tgindex
Wilaya Institute™

Wilaya Institute™

Статистика

"ሁለንተናዊ እነፃ!" ስለተቀላቀላችሁን ደስታችን እጥፍ ነው!❤️ በዚህ ቻናል ፦ 📍 "Reflection On Book" ብለን የሳይኮሎጂን መጽሐፍት በኢስላም እንቃኛለን 📍 በየ ንጋቱ የጠዋት መልዕክቶችን በድምፅ ያገኛሉ። 📍ፀጋን ሚያስታዉሱ እውነታዎችን ያገኛሉ። 📍ራስ ግንባታ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ይወስዳሉ። Know That You're the Loved and Choosen Soul.!።❤️

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
610
+8 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
293
20 постов
Вовлечённость
48,0%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
61
1/48двое суток
69
1/72трое суток
75

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በ ኸሚሱ ምሽት የረቢዕ ሽታ ሲነፍስ....

  • Come, come, whoever you are. Wanderer, worshipper, lover of leaving, it doesn't matter. Ours is not a caravan of despair! Come, even if you've broken your vows a thousand times. Come. Come yet again. Come. — Rumi

  • https://t.me/Nur_media26?livestream=cd0851960af44b0fa9

  • ከሽኝቶች ኹሉ እጅግ ከባዱ ሽኝት....🥹 ወደ ሰይዳችን ﷺ ቤት የተጠራን ስው መሸኘት ነው...🥹🤲 አላህ ይህን ነገር ተመልክቶ ላነበበ ሁሉ ይወፍቀው🤲

  • ብዙዎችን ሸኝተሃል! እስካሁን ድረስ ግን በዱንያ ውስጥ እንግዳ መሆንህን አልተረዳህም!?…

  • ይህን ስትሰሙ ምን ትዝ ይላችኋል?🥹 ትዝታ....

  • አላህ ሆይ...🤲 ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ብለን ከምንዘናጋው አታድርገን🤲፡፡ ካንተው ጀነት የበለጠ ጥሩ ቦታ የለምና... አባታችን አደም በሷ ዉስጥ ሆነው ጭምር ፈተና አግኝቷቸው የለ?🥹 በዒባዳችን ብዛትም ምንጃጃል አታድርገን🤲 ኢብሊስ ከዚያ ረጅም የዒባዳ ሕይወት በኋላ ምን እንዳጋጠመው አይተን የለ...🥹 ያ ረብ...

  • ኢላሂዋ...!! እኛን ለእኛ የተውከን ዕለት ነው አበቃልን የምንለው። እኛን ለእኛ የተውከን ዕለት ነው መሞታችንን የምናረጋግጠው። የፈለገ ነገር ቢመጣ እዚህች ሀገር ላይ በፍፁም እኛን ለእኛ አትተወን ፣ ከእቅፎችህ ዉስጥ አድርገን ፣ እጃችንን ይዘህ ካለንበት አውጣን ፣ ወደ ተወዳጁ ስፍራህም የተሳብን አድርገን!

  • ኢላሂ! ~ ባንተ ታውቀን ባንተ ከሚያምፁት አታድርገን፣ለሰው ጠቁመን ተቃራኒውን ከሚጓዙ አታድርገን፣ በአፍ ቀርበውህ በተግባር ከሚርቁህ አታድርገን፣ በምላስ ከሚያመልኩህ በልቦና ከሚሸሹህ አታድርገን፣አለባበሣችንን እንዳሳመርክ ዉስጣችንን አሳምርልን!

  • በማለዳችሁ ይህቺን ያዙባት ሰይዲና ዓሊይ (ረ.ዐ) ይህችን ስንቅ ይቋጥሩልናል። “በእርሱ እና በአላህ ﷻ መሃል ያለዉን ያስተካከለ ፤ በእርሱ እና በሰዎች መሃል ያለዉን አላህ ﷻ ያስተካክልለታል። የአኺራዉን ጉዳይ ያስተካከለ ፤ አላህ ﷻ የዱንያዉን ጉዳይ ያስተካክልለታል። በነፍሱ ዉስጥ ተቆጣጣሪ (አስጠንቃቂ) ያለው ሰው ፤ ከአላህ ደግሞ ጠባቂን ይኖረዋል።” ምን ያምር ንግግር...🤌🤍

