Wabi Media | ዋቢ ሚዲያ
Статистикаዋቢ ሚዲያ | Wabi Media ትክክለኛ መረጃ ለሚፈልጉ! Fast, reliable, and verified content at your fingertips. 🔔 ሰብስክራይብ በማድረግ የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ። Join us to stay updated! 💬 Contact: @Wabi_Media
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 20
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 47
- 1/48двое суток
- 53
- 1/72трое суток
- 58
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በምህጻሩ (RSF) የሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱምን ጨምሮ የሱዳን ጦር በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ ከተሞች ላይ ዛሬ በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ጥቃት አደረሰ። የዓይን ምስክሮችና የጦር ምንጮች እንዳሉት የዛሬው ጥቃት ለወራት ከተፈጸሙት ጥቃቶች በከፍተኛ ደረጃ የተቀነባበረ ነው። ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ኻርቱምን ፣ በኮርዶፋን የምትገኘው ኤል ኦቤይድ እና የሰሜን ሱዳን ከተሞችን አትባራን እና ኤል ዳመርን ብዛት ባለቸው ድሮኖች መደብደቡን የሱዳን ጦር ምንጭ ተናግረዋል። የሱዳን ጦር የፈጥኖ ደራሹን ኃይል አስወጥቶ መልሶ የያዛት እና ከዚህ ቀደምም የድሮን ጥቃቶች ዒላማ የሆነችው ኻርቱም ለወራት አንጻራዊ መረጋጋት ሰፍኖባት ነበር።በኻርቱም ጥቃቱ የደረሰው ከማለዳው 11 ሰዓት ላይ እንደነበር በወቅቱም ከኦምዱርማን በስተሰሜን በሚገኘው ዋዲ ሴይዲና ከተባለው የሱዳን ጦር ሰፈር በኩል ደግሞ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳይሎች ድምጽ መሰማቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የዓይን ምስክሮች እንደተናገሩት ሰሜን ኻርቱም ከናይል ወንዝ ባሻገር በኤል ድሮሽባ አካባቢ ሁለት ድሮኖች አንድ መስጊድና የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር መተዋል።ድሮኖቹ በአየር መቃወሚያ ይመቱ አይመቱ ወዲያውኑ የተባለ ነገር የለም።በሲቭሎች ላይ የደረሰ ጥቃት ይኑር አይኑርም የተሰማ ነገር የለም። በሱዳኑ ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ ይገመታል። Via: DW @Wabi_Media
መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ የደረሳት ሲሆን በዚህ መዘርዝር ውስጥ በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ይገኙበታል፡፡ ሙሉ ዝርዝራቸው ተከታዩ ነው፡- 1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው 2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም 3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው 4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ 5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ 6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው 7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ 8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው 9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው 10. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ 11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 12. አቶ አለልኝ ምህረት 13. አቶ መንበር አለሙ 14. አቶ ማይክ መላክ 15. አቶ አሳምነው ታደሠ 16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ 17. አቶ እሱባለው በለጠ 18. አቶ እስክንድር ሽፈራው 19. አቶ መሰለ ቸሩ 20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ 21. አቶ ጫኔ ዘየደ 22. ወ/ት ሃሊማ አህመድ 23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ 24. አቶ ሲሳይ መልካሙ 25. አቶ ታደሰ ወዳይነው 26. አቶ በላይ ሲሳይ 27. አቶ ያሬድ ግርማ 28. አቶ ማረው ስለሺ 29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ 30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ ለአዲስ ማለዳ የደረሳት ደብዳቤ እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከመንግስት ጋር በጀመረው ውይይት በመጨረሻ ፈርሙ የተባሉት ተከታዮቹን ጉዳዮች ያካትታል፡- “በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ውሰዱ፤ በአማራ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለሞቱ ሰዎች፣ ለቆሰሉ ሰዎች (በየመዝገብ ቁጥሩ ይለያያል) ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ለወደመው በበሊዮን የሚገመት ንብረት ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እና እሳቤ ካልተመራች ማለታችሁን ወንጀል ነው በሉ፤ ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ” በቅድመ ሁኔታ እንደቀረበላቸው አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ያመላክታል፡፡ ይህንን ተከትሎ ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ “እኛ ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ በህግም፣ በሞራልም፣ በታሪክም ተቀባይነት የለውም ብለን አንፈርምም” ብለዋል፡፡ አክለውም፤ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችም ህጋዊ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ የ60 ሚሊዮን ህዝብን መልካም እሴት ወንጀል ነው ብለን አውቀን አንሰጥም ወንጀልም አይደለም፤ በህገመንግስት እና በዓለምአቀፍ ህጎች ነፃ ሆኖ የመኖር መብታችንን ፈቅደን አንተውም፤ በህግ የተከለከለውን ራስን መከላከል እና ራሳችንን ወንጀለኛ አናደርግም” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡ Via Addis Maleda @YeneTube @FikerAssefa @Wabi_Media
🇪🇹 አትሌቶች እና አሰልጣኞች በአሜሪካ መቅረታቸው ተሰማ ! በኦሬገን በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ከ 20ዓመት በታች ሻምፒዮና የተሳተፉ የኢትዮጵያ ልዑክ አባላት በአሜሪካ መጥፋታቸው ተሰምቷል። ለውድድሩ ወደ አሜሪካ ካቀናው ልዑክ ቡድን ውስጥ ሰባት ያህል አባላት መኮብለላቸው ተገልጿል። ከልዑክ ቡድኑ ጋር የማይገኙት አባላት 4️⃣ አትሌቶች እና 3️⃣ አሰልጣኞች መሆናቸው ተነግሯል። ወደ አሜሪካ ካመሩት አራት አሰልጣኞች ሶስቱ መቅረታቸውን ተከትሎ አሰልጣኝ መሰረት ብቻ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ላይ ይገኛሉ ተብሏል። ኢትዮጵያ በውድድሩ 2️⃣ የወርቅ ፣ 3️⃣ የብር እና 1️⃣ የነሐስ ሜዳልያ በማሳካት ማጠናቀቋ አይዘነጋም። መረጃው የጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ( ሀትሪክ ስፖርት )ነው። @Wabi_Media
ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ማስተማር ይፈልጋል። 🔔 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን እንዲሁም ነፃ የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት በነፃ ትምህርት ዕድሉ ይሰጣል፡፡ 9ኛ ክፍል ብቻ የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ● አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● አሶሳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ባህር ዳር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት 9ኛ እና 10ኛ ክፍል የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ● ቡኢ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ● ቦንጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለ9ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች ● በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 85 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች 80 እና በላይያመጣ/ያመጣች ● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት ለ10ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች ● በ2017 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት 95 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች ● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነት 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት ኦንላይን ይመዝገቡ 👇 https://sbs.moe.gov.et/apply የመመዝገቢያ ጊዜ 👇 እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት ይገለፃል፡፡ የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች በሚደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው ተብሏል፡፡ @Wabi_Media
