- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 44
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 13
- 1/48двое суток
- 14
- 1/72трое суток
- 16
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
22 አሁንም ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ አለችው። 23 ኢየሱስም፦ ወንድምሽ ይነሣል አላት። 24 ማርታም። በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንዲነሣ አውቃለሁ አለችው። 25 ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ 26 ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።
5 ኢየሱስም ማርታንና እኅትዋን አልዓዛርንም ይወድ ነበር። 6 እንደ ታመመም በሰማ ጊዜ ያን ጊዜ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ፤
4 ኢየሱስም ሰምቶ። ይህ ህመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ።
“ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋራ ትልቅ ትርፍ ነው።” 1 ጢሞቴዎስ 6 : 6 @kaluproject
mattew 6:-25-34
25 ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን? 26 ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን? 27 ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? 28 ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ 29 አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም። 30 እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? 31 እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ 32 ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። 33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። 34 ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።
ክብር ይሁን ክብር Geja KHC 'A' Choir ⌚️10:32 ደቂቃ | 💾 °.°𝙢𝙗 #react አድርጉት (👍🥰❤😍🔥 ) sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯 Facebook | Telegram | Youtube | Instagram | Tiktok | X(Twitter) | sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
የህይወት ምንጭ ኢየሱስ ሁልጊዜ አመልክሀለሁ
ዕዝራ 7፡10 እና ዕዝራ 7፡25
25 አንተም ዕዝራ፥ በእጅህ እንዳለው እንደ አምላክህ ጥበብ መጠን በወንዝ ማዶ ባሉ ሕዝብ ሁሉ የአምላክህን ሕግ በሚያውቁ ሁሉ ላይ ይፈርዱ ዘንድ ዳኞችንና ፈራጆች አስነሣ የማያውቁትንም አስተምሩአቸው።
10 ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።
የተሐድሶው መሪ ማርቲን ሉተር እና ጸሎት ማርቲን ሉተር በየቀኑ ከ2 እስከ 3 ሰዓታት የመጸለይ ልማድ ነበረው። የሥራና የአገልግሎት ጫና በበዛበት ጊዜ እንኳን ሳይቀር ጸሎቱን አያቋርጥም ነበር። በአንድ ወቅት እንዲኽ ማለቱ ይነገርለታል፦ "ዛሬ ብዙ የማከናውናቸው ሥራዎች ስላሉብኝ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ሰዓታት በጸሎት ማሳለፍ አለብኝ።" ማርቲን ሉተር ጸሎቱ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነበር ማለት ይቻላል። መዝሙረ ዳዊትንና የጌታን ጸሎት በየቀኑ ይጸልይ ነበር። በየመሐሉም የራሱን ጸሎት እያስገባ እንደማሳረጊያም የጌታን ጸሎት(አባታችን ኾይ) ይጸልይ ነበር። ማርቲን ሉተር Peter Beskendorf የሚባል ጸጉር አስተካካይና ወዳጅ ነበረው። እናም ስለ ጸሎትና የጸሎት ዘዴ ደብዳቤ ጽፎለት ነበር። በዛ ደብዳቤውም ITCP ብሎ የጠራውን ዐራት ቀለል ያሉ ዘዴዎችን አስተምሮት ነበር። ይኽም ዘዴ የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት ወደ ጸሎት እንደምንቀይርና ቃሉን ለማሳላሰል የሚጠቅመንን ዘዴ ጠቁሞታል። 🔥 I= Instruction= ባነበብኩት ክፍል ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ራሴ ወይም ስለ ሕይወት ያገኘኹት ትምህርት ወይም መመሪያ ምንድን ነው? 🔥 T= Thanksgiving= በዚኽ ክፍል እግዚአብሔርን የማመሰግንበት ነገር ምንድነው? 🔥 C= Confession= ይኽንን ቃል የተላለፍኩበትና ጌታን ያሳዘንኩበት ድካሜ፣ ኃጢአቴ ምንድን ነው? 🔥 P= Prayer= በዚኽ ቃል መሠረት እግዚአብሔር ምን እንዲያደርግልኝ እፈልጋለኹ? እያሉ ቃሉን መሠረት አድርጎ በመጸለይ አሰልቺነትንና ድግግሞሽ ማስቀረት እንደሚቻል አስተምሮታል። ይኽንን የማርቲን ሉተር ዘዴን እንዴት እንደምንጠቀም በምሳሌ እንመልከተው። ምንባብ፦ መዝሙር.23:1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፣ የሚያሳጣኝም የለም ITCP በቅደም ተከተሉ መሠረት፦ I= Instruction= ያገኘኹበት ትምህርት፦ እግዚአብሔር እኔን የሚያስብ፣ የሚመራኝና የሚያስፈልገኝን ኹሉ የሚያሟላ ታማኝ እረኛዬ እንደኾነ ያስተምረኛል። T= Thanksgiving= ምስጋናዬ "አምላኬ ኾይ! እስከ ዛሬ ድረስ እረኛዬ ኾነኽ ስለጠበቅኸኝ፣ ሳልጠይቅኽ እንኳ የሚያስፈልገኝን ስላሟላኽልኝ አመሰግንኻለኹ።" C= Confession= ኑዛዜዬ "ጌታ ሆይ! አንተ እረኛዬ ኾነህ ሳለኽ፣ ብዙ ጊዜ በጭንቀትና በፍርሃት ስወደቅ፣ በአንተ ከመደገፍ ይልቅ በራሴ ጥረት ብቻ ለመቆም ስሞክር የነበረኝን እምነት በማጣት ስላሳዘንኩኽ ይቅር በለኝ" P= Prayer= ልመናዬ "አምላኬ ኾይ! በየቀኑ በምኼድበት መንገድ ኹሉ አንተን እረኛዬ አድርጌ እንድከተልህ፣ በነገሬ ኹሉ በአንተ እንድታመንና ሰላምኽን እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ" (እናንተም እስኪ አንድ ጥቅስ ውሰዱና በITCP ዘዴ ጸልዩ።) ማርቲን ሉተር ጸሎትን ከግንኙነት ይልቅ እንደ አንድ መፈጸም እንደሚገባን ሥርዐት ብቻ እንዳናየው ያስተምር ነበር። ቃላትን በማብዛት የሚደረግ ረጃጅም ጸሎትን አይደግፍም ነበር። ይልቁንም ጸሎት አጭር፣ ትኩረት ያለው እና ከልብ የመነጨ መኾን እንዳለበት ያምን ነበር። ምንጭ ✍ አገልጋይ ብርሃኑ 🗓 ሐምሌ 16/2018 የጌታ ዓመት
አምላኬ መልዐኩን ልኮ በወንድም አወቀ ገብሬ ህያው ተስፋ ሬዲዮ
When God shows us only the next step and not the whole picture, know that God loves us to lead near enough to walk beside us. Let’s take a step in faith on steps we can see and trust Jesus for the steps we can’t see. When darkness is all around us, the word of the Lord, the Bible, like a flaming torch, reveals our way #jesuslovesyou #JesusisGod #trustJesus #readBible
@kaluproject
ምን አለ ከዚህ በላይ ፍቅር
በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው። 1st timoty 4:12
https://youtu.be/XWPIB2i_bVw?si=-W7pow-MX1jWuSoM
9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ 10 በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።
3-4 ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 5 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ 6 ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