tgindex
Min Keman ምን? ከማን?

Min Keman ምን? ከማን?

Статистика

ይህ ትኩረቱን በጥራት እና ግብይት ላይ አድርጎ፣ ጥራትን በማህበረሰቡ ዉስጥ ባህል እንዲሆን በማድረግ የተቃና የግብይት ስርዓት ለመፍጠር የሚሰራ ማህበራዊ የሬዲዮ ፕሮግራም እና መጽሔት ዝግጅት ክፍል ነዉ። (በትርታ FM 97.6) ለተጨማሪ መረጃ፦ +251978111281

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
33
Всего постов
138
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
1 422
0 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
191
40 постов
Вовлечённость
13,4%
к подписчикам
Постов в день
4,7
всего 138
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
194
1/48двое суток
222
1/72трое суток
239

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የኢትዮጵያ ቡና 1 ኪ.ግ በ2,275 ዶላር ተሸጠ። =========================== በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው “ሶሊሞ ሶርሲንግ ሻንጋይ ኩዌይ” የዓለም አቀፍ የቡና ጨረታ ላይ የኢትዮጵያ ልዩ ቡና አዲስ የዓለም የዋጋ ሪኮርድ በማስመዝገብ በታሪክ ያልታየ ከፍተኛ ዋጋ አገኘ። በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አንድ ኪሎግራም የኢትዮጵያ ቡና በ2,275 የአሜሪካ ዶላር (ከ364 ሺህ የኢትዮጵያ ብር በላይ) በመሸጥ የኢትዮጵያ የቡና ክብርን ከላይ ሰቅሎታል። ይህን ታሪካዊ ዋጋ ያወጣው ቡና በሲዳማ ክልል በንሳ በተባለው አካባቢ በአርሶ አደሮች በጥንቃቄ የተመረተ ሲሆን በዘመናዊው “አናኢሮቢክ” የማቀናበሪያ ዘዴ ተዘጋጅቶ ለገበያ የቀረበ ነው። ቡናው ያለው ተፈጥሯዊ ጣዕም፣ ልዩ መዓዛና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ በጨረታው ላይ በተገኙ የዓለም አቀፍ ቡና ገዢዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን የሀገራችንን ቡና አምራቾች የላቀ #ጥረት እና የኢትዮጵያን የቡና ገበያ ገናናነት በዓለም አቀፍ ደረጃ በድጋሚ ያረጋገጠ መሆኑን የዘገበው ስፑትኒክ ነዉ። #ምንከማን #minkeman #getutemesgen #Addisabab #Ethiopia #Quality #Marketing Telegram: t.me/minkeman Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL Tiktok: tiktok.com/@minkemand YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

  • 🧾ገላጭ ጽሑፎችን ማረጋገጥ 🍒የታሸገ የወይራ ፍሬ ምርት በምንገዛበት ወቅት በማሸጊያው ላይ፦ የምርት ስም፣ የወይራ ፍሬ ዓይነት፣ የአምራቹ ስም፣ የተመረተበት ቀን፣ የምርቱ የመጠቀሚያ ጊዜ የማብቂያ ቀን፣የባች ቁጥር፣ የጥሬ እቃዎች ዝርዝር፣ የአቀማመጥ/የማከማቻ መመሪያ በግልጽ መቀመጡን ማረጋገጥ ይገባል። (በሀብታሙ ጋሻዉ) #ምንከማን #minkeman #Addisabab #Ethiopia #Quality #Marketing Telegram: t.me/minkeman Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL Tiktok: tiktok.com/@minkemand YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

  • #ምን_እንዴት_እንግዛ የታሸገ የወይራ ፍሬ (Packaged Olives) ========================== የታሸገ የወይራ ፍሬ ከወይራ ዛፍ (Olea europaea) የሚገኝ ሲሆን፣ ይህ ዛፍ በሜዲትራኒያን አካባቢ ከሺዎች ዓመታት በፊት ጀምሮ ለተለያዩ የምግብ አይነቶችና ለወይራ ዘይት ማዘጋጃነት ጥቅም ላይ ይውል እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። ሆኖም በቆርቆሮ በማሸግ በኢንዱስትሪ ደረጃ እንዲቀነባበርና ለአብዛኛው ህዝብ እንዲደርስ በማድረግ ረገድ Charles M.Gifford የተባለ በአሜሪካ ካሊፎርንያ ሳንድያጎ የነበረ የወይራ ፍሬ #olive አምራች የሆነ ሰው ስሙ በቀዳሚነት ሲጠቀስ ለዚህም ከሳንድያጎ የግብርና ማህበር በ1902 ሽልማት ተበርክቶለታል። በአሁኑ ወቅት #የታሸገ_የወይራ_ፍሬ አለም አቀፍ የገበያ ድርሻ (2026 ግምት) 2.57 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን በ2032 ይህ የገበያ ድርሻ ወደ 4.2 ቢሊዮን ዶላር ያድጋል ተብሎ ይገመታል። በአሁኑ ወቅት የታሸገ የወይራ ፍሬ በአለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው በዋናነት በፒዛ ዝግጅት ወቅት (በፒዛ ላይ ከላይ በማድረግ) ሲሆን በተጨማሪም በሰላጣ፣ በሳንድዊች፣ በፓስታ፣ በምግብ ማስጌጫ እና በተለያዩ የምግብ ዝግጅቶች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። ⚙️የአመራረት ሂደት 1.ጥሬ እቃ መቀበልና መመርመር 🍒የወይራ ፍሬ ወደ ፋብሪካ ገብቶ ከመቀነባበሩ በፊት በመጀመሪያ የፍሬው የመብሰል ደረጃ፣ ቀለም፣ መጠን፣ የጉዳት እና የመበስበስ ሁኔታ እንዲመረመር ከተደረገ በኋላ የበሰበሰ፣ የተበላሸ፣ በተባይ የተጎዳ ወይም በሻጋታ የተጠቃ ፍሬ እንዲለይ በማድረግ ለቀጣይ ሂደት በሚያመች መልኩ የማዘጋጀት ሂደት ነው። 2. ማጽዳትና መለየት 🍒የወይራ ፍሬው ከቅጠል፣ ከአፈር፣ ከድንጋይ እና ከሌሎች ባዕድ ነገሮች እንዲፀዳ ከተደረገ በኋላ በመጨረሻ የሚመረተው ምርት ተመሳሳይ መጠንና ጥራት እንዲኖረው ለማድረግ ተመሳሳይ መጠን ያላቸው ፍሬዎች በአንድነት እንዲሰበሰቡ ማድረግን ይጨምራል። 3. የመራራነት መቀነስና ማቀነባበር 🍒የወይራ ፍሬ በተፈጥሮው #oleuropein የተባለ መራራ ንጥረ ነገር በውስጡ ስላለው በቀጥታ ለመብላት አይመችም። ስለዚህ እንደ የምርት አይነቱ ፍሬውን በጨው ውሃ ተዘፍዝፎ እንዲፈላ (Ferment) በማድረግ፣ በሶዲየም ሃይድሮክሳይድ እንዲታጠብ በማድረግ እና በሌላ ተገቢ የማቀነባበሪያ ዘዴ መራራነቱን እንዲቀንስ የማድረግ ሂደት ነው። 🍒ይህ ሂደት መራራነቱን ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን የፍሬውን ጣዕምና ለምግብ ተስማሚነት ለማሻሻል ይረዳል። 4. ማጠብና ፍሬው ተዘፍዝፎ የሚታሸግበትን ውህድ (Solution) ማዘጋጀት 🍒መራራነቱን ለመቀነስ የተጠቀምንባቸውን ኬሚካሎች ሙሉ በሙሉ በውሃ በማጠብ እንዲወገዱ ካደረግን በኋላ ምርቱ ታሸጎ የሚቀመጠበት ውህድን ከውሃ ከጨው እና አሲዳማነቱን ለመጠበቅ የሚረዱ ሌሎች ንጥረ ነገሮችን በመጨመር የማዘጋጀ ሂደት ነው #የጨው መጠን፣ pH እና ሌሎች የሂደት መለኪያዎች በተገቢው ደረጃ መቆጣጠር የምርቱን ጥራትና ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ ነው። 5. መሙላት እና ማሽግ 🍒የተዘጋጀውን የወይራ ፍሬ እንደ መጠኑና አይነቱ ከተመደበ በኋላ በቆርቆሮ ማሸጊያ ወይንም በጠርሙስ (glass jar) ወይም በሌላ ለምግብ ተስማሚ ማሸጊያ ውስጥ እንዲሞላ በማድረግ ከላይ የተዘጋጀውን የወይራ ፍሬውን ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ ለረጅም ጊዜ ለማስቀመጥ የሚረዳውን ውህድ በመጨመር የማሸግ ሂደት ነው። 6. በሙቀት ማከም (heat treatment) 🍒ይህ ሂደት በምርቱ ውስጥ ሊያድጉ የሚችሉ ጎጂ ረቂቅ ህዋሳትን ለመግደል/ለማጥፋት በሚያስችል ሳይንሳዊ በሆነ የሙቀት መጠን ለተወሰነ ጊዜ ምርቱ እንዲቆይ በማድረግ ምርቱ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ የማድረግ ሂደት ነው። 7.ማቀዝቀዝ 🍒ከሙቀት ሕክምናው በኋላ በማሸጊያው ላይ የተፈጠረውን ከፍተኛ ሙቀት እንዲወጣ በማድረግ ምርቱ እንዲቀዘቅዝ የማድረግ ሂደት ነው። የማቀዝቀዝ ሂደቱ በትክክል መከናወኑ የማሸጊያውን ሁኔታ እና የምርቱን ጥራት ለመጠበቅ ይረዳል። 📣በግዥ ወቅት መደረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች 1.ገጽታ (Appearance) 💸የታሸገውን የወይራ ፍሬ በጠርሙስ ውስጥ የታሸገ እንደሆነ ጥሩ ብርሃን ባለበት ቦታ ላይ አድርገን ስንመለከተው ምንም ዓይነት የሚሳፈፉ ባእድ ነገሮች የሌሉበት፣ ምንም ዓይነት ሻጋታ የማይታይበት እንዲሁም አረፋማ ወይም ደመናማ ገጽታ የሌለው ንጹህ የሆነና አሻግሮ ማሳየት የሚችል ገጽታ ሊኖረው ይገባል። እንዲሁም በጠርሙስ ውስጥ የሚታይ ምንም ዓይነት ይብዛ የሚፍለቀለቅ ጋዝ (air bubble) መኖር የለበትም የበዛ የጋዝ መፍለቅለቅ የሚታይ ከሆነ ምርቱ በባክቴሪያ መጠቃቱን እና መበላሸቱን የሚያሳይ ነው። 💸በቆርቆሮ የታሸገ እንደሆነ ቆርቆሮ አለመነፋቱን እንዲሁም ቆርቆሮው ምንም ዓይነት ዝገት፣ የፈነዳ እና የሚያፈስ/የሚያዥ ወይንም ደግሞ ወደ ውስጥ በጣም የተጨመቀ/የተጨራመተ አለመሆኑን ማረጋገጽ ይገባል። 💸ቆርቆሮ የተነፋ እንደሆነ ምርቱ በባክቴርያ የተበከለ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ምናልባትም እጅግ በጣም ገዳይ በሆነው closestridium botlinum በተባለው ባክቴሪያ የተጠቃ እና ከላይ ባየነው በሙቀት አማካይነት ባክቴሪያዎችን የመግደል ሂደት በአግባቡ ያላለፈና ለብልሸት የተዳረገ እንደሆነ ማሳያ ነው። 2.. ቀለም (Color) 💸የወይራ ፍሬ ቀለም እንደ ዝርያውና እንደ የማቀነባበሪያ ዘዴው የተለያየ አይነት ቀለም ማለትም አረንጓዴ፣ ጥቁር፣ ቡናማ ወይም ሌላ ተፈጥሯዊ ቀለም ሊኖረው ቢችልም ፍሬውን ግን ስንመለከተው እንደየቀለም ዓይነቱ ወጥ የሆነ ቀለም ሊኖረው ይገባል። ይህም ማለት በአረንጓዴ ፍሬ ላይ በብዙ ቤት ላይ ጥቁር ቀለም ወይንም በጥቁር ፍሬ ላይ በብዙ ቤት ላይ አረንጓዴ ቀለም ልናይ አይገባም። በተጨማሪም በፍሬዎች ላይ ምንም ዓይነት የገረጣ/faded ቀለም እና በፍሬው ላይ የሚታዩ የበዙ ነጠብጣቦች ሊኖሩ አይገባም። 💸ቀለሙን ስንመለከት የፍሬውን ቀለም ብቻ ሳይሆን የወይራ ፍሬው የታሸገበትን ውህድ (brine solution) ቀለም መመልከት ይኖርብናል። ይህ ውህድም በብርሃን ላይ ስናስቀምጠው አሻግሮ ማሳየት የሚያስችልና ምንም ዓይነት ነጭ የሆነ ወይም አረፋማ ቀለም ወይንም የተለየ አይነት ቀለም ሊኖረው አይገባም። 3.የወይራ ፍሬው ጥንካሬና ቅርጽ (Texture) 💸የወይራ ፍሬው ያልተሰባበረ እና ወጥ የሆነ ቅርጹን ጠብቆ ያለ መሆን ይኖርበታል። ከዚህ በተቃራኒ እጅግ ለስላሳ ሆኖ ለመበታተን የተቃረበ ወይንም ደግሞ እጅግ ጠንካራ የሆነ ፍሬ መሆን የለበትም። 4. ሽታ (Odor) 💸ከታሸገበት ማሸጊያ ወይንም ከፍሬው ላይ የሚመጣው ሽታ ለምርቱ የተለመደ እና ንጹህ መሆን አለበት። ከዚህ በተለየ ግን የበሰበሰ፣ የሻጋታ፣ የተቃጠለ፣ እጅግ የሚያስጠላ ወይም ሌላ ያልተለመደ off-odor ካለ የምርቱን መበላሸት የሚያሳይ ነው። 5.ጣዕም (Taste) 💸ጥራት ያለው የወይራ ፍሬ ከምርቱ ዓይነት ጋር የሚስማማ ጣዕም የሚኖረው ሲሆን ከመጠን በላይ መራራ የሆነ፣ የተበላሸ እና የሻገተ የሚመስል ጣእም እና ብረት ብረት የሚል ጣዕም ወይም ሌላ ያልተለመደ ጣዕም ካለ ምርቱ ላይ የጥራት ችግር እንዳለ የሚያሳይ ነው።