"ኢራን ለገደለቻቸውና ለጎዳቻቸው ሰዎች ካሳ መክፈል አለባት" — ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በተከሰተው ግጭት የደረሰብኝ ውድመት ይካስ ስትል ለጠየቀችው ቴህራን፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠንካራ ምላሽ ሰጥተዋል። ትራምፕ በራሳቸው 'ትሩዝ ሶሻል' (Truth Social) የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ባስተላለፉት መልእክት፣ ኢራን ካሳ ለመጠየቅ ያቀረበችው ሀሳብ "አስደናቂ" ነው ካሉ በኋላ፣ ይልቁንም ቴህራን በተለያዩ ግጭቶች እና በመንገድ ዳር ቦምቦች ለገደለቻቸው እና ለጎዳቻቸው ሰዎች በሙሉ ካሳ መክፈል እንዳለባት ገልጸዋል። ቴህራን የሆርሙዝ ሰርጥን (Strait of Hormuz) ለመክፈት እና የተጣሉባትን ማዕቀቦች ለማንሳት በሚደረጉ ውይይቶች ወቅት፣ ባለፉት ወራት በደረሰባት የጦርነት ውድመት አሜሪካ ካሳ እንድትከፍላት ጠይቃ ነበር። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአንጻሩ በአሜሪካ ተደራዳሪዎች በኩል ኢራን በውጊያ ላይ ለተገደሉ የአሜሪካ ወታደሮች፣ ለተጎዱ ቤተሰቦች (እ.ኤ.አ. በ2000 በዩኤስኤስ ኮል ላይ ከደረሰው ጥቃት ጀምሮ) እና በሃገር ውስጥ በነበሩ ተቃውሞዎች ለተገደሉ የኢራን ዜጎች ጭምር ካሳ እንድትከፍል ጥያቄው በድርድር ወቅት እንዲቀርብ አዘዋል። የሁለቱ ወገኖች የካሳ ጥያቄ መወራወር የነገሰበትን ቀጣናዊ ድርድር እና የሆርሙዝ ሰርጥን የመክፈት ሂደት ይበልጥ ያወሳስበዋል ተብሎ ተጠብቋል። @Wabi_Media
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የተፈፀመ‼️ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት ግልሰቦች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል። ድርጊቱ የተፈጸመው አገና በተባለችው ልዩ ቦታ ሲሆን ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት ኃይሎች ከአካባቢው የአበሽጌ አገና ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተጠቅሷል። Via: @mesretmedia @Wabi_Media
видео или голосовое, без подписи
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጡ 11 አዳዲስ የሥራና ተግባር (የሙያ) ዓይነቶችን ይፋ አድርጓል። ትምህርቱ ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን የሚሰጥ ሲሆን፣ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በ12 የሙያ ዓይነቶች መተግበሩ ይታወሳል። ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጨመሩ 11 የሙያ ዓይነቶች ቴክኖሎጂና ጥገና፦ ብረታ ብረት፣ አውቶሞቲቭ፣ ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፣ ቧንቧ ሥራ ዲጂታልና አልባሳት፦ ሶፍትዌር ማበልጸግ፣ አልባሳት ቴክኖሎጂ ግብርናና ጤና፦ ሰብል አመራረት፣ ጤና ክብካቤ አገልግሎት አገልግሎትና ውበት፦ ሆቴል አገልግሎት፣ ምግብ ዝግጅት፣ ፀጉር ሥራና ውበት ከትምህርት ቢሮዎች የሚጠበቁ ቅድመ-ዝግጅቶች በጀትና ዕቅድ፦ አስፈላጊውን በጀት መደደብ እና ተማሪዎች ሙያ እንዲመርጡ ማድረግ። ሰው ኃይል፦ የየሙያዎቹን መምህራን መቅጠር እና ስልጠና መስጠት። ግብዓትና ቅስቀሳ፦ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ማሟላት እና የሕዝብ ንቅናቄ መፍጠር። @Wabi_Media
видео или голосовое, без подписи
#ጥቆማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን በምስራቅ ጎህ የሳይንስ ልህቀት ማዕከል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ በሳይንስ ልህቀት ትምህርት ቤቱ ለመማር የምትፈልጉ ተማሪዎች እስከ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡ የመመዝገቢያ ሊንክ 👇 https://bs.ministry.et (ዝርዝር መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዙት የቢሮው ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡) @Wabi_Media
ቪድዮ ፦ በቻይና በተከሰተ 'ዶልፊን' የተባለ ከባድ አውሎንፋስ ምክንያት ባለስልጣናት የፋይናንስ ማዕከል ከሆነችው ሻንጋይ ጨምሮ ከአገሪቱ ምሥራቃዊ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቤታቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። አውሎ ንፋሱ ከፍተኛ ዝናብ ያስከተለ ሲሆን በተከሰተበት ክልል በሙሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችን አቋርጧል። ሰኞ ዕለት ብቻ በሻንጋይ ውስጥ ወደ 1,000 የሚጠጉ በረራዎች ተሰርዘዋል። @Wabi_Media
ከ2010 በኋላ የወጡ አብዛኛዎቹ አዋጆች በችኮላ የተዘጋጁ በመሆናቸው በተደጋጋሚ እንዲሸሻሉ መደረጋቸው በጥናት ተመላከተ ከ2010 ዓ.ም. በኋላ የወጡ አብዛኛዎቹ አዋጆች በችኮላ የተዘጋጁ በመሆናቸው ለተደጋጋሚ ማሻሻያ መጋለጣቸውንና ከአዋጆቹ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጩ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲወጡ ምክንያት መሆናቸውን የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ጥናት አመላከተ። ኢንስቲትዩቱ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ባካሄዳቸው አምስት ጥናቶች ላይ ባደረገው የማጽደቂያ ዓውደ ጥናት ግኝቶቹን አቅርቧል። ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ ሁሉንም አዋጆች የሸፈነ ሲሆን፣ በሀገሪቱ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት መረጋጋትን የሚመለከት የተለየ ፖሊሲ እንደሌለ ጠቁሟል። ለአብነትም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የወጣው አዋጅ በተመሳሳይ ዓመት በሌላ አዋጅ መሻሻሉንና ከሁለት ዓመት በኋላም በ2015 ዓ.ም. እንደገና መሻሻሉን ጥናቱ አመላክቷል። በተጨማሪም አንዳንድ አዋጆች ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች እንዳሏቸው ጥናቱ ጠቁሟል። በሕገ መንግሥቱ ውስጥም አሻሚ ቃላት፣ ግልጽነት የጎደላቸው አንቀጾችና አንዳንድ የሚጋጩ መርሆዎች መኖራቸውን ጥናቱ አመላክቶ፣ የሕገ መንግሥቱ ትርጓሜ ጉዳይ በጥናት እንዲታይ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል። ደንቦችና መመሪያዎች በየጊዜው ሲሻሻሉም በቂ ጥናትና ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ ጥናቱ አሳስቧል።ዘገባው የሪፖርተር ነው። @Wabi_Media
видео или голосовое, без подписи
በብሔራዊ የምክክር ጉባዔው "ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ እና አርብቶ አደር ጉዳዮች" በሚለው አጀንዳ ስር የቀረቡ ዋና ዋና ነጥቦች ማጠቃለያ፡- 1. የመሬት ባለቤትነት ሦስት አማራጮች፡ መሬት የግል፣ የመንግስት፣ ወይም የህዝብና የመንግስት ይሁን የሚሉ ሀሳቦች ቀርበዋል። ስጋቶች፡ የግል ከሆነ በጥቂት ባለሀብቶች እጅ ይወድቃል፤ የመንግስት ከሆነ ደግሞ የህዝቡ የመጠቀም መብት ይነጠቃል የሚል ስጋት ተነስቷል። መፍትሔ፡ የጋራ፣ የደን፣ የወንዝ እና የማዕድን ቦታዎች በመንግስት እጅ እንዲሆኑ፤ አርሶ አደሩ በመሬቱ የመጠቀም መብቱ እንዲከበርና መሬት ሲወሰድ ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈል የሚያዝ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ተጠይቋል። 2. የግብር እና የደመወዝ ሁኔታ ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ የደመወዝ አነስተኛነት እና የግብር ጭቆና በመኖሩ ግብር እንዲቀነስ አብዛኛው ተሳታፊ ተስማምቷል። ዝቅተኛ ደመወዝተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑና ለከፍተኛ ደመወዝተኞች ደግሞ የግብር ምጣኔው እንዲቀነስ ተጠይቋል። 3. ፍትሃዊ የሀብት እና የመሰረተ ልማት ክፍፍል የኢንዱስትሪ እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ በመካከለኛው ሀገር ላይ ብቻ ሳይወሰን ለሁሉም ክልሎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲዳረስ፤ ለአርሶ አደሩም ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶች እንዲቀርቡ ተጠይቋል። 4. የሕዝብ ቆጠራ እና ውክልና የ1999 ዓ.ም የሕዝብ ቆጠራ ትክክለኛ ባለመሆኑ ክልሎች የተገባንን የበጀት እና የመቀመጫ ድርሻ አጥተናል በሚል ካሳ ጠይቀዋል። ወደፊት የሚደረግ የሕዝብ ቆጠራ በገለልተኛ አካል እንዲካሄድ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። @Wabi_Media
የኤሌክትሪክ ኃይል አዲስ ኃይል ማስገቢያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ በሙሉ ተነሳ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስገቢያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች ይጠየቅ የነበረውን ከ3 እስከ 9 በመቶ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ። ቀደም ሲል የዱቤ ክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ወለድ ይጣል ነበር። አሁን ወለዱ መነሳቱ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ዜጎች የምስራች መሆኑንና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተጀመረው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር በሁለት ሳምንታት ብቻ 19,231 አዳዲስ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል። ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 664,505 አዳዲስ ደንበኞችን ያገናኘ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም. ደግሞ 1.1 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን ለማገናኘት አቅዷል። ኢንጅነር ጌቱ እንደገለጹት፣ አገልግሎቱ በ70 ዓመታት ታሪኩ 5.88 ሚሊዮን ደንበኞችን ማገናኘት ችሏል፤ አሁን ግን በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ደንበኞችን የማገናኘት አቅም ላይ ደርሷል። @Wabi_Media
አሜሪካ ኦሬገን እያስተናገደች ባለው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጡ። ዛሬ ምሽት ፍጻሜውን በሚያገኘው ውድድሩ ኢትዮጵያውያን ተጨማሪ ሜዳሊያ ካገኙ ደረጃቸውን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል። ከ147 ሀገራት የተወጣጡ ከ1800 በላይ አትሌቶች ባሳተፈው ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ እስካሁን በሴቶች በሶስት ሺ መሰናክል እና በሶስት ሺ ሜትር የሩጫ ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች። በተጨማሪም ሶስት የብር እና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፋለች። 35 ሃገራት ብቻ በሰንጠረዡ ውስጥ መግባት በቻሉበት ውድድሩ ኢትዮጵያ እስካሁን ስድስት ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአሜሪካ እና ጣልያን ቀጥሎ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል። በውድድሩ አሜሪካ በስምንት ወርቅ፣ ስድስት የብር እና አራት የነሐስ በድምሩ 18 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አንደኛ ደረጃን ይዛለች። ጣልያን በሶስት ወርቅ እና ሁለት ነሐስ በድምሩ አምስት ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። @Wabi_Media
የመሬት መንቀጥቀጥ‼️ በትናንትናው እለት በመተሃራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። በዛሬዉ እለት ምሽት 2 ሰዓት ከ 11 ደቂቃ ላይ በመተሃራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.6 የተለካ መሆኑን ቮልካኖ ዲስከቨሪ የተሰኘዉ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የእሳተገሞራ ፍንዳታዎችን የሚከታተል ተቋም በገጹ አሳዉቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ በአዲስአበባም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ተሰምቷል። @Wabi_Media
Google messages ስትጠቀሙ RCS On ማድረጋችሁ ምን ይጠቅማችኋል? Message ስትልኩ ብር አይቆርጥባችሁም። ነገር ግን Data ማብራት ይጠበቅባችኋል። የምትልኩለት ሰው Google messages የሚጠቀምና Online መሆን አለበት። የGemini AI እዛው Google messages ላይ መጠቀም ትችላላችሁ። የድምፅ መለዕክት፣ ፎቶ፣ location፣ GIFና Sticker መላላክ ትችላላችሁ። End-to-End encrypted ነው። ያ ማለት የምትልኩትን መልዕክት ማንኛውም service provider (ቴሌ ወይም ሳፋሪኮም) የማየት እድል የላቸውም። ግን ሁለታችሁም Google messages ከተጠቀማችሁና E2EE on ከሆነ ብቻ ነው። Message የላካችሁለት ሰው የላካችሁትን መልዕክት ማየቱና አለማየቱን ማዎቅ ትችላላችሁ። እንዲሁም type በሚያደርግበት ጊዜ Typing....ይላችኋል። እዚ ጋ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባችሁ RCS on አድርጋችሁ Message ስትልኩ እናንተ data ካላበራችሁ message error ይላችኋል። የምትልኩለት ሰውም Online ካልሆነ የላካችሁት message አይገባለትም። ይህን ነገር ለማስተካከል የምትልኩለት ሰው profile ላይ ገብታችሁ "Only send SMS and MMS messages" የሚለውን On ማድረግ ይጠበቅባችኋል። @Wabi_Media
#Ethiopia የፌደራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ጥናት በኢትዮጵያ ወጥ ፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ምክንያት የህግ አወጣጥ ስርዓቱ አለመረጋጋት እንዳጋጠመው አመለከተ። ዋና ዋና ችግሮች፦ ህጎች በፖሊሲ ፋንታ የአስፈጻሚውን ጊዜያዊ ፍላጎት መሰረት አድርገው በችኮላ መውጣታቸው። ተደጋጋሚ የአዋጅ ማሻሻያዎች፣ ሰፊ መሻሮች እና ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች መኖር። የባለሙያ እጥረት፣ የተቋማት አለመናበብና የህዝብ ተሳትፎ ማነስ። ተፅዕኖ፦ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንትን ማስተጓጎሉና የዜጎችን የመብት ግንዛቤ መቀነሱ። የቀረቡ መፍትሔዎች፦ ወጥ ፖሊሲ ማዘጋጀትና ገለልተኛ የህግ ኮሚሽን ማቋቋም። የፓርላማ ኮሚቴዎችን አቅም ማጠናከርና የህዝብ ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ። ፍርድ ቤቶች ህገ-መንግስታዊነትን የመተርጎም ስልጣን እንዲኖራቸው ማድረግና አሰራሩን ከፖለቲካ ተጽዕኖ ነፃ ማውጣት። @Wabi_Media
#Ethiopia "ታጣቂዎች ከውጭ ኃይሎች ጋር በመሻረክ 'ያልተቀደሰ ጋብቻ' ፈጥረዋል" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በኦሮሚያ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲረዱ "ያልተቀደሰ ጋብቻ" መፍጠራቸውን ገለጹ። ታጣቂዎቹ ኤርትራን እና ሱዳንን ጨምሮ ከውጭ ተዋናዮች ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሕዝቡ በጥንቃቄ ሊረዳው እንደሚገባ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሀገሪቱን በብቸኝነት ይመራ የነበረው ቡድን ያጣውን ሥልጣን በኃይል ለመመለስ ማሰቡ ለሀገሪቱ ግጭቶች መንስኤ መሆኑን ገልጸዋል። @Wabi_Media