Orthodoxy
Статистикаየመጻሕፍት ጥቆማ ፣ ከመጻሕፍት የተወጣጡ ሀሳቦች ፣ አርቲክሎች እንዲሁም አስተማሪ ትምሕርትና ውይይቶችን የሚጋሩበት ቻናል ።
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 29
- 1/48двое суток
- 33
- 1/72трое суток
- 35
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ትምሕርተ ሥላሴ ክፍል ሁለት በሥላሴ ትምህርት ላይ ያሉ መሠረታዊ ትምሕርቶችን ወደማየት እንግባ። PERICHORESIS የእንግሊዝኛ ትርጉሙ፥ mutual interpenetration ነው። ከላይ፥ ሰዎች በቦታና በጊዜ የተለያዩ ናቸው በሥላሴ ዘንድ ግን ይህ የለም በሚል አንስተናል። ጌታችን በወንጌል "እኔ በአብ እንዳለው አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ.." ይላል(ዮሐ 14:11)። አብ አብነቱን ሳይለቅ፣ ከወልድ ጋር፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለመደባለቅ፣ ያለመቀላቀል፥ በሁለቱ አካላት ውስጥ ሕልው ሆኖ ያኖራል። ወልድም መንፈስ ቅዱስም በተመሳሳይ። ይህ አስተምህሮ፥ ሶስቱም የሥላሴ አካላት ተመሳሳይ የመለኮት ቦታ የሚይዙ ፣ በሁሉም ያሉ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው። አንዱን በማየትም ሶስቱንም እናያለን እንጂ አንዱን ነጥለን ብቻ የምናይ አይሆንም። ውስጣዊ ግብር (AD INTRA) እና ውጫዊ ግብር (AD EXTRA) ግብር ውስጣዊ እና ውጫዊ በሚል ይከፈላል። ውስጣዊ ግብር ወይም አካላዊ ግብር ከላይ ያልነው ነው። አካላዊ ግብር ለአንዱ ብቻ የሚሰጥ ነው። አለመገኘት ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ አይሰጥም። መስረጽም ለወልድና ለአብ አይሰጥም። ሥላሴ በውስጣዊ ግብር ሶስት ናቸው። በውጫዊ ግን መለያየት የለም። አንድ ናቸው። ውጫዊ ግብር ማለት፥ ሥላሴ ከአለም ጋር ያላቸው ግንኙነት ነው። " አለምን የፈጠረው አብ ነው እንጂ ወልድ አይደለም መንፈስ ቅዱስም አይደለም። አለምን ያዳነው ወልድ እንጂ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይደለም። የቀደሰውና አዲሱን ፍጥረት የፈጠረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ አብና ወልድ አይደለም።" አንልም። በውጫዊ ሥራ ላይ ልዩነት የለም። መጽሐፍ ቅዱስም ፍጥረት ሆነ ማዳን በሶስቱም አካላት የተከናወነ መሆኑን ይነግረናል። በውጫዊ ሥራ ልዩነት የለም ብለን ግን፥ መፍጠርን ለአብ፣ ማዳንን ለወልድ፣ መቀደስን ለመንፈስ ቅዱስ እንሰጣለን። ወልድና መንፈስ ቅዱስ አለም አልፈጠሩም ማለት እንጂ ስሕተቱ እንዲህ መስጠቱ ስሕተት የለውም። ሶስቱም የሚሰሩ ቢሆኑም በአንድ agent ይሰራሉና። ይህ Appropriation ይባላል። በአጭሩ አንዲህ እናስቀምጠው፥ ሶስቱም አካላት በፍጥረት ሥራ ላይ የሰሩ ቢሆኑም ለአብ ሰጥቶ መናገር ተገቢ (appropriate) ይሆናል። ማደን የሶስቱም ሥራ ቢሆንም፥ ለወልድ ሰጥቶ መናገር (appropriate)ነው። መፍጠር የሶስቱም ቢሆንም በአንድ agent መጥራት appropriate ይሆናል። በውጫዊም ሆነ በውስጣዊ ግብር ላይ ግብሩ የሚሰራበት order እንዳለ ማንሳት አስፈላጊ ነው። ይህ order የአካላት ተዋረድ እንዳልሆነ መዘንጋት የለበትም። ግብሩ ሁሌም፥ ከአብ በወልድ በኩል በመንፈስ ቅዱስ የሚሰራ ነው( From the Father through the Son by the Holy Spirit)። ተገላቢጦሹ አይሆንም። ይህም በነገረ መለኮት ቋንቋ Taxis ይባላል። እንቀጥላለን።
ትምሕርተ ሥላሴ ክፍል አንድ Trinitarian Terms ነገረ እግዚአብሔር ጥናት ስንጀምር፣ ጥናቱ ሁለት ጥያቄ ላይ የቆመ መሆኑን አንሥተናል። " እግዚአብሔር ምን ይመስላል?" የሚልና " እግዚአብሔር ማን ነው?"። አንደኛውን ጥያቄ የእግዚአብሔር ባሕርያት ወይም ጠባያት በማየት ለማጥናት ሞክረናል። ሁለተኛው ጥያቄ ወደ የሥላሴ ትምሕርት ይወስደናል። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመግቢያ የሚሆን አረዳድ የሚያስይዝ ጽሑፍ እናቀርባለን። ወደ ትምሕርቱ ከመግባታችን በፊት ቃላቱን ማወቅ አለብን። ካላወቅን ትምሕርቱን ለመረዳት እንቸገራለን። ስለዚህ በዚህ ክፍል ቃላቱንና የተወሰኑ መሠረታዊ ሀሳቦችን እናነሣለን። ሥላሴ በአካል ሶስት በባሕርይ አንድ እንላለን። ባሕርይና አካል ራሱ ምን ማለት ነው? አካል፦ አካል ሥጋ ማለት አይደለም። አካል ማለት፣ እኔ የሚል ማንነት ያለው ማለት ነው። ለምሣሌ፣" እመቤታችንን ያበሰረው ማን ነው?" ተብሎ ቢጠየቅ፣ ጥያቄው "ማን" የሚል ነው። የማንነት ጥያቄ ማለት ነው። ስንመልስም ቅዱስ ገብርኤል እንላለን። ባሕርይ፦ ባሕርይ የአካልን ምንነት የሚለይ ነው። ለምሣሌ፣ "ቅዱስ ገብርኤል ምንድነው?" ተብሎ ቢጠየቅ፣ ጥያቄው "ምን" የሚል ነው። የምንነት ጥያቄ ማለት ነው። ስንመልስም፣ መልአክ እንላለን። የአካልን ምንነት እንደለየን ልብ እንበል። በሥላሴ ዘንድ "እኔ" የሚሉ ሶስት አካላት አሉ። "ማን" ብለን ስንጠይቅ፣ ሶስት እኔ ባይ ማንነቶች አሉ። በባሕርይ ግን አንድ ናቸው። አብ ምንድነው? ወልድ ምንድነው? መንፈስ ቅዱስ ምንድነው? ስንል ሶስት የተለያየ መልስ አናገኝም። አካል Incommunicable ነው። share አይደረግም። አብ ወልድ አይደለም። ወልድም መንፈስ ቅዱስ አይደለም። መንፈስ ቅዱስም አብ አይደለም። ባሕርይ ግ Communicable ነው። share የሚደረግ ማለት ነው። Share ይደረጋል ሲባል ግን ጥንቃቄ ያሻል። አንዱ አካል ከመለኮታዊ ባሕርይ የሆነ ያህል ክፍል ይይዛል፣ ሌላኛው አካል የሆነ ክፍል ይይዛል አይደለም። እግዚአብሔር part የለውም። ወጥ ነው። ሶስቱ አካላት ጋር መለኮታዊ ባሕርይ በምልአት ነው ያለው። ከላይ ስለ ባሕርይ ስንናገር፣ "አብ ምንድነው? ወልድ ምንድነው? መንፈስ ቅዱስ ምንድነው?" ለሚለው ጥያቄ መልሳችን አንድ እንደሆነ አንስተናል። እዚህ ጋር የሚነሣ ጥያቄ አለ። ጴጥሮስ፣ ጳውሎስና ዮሐንስ ሶስት አካል ናቸው። ባሕርያቸው አንድ። ነገር ግን ሶስት ሰዎች ይባላሉ። በሥላሴ ይህ ለምን አይሰራም? ተብሎ ይጠየቃል። ይህ ጥያቄ የዘነጋው ነገር፣ እኛና እግዚአብሔር ፍጹም ምስስሎሽ እንደሌለን ነው። እግዚአብሔር አንድ ነው ሲባልና ሰዎች አንድ ባሕርይ ነው ያለን የሚለው ቋንቋ univocal አይደለም። analogical ነው። univocal የማይሆንበትን ምክንያትም እናስረዳ። ጳውሎስ፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ የፈቃድ አንድነት የላቸውም። እውቀታቸውም አንድ አይደለም። በጊዜና በቦታም ይለያያሉ። ከዚህ የተነሣ፣ በመካከላቸው distinction ብቻ አይደለም ያለው፣ separation ጭምር እንጂ። በሥላሴ ዘንድ ግን ይህ ሁሉ የለም። ፈቃዳቸው፣ አሳባቸው ፣ እውቀታቸው አንድ ነው። የጊዜ ልዩነት የለም። አንዱ በአንዱ ውስጥ ሕልው ሆኖ በመኖሩ የቦታ ልዩነትም የለም። በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች፣ ሶስት ሰዎች እንደምንለው ሶስት አምላኮች ልንል አይቻለንም። ባሕርያዊ ልዩነታችንም ሰዎችን በባሕርይ "አንድ" ስንለና እግዚአብሔር "አንድ" ስንል univocal እንዳይሆን ያደርገዋል። አሁን በምስራቁ ብዙም ያልተለመደ ክፍፍል እናምጣ። በእኛ ዘንድ አይለመድ እንጂ ከመሠረቱ ሥላሴን ለማስረዳት የሚጠቅም በመሆኑ በተወሰነ እንየው። Five notions ፦ notion አካልን የምንለይበት መለያ ነው። በሥላሴ ዘንድ አምስት notions አሉ። እነርሱም፥ አለመገኘት፣ አባትነት፣ ልጅነት፣ ማስረጽና መስረጽ። Four properties፦ property የአንዱ አካል ብቻ ገንዘብ የሆነ ነው። ከሌላው ጋር የማይጋራው። አለመገኘትና ማስገኘት የአብ ብቻ ነው። መወለድ የወልድ ብቻ ነው። መስረጽ የመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። Four relations፦ አካላት የሚገናኙበት ወይም የሚዛመዱበት ዝምድና አላቸው። ከላይ five notions አሉ ብለናል። አመገኘት ዝምድናን የሚገልጽ ባለመሆኑ እናወጣዋለን። በዚህም አራት ይቀራሉ። አራቱም፥ አባትነት፣ ልጅነት፣ ማስረጽና መስረጽ ናቸው። እንቀጥላለን።
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሰን። ከነገ በኋላ አንድ አንድ ቀን እየዘለልን ትምሕርተ ሥላሴ ላይ አጫጭር ጽሑፍ እናጋራለን። የሚከተሉት ርእሶች ይዳሰሱበታል። -የ Term'ዎች ትርጉም -በትምሕርተ ሥላሴ ላይ ያሉ መሠረታዊ ሀሳቦች - መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት(ሥላሴ በብሉይ ኪዳን) - የFilioqoue ውዝግብ -ትምሕርተ ሥላሴ ላይ የተነሡ ምንፍቅናዎች -ትምሕርተ ሥላሴን ለማብራራት የምንጠቀማቸው ምሣሌያት ትክክል ናቸውን? -ሥላሴ ቅድመ ኒቅያ በነበሩ አባቶች -ሄኔሬዎስና ሰማእቱ ዮስጢኖስ የሥላሴ አማኝ አይደሉምን? እግዚአብሔር ይርዳን። የምንጠቀማቸውን ዋቢ መጻሕፍት ከማስቀመጥ የተቆጠብነው መጻሕፍቱ በብዛት የOO ስላልሆኑ፣ የተወሰኑትን ሊያሳስት ይችላል በሚል ፍርሃት ነው።
Peter Kreeft'ም , Socratic Logic የሚለው ስለ አመክንዮ በጻፉት መጽሐፍ ላይ፥ "በጥራት መጻፍ መቻል በጥራት ከማሰብ ጋር የተጣመረ ነው። የአንዱ መኖር ወይም አለመኖር፣ የሌላውን መኖር ወይም አለመኖር ያስከትላል። በጥራት መጻፍ አለመቻል በጥራት ማሰብ አለመቻልን ይወልዳል። በጥራት ማሰብ አለመቻልም በጥራት አለመጻፉን ይወልዳል።" ይላሉ። በአጭሩ ሁለቱ ተመጋጋቢ ናቸው። አይለያዩም። አሁን ላይ የማሰብ እጥረት ተንሰራፍቶ ካለ፥ ልንገረስሰው የምንችለው በመጻፍ ነው። personal Jornal በማዘጋጀት ማሰብን እንለማመድ። አንድ ጸሐፊ እንደሚናገረው፥ " ላለማሰብ የቆረጥን" አንሁን😁
አዳዲስ ዕቅበተ እምነት ላይ ለመሥራት ለምትመጡ ልጆች.. አሁን አሁን ብዙ አዳዲስ ልጆች በብዛት ወደ ዕቅበተ እምነት ሥራ እየመጡ ነው.. ይሄ በጣም ደስ የሚል ነው.. ጌታ ይርዳቸው.. ሁሉንም በጸሎትም ልናስባቸው ይገባል.. ግን ደግሞ እንደው ከጠቀመ ጥቂት ሐሳብ ላስቀምጥ.. - ከቅዱስ ቁርባንና ከጸሎት አትራቁ.. አልያ የጌታ አገልጋይ መሆን ይከብዳል.. ስትጸልዩ ሁሌም “ጌታ ሆይ አንተ ተጠቀምብኝ.. እኔ ሳልሆን አንተ ክበርበት” በሉት.. እርሱ ሞገስን ይሰጣችኋል.. ጌታ ሕዝቡን እንድታገለግሉ ይሾማችሁ ይጀምራል.. - ትእቢት ከእናንተ ይራቅ.. ምንም ሥራ ስትሠሩ ብዙም እንደው ምስጋና እና እውቅና አትጠብቁ.. ጌታ ይመስገንበት.. እናንተ ባሪያ እንደሆናችሁ ብቻ አስቡ.. እናንተ ስትመሰገኑ ሳይሆን ጌታ ሲመሰገን ደስ ይበላችሁ.. - ስትሠሩ ለመታወቅ ወይም ደግሞ “እርሱ ጎበዝ ነው” ለመባል ስትሉ ብቻ በፍጹም አትሥሩ.. ይልቁንም ሰውን ለመጥቀም ብቻ ሥሩ.. ራሳችንን ለማሳየት ስንሞክር ጌታ በእኛ አይሠራም.. ብቻችንን የምንደክም እንሆናለን.. ከዚያ በተረፈ ግን በርቱ ሁላችሁም.. የተወደዳችሁ ናችሁ በጣም