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • #እንዲያውቁት #ነዳጅ የሚገኝባቸው ማደያዎች ================== የነሐሴ 8 አርብ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ #ነዳጅ_ማደያ አገልግሎት የሚሰጡ እና በማደያዎቹ በመሰራጨት ላይ ያለው የተሽከርካሪዎች #ናፍጣ እና #ቤንዚን አቅርቦት መጠን መረጃ፤ #ምንከማን #minkeman #addisababa #Ethiopia #Oil #gasstation #HormuzStrait #usa #iran Telegram: t.me/minkeman Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL Tiktok: tiktok.com/@minkemand YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

  • በሚቀጥሉት 10 ቀናት ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል። ========================== የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያስተናግዱ ገለጸ። 🌦በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው ምሥራቅ እና ሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖራቸው በመግለጫው ተመላክቷል። 🌨በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች እርጥበታማ የአየር ሁኔታም ከመጠናከሩ ጋር በተገናኘ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያስተናግዱ ይጠበቃል። 🌨በሰሜን ምሥራቅ፣ ምሥራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። 🌧በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱን አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ ከሚከሰቱት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ጋር ተያይዞ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል። #ምንከማን #minkeman #Addisabab #Ethiopia #Quality #Marketing Telegram: t.me/minkeman Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL Tiktok: tiktok.com/@minkemand YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • #እንዲያውቁት #ነዳጅ የሚገኝባቸው ማደያዎች ================== የነሐሴ 7 ሀሙስ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ #ነዳጅ_ማደያ አገልግሎት የሚሰጡ እና በማደያዎቹ በመሰራጨት ላይ ያለው የተሽከርካሪዎች #ናፍጣ እና #ቤንዚን አቅርቦት መጠን መረጃ፤ #ምንከማን #minkeman #addisababa #Ethiopia #Oil #gasstation #HormuzStrait #usa #iran Telegram: t.me/minkeman Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL Tiktok: tiktok.com/@minkemand YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

  • የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ፍላጎት በግማሽ ያሟላል። ========================== የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ከተመረተው አጠቃላይ 35,671 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ውስጥ፣ ግማሽ ያህሉ ወይም 18,360 ጊጋ ዋት ሰዓት ከህዳሴው ግድብ ብቻ የተመረተ መሆኑን አስታወቀ። ግድቡ በቂ ውሃ በመያዙ እና ተርባይኖቹ ሙሉ አቅማቸውን በመጠቀማቸው የኃይል ምርቱ ከአምናው በ23% አድጓል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሙሉ አቅሙ 5,150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ሀገሪቱን ከቀድሞው በበለጠ እየደገፈ ይገኛል። #ምንከማን #minkeman #SHEGER #Addisabab #Ethiopia #Quality #Marketing Telegram: t.me/minkeman Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL Tiktok: tiktok.com/@minkemand YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

  • የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት (AFRIMETS) https://youtube.com/watch?v=kIkS0dL3eyo&si=uBuSbkcieosdMxOT

  • የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ጥራት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ። ========================== የኢትዮጵያ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሃሰን ቀደም ሲል በነዳጅ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች ላይ ይስተዋል የነበረውን የጥራት ማነስ እና ህገወጥ አሠራር ለመቅረፍ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን አስታወቁ። ሚኒስትር ዴኤታው፤ የዘርፉ አቅርቦት ከዚህ ቀደም ጥራት የጎደለው፣ ለሐሰተኛ ምርቶች የተጋለጠ እና ለተለያዩ ማጭበርበሮች ክፍት ሆኖ መቆየቱን ገልጸዉ ይህንን ችግር ለመቅረፍም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ጠንካራ የአቅርቦት ሰንሰለት ለመዘርጋት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪና የመለዋወጫ አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የሽያጭ ማዕከላትንና የማገጣጠሚያ ተቋማትን እንዲመሠርቱ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ፣ ሃይብሪድ እና የተፈጥሮ ጋዝ ለመቀየር የሚያስችሉ መሣሪያዎችና መለዋወጫዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ የፖሊሲ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል። የከተማ እና የሀገር አቋራጭ ታክሲዎችን ወደ ኤሌክትሪክና ሌሎች ጽዱ የኃይል አማራጮች ለማሸጋገር የሚያስችል ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ሥራ መገባቱንም ሚኒስትር ዴኤታው መናገራቸውን የዘገው ኢትዮ ኤፍ ኤም ነው። #ምንከማን #minkeman #Addisabab #Ethiopia #Quality Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL Tiktok: tiktok.com/@minkemand YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • #እንዲያውቁት የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ መጥታችሁ መውሰድ ትችላላችሁ ተባለ። ========================== በአዲስ አበባ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ፖሊስ መምሪያ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተሽከርካሪ እቃዎችን በመስረቅ የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦችንና የተሰረቁ እቃዎችን ይገዙ የነበሩ 2 ተቀባዮችን በድምሩ 7 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ። ፖሊስ በክፍለ ከተማው በተበራከተው የመኪና እቃ ስርቆት ላይ የተመሠረተ ክትትል ሲያደርግ ከቆየ በኋላ፣ ለአንድ ወር ከ15 ቀን በተካሄደ ምርመራ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል ብሎ የጠረጠራቸውን 5 ግለሰቦች እና የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን ሲገዙ እንደነበር የተረጋጠ 2 ግለሰቦች መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል። በሸገር ሲቲ መልካ ኖኖ ወረዳ፣ አንፎ በሚባል አካባቢ የተሰረቁ የመኪና እቃዎች በሚቀበሉት ግለሰቦች ሱቅ ላይ በሕግ አግባብ በተደረገ ፍተሻ፦ 🚙የተሽከርካሪ ጌጅ 🚙ስፖኪዮ 🚙ዳሽቦርድ 🖨ፎቶ ኮፒ ማሽን 🖥ኮምፒውተር 🔫ሶስት (3) ህገወጥ ሽጉጦችና 2 ጥይቶች 🔪መቁረጫ መሣሪያዎች 🚕ኮድ 2 አ/አ 40817 የሆነ ዴኤክስ ተሽከርካሪ 🚗ኮድ 3 አ/አ 96821 የሆነ ፕላትስ ተሽከርካሪ ተገኝተዋል። 👂እቃዎቻቸው የተሰረቁባቸው ዜጎችም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ዋና ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ የተያዙትን እቃዎች መለየትና የራሳቸውን ንብረት መርጠው መረከብ እንደሚችሉ ፖሊስ አስታውቋል። 👇👇👇 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

  • #የምግብ ዋጋ በ3 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድሱ ተገለፀ። ========================== በግብርና ምርቶች አቅርቦት ላይ እየጨመረ የመጣውን ስጋት ተከትሎ የዓለም የምግብ ዋጋ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ታይቶ ወደማታውቀው ከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡ ተገለጸ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና እርሻ ድርጅት #FAO የምግብ ዋጋ መረጃ ጠቋሚ በሐምሌ ወር 0.6% ማደጉን አስታውቋል። ይህ ጭማሪ በዋናነት እንደ እህል፣ ስኳር እና የአትክልት ዘይቶች ባሉ ቁልፍ የንግድ ዕቃዎች ላይ በታየው ከፍተኛ የዋጋ ንረት የተከሰተ ነው። በጥቁር ባህር ክልል ውስጥ እየተባባሰ የመጣው የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ወሳኝ የኤክስፖርት መስመሮችን በማስተጓጎሉ፣ ዓለም አቀፍ የስንዴ ዋጋ ከዓመት ዓመት በ10% ገደማ እንዲጨምር አድርጓል። በአውሮፓ የከረረ ሙቀት እና በአሜሪካ ኮርን ቤልት አካባቢ ያለው የማያቋርጥ ድርቅ የምርት ማከማቻ አዝማሚያዎችን እየጎዳው ይገኛል። የአቅርቦት ሰንሰለት ተጋላጭነቶች መቀጠላቸው ለገበያ ተንታኞች ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ መጪው ኤል ኒኖ ክስተት፣ ከፍ ያለ የኃይል ዋጋ እና የማዳበሪያ እጥረት ተዳምረው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሸማቾች ላይ ቀጣይነት ያለው የዋጋ ግሽበት ግፊት እንደሚፈጥሩ ተመላክቷል ሲል የዘገው ቅዳሜገበያ ነዉ። #ምንከማን #minkeman #Addisabab #Ethiopia #Quality #Marketing #Inflation Telegram: t.me/minkeman Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61550090741996&mibextid=ZbWKwL Tiktok: tiktok.com/@minkemand YouTube: https://youtube.com/channel/UCS2tkkhphE8qAgM9e2xBR0g?si=A3CoBtFqLLwqfILv

Min Keman ምን? ከማን? — tgindex