- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 477
- 1/48двое суток
- 546
- 1/72трое суток
- 589
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ዉድ የት/ቤታችን ወላጆች የLKG ክፍል ተማሪዎች ክፍያ በsystem error ምክንያት ከመደበኛው ክፍያ ውጭ የተላከላቸው መልዕክት አሁን ስለተካከለ sms በተላከላቸው master ID በመጠቀም cbe birr; cbe bank ወይም የት/ቤታችን ግብ በአካል በመገኘት ክፍያ እንድትፈጽም እናሳስባለን። #.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
ዉድ የት/ቤታችን የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ከስር ያለዉን ድህረገጽ በመጠቀም ዉጤታችሁን ማየት እንደምትችሉ ለመግለፅ እንወዳለን። https://sidama6.ministry.et/#/result
የሲዳማ ክልል የ2018 የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ዉጤት ይፋ ሆነ
ዉድ የት/ቤታችን ተማሪዎች ዉጤታችሁን ከስር ያለዉን ድህረገጽ በመጠቀም ማየት እንደምትችሉ ለመግለፅ እንወዳለን። https://sidama.ministry.et/#/result
በሲዳማ ክልል የ2018 የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዉጤት ይፋ ሆነ ****
#.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
መምህርነት የሙያዎች ሁሉ አባት ስለመሆኑ የሚከራከር የለም። ሁሉም ሙያዎች በመምህርነት ድልድይ የተሻገሩ ናቸው። ተማሪዎቻቸውን እንደ ልጆች የሚያዩ አስተማሪዎችም ለአገር የሚጠቅሙ ዜጎችን በማፍራት በኩል ቀጥተኛ ሚና አላቸው። የተከበራችሁ የትምህርት ቤታችን መምህራን በእናንተ ዉስጥ ያለዉ ብርሃን የማይጠፋና በምታስተምሯቸዉ ልጆች ልብ ዉስጥ ለዘላለም የሚኖር በመሆኑ በ2018 ዓ/ም ላሳያችሁት ትጋትና ሙያዊ ስነ ምግባር ሌክ ሳይድ አካዳሚ ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል። #.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
ት/ቤታችን የ2018 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎቻችንን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል። ፍሬያማ ዜጋ መፍጠር የሁልጊዜ ግባችን ነዉ #.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
መሪነት ልደት ስለ ሕይወት፣ ዕድገትና አመራር ለመናገር ጥሩ አጋጣሚ ነው፤ ምክንያቱም ሰዎች በእንደዚህ ዓይነት ጊዜያት ውስጥ በተፈጥሯቸው ስለ ሕይወት ትርጉም በይበልጥ ያሰላስላሉ። ይህንን ቀጥሎ የቀረበዉን አጭር ታሪክ አንብባችሁ ከታሪኩ አንድ ቁም ነገር ትማራላችሁ። ፋኖስ እና የንጋት ኮከብ በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ሳሙኤል የሚባል አንድ ወጣት መምህር ይኖር ነበር። በየምሽቱ ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ሲመለስ አንዲት ትንሽ የዘይት ፋኖስ ይዞ ይጓዛል። የመንደሩ ሰዎች ብዙ ጊዜ ያዩት ነበር። ከዚያም አንድ ቀን "ያንን ደካማ ፋኖስ ለምን ትይዛለህ? ጨረቃ እኮ የበለጠ ታበራለች።" ብለው ይጠይቁታል። ሳሙኤልም ዝም ብሎ መንገዱን ይቀጥላል።በአንድ ወቅት ከባድ ዝናብ መንደሩን መታውና መንገዶቹ ጨለሙ፣ ብዙ ሰዎችም ከስራ ሲመለሱ እቤታቸው ለመግባት ተቸገሩ። ጨረቃዋም ከደመና በስተጀርባ ተሰወረች። በዚያን ምሽት ሳሙኤል ትንሹን ፋኖሱን አብርቶ በመንደሩ ውስጥ እየተጓዘ ሁሉም ሰው በሰላም ቤቱ እስኪደርስ ድረስ አገዛቸው። በማግስቱ ጠዋት አንድ ወጣት፣ "ያቺ ትንሽ ፋኖስህ እንዴት የዚህን ያህል ሰው ልትረዳ ቻለች?" ሲል ጠየቀው። ሳሙኤልም፣ "ፋኖሰ ከጨረቃ ጋር አይወዳደርም። በቆመበት ቦታ ላይ ብርሃን ይሰጣል እንጂ" ሲል መለሰ። ከዓመታት በኋላ ሳሙኤል ካስተማራቸው ሕፃናት መካከል ብዙዎቹ መሪዎች፣ መምህራንና ሙዚቀኞች ሆኑ። መምህራቸው በመንደሩ ውስጥ ደማቅ ሰው ለመሆን መቼም ቢሆን ሞክሮ እንደማያውቅ ያስታውሱ ነበር። እርሱ የሞከረው በፊቱ ያለውን መንገድ ማብራት ብቻ ነበር።የመንደሩ ሰዎችም የወጣቱን መምህር ተፅዕኖ ተገንዝበዋል ። ከታሪኩ የምትወስዱት ቁምነገር ይህ ነው እውነተኛ አመራርን መማር የእድሜ ገደብ የለውም።ይልቁንም ሌሎችን በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ መምራትና መንገድ ማሳየትን ለመለማመድ ለናንተ ለተማሪዎች ጊዜው አሁን ነው። የተሻለ ሀሳብ ካላችሁ ለጓደኞቻችሁ፣ ለመምራን እና ለወላጆቻችሁ ከማቅረብ ወደኋላ አትበሉ።ትናንሽ ድርጊቶች ብዙ ሰዎችን ሊያነሳሱ (ተፅዕኖ ሊያሳድሩ) ይችላሉና። መሪዎች ከማዘዛቸው በፊት ያገለግላሉ። መታዘዝ የምትችሉ አገልጋይ ልጆች እንደሆናችሁ ግልፅ ነው። ሆኖም ገዢ ሀሳብ አፍላቂ፣ ፈጣሪ እና የወደፊቱ የቴክኖሎጂ ዘመን መሪዎችም ለመሆን መነሳት አለባችሁ። አልበርት አንስታይን እና ሌሎች ታላላቅ ሰዎች እንደሚገልፁት፤ በዓለም መድረክ ምን እንደተሰጣችሁ ሳይሆን በተሰጣችሁ ዝንባሌና ክህሎት ምን እንደሰራችሁ የምትጠየቁበት ዘመን ከፊታችሁ ይመጣል። የአንድ ሰው ብርሃን ሙሉ ማኅበረሰብን ሊረዳ እንደሚችል የወጣቱ መምህር ተሞክሮ ከላይ ተጠቅሷል። ህልማችሁ ኳስ ተጫዋች መሆን ከሆነ በዚህኛው የዕረፍት ሁለት ወር ጀምራችሁ ዕዩት። ዶክተር፣ መሃንዲስ፣ አስተማሪ ወዘተ. በመሆን ወደፊት በቅታችሁ እንድትገኙ ዛሬ አንድ ነገር ተማሩ... ሞክሩ። የነገ ተፅዕኖ እና ስኬት የሚገኘውም በመልካም ስብዕና ነውና የባህርይ መስተካከልንም ትኩረት ስጡት። ስለዚህ፣ እናንተም በዚህ መንገድ እንድታስቡ አስታውሳችኋለሁ፤ አሁን ደግሞ የኔን ሀሳብ እነግራችኋለሁ ፦ "እያደግሁ ስመጣ በሰማይ ላይ እንዳለ ደማቅ ኮከብ ለመሆን አልተመኘሁም። ይልቁንም ሌሎች የህይወት መንገዳቸውን እንዲያገኙ እና የተፈጥሮ ችሎታቸውን እንዲያውቁ ማገዝ የምሻ ትንሽ ፋኖስ መሆን የዕለት ተዕለት ስራዬ ነው፣ በዚህም ደስተኛ ነኝ እላችኋለሁ።" መጪውን ጊዜ በበጎ አድራጎት ስራ፣ በመንፈሳዊ እና ሁለንተናዊ እድገት ስልጠና፣ በቋንቋ ስልጠና ላይ እንደምታሳልፉ እጠብቃለሁ። ባጠቃላይ ጥሩ የዕረፍት ጊዜ እንዲኖራችሁ እመኛለሁ። እወዳችኋለሁ።(መምህር ዳንኤል) #.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
ዉድ ተማሪዎች ስለእናንተ ስኬት ለሚተጉ አባቶች ፍቅራችሁን ግለፁላቸዉ። እወድሃለሁ አባቴ እንበል። #.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
የ2018 ዓ/ም የሁለተኛ መንፈቅ አመት የማጠቃለያ ፈተና ፕሮግራም
ለት/ቤታችን መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በመሉ ዉድ የትምህርት ቤታችን መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች የመምህርት መረተች አበራ ባለቤት ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ ትምህርት ቤታችን የተሰማዉን ጥልቅ ሐዘን ይገልፃል። ዉድ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የቀብር ስነ ስርዓቱ ነገ እሁድ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ስለሆነ ሁላችሁም የትምህርት ቤታችን ሰራተኞች ቀደም ብላችሁ በትምህርት ቤታችን ቅጥር ግቢ እንድትገኙ ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን። ትምህርት ቤታችን ለመላዉ ቤተሰቡ መፅናናትን ይመኛል።
የሒሳብ መምህር ከበደ ቡኖም ተከታዩን ምላሽ ሰጥቶናል። #.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
አንዳንድ የት/ቤታችን መምህራንና ተማሪዎች የ2018 ዓ/ም የሚኒስትሪ ዝግጅት ምን ይመስላል ብለን ለጠየቅናቸዉ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዉናል። #.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የተነቃቃ አዕምሮ በትምህርት አቀባበል ላይ ጥሩ በመሆኑ የኬጂ መምህራኖቻችን ከርዕሰ መምህርት ፉርኖ ጋር በመሆን የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።❤️❤️❤️❤️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #.ሌክ ሳይድ አካዳሚ #.ሐዋሳ ኢትዮጵያ
የ2018 ዓ/ም የስድስተኛና የስምንተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ተፈታኝ ተማሪዎቻችን በት/ቤታችን ርዕሰ መምህር በአቶ ንጋቱ ሰጥ አርጋቸዉ አጠቃላይ ስለፈተናዉና ተያያዥ ጉዳዮች በትላንትናው ዕለት ገለፃ ተደርጎላቸዋል።