እግዚአብሔር ፍጹም ቸር ነው (God is perfectly good) ( ክፍል ሁለት የቀጠለ) -ለነገረ እከይ ከእግዚአብሔር ባህርያት መካከል ከእግዚአብሔር ቸርነት ይልቅ የበለጠ ማዕከላዊ የሆነ ሌላ ባህሪይ የለም። መዝ. ፻:፭"እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።"እንዲሁም ማር.፲:፲፰ "ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።" ሲል ተናግሯል። -የእግዚአብሔር ቸርነት ከደግነት ወይም ከርህራሄ እጅግ የላቀ ትርጉም አለው። ቅድስናውን፣ ጽድቁን፣ ፍርዱን፣ ምህረቱን፣ፍቅሩን፣ ታማኝነቱን እና እውነተኝነቱን ያካትታል። ቸር አምላክ ክፍት እንዲኖር ይፈቅዳልን ? ➔ቸር አካል ከቻለ ሁልጊዜ መከራ እንዳይከሰት ይከላከላል። ➔እግዚአብሔር ደግሞ ፍጹም ቸር ነው። ➔ስለዚህ፣እግዚአብሔር መከራን ሁሉ እንዳይኖር መከላከል አለበት። -እንዲሁ በደፈናው ስናየው አሳማኝ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ያለውን ስናይ ይህ ሙግት የተሳሳተ እንደሆነ እንረዳለን።ጥቂት ምሳሌዎች እንይ፥ ወላጆች ልጆቻቸው ከበለጠ በሽታ ለመጠበቅ ሲሉ በክትባት ጊዜ የሚኖረውን ሕመም እንዲታገሱ ያደርጓቸዋል። መምህራን መማር ጥረት የሚጠይቅ ነገር እንደሆነ ስለሚያውቁ ተማሪዎቻቸውን ከባድ የቤትስራ እና አሳይመንት እንዲሰሩ ያደርጓቸዋል። ሐኪሞች ጊዜያዊው ሕመም ፈውስ እንደሚያስገኝ ስለሚያውቁ ሕመም ያለበትን ቀዶ ህክምናዎችን ያደርጋሉ። -በእያንዳንዱ ምሳሌዎች ውስጥ፣ ጥሩ ሰው የሆነ አካል የበለጠ በጎ ነገርን ለማስገኘት ሲል የተወሰነ መከራ እንዲኖር ሲፈቅድ እናያለን። እነዚህ ምሳሌዎች የሰው ልጅ የመከራ ዓይነት ሁሉ የሚያስረዱ ባይሆኑም፣ ሕመም እንዲኖር መፍቀድ ከእውነተኛ ፍቅር ጋር በጭራሽ የማይጣጣም አለመሆኑን ግን ያሳያሉ። እግዚአብሔርም ቢሆን ከሰው ልጅ አእምሮ በላይ ለሆኑ ምክንያቶች ሲል ጊዜያዊ መከራዎች እንዲኖሩ ሊፈቅድ ይችላል። ትንቢተ ኢሳ. ፶፭: ፰ "አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር።" እንቀጥላለን።
ነገረ እግዚአብሔር ፡ ክፍል አምስት(የመጨረሻ ክፍል) እግዚአብሔር የማይለወጥ ነው( Immutable) እግዚአብሔር ፍጹም ነው ብለናል። ፍጹምነት ደግሞ አይለወጤነት ነው። ለውጥ፣ ወይ ወደ ፍጽምና ነው። ወይም ከፍጽምና ነው። እርሱ ፍጹም ነውና ወደ ፍጽምና አይለወጥም። ፍጹም አለመሆን አይችልምናም ከፍጽምና አይለወጥም። አለመለወጥ በዋነኝነት ይሄ ነው። ሰፋ ካደረግነውም እንዲህ መግለጽ ይቻላል- በባሕርይ፣ በእውቀት፣ በፈቃድና በዓላማ አለመለወጥ። እግዚአብሔር አይለወጥም ስንል ይህን እያልን ነው። እንዲህ መሥመር ማበጀቱ ፣ አንዳንዶች የእግዚአብሔርን ሰው መሆን በመያዝ፣ እግዚአብሔር ተለወጠ በሚል የሚከሱ በመኖራቸው ነው። የዚህ የመጀመሪያው ችግር እግዚአብሔር በሥጋዌ መለወጥ አገኘው የምንል አለመሆኑ ነው። ሲቀጥል፣ ከላይ ካሰመርነው፣ ሥጋዌው የሚወጣ አይደለም። በተመሳሳይ፣ እግዚአብሔር ከፍጥረታት በፊት ፍጥረት ባለመኖሩ ፈጣሪ አልነበረም። ነገር ግን በመፍጠሩ ተለወጠ እንደማንለው ለሥጋዌውም እንደዛው ነው። ➔እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ሁሉን ቻይነት፣ ሁሉንም የትኛውንም ነገር የመሥራት አቅም ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው። የሚሳነው ምንም የለም። ነገር ግን ሁሉን ቻይነት ሲለጠጥ ይታያል። ባልሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ሲውል። ስለዚህ በተወሰነ አፍታቶ ማየቱ ይጠቅማል። ሁለት አይነት አለመቻል(ጠብቆ ይነበብ) አለ። የመጀመሪያው፣ ነገሩ የሚቻል ሆኖ አድራጊው የማይችለው ከሆነ ነው። ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የለም። ሰውም የሚችለው የሆነ አቅም ተሰጥቶ በመሆኑ ፣ "ይህ የማይቻል ነው እንዲህ ካልሆነ በቀር።" በሚል "በቀርን" እንጨምርበታለን። ለምሣሌ፣ "ነገን ማወቅ አይቻልም።" እንላለን። "በበቀር" ግን የሚቻል ሊሆን ይችላል- "እግዚአብሔር ካልገለጠለት በቀር" ብለን- ለምሣሌ። ሁለተኛው አለመቻል፣ ነገሩ በራሱ የማይቻል፣ የማይሆን ሲሆን ነው። Intrinsically Impossible እንለዋለን። ለላይኛው አለመቻል " በቀርን" እንጨምራለን። ለዚህኛው ግን ምንም የሚቻልበት መንገድ ስለሌለ ወይም ነገሩ የማይሆን ስለሆነ "በቀር" ጨምረንበትም አይሆንም። ነገሩ nonsense ነው። የላይኛው፣ ለእግዚአብሔር የማይቻል አይደለም። በዚህ ግን ለእግዚአብሔርም አይቻልም። ለእግዚአብሔር የማይቻለው ሳይችል ቀርቶ አለመሆኑን ልብ እንበል። ነገሩ የማይሆን ወይም የሌለ በመሆኑ ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ስንልም logically possible የሆኑ ወይም intrinsically possible የሆኑ ነገሮችን እንጂ intrinsically impossible የሆኑ ነገሮችን ይችላል አይደለም። ይህን አለመቻል ግን ከአቅም ማንስ ጋር ማገኘት ነገሩን ፈጽሞ መሳት ነው። ለምሣሌ፣ እግዚአብሔር ከለር የሌለው ከለር መፍጠር አይችልም። እግዚአብሔር ክብ አራት ማዕዘን መፍጠር አይችልም። እኚህ፣ የሌሉና nonsense የሆኑ ነገሮች ናቸውና። የእግዚአብሔር ጠባያት ላይ ያልነካናቸው ብዙ አሉ። እጅግ ላለማርዘም በዚሁ እንዝጋ። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፣ እግዚአብሔር ማን ነው የሚለውን ጥያቄ የሚያትተውን የሥላሴን ትምሕርት ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ማየት እንጀምራለን።