  • ይህን ቀን እዚያው ባህሩ ደጅ እንደሆንን አድርገን እስኪ እናስበው...? كَلَّآۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهۡدِينِ «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» እንዴት የሚያምር አንቀፅ መሰላችሁ... እስኪ እናስተንትነው...? 📌 የቆሙ ሰዎች እንዳያቆሙህ ትምህርት ይሰጥሃል!! አንዳንድ ሰዎች የሚተቹ ቃላትን መሰንዘር ልማድ ይሆንባቸዋል ፤ ምንም ሳይሰሩ በሚሰራው…

  • ይህን ቀን እዚያው ባህሩ ደጅ እንደሆንን አድርገን እስኪ እናስበው...? كَلَّآۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهۡدِينِ «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» እንዴት የሚያምር አንቀፅ መሰላችሁ... እስኪ እናስተንትነው...? 📌 የቆሙ ሰዎች እንዳያቆሙህ ትምህርት ይሰጥሃል!! አንዳንድ ሰዎች የሚተቹ ቃላትን መሰንዘር ልማድ ይሆንባቸዋል ፤ ምንም ሳይሰሩ በሚሰራው ሰው ቦታ ላይ ሳይቀመጡ በእርሱ ሚዛን የመመዘን ብቃቱም ሳይኖራቸው አንተ እኮ አትችለዉም ይሉሃል! ይሉሻል! ልክ ያን የአላህ ባርያ ሙሳን (ዓ.ሰ)... "ከባህሩ አጋፈጥከን ከጀርባ የሰራዊት ዶፍ እየመጣ ነው! በቃ እኮ አለቀልን ምን ልታደርገን ነው ከዚህ በላይ...!?" ብለው በዉስጡ ያለዉን የእምነት ጥንካሬ ታሳቢ ባለማድረግ ተስፋ እንደቆረጡበት ማለት ነው... ግን እርሱ ምን አለ...? "ጥሎ ማይጥለው ከኔ ጋር ነው እኔ ማየዉን እያያችሁ አይደለም ጌታዬ ሚሰራልኝን ታያላችሁ ቆማችሁ አትፍረዱኝ...!!" አለ

  • Wilaya Institute™ pinned a photo

  • وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِيرٖ "እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡" Al-Qur'an 35:14 እንዴት የሚያምር አንቀፅ መሰላችሁ... እስኪ እናስተንትነው...? ሙሀረም ዘጠኝ ነገ ማለትም ረቡዕ ፣ አሹራ ሀሙስ ሲሆን ጁምዐ ደግሞ አስራ አንደኛው ቀን ሆኖ ይውላል ሌሎችንም በማስታወስ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን።🤍

  • https://t.me/Nur_media26?livestream=ac098ff3166a531eaf

  • https://t.me/Nur_media26?livestream=ac098ff3166a531eaf

  • አሁንም እናስታዉስ...! ስናነጋ ምናነጋው በጌታችን አላህ ﷻ ፀጋ ነው። አመስግን! የበረካ ዉሎ ይሁን🤲

  • የአላህ ነቢይ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ሙሃጂር ማለት አላህ የከለከለውን ነገር የተወ ሰው ነው።»

  • የትልቅ ስኬት መነሻ ጥልቅ ፍላጎት ነው! ይሄን ሁሌም በአዕምሯችን ማሰብ አለብን፤  ብዙም ያልተቀጣጠለ እሳት ብዙ ሙቀት እንደማይሰጠን ሁሉ ደካማ ፍላጎትም ደካማ ውጤት ነው የሚሰጠን። ሁሌም የማይበርድ ፍላጎት የማይቋረጥ ፅኑ መሻት ያስፈልገናል! አላህም የዚያን ጊዜ ነው የእገዛ እጁን ከምን ጊዜዉም በላይ ሚዘረጋልን። ይህን ለመረዳት ሰይዳችን ﷺ የበድርን ጦርነት ለማሸነፍ ምን ያህል ፍላጎት እንደነበራቸው ፣ ህዝባቸዉንም ሆነ ከሳቸው በኋላ ሚመጣዉን ትውልድ ወደ ከፍታው ለማድረስ ምን ያህል የተቀጣጠለ እሳት ዉስጣቸው እንደነበር ማየት ብቻውን በቂ ነው!። ለአዲሱ ዓመተ ሂጅራ ቀጣይ ጉዞ ምን ግብ ቀርፀናል? 📲 @On_wilaya

