞ የመጣ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ቢሆንም፣ ምናልባት ይህ ሦስተኛው ደረጃ (የማስረጃ ብልጫ/እንደ ፍትሐ ብሔር) በረቂቁ ላይ እንዳለው ከጸደቀ ግልጽነት የሚጎድለውና በአፈጻጸም ረገድም ክርክር ሊያስነሳ እንደሚችል መገመት ይቻላል። በተለይም ተከሳሹ ድርጊቱን በፍሬ ነገር ደረጃ ካመነ የማስረዳት ግዴታው ወደ እሱ ስለሚዞር በመጀመሪያ የተከሳሽ ማስረጃ ይሰማል ወይስ የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ነው የመከላከያ ማስረጃ የሚሰማው የሚለው አከራካሪ ሊሆን ይችላል። ተከሳሹ ባመነበት ፍሬ ነገር ላይ ዓቃቤ ሕግ ማስረጃ እንዲያቀርብ ይገደዳል ወይ የሚለውም በተግባር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

  • #የዋስትና_መብት_በተመለከተ_የሰበር_ዉሳኔዎች። ➽ቅፅ 7 ሰ/መ/ቁ 31734 በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት ዋስትና ለመከልከል ግምት ብቻ በቂ ቢሆንም ነገር ግን ለግምቱ በቂ መንደርደሪያ ምክንያት ሊኖር የሚገባ ስለመሆኑ። ግምቱ በጠባቡ መተርጎም ያለበት ስለመሆኑ። አመልካች ፓስፖርትና በርካታ አገሮች መግቢያ ቪዛ ይዞ መገኘት ግምቱ ለመውሰድ በቂ ምክንያት ነው ቢባልም ከአገር የማይወጣበት ሁኔታ በመፍጠር የዋስትና ግዴታውን አክብሮ እንዲቀርብ የሚያደርግ ትእዛዝ መስጠት እየተቻለ የዋስትና መብት መከልከል በአግባቡ ስላለመሆኑ። ➽ ቅፅ 12 ሰ/መ/ቁ 59304 የወ/መ/ሼ/ሼ/ሕ/ቁ 67(ሀ) በዋስትና ወረቀቱ የተመለከቱ ግዴታዎች የሚፈፅም የማይመስል . ፍርድ ቤቱ ዋስትና መብት ለመከልከል ግምቱን መነሻ የሚያደርገው ሁኔታዎች በተጠቀሰው ድንጋጌ በግልፅ አልተመለከተም። እንዲህ ከሆነ አንድ ተከሰሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዴታውን የሚፈፅም የማይመስል ነው ተብሎ ግምት የሚወሰደው በቂና ሕጋዊ ሊባሉ የሚችሉ ምክንያቶች ሲኖሩ ብቻ ስለመሆኑ። የክሶች ብዛትና ከባድነት ፍርድ ቤቱ ይህን ምክንያት ለግምቱ መነሻ እንዲያደርግ በሕጉ የተከለከለ ነው ለማለት አይቻልም በማለት የሰጠው ውሳኔ። ➽ ቅፅ 13 ሰ/መ/ቁ 67874 በዚህ መዝገብ ቀረበው ክስ እስከ 25 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራትና የገንዘብ የሚያስቀጣ ነበር። ተከሳሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዴታውን የሚፈፅም የማይመስል ነው፥ ማስረጃም ሊያጠፋ ይችላል ተብሎ ግምት የሚወሰደው በቂና ሕጋዊ ሊባሉ የሚችሉ ምክንያቶች ሊሆኑ ይገባል ተብሎ የሚታመን ሲሆን በቂና ሕጋዊ ናቸው የሚለው ጉዳይ ከተለያዩ ከባቢያዊ ሁኔታዎችና ከጉዳዩ ልዩ ባህሪ አንፃር እየታየ በፍርድ ቤት ግንዛቤ ሊወስድባቸው የሚችላቸው ነጥቦች ናቸው ተብሎ የሚታሰብ እንጂ ቁርጥ ያለ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች አሉ ለማለት የማይቻል ጉዳይ ነው። ስለሆነም በወ/መ/ሼ/ሼ/ሕ/ቁ 67 በጠቅላላው ሲታይ ፍርድ ቤት ዋስትና መብትን የሚነፈግባቸውን ሁኔታዎች የሚያሳይ ሲሆን ምክያቶች ፍርድ ቤት ከተለያዩ ሁኔታዎች በመመልከት ሊመዝናቸው የሚገባቸው ሲሆን የድንጋጌው ቅርፅ ፥ ይዘትና መንፈስ በሁኔታዎች ግምት የመውሰድ ያለመውሰድ ጉዳይ የስር ፍርድ ቤት ሥልጣን(ዲስክሬሺን) መሆኑ ያሳያል። በአመልካቾች የተመሰረትው ክስ ሊያስከትል ከሚችለው የእስራት ቅጣትና ገንዘብ መቀጮ ከባድ በመሆኑ፥ ምስክሮች የማባባልና