tgindex
Ethiopian SDA Songs in Lyrics

Ethiopian SDA Songs in Lyrics

Статистика
Последний пост
6 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
151
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
387
20 постов
Вовлечённость
256,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
76
1/48двое суток
87
1/72трое суток
93

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 🔴ፍቅር ነው ለነፍሴ ጥማት  የሚሆን  እርካታ ረሀቤን ሚያጠግብ ህይወቴን ሚያረካ እግሮቼን  ያፀና ከቶ  እንዳልወድቅ ላይጥለኝ ላይተወኝ በእጁ የያዘኝ ፍቅር ነው እየሱስ ፍቅር ነዉ ፍቅር ነው ጌታዬ ፍቅር ነው በሃጢአቴ ሊያጠፉኝ ያቀዱ ጠላቶቼ ዉድቀቴን ሲመኙ ሞቴን ሲጠባበቁ በጊዜው ሲደርስልኝ እውነተኛው ፈራጅ ታሪኬ ተቀይሮ ሞቴ ተሻረልኝ አልሆነም ጠላት እንዳሰበዉ እየሱሴ በፍቅሩ አስመለጠኝ ፍቅር ነው እየሱስ ፍቅር ነዉ ፍቅር ነው ጌታዬ ፍቅር ነው ለተሰጠኝ ፍቅር ምላሽም ባይሆንም የማቀርበው ምስጋና ዉለታውን ባይከፍለውም ይዤ   እመጣለሁ  የከበረ ስጦታዬን ሽቶዬን አፈሳለሁ ከእግሩ ስር ተንበርክኬ አይበቃም ይህም ለጌታዬ እራሴንም እሰጣለሁ ጨምሬ ፍቅር ነው እየሱስ ፍቅር ነዉ ፍቅር ነው ጌታዬ ፍቅር ነው ዘማሪ ምህረተአብ ሚልክያስ #ፍቅር_ነው #ምህረተአብ_ሚልክያስ #Fiker_new #Mihretab_Milkiyas       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴አይረባኝም አይረባኝም ከቶ አይሆነኝም ካንተ ውጪ እኔን አይጠቅመኝም ሲያዩት ያማረው የሚያጓጓው ካንተ ያልሆነው የሚስበው ወደ ሞት የሚወስደው መንገድ ነው ለኔ አይጠቅመኝም አይረባኝም ... ሰውን አስደስታለሁ ብዬ ጓደኞቼን ብሰማ አብልጬ ለጥቂት ጊዜ በኃጢአት ብደሰት ለኔ አይጠቅመኝም አይረባኝም ... ዘላለማዊ ክብሩን ትቶ የተዋረደ ለእኔ ሞቶ እንዳንተ እኔን እስከ ሞት የሚወድ ከቶ አይገኝም አይረባኝም ... ዓለምህን ሁሉ ትተሃል ለእኔ እኔም ላንተ ልኑር መድኅኔ አይረባኝም ... #Bereket_Feleke #Ayrebagnem #አይረባኝም #በረከት_ፈለቀ       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴የምጠብቅህ ተስፋዬ የምጠብቅህ ተስፋዬ ኢየሱስ መመኪያዬ/ሙሽራዬ ሌሊቱ ረዥም ነው ወይ በቶሎ አትመጣም ወይ ጠባቂዎችን ጠየቅኩ ስለ ሌቱ ርዝመት ስለውዴ መምጣት የሚቀረውን ወራት አይዘገይም አሉኝ በቶሎ ይመጣል ከደጁ አልርቅም ውዴ ይመለሳል የምጠብቅህ ተስፋዬ አንተ የጻፍክልኝን የፍቅር ደብዳቤ አንድም ሳላስቀረው ሁሉንም አንብቤ ልቤ ተነሳስቷል ሊያይህ እጅግ ናፍቋል መቼ ነው የምትመጣው ሰዓቱኮ ደርሷል የምጠብቅህ ተስፋዬ ያኔ የነገርከኝን ምልክቱን ሳየው አሁን በዘመኔ ወቅቱን ሳስተውለው ወደ አባትህ ሀገር ልትወስደኝ ጊዜው ነው የብቸኝነቴን ዘመን አሳጥረው የምጠብቅህ ተስፋዬ በልቼ አያጠግበኝ ጠጥቼ አያረካኝ ስለውዴ ሳስብ ይህ ምድር ሰለቸኝ ዓይኖቼ ተራቡ ልቤ እጅግ ናፍቋል ያን የቀድሞ ሀገር ልንሄድ ጊዜ ደርሷል የምጠብቅህ ተስፋዬ ይቆያል አትበሉኝ አታባቡት ልቤን ሊያየኝ ይቸኩላል አውቃለሁ ንጉሤን ያ የፍቅር ድምጹ ዛሬም ይሰማኛል እኔን ሊያሳርፈኝ ውዴ ይመለሳል የምጠብቅህ ተስፋዬ #የምጠብቅህ_ተስፋዬ #Mamo_Petros_New_Song_SDA_Singer_Album_3       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴ጠብቀኝ ስንቱ አለሁ እያለ የቆመ መስሎት ከቤትህ ራቀ ዓለም አታልሎት የኔ ግን ፀሎቴ ሁልጊዜም አንድ ነው ከቤትህ እንዳልርቅ ጠብቀኝ እላለሁ ጠብቀኝ/4 ጌታዬ ጠብቀኝ ዓለም እንዳታታልለኝ ጠብቀኝ/4 አባቴ ጠብቀኝ ዓለም እንዳታስቀረኝ ጠብቀኝ በምህረት ያለአንተ መጓዝ አልችልም እጄን በእጅህ ካልያዝከው ለብቻዬ አይሆንልኝም የሚታየው ነገር እጅግ በበዛበት አይኔ እንዳያማትር ወደ ዓለም ውበት ጌታዬ ጠብቀኝ አንተን እንዳልክድህ እንዳልንሸራተት እጄን ያዝ በእጅህ ጠብቀኝ ጌታዬ ... ይህን ጉብዝናዬን ዓለም ሲፈልገው የሚማርክ ነገር ለልቤ እያሳየው ወደ ሞት ሊነዳኝ ከአምላክ ተለይ ሲል እንድይዝህ እርዳኝ ጌታ እንዳልታለል ጠብቀኝ ጌታዬ ... ወደዚህች ከተማ ሄጄ እነግዳለሁ በዚያም አተርፋለሁ ደግሞም እኖራለሁ ብሎ እያለ ልቤ ቀኑ እንዳያልፍብኝ ይህን ጉብዝናዬን ጌታ ክበርበት ጠብቀኝ ጌታዬ ... #ጠብቀኝ #Dawit_Kasa_SDA_Singer       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴ምህረትህን እሻለሁ ከሀጢአት ሰንሰለት ተብትቦ ካሰረኝ ካልተገራ ምኞት ጠፍንጎ ከያዘኝ ድል አድርጌ መውጣት መሄድ የተሳነኝ መንገዴን የሳትኩኝ ደካማ ፍጡር ነኝ በተሰበረ ልብ በእሽታ መንፈስ ዙፋንህ ስር አለው በእጆችህ ልዳሰስ ምህረትህን እሻለሁ ከነፍሴ አጥብቄ ፊትህ መጥቻለው መድከሜን አውቄ ሀኪሜ አንተ ነህ ውስጤን የምትፈውስ የቆሸሸውን ልቤን አንፅተህ ምትቀድስ የሱስ አልተሳልክም በውስጥ ማንነቴ ስጋዬን አንግሼ አልሾምኩህም በቤቴ ሀጥያት ሰለጠነ ነግሶ በህይወቴ መላቀቅ ተሳነኝ ከክፉ መሻቴ ነፍሴን ያጎበጣት የኃጢአቴ ቀንበር ይውረድልኝና ከላዬ ይሰበር ምህረትህን እሻለሁ ... በደሌ እጅግ በዝቶ ፊትህን ሰወረብኝ አለማስተዋሌ ከፈቃድህ አራቀኝ በዓመፃ ተግባሬ እጅጉን ተከፋህ በአስመሳይነቴ አዘንህ ተከዝህ አውቃለሁ በደሌን መተላለፌን ከፊትህ አትጣለኝ ይቅር ብለህ አንሳኝ ምህረትህን እሻለሁ ... #ምህረትን_እሻለሁ #Shino_Natanim_Choir       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴አጋፔ ባርኮቴን እቆጥራለሁ እዘረዝራለሁ ያደረግኽልኝን አውቄልሃለው ወደ ልቤ ጓዳ በሞገስ ገብተሃል ባልወደድኩህ ጊዜ ቀድመህ ወደኸኛል ምን ልበል ምን ልናገር እጄን በአፌ ላይ ከመጫን በቀር ልቤ ቀልጧል እጅግ ወደኸኛል ወዮልኝ አምላክ ቀርበኸኛል የዓይንህ ብሌን ነኝ እመሰክራለሁ በእጆችህ መዳፍ ላይ ቀረፅከኝ አውቃለሁ የሚደርስብኝን አንተ ታውቀዋለህ ተሸክመኸኛል በዘላለም ክንድህ ምን ልበል... አጋፔ ታላቅ ፍቅር አጥንትን የሚሰብር እስትንፋስ አይቀርልኝ ፍቅርህን ሳስብ ክቡር ስም ጣፋጭ ስም እኩያ የሌለው የምድር ዳርቻ ገልፆ የማይጨርሰው በማለዳ በሌት ፊቱ የማይቀያየር ባለ ብዙ ምህረት ፍቅር እግዚአብሔር ምን ልበል... አጋፔ ታላቅ ፍቅር አጥንትን የሚሰብር እስትንፋስ አይቀርልኝ ፍቅርህን ሳስብ       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴የእምነቴ ጀማሪ የእምነቴ ጀማሪ እየሱስ የእምነቴ ፈፃሚ እየሱስ የህይወቴ ጀማሪ እየሱስ የህይወቴ ፈፃሚ እየሱስ አንተን ብቻ እያየሁ ሁል ጊዜ መኖር ይሻለኛል በቤትህ መሪ ነህ ለህይወቴ ጌታዬ አቅጣጫን ጠቋሚ ጌታዬ የማትሳሳተው ጌታዬ የማትሰናከል ጌታዬ ታዲያ ሰውን ማየት ለምኔ  ዓይኔ ባንተ ይረፍ መድኅኔ ታዲያ ሰውን ማየት ለምኔ ልቤ ባንተ ይረፍ መድኅኔ የእምነቴ ጀማሪ ... ነውርን ሁሉ የናቅህ ጌታዬ በመስቀል የታገስክ ጌታዬ እኔን ልታድነኝ ጌታዬ ሁሉን ነገር የቻልክ ጌታዬ ታዲያ ካንተ ውጪ ማን አለ  ዓይን የሚጣልበት የት አለ ታዲያ ካንተ ውጪ ማን አለ ልብ የሚጣልበት የት አለ የእምነቴ ጀማሪ ... ቢያምኑህ የምትታመን ጌታዬ ቢጠሩህ የምትሰማ ጌታዬ ድካምን የምታውቅ ጌታዬ ትከሻህም ሰፊ ጌታዬ ቢደገፉብህ ታስመካለህ መች እንደሰው ችላ ትላለህ የእምነቴ ጀማሪ ... ሸምበቆም አይደለህ ጌታዬ ተሰብረህ አትዋጋ ጌታዬ አንተን ሲደገፉ ጌታዬ በእርግጥ ታጸናለክ ጌታዬ ቅጥቅጥ ሸምበቆን አትሰብርም የሚጤስን ጧፍ አታጠፋም ቸርነትህ በህይወት ያኖራል ደግነትህ በቤት ያፀናል የእምነቴ ጀማሪ ...       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴አትለፈኝ በህይወቴ ዘመናት እንዲያው ተቆጠሩ ለጌታ ሳልሰራ አመታት ነጎዱ ሲሰለቸኝ በላዬ ጊዜያትን መቁጠሩ ነፍሴ እንዲፈወስ ንካትን ናፈኩኝ አትለፈኝ ጌታ ፍፁም ሳትባርከኝ በመንፈስህ ሞልተህ እኔን ሳትሰራኝ ደካማ ልጅህ ነኝ ሀይልህ ሚያስፈልገኝ እባክህ ጌታ ሆይ አትለፍ ሳትነካኝ ሳትነካኝ ዳስሰህ ሳትፈውሰኝ አይተህ ለደረቁ አጥንቴ እስትንፋስን ዘርተህ ስሜን ሳትቀይረው ታሪኬን አድሰህ አትሂድ አባት ሆይ ከልቤ ደጅ ደርሰህ አትለፈኝ ጌታ ... መሄጃ መንገዴን ጨለማ ከበበኝ የዕውርነት ህይወት መኖሩ አቃተኝ ጌታዬ በልብህ ዳግም ራርተህልኝ ማዳንህን እንዳይ አይኖቼን አብራልኝ አትለፈኝ ጌታ ... አትለፈኝ ጌታ ... #አትለፈኝ #Hossana_Natanim_Choir       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴አዳም የት ነህ? አዳም የት ነህ x3 በገነት መሃል ፈለኩህ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጠራሁህ ባስቀመጥኩ ስፍራ ግን አጣሁህ በገነት መሃል ትኖራለህ ሀመልማሉን ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን ከዚች በለስ ከበላህ - ልጄ ሆይ አስተውል ሞትን ትሞታለህ ብዬ እንደነገርኩህ ጠርቼ ባቆይህ እስክመለስ ሄጄ አንተ ግን ቃልኪዳን አፍርሰህ - በድንገት ጠፋኸኝ ልጄ ሆይ ወዴት ነህ አዳም የት ነህ ... ስትሸሸኝ አለሁ ስከተልህ ስታለቅስ መጣሁ ላባብልህ አንተ ግን በጣም ጨክነሃል - ለምን ነው ሳቀርብህ መራቅን መርጠሃል ልጄ ሆይ ስማኝ እጣራለሁ አሁንም አዳም የት ነህ እላለሁ ደጋግመህ ከእቅፌ እየወጣህ - ነውና ባስቀመጥኩህ ስፍራ እንዳላጣህ አዳም የት ነህ ... ልጄ ሆይ ዛሬም እሻሃለሁ ካለህበት ቶሎ ና እልሃለው ለመጨረሻ ጊዜ ስመጣ - እባክህ ድጋሚ ከስፍራህ እንዳላጣህ ዝም ብዬ ሳየው ደጅህን እታዘበዋለው እጅህን በንስሐ ፊቴ ካልመጣህ የአዳም ዘር ለዘላለም መቃጠል ነው እጣህ ወንድሜ አንተስ እንደምን ነህ ጠፍተሃል ወይስ አለህ እንዴት ነህ እስኪ አንዴ ተመልከት ራስህን - ንቃ እና የምትገኝበት ስፍራህን           የአለምን ብልጭልጭ እያየህ ሳታስብ ከመንጋው የተለየህ ዛሬ ግን ነውና ፍፃሜ - ቶሎ ና ወደ በረትህ ግባ ወንድሜ አዳም የት ነህ ... #አዳም_የትነህ? #Hossana_Natanim_Choir       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 1 апр.2302из SDAsong

    🔴ይህ ተስፋ አለን ይህ ተስፋ አለን ልብን የሚያሞቅ የጌታ መምጣት ተስፋችን እምነት አለን ክርስቶስ የሰጠን በቃሉ ተስፋ መታመን አሁን ቀኑ ቀርቧል ነገድ ሁሉ ይነቃል በኃይልም ይዘመራል ሃሌሉያ መጣልን ይህ ተስፋ አለን ልብን የሚያሞቅ የጌታ መምጣት ተስፋችን #Meklit_and_Rahel_SDA_Singers #ይህ_ተስፋ_አለን       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 30 мар.21622из SDAsong

    🔴እስቲ ድምፄን ላሰማ እስቲ ድምጼን ላሰማ መቅደስህ ገብቼ በገናዬን ላንሳ ማልጄ ማልጄ ቅር ቅር ይለኛል ሳላመልክ ብወጣ ለተገባው ጌታ ምስጋናዬን ላብዛ ድምጼን አልቆጥብም ሰጥቶኛል አንደበት ዝቅ ዝቅ ብዬ ክብሬን ልጣልለት እስቲ ድምጼን ላሰማ ... እንዴት ያስችለኛል ዝም ብሎ መሄድ ለውለታው ምላሽ ጥቂትም ሳላደርግ ሳልቀንስ ሳልቆጥብ ልሰዋ ለውዴ እንዲህ ተደርጎልኝ አላስቻለኝ እኔን ኧረ ማን ነው እንደ አንተ ለእኔ የደረሰ ኧረ ማን ነው እንደ አንተ ልቤን ያሳረፈ #እስቲ_ድምፄን_ላሰማ #Wudassie_Hawassa_SDA_Choir_Song_Album_2       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 23 мар.21423из SDAsong

    🔴 ያልጠፋነው ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ነውና ርህራሄውም አያልቅምና በየማለዳ አዲስ ነውና ታማኝነቱ ብዙ ነው ጌታ እውነተኛ አባት ነው ፍርዱ ቅንና ፍትሃዊ አምላካችን ሰማያዊ እርሱ ሆኖ በከፍታ በታች ያለውን በዝቅታ ሁሉን ያያል ያውቃል ጌታ ሆኖም አልፏል በይቅርታ ያልጠፋነው ... ጌታ እንደስራችን ክፋት እንደበደላችን ብዛት ቢከፍለንማ ለሁላችን ማን ይተርፋል ከመሃላችን ግን ስናሳዝነውም አዝኖ አላጠፋንም ጨክኖ አለን ዛሬም በርህራሄው ምስጋናችን ለእርሱ ይኸው ያልጠፋነው ... በሰማይ ቢሆን በምድር የለም ከእርሱ ሚወዳደር በእርግጥም እርሱ ሀያል ነው ግን ማንንም የማይንቀው እጅግ የቆሸሸዉን ሰው በደሙ አጥቦ የሚያነፃው እንዴት ያለ ድንቅ ወዳጅ ነው በደለኛውን የሚምረው ያልጠፋነው ... #ያልጠፋነው_ከእግዚአብሔር #Yibarek_Tagese       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 20 мар.2012из SDAsong

    🔴አጽናኙ መንፈስህ አጽናኙ መንፈስህ ከኛ ጋራ ይሁን እንዳናሳዝንህ ሁልጊዜ ይውቀሰን የደረቀው ህይወት የሚለመልመው እርሱን ስናገኝ ነው የሚረሰርሰው መንፈስህ እንዳይሄድ ከመሀከላችን እባክህ ታረቀን ውዱ አባታችን ተግባራችን ሁሉ አንተን ቢያሳዝንም ከቁጣህ ተመለስ ምህረትህ ይብዛልን ጽድቅን አናደርግም ስራችን ጥፋት ነው የሀጥያት ጉዞ ነው ሁሌ የምንጓዘው ቢሆንም አምላክ ሆይ እኛን አትጣለን ይቅርታህ ብዙ ነው መጣን ተቀበልን መንፈስህ እንዳይሄድ ... ህግህን በመናቅ ብዙ ተጉዘናል ተግሳፅህን ንቀን ለዓለም ተግዝተናል ጌታ ሆይ ቀስቅሰን ልጆችህ እንንቃ ያጎረሰንን መንከሳችን ያብቃ መንፈስህ እንዳይሄድ ... ፍቅርህን ስትሰጠን እኛ ግን ስንገፋህ ብዙ ዓመት አልፎናል ከቶ ሳንረዳህ ዛሬ ግን አባት ሆይ ትዕግስትህ ገብቶናል ወደ አንተ መልሰን ቤትህ ይሻለናል አጽናኙ መንፈስህ ... መንፈስህ እንዳይሄድ ... #አጽናኙ_መንፈስህ #Abonsa_SDA_Choir_Song_album_2       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 17 мар.1952из SDAsong

    🔴የዚያኔ ምስጋና ይፈልቃል ዛሬ በምሬት በስቃይ ኑሮ ተከበናል በሀሳብ ጭንቀት በአእምሮ ህመም ተውጠናል ለቅሶ እና ዋይታ ዙሪያችን የከበበን ይቀርና ቅርብ ነው አይቀርም ከአፋችን ሊፈልቅ የድል ምስጋና የዚያኔ ምስጋና ይፈልቃል ከኢየሩሳሌም ከአንደበት ዝማሬ ይሰማል ለዘላለም እንዳለቀስን አንቀርም በእንባ ስቃይ አንኖርም የሞት ሀገር ኑሮ እንላለን በል ደህና ሁን በየወር በየሰንበት እናዜማለን ዝማሬያችን የዚያኔ ነው ሃሌሉያ የዚያኔ ነው እልልታ በባርነት ግዞት ረግጦን የገዛው ያ ረሃቡ ስንገባ ስንወጣ ለኑሮ ውድነት ማሰቡ እራቁትነት በዝቶ ድህነት በሽታ ህመሙ ያበቃል ያከትማል የአእምሮ ክስ ቅዠት ህልሙ በሆነው ባልሆነው ተከሰን የታመምንበት በጨካኝ አንደበት በምላስ ጦር የተወጋንበት አይኖርም ይፋቃል በክርስቶስ ደም ያ ጠባሳ ለዚያ እንሆናለን ያበቃል ያ ሁሉ አበሳ ዛሬ በጦር ሜዳ ላይ ነንና ተጨንቀናል ምርኮዋችን ተወስዶ ነጋ መሸ ምጥ ይዞናል በኃጢያት ረግረግ ውስጥ ያሉ ሲወጡ የዘፈቁ እልል ልንል ቀርቧል የዘመናት ተስፋ ሲመጣ ፃዲቁ #የዚያኔ_ምስጋና_ይፈልቃል #Beyene_Bedicha_SDA_Singer_album_5       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 15 мар.18911из SDAsong

    እጆቻችንን ወዳንተ ዘርግተናል በምድር ላይ የሚረዳን ካንተ ሌላ ማን አለና እግዚአብሔር ሆይ ከእኛ አትራቅ መንፈስህን አትውሰድብን አንተማ የራቅኸን ቀን ጉዳችን ነው መድኃኔአለም ስንጮህ የሚሰማ ስንዝል የሚያበረታን ካንተ ሌላ የለን ተስፋ እራራልን ስናጠፋ ከእጆችህ ስታበላን ብንል እንኳን አላበላኸን ይህማ ልማዳችን ጥንትም ያለ ነው በጉዞዋችን አቤቱ አትቆጣ ምህረትህ ወደ እኛ ትምጣ በክፉዎች መንገድ ጭራሽ አትሂዱ በዋዘኞች ወንበር ከቶ አትቀመጡ ብለህ የነገርከን ከልባችን ጠፍቶ እንዳንጎዳ አባት መንፈስ ከእኛ ርቆ መንፈስ ቅዱስ ለክብርህ ተጠቀመን #እጆቻችንን_ወደ_አንተ #HAWASSA_TABOR_SDA_CHOIR_ALBUM_1       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 13 мар.1761из SDAsong

    🔴ሰንበት ቅዱስ ብፁእ የሰንበት ቀን እግዚአብሔር የባረካት የፍጥረት መታሰቢያ ሁለመና የሚያርፍባት ፈቃዴን ከማድረግ ልጠበቅ ካንተ ብቻ ልስማ ልማር መፈጠሬን መቤዠቴን ወደኋላ ዞሬ ላስብ በአንዱ የበደለ በሁሉ በድሏል ብለሃልና እምነት ቢሆን ፀጋ ህግህን አይሽርምና ላንተ ያለኝን ፍቅር ላሳይ በመታዘዝ ልኑር ህግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ይሁን ፀጋም ወደ መታዘዝ አንተን ወደ ማክበር ይምራኝ ፈቃዴን ከማድረግ ልጠበቅ ካንተ ብቻ ልስማ ልማር መፈጠሬን መቤዠቴን ወደኋላ ዞሬ ላስብ በአንተ አርፋለሁ ብዬ ሰንበትህን ስጠብቅ ዲያቢሎስ መጣና ሹክ አለኝ ከብዙኃን ጋራ ገፋኝ ድሮስ እውነት ሰው መቼ አላት ጥቂቶች ብቻ ተቀበሏት ቅዱስ ብፁእ የሰንበት ቀን ... መልካም ሰንበት #ሰንበት #Kirubel_Manyazewal       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 12 мар.18512из SDAsong

    🔴 አምነዋለሁ ዛሬን አይቶልኝ ነው በስሜ የጠራኝ ከእናቴ ማህፀን ሳለሁ ገና አወቀኝ/x2 በእጆቹ መዳፍ ላይ ተቀርጫለሁ ከአይኑ ተሰውሬ እኔ መቼ አውቃለሁ/x2 ሁልጊዜ ይጠብቀኛል/x3 በእጁ ላይ ቀርፆኛል ሁልጊዜ ይጠብቀኛል/x3 እንደ ዓይኑ ብሌን ያየኛል አምነዋለሁ/x3 ጌታዬ ታማኝ ነው አምነዋለሁ/x3 ጌታዬ ታማኝ ነው ነገ ምን ይሆናል ብዬ አልጨነቅም እኔን የሚያስፈራኝ በፍጹም አይኖርም/x2 ሁልጊዜ የማይተኛ የማያንቀላፋ ታማኙ እረኛዬ ጌታ እኔ ጋር ነው/x2 ሁልጊዜ ይጠብቀኛል ... ትላንት ያሳለፍኩት የህይወት ዘመኔ ጌታ እንደሚረዳኝ ምስክር ነው ለኔ/x2 ስለ ነገ ደግሞ ቃል ተገብቶልኛል እኔ እረዳሃለሁ አትፍራ ብሎኛል/x2 ሁልጊዜ ይጠብቀኛል ... #አምነዋለው #Dawit_Kasa_SDA_Singer       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 11 мар.16121из SDAsong

    🔴ምስክር ነኝ እኔ አይቻለው በዓይኔ አይቻለው ልመናዬን ስትመልስ ጩኸቴን ስትሰማ አይቻለው ሰምቻለው ከምጠብቀው በላይ ተዓምር የምታሳይ ለማስበው በላይ ድንቅን የምታደርግ ለቃልህ እጅግ ታማኝ እውነተኛም ነህ እኔ ምስክር ነኝ አይቻለው ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም ከስጦታዎች በላይ ልጅህን ሰጥተሀል መዳኔም በእርሱ ሆኗል አዲስ ቅኔ ተቀኝቼ ባመጣ መስዋዕትንም በፊትህ ብደረድር የበረከቶችህን ያህል ምላሽ አላገኝም ላመስግንህ እንጂ ሌቱን ሙሉ ስደክም ስለፋ አድሬ አንተ በመጣህ ጊዜ በታንኳዬ ገብተህ መረብህን ጣል ባልከኝ ጊዜ ለአንድ ሁለት ብዬ ግን አንተ አትረፈረፍክልኝ ወደ ሰማይ ዓይኖቼን ባቀኛ በምድር ዙሪያም ብመለከት የእጆችህ ፍጥረት እንኳን ስራህን ያወራሉ ውብ እና ድንቅ ሆነ ልመናዬን አይተህ በጊዜ የምትመልስ ጩኸቴንም ሰምተህ ሰምተህ ዝም የማትል ዝናብን ለጻድቅ ብቻውን ለማትለይ እኔ ምስክር ነኝ አይቻለው #ምስክር_ነኝ #One_way_SDA_singers       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 10 мар.3 622219

    🔴 ጌታ መቼ ትመጣለህ ጌታ መቼ ትመጣለህ የሱስ መች ትመለሳለህ ሁሉንም አየነው ሁሉንም ሰማነው መምጣትህ ነው የሱስ እጅግ የናፈቀን ከአመፃ ብዛት ፍቅር ቀዘቀዘ  ኃጢአት ፅዋው ሞልቶ ከመፍሰስ ደረሰ አንብበነው ነበር የተናገርከውን ትንቢቱ ሲፈፀም ዛሬ ሁሉን አየን ጌታ መቼ ... ሰው ሁሉ ይሮጣል ጎህ ሲቀድ ማለዳ ሲመሽ ይመለሳል ውሎ ምድረ በዳ ልብ ሁሉ ለድካም ለህመም ተጋለጠ  የሱስ ያንተን መምጫ ተፈጥሮ ናፈቀ ጌታ መቼ ... የአምልኮ መልክ በዛ አፈ ጮሌነት ኃይማኖት ተዘርፏል በጨካኝ ጠላት አቤቱ ያስፈራል ዘመኑን ስናየው ምፃትህ አይዘገይ ምርጫችን አንተን ነው ጌታ መቼ ... አመፅ እጅግ ገንኖ ለሰው ፅድቅ መሰለው ሁሉም ተለማምዶት ወዳጁ አደረገው እንዴት ይቻልሃል ይህን አይተህ ዝምታ እንደ ተስፋ ቃልህ አሜን ማራናታ ጌታ መቼ ... #ጌታ_መቼ_ትመጣለህ #Mamo_Petros_SDA_Singer_album_2       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁

  • 🔴የአምላኬ ውለታ ድንቁን ስራ አይቻለሁ እኔም በአይኖቼ እመሰክራለሁ ዘወትር በህዝብህ ፊት ቆሜ የአምላኬ ውለታ ዘወትር እጅግ ብዙ ነው ምስጋና ዙፋኑን ይሙላው እርሱ ኃያል ነው አይረሳም አይረሳም የእርሱ ውለታ በሰማይም በምድርም ከፍ ይበል ጌታ ምርኮዬን መለሰልኝ ለእርሱ ይሁን ምስጋና ዘወትር እቀኝለታለሁ ባማረ ዜማ ስሙን ጠርቼ አላፈርኩም በሁሉም ነገር አምላኬ ብዬ አላጣሁኝም ለእርሱ ይሁን ክብር ሀዘኔ ይኸው ተለወጠ ዛሬ በደስታ ለዘላለም ከፍ ይበል የጌቶች ጌታ ቀን ጨልሞ ግራ ገብቶኝ ሳጉረመርም መላ ጠፍቶ ብቻዬን ሆኜ ሳለሁ በሃዘን የምስኪኖች አባት እንደሰው ቆሞ አላየኝም ለእኔም የፅድቅ ፀሃይ ወጣ ይንገስ ዘላለም እንደ ኢያሪኮ ዳገት ሆኖ ከፊት ለፊቴ እጅግ ከብዶ ያሰቃየኝ ሁሉ ጭንቀቴ በአምላክ ኃይል ተደረመሰ ቅጥሩ ፈረሰ ምን ተስኖት የእኔ አምላክ ሁሉን ድል ነሳ #የአምላኬ_ውለታ #Abera_Masebo_SDA_Singer       sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ   👇JOIN OUR CHANNEL👇           ▷ @SDAEnglish ◁             ▷ @SDAsong◁     ▷ @SDAInstrumentals ◁        ▷ @SDASongLyrics◁        👇JOIN OUR GROUP👇     ▷  @SDAinstrumental ◁        👇👇Inbox Chat 👇👇               ▷  @Simera1  ◁