tgindex
Teter Wuha ጠጠር ውሃ°( TW )°

Teter Wuha ጠጠር ውሃ°( TW )°

Статистика

በዚ ቻናል የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ዶግማ ቀኖና እና ትውፊትን እንዲሁም መፅሐፍተ ሊቃውንትን እና አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ኪናዊ ስራዎችን ይቀርብበታል ። የዩቱዩብ ቻናሌ ነው ጎራ በሉ፦ https://www.youtube.com/@teter-wuha_tw

Последний пост
10 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
141
0 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
21
29 постов
Вовлечённость
14,9%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
9
1/48двое суток
10
1/72трое суток
11

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ►          በእንተ ቅድስና                 ( በአማን ነጸረ ) -- በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን ሲባል፡- ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ሰማዕታት፣ ሊቃውንት (ጳጳሳት)፣ መናንያን /ገዳማውያን/፣ ደጋግ ሰብአ ዓለም ይጠቀሳሉ፡፡ -- ቅዱሳን ዜግነትና ተቋማዊ አጥር ባይኖርባቸውም በልማድ እንደየሚከበሩበት ቦታ ስፋትና ጥበት አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ እየተባሉ ይለያሉ፡፡ -- እርሱ ያከበራቸውን በቅድስና መቀበሉ አስቀድሞ በጉባኤ ደረጃ አልነበረም፤ በልዩ ልዩ መገለጥና በገቢረ ተአምራት ክብራቸው በአደባባይ ሲታወቅ እንጂ፡፡ -- ሰማዕታት የሆኑ እንደሆነ ምስክርነቱ የአደባባይ ነውና በቀደመው ዘመን በቶሎ ቅድስና ያገኛሉ፡፡ ሰማዕትነቱ ለርትዕት ሃይማኖት መሆን አለበት፡፡ ላመነበት ልዩ ልዩ ዐላማ የሞተ ሁሉ ሰማዕት አይባልም፡፡ ከቅድስና ስያሜ በኋላ ስለሚከተለው ብዙ ተብሏል፡፡ -- እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና ቅዱስ ባስልዮስ ያሉ በአፍም በመጻፍም የገነኑ አበው ተግባራቸውና ቅድስናቸው ከመጉላቱ የተነሣ ከቤተ ክህነቱ ቀድሞ ምዕመኑ በቅድስና ጠርቷቸዋል፡፡ ቅድስናው በገቢረ ተአምርና በራእይ የሚገለጥም አለ፡፡ --- በዚህ ዘመን ግን ከሞላ ጎደል በሁሉም ሐዋርያዊ ትውፊትን በሚከተሉ አብያተ ክርስቲያናት ቅድስና በቃለ ሲኖዶስ እንዲጸድቅ ይጠበቃል፡፡ የእኛም አካሄድ ተመሳሳይ ነው፡፡ -- ሌላው ግን በቤታችን ከቃላት ይልቅ ዐውድ ላይ አለማተኮር አሁንም ውዥንብር መፍጠሩ ይሠመርበት፡፡ መጻሕፍቶቻችን ‹‹ጻድቅ፣ ቅዱስ፣ ርቱዐ ሃይማኖት፣ ሰማዕት›› እያሉ የሚጠሯቸው፣ በስንክሳር ታሪካቸውን ወይም ድርጊታቸውን የመዘገቡላቸው፣ ሊቃውንት መልክእ የደረሱላቸው ልዩ ልዩ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ መልካም ቅጽሎች ስለተሰጧቸው ታቦት የተቀረጸላቸው ወይም ሊቀረጽላቸው የሚገባ፣ ገድል የሚጻፍላቸውና በፊታቸው መብራት የሚበራ ቅዱሳት ሥዕላት የሚሳሉላቸው ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ቅድስና ሲሰጥ በጥናት ቢደገፍም መልካም ነው፡፡ በተረፈ … በግል እንደ ሽልማት የሚሰጡ የቅድስና ስያሜዎች የዝርውነት ምልክቶች ናቸውና ባይለመድ መልካም ነው፡፡  ቅድስና በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ሥር እስከሆንን ድረስ በአወዛጋቢ ሁኔታ መሰጠት የለበትም፡፡ ካቶሊኮች ቅድስና ሲሰጡ “devil’s advocate” የሚሉት ዚያን የቅድስና ስያሜ ተቀባይ እንበለ ሕፀፅ መሆን የሚያረጋግጥ የተቃራኒ ማስረጃ አጣሪ አካል እስከ ማቆም ይደርሳሉ፡፡ እነደዚያ እንሁን (infallibility እናረጋግጥ) ባንልም አንዱ በቅድስና ሌላው በወቀሳ ሊያነሳውን የሚችለን ሰው ቅድስና አሰጣጥ ለቅዱስ ሲኖዶስ መተው የተገባ ነው፡፡ በልማደ መጽሐፍ ‹‹ወሀሎ አሐዱ ብእሲ ጻድቅ ወኄር›› የተባለውን ሁሉ ቀን ሰይመን ታቦት ቀርፀን በቅድስና ካልጠራን አይባልም፡፡ መምህር በአማን ነጸረ

  • ​​​​​​ፍልሰታ ምን ማለት ነው? ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።" ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡›› ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡  ‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡››  ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡ ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡ እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡  ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  • The Perception Of Reality Is More Real Than Reality It Self.

  • ፆመ ፍልሰታ 1. ሐዋርያት ጾሙን ለምን ጾሙት? ጾመ ፍልሰታ ማለት ምን ማለት ነው? «ፍልሰታ» የሚለው ቃል «ፈለሰ» (ከቦታ ወደ ቦታ ተዛወረ /ተሻገረ) ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን፣ «ጾመ ፍልሰታ» ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ከሞተች በኋላ ከምድር ወደ ሰማይ የመፈለሷን (የማረጓን) ምስጢር በማሰብ የሚጾም ጾም ነው። 1_ለምን እንጾማለን? 👉የሐዋርያትን አርአያ ለመከተል፦ ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ አይተው ለመባረክ ያበቃቸው ዘንድ «እሱ(ቅዱስ ቶማስ)ያየውን እኛ ሳናይ» ብለው ያደረጉትን ጾምና ጸሎት አርአያ በማድረግ። 👉 የእመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገት ለማሰብ፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእመቤታችንን ሥጋ ከ መቃብር አውጥቶ ወደ ሰማይ ማሳረጉንና መነሳቷን በሃይማኖትና በደስታ ለማሰብ። 👉በረከትና ምሕረትን ለማግኘት፦ በጾም፣ በጸሎትና በንስሐ ወደ እግዚአብሔር ቀርበን የነፍስና የሥጋ በረከትን፣ የበደላችንን ይቅርታ ለማግኘት። 2. በጾሙ ወቅት ምን ማድረግ አለብን? 👉በቤተ ክርስቲያን በሚደረጉ የማኅበር ጸሎቶች፣ ቅዳሴና ምህላ ላይ መሳተፍ፣ በግልም ጸሎትና ስግደትን ጭምር። 👉 በንስሐና በቁርባን መዘጋጀት፦ ወደ ንስሐ አባት ቀርቦ ንስሐ መግባትና ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል። 👉 ለተቸገሩት ወገኖች ምጽዋት መስጠት፣ ሰላምንና ፍቅርን ከሰው ሁሉ ጋር ማጠናከር። 👉ከምግብ ብቻ ሳይሆን ከአንደበት፣ ከአእምሮና ከዓይን ኃጢአት በመጠበቅ በእውነተኛ መንፈሳዊ ህይወት ማለፍ። ድጂታል ሚዲያም እንቀንስ።ዓይን ክፉ ከማየት፥ጆሮም ክፉ ወሬ ከመስማት፥ ይቆጠቡ! 3. የሰበኑ (የልብሷ) ምስጢር ቅዱስ ቶማስ በደመና ሲመጣ እመቤታችን የተገነዘችበትን ሰበን (ጨርቅ) ሰጥታዋለች። ሐዋርያትም ለበረከት ተካፍለውታል። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ በካህናት እጅ የምናየው ነጭ ጨርቅ (ማኅፈድ) የዚሁ የሰበኗ ምሳሌ ነው! ጾመ ፍልሰታን በፍቅርና በበረከት እንድንጾም የእመቤታችን አማላጅነት እና እናትነት ፍቅሯ ይደርብን ።

  • የመንፈሳዊ ጦርነት መዘንጋት "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።" ኤፌ 6÷12 አንድ ክርስቲያን ጠላት መኖሩን ካላመነ፣ ለጦርነቱ የሚያስፈልገውን መንፈሳዊ ጋሻ (ጸሎት፣ ጾም፣ ስግደት) አይጠቀምም። ሰይጣን የለም የሚለው ሐሳብ የራሱ የሰይጣን ስትራቴጂ ነው። ይህን በማመን ሰው የጦርነትን ሕልውና ይክዳል። ቅዱሳን መላእክትን "ርዱኝ" ብሎ መጠራት ማለት በጦርነት ውስጥ እንዳለን ማመን ነው። የመንፈሳዊ ጋሻ መዘንጋት ከኃጢአት ይልቅ እግዚአብሔርን መምረጥ ያቃተን፣ ጦርነት ውስጥ መሆናችንን ስለምንረሳ ነው። ጦርነት ውስጥ መሆናችንን ስናውቅ ደግሞ፣ ቅዱስ ሚካኤልን መጠራታችንና መንፈሳዊ ሥርዓታችንን (ጾምና ጸሎት) መያዛችን ለድል ያበቃናል። ኃጢአት የሰይጣን መረብ ከሆነ፣ ያንን መረብ ለመበጠስ በራሳችን ኃይል አንችልም ሰይጣን የለም ብለን ስናስብ በየዕለቱ ለሚገጥሙን ፈተናዎች የእግዚአብሔርን ኃይል፣ የቅዱሳን መላእክትን አማላጅነት እና የቅዱሳን አባቶችን ተራዳኢነት አንሻም ይህ ደግሞ በኃጢአት ጦርነት ውስጥ ብቻችንን እንድንቀር ያደርገናል። ​ የጠላት መኖርን መዘንጋት ለኃጢአት መሸነፍ መጀመሪያ ነው። ከኃጢአት ይልቅ እግዚአብሔርን መምረጥ ያቃተን፣ የጠላትን (የሰይጣንን) ተንኮል እና የኃጢአትን አደገኛነት አቅልለን ስለምናይ ነው። ሰይጣን የለም ብለን ስናስብ፣ "ለኃጢአት አይሆንም ማለት" የሚል መንፈሳዊ ግዴታ አይሰማንም። ቅዱስ ኒኮላይ እንደሚያስተምሩት ጠላት ድብቅ ከሆነ መከላከያውም ድብቅ (መንፈሳዊ ሥርዓት) መሆን አለበት። መንፈሳዊ ሥርዓት (ጸሎት፣ ጾም፣ ንስሐ) ማለት የሰይጣንን መኖር እና ተንኮል አውቀን፣ ጋሻችንን የምንጠብቅበት መንገድ ነው። ከኃጢአት ይልቅ እግዚአብሔርን መምረጥ የሚያስችለን ኃይል፣ ጠላት መኖሩን በንቃት ስንረዳ ነው። ንቃት፦ በንቃት የምንኖር ክርስቲያኖች፣ ለኃጢአት "አይሆንም" ለማለት የሚያስፈልገን የመንፈሳዊ ሥርዓት ጉልበት ይኖረናል። "የሰይጣን ታላቁ እና በጣም አደገኛው ስልት፣ ሰዎች እሱ እንደሌለ እንዲያምኑ ማድረግ ነው። ሰዎች ሰይጣን የለም ብለው ሲያምኑ :- ○ በዚያው ልክ መንፈሳዊ ጥንቃቄያቸውን ይተዋሉ፤ ○ የጸሎት ጋሻቸውን ይጥላሉ፤ ○ የጾም መሣሪያቸውን ይጥላሉ እርሱም ይበልጥ በድብቅ እየሠራ እነርሱን ከእግዚአብሔር መንገዶች ያርቃቸዋል።" ሰይጣን የለም" ወይም "የሰይጣን ተጽዕኖ የለብኝም" ብለን ስናስብ፣ በየቀኑ የምንወድቅበት ኃጢአት የሰይጣን የጦር ሜዳ መሆኑን እንዘነጋለን። ጥንቃቄን መተው ጠላት መኖሩን የማያምን ሰው ራሱን አይጠብቅም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚያስተምረው፦ አንድ ክርስቲያን "ሰይጣን የለም" ብሎ ሲያስብ ለኃጢአት ፈተና ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ጋሻ (ጾም፣ ጸሎት፣ ንስሐ) አያስፈልገውም ብሎ በራሱ ይተማመናል። ይህ ደግሞ ለኃጢአት መሸነፍ ዋነኛው ምክንያት ነው። ኃጢአት የሰይጣን መረብ ነው፤ መረቡን ያላየ ሰው ደግሞ በቀላሉ ይያዛል። ሰይጣን እንደሌለ የሚያምን ሰው፣ ኃጢአትን እንደ "ፈተና" ሳይሆን እንደ "ደስታ" ወይም "ምርጫ" ብቻ ነው የሚያየው። "የሰይጣን ታላቁ ተንኮል እና የድል አድራጊነቱ መለኪያ፣ ሰዎች እሱ እንደሌለ እንዲያምኑ እንዲረሱ ማድረግ ነው።" ​እኛ "ሰይጣን የለም" ብለን ስናስብ፣ በዙሪያችን ባለው ፈተና ላይ ጥንቃቄ አናደርግም። ለክፉ ሀሳቦች "አይሆንም" ማለት የምናቆመው፣ በውስጣችን የሚሠራው የጠላት ተንኮል መኖሩን ስንዘነጋ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት ሰይጣን እንደሌለ ማመን ማለት ደግሞ፣ "ጠላት የለም" ብሎ ጋሻን መጣል ነው። ጋሻውን የጣለ ክርስቲያን ደግሞ ለኃጢአት በቀላሉ ይሸነፋል። "ሰይጣን የለም" ብሎ ማሰብ ሆነ መርሳት ለኃጢአት በር የመክፈት ትልቁ ስህተት ነው" ​ስለዚህ፣ ሰይጣን እንደሌለ ማሰብ ከኃጢአት ይልቅ እግዚአብሔርን መምረጥ የምናቅተበት አንዱ ዋና ምክንያት ነው። ይህን ስንዘነጋ፦ 1. ​ፈተናን እንደ ቀላል እናያለን። 2. ​የመንፈሳዊ ሥርዓታችንን (ጾምና ጸሎት) አስፈላጊነት እንንቃለን። 3. ​የኃጢአትን ሥልጣን ዝቅ እናደርጋለን። ቅዱስ ኒኮላይ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል "ዲያብሎስ ሰዎችን ለማታለል ከሚጠቀምባቸው እጅግ አደገኛ ዘዴዎች አንዱ፣ ሰዎችን 'ሰይጣን የለም' ብለው እንዲያምኑ ማድረግ ነው። ሰይጣን የለም ብለህ የምታምን ከሆነ፣ እንደ ጠላት የምትዋጋው የለም ማለት ነው። ጠላት የለም ብለህ ስታስብ ደግሞ፣ የሰማይ ሠራዊት አለቃ የሆነውን ቅዱስ ሚካኤልን 'ርዳኝ' ብለህ ልትጠራው አትችልም። በዚህም ምክንያት፣ በጦርነት ውስጥ እያለ ምንም መሣሪያ እንደሌለው ወታደር፣ ያለ ጥበቃ በኃጢአት ዓለም ውስጥ ብቻህን ትቀራለህ።"

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሪፐብሊኮች ከዘውዳዊ ሥርዓቶች በበለጠ የተረጋጉ ይሆናል፤ ይበልጥ እራሳቸውን መከላከል የሚችሉና ግዛታቸውን በጦርነት በማስፋፋት ረገድ ይበልጥ ስኬታማ ይሆናሉ፡፡ ይህም በተወሰነ መልኩ ለራስ መቆምን በማዝቀጣቸው ወይም በመመከታቸው ምክንያት ሳይሆን፣ ይልቁንም ለጉዳዩ ይበልጥ የሰፋ ነፃነት በመስጠታቸውና በዚህም ጀግና፣ መጨቆንን የማይሻ፣ በራሱ የሚተማመን ግለሰብን በመፍጠራቸው ምክንያት እንጂ፡፡   ለሪፐብሊኩ ዘለቄታ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ምንም ሆነ ምን፣ ሪፐብሊኩ ላይ የተጋረጠው ችግር ወደ ጨቋኝ ሥርዓት (tyranny) አለመለወጡን ማረጋገጡ ወይም የመውደቂያውን ጊዜ በተቻለ መጠን ማራዘሙ ላይ ነው፡፡ ሪፐብሊኮች የተረጋጉ እንደሆኑ መቀጠል የሚችሉት፣ ማንም ቢሆን ሌሎቹን ሁሉ በቀላሉ ለመቆጣጠር የሚያስችለውን መጠን ያለፈ ሥልጣን እንዲኖረው ሳይፈቀድለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ፈጠራ በተሞላበት መንገድ እንዲፎካከሩ ባስቻሉ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ በላይኛው መደብ የህብረተሰብ ክፍል ወይም የንግድ መስመሩን በተቆጣጠሩት እና በአጠቃላዩ ሕዝብ መካከል ግጭት መኖሩ አይቀሬ ነው። የላይኛው መደብ ብዙሃኑን ይጫነዋል፤ ብዙሃኑ ደግሞ ከዚህ ጫና ነፃ ለመውጣት ይመኛል። እንዲህ ያለው ግጭት የማይቀርና ለመፈንዳት ሰበብ የሚፈልግ ነው። በሮም ሪፐብሊክ በተራው ሕዝብ እና በመሳፍንቱ መካከል የነበረው ትንቅንቅ ማኪያቬሊ እንደምሳሌነት የተመለከተው ነው። ተፃራሪ ፍላጎቶች ጥሩ ሕጎች የሚፈጠሩበትን ኃይል ያመነጫሉ፤ ይህም እንዲህ ያለ ግጭት በአግባቡ በተዋቀሩ የፖለቲካ ተቋማት አማካኝነት ከተገደበ ነው። ማኪያቬሊ፣ በተግባር ያሉ የመንግሥት ዓይነቶች እንደየሕዝባቸው ሁኔታ እንደሚለያዩ ተረድቷል፤ ነገር ግን እሱ እንደሚያስበው፣ ከሁሉም የተሻለው የመንግሥት ዓይነት፣ አርስቶትል እንደሚደግፈው ዓይነት፣ ቅይጥ ሕገ-መንግሥት ያለው ሪፐብሊክ ነው፡፡ ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ትርጉም ያለው ድርሻ ሲኖረው ሁሉም በክብራቸው፣ በንብረታቸው እና በሰውነታቸው የዋስትና ስሜት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡ ሕጐቹ ግልፅ እና በሕዝብ የሚታወቁ ሊሆኑ ይገባል፡- ዜጐቹ ሳይቀጡ በከፍተኛ የእርግጠኛነት መጠን መሥራት የሚችሉትንና የማይችሉትን ሊያውቁ ይገባል፡፡ ጥቅል ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና መበረታታት ያለበት ሲሆን፣ ከመጠን ያለፈ የግለሰብ ሀብት እና ቅንጦት በሕጐች መገደብ ይኖርበታል፡፡ ለዜጐች ጥቅሞች ጐልህ እውቅና ሊሰጥ ይገባል፤ እንዲሁም ክብር እና ዝና ለሚሹ ሁሉ በመንግሥታዊ አገልግሎቶች ላይ እንዲሳተፉ መፈቀድ አለበት፡፡ ሕዝባዊ ሞራልን ለመገንባት እና ለመጠበቅ መንግሥታዊ ሃይማኖት መኖር አለበት፡፡ ሆኖም ይህ ሃይማኖት ደካማነትንና ተገዢነትን የሚያበረታታው ክርስትና መሆን የለበትም፡፡ ሪፐብሊኩን ለመጠበቅም ሆነ በወረራ ጦርነቶች ይዞታውን ለማስፋፋት በዜጐች የተዋቀረ ሠራዊት ሊኖር ይገባል፡፡ ሠራዊቱ ለትምህርታዊ እና ለወታደራዊ ዓላማ ይተጋል፡- በዜጐች ዘንድ ለባለሥልጣን ክብር መስጠትን፣ አርበኝነትን እና ወታደራዊ ሥነ-ምግባርን ያሰርፃል፡፡ በተጨማሪም ግለሰባዊ ህልሞች (ምኞቶች) ተፈጥሯዊ እና ጤናማ ተፈፃሚነት የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡ በሪፐብሊኩ ውስጥ ያለ ህይወት እጅግ የተመቸ መሆንም የለበትም፡፡ በችግር እና በአደጋ ጊዜ ህብረተሰባዊ ጥምረት እና ጥንካሬ ቀድሞውኑ ተረጋግጠዋል፡፡ እንዲህ ያሉ ጊዜያት በሕዝቡ ያለውን መልካምነት በማውጣት በአብሮነት እንዲሠራ ብርታት ይሆኑታል፡፡ በአጭሩ ማኪያቬሊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን የተለያየ ዓይነት እና መጠን ያለው ሥልጣን በመያዝና የያዙትንም ላለማጣትና የበለጠ ለማጠናከር የሚሞክሩ የግለሰቦች እንቅስቃሴ እንደሆነ አድርጐ ይወስደዋል፡፡ “The Prince” እና “The Discourses” ሥራዎቹ ጉልህ የሚባል ልዩነት የላቸውም፤ እርስ በርስ የሚቃረኑም አይደሉም፡፡ ሁለቱም የሰው ልጅ ተፈጥሮ ግለሰባዊ፣ ተፎካካሪና አስፈላጊ ሲሆንም ጨካኝ እና ሥርዓት አልበኛ የመሆኑን ምልከታ ይጋራሉ፡፡ “The Prince” ልዑሉ ከሰብዓዊ ተፈጥሮ የሚመነጩ ኃይሎችን ለራሱ በሚጠቅመው መልኩ እንዴት እንደሚቆጣጠር የሚያሳይ ነው፤ “The Discourses” ደግሞ እነዚህ ኃይሎች አንድነትን እና ሕዝባዊ ደህንነትን በሚያረገጋግጥ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ የሚጠቁም ነው፡፡ ሆኖም በሁለቱም ላይ የሚገኙት ኃይሎች ተመሣሣይ ናቸው፡፡ ብዙውን ጊዜ ማኪያቬሊ መንግሥታት ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ምክንያት ሊኖራቸው ይገባል (raison d’état) ለሚለው እሳቤ ጠንካራ ትኩረት በመስጠት ረገድ የመጀመሪያው የፖለቲካ ፅንሰ-ሐሳብ አፍላቂ እንደሆነ ይነገራል። ይህ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ይህ ብቻ አይደለም። ማኪያቬሊ፣ ለመንግሥት እርምጃዎች የሚታይ ምክንያት በሌለበት ሁኔታ እንኳን፣ “virtù” ብሎ ለሚጠራቸው የተግባር ብቃቶች ጥምረት አድናቆት አለው። የዚህም ምክንያቱ ሥልጣን ከሚያስከትላቸው ውጤቶች በላይ እራሱ ሥልጣን የተባለው ነገር ይበልጥ ይመስጠዋልና ነው። ለማኪያቬሊ፣ ሥልጣን ተግባራዊ የሚሆንባቸው የመጨረሻ ውጤቶች የቀዳሚነት ሳይሆን የሁለተኛነት ደረጃ ያላቸው ስለመሆኑ ልብ ማለት አይቀርም፡፡ ማኪያቬሊ በሁሉም መደበኛ መመዘኛዎች ጨካኝ እና ጨቋኝ የነበረውን የጣሊያን ወታደራዊ መሪ ሴዛሬ ቦርጂያ፣ የሞራል ጠባዩን ሳይሆን ውጤታማነቱን ያደንቅለታል፡፡ በጊዜው ከነበሩትም ሆነ ከቀደሙት ከአብዛኛዎቹ በተቃራኒው፣ ፖለቲካ ከሞራል አኳያ ገለልተኛ የሆነ ጥበብ ስለመሆኑ ማኪያቬሊ አጠንክሮ ያምናል፡፡ ከማንም በላይ ይህንን ፖለቲካዊ ክስተቶች እና ግንኙነቶች ሊተነተኑ የሚገባበትን ጉልህ ምልከታ የማበርከቱ እውነታ ነው፣ የእርሱ ልፋት በፖለቲካ እሳቤ ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ቦታ ሊሰጠው ያስቻለው፡፡ Fifty Major Political Thinkers, Ian Adams and R. W. Dyson ለበለጠ ንባብ ቀዳሚ ምንጮች፡ The Discourses, ed. L.J. Walker and B. Crick (Harmondsworth: Penguin, 1970). The Prince, ed. Q. Skinner and R. Price (Cambridge: Cambridge University Press, 1988). ተቀፅላ ምንጮች፡ Pocock, J.G.A.: The Machiavellian Moment (Princeton, NJ: Princeton University Press, 1975). Skinner, Q.R.D.: The Foundations of Modern Political Thought, vol. 1: The Renaissance (Cambridge: Cambridge University Press, 1978). Machiavelli (Oxford: Oxford University Press, 1981). Viroli, M.: Machiavelli (Oxford: Oxford University Press, 1998).

  • እንደሚፈጠር፣ ታማኝነት እንዴት እንደሚቀየር፣ የኃይል ምዛኑ እንዴት እንደሚለወጥ፣ እና ሌላ ሌላውንም አያውቁትም። በአንፃሩ ላልረጋው እና ለጊዜያዊው የተግባራዊ ጉዳዮች ዓለም፣ በጥቅሉ ሰብዓዊ ፍጡራን ግትር እና የማይለዋወጥ ባሕሪይ አላቸው። የሰው ልጅ ፀባይ እና ባሕሪይ፣ በዚህም ሁኔታዎችን የሚያካሂድበት መንገድ በመደበኛ መልኩ የማይለዋወጥ እና ተከታታይ ነው ማለት እንደሚቻል ማኪያቬሊ ተመልክቷል። በርግጥም ዘ-ልማዳዊ የሞራል ትምህርት የምንለው ሂደት እንዲህ ያለውን የማይለዋወጥ እና ተከታታይ ባሕሪይ እንዲያጎለብት ያደርገዋል (ከልጅነቱ አንዳንዴ ብቻ ወይም ለእርሱ ዓላማ ሲመቸው ብቻ ሞራላዊ እንዲሆን ተደርጎ አላደገማ)። ታዲያ ዕድል የምትጥለን ሁኔታ እንዲህ ላለ ተለዋዋጭነት የተጋለጠ በሆነበት ዓለም የማይለዋወጥ የአካሄድ ስልት መያዛችን ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? እራስህን የምታገኝበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ ሁልጊዜ በተመሳሳይ መንገድ መራመድ ወይም ተመሣሣይ እርምጃ መውሰድ የአደጋ መገለጫ መሆኑን ማኪያቬሊ ያስረግጣል። ይህም በይበልጥ በተለዋዋጭ እና በጭካኔያዊ የፖለቲካ ዓለም ውስጥ ለመኖር የምትሞክር ልዑል፣ በተለይም አዲስ ልዑል ከሆንክ እውነት ነው። እናም በጥቅሉ ለማኪያቬሊ “virtù” ማለት የዕድልን ግፊቶች ለመጋፈጥና አስፈላጊ በሆነ መንገድ ሁሉ ለመቅረፍ የሚያስችል የአንድ ግለሰብ ብቃት ወይም ችሎታ ነው። ፖለቲካዊ ስህተትን ለማስቀረት በሚደረግ ትንቅንቅ ውስጥ፣ ዕድል ልክ እንደ ነዝናዛ እና አቃጣይ ሴት እንደሆነች ይነግረናል። እናም አንድ ሰው ሊያስተካክላት ይገባዋል፤ አንዲት ነዝናዛ እና አቃጣይ ሴትን እንደሚያስተካክለው፤ ሰጥ ለጥ እስክትል በመምታት (ይህ የተባለበትን ዘመን ልብ ይሏል)። ልዑሉ ከዕድል ጋር በሚጋፈጥ ጊዜ በግትር የሞራል ባሕሪይ መወሰን አያዋጣውም። ከነገሮች የሚላመድ መሆን ይገባዋል። በውስጡ ያሉትን አንበሳነት እና ቀበሮነት ሁለቱንም የመጠቀም አቅም እና ዝግጁነት ሊኖረው ይገባል፤ ሰውም አውሬም የመሆን አቅም ሊኖረው ይገባል። ምህረት ማድረግ ውጤት ሲኖረው መሐሪ ይሁን፤ ሆኖም አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ ምህረት-የለሽ፣ ጨቃኝ እና አንቀጥቃጭ ይሁን። አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሀቀኛ እና እውነተኛ ይሁን፤ ነገር ግን አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥመው የሚዋሽ እና ቃሉን የሚያጥፍ ይሁን። ልዑሉ ሁኔታዎች የሚጠይቁትን ነገር ሁሉ ማድረግ ይገባዋል፤ እናም እነዚያ ሁኔታዎች ዘ-ልማዳዊ የሞራል እሴቶችን እና ክርስቲያናዊ ምግባሮችን እንዲገፋ ወይም እንዲጣረስ ካስገደዱትም የራሱ ጉዳይ፣ ያደርገዋል። የሥልጣን ማጣት አጋጣሚዎችን በሚጨምሩ መንገዶች መጓዝ፣ ወይም ሥልጣንን ይዞ የመቆየት አጋጣሚዎችን የሚጨምሩ መንገዶችን አለመከተል እራስን እንደመጣል ነው። አብዛኞቹ የማኪያቬሊ ዘመን ሰዎች፣ እንዲሁም አብዛኞቹ በኋላ የመጡ ተቺዎቹ እርሱ የጥፋት አስተመሪ ነው የሚል አቋም ነበራቸው፡፡ በአሥራ-ሰባተኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ፣ የማኪያቬሊ ስም ለጨቋኝ ሥርዓት (tyranny) እና ለከሀዲ ስያሜዎች ተለዋጭ አቻ ስም ሆኖ ነበር፡፡ ሆኖም ማኪያቬሊ እርኩሰትን ወይም ጥፋትን እንደማያስተምርና የእርሱም ልዑል እርኩስ እንዳይደለ ለመመልከት አያስቸግርም፡፡ ከመደበኛው የሞራላዊነት ምልከታ አንፃር፣ ማኪያቬሊ የፖለቲካ ተዋናዮች አስከፊ ነገሮችን እንዲፈፅሙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደሚያስገድዷቸው ለማመን እጅግ የተዘጋጀ ነው። ምናልባት ይህ አሳዛኝ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተከትሎ የአካሄድ ስልቱን መለዋወጥ የማይችል ልዑል ረዘም ላለ ጊዜ በልዑልነቱ ያለመቀጠሉ እውነታ እንዳለ ነው። ይህ የህይወት እውነታ ነው፤ እናም ይህ በመሆኑ እጅን ማሽሞንሞን ፋይዳ ቢስ ነው ሲል ማኪያቬሊ ያስባል። ብዙ ሰዎች ፀባያቸው ወይም ትምህርታቸው አስቀድሞ እንዲሆኑ ካደረጋቸው ማንነት መለወጥ አይችሉም፤ ወይም ደግሞ በአንድ መንገድ ተጉዘው ስኬታማ ከሆኑ፣ በሌላ መንገድ መሄድን እንዲለምዱ እራሳቸውን ማስገደድ አይቻላቸውም። አንድ ሰው የህይወቱን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተከትሎ የአካሄድ ስልቱን ወይም ፀባዩን መለወጥ ቢችል ዕድሉ መቼም ቢሆን አትለወጥም ነበር። እንደ ማኪያቬሊ ሐሳብ፣ ስኬታማ ልዑል ማለት ይህንን በትክክሉ ማድረግ የሚችል ሰው ነው። የዕድልን ውጤቶች የሚመክትበት ችሎታው ገደብ-የለሽ መሆነ መልኩ ተጣጣፊ፣ ነፋሱ በነፈሰበት ነፋሽ የመሆን ችሎታ ነው። የሚያደርገው ሁሉ የተደረገው ሁኔታዎች ስላስገደዱት ነው፤ እንዲሁ ባሕሪይው ወይም የሞራል መርሆዎች ስለመሩት አይደለም የሚያደርገው። ስለዚህም ልዑሉን እጅግ በቀላሉ ሞራል-አልባ (amoral) እንደሆነ አድርገን መግለፅ እንችላለን። ጥሩም ሆነ መጥፎ አይደለም፤ እርኩስም ሆነ ተቃራኒው አይደለም። የሞራል-አልባነት ባሕሪይ አለው። በአንድ በተወሰነ መንገድ እንዲራመድ የሚያደርገው ግትር ማንነት ወይም የሕሊና ልማድ የለውም። ግትር ማንነት ካላቸው ብዙ ሰዎች በተቃራኒው፣ ሙሉ ለሙሉ የሞራል ልዕልና ያለው የመሆን ወይም ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ጨካኝ የመሆን ችሎታ ያለው ሲሆን፣ ሁለቱንም እንዴት መሆን እንደሚችል ያውቅበታል። ዘ-ልማዳዊዎቹ የሞራል እሴቶች እንዲሁ የእርሱ ባሕሪይ አካሎች አይደሉም። አብዝቶም ሆነ አሳንሶ የሚያቀነቅናቸው ፍፁሞች አይደሉም፤ እንዲሁ ሲፈልግ በፈቃዱ የሚያነሳቸውና የሚጥላቸው የእርምጃ ስልቶች ናቸው። የማኪያቬሊ ሪፐብሊክ ማኪያቬሊ ስለሰው ልጅ ተፈጥሮ እና ባሕሪይ ያለው አመለካከት፣ ምንም እንኳን ሥልጣን በቀላሉ ሊጠና የሚችለው በአዲስ ልዑል ጊዜ ቢሆንም፣ ጤናማና ይበልጥ ስኬታማ የመንግሥት ዓይነት ከዘውዳዊ (monarchy) ይልቅ ሪፐብሊክ ነው ወደሚል ድምዳሜ አምርቶታል፡፡ ይህ “The Discourses” የተሰኘው ሥራው ዋና ጭብት ነው፤ “The Prince” ከተሰኘው እጅግ የተለየ፣ ነገር ግን በተመሳሳይ መላምት ላይ የሚንሳፈፍ ሥራው ነው፡፡ በዘውዳዊ ሥርዓት አንድ ሰው ላዕላይ ወይም ጠቅላይ ሥልጣን አለው፡፡ አንደ ሰው በእርሱ ተገዢ ከሆኑት ሁሉ የሚፈልቀውን ግንፈላ ለመገደብ በቦታው ተቀምጧል – ለህልውናው ካሰበም ሊገድብ ግድ ነው፡፡ በሪፐብሊኩ ውስጥ እያንንዱ ግለሰብ ልዑል ነው፤ እያንዳንዱ ግለሰብ ለደህንነቱ፣ ለነፃነቱ እና ለንበረቱ ከለላነት የራሱን “virtù” የማጎልበት እና ተፈፃሚ የማድረግ ችሎታ ያለው ሲሆን፣ በዚህም የሁሉም የሆነ ምቾት እና ደህንነት የሚያመጣ የጋራ ወይም ሕዝባዊ “virtù” ይፈጥራል። ማኪያቬሊ እንደሚለው፣ በዘውዳዊ ሥርዓት አንድ ሰው ብቻ ነፃ ነው፤ በሪፐብሊክ ግን ሁሉም ነፃ ናቸው፡፡ ይህ የጋራ “virtù” ከውድጅት ወይም ከመተሳሰብ የሚመነጭ አይደለም። ሰዎች የሚተባበሩት የጋራ ጥበብ እና ጥረት በጥቅሉ ግለሰባዊ ከሆነው ከማንኛውም እንደሚሻል በማወቃቸው ምክንያት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በተመሳሳይ ሰዓት ሰዎች ዋጋ ለሚሰጧቸው – ዝና፣ ክብር፣ ሀብት – ነገሮች ከሌሎች ጋር የሚፎካከር ቢሆንም፣ የራሱን ጥቅም የሚያስጠብቅለት እስከሆነ ድረስ ከሌሎች ጋር ይተባበራል፡፡ ሪፐብሊክ፣ የመተባበር ጥቅምን እና ከሌሎች ጋር አብሮ ጥሮ ግልፅ በሆነ መድረክ ራስን በማሳየት “virtù” የተባለውን ክህሎት የማጎልበት አማራጭን ያጐናፅፋል፡፡

  • ማኪያቬሊ፣ ልዑሉ በዋነኛነት በታቀደ የኃይል እና የማጭበርበር አጠቃቀም ላይ መመርኮዝ እንዳለበት ይጠቁማል። ምክንያቱም የሰው ልጅ የራሱ የራስ ወዳድነት ስሜቶች ባሪያ ስለመሆኑ ቅድመ-ግምት መውሰድ የሚገባን ሲሆን፣ ሕዝቦችን ምክንያታዊ የሆነ ፈቃዳቸውን በማግኘት ወይም ጥሩ የሆነ የሞራል ምሳሌን በማሳየት መግዛት (ማስተዳደር) ይቻላል ብሎ ማሰብ ፋይዳ-ቢስ እና ለአደጋ የሚጥል ነው። ምርጫ ባለበት ቦታ ሁሉ፣ ሰዎች ለሞራላዊ አስተውሎ መስፈርቶች ሳይሆን ለስሜታቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ። ስለዚህም የሌሎችን ስሜቶች አውቆ ጥቅም ላይ በማዋል ነው፣ እንዲያደርጉ የተፈለገውን የሚያደርጉ እንዲሆኑ ማድረግ የሚቻለው። በፖለቲካ ዓለም ውስጥ ምክንያትን ወይም አስተውሎን (reason) በአግባቡ መጠቀም የሚባል ነገር የለም። ሰብዓዊ ባሕሪይን የሚቆጣጠሩ አራት ስሜቶች እንዳሉ ማኪያቬሊ ይጠቁማል። እነዚህም ፍቅር፣ ጥላቻ፣ ፍርሃት እና ንቀት (አለማክበር) ናቸው። ፍቅር እና ጥላቻ እርስ በርሳቸው የሚጠፋፉ ወይም በአንድነት ሊቆሙ የማይችሉ ናቸው፤ በተመሣሣይ ሰዓት አንድን ሰው ማፍቀርም፣ መጥላትም የማይቻል መሆኑ ግልፅ ነው። በተመሣሣይም፣ አንድን ሰው መፍራት እና አለማክበር አይቻልም፤ እናም ፍርሃት እና ንቀት አይጣጣሙም። ሆኖም ፍቅር እና ፍርሃት ተጣጣሚ ወይም በአንድነት የሚቆሙ ናቸው፤ ጥላቻ እና ንቀት፣ ጥላቻ እና ፍርሃት፣ ፍቅር እና ንቀትም እንዲሁ ተመጋጋቢ ናቸው። በማያሻማ መልኩ ልዑሉ እንዲሰፍኑ የሚሻቸው ስሜቶችም ተመጋጋቢዎቹ ፍቅር እና ፍርሃት ናቸው። ሕዝቦች በገዢያቸው ላይ ጥላቻ እና ንቀት ካሳደሩ እነሱን መቆጣጠር የማይቻል ሲሆን፣ እንዲያውም በገዢው ላይ ለመነሳት ሰበብ የሚፈልጉ ይሆናሉ። ስለዚህም ፍቅር እና ፍርሃት እንዲሰርፁና ንቀት እና ጥላቻ እንዲወገዱ ያስፈልጋል። ለአንድ ገዢ ሥልጣኑን ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጉዞ ሊገጥመው የሚችለው እጅግ አስከፊው ነገር በሕዝቦቹ መናቅ እንደሆነ ማኪያቬሊ ይጠቁማል። እናም ምንም እንኳን ፍቅር እና ፍርሃት ከሁሉም የተሻለው ጥምረት ቢሆንም፣ ከፍቅር እና ንቀት ይልቅ ጥላቻ እና ፍርሃት ተመራጭ ነው። ፍርሃት ያለበት የትኛውም ጥምረት ጥሩ ነው፤ ምክንያቱም ተገዢዎችን በሚያድርባቸው ፍርሃት አማካኝነት መቆጣጠር ይቻላል ማለት ነውና። በሌላ በኩል፣ ሌላኛው ተጣማሪ ፍቅር ቢሆንም እንኳን፣ ንቀት ያለበት የትኛውም ጥምረት መቀረፍ ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የገዢውን የማስገደድ ሥልጣን የሚነጥቅ ይሆናልና፤ ምክንያቱም ፍርሃት እና ንቀት በአንድነት የሚቆሙ አይደሉምና። መፈቀር የግድ አስፈላጊ አይደለም፤ ነገር ግን መፈራት የግድ አስፈላጊ ነው፤ እንዲሁም አለመናቅ ደግሞ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ማለትም ቀጥ በቀጥ ሲገለፅ፣ የልዑሉ ሥልጣን መሠረት የተጣለው በኃይል ላይ እና ይህን ኃይሉን ያለርህራሄ የመጠቀም ፈቃደኝነቱ ላይ ነው። ይህም ልዑሉ እንዲኖረው የሚያስፈልጉት ብቸኛ ጥበባት ወታደራዊ ጥበባት ናቸው የሚለውን የማኪያቬሊ ማስረገጫ የሚመለከት ነው። የማኪያቬሊ ሬኔይሳንስ ዘመን ፀሐፊዎች ልዑሉ የጎለበተ እና ሰብዓዊነት ያደረበት መሆን አለበት የሚለውን ሐሳብ እንደመፈክር ወስደውት ቆይተዋል፤ ለጥበባት፣ ለሩህሩህነት፣ ለብልህነት እና ለመሳሰሉት ቦታ የሚሰጥ መሆን አለበት። ሆኖም ለማኪያቬሊ ለልዑሉ ተገቢ የሆነ ጥናት የጦርነት ጥበብ ነው። ለዚህም ምክንያቱ፣ ለማኪያቬሊ፣ ፖለቲካ ራሱ ድምፅ-አልባ ጦርነት ነው። በገዢው እና በተገዢዎቹ መካከል ያሉት ግንኙነቶች፣ በመጠን ደረጃ ባይሆንም እንኳን በይዘት፣ በሉዓላዊ መንግስታት መካከል ካለው ግንኙነት ጋር ተመሣሣይ መሆናቸውን ያምናል። ሀገራት ሁልጊዜም እንደደመና በተንዣበበ ወይም ደግሞ በተግባር ባለ ጦርነት ውስጥ እንደሆኑት ሁሉ፣ ተገዢዎችም ከገዢያቸው ጋር ዘላቂነት ባለው ጦርነት ውስጥ ናቸው። ስለዚህም የልዑሉ ትክክለኛ ፖሊሲ እርሱን ለመገታተር በቂ ኃይል ያለው ሰው አለመኖሩን ማረገጋገጥ ነው፤ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት ሰዎች ካሉ፣ ሥልጣን የመያዝ አጉል ፍላጎት ያለጥርጥር ለእርሱ ፈታና ይሆኑ ዘንድ እንደሚገፋፋቸው መገመት ይገባዋል። በሌላ በኩል፣ በሀገራት መካከል ጦርነት ለተወሰነ ጊዜ ሊራዘም እንጂ መቼም ቢሆን ሊወገድ እንደማይችላ ማኪያቬሊ ያስባል፤ ይህንንም ያልተገነዘበ ልዑል ወደ ጥፋት እያመራ ነው። የልዑሉን ኃይል የመፈተን አቅም ያላቸው አጎራባች ኃይላት ካሉ፣ ጦርነት አይቀሬ ነው፤ ምክንያቱም ከወዲያኛው ወገን የአደጋ ስጋት እስካልተቀረፈ ድረስ፣ ሁለቱም ወገኖች ደህንነት ተሰምቷቸው አርፈው አይቀመጡም። እናም ዕድሉን ካገኘ ማጥቃት፣ ካልሆነ ደግሞ የሌላውን የማጥቃት ዕድል በዲፕሎማሲ ማክሸፍ ሁሌም ቢሆን የተሻለ ነው። ኋላ ራስ ላይ ጉዳት ለማምጣት ጦርነትን ማቆየት ወይም ለወደፊት ማራዘም አይገባም። ከሁሉም በላይ ልዑሉ ሌሎችን መጉዳት ግድ ከሆነበት፣ ለዘለቄታው ኃይላቸውን በሚያሳጣቸው ወይም ከነጭራሹ በሚያወድማቸው መንገድ ማጥቃት አለበት። ይህን ካላደረገ፣ የመበቀል ፍላጎታቸው ተፈጥሯዊ ህልማቸውን ያጠነክረውና እርሱን መቀመቅ ለመክተት በሚያደርጉት ጥረት የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም። በዚህም የተነሳ የማኪያቬሊ የሞራላዊነት እና የፖለቲካ ምልከታ፣ ከተለመደው ጥሩ መሪ የግድ ጥሩ ሰውም ነው ከሚለው አቋም እጅግ የተለየ ነው። ጥሩ መሪ በራሱ አኗኗር እና በራሱ ተግባራት ላይ የሞራል ልዕልናን (virtue) ያሳያል፣ ለተገዢዎቹ መልካም ምሳሌ ይሆናል፣ የራሱን ብቻ ሳይሆን የጋራ የሆነውን ጥሩ ነገር ለማረጋገጥ ይጥራል፣ ከቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ምክር ይሰማል ከሚለው ጋር ይለያያል። “The Prince” ላይ ላየነው ማኪያቬሊ፣ ፖለቲካ ሥልጣን ወይም ኃይል ስለማግኘት እና የራስ አድርጎ ስለማስቀረት ነው። ‘virtue’ ለሚለው ቃል ክህሎታዊ መሰል ትርጓሜ ሰጥቶታል። ለማኪያቬሊ ‘virtue’ ማለት ሞራላዊነት ወይም የሞራል ልዕልና አይደለም፤ ይልቁኑ አንድ የሆነ የክህሎት ወይም የችሎታ ዓይነት እና እርሱን ጥቅም ላይ የማዋል ፈቃደኝነት በአንድ ላይ ተዳምረው እንደማለት ነው። (ምልከታዎቹን ለመተንተን ሲባል በጣሊያንኛ “virtù” የሚለውን ቃላ እንዳለ ለማስቀረት በተለምዶ ጥቅም ላይ ይውላል እንጂ አግባቡ ሌላ ነው።) ይህን ሐሳብ ማኪያቬሊ “The Prince” ላይ በገለፃቸው “virtù” እና “fortuna” መካከል ያለውን ተዛምዶ በመመርመር ማስተጋባት እንችላለን። ሁላችንም በተወሰነ መጠን በተለዋዋጯ የዕድል አምላክ (Fortuna) ቁጥጥር ስር መሆናችንን ይጠቁማል፤ እንዲሁም ተሞክሮ እንደሚያስተምረን፣ በተለምዶ በምናውቃቸው የሞራል ልዕልናዎች (virtues) እና በጥሩ ወይም በመጥፎ ዕድል ክስተቶች መካከል ሁሌ ግንኙነት የለም። ታምኝ እና ጎበዝ ነጋዴ መርከቦቹ ሁሉ በማዕበል ሊሰምጡ ይችላሉ፤ እናም የእርሱ ታማኝነት አያግዘውም። ትጉህ እና ፈሪሐ-እግዚአብሔር ያለው ገበሬ ሰብሉ በሙላ በዶፍ ዝናብ ሊወድምበት ይችላል። ህይወት በተመቻቸ ቦይ አትፈስም፤ የማይገመቱ እና የማይጠበቁ ነገሮች ይከሰታሉ፤ የምንኖረው አንድ ሰው በሚገባው እና በሚያገኘው መካከል አስፈላጊ ተዛምዶ በሌለበትና ሞራላዊ ወጥነት በማይታይበት ዓለም ነው። እናም ይህ ተገማችነት ማጣት እና ሞራላዊ ወጥነት አለመኖር ከሌላ ቦታ ይልቅ በይበልጥ የሚታየው በፖለቲካዊ መድረክ ነው። የተለዋዋጩን እና መረጋጋት የማይታይበትን ዓለም ፖለቲካ የተቆጣጠሩት በከፍተኛ መጠን በዕድል ቁጥጥር ስር ናቸው። በርግጠኝነት ለእነሱ በመከዳት እና በመሸለም መካከል ትስስር የለም። ከዛሬ ነገ ምን

  • ኒኮሎ ማኪያቬሊ (1469-1527) በጣሊያን፣ ፍሎረንስ ውስጥ ጥንታዊ መሠረት ካለው፣ ነገር ግን ኪሳራ ላይ ከወደቀ ቤተሰብ ነው የተወለደው – ኒኮሎ ማኪያቬሊ፡፡ በፍሎረንስ ሪፐብሊክ ውስጥ ማገልገል የጀመረው በ1494 ሲሆን በፈረንሳይ፣ በሆሊ ሲ እና በጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎችን ፈጽሟል፡፡ በ1521 የፍሎረንስ ሪፐብሊክ ሲያከትምለት ለአጭር ጊዜ ቢሆንም የእስራት እና የግርፋት እጣ ገጥሞት ነበር፡፡ በኋላም የግል ህይወቱን መርጦ በ1513 “The Prince”፣ በ1516 ገደማ “The Discourses”፣ እንዲሁ በ1520 አከባቢ “The Art of War” የተሰኙ ሥራዎቹን ይፋ በማድረግ በፖለቲካዊ ትንታኔ፣ በወታደራዊ ፅንሰ-ሐሳብ እና በታሪክ ጥናት ላይ እራሱን አጠመደ፡፡ “The Prince” (ወይም ልዑሉ) የተሰኘውን ጽሁፉን የማዘጋጀቱ ከፊል ዓላማ፣ የፅሁፉ መታሰቢያነቱ የተበረከተለትን የሜዲቺ ቤተሰብ የሆነውን ሎሬንዞን ለማማለል ነበር፤ ይሁንና እስከ 1525 ድረስ ለመንግሥታዊ አገልግሎት ጥሪ አልተደረገለትም ነበር፡፡ ብዙ አልቆየም፤ የሜዲቺ ቤተሰቦች ሥርዓት በ1527 ሲገረሰስ እንደገና ከመንግሥት ቢሮ ተገለለ፡፡ በህይወቱ የመጨረሻ ዓመታት “History of Florence” የተሰኘ ሥራውን አጠናቋል፤ እንዲሁ ዘመን በመቁጠር ላይ የሚያተኩር ሳይሆን፣ አስገራሚ በሆነ መልኩ ውስብስብ ምክንያታዊ ግንኙነቶችን ያቀረበበት በፍሎረንስ ታሪካዊ ክስተቶች ላይ የሚሽከረከር ሥራው ነው፡፡ ማኪያቬሊ፣ የመካከለኛው ዘመን የፖለቲካ እሳቤ መገለጫ የነበሩት ሃይማኖታዊ እና ክርስቲያናዊ ጉዳዮች አይጥሙትም፡፡ የተባለውን የመፈጸምና የመገዛት ክርስቲያናዊ መርሆዎችን በቁርጠኝነት የሚከተል የዋህ ሕዝብ ጭካኔ በሞላው የዓለም ፖለቲካ ውስጥ ሊጐለብት እንደማይችል በማመኑ እርሱና ክርስትና ጠላት ናቸው፡፡ ለውጫዊ ወረራና ለውስጣዊ አመጽ አቅሙን ያጠናከረ መንግሥት የመመስረትና ጥንካሬውንም የማራዘም ፍላጐት ያነገበ ሪፐብሊክአዊ እና አርበኛ ነው፡፡ ይህ ፍላጐቱ እራሱን በሁለት መንገዶች ይገልፃል፡፡ “The Prince” ላይ የማኪያቬሊ ትኩረት አንድ ሰው በተገዢዎቹ ላይ እንዴት መንጐማለል እንደሚችል ማሳየት ነው፤ “The Discourses” ላይ ደግሞ አንድ የሪፐብሊክ ሥርዓት የዜጐቹን መሠረታዊ የራስ-ወዳድነት ጥንካሬዎች ሕዝባዊ ጠቀሜታ ወዳላቸው መንገዶች በመቀየስ እንዴት ዘላቂ እና የበለፀገ መሆን የመቻሉን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ የማኪያቬሊ ስልት፣ በተለይ ጥንታዊና ዘመን አይሽሬ ክስተቶችን እንደምሳሌ በማጣቀስ ላይ የሚመረኮዝ ሆኖ፣ ታሪክ ተኮር እና ንፅፅራዊ ነው፡፡ ዓላማው ክስተቶች በሚከሰቱባቸው ሁኔታዎች አማካኝነት እንዴት የተወሰኑ (በሁኔታዎቹ ላይ የተመሠረቱ) እንደሆኑ ማሳየት፣ ምክንያቶቻቸውን መጠቆም፣ እንዲሁም ለሰው ልጅ ግንኙነቶች እና ባሕሪይ መሠረት የሆኑ ጥቅል መርሆዎችን ግልፅ ማድረግ ነው፡፡ በተጨማሪም የማኪያቬሊ መሠረታዊ ተስፋ ጠንካራ ልዑል አንድ ቀን ጣሊያንን አንድ ያደርጋታል፣ ከዚያም ሪፐብሊካዊ የመንግሥት ሥርዓት ይፈልቃል (ይመሠረታል) ዓይነት ነው፡፡ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ማኪያቬሊ፣ በአጠቃላይ ፅሁፎቹ ወጥ የሆነ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ፅንሰ-ሐሳብን ይከተላል፡፡ ጉልህ ቦታ የሚሰጠው የዚህ ፅንሰ-ሐሳብ ክፍል የሰው ልጅ ተፈጥሮ ለውጥ-የለሽ ወይም የማይቀያየር ነው የሚለው ነው፡፡ ይህም ነው፣ ስለ ፖለቲካ ጥቅላዊ ድምዳሜዎችን እንድንወስድ የሚያስችለን፡፡ ምንም እንኳን ባሕሪያቸው ሁልጊዜ የአኗኗር ሁኔታቸውን ተመርኩዞ በተወሰነ መልኩ ሊቀየር ቢችልም፣ የሰው ፍጡራን ተመሳሳይ መሠረታዊ ጠባያትን ያሳያሉ፤ እንዲሁም እነዚህ ጠባያት በተለምዶ የሚደነቁት (ጥሩ ቦታ የሚሰጣቸው) ዓይነት አይደሉም፡፡ ማኪያቬሊ “The Prince” ላይ ይህን ይላል፡- “ስለሰዎች በጥቅሉ እንዲህ ብሎ መደምደም ይቻላል፡- ምስጋና የለሽ፣ የማይታመኑ፣ ውሸታሞች እና አጭበርባሪዎች ናቸው፤ ምሽግ ውስጥ የሚያቀረቅሩና ትርፍ ለማግኘት የሚስቆነቆኑ፤ በደንብ ስትንከባከቧቸው የናንተ ናቸው… አደጋ ላይ ስትወድቁ ግን ፊታቸውን ያዞሩባችኋል።” ማኪያቬሊ “The Discourses” ላይም ይቀጥላል፡- “ሰዎች ሁሉ መጥፎና አጋጣሚውን ባገኙ ቁጥር የጨካኝነት ተፈጥሯቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ የሆኑ ናቸው፡፡ የተጠናወታቸው ተግባረ-ጥፋትነት ለጊዜው ባይታይ (ቢደበቅ)፣ በሆነ ባልታወቀ ምክንያት መሆን አለበት፤ እናም እራሱን የሚያሳይበት አጋጣሚ አጥቶ ነው ብለን መገመት ይኖርበናል፤ ነገር ግን የሁሉም ዓይነት እውነት አባት መሆኑ የተነገረለት «ጊዜ» አደባባይ ሊያወጣው አይሳነውም፡፡” የሰው ልጅ ተጠናውቶ–ጥፋት (evil disposition) መነሻው ጽኑ መሠረት ያለው ራስ-ወዳድነት እንደሆነ ማኪያቬሊ ያምናል፡፡ ይህ ራስ-ወዳድነት በቀዳሚነት እራሱን የሚገልጠው ጥልቅ በሆነ ራስን የመጠበቅ እና የደህንነት ፍላጐት ውስጥ ነው፡፡ ከዚያም ደህንነት በተረጋገጠ ጊዜ ለግል ሥልጣን እና ተቀፅላው ለሆነው ዝና የሚደረግ የአንድ አቅጣጫ ትጋት ይሆናል፡፡ በተጨማሪ ሥልጣን ማለት ነፃነት ነው፤ ሰዎች ለሥልጣን ዋጋ እንዲሰጡ ካደረጓቸው ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ ይህ አንዱ ነው፡፡ ሌሎችን መግዛት የማይሹት እንኳን ቢሆኑ፣ ቢያንስ ቢያንስ ሙሉ ለሙሉ በሌሎች ቁጥጥር ስር እንዳይወድቁ እራሳቸውን ለመከላከል የሚያስችል ሥልጣን እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፡፡ ዓለም በጨቋኞች እና ላለመጨቆን በሚታገሉት መካከል የተከፋፈለች ናትና፡፡ ይህ ሥልጣንን የመሻት ሁኔታ በሰው ልጅ ባሕሪይ ላይ ጉልህ ሚና በመጫወቱ ምክንያት ነው፣ ፖለቲካዊ ህይወት ምንጊዜም ቢሆን የትንቅንቅ ጠባይ እንዲኖረው ያደረገው፡፡ ፖለቲካ፣ ፕሌቶ እና አርስቶትል ይቻላል ስለሚሉት የመተባበር እና አንዱ ባንዱ ላይ የመደጋገፍ ዓይነት አይደለም፣ ሊሆንም አይችለም፡፡ በርግጥ ሰዎች መተባበርን (አብሮ መሥራትን) ይችላሉ፤ ነገር ግን ይህን የሚያደርጉት ትብብሩ እነሱን የሚያብስ (የሚጠቅም) እስከሆነና መሆኑ እስከቀጠለ ድረስ ብቻ ነው፡፡ የፖለቲካ ግብ ሕብር የሰፈነበት የጋራ መልካምን ማምጣት ነው የሚለው ተለምዷዊ አስተያት ቅጥፈት ነው፡፡ ፖለቲካ ትግልን የግድ ያካትታል፡፡ ማኪያቬሊ እንደሚለው፣ በንጉሣዊ ሥርዓት ውስጥ ያለው ትግል፣ አንድ ሰው የተቀሩትን ሁሉንም ለመቆጣጠር በሚል የሚደረግ ትግል ነው፡፡ የልዑሉ የግል እርካታ ማግኘት ለአጠቃላይ ሕዝቡም መልካም ሊሆን መቻሉ እውነት ነው፡፡ የጨካኙ የጣሊያን ልዑል፣ የሲዛሬ ቦርጂያ ወሳኝ ብቃቶች ናቸው ጣሊያንን ለማዋሃድ በትክክል የሚያስፈልጉት፡፡ ነገር ግን የልዑሉ ቀዳሚ ዓላማ ሥልጣኑን ማስጠበቅ እና ሥልጣኑን በነፃነት ማጣጣም ነው፡፡ ገና ሥልጣኑን የጨበጠና በዚህም መንበሩ ተደግፎ የቆመው በባሕል፣ በሕዝቡ ቸልተኝነት ወይም ሕዝቡ ለእርሱ ቤተሰብ ባለው አክብሮት ያልሆነ ልዑልን ስንመለከት ከላይ የተገለፀው ትግል ይበልጥ ግልጽ ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ ‹አዲሱ› ልዑል ቦታውን የሚያመቻቸውና ዘላቂ የሚያደርገው በራሱ ጥንካሬና ብቃት ብቻ ሊሆን ይገባል፡፡ እናም “The Prince” የተሰኘው ሥራው ልዑሉ ይህንን እንዴት ማድረግ እንደሚችል የሚተነትን ነው፡፡

  • THE MORE CORRUPT THE STATE, THE MORE NUMEROUS THE LAWS. ~ Tacitus የአንድ መንግሥት ሙስና እና ብልሹነት በጨመረ ቁጥር፣ የሚያወጣቸው ሕጎች ቁጥርም አብሮ ይጨምራል። ስርዓቱ በበሰበሰ ቁጥር ሕጉ ይበዛል። የሮማው ታሪክ አዘጋጅና ፈላስፋ ታሲተስ (Tacitus) በታዋቂው "Annals" መጽሐፉ ላይ የተናገረው ይህ አባባል፣ አንድ መንግሥት የዜጎቹን ሥነ-ምግባር፣ ፍትሕ እና እውነተኛ አስተዳደር ማረጋገጥ ሲሳነው በምትኩ ብዙ ሕጎችንና ደንቦችን በመደርደር ብቻ ችግሩን ለመሸፈን ወይም ለመቆጣጠር እንደሚሞክር የሚያሳይ ጥልቅ ምልከታ ነው።

  • ጳውሎስ ታማሚ ነበር፤ ግን መንፈስ ቅዱስ ስለ አደረበት በለበሳቸው ልብሶች ለድውያን ድኀነትን የሚሰጥ ሆነ፤ ጴጥሮስም ሰውነቱን ታማሚ ነበር ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ ፍጹም ሀብት ስለአደረበት በመንገድ ሲያልፍ ጥላው በአረፈባቸው ጊዜ ጥላው ድውያኑን አዳነ።                  ሃይ አበ ፴፫÷፶፫ አባቶቻችን!! በእናንተ ያደረ መንፈስ ቅዱስ ለእናንተ ጥብዐቱን እንደሰጣችሁ ለእኛም ጥብዐቱን ይሰጠን ዘንድ እንማልዳችኋለን!!!!

  • Never quit, never surrender, never stop moving forward no matter what the world throws at me. One day I WILL break through and it will all make sense.

  • አባት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሰው ልጆች በሙሉ ሕይወት ውስጥ የሚያልፉባቸው ወይም የሚያከብሯቸው ሰባቱ አባቶች ተብለው የሚታወቁ አሉ። ሰባቱ አባቶች - : ፩,  ሰማያዊ አባት (እግዚአብሔር): የሰው ሁሉ የነፍስና የሥጋ ፈጣሪ እንዲሁም የሁላችን አባት ነው። ፪,  ወላጅ አባት: በሥጋ ወልዶ ያሳደገን፣ የዕለት ጉርስና እንክብካቤ ያደረገልን ምድራዊ አባት ነው። ፫, የነፍስ አባት: መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚመራ፣ ከኃጢአት የምንነጻበትንና ከፈጣሪ ጋር የምንታረቅበትን ምክር የሚሰጠን አባት (ካህን) ነው። ፬,  የክርስትና አባት: በክርስትናችን ወቅት ዋስና ጠበቃ በመሆን፣ በሃይማኖት እንድንጸና የሚያስተምረንና የሚመክረን አባት ነው። ፭,  የጡት አባት: እናት ጡት አጥብታ ለማሳደግ ስትቸገር (ወይም በሌላ ምክንያት) በጉዲፈቻ አሳድጎ ለቁም ነገር ያበቃን አባት ነው። ፮,  የቆብ አባት: መነኮሳትና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በምንኩስና ደረጃ ሲደርሱ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን እንዲመራላቸው የሚሾሙት አባት ነው። ፯,  የቀለም አባት: እውቀት (ፊደል) የቀሰምንበት፣ የሕይወትን ሚስጥርና ትምህርት ያስተማረን መምህር/አባት ነው።

  • የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና የዓለም መምህር ቅዱስ ጳውሎስ

  • ​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን። የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች የቅዱሳን ሐዋርያት የቃል ኪዳን ልጆችና የዚህ ገጼ ወዳጆቼ እንደምን ሰነበታችሁ? እንደምንስ አረፈዳችሁ ?አመሻችሁ? የሰማይና የምድር ጌታ የቅዱሳኑ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን። ዛሬ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን አቆጣጠር ሐምሌ ፭ ቀን ነው ይህ ዕለት ተራ ቀን አይደለም የዓለምን ጨለማ በወንጌል ችቦ የገፉ የክርስቶስን መንጋ በጥበብና በደም ማኅተም የጠበቁ የሁለቱ ታላላቅ የምድር መብራቶች የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና የዓለም መምህር ቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት ዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው እስኪ የዕለት እንጀራችንን ከመቁረሳችን በፊት ሰብሰብ ብለን ወደ ኋላ ወደ መጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን እንጓዝ በጥበብ መንፈስ ወደ ኋላ ተመልሰን በገሊላ ማዕበልና በደማስቆ በረሃ ውስጥ የተሰሩትን የእነዚህን ሁለት ዓለቶች ድንቅ የሕይወት ታሪክ ምስጢር በአንድነት እንቃኝ። በጸሎታችሁ አስቡኝ። ከመረብ ስፌት እስከ ልብ አደን ​ዘመኑ የሮማውያን የጭካኔ በትረ መንግሥት ዓለምን ያንቀጠቀጠበት ወቅት ነበር በገሊላ ባሕር ዳርቻ ዕድሜው 55 ደርሶ ሸብቶ የባሕሩን ሞገድና መከራ አጣጥሞ የሚኖረው የቤተሳይዳው ስምዖን (ጴጥሮስ) መረቡን ይሰፋል ሕይወቱ ልክ እንደ ባሕሩ ሁልጊዜ የሚናወጥ ይመስል ነበር ነገር ግን ከተራ ዓሣ አጥማጅነት ወደ “ሰው አጥማጅነት” የሚቀይረው የናዝሬቱ አምላክ በባሕሩ ዳርቻ ቆመ ​“ሁሉንም ትተህ ተከተለኝ” የሚል መለኮታዊ ድምፅ በባሕሩ ላይ አስተጋባ። ስምዖን ያረጀ መረቡን የታመነች ታንኳውንና የምድሩን አባቱን ጥሎ መለኮታዊውን መግነጢስ ተከተለ በቂሳርያ አደባባይም የአይሁድ ሊቃውንት ሊደርሱበት ያልቻሉትን ሰማያዊ ምስጢር በልቡ ጓዳ አበራው “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” አለው ያን ጊዜ የሰማይና የምድር ጌታ የስምዖንን ስም ቀይሮ በአረማይክ “ኬፋ” (ዓለት) አለው። በሌላ በኩል ደግሞ ሳውል የተባለው ጐልማሳ በታላቁ መምህር ገማልያል እግር ሥር ተቀምጦ ሕገ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን የጠጣ በአይሁድ ሸንጎ ውስጥ ትልቅ ሥልጣን የነበረው ባለግርማ ፈሪሳዊ ነበር እርሱ ለሕጉ ቀናተኛ በመሆኑ የቅዱስ እስጢፋኖስን ደም ያፈሰሱትን ሰዎች ልብስ ይጠብቅ የነበረ ጨካኝ ሰው ነበር የክርስቲያኖችን ስም ለማጥፋት የፈቃድ ደብዳቤ ይዞ ወደ ደማስቆ ሲገሰግስ ግን ከሰማይ የወረደው ብርሃን ከፈረሱ ላይ ብቻ ሳይሆን ከነበረበት የጥፋት ዙፋን ላይ ቁልቁል ፈጠፈጠው ​“ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል” ይህ ድምፅ የሳውልን ሥጋዊ ዓይን አጠፋው የውስጥ መንፈሳዊ ዓይኑን ግን በብርሃን ከፈተው ለሦስት ቀናት በጨለማና በጾም የቆየው ሳውል በአናንያ እጅ ተጠምቆ ሲወጣ አዲስ ፍጥረት ሆነ ስሙም ጳውሎስ (ብርሃን/ታናሽ) ተባለ የቤተክርስቲያን አሳዳጅ የነበረው ሰው የቤተክርስቲያን ታላቅ ጠባቂ ሆነ። ​ምስጢራዊው ፈተና እና የንስሐው ዕንባ ​ጴጥሮስ ጌታውን እጅግ ይወደው ነበር ነገር ግን ፍቅሩ በሰውኛ ቅንዓትና በራሱ መተማመን የተሞላ በመሆኑ የፈተናው ማዕበል ሲመጣ ተናወጠ በዚያች ቀዝቃዛ ሌሊት በቀያፋ ግቢ ውስጥ እሳት እየሞቀ ሳለ የአንዲት ገረድ ጥያቄ የዓለቱን ልብ አሸበረው “አላውቀውም” ብሎ ሦስት ጊዜ ካደ ​ያን ጊዜ ዶሮው ጮኸ ጌታም በደሙ ከተሸፈነው ፊቱ ላይ ዞር ብሎ አየው ያ እይታ የፍርድ ሳይሆን የይቅርታ እይታ ነበር ጴጥሮስ ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ ያ ዕንባ መለኮታዊው እሳት የካደውን ልብ መልሶ ያቀለጠበትና እንደገና የሰራበት ምስጢር ነበር። ከትንሣኤ በኋላ በጥብርያዶስ ባሕር ላይ ጌታ ሦስት ጊዜ “ትወደኛለህን?” ብሎ ሲጠይቀው ጴጥሮስ ቀድሞ እንደነበረው “እኔ ከቶ አልሰናከልም” አላለም “ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ” በማለት ራሱን ዝቅ አደረገ ጌታም በቀልን የሚተው ንስሐን የሚቀበል አምላክ ነውና “ግልገሎቼን አሠማራ በጎቼን ጠብቅ” በማለት ታላቁን መንጋ የመጠበቅ አደራውንና የቁልፍ ሥልጣኑን መልሶ አስረከበው። ​ የሁለቱ መብራቶች ፍጻሜ ​እነዚህ ሁለት ታላላቅ ዓለቶች ወንጌልን በዓለም ዙሪያ ዘሩ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአንድ ቀን ስብከት 3,000 ሕዝብን ማረከ አልጋ ቁራኞችን ፈወሰ ጣቢታን ከሞት አስነሣ ጳውሎስ ደግሞ በሦስት ታላላቅ የሐዋርያት ጉዞዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን በእግሩ እየተጓዘ አሕዛብን ሁሉ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስቶስ እውነተኛ ብርሃን መለሰ ። ነገር ግን የዚህች ምድር ቆይታቸው የሚያበቃበት ሰዓት ደረሰ ጨካኙና መምለኬ ጣዖት የነበረው ንጉሥ ኔሮን ቄሣር በሮም አደባባይ ሁለቱንም ለሞት ፈረደባቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ መስቀሉን ሲያይ “እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን እኔ ልክ እንደ እርሱ ቀና ብዬ ልሰቀል አይገባኝምና ቁልቁል (ዘቅዝቃችሁ) ስቀሉኝ” አላቸው። በታላቅ ትሕትና ራሱን ዘቅዝቆ በመስቀል ላይ ሆኖ በሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም ነፍሱን ሰጠ ሥጋውንም ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ በወተት አጥቦ በነጭ ሐር ገንዞ ቀበረው። ቅዱስ ጳውሎስ ለሁለት ዓመት ተኩል በጨለማ ቤት ታስሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በኦስትያ መንገድ ላይ አንገቱን ለሰይፍ ሰጠ ሰይፉ ሲያርፍበት ሥጋው ወደ መሬት ወደቀ ነፍሱ ግን ወደ ሰማያዊው ክብር በረረች። ​ የተወደዳችሁ ወዳጆቼ የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ እንዲሁ የሩቅ ዘመን ታሪክ ብቻ አይደለም ዛሬ ለእኛ ለሕይወታችን ትልቅ መስታወት ነው ጴጥሮስ በባሕር ማዕበል ውስጥ አልፎ ክዶ በንስሐ ተመልሶ የትሕትናን ጥግ አሳየን ጳውሎስ ደግሞ ከአሳዳጅነት ወደ ተሳዳጅነት ተቀይሮ ለሃይማኖት አንገትን ለሰይፍ መስጠት ምን ማለት እንደሆነ አስተማረን አንደኛው በትሕትና ቁልቁል ተሰቅሎ መሬትን ሲያይ ሁለተኛው በሰይፍ ተመትቶ ወደ ሰማይ አሻቀበ ሁለቱም በተቃራኒ መንገድ ተጉዘው ግን በአንድነት በክርስቶስ ማዕድ ላይ አረፉ። እኛስ ዛሬ በሕይወታችን ስንት ጊዜ ጌታን በኃጢአታችን ክድነው ይሆን? እንደ ጴጥሮስ ወጥተን የምናለቅስበት የንስሐ ዕንባ አለን? ወይስ እንደ ሳውል በክፉ መንገድ ስንጓዝ “ስለምን ታሳድደኛለህ?” የሚለውን የጌታን ድምፅ ሰምተን ከፈረሳችን (ከትዕቢታችን) ለመውረድ ፈቃደኞች ነን? ​የገሊላው ተራ ዓሣ አጥማጅና የጠርሴሱ ታላቅ ሊቅ ዛሬ በአንድነት በሰማያዊቷ እየሩሳሌም ዘውድ ደፍተዋል የእነዚህ የቅዱሳን ሐዋርያት ረድኤት በረከት አማላጅነትና ጥበቃ ሁልጊዜ ከሁላችን ጋር ይሁን እግዚአብሔር አምላክ በጽናታቸው ያጽናን በሃይማኖታቸው ይጠብቀን አሜን ይሁን ይደረግልን። ​ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። ይቆየን። ​መልካም የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓል ይሁንላችሁ ይሁንልን።

  • ጸሎት አንድ ሰው ቢበላም፣ ቢጠጣም፣ ቢቀመጥም፣ በመንገድ ቢጓዝም ወይም ሌላ ማንኛውንም ነገር ቢያደርግ ዘወትር እንዲህ እያለ መጮህ (መጸለይ) አለበት "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ማረኝ!" ..... ስለዚህ ልብህ ጌታን እንዲያቅፈው፥ ጌታም ልብህን እንዲያቅፈው የጌታችን የኢየሱስን ስም ሳታቋርጥ ጥራ።                        ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ።                        1ኛ ተሰሎ 5÷17

  • Practice The Arts Of Not Complaining /አለማሳበብን ተለማመድ

  • አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ደጆቼን ክፈትልኝ። ፩~የአእምሮ ደጄን/ የምናሰላስልበት፣የምናቅድበት/የሚዘጋው ድንቁርና ነው። አለማወቅ አለመማር ለመማር አለመፈለግ ከዚህ ለመውጣት ክፉ ሃሳብን መሸሽ እና መርጦ መቀበል። ፊል4÷8 "በቀረውስ ወንድሞች ሆይ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን እነዚህን ዐስቡ።" አበው "ሃሳብ ሰውን ይቀርፃል።" ፪~የልቦናዬን ደጄን / እና ፫~የፈቃዴን ደጄን ።

  • አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ደጆቼን ክፈትልኝ። ፩~የአእምሮ ደጄን/ የምናሰላስልበት፣የምናቅድበት/የሚዘጋው ድንቁርና ነው። አለማወቅ አለመማር ለመማር አለመፈለግ ከዚህ ለመውጣት ክፉ ሃሳብን መሸሽ እና መርጦ መቀበል። ፊል4÷8 "በቀረውስ ወንድሞች ሆይ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን እነዚህን ዐስቡ።" አበው "ሃሳብ ሰውን ይቀርፃል።" ፪~የልቦናዬን ደጄን / የነፍስ ማዕከል እና ፫~የፈቃዴን ደጄን፣ለማድረግና ላለማድረግ የሚረዳን ።

Teter Wuha ጠጠር ውሃ°( TW )° — tgindex