የባዶነት ስሜት( ክፍል 2) > ታዲያ ይህን የባዶነት ስሜት በምን እንሙላው? > በውስጣችን ያለው ባዶነት የተመኘናቸውን ነገሮች በመፈጸም፣በሀብት የማናገኘው ወይም የማንሞላው ከሆነ፣ ታዲያ ይህ ነገር በምን ሊሞላ ይችላል? > ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ኦጉስቲኖስ፦ «የሰው ልጅ በውስጡ ትልቅ የማይሞላ ጉድጓድ አለ፤ በሁሉም ከሚሞላ አምላክ በቀር ሊሞላ አይችልም» ይለናል። የባዶነት ስሜት የሰው ልጅ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ላይ በሚፈጠር ክፍተት ወይም ከአምላኩ ጋር ያለው ግንኙነት ሲቋረጥ የሚፈጠር ስሜት ነው። ይህ የባዶነት ስሜት በቁሳዊ ነገር የምንሞላው የስጋዊ ርሀብ አይደለም። ልክ ጥማታችንን ውሃ ስንጠጣ እንደምናረካው፣ እንዲሁ ውስጣችን ለመርካት መንፈሳዊነትን ይፈልጋል። ስለዚህ ነገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል፦ «ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋል። እኔን የሕያው ውሃ ምንጭ ትተውኛል፤ የተቀደዱትን ጉድጓዶች፣ ውሃውንም መያዝ የማይችሉትን ጉድጓዶች ቆፍረዋል።» ኤር 2:13 በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሠረት የሰው ልጅ ሁለት ስህተት ይሰራል። 1. አንደኛ፣ የሕይወትን ትርጉም ከሚያገኝበት ከእግዚአብሔር ይርቃል። 2. ከዚያ በኋላ በምድር በተፈጠሩ እሳቤዎች የሕይወቱን ትርጉም ይፈልጋል፤ ይህም ደግሞ ወደ ባዶነት ይመራዋል። በመንፈሳዊነት ውስጥ ግን የውስጣችን ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን። «እኔ ምንድን ነኝ? የመኖሬስ ዓላማ ምንድን ነው?» ብንል፣ «በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርን፣ ክብሩን ለመወረስ የተመረጥን እንደሆንን» መንፈሳዊነት ያስረዳናል። የዋጋ ቢስነት ስሜት ሲሰማን፣ «በከበረ በእግዚአብሔር ልጅ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ዋጋ ተገዝተሃል» ብሎ ውድ መሆናችንን ይነግረናል። ሌላው ትልቁ ነገር በመንፈሳዊነት (በክርስትና ) ውስጥ ተስፋ አለ፤ የመጣነው ያለዓላማ አይደለም፣ መንግስቱን እንድንወርስና ከእርሱ ጋር በኅብረት እንድንኖር ነው። ይህተስፋ የሰው ልጅ ነገን እንዲጠብቅ ያደርገዋል። ይህን በደንብ የሚያስረዳን የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልዕክቱ ላይ ሲጽፍ ሁለት ጊዜ «በጌታ ደስ ይበላችሁ» እያለ ይጽፋል። በዚህ ጊዜ ግን እንደ አሁኑ ፓስተሮች ወይም ሰባኪዎች በድሎት ውስጥ ሆኖ ወይም በጥጋብ ሕይወት ውስጥ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም በቀዝቃዛ እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ነበር። ነገር ግን የክርስቶስን ፍቅር እና የሚቀበለውን አክሊል እያሰበ በመከራው ደስ ይለው ነበር። የሕይወት ውሃ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል የጠጣ መንፈሳዊ ሰው፣ ቢያገኝም ቢያጣም፣ ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሆነ ያውቃል። ሀሳቡ ባይሳካም፣ የተመኘው ባይሆንም ዋጋ ቢስነት አይሰማውም። የተሻለው ነገር እንዲመጣ ያውቃልና በተስፋ ደስ ይለዋል። የመንፈስ ባዶነት በዚህ ዘመን ትውልድ ችግር ብቻ አልነበረም። ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶች የሕይወትን ትርጉም ለማግኘት ፍልስፍናን እስከ ጥግ ተማርረዋል። ለምሳሌ ቅዱስ ኦጉስቲኖስ «ከዚህ ዓለም ደስታ ይሰጠኛል» ብሎ ያሰበውን በሙሉ ያደርግ ነበር። ዘፈን፣ መጠጥ፣ በስጋ፣ በሴሰኝነት ውስጥ እርካታ ለማግኘት ያስብ ነበር። ነገር ግን አሁንም ከባዶነት ስሜት አልወጣም። እናቱ ትልቅ አማኝ ክርስቲያን ነበረች፤ በእሷ ጸሎት ክርስትናን ተቀበለ። በክርስትና እንዴት ልቡ እንዳረፈ እንዲህ ሲል ይገልጻል «ላንተ ፈጥረኸናልና ጌታ ሆይ፣ በአንተ እስካያርፍ ድረስ ልባችን እረፍት የለውም።» ይህ የሕይወታችን ትርጉም በምናሳካው ስኬት፣ በምናገኘው ሀብት ውስጥ ለማግኘት ለምንባዝነው ትልቅ ትምህርት ነው። የተፈጠርነው በዓላማ ነው፤ እርሱን (እግዚአብሔርን) እያመሰገንን መንግስቱን ለመወረስ ነው። ወደዚያ ሀሳብ እስካልተመለስን ድረስ ልባችን እረፍት የለውም። የማስያስ ልጅ
የእግዚአብሔር ባህርያት (ሁሉን ቻይ፥ፍጹም ቸር፥ሁሉን አዋቂ)-ክፍል ሁለት -እግዚአብሔር ፍጹም ቸር ወይም ፍጹም ቻይ ባይሆን ኖሮ The problem of Evil የሚባል ነገር ባልኖረ ነበር። -የእግዚአብሔር ባህርያት በማንነቱ ላይ የተጨመሩ የተነጠሉ ነገሮች ሳይሆኑ የእግዚአብሔር ፍጹም ማንነቱ መገለጫዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ባህርይ ፍጹም እንደሆነ ደጋግሞ ይነግረናል፦ኦሪት ዘዳ. ፴፪:፬፤" እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ እርሱ እውነተኛና ቅን ነው።" መዝ. ፻፵፭:፲፯"፤ እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።" እነዚህ ጥቅሶች የእግዚአብሔር አላማዎች ከሰው ልጅ አእምሮ በላይ በሆኑበት ጊዜ እንኳ፣ የእግዚአብሔር ሥራዎች ሁልጊዜ ከፍጹም ባህርዩ ጋር የሚስማሙ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። እግዚአብሔር ሁሉም ቻይ ነው (Omnipotent) -እግዚአብሔር ሁሉም ቻይ ነው ስንል logically ሊሆኑ የሚችሉት እና ከራሱ ፍጹም ባህርይ ጋር የሚስማሙት ነገሮችን ማድረግ ይችላል ማለት ነው። እግዚአብሔር የሚከተሉት ነገሮች ማድረግ አይችልም፥ መዋሸት (ቲቶ.1፡2)፣ራሱን መካድ(2ጢሞ.2:13)፣በክፉ መፈተን(ያዕ.1:13)፣ ከቅዱስ ባህርዩ ጋር የሚጋጫ ነገር ማድረግ አይችልም። እነዚህ የእግዚአብሔር ኃይል ውስንነቶች አይደሉም። ይልቁንም የእግዚአብሔር ኃይል ከፍጽምትነቱ የተነጠለ አለመሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። ሊዋሽ የሚችል አምላክ እውነተኛ አምላክ ሊሆን አይችልም። -እግዚአብሔር ባለ አራት ማዕዘን ክብ፣ ከለር የሌለው ከለር፣ ያገባ ላጤ መፍጠር ይችላል ወይ ? ብሎ መጠየቅ የሁሉን ቻይነት ትርጉም አለመረዳት ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ እውነተኛ የሚሆኑ ሳይሆን logically contradictory የሆኑ ናቸው፤ ትርጉም ያለው ሀሳብ የሌላቸው የቃላት ስብስቦች ናቸው። -እግዚአብሔር logically possible የሆነ ነገር ነው ማድረግ የሚችለው ስንል፤ ታዲያ እግዚአብሔር ሎጂክ ይገድበዋል ማለት ነው ? የሚል ጥያቄ ይነሳል። መልሱም፣ እግዚአብሔር ራሱ የሎጂክ መሠረት ነው፤ ማለትም የሁሉም ነገሮች ምንጭ እርሱ ነው። ስለዚህ፣ ነገሮች ሁሉ የሚሠራው በዚህ መሠረት ነው። illogical መሆን አይችልም ስንል ራሱን አይቃረንም ነው፤ ምክንያቱም ምሉዕ ነው እርሱ፣ illogical መሆን ደግሞ ጉድለት፣ ሕጸጽ ነው። ጉድለት ደግሞ፣ ከእርሱ የተለየ ነገር ስለሆነ ከራሱ ሊለይ ራሱን ሊቃረን አይችልም የሚል ድምዳሜ የሚያመጣው መልስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት በዚህ መልክ ይገልጠዋል፥ ትንቢተ ኤር. ፴፪:፲፯"አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም።" እንዲሁም፦ማቴ.፲፱:፳፮ "ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፦ ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው።" እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር በፍጥነት ላይ ያለውን ወሰን የሌለው ስልጣን የሚያረጋግጡ ሲሆኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሥራዎቹ ሁሉ መነሻ ሁል ጊዜ ጥበብ፣ ቅድስና ዓላማ መሆኑን አስቀድመው ይናገራሉ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት በጭራሽ ያለ ምክንያት ወይም ያለ ዓላማ የሚገለጥ አይደለም፤ ይልቁንም ሁልጊዜ በጥበቡ እና በቸርነቱ የሚመራ ነው። እንቀጥላለን።
ነገረ እከይ(The problem of Evil)-ክፍል አንድ ➔የክፋት መኖር ከጥንት ጀምሮ የአምላክ መኖር እና አለመኖር ላይ ከሚደረጉ መከራከርያ ሀሳቦች ዋነኛው ነው። መንስኤው፣ የሚከተሉት አራት ሀሳቦች በአንዴ እውነት ሊሆኑ አይችሉም የሚል ነው። እነሱም፥ 1.አምላክ አለ። 2. አምላክ ፍፁም ቸር ነው። 3. አምላክ ሁሉን ቻይ ነው። 4.ክፋት አለ። ➔ አምላክ ፍጹም ደግ ነው፤ ሁሉን ቻይ ነው ብለን ክፋት አለ ልንል አንችልም፤ ነገር ግን ክፋት መኖሩ የታወቀ ነው። ክፋት መኖሩ የሚከተሉትን ችግሮች ይፈጥራል በሚል መከራከሪያዎች ይቀርባሉ፥ ➔እግዚአብሔር ክፋትን ለማስወገድ ፈቃደኛ ሆኖ፣ ነገር ግን ማድረግ ካልቻለ፤ ሁሉንም ቻይ አይደለም። ➔እግዚአብሔር ክፋትን ማስወገድ የሚችል ሆኖ፣ ነገር ግን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆነ፤ ፍፁም በጎ ሊሆን አይችልም። ➔እግዚአብሔር ክፋትን ለማስወገድ የሚችል እንዲሁም ክፋትን ለማስወገድ ፈቃደኛ ከሆነ፤ ታዲያ ክፋት ለምን በመኖሩ ይቀጥላል ? እነዚህ አራቱም ሀሳቦች በአንድ ጊዜ እውነት መሆናቸውን የምናሳየው፣ ወይም ለዚህ problem መፍትሔ የምናገኘው፥ ሀሳቦቹ ምን እንደሆኑ በማብራራት ነው። ክፋት ራሱ ምንድን ነው ?እግዚአብሔር ሁሉ ቻይ ነው ሲባል እንዴት ነው ? እግዚአብሔር ፍፁም ደግ ነው ሲባል እንዴት ነው ? የሚሉትን ከፋፍለን የምናይ ይሆናል፥ ➔ክፋት ስንል በሁለት ይከፈላል። Moral Evil (የሥነ-ምግባር ክፋት) እና Natural Evil (የተፈጥሮ ክፋት)። 1.Moral Evil ፦ይህ የሰው ልጅ ነፃ ፈቃዱን በተሳሳተ መንገድ በመጠቀም የሚያመጣው የክፋት አይነት ነው። ለአብነት፣ ግድያ፥ ስርቆት፥ ሙስና፥ ባርነት፥ ዘረኝነት...ወ.ዘ.ተ። ለሥም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለዚህ ክፋት ሲናገር፣ "ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።" ማቴ. ፲፭:፲፱ ይለናል። 2 Natural Evil፦የሰው ልጅ ወዶ፥ ፈቅዶ የሚያመጣው ክፋት ሳይሆን በተፈጥሮ ሂደቶች የሚመጡ ናቸው። ለአብነት ያህል፥ - የመሬት መንቀጥቀጥ፥ አውሎነፋስ፥ ካንሰር፥ የጎርፍ አደጋ፥ ድርቅ፥ ወረሽኝ...ወ.ዘ.ተ። ➔ይህን ክፋት ለማብራራት የበለጠ ከባድ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ኩነቶች የሰው ልጅ ወዶ እና ፈቅዶ የሚያመጣቸው ባለመሆኑ። ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ እንዲህ ይላል፥ ሮሜ 8:20-22 "፳፤ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤ ፳፩፤ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። ፳፪፤ ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።" ክፋት ህልውና አለውን ? ➔አውግስጢኖስ ክፋት ራሱን የቻለ ነገር ወይም ህልውና ያለው ነገር አይደለም ይላል። ይልቁንም ክፋትን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፥ ፥ ጨለማ ማለት የብርሃን አለመኖር እንጂ በራሱ ህልው እንዳልሆነ፤ እንዲሁም ክፍትም የመልካም ነገር አለመኖር ነው። ዘፍ.፩:፴፩፤" እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ።" ይላል። ስለዚህ እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ከሆነ፤ ክፋትን እግዚአብሔር አልፈጠረም ማለት ነው። እግዚአብሔር ያልፈጠረው ነገር ደግሞ ህልውና የለው ማለት ነው። ይህንን ለማጠናከር ጥቂት ምሳሌዎች እንመልከት ፥ ዕውርነት የሚመጣው ማየት ባለመቻል ነው፤ ህመም አዲስ የአካል ክፍል ሳይሆን የጤናማ ሰውነት መበላሸት ነው፤ በተመሳሳይ መልኩ የሰው ልጅ መልካምነት መበላሸት Moral Evil ነው። እንቀጥላለን።
የባዶነት ስሜት የባዶነት ስሜት ብዙ ጊዜ በሕይወታችን ውስጥ የመኖር ትርጉም ስናጣ ወይም ደግሞ የመኖርን ዓላማ ስናጣ የሚሰማን ስሜት ነው። የሰው ልጅ ደስታ ይርቀዋል ነገር ግን ምክንያቱ ምን እንደሆነ አያውቅም። የሆነ የጎደለው ነገር እንዳለ ይሰማዋል፤ ሆኖም ችግሩ ምን እንደሆነ አያውቅም። ሁሉ ነገር በእጁ እያለ አሁንም ተጨማሪ ነገር ይፈልጋል። «የሆነ ነገር ቢሳካልኝ፣ የሆነ ነገር ባገኝ ሙሉነት ይሰማኛል» ቢልም፣ ያሰበውን ሲያገኝ መልሶ ባዶነቱና አለመርካቱ አብሮት ይኖራል። ይህ ስሜት በአንድ ጊዜ የመጣ የስሜት መገለበጥ ሳይሆን፣ ቀስ በቀስ በሕይወታችን በምናደርጋቸው ነገሮች ትርጉም እያጣን ስንሄድ የሚሰማን ስሜት ነው። ከዚህ ስሜት ለመውጣት ወጣቱ ኢንተርኔት ላይ ይውላል። ነገር ግን ስልኩ ከእጁ ሲርቅ ባዶነቱ መልሶ ይመጣል። በዚህ ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ ስልኩ ጋር ያሳልፋል። ይህ ስሜት ድሃም ሆነ ሀብታም ላይ ሊፈጠር ይችላል። 1. የድሃው ወይም የአቅም የሌለው ሰው ችግር ይህ ሰው በየቀኑ ለምግብ፣ ለቤት እና ለህልውና በሚያደርገው ትግል ውስጥ ሲቆይና ተመሳሳይ ሕይወት ሲያሳልፍ ሕይወት ከንቱና በመከራ የተሞላች ሆና ትታየዋለች። ዓላማዬ ያለው ነገር አለመሳካቱ ዋጋ ቢስ እንደሆነ እንዲሰማው ያደርገዋል። 2. የስኬታማው ወይም ሀብታም የሚባል ሰው ችግር ይህ ሰው ትርጉም የሚያጣው በመሰላቸትና ግብ በማጣት ምክንያት ነው። የሚፈልገውን ነገር ሲያገኝ ጊዜያዊ ደስታ ይሰጠዋል፤ ነገር ግን ከዚያ ደስታ ጋር ይላመድና ሌላ ደስታ የሚሰጠውን ማሳደድ ይጀምራል። ይህም ደግሞ ቁሳዊ ነገሮች የሚሰጡት ደስታ ጊዜያዊ እንደሆነ ማሳያ ነው። በአንድ ነገር አለመርካቱ ሕይወትን አድካሚ ያደርግበታል። የሰው ልጅ ዋና ተነሳሽነት ደስታ መፈለግ ሳይሆን ትርጉም መፈለግ ነው። ሀብታም ከራሱ በላይ ለሆነ ዓላማ መኖር ሲያቅተው፣ ድሃውም በሚኖረው ተመሳሳይ ሕይወት ተስፋ ሲያጣ ሕይወት ትርጉም ታጣለች። ምክንያቱም የሕይወት ትርጉም የሚመጣው ባለን ሀብት ብቻ ሳይሆን፣ ለሕይወት ከምንሰጠው ምላሽ ነውና። ሰው በውስጡ ያለው ባዶነት ሲያይልበት፣ ከዚህ ሁኔታ ለመውጣት ራሱን ለማጥፋት ይገደዳል። ይህም የሰው ልጅ በውስጡ ያለውን ባዶነት በውጫዊ ነገሮች ለመሙላት ሲሞክር የሚፈጠር ነው። ያመነው ሰው ወይም ያፈቀረው ሰው ሲከዳው፣ «ይሆናል» ብሎ ያሰበው ነገር መና ሲቀርበት ተስፋ ወደ መቁረጥ ይዳርገዋል። የባዶነት ስሜት በውስጣችን ከሚፈጥረው አደገኛ ነገር ውስጥ አንዱ ተስፋ መቁረጥ ነው። ተስፋ፣ የሰው ልጅ በመከራ ውስጥ ሆኖ እንኳ «ነገን እንዲመኝ» ወይም ደግሞ «ነገን እንዲያስብ» ጉልበት እንደሚሆነው ታዋቂው ፈላስፋ ቪክቶር ፍራንክል እንዲህ ይለናል «የሰው ልጅ በመከራ ውስጥ ሆኖ ነገን እንዲመኝ የሚያደርገው በውስጡ ተስፋ ሲኖር ነው» ይላል። ሌላው፣ በሕይወት ትርጉም ማጣት ወደ ስነ-ምግባር ጥሰት ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል። በአጭሩ፣ ሀብታም ይሁን ድሃ፣ የሕይወትን ትርጉም በቁሳዊነት ወይም ስሜት ላይ የመሰረተ ከሆነ ወደ እንስሳዊ ጭካኔ የመውረድ እድሉ ሰፊ ነው። > ታዲያ ይህን የባዶነት ስሜት በምን እንሙላው? > በውስጣችን ያለው ባዶነት የተመኘናቸውን ነገሮች በመፈጸም፣በሀብት የማናገኘው ወይም የማንሞላው ከሆነ፣ ታዲያ ይህ ነገር በምን ሊሞላ ይችላል? ይቀጥላል.....
ነገረ እግዚአብሔር ፡ ክፍል አራት ጣባያቱን አንድ በአንድ በጥቂቱ ለማየት እንሞክር። ➔እግዚአብሔር መንፈስ ነው ዮሐንስ 4-24 "እግዚአብሔር መንፈስ ነው" ይለናል። እግዚአብሔር መንፈስ ነው ስንል እንደኛ ያለ የሰውነት ክፍል የለውም፣ ቁሳዊ አይደለም እያልን ነው። የእግዚአብሔር መንፈስነት፣ መላእክት መንፈስ ከሆኑት ፣ የሰው ነፍስም መንፈስ ከሆነችው መሆን እጅግ የራቀ መሆኑን ጠቅሶ ማለፉ አስፈላጊ ነው። ከዚህ ርእቱ ትምሕርት በተቃራኒ ያለ ውጉዝ ትምሕርት አለ። እርሱም ፥ እግዚአብሔር እንደኛ ያለ ቁሳዊ አካል አለው የሚል ነው። የቤተክርስቲያን አባቶች በስምምነት ይህን ትምሕርት አውግዘውታል። እግዚአብሔር እንደ ሰው ያለ የአካል ክፍላት እንደሌለው በስፋት አስተምረውማል። በመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኛቸው፣ እግዚአብሔር እጅ፣ እግር አለው የሚሉ ንባባትም በሰውኛ የተነገሩ መሆናቸውን ያስተምሩናል። ለምሣሌ ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘእንዚናዙ ፣ Theological Oration 31 ላይ፥ መጻሕፍት እግዚአብሔር መመልከቱን ለመግለጽ "ፊት" እንደሚሉ፤ መስጠትና መቀበልን ለመግለጽ "እጅ" እንደሚሉ ያስተምራል። በቅዱሱ ትምህርት፣ መጽሐፍ ቅዱስ እጅ፣ እግር በማለት የእግዚአብሔርን ሥራ በሰውኛ (anthropomorphic) መልኩ እየገለፀ እንጂ ሌላ አይደለም። ➔Simplicity of God እግዚአብሔር simple ነው። simple ማለት፣ ለመረዳት ቀላል ማለት አይደለም። Compound ያልሆነ ማለት ነው። ክፋላት አካላት የሌሉበት ወጥ የሆነ ማለት ነው። ከላይ ያየነው፣ እግዚአብሔር እንደኛ ያለ የሰውነት አካል አለው የሚለው ትምሕርት ሌላ የሚስተው ነገርም እዚህ ጋር ይነሣል። እግዚአብሔር እንደኛ ያለ የሰውነት ክፋላት አለው ካልን Divine Simplicityን መካዳችን እርግጥ ይሆናል። ይህን መካድ ደግሞ እጅግ ብዙ ስሕተት ውስጥ የሚከት ነው። አንዳንዶች፣ ክርስቲያኖች Divine simplicity'ን በትምሕርተ ሥላሴ እንደምንክድ ይከሱናል። ትምሕርተ ሥላሴ ላይ፥ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስን የእግዚአብሔር ክፍላት እንደሆኑ በስሕተት ከመረዳት የመጣ ክስ ነው። በእኛ አስተምህሮ፣ በሥላሴ አካላት መካከል ምንም አይነት ክፍፍል የለም። አብ የአምላክነትን የሆነ Percent የሚይዝ ወይም የአምላክነት part አይደለም። በምልአት አምላክነትን የሚይዝ እንጂ። ወልድም መንፈስ ቅዱስም። ➔Aseity በኦሪት ዘፍጥረት የሁሉም ነገሮችን መጀመሪያ እናያለን። በዘፍጥረት ያልጀመረው ብቸኛው አካል እግዚአብሔር ነው። እርሱ፣ ሲጀመርም በሆነ ጊዜ መኖር የጀመረ አይደለም። አስገኚ የሌለው፣ በራሱ ሕልው የሆነ ነው። ይህ፣ በፍጥረትና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን መሠረታዊ ልዩነት ያሳየናል። ለፍጥረት አስገኚ አለው። ለእግዚአብሔር ግን የለውም። ይህን ነው Aseity የምንለው። ቃሉ ከላቲን የመጣ ሲሆን፣ "a" ማለት "ከ" ወይም from የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፣ "se" ማለት "ራስ" ወይም self ነው። ትምሕርቱ ሌላ ምንም ሳይሆን እግዚአብሔር አስገኚ የለውም፣ በማንም ላይም ጥገኛ አይደለም ማለት ነው። ➔እግዚአብሔር ወሰን አልባ ነው እግዚአብሔር የማይወሰን ነው። የማይወሰን መሆኑን በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን። አንድ- እግዚአብሔር ከራሱ አንጻር ወሰን አልባ ነው( God is infinite in relation to himself)። ይህ የእግዚአብሔር absolute perfection ይባላል።እግዚአብሔር ፣ ፍቅርን፣ ጸጋን .... የሚይዘው እጅግ በበዛ መልኩ አይደለም። ወሰን በሌለው መልኩ ነው። 2-እግዚአብሔር ከጊዜ አንጻር ወሰን አልባ ነው። ይህ የእግዚአብሔር ዘላለማዊነት ይባላል። መነሻ ሆነ መድረሻ ነጥብ የለውም። ጊዜ፣ sequence ያለው ነው። ማለትም፣ በፊት በኋላ የሚል ተከታታይነት። በእግዚአብሔር ዘንድ ይህ የለም። ዘላለማዊነትም ይህ የሌለበት ሁኔታ ነው። 3- እግዚአብሔር በቦታ የማይወሰን ነው። በሁሉም ቦታ ያለ የማይገደብ አምላክ ነው።
ነገረ እግዚአብሔር ፡ ክፍል ሶስት Attributes of God ( የእግዚአብሔር ጠባያት ) ስለ እግዚአብሔር ጠባያት ስንናገር አረዳዳችን ከሁለት የሚመነጭ ነው። 1- ከፍጥረት ጋር ባለው ልዩነት ከምንገነዘበው። ለምሣሌ፣ ፍጥረት አስገኚ አለው፤ እግዚአብሔር ግን የለውም። ፍጥረት በጊዜ ውስጥ ነው፤ እግዚአብሔር ግን በዘላለም ያለ ነው እያልን እንደምንረዳው ያለ ማለት ነው። ሁለተኛው፣ ከፍጥረት ጋር ያለውን ዝምድና በማየት የሚመጣ አረዳድ ነው። ማለትም፣ ፈጣሪነቱ ፥ መጋቢነቱ ፥ መሐሪነቱ ...ወዘተ። ሌላው ስለ እግዚአብሔር ጠባያት ስንማር አንድ አይነት የተለመደ ክፍፍል አለ፤ የማይጋሩ ጠባያት (Incommunicable attributes)እና የሚጋሩ ጠባያት (Communicable attributes) በሚል ነው። የማይጋሩ ጠባያት የምንላቸው፥ በሁሉም ቦታ ያለ መሆኑ ፣ ዘላለማዊ መሆኑ እና ወሰን አልባ መሆኑ ሊጠቀሱ የሚችሉት ናቸው። እኚህ የአማላካችን ጠባያት በፍጥረታት ዘንድ የሚገኙ አይደሉም። በሌላ በኩል፥ ፍቅር መሆኑ ፣ መሐሪ መሆኑ እና መልካም መሆኑ የሚጋሩ ናቸው፤ ማለትም በፍጥረት ውስጥ ልናገኛቸው የምንችላቸው ናቸው። እዚህ ክፍፍል ላይ ግን አንድ ነጥብ ልብ ማለት ያሻል። የማይጋሩ ጠባያት ያልናቸው፣ ውስንነት ባለው መልኩ ለፍጥረት ሊነገሩ ይችላሉ። ለምሣሌ፣ እግዚአብሔር የማይለወጥ ነው። ፍጥረታት ዘንድ ግን ለውጥ አለ። ነገር ግን በሆነ መልኩ፣ ውሱንነት ባለው መልኩ ወጥነት ወይም አለመለወጥን የምናይባቸው ሁናቴዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ መሆኑ ግን ጠባያቱ የሚጋሩ ናቸው ወደሚል በምንም አይወስድም። በሌላ በኩል፣ የሚጋሩ ጠባያት ያልናቸው እንዴት ባለ መልኩ የሚጋሩ ናቸው የሚለውን አስቀድመን ባነሣነው ትምሕርት አንጻር መረዳት ያስፈልጋል። እግዚአብሔር መልካም ነው ስንልና ዮሐንስ መልካም ነው ስንል univocal አይደለም ንግግራችን፣ analogical ነው።
ነገረ እግዚአብሔር ላይ ጽሑፋችን አልቋል። ረዘም ያለ ስለመሰለን ቆራርጠን እናጋራለን። ከዚያ አንድ ላይ በpdf እናስቀምጣለን። አንዳንድ ቃላትን ወደ አማርኛ መመለስ ስለቸገረን በኢንግሊዘኛው ትተነዋልና በዚያ እንዳትረበሹ። ሲቀጥል አንዳንድ ሀሶቦችን ረጋ ብሎ ማንበብ ሊጠይቅ የሚችል በመሆኑ ረጋ ብላችሁ አንብቡት። ቀጣይ ትምሕርተ ሥላሴ ላይ ከዚህ በጠነከረ፣ በተደራጀና በሰፋ መልኩ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጽፋለን፤ እግዚአብሔር ይርዳን።
ነገረ እግዚአብሔር ፡ ክፍል ሁለት ቋንቋችን በነገረ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ባሕርይን ለመግለጽ ቃላትን እንጠቀማለን። ከዚህ የተነሣ ቃላት በነገረ እግዚአብሔር ውስጥ ምን አይነት ሚና እንዳላቸው መረዳት አስፈላጊ ነው። ቋንቋ univocal, equivocal ወይም analogical ሊሆን ይችላል። ከነገረ እግዚአብሔር አንጻር እንዴት ይሆናል? የሚለው በዚህች ጽሑፍ እንቃኛለን። Univocal ማለት…
Apostasy is almost always practical before it is intellectual
“ቅዱሱ በሰይፍ ወደሚቀላበት አደባባይ ከደረሰ በኋላ የሞት ጥላ ዙሪያውን ቢከበውም ‹‹የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል›› ብሎ የተነገረውን የጌታን ቃል አምኖ የልብሱን ኮሌታ ከፍ በማድረግ አንገቱን ለሰያፊው አመቻቸ፡፡(ዮሐ 11:25) ወታደሩም በያዘው ሰይፍ የጳውሎስን አንገት ከሰውነቱ ለየው፡፡ በቃሉ ትምህርት ምድርን ወደ ገነት የቀየረው፣ የብዙዎችን ስብራት የጠገነው፣ ሙት ያስነሣው፣ ሽባ የተረተረው የጳውሎስ አፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ታተመ፡፡ ይህ እንኳን ሰውን ሰማይና ምድርንም የሚያስደነግጥ ክስተት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሊቁ በመልክእ ነገሩን ሲያደንቅ ‹‹ጳውልስ ወጴጥሮስ አመ አፉክሙ ተኀትመ፣ ዘበሰማያት ወዘበምድር እስከ ንፍቀ ሰዓት አርመመ ››/‹‹ጳውሎስ እና ጴጥሮስ ሆይ፣ አንደበታችሁ በተዘጋ ጊዜ፤ በሰማይም በምድርም እስከ ግማሽ ሰዓት ዝምታ ሆነ ›› የሚለው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነትን በሚቀበልበት ጊዜ በቦታው ላይ የነበሩ የዓይን ምስክሮች እንዳሉት ሞቱም በተአምራት የተከበበ ነበር፡፡ እነዚህም ሰዎች በሰይፍ ከተቆረጠው ከቅዱሱ አንገት ደም እና ውኃ ፈልቋል ያሉ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ራሱ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት እንደ ነጠረችና በእነዚያም ቦታዎች ላይ ውኃ (ጠበል) መፍለቁን ተናግረዋል፡፡” ቅዱስ ጳውሎስ፣ ገጽ፡ 410 ቅዱሱ ሰማዕት ጳውሎስ ሆይ፣ እንደ ኤፌሶን ሽማግሎች ስለ ክርስቶስ የተሰየፈች አንገትህን አንድ ጊዜ አቅፈን እንስመው ዘንድ ብታድለን ምን ነበር?! #ኃምሌ 5 ሮም አደባባይ ላይ!
ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት እኔ ባሪያው ነኝ ማለት ነው። ባሪያው ነኝ ማለት የራሴን ፈቃድ የማደርግ አይደለሁም ፣ የእርሱን ፈቃድ የማደርግ እንጂ ማለት ነው። እኔን ደስ ባለኝ መንገድ የምኖር አይደለሁም ፣ እርሱን ደስ በሚያሰኘው መንገድ የምኖር እንጂ ማለት ነው። በህይወቴ ላይ ፣ ሙሉ ለሙሉ ስልጣን ያለው እርሱ እንጂ እኔ አይደለሁም ማለት ነው። ይህ መጀመሪያ comfort ላይሰጠን ይችላል። ነገር ግን የተጠራነው በcomfort እንኖር ዘንድ አይደለም። ለዚህ ነው የምስራቅ ኦርቶዶክስ አባት ሴራፊየም ሮዝ ፥ Orthodoxy can't be comfortable unless it is fake የሚሉት። ሁላችንም ለዚህ ራሳችን ለማዘጋጀት መጣር አለብን። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፥ "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብለን ራሳችን ለአንተ መስጠትን አስችለን።አሜን።
ክርስቶስ በምድር ላይ ያደረጋቸው እንዲሁም የተናገራቸውን ነገሮች በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር ብቻ የተነገሩት ሆነው እነዚያንም ለራሱ አድርጎ ሲናገር እናያለን። እነዚህም ማንም ፍጡር ብቻ የሆነ አካል ተነስቶ ለራሱ ሊናገራቸው አይችልም። እስኪ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን እንመልከት ትንቢተ ኢሳይያስ 40: --- ⁶ ..ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፤ የሰውም ክብሩ ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነው። ⁷ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው። ⁸ ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል። የሚል ቃል በትንቢተ ኢሳያስ እናገኛለን። ህዝቡ ሳር ነው ካለ በኋላ ሳሩም እንደሚደርቅ የአምላክ ቃል ግን ፀንቶ ለዘለአለም እንደሚኖር ይናገራል። በተመሳሳይ በብሉይ ኪዳን መዝ119: --- ⁸⁹ አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘለዓለም ይኖራል። በማለት ቃሉ ለዘለአለም የሚኖረው እና የማያልፈው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ያስቀምጣል። ወደ ሀዲስ ኪዳን ስንመጣ ክርስቶስ ይህንኑ ቃል ለራሱ ተጠቅሞት እናያለን ማቴ 24:35 እንዲሁም ማር13:31 ላይ እንዲህ ይላል "ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም" ይህ ክፍል የሚያሳየን ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። ፍጥረት ሁሉ ሰማይ እና ምድር :ሳር እና ቅጠሉ በሚደርቁበት እና በሚያልፉበት በመጨረሻው ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ግን የማያልፍ መሆኑን አስቀድሞ በብሉይም ተነግሯል። ይህ ቃል ለፍጥረት የሚነገር ሳይሆን ዘላለማዊ ለሆነው ለእግዚአብሔር ብቻ የሚነገር ነው።ስለዚህ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን የምናይበት አንዱ ክፍል ነው። p1; የእግዚአብሔር ቃል ለዘለአለም አያልፍም p2; የክርስቶስ ቃል ለዘለአለም አያልፍም then ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን ከዚህ እናያለን። ቅዱስ ጴጥሮስም በመልዕክቱ እንዲህ ሲል አስቀምጦታል 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:24-25 --- ²⁴ ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ ²⁵ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል።በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው። ለዘለአለም ቃሉ የማያልፍ ለዘለአለም የሚኖር ከፍጡር ማን ነው? ይህ ለፍጡር ወይም አምላክ ላልሆነ አይቻለውም ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልዕክቱ ትላንትናም ዛሬም እስከ ዘለአለም የሚኖር እርሱ ነው እንዳለው። ስለዚህ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን በማያልፈው ቃሉ መመልከት እንችላለን።
በእግዚአብሔር መልክ መፈጠር በውስጡ በርካታ ነገሮችን ይዟል። አመክንዮ(reason) አንዱ መልክ ነው። ነገር ግን ብዙም ስንጨነቅለት አይታይም። ግዴለሽ ከመሆን ባለፈም የምንገፋው ጥቂቶች አይደለንም። logical መሆን ፣ በጥልቀትና በትክክል ማሰላሰል የእግዚአብሔርን ስጦታ መጠበቅ ፣ እርሱንም መምሰያ በመሆኑ ፣ ሥነ- አመክንዮን ማጥናት ፣ እንደ አንድ መንፈሳዊ ተግባር ሊወሰድ ይችላል።