  • የሂጅራው ሌላኛው ገጽታ፡ ከለመዱት ነገር መላቀቅ እና የስነ-ልቦና ጉዞ 🌙✨ "ሂጅራ" (ስደት) ስንል ወደ አእምሯችን ፈጥኖ የሚመጣው ከመካ ወደ መዲና የተደረገው የቦታ ሽግግር ነው። ነገር ግን ከዚህ አካላዊ ጉዞ በስተጀርባ፣ እጅግ ጥልቅ እና ፈታኝ የሆነ "የስነ-ልቦና ጉዞ" እንደነበር እናስተውል ይሆን? ሂጅራ መኖሪያ ቦታን ከመቀየር ያለፈ፣ ከስረ-መሰረት የመነቀል ያህል ከባድ ህመም የነበረው፣ እንዲሁም ከተወሳሰቡ ስሜታዊ፣ ማህበራዊና ቁሳዊ ትስስሮች የመበጠስ ሂደት ነበር። ይህ ታላቅ ክስተት የሰው ልጅ ከለመደው ነገር ጋር ካለው ቁርኝት በላይ አላማው እንዴት ከፍ ሊል እንደሚችል ያሳየናል። ይህን ጥልቅ ጉዞ በአራት አጫጭር ነጥቦች እንመልከተው👇 💔 1. ከስረ-መሰረት የመነቀል ህመም ለሰሃባዎች መካ የማንነታቸው ማዕከል፣ የትዝታቸው ማህደር እና የማህበራዊ ክብራቸው መገለጫ ነበረች። ይህን ሁሉ ጥሎ መውጣት ራስን እንደማጥፋት የሚቆጠር ከባድ መስዋዕትነት ነበር። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መካን ሲለቁ ቆም ብለው፡- "በአላህ እምላለሁ! አንቺ ለእኔ ከምድር ሁሉ በላጭና ወደ አላህም የተወደድሽ ነሽ፤ ባያስወጡኝ ኖሮ ከቶ አልወጣም ነበር" ማለታቸው ሂጅራ ስሜት አልባ ጉዞ እንዳልነበር፣ ነገር ግን ከሰውኛ ስሜት ይልቅ ለከፍተኛ አላማ ቅድሚያ የመስጠት ትልቅ ትምህርት መሆኑን ያሳያል። 🚀 2. ከአስመሳይ የመረጋጋት አዙሪት (Comfort Zone) መውጣት የሰው ልጅ በተፈጥሮው (ጎጂ እንኳን ቢሆን) የለመደውን ነገር ሙጭጭ የማለት ባህሪ አለው። መካ ውስጥ መቆየት ግን ሀሳብን ቀስ በቀስ የሚገድልን ሁኔታ መቀበል ነበር። ስለዚህም ሂጅራ እድገትን ከሚያቀጭጭ አካባቢ በድፍረት በመውጣት አዳዲስ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ የተደረገ ታላቅ አብዮት ነው። 🔄 3. ዘላለማዊው የሂጅራ ትርጉም ሂጅራ በታሪክ ተከስቶ ያለፈ ክስተት ብቻ አይደለም። ከመካ ወደ መዲና የሚደረገው ስደት ሲያበቃ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጽንሰ-ሀሳቡን አደሱት፡- "እውነተኛ ስደተኛ (ሙሃጂር) ማለት አላህ የከለከለውን ነገር የተወ (የራቀ) ነው።" ይህ ማለት ዛሬም እያንዳንዳችን ከወንጀል፣ ከስንፍና፣ እና ከኋሊት ቀርነት... ወደ ታዛዥነት፣ ንቃትና ስኬት ስንጓዝ የሂጅራን መንገድ እየተገበርን ነው ማለት ነው። ⛓️ 4. ከቁስ ባርነት ነፃ መውጣት ንብረትን፣ ቤትን እና በአቋማቸው ያልፀኑ ቤተሰቦችን ሳይቀር በፈቃደኝነት ጥሎ መሄድ፣ ከ"ነገሮች ባርነት" ነፃ የመውጣት ትልቅ ተግባራዊ ስልጠና ነበር። አእምሮን ከቁስ በላይ ለሆነ ታላቅ አላማ (ለአኼራ) ቅድሚያ እንዲሰጥ አስችሎታል። የቁስ ፍቅር ያሰረው ትውልድ ታላላቅ ውሳኔዎችን መወሰን አይችልምና! ✨ በአጭሩ፡- እውነተኛ ነፃነት የሚጀምረው አካባቢን ከመቀየር በፊት፣ ውስጣዊ አእምሯችንን የለመደውን መጥፎ ነገር እንዲተው ከማድረግ ነው! የአላህ ሰላምና እዝነት በነብዩ ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን። 💚