የማጥፋት ዕድል አመልካች ሊሰሩ የሚችሉባቸው ሁኔታዎች በመኖራቸው ግምት መውሰዱ ለፍርድ ቤት የተከለከለ አይደለም። ግምት መውሰድ ፍርድ ቤት ስልጣን ነው። ግምት በቂ ነው ወይስ አይደለም የማስረጃ ምዘና ነው። መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ውሳኔ የሰጠበት። ➽ቅፅ 20 ሰ/መ/ቁ 131863 የወ/መ/ሾ/ሾ/ህ/ቁ 67(ሀ) ድንጋጌዎች ቋሚ የመኖሪያ ቤት ባለመኖሩ ምክንያት በተለያዩ ጊዜ የተለያየ ቦታ እየተዘዋወረ ቤት እየተከራየ መኖሩን መነሻ በማድረግ ብቻ ተከሳሹን የዋስትና መብቱ መንፈጉ ታስቦ የተደረገ ድንጋጌ አይደለም። ➽ሰመ/ቁ 253740 የተከሰበበት ወንጀል ከባድ ነው የሚጣልበትን ቅጣት ፈርቶ በቀጠሮ ቀን ላይቀርብ ይችላል በሚል ግምት ብቻ የዋስትና መብት መከልከል ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ። በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ ጥያቄ ተቀባይነት ከሚያጣባቸው ምክንያቶች አንዱ አመልካቹ በዋስትና ወረቀት የተመለከቱትን ግዴታዎች የሚፈጽም የማይመስል የሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ በአንቀጽ 67(ሀ) ሾር ተደንግጓል፡፡ ፍርድ ቤቶች በዚህ ምክንያት ዋስትና መከልከል የሚችሉበት ምክንያት በህጉ ላይ በግልጽ አልተመለከተም፡፡ ይሁንና ድንጋጌው ፈቃጅ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ከድምዳሜ ሊደርስ የሚችለው በዘፈቀደ ሳይሆን በቂ ምክንያትና መረጃ ላይ ተመስርቶ መሆን። ቅጣትን መፍራት በተከሳሹ ላይ ብቻ የተለየ ባህርይ ነው በማለት የሚያስችል በቂ መነሻ የለም፡፡ ይህም ቢሆን የዋስትና ግዴታውን ያከብድ እንደሆን እንጂ ዋስ መብቱን ለመንፈግ በቂ ምክንያት አይደለም፡፡ ግዴታውን አክብሮ አይቀርብም ለማለት የሚያስችል ሌላ በቂ ምክንያት በሌለበት ቅጣቱ ከባድ ነው በሚል መነሻ ብቻ ዋስትና መንፈግ ተገቢነት የለውም፡፡ ➽ሰመቁ 273144 እና ሰመ/ቁ 29430 በተከሳሹ ላይ ምስክር የሚሆነውን ሰው ማንነቱ ታውቆ ለፖሊስ የምስክር ቃል ሰጥቶ እያለ ምስክር ሊያባብል ይችላል ተብሎ ዋስትና መብት ሊነፈግ እንደማይገባ። በዋስትና ቢወጣ የዋስትና ግዴታውን አክብሮ ሊቀርብ የማይችል ስለመሆኑ በቂና ሕጋዊ ሊባሉ የሚችሉ ከባቢያዊ ሁኔታዎች ሳያመላክት ወንጀሉ የተፈፀመበት ሁኔታና ክብደት በአኳያ በዋስትና ቢወጡ ይመለሳሉ የሚል እምነት የለኝም በሚል የሚሰጥ የዋስትና ክልከላ ንፁህ ሆኖ የመገመት መብታ የሚጋፋ በመሆኑ ግምቱ ህጋዊና በቂ ምክንያት የሚባል ስላለመሆኑ። ➽ያልታተመ ሰ/መ/ቁ 233903 አመልካች የተከሰሰበት ወንጀል አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 168(2) ድንጋጌ ዋስትነ የማይከለክል ነው። ፍርድ ቤቶች የተከሳሽ የዋስትና መብት ለመከልከል የሚችሉት በዘፈቀደ ሳይሆን ተከሳሹ የዋስትና ግዴታውን አክብሮ ሊቀርብ አይችልም ለማለት በቂና አሳማኝ ምክንያት በተገኘ ስለመሆኑ ። የተከሰሰበት ወንጀል ኮንትሮባንድ ነው፥ የመኖሪያ አድራሻው ሌላ ቦታ ነው፥ የሥራ ሁኔታው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያንቀሳቅስ ነው በማለት ዋስትና መብት መከልከል አይቻልም። ↪️ ሰመ/ቁ 275196 ተደራራቢ ክሶቸ በመቅረባቸው ብቻ የዋስትና መብት የሚያስነፍግ አለመሆኑ። 👇👇👇 https://t.me/ethiolawtips

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи