🌅ኦርቶዶክሳዊ_የክርስትና_ሕይወት🌅
Статистика👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 📗ይህ ችልናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ምዕመናንን መንፈሳዊ ሕይወት ለማበርታት፣ ለማጠንከርና ለማጽናት ይረዳ ዘንዳ📗 🌄🌄 ✅የምክር፣ 🌄🌄✅የተግሳፅ፣ 🌄🌄✅የህይወትና 🌄🌄✅የሥርዓት ትምህርቶችና ጽሑፎች የሚቀርቡበት ቻናል ነው። 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
- Последний пост
- 20 февр. 2024 г.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/7vncH51xlpk
https://youtu.be/lkjNeU1dr0w?si=D1jCSD3HQiTSKKME
🛑🛑የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ የተዋህዶ ልጆች አክሊል ሚዲያ ተተኪ ዘማርያን የምናፈራበት መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ ተከፈተ አሁኑኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ለነፍስዎ ብዙ ነገር ያተርፋሉ@aklil media https://youtu.be/-S_ZG86A9Bc?si=0HlMPv5UnuqJ9Vv4
https://youtu.be/YVhWQgL2WHM?si=qgLT8LjuCCGmU1aa
https://youtu.be/1upthY0NBG4
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንኳን ለታላቁ ጾም አብይ ጾም የቅበላ መዘጋጃ ቀን አደረሰን አደረሳችሁ! በዚህ የዐብይ ጾም ዝግጅታችን ወቅት ሁላችን ክርስቲያኖች እንደሚታወቀው የመጀመሪያው ዓላማችን ከመምህረ ንስሐችን ጋር መገናኘት ነው:: የተጣላነውን መታረቅ የበደልነውን መካስ ለጾም ለጸሎት ለስግደት ለምጽዋት መልካምና በጎ ነገር ለማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር መነሳሳት:: የጸሎት የሰዓታት የኪዳን የቅዳሴ የስብከት ፕሮግራሞችን ለመካፈል ዕቅድ ማውጣት:: በመቀጠል የፀሎት መጻሕፍትን ማዘጋጀት መንፈሳዊ መጻሕፍቶችን ማዘጋጀት በዐብይ ጾም ወቅት የምንሳለማቸውን ገዳማት በዕቅድ በመያዝ ለበረከት ለመባረክ ለመቀደስ ዕቅድ ይዘን ዐቢይ ጾምን መጎዝ ያስጠቅማል:: #ቅበላ በዚህ ጽሑው ውስጥ ደግም ስለ ቅበላ አንዳንድ ነገሮች እንማማር:: ቅበላ ቃሉ ራሱ ወደ አንድ ነገር ነው የሚመራን:: አንድ የሆነ ነገርን መቀበል መጠበቀ ወደሚለው:: በዚህም አንድ የምንቀበለውን ነገር ለእንግዳው ነገር መዘጋጀት መዘጋጂያ ጊዜ ነው እንደ እንግዳው ዓይነት ክብር ዝግጅት በማድረግ:: በዚህም ምክንያት አሁን ከፊታችን የምንቀበለው ታላቅ የጾም እንግዳ አለ ታዲያ ይህን እንግዳ ለመቀበል ቅበላ እናደርጋል የምንቀበለውም እንግዳ ጾም ነውና በንስሐ ታጥበን ከቂም ከበቀል ርቀን ይህን እንግዳ መቀበልን ግድ ይለናል:: አባቶቻችን ዐብይ ጾም ከመግባቱ በፊት ለሰባትም ለሦስትም ቀን ጾምን ጾመው ቅበላ ያደርጋሉ:: ቅበላን በመብል በመጠጥ ሳይሆን ጾምን ራሱን ጹመው ቅበላ ያደርጉባታል አበው:: ምክንያቱም በጉጉት የሚጠብቁት የሚጠቀሙባት በዓመት የሚናፍቁት ታላቅ የጾም እንግዳ ሊቀበሉ ነውና! እንግዳ ሲመጣ እንደ እንግዳው ክብር መዘጋጀት ይገባልና:: እኛ ልጆቻቸው ዛሬ እንደሚታየው እንደነርሱ ባንሆን እንኳ እነርሱ የሰሩትን ሥራ ሠርተን ልንመስላቸው ይገባ ነበር:: ግን ፈጽሞ ተለየን ራቅናቸው ሆድ አምላኪዋች ስለሆን በፀጋም በረድሄትም ራቅናቸው:: #ቅበላ_ምግብን_በመበቀል_አልነበረም_በጾም_እንደ_አበው_ይገባ_ነበር_ግን_ለክርስቲያኖች_በማይገባ_በመብል_በመጠጥ_በዝሙት_በጭፈራ_በዳንኪራ_ጾምን_መቀበል_ነውር_ኢ-ክርስቲያናዊ_በሆነ_መንገድ_አደረግነው:: በዚህም ቅበላን በተሳሳተ አካሔድ ሔደን ዓለም በምተደሰኩረው ዲስኩር ተነድተን በጭፈራ በስካር በመብል እንዳናደርገው እንድንጠነቀቅበት የቤተ ክርሥቲያን የሥርዓት መጻሕፍት ያስተምረናል:: በማንኛውም ቀን ቢሆን ለክርስቲያን በዚህ ግብር መታደም መታየትም ማሰብም አይገባም:: በክርስቶስ ደም የከበረን ሰውነት በእንደዚህ ግብር ማቆሸሽ ተገቢ አይደለምና:: በየደብሩና በየገዳሙም ሱባኤ ያሰብንም ንስሐ ገብተን የበደልነውን ክሰን የቀማነውን መልሰን በፊት ከምንበላው ከምንጠጣው ቀንሰን በመጥን ብቻ ሳይሆን በዓይነትም ቀንሰን አስመሳይ ሳንሆን ሆነን መጾም መጸለይ መስገድ መመጽወት እንዳለብን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍት ይነግሩናል:: አበው "ከምግብ ከመከልከል ብቻ ጾምን እንጾማለን አትበሉ ይህንንም ጨምሩ ከክፉ ግብር መራቅም ጾማችንን ትክክል ታደርጋለች" ይላሉ:: ከጾም በኋላ በሚኖረው ሕይወታችን በረከታችንን ሳናስወስድ የተውነውን ግብር ተመልሰን ሳንደግመው ልንጓዝ ያስፈልጋል:: በዚህም የአባቶቻችን ልጆች እንባላለን አባቶቻችን የወረሷትን መንግስት በእውነት እንወርሳለን:: ለዚህም አምላከ ተክለ ሃይማኖት ይርዳን አሜን! ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን:: Ethiopian_Orthodoxdaily የተወሰደ።
የነነዌ ሰዎችና እኛ ከነነዌ ሰዎች በላይ ማን ክፉ ነበር? ከእነርሱ በላይ አላዋቂስ ማን ነበር? ("ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ" ተብለው ተጠርተዋልና፡፡) ነገር ግን እነዚህ አሕዛብ፣ እነዚህ አላዋቂ፣ እነዚህ አንድ ሰውስ እንኳን የጥበብን ነገር አስተምሮአቸው የማያውቁ፣ እነዚህ ከማንም ይኹን ከማን እንደዚህ ዓይነት ትእዛዝን ያልተቀበሉ ሰዎች ነቢዩ፡- “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” ሲል በሰሙት ጊዜ ክፉ ልማዳቸውን ኹሉ በሦስት ቀናት ውስጥ አስወግደዋል (ዮና.3፥4)፡፡ ዘማዊው ንጹህ፣ ደፋሩ ትሑት፣ ስስታሙና ጨቋኙ ራሱን የሚገዛና ደገኛ፣ ሐኬተኛውም ትጉህ ኾነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ያሻሻሉት ክፋታቸውን ኹሉ እንጂ አንዱን ወይም ኹለቱን ወይም ሦስቱን ወይም አራቱን አይደለም፡፡ “እንዲህ የሚልስ የት አለ?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነርሱን ሲወቅሳቸው የነበረውና፣ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” ብሎ የተናገረው ነቢይ መልሶ ደግሞ የዚሁ ፍጹም ተቃራኒ የኾነን ምስክርነት አስቀምጧልና፤ እንዲህ ሲል፡- “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ” (ዮና.1፡5፣ 3፡10)፡፡ ተመልከት! ከዝሙት ወይም ከአመንዝራነት ወይም ከሌብነት ራቁ አላለም፤ “ከክፉ መንገዳቸው” እንጂ፡፡ እንዴትስ ከዚያ ሊርቁ ቻሉ? ይህን እግዚአብሔር ያውቋል እንጂ ሰው ሊመረምረው አይችልም፡፡ እንግዲህ አሕዛብ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ክፋታቸውን ኹሉ ማስወገድ ከቻሉ፥ ለአያሌ ቀናት የተመከርንና የተዘከርን እኛ ግን አንዲት ክፉ ልማድን [ለምሳሌ መሐላን] ሳናስወግድ ስንቀር ልናፍር አይገባንምን? ከዚህም በላይ እነዚህ ሰዎች ቀድሞ ክፋታቸው ጣሪያ ደርሶ ነበር፤ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” የሚለውን ስትሰማ ከክፋታቸው ብዛት በቀር ሌላ ምንም ልትገነዘብ አትችልምና፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መልካም ምግባር ፍጽምና መድረስ ተችሏቸዋል፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለበት ቀናት ወይም የጊዜ ብዛት አያስፈልግምና፡፡ በተቃራኒው ይህ ፍርሐት በሌለበት ደግሞ የጊዜ ብዛት ምንም ጥቅም የለውም፡፡ የዛጉ ብረቶችን በውኃ ብቻ የሚያጥባቸው ሰው ምንም ያህል ጊዜ እነርሱን በማጠብ ቢያሳልፍም እነዚያን ዝገቶች ኹሉ ማስለቀቅ አይቻለውም፡፡ ወደ እሳት ጨምሮ የሚያወጣቸው ሰው ግን አዲስ ከተሠሩ ብረቶችም ጭምር ሳይቀር እጅግ ጽሩያን ያደርጋቸዋል፡፡ በኃጢአት የዛገ ልብም እንዲሁ በትንሽ በትንሹና በግድየለሽነት ኾኖ ዕለት ዕለት ንስሐ ቢገባም ምንም ጥቅም አያገኝም፡፡ ራሱን ወደ እቶን - ይኸውም ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሚጥል ከኾነ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ኹሉንም ማስወገድ ይቻለዋል፡፡ (በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፥ ፳:፳፩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)
видео или голосовое, без подписи
ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁል ጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ እንኳን አደረሳችሁ!
#የማኅበረ_ሥላሴ_አንድነት_ገዳም_ሙሉ_መልእክት_እንዲህ_ይላል፦ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ "በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱአምላክ አሜን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኛችሁና በደሙ የዋጃችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቤታችሁም ያላችሁ በህመም ምክንያት በሆስፒታል ያላችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ በጦር ሜዳም ያለችሁ እንዲሁም በተለያየ ስፍራ የምትገኙ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታችንን በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡ እኛ ማኅበረ ስላሴ እንድነት ገዳም የምንገኝ ማኅበረ መነኩሳት በሀገራችን ሰላም መታጣት ምክንያት ከሀዘናችን ጋር አምላክ አበው ክብር ምስጋና ይግባዉ ደኅና ነን፡፡ እግዚአብሔር ገና ሃያ ሁለቱን ስነ-ፍጥረት ፈጥሮ ሳያበቃ ሳጥናኤል በዓለተ ረቡዕ በሶስተኛዉ ሰማይ በጌታ ላይ በማመጽ በጀመረዉ ጸብ ምክንያት ከመላዕክቱ ጋር ተዋግቶ ተሸንፎ ወደ ምድር ተጥሎ እነሆ ያለ እረፍት ለሰባ ሺ አምስት መቶ አመታት በመላዉ ዓለም ደም ሲያፈስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ፡፡ ጌታ የተሰጠዉ የቀጠሮ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ታግሶታል፡፡ አሁን ግን ከወትሮዉ ለየት ያለዉ ነገር የእግዚአብሔር ቤተ - መቅደስ በሆነችዉና የቅዱሳን የአስራት ሀገር በተሰኘችው በኢትዮጵያ ሀገራችን የሳጥናኤል ጭፍሮች ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ብለዉ ዘምተዉ በታሪክም ያልሰማነዉ በዘመናችንማ አይተን የማናቀዉ የእርስ በእርስ እልቂት እንኳን ከክርስቲያን ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ድርጊት ተፈጽሟል እየተፈጸመም ነዉ፡፡ ሰይጣን ብቻዉን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ከሰዉ ጋር ሆኖ በሰዉ ልብ አድሮ ግን ምንም የሚቀረዉ የሀጢያት ሥራ የለም፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፡፲፭ ላይ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ ያለዉ የጌታ ቃል ተጥሷል፡፡ ቀድሞ አንድ ሰዉ ለሥራም ሆነ ለንግድ ወይም ለተለያየ ጉዳይ ወደ ማያዉቀዉ ወደ ሚያዉቀዉም በኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገር ወይም ክልል ሲዘዋወር ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ነኝ ብሎ አይጨነቅም፡፡ የእግዚአብሔር እንግዳ ተብሎ ከመሸበት ገብቶ እግሩን ታጥቦ ቤት ያፈራውን በልቶ ጠጥቶ ከመልካም ምንጣፍ ተኝቶ አድሮ ሲነጋ ተነስቶ መርቆ ቀሪዉን ምንገድ ይጓዛል፡፡ ዛሬ ግን ያ ቀረና የእግዚአብሔር እንግዳ እራቱ ጥይትና ገጀራ መጠጡ ደም ሆኗል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ ፳፭፥፵፪ ላይ የተጠቀሰዉ እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበላችሁኝም ብራብ አላበላችሁኝም የሚለዉ የጌታ ቃል ትዉልዱን እየተዋቀሰዉ ነዉ፡፡ በእርግጥም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ ብሎ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንደተናገረዉ እንግዶች የሰላም ተጓዦች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ነገር ግን የሰላም ሰዎችም አብረዉ ተጨፍልቀዉ የጥፋት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አሁንም ታግሶናል፡፡እኛ አሁን ከሞት የተረፍነዉ ከጥላ ያረፍነዉ በጽድቃችን አይደለም በቸርነቱ ለንስሐ ጊዜ ተሰጥቶን ነዉ እንጅ፡፡ ነቢያት ስለ ጥፋት ሲተነብዩ በሰዉ ልጅ ሐጥያት ከእግዚአብሔር የሚታዘዘዉን መቅሰፍት ማስገንዘባቸዉን እንጅ ጥፋት ዝም ብሎ ደርሶ የሚታዘዝ አይደለም፡፡ #አሁን_በኃጢያታችን_ምክንያት_እየተጎነጨነዉ_ያለዉ_መከራ_ከዚህ_በፊትብዙ_የተነገረ_ቢሆንም_በትንቢተ_ዮናስ_ታሪካቸዉ_እንደተጠቀሰዉ_እንደ_ሰብዓዊ_ነነዌ_ወደ_እግዚአብሔር_በጾም_በጸሎት_ሆኖ_በመለመን_በማልቀስ_መከራዉን_ማስቀረት_እንዲቻል_ቅዱሳን_በመጽሐፍት_አስተምረዉናል፡፡ በኖህ ዘመን ምድር በዉሃ ሙላት የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት ነዉ፡፡ በሎጥ ዘመን በሰዶም ሀገር የተቃጠለችዉና ከምድረ ገጽ የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት ነዉ፡፡ ዛሬስ እየተሰራ ያለዉ ኃጢያት በዚያ ዘመን ከነበረዉ ያንሳልን ? ያን ጊዜስ በንስሀ ላልተመለሱ ሰዎች ፈርዶ ያጠፋቸዉ አምላክ ዛሬስ ፈርዶ ማጥፋቱ ይሳነዋል ወይ ? አይሳነዉም እንዲያዉም እንደ ዘመናችን ኃጢያት ብዛትና ክብደት ላልፈረደብን እግዚብሔር እያመሰገንን ይህን መልዕክት በያላችሁበት ሲነበብላችሁ ከሰማችሁት በኋላ ወደ ልባችሁ ተመለሱ #ከእንግዲህ_ወዲህ_በዘር_በጎሳ_በቋንቋ_በሀገር_በብሔር_መለያየት_ይብቃ_መገዳደል_ይብቃ_መዘራረፍ_ይብቃ_መሰደድም_ይብቃ_አጠቃላይ_የጥፋት_ዘመቻ_ይብቃ፡፡ ወደ ቀድሞ ኢትዮጵያዊ አንድነታቸን እንመለስ በኅብረት ተቻችለን እንኑር፡፡ የኃጢያታችንን ካባ አዉልቀን በነብስም በሥጋም የሚያድነንን የንስሐ ካባ እንልበስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፥፲፪ ላይ እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ብሎ ጌታችን ባዘዘን መሰረት ጥላቻን አስወግደን የዘር ፣የጎሳ፣ የቋንቋ ፣ የክልል ልዩነት ሳይኖረን እርስ በእርሳችን እንዋደድ፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፬፥፳፯ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ያለዉ ጌታ ቃሉ አይለወጥም እና ይህ ከሆነ ብቻ እዉነተኛዉን ሰላም ማግኘት ይቻላል፡፡ የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ነብዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ምዕ ፩፥፲፱ ላይ ‹‹ እሺ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት ትበላላችሁ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኃለች የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና›› የሚለዉን የትንቢት ቃል ዛሬም በእኛ ኢትዮጵዊያን ላይ እንዳይደርስብን ለእግዚአብሔር ቃል እንታዘዝ እና ክፋትን ሁሉ ትተን ንስሀ ገብተን የምድርን በረከት እንብላ፡፡ አለበዚያ ግን ምሕረት በእጁ የሆነ አምላክ መዓተም በእጁ ነዉና ምርጫዉ ግን የእናንተ ነዉ፡፡ #በሀገራችን_ሰላም_ይሰፍን_ዘንድ_ማንኛዉም_ክርስቲያን_የተጣላ_ታርቆ_የበደለ_ክሶ_ይቅር_ተባብሎ_ከጥቅምት_፳፬_እስከ_ጥቅምት_፴_ቀን_፳፻፲፪ ዓ.ም ድረስ ልጅ አዋቂ ሳይለይ እስከ ዘጠኝ ሰዓት እየጾማችሁ በሀዘን በለቅሶ ምህላ በመያዝ ከእግዚአብሔር ምህረትና ይቅርታ በጋራ እንድንለምን እኛ የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ማኅበረ መነኮሳት ሁሉን በፈጠሩ በቅድስት ሥላሴ ስም አምላክን በወለደች በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በታላቅ አክብሮት መልዕክታችንን ለመላዉ ሕዝበ ክርስቲያን አስተላልፈናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም ይስጥልኝ የሞቱትን ሁሉ ነብስ ይማርልን የጠፋዉን የተቃጠለዉን የወደመዉን ንብረት ሆሉ ይተካላችሁ አሜን ይሁን ይደረግልን 🎚መምህር አባ ወልደ ሰንበት ነጋሽ 🎚የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም አበመኔት @Mnenteyiklo @Mnenteyiklo 🏳🏳🏳🏳🏳🏳🏳🏳🏳🏳🏳🏳
" እስመ ነገረ መስቀሉሰ ዕበድ ውእቱ በኀበ ኅጉላን ወበኀቤነሰ ለዕለ ድኀነ ኃይለ እግዚአብሔር ውእቱ- የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው:: 1ኛ ቆሮ.1÷18 እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓል!
видео или голосовое, без подписи
እንኳን ደስ አላችሁ የማህበረ ቅዱሳን የቴሌቭዥን ጣብያ የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ! ማህበረ ቅዱሳን (EOTCMK) NILESAT 7W...../Eutelsat 7/8 11555 V 27500 ♻️♻️♻️🌑♻️♻️♻️🌑♻️♻️♻️
ለኦርቶዶክሳውያን ! + አባቶቻችን ነገ ነሐሴ 30 ቀን አስቸኳይ ስብሰባ ያደርጋሉ፡፡ + ለምን ታዲያ እኛስ እንደ ምእመንነታችን ማድረግ የምንችለውን አናደርግም? + ለምን እነርሱ ሲሰበሰቡ እኛም አብረን የዓቅማችንን ያህል በፈቃደኝነት አንጾምም? + ለምን የዓቅማችንን ያህል ሌላ ጊዜ ከምንጸልየው በተጨማሪ ጸሎት አናደርስም? + አሕዛብ የነበሩ የነነዌ ሰዎች ሊመጣ ከነበረው መዓት በእውነተኛ ንስሐቸው በጾም በጸሎት ከተረፉ፥ ክርስቲያን የኾንን እኛ'ማ እንዲህ እንደ ዓቅማችን ብናደርግ እግዚአብሔር የበለጠ ይሰማናል፡፡ + ስለዚህ ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ወገኖቼ መንግሥት የሚሠራውን በቁዔት የለሽ ድራማ ትተን ይህን ሠናይ ሥራ ብናደርግ መልካም ነው፡፡ @yohansafework
"ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ...ክብር ለሚገባው ክብርን ሥጡ"! ሮሜ 13፡7 ቅድስናን፤እምነት፤ሰማእትነትን፤ ከሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተገኘ አምላክም በአንተ አምላክነቱ ተገለጠ ተመሰገነ፤ በአንተ እምነት ተደስቷልና። ቅድስናህን፣ክብርህን በመጠጥ ስም ሊነገድበት ሊጎድፍ አይገባውምና ስምህ ክብርህ በአምላክ ዘንድ ሞገስን አጊንቷልና.... እግዚአብሔርን እስከሞት ድረስ ታምነው ያከበሩት ቅዱሳኑን እግዚአብሔር ደግሞ የድል አክሊልን፣ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ሰጥቶ አክብሯቸዋልና እኛም በቃልኪዳናቸው በምልጃቸው ከጥፋት እንዲታደገን ቅዱሳኑን እናክብር! #ክብር_ለሚገባው_ክብር_እንስጥ! ❌ በሰማዕቱ ስም እና ስዕል የሚደረገውን የመጠጥ ንግድ እንቃወማለን!❌ @Mnenteyiklo @Mnenteyiklo 💐🍀💐🍀💐🍀💐🍀💐🍀💐🍀
እነሆ የቅዳሴ ተሰጥኦ መቀበያ በግዕዝ በአማርኛና በእንግሊዘኛ ለምዕመናን ያጋሩ @ethiopianorthodoxs
🔥 🔥 #እሳቱን_እንቆስቁስ 🔥 🔥 አንዲት ሴት ነበረች። እንጀራ ልትጋግር እሳት አያይዛ ምጣዷን ጣደች። እዛው ኩሽናዋ ውስጥ ስትንጎዳጎድ ለአፍታ ቆይታ ወደ ምጣዷ ዘወር ብትል... አንድ ትልቅ አይጥ መኻል ምጣዱ ላይ ጉብ ብሎበት ተመለከተች። ነደዳት፤ ተበሳጨች። በእልኽ እሳቱን ልትቆሰቁስበት፣ ልታነደውም ያዘጋጀችውን ፍልጥ የአይጡን ወገብ ትልበት ዘንድ አነሣች። (የአይጡን ወገብ ስትሰብር የምጣዱ 'ወገብ' እንደሚሰበር ትዝም አላላት።) ፍልጡን በኹለት እጇ ጠበቅ አ'ርጋ ይዛ ወደ አይጡ በማነጣጠር ከአናቷ በላይ አንደረደረችው። ካንደረደረችበት ወደ ፊት ከመሰንዘሯ በፊት ግን ነገሩን ኹሉ በሽንቁር አጮልቃ ስትከታተል የቆየችው ጎረቤቷ "እቴ! ፍልጡን ተይው! እሳቱን ቆስቁሺው" አለቻት። (እሳቱ ሲያቃጥለው በራሱ ይሔዳል በሚል እሳቤ)። ... #ምጣድ_የተባለ_ሰውነታችን_ነው_ሰብእናችን። #እሳት_የተባለች_ሃይማኖት_ናት_ተዋሕዶ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር" እንዲል። (ሉቃ. 12:49)። ምጣድ የተባለ ሰውነታችንን እሳት በተባለች ሃይማኖት ላይ ስንጥድ ኹሌም ቢሆን አይጡ ይመጣል። ካለ ምንም ኃፍረት መኻል ምጣዳችን ላይ ጉብ ይላል። #ዘረኝነት_አይጥ_ነው_ድንገት_ሳናስበው_በጣድነው_ምጣድ_ላይ_ጉብ_የሚል። ሰማያዊም ምድራዊም እንጀራን ለማብሰል የሚያስችል ግለት ሳይኖረን የሚሰፍርብን ጥቁር አይጥ። በመንፈሳዊነት ዋዕይ ካላቃጠልነው ሊቦጠቡጠን የተጫነን ሸክም። #አይጥ_ልብስን_ይቀዳል_በአንድነት_የተሰፋውን_ይለያያል_ዘረኝነትም_እንዲሁ_ነው_ሰብእናን_ይቀዳል፤ በአንዲት ሃይማኖት የአንድ አካል ብልት የሆንነውን ይለያያል። #ተሐድሶ_አይጥ_ነው_ምንፍቅና_ከተባለው_የአይጥ_ዝርያ_የተገኘና_በክሕደት_የሰባ_ጠብደል_አይጥ። እሳቱን ቶሎ ቆስቁሰን ምጣዳችንን አግለን ተለብልቦ ካልሔደ አደገኛና መርዛማ ነው፤ በ'ኩሱ' እንኳን ምጣዳችንን ለመበከል ወደ ኋላ የማይል ነውረኛ አይጥ ነው። ከቻለ ምጣዳችን እንዲሰበር ካልቻለ ደግሞ እንዲሰነጠቅ የማያደርገው ጥረት የለም። መዝሙር በሚመስል ዘፈን፣ ሽብሸባ በሚመስል ዝላይ ምጣዳችንን በማወዛወዝ ዱቄት ሊያደርግ የሚጥርና ተመስጦን የሚረብሽ አይጥ ነው። ያሰስነው ምጣድ ላይ ተቀምጦ እኛን በማበሳጨት ፍልጡን እንድናነሣ ዘወትር ይጋብዘናል፤ ዋና ዓላማው የምጣዱ መሰበር ነዋ! ዋናዎቹን አነሣን እንጂ እሳቱ ላይ ስንጣድ የሚወጡብን አይጦች ብዙ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ወዳጆቻችንም አይጥ ሆነው ይመጣሉ። ቤታችን ሽንቁር እስካለው ድረስ ብዙ የአይጥ ዝርያዎች ምጣዱ ላይ ለመውጣት መሽቀዳደማቸው አይቀርም። በዚህን ጊዜ ታዲያ እሳቱን በመቆስቆስ ፈንታ ፍልጡን ካነሣን የአይጦቹን ዓላማ አሳካን ማለት ነው። #በሃይማኖት_ፍቅር_ልቡ_የነደደ_ስንቱ_አይጡን_ለማባረር_ፍልጡን_አዘውትሮ_እያነሣ_ስንት_ምጣድ_ሰበረ! ወዳጄ ሆይ! አይጡ ተቃጥሎ እንዲሔድ እሳቱን ቆስቁሰው 'ባክህ። #ጸሎት_መቆስቆሻው_ነው_ጾም_ስግደት_ትምህርት_ቅዳሴ_ጉባኤ_ንስሐ_ቁርባን_ሱባኤ_ምጽዋት_ምግባር_ኹሉ_መቆስቆሻዎች_ናቸው። ይህ ማለት ግን በሰበቡ ተዘናጋ ማለት አይደለም። ዋና ዓላማህ እንጀራ የሚገኝብህ ምጣድ መኾን ነው። መቼስ አይጥ ባለበት ምጣድ እንጀራ እንደማይጋገር ግልጽ ነው። ስለዚህ እንጀራን ለማግኘት አይጡ መሔድ አለበት። መጀመሪያ አይጥ መሆኑን አረጋግጥ፤ ከዚያም አባረው! ግን አባራለው ብለኽ ምጣዱን እንዳትሰብር ተጠንቀቅ፤ እሳቱ መንደዱን አረጋግጥ፤ በርትተህ ቆስቁስ... የኔና ያንተ ትልቁ ችግር ለመቆስቆስ አዋጅ መጠበቃችን ነው። "እነ እንትና ለምን ለ3 ቀን ቆስቁሱ የሚል አዋጅ አያውጁም?" እንላለን። "አትቆስቁሱ" እንዳላሉ እንዘነጋለን። ላለመቆስቆስ ሰበባችን ብዛቱ! ታዲያ ምጣዱ እንዴት አይቀዘቅዝ!? ባልጋለው ምጣዳችን ላይስ አይጦቹ እንዴት አይፈነጩበት!? ወዳጄ ሆይ! #ለምጣዳችን_ደኅንነት_እሳቱን_እንቆስቁስ! ✍ ዲ/ን ሕሊና በለጠ 🔥🔥 @SPIRITUALITY 🔥🔥 🔥🔥 @SPIRITUALITY 🔥🔥
#አምስተኛ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞነበር ኒቆዲሞስ በመጀመር ላይ እንደ አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ የተመለከተው። "ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን "ሲልም ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ ብቻ መስሎት ስለነበር ነው። ጌታችን ግን ከሰማይ ተልኮ የመጣ መኾኑንና ነቢይ አለመኾኑን በኹሉም ቦታ ያለ መኾኑን በማብራራት አስተምሯል። በመኾኑም #ኒቆዲሞስ_ኾይ_እኔ_እዚህም_እዛም_አለኹኝ_እንደነቢያት_የምላላክ_አይደለኹም_በሰማይም_ከሰማይም_በታች_አለኹኝ_ሲል_ነው። ይህ እንግዲህ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዌ የመለኮትን ምሉዕ በኩለሄ መኾን አለማስቀረቱን ያስገነዝበናል። አይሁድ ለከባድ ስሕተት የተጋለጡት ክርስቶስን ውስን አድርገው እንደራሳቸው በማየት ነው። የሚናገራቸው ንግግሮች ይገባቸዋል ነገር ግን አይቀበሉትም። እርሱ እናንተ ሥጋዬን ብቻ በማየታችሁ ምክንያት ተራ ዕሩቅ ብእሲ ነህ ትሉኛላችሁ እኔ ግን በሰማይም በምድርም የመላኹ ነኝ በማለት ከሰማይ ከወረደው በቀር በሰማይ የሚኖር ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው እንጂ በማለት በአንቀጸ ኒቆዲሞስ ለአይሁድ ያስረዳው። ❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖ @SPIRTUALITY @SPIRTUALITY #ስድስተኛ_ከሰማይ_የወረደው_በራሱ_ፈቃድ_እንደኾነ_ወደ_ሰማይም_ያረገው_በራሱ_ፈቃድ_መኾኑን_ሲያስረዳ_ነው። ሌሎች ቢያርጉ እግዚአብሔር ነው የሚያሳርጋቸው የሚወስዳቸው ርሱ ግን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ስለኾነ በራሱ ሥልጣን ነው ያረገው። ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ማለት በሥልጣኑ ወረደ በሥልጣኑ ወጣ ማለት ነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ድል መንሣት ባለበት የነጋሪት ድምፅ እግዚአብሔር ዐረገ አለ(መዝ 46፥5)፤ ርሱ ዐረገ አለ እንጂ መላእክት አሳረጉት አላለም፤ በፊቱ መንገድ የሚመራ አልፈለገም፤ በዚያው ጎዳና ርሱ ዐረገ እንጂ፤ ኤልያስ በዚያ መንገድ እንደ ክርስቶስ እንዲህ ሊያርግ አልቻለምና የኤልያስ ባሕርይ በዚኽ መንገድ ሊያርግ አልቻለም፤ መላእክት ወደ ታዘዙበት ቦታ ወሰዱት እንጂ(2ነገ 2፥11) አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሚኾን የእግዚአብሔር ቃል መላእክትን የፈጠረ ነውና በሥልጣኑ ዐረገ፤ ስለዚህም ወንጌላዊው ሉቃስ የሐዋርያትን ሥራ በሚናገር መጽሐፍ ወደ ሰማይ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ርሱ አቅንተው ያዩ እንደነበር ተናገረ፤ አሳረጉት አላለም ወይም ተሸከሙት አላለም፤ ያረገበት ቦታ ገንዘቡ ነውና" ሃይ ዘቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ ምዕ 67 ክፍል 13 ቁጥር 12-15። ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም የጌታን ዕርገት እንዲህ ይገልጽልናል "#በራሱ_ሥልጣን_ተነሣ_ርሱን_ያስነሣው_ማንም_አይደለም_በሚያርግም_ጊዜ_ማንም_ርሱን_ያሳረገ_አይደለም። ኤልያስን አስመልክቶ ዕርገቱ በጌታ አማካኝነት የኾነ ነውና እንዲያርግ ያደረገው ጌታ ነው፤ ከዚህም የተነሣ በሠረገላ እና በእሳት ፈረስ የከበረ ሥነ ሥርዐት ተደረገለት(2 ነገ2፥11)፣ ምክንያቱም ወደ ዐረገበት ቦታ በራሱ ማረግ አይቻለውምና፤ የጌታችን ግን እንደተጻፈ ተለየ፤ ወደ ላይ ለመነሣት ምንም ዐይነት መንኮራኩር አላስፈለገውም፤ በአንድ ቦታ በተወሰነ ጊዜ የሚቀመጡት ሰው በአጋዥ መውጣት ያስፈልገዋል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ብቻ ነውና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱ እግዚአብሔር ነውና መንኮራኩር አያስፈልገውም "(ነገረ ክርስቶስ ገጽ 219-220)። በመኾኑም ጌታችን ከሰማይ በራሱ ሥልጣን የተዋሐደውንም ሥጋ በራሱ ሥልጣን እንዳሳረገ የሚያስረዳ ንባብ ነው። ሰማያዊ ሥልጣን ያለው የሥልጣን ባለቤት መኾኑን ማቴ 10 ላይ ለዐሥራ እንደወረደኹለቱ ሐዋርያት ሙታንን የማስነሣት፣ ድዊያንን የመፈወስ፣ አጋንንትን የማስወጣት ሥልጣን እንደሰጣቸው ያስገነዝበናል። ያም ብቻ የቅድስት ሥላሴን ልጅነት የምናገኘው እርሱን አምላክ ነው ብለን ስንቀበለው በሚሰጠን ሥልጣን ነው። መጽሐፍ ለተቀበሉት ኹሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይኾኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው ተብሎ በዮሐ 1 ላይ ሳይኾንተጽፏል። ❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖ @SPIRTUALITY @SPIRTUALITY #ሰባተኛ_ቅዱስ_አውግስጢኖስ_ደግሞ_ወደ_ሰማይ_የምንወጣበትን_መንገድ_ሊሰጠን_መውረዱንና_ወደ_ሰማይ_ይዞን_ወጥቶ_ደግሞ_የእግዚአብሔርን_ፈቃድ_የምናደርግበትን_ኃይል_ለእኛ_እንደሰጠን_ሲያስረዳ_ነው ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም የተባለው። ከሰማይ ከወረደው ሲል መንገዱን እንደሰጠን፤ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንረዳበትን ኃይል እንደሰጠን የሚያስረዳ ነው። #በኢየሱስ_ክርስቶስ_አምላክነት_ሥጋዌ_ስናምን_የሰማዩን_የእግዚአብሔርን_ፈቃድ_የምንረዳበትን_ጥበብ_ኃይል_እናገኛለን_ሲል_ነው። እንግዲህ መንገዷ ማለት እውነተኛይቱ ሃይማኖት ናት፤ነብዩ ሆሴዕ የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ናት ጻድቃን ይሔዱባታል ኃጥአን ግን ይወድቁባታል በማለት የገለጸልን ንጽሕት መንገዳች አንዲቷ ሃይማኖታችን ናት። በዚህች ርትእት መንገድ ስንጓዝ ፈጻሚያነ ፈቃደ እግዚአብሔር ወደ መኾን እንሸጋገራለን። ❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖ @SPIRTUALITY @SPIRTUALITY ስምንተኛ አኹንም ቅዱስ አውግስጢኖስ እንዲህ ይላል። #ባል_እናትና_አባቱን_ይተዋል_ከሚስቱም_ጋር_አንድ_ይኾናል_እንደተባለ_የቤተክርስቲያን_ሙሽራ_ክርስቶስም_አብን_አባቱን_ትቶ_ሲባል_ቅዱስ_ጻውሎስ_እንዳለው "እርሱ የእግዚአብሔር መልኩ ነው ቀምቶ እግዚአብሔር የኾነ አይደለም። ነገርግን የባሪያውን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ዝቅ አደረገ። ፊል 2፥7 በሚለው ነው። #እናቱን_ትቶ_ሲል_ከእናቱ_መወለዱን_ሲል_ነው_ከሚስቱ_ማለትም_ከሙሽሪት_ቤተክርስቲያን_ጋር_አንድ_ኾነ_ማለት_ነው። በዚህም ምክንያት ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል፦ ከሰማይ ከወረደው ጋር አንድ አካል ያልኾነ ወይም ከሰማይ የወረደው ያላደረበት ማንም ወደ ሰማይ ሊወጣ አይችልም። ከሰማይ በወረደው በእግዚአብሔር አሳራጊነት ካልኾነ በቀር ማንም ሊያርግ አይችልም። ይህ የሚያሳየው አንድነትን ነው። ቤተክርስቲያንን ያለ ክርስቶስ ማረግ አትችልም ሲል ነው። ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ሲኾን ቤተክርስቲያን ደግሞ አካሉ ናትና የቅዱሳን ኹሉ ዕርገት በባላቸው በክርስቶስ ወይም በራሳቸው በክርስቶስ የሚኾንና ርሱም አንድ መኾኑን የሚያስረዳ ነው። ስለዚህ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጎምደው ራሳቸውን በነፍስ በሽታ ውስጥ እንደከተቱት መናፍቃን ሳይኾን በቅድስናና በንጽህና አጥርነት ራሳቸውን ጠብቀው በእግዚአብሔር መንፈስ በተረዱት በአባቶቻችን ትርጓሜ መሠረት የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር እንድንጠጣ እግዚአብሔር ይርዳን አሜን። @SPIRTUALITY @SPIRTUALITY ❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር!❖ በዲ/ን ዮሐንስ
❖❖ #ከሰማይ_ከወረደ_በቀር ❖❖❖ በዚህ ሳምንት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን የጌታችንን ከሰማያት መውረድ ታስተምረናለች። #ከሰማይ_ከወረደው_በቀር_ወደ_ሰማይ_የወጣ_ማንም_የለም_እርሱም_በሰማይ_የሚኖር_የሰው_ልጅ_ነው ዮሐ 3፥13 የሚለው ምንባብ ይነበባል። በዚህ ሳምንትም ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለሚተነተን ማብራርያውን መመልከት ተገቢ ነው። ስለ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ስንናገር በውሰጡ #ስለ_አምላክነቱ_ፈጣሪነቱ_እግዚአብሔርነቱ_ስለ_ምሥጢረ_ተዋሕዶም_ጭምር_ነው_የምንነጋገረው። እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በሐዋርያትና በሊቃውንት መንፈስ ኾነው ለሚረዱ እውነተኛና ሐዋርያዊ ምእመናን የቅዱሳት መጻሕፍት ምሥጢር ተቀድቶ እንደ ማያልቅ የውኃ ምንጭ ስለኾነ ነፍሳቸው በትርጓሜ ትረካለች። አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያንን እውነተኛና ትክክለኛ ከሚያደርጓት ዐበይት ነገሮች ውስጥ አንዱ በሐዋርትና በሊቃውንት ትርጓሜ ላይ መመሥረቷ ነው። የሐዋርያትን ትምህርት የማትቀበል ጉባዔ በምንም መልኩ ትክክል ልትኾን አትችልም፤ በዚህም መሠረታዊ ምክንያት በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ትርጓሜ ላይ ክርክር ሲነሣ ሐዋርትና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ምን ብለው ተረጎሙት ብሎ መጠየቅ ቀዳማዊ ሊኾን ይገባዋል። ነቢያትና ሐዋርያት የጻፉትን መጽሐፍ ቅዱስ ብለን የምንጠራውን እንቀበለዋለን። ይህ መጽሐፍ ልክ እንዳልታረደ በሬ ነውና የግድ ምግብ ኾኖ ለመበላት ሦስተኞቹን የቤተክርስቲያን አባቶችን ይፈልጋል፤እነርሱም ልክ እንደ አራጆችና ሠርተው እንደሚያበሉ ሰዎች ናቸው። እንግዲህ አንድ ሰው ነቢያትንና ሐዋርያትን እቀበላለሁ ብሎ በእነርሱ የተጻፉትን ቅዱሳት መጻሕፍት ባያጣጥምና ባይመገባቸው እቀበላለሁ ማለቱ ስለምንድነው? በእርግጥ በሬ ሳይታረድ ሊበላ የሚችለው ለጅቦች እንጂ ለሰዎች እንዳይደለ የታወቀ የተረዳም ነገር ነው። ማንም ሰው ቢኾን እኔ ክርስቲያን ነኝ ካለ በነቢያት ትንቢት በሐዋርያት ስብከትና በሊቃውንት ትርጓሜ ማመን ግድ ይለዋል። ካልኾነ በጉን ይዞ አርዶ መብላት ባለመቻሉ ብቻ ሳይጠቀምበት ያልፋልና። እስኪ አኹን ያነሳነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በዚህ መንፈስ እንመርምረው፦ 👉 ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል #አንደኛ_ከሰማይ_የወረደ_ሰማያዊ_የኾነ_ደግሞም_ወደ_ሰማይ_የወጣ_ማንም_የለም_ማለት_ነው። ሰማይ ያለው በወል ስም ነው እንጂ ከአንደኛው ሰማይ ሲል አይደልም፤ ከአርያም የወረደ ወደ አርያምም የወጣ ማንም የለም ሲል ነው እንጂ። ቅዱሳን ሲጀመር ከሰማይ የመጡ አይደሉም በመኾኑም ከሰማይ ከወረደ የሚለው እነርሱን የማይመለከት መኾኑን ከተረዳን የሄኖክ፣ የኤልያስ፣ የዕዝራእና የሌሎችም ቅዱሳን ዕርገት። ከዚኛው ጋር አንድ እንዳልኾነ ግልጽና የተረዳ ነው። እነርሱ ከምድር ዐርገው ወደ ብሔረ ብፁዐን የሔዱ እንጂ ጥንቱን ከሰማይ የወረዱ አይደሉምና ለእነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተገለጸው ጋር ፈጽሞ አይጋጭም። እንዲያውም ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ተወሰደ፤ ሄኖክን እግዚአብሔር ወሰደው። ለእነዚህ ለኹለቱ ረዳት አስፈልጓቸዋል፤ ጌታችን ግን በራሱ ሥልጣን ምንም ረዳት ሳይሻ ነው ያረገው ይልና እነዚህ ኹለቱ ቅዱሳን የክርስቶስን ዕርገት በምሳሌነት የሚያሳዩ ናቸው፤ ሄኖክ ከሕገ ኦሪት በፊት ላሉት፤ ኤልያስ ደግሞ በሕገ ኦሪት ላሉት የክርስቶስን ሥጋዌና የተዋሐደውን ሥጋ ይዞ ማረግ የሚያመለክቱ ናቸው በማለት ወደተለየና ድንቅ ወደ ኾነ ምሥጢር ይስበናል። ❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖ 👉 #ኹለተኛ ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል ወረደ የሚለው ሥጋዌውን የሚያስረዳ ነው፤ ለእግዚአብሔር መውጣት መውረድ የለበትምና። ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር መኾኑ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ውስጥ የሚገኝ እውነታ ነው። ዮሐ 1፥1 የሐዋ 20፥ 28፤ ፊል 2፥7። ወጣ የሚለው ደግሞ የተዋሐውን ሥጋ አሣረገ ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ባለጸጋው እኛ በእርሱ ድህነት ባለጸጋ እንኾን ዘንድ ደሀ ኾነ በማለት እንደተናገረ፤ ዝቅ ብሎ እኛን ከፍ አደረገን ማለት ነው። በመጽሐፍ የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ እንደተባለ የእኛን መዋረድ ዐይቶ ሰው ኾኖ ሥጋ ማርያምን ተዋሕዶ ተዋርደን የነበርነውን ከፍ አደረገን ማለት ነው። በትሕትናው ልዕልናን ሰጠን ሲል ነው። ❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖ #ሦስተኛ አይሁዳዊያን ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ወደሰማይ ዐርጎ ዓሥርቱን ትዕዛዛት ይዞ መጣ ብለው ያምኑ ስለነበር #ከሰማይ_የወረድኩት_እኔ_ነኝ_እንጂ_ሌላ_ማንም_አይደለም_ብሎ_የአይሁድን_የተሳሳተ_እምነት_በመምህራቸው_በኒቆዲሞስ_በኩል_ለመግለጥ_ስለፈለገ ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደሰማይ የወጣ ማንም የለም አለ። ከእንግዲህ ወዲህ ሙሴ ወደ ሰማይ ዐርጎ ነው ትዕዛዛትን ይዞ የመጣው አትበሉ ከሰማይ የመጣሁት እኔ ነኝ ሙሴ ወደ ሰማይ ሔዶ አልመጣም ሲል ነው። ❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖ #አራተኛ_ምሥጢረ_ተዋሕዶን_ሲያስረዳ_ነው። ከማይ ከወረደው በቀር ወደሰማይ የወጣ ማንም የለም ርሱም በሰማይ የሚኖር የሰው ልጅ ነው ይላል። ይህንን ንግግር ሲናገር ጌታችን በሥጋው በምድር ነው የነበረው ኾኖም ግን በሰማይ የሚኖር የሰው ልጅ አለ በማለት ገለጸ፤ #ለምን_ቢባል_እግዚአብሔር_በኹሉም_ቦታ_ስላለ_ያን_በኹሉ_ቦታ_መኖርን_በተዋሐድኩት_ሥጋ_ገንዘብ_አድርጌዋለሁኝ። ሥጋ ከመለኮት ጋር ሲዋሐድ አንዱ የአንዱን ገንዘብ ገንዘብ ስለሚያደርግ፤ ምንም እንኳ ሥጋ ውስን ቢኾንም በምሥጢረ ተዋሕዶ ምሉእ በኩለሄ የኾነውን የእግዚአብሔርን የባሕርይ መገለጫ ገንዘብ አድርጌዋለሁ ሲል ነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ "ይህ የወረደው ኹሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ኹሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው "ኤፌ 4፥10 ያለው። የወረደውና የወጣው በተዋሕዶ አንድ ኾነዋል ሲልነው። ወዴት እንደወጣም ሲናገር ከሰማያት ኹሉ በላይ ነው የሚለው ይህም የሚያስረዳው አምለክነቱን ነው ከሰማያት ኹሉ በላይ ያለው አምላክ ነውና። ለዚህ ነው ቅዱስ ቄርሎስ ጌታችንን መድኃኒታችንን የሚከፍለው ኹለት አካል ኹለት ባሕርይ የሚለው ከአብ የተወለደው ወልድ ወደ ሰማይ ካረገው ልዩ እንደኾነ ወደ ሰማይ ያረገው ሰው ከአብ ከተወለደው ልዩ እንደኾነ የሚናገር አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደኾነ የማያምን የተወገዘ የተለየ ይኹን" ያለው ድር.ቄር ገጽ 265። ❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖
✝መጽሐፍን በመመርመር ተወስነህ እንድትኖር ዕወቅ በዚያውም ጸንተህ እንድትኖር ዕወቅ ይህን ያደረግህ እንደሆነ ራስህን ታድናለህ´´✝ 📚📚📚 📚📚📚 📙መምህረ አሕዛብ ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፋቸው መልእክታት መካከል ለግል ሰዎች የተላኩ መልእክታትም ይጠቃለላሉ። ከእነዚህም ወደ ጢሞቴዎስ የላካቸው ሁለቱ መልእክታት በኤጲስ ቆጶስነት ሲያገለግል ሊጠነቀቅባቸው የሚገቡ ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ የሚያስገነዝቡ ናቸው። በቤተ ክርስቲያን ደረጃ ሊኖር የሚገባውን ትክክለኛ ሥርዓት ከዘረዘረ በኋላ የሕዝቡ መሪ ሆኖ የተሾመው ራሱ ጢሞቴዎስ በሕዋሳቱ ላይ ሊሠራ የሚገባውን ሥርዓት አያይዞ ይጽፍለታል። ከእነዚሀ ምክሮች መካከል ከላይ በርእሳችን የጠቀስነው ኃይለ ቃል አንዱና ዋነኛው ነው። ቃሉ ሁልጊዜ መጻሕፍትን በመመልከት መኖር እንደሚገባ ይህን ማድረግም ያለውን በረከትም ይገልፃል። «ራስህንና የሚሰሙህን ታድናለህ» በማለት። ይህም መጻሕፍትን መመልከት የመዳንና ያለመዳን (የህልውና) ጉዳይ መሆኑን ያሳየናል። ነቢዩ በትንቢቱ «ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል» ያለውን ቃል ጌታ በወንጌል «ስኅትክሙ በኢያእምሮ መጻሕፍት» «መጻሕፍትን ባለማወቅ ሳታችሁ።» ብሎ ምክንያቱን ከመጻሕፍት ጋር ማገናኘቱ እውነትም መጻሕፍትን ካለማንበብ ስኅተት ሲብስም ጥፋት የሚመጣ መሆኑን ያስተምረናል። ሐዋርያው ደግሞ የጉዳዩን ታላቅነት በሚያስረዳ መልኩ «ወዘልፈ ሀሉ ባቲ» «ሁልጊዜ በእርሱ ኑር» በማለት መጻሕፍትን መመልከት የጥቂት ጊዜያት ሥራ አለመሆኑን አያይዞ ገልጿል። 📚📚📚 📚📚📚 📘በሁለተኛው መልእክቱ ላይ ደግሞ «ተአምር በኀበ መኑ ተምህርከ እምንዕስከ መጽሐፈ ቅዱሰ በሃይማኖተ ኢየሱስ ክርስቶስ» «ከሕፃንነትህ ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማን እንደተማርክ ታውቃለህና» በማለት በመጀመሪያው መልእክቱ ላይ የጠቀሳቸውን ትእዛዛት የበለጠ አብራርቷቸዋል። ሁልጊዜ አንብብ ብሎ ያዘዛቸው መጻሕፍት ከመጻሕፍተ ጥንቆላ የተለዩ ንጹሐት ከመጻሕፍተ ምኑናት የተለዩ ክቡራት እንደሆኑ ለማሳየት «ቅዱሳት መጻሕፍት» ብሎ ሲጠራቸው እነዚህም ልብ እንደፈቀደ የሚነበቡ ብቻ ሳይሆኑ የምንማራቸው መሆኑን ለማሳየት «እንደተማርከው» የሚል ቃልን አስቀምጦልናል። መማሩም ከሐሰተኛ መምህር እንደሆነ «ዕውርን ዕውር ቢመራው» ይሉት ብሂል ይፈፀማልና «ከእኔ እንደተማርከው ታውቃለህና» በማለት ለገበታ ሰው እንዲመርጡ ለትምህርትም (ለመፅሐፍትም) መምህር መምረጥ እንደሚገባ ተናግሯል። 📚📚📚 📚📚📚 📗ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ በትእዛዝ ደረጃ ብቻ የተገለፁ ሳይሆኑ በቅዱሳንና በቅዱሳን አምላክ በጌታ ሕይወት ውስጥ የተገለጡ እውነታዎች ናቸው። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ ጌታችን ወደ ምኩራብ ገብቶ የነቢዩ የኢሳይያስን መጽሐፍ ገልጦ እንዳነበበ ተጽፏል። ስለ ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም ታሪክ የተፃፈባቸው መጻሕፍትም እመቤታችን ቅዱሳት መጻሕፍትን ታነብ እንደነበር በተለይም «ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች» ከሚለው ክፍለ ትንቢት ስትደርስ «በዘመኗ ደርሼ ምነው ባገልገልኳት» እያለች ትመኝ እንደ ነበር ይተርካሉ። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል «ደስ ይበልሽ» እያለ ሲያበሥራት ከመዝኑ እንጋ አምኃ ይትአምኁ›› ‹‹እንዲህ ያለ ሰላምታን እንዴት ይቀበሉታል?›› ብላ መናገሯ እናቷ ሔዋን የሳተችበትን ታሪክ ከኦሪት መጻሕፍት መማሯን ያሳያል። በእነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በእነ ቅዱስ ቄርሎስ በገዳማት ብቻቸውን ተጥለው ባሉ በቅዱሳን ዘንድ መጻሕፍት የነበራቸውን ታላቅነት «እንዳንተርክ ጊዜ ያጥርብናል።» 📚📚📚 📚📚📚 📕በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ታዋቂነትን ያገኙ ሰዎች፣ ታላላቅ መሪዎችና ርቱዕ አንደበት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሰዎች በእርግጠኝነት አንድ የጋራ ነገር አላቸው ይህም ምንም እንኳን ምኑናት ቢሆኑም መጻሕፍትን ማንበባቸው ነው። መጻሕፍትን ማንበብ ነፍስን ለማዳን ለሌላውም የሕይወት መንገድ ከመሆንም ሌላ ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ ለመመልከትና አእምሮንም ለማስፋት ይረዳሉ። የመጻሕፍትን ጥቅም ለመናገር እጅግ ብዙ መጻሕፍትን ብንጽፍ እንኳ ሁሉን ዘርዝረን አንዘልቀውም። በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያውያን የራሳቸው ቋንቋና ጽሑፍ ያላቸው እንደመሆናቸውና አንባቢያን የሆኑ ሊቃውንት በፊታቸው እንደ አብነት ሳሉላቸው በንባብ የሰነፉ መሆናቸው ምንም ዓይነት ምክንያት ሊሰጠው አይችልም። 📚📚📚 📚📚📚 📒ስለዚህም እንደ ጢሞቴዎስ «ከሕፃንነትህ ጀምረህ» የሚለው ምስክርነት ባይሰጠንም እንኳ ለራሳችን ሕይወትና ሌሎቹንም ማዳን የሚገኝበትን ጥበብ የሚያስተምሩትን ቅዱሳት መጻሕፍት እናንብብ ከእውነተኛ መምህራን እንማር! «የተፃፈው ሁሉ እኛን ለመምከር ተፅፏል።» ተብሎ ተጽፏልና። ሮሜ 15፥3 📖ወስበሐት ለእግዚአብሔር!📖