THE MUSLIM NEWS
Статистикаወደ The Muslim News Telegram እንኳን በደህና መጡ! በየቀኑ አጫጭር የዜና ጽሑፎች፣ እውነተኛ እና ፈጣን የዜና መረጃዎች እኛ ጋር ያገኛሉ ። ለጓደኞችዎ ማጋራትን አይርሱ። ለማንኛውም ሃሳብ አና አስተያየት @JornalSalah
- Последний пост
- 4 июн. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የ27 ዓመቱ አይርላንዳዊ የMMA ተፋላሚ ፓዲ መኮሪይ በጋዛ ጦርነት ከተሳተፈ እስራኤላዊ ተፋላሚ ጋር በሮማ ተጋጥሞ አሸንፏል። ፓዲ በውድድሩ እስራኤላዊውን ተፋላሚ በሚያጠቃበት ሰዓት "ይህ ለፍልስጤም ሲባል ነው!" እያለ ነበር።ከውድድሩም በኃላ የፍልስጤምን ባንዲራ ክፍ አድርጎ ሲያውለበልብ ታይቷል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🕋 የሐጅ መረጃ፡ ሚሊዮኖች በሐጅ ዋዜማ በሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ ለመሳተፍ ከመላው ዓለም ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ የሚጓዙ ምዕመናን መግባት ቀጥለው በክንውኑ ዋዜማ ላይ ደርሰዋል። ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው፣ እስከ ሰኞ ድረስ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ገደማ ምዕመናን ሳዑዲ ገብተዋል። በዘንድሮ ሐጅ በቁጥር ከፍተኛውን ምዕመናን የላከችው እንደ ቀዳሚዎቹ ዓመታት ሁሉ ኢንዶኔዥያ ሆናለች። ሀገሪቱ 221 ሺሕ ኮታ ለሥነ ሥርዐቱ ብትቀበልም በቂ ባለመሆኑ ለቀጣዩም ዓመት በርካታ ሺሕዎች ተመዝግበው ተራ እየጠበቁ እንደሚገኙ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በተከታይነት ፓኪስታን 180 ሺሕ፣ ሕንድ 175 ሺሕ 25፣ ባንግላዴሽ 127 ሺሕ 198፣ ናይጄሪያ 95 ሺሕ፣ ኢራን 87 ሺሕ 550፣ አልጄሪያ 41 ሺሕ 300፣ ቱርክ 37 ሺሕ 770፣ ግብፅ 35 ሺሕ 375 እና ሱዳን 32 ሺሕ 200 ምዕመናን በመላክ እስከ አስረኛ ደረጃ መቀመጣቸውን የዘገበው አቪዬሽን ኤቱዜድ ድረ ገጽ ነው።
🕋 የሐጅ መረጃ፡ ሚሊዮኖች በሐጅ ዋዜማ በሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ ለመሳተፍ ከመላው ዓለም ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ የሚጓዙ ምዕመናን መግባት ቀጥለው በክንውኑ ዋዜማ ላይ ደርሰዋል። ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው፣ እስከ ሰኞ ድረስ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ገደማ ምዕመናን ሳዑዲ ገብተዋል። በዘንድሮ ሐጅ በቁጥር ከፍተኛውን ምዕመናን የላከችው እንደ ቀዳሚዎቹ ዓመታት ሁሉ ኢንዶኔዥያ ሆናለች። ሀገሪቱ 221 ሺሕ ኮታ ለሥነ ሥርዐቱ ብትቀበልም በቂ ባለመሆኑ ለቀጣዩም ዓመት በርካታ ሺሕዎች ተመዝግበው ተራ እየጠበቁ እንደሚገኙ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በተከታይነት ፓኪስታን 180 ሺሕ፣ ሕንድ 175 ሺሕ 25፣ ባንግላዴሽ 127 ሺሕ 198፣ ናይጄሪያ 95 ሺሕ፣ ኢራን 87 ሺሕ 550፣ አልጄሪያ 41 ሺሕ 300፣ ቱርክ 37 ሺሕ 770፣ ግብፅ 35 ሺሕ 375 እና ሱዳን 32 ሺሕ 200 ምዕመናን በመላክ እስከ አስረኛ ደረጃ መቀመጣቸውን የዘገበው አቪዬሽን ኤቱዜድ ድረ ገጽ ነው።
видео или голосовое, без подписи
የመጨረሻዉ ሆስፒታል ስራዉን አቆመ። በሰሜን ጋዛ የመጨረሻው ሆስፒታል በእስራኤል ትዕዛዝ ስራዉ ለማቆም መገደዱ ተገለፀ። በሰሜን ጋዛ ግዛት የመጨረሻው የጤና አገልግሎት የሚሰጠው ሆስፒታል የእስራኤል ጦር በአስቸኳይ እንዲለቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ ከአገልግሎት ውጪ መሆኑን የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ እንዳሉት ህሙማን ጃባሊያ ከሚገኘው አል-አውዳ ሆስፒታል ወደ ሌላ ስፍራ ተወስደዋል። እስራኤል እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠችዉ ምላሽ ባይኖርም በሆስፒታሉ ያሉ ሰዎች የእስራኤል ጦር ሃይል ሊሰነዝረዉ በሚችለዉ ጥቃት ፈርተዉ መሸሻቸዉን ተናግረዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ባለፉት ሁለት ሳምንታት የቀጠለው ግጭት ሆስፒታሉን ጎድቷል፣ ተደራሽነቱን አቋርጧል ብሎም ህሙማን ህክምና እንዳያገኙ አድርጓል። ከ27 የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም የስደተኞች ኤጀንሲ ጤና ጣቢያ ዘጠኙ በስራ ላይ እንደነበሩ ተመላክቷል። ኤጀንሲዉ ጋዛን "በምድር ላይ እጅግ የተራበች ቦታ" ሲልም ጠርቷል። እስራኤል በተያዘዉ የፈረንጆቹ አመት የሁለት ወራት የተኩስ አቁም ስምምነት ካደረገች በኋላ ጥቃቷን በጋዛ አጠናክራ ቀጥላለች። ዘገባዉ የቢቢሲ ነዉ
видео или голосовое, без подписи
የሊቨርፑል ደጋፊዎች የፍልስጤምን ባንዲራ እያውለበለቡ የክለባቸውን የፕሪሚየር ሊግ ድል አከበሩ። የሊቨርፑል ደጋፊዎች የእግር ኳስ ክለባቸውን የፕሪሚየር ሊግ ድል ለማክበር ጎዳናዎች በወጡበት ወቅት፣ ብዙዎች ከጋዛ ጋር ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት የፍልስጤም ባንዲራዎችን ሲያውለበልቡ ታይተዋል። እ.ኤ.አ. በጥቅምት 7 ቀን 2023 እስራኤል በጋዛ ላይ ጦርነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ የእግር ኳስ ደጋፊዎች አጋርነታቸውን ለማሳየት እና እስራኤል በጋዛ ላይ በምትፈጽመው ጥቃት ምክንያት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የበለጠ ከባድ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት ለማድረግ የፍልስጤም ባንዲራዎችን ወደ ስታዲየሞች ይዘው መጥተዋል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በጋዛ 13,901 ሴቶች ባሎቻቸውን በጦርነት ማጣታቸው፣ 6600 ፍልስጤማውያን በእስራኤል መታገታቸው፣ 12,800 ተማሪዎች መገደላቸው ተነገረ። እስራኤል እስካሁን በጋዛ ላይ አደረሰችው በተባለው ጥቃት ከ54,000 ሟቾች መካከል፣"70% ጥቃት ደርሶባቸው የተገደሉ ናቸው" ተብሏል። እንዲሁም በጦርነቱ፣ "1,155 የህክምና ባለሙያዎች፣ 94 ጋዜጠኞች። 736 የጋዛ ፓሊስ አባላት ተገድለዋል። "6600 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ታግተዋል። 12,800 ተማሪዎች ተገድለዋል። 910 መምህራን፣ ሳይንቲስቶችና የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች ህይወታቸው አልፏል። 981 መስጊዶች ወድመዋል። 216 የመንግስት ቢሮዎች ፈራርሰዋል። 276 ሆስፒታሎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። 136 አምቡላንሶች ተቃጥለዋል። 100,000 ቶን ቦምብ ፍንዳታዎች ተፈፅመዋል" ተብሏል። @ThiqahEth
видео или голосовое, без подписи
በጋዛ የሟቾች ቁጥር 54,000 እንደደረሰ፣ 38,495 ህፃናት ያለ አሳዳጊ በጋዛ እንደሚገኙ ተገለጸ። እስካሁን በእስራኤል ጥቃት በጋዛ ስለደረሰው ጉዳት ቁጥሮች ምን አሉ? "ጦርነቱ ከተጀመረ ከኦክቶበር 07/2023 በኋላ፣ በጋዛ የሟቾች ቁጥር 54,000 ደርሷል። ከእነዚህ መካከል 17,861 የሚደርሱት ህፃናት ናቸው። 123,308 ፍልስጤማውያን ቆስለዋል፣ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከእነዚህ መካከል 15,000ዎቹ የረጅም ጊዜ ማገገሚያ የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፣ 12,700 የሚሆኑት ደግሞ ከሀገር ውጭ መታከም አለባቸው። 10,100 ሰዎች ደግሞ የግፍ ጭፍጨፋ ደርሶባቸዋል። ከ2000 በላይ ቤተሰብ ተበትኗል" ነው የተባለው። "38,495 ህፃናት ያለ አሳዳጊ በጋዛ ይገኛሉ" ተብሏል።
በዓለም ጤና ድርጅት የጄኔቫ ዋና ጽ/ቤት የፍልስጤም ሰንደቅ ዓላማ እንዲውለበለብ ውሳኔ ተላለፈ። የዓለም ጤና ድርጅት የፍልስጤም ሰንደቅ ዓላማ በጄኔቫ ዋና ጽ/ቤት እንዲውለበለብ የሚደግፈውን የውሳኔ ሐሳብ በአብላጫ ድምጽ ያጸደቀው ማክሰኞ እለት ባካሔደው ስብሰባ ነው፡፡ የውሳኔ ሐሳቡ ከአባል ሀገሮች መካከል 95 ድጋፍ ሲያገኝ፣ እስራኤልን ጨምሮ አራት ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ የድጋፍ ድምጽ ከሰጡት ውስጥ በቀጣይ ሰኔ ወር ለፍልስጤም ሀገረ መንግሥት ዕውቅና እንደምትሰጥ ያሳወቀችው ፈረንሣይ እና ጃፓን ይገኙበታል፡፡ ከእስራኤል ጋር የወገኑት ደግሞ ሐንጋሪ፣ ቼክ ሪፐብሊክ እና ጀርመን ናቸው፡፡ 27 ሀገሮች ድምጽ ተዐቅቦ በሰጡበት የውሳኔ ሐሳብ፣ ከድርጅቱ እየለቀቀች የምትገኘው ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህኛው ምድብ ውስጥ መካተቷን የፍልስጤም ዜና አገልግሎት ዋፋ ዘግቧል፡፡ ከውሳኔው በኋላ የተናገሩት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፍልስጤም ቋሚ መልዕክተኛ ኢብራሂም ኽራይሺ፤ ውሳኔው “ተምሣሌታዊ ከመሆኑ በተጨማሪ ለጤና ጉዳዮች አስተዋጽኦ የምናበረክት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አካል መሆናችንን የሚያረጋግጥ ነው” ብለውታል፡፡ ክራይሺ አክለውም ፍልስጤም በቅርቡ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሁሉም የተባበሩት መንግሥታት መድረኮች ውስጥ ሙሉ አባልነት ታገኛለች የሚልተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አባል ከሆኑት 193 አገራት መካከል 150 ገደማ ሀገሮች የፍልስጤምን ሀገርነት በይፋ ዕውቅና ሰጥተዋል። ሆኖም በምክር ቤቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ካላቸው መካከልዩናይትድ ስቴትስ እና ብሪታንያ እስካሁን ድረስ ዕውቅና አልሰጡም፡፡ #ሚንበር_ቲቪ
በሂጅሪ ዘመን ቀመር የተከታዩ ዙል ሒጃ ወር አዲስ ጨረቃ መታየቱ በሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ባለሞያዎች በመረጋገጡ ዛሬ ማክሰኞ 11ኛው የዙል ቀዕዳህ ወር በ29ኛ ቀን ተጠናቋል። በዚህም መሠረት ነገ ረቡዕ የቀጣዩ ወር የመጀመሪያ ቀን ሆኖ ይውላል። የዘንድሮ ዒድ አል አድሐ በዓል ደግሞ በሚቀጥለው ሣምንት ጁመዓ ግንቦት 29/2017 ተከብሮ የሚውል ይሆናል። (ሚንበር ቲቪ)
видео или голосовое, без подписи
የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ በጋዛ አንዲት ሕጻን ልጅ ከእሳት ለማምለጥ የምታደርገው ልብ ሰባሪ ጥረትን የሚያሳይ ቪዲዮ በ ማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ ዓለምን አሳዝኗል። የ5 ዓመቷ ህፃን እስራኤል በጋዛ ከተማ የትምህርት ቤት መጠለያ ላይ ባደረሰችው ከባድ ጥቃት ከእሳት ሞት ተርፋለች።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи