tgindex
ወልድ ዋሕድ ኮርስ

ወልድ ዋሕድ ኮርስ

Статистика
Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
353
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
162
23 постов
Вовлечённость
45,9%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
76
1/48двое суток
87
1/72трое суток
93

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ሰላም ለኪ ሲባል ለምን እንሰግዳለን ? ሰላም ለኪ ብለን የእመቤታችን ጸሎት ስንጸልይ አንገታችን ዘንበል የምናደርግበት ምስጢር አስቀድሞ በትንቢት የተነገረ÷ አሁን እየተፈጸመ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው። “ ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግምባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፥ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም። “ ትንቢተ ኢሳይያስ 49 ፥ 23

  • 13 авг.75из weldwahid

    አሁንም የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት ከይሁዳ ወገን ለኾነችው ንጽሕት ርግብ መፀነስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ የጾታዊ ተዋሕዷቸው ቀን ይኽቺ እንዴት ያለች የተመረጠች ቀን ናት፤ ለንጉሥ ማደሪያ አዳራሽ መመሥረት የተደረገባት (የኾነባት) የደስታ ቀን እንዴት ያላት ቀን ናት። (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ አርጋኖን ዘረቡዕ)

  • 12 авг.811из weldwahid

    ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ "ሰዎች የሰው ልጅ ማን ይሉታል?" ክፍል -2 በ ዲ/ን ዳንኤል ታደለ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

  • ሰላም ለእናንተ ሱባኤ እንዴት ነው? ወርሐዊ ጉባኤያችን ነሐሴ 10 ቀን 2018 10:30 መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን በ17 የምርቃት መርሐ ግብር ስለሆነ። መልካም ሱባኤ

  • 11 авг.911из weldwahid

    ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ "ሰዎች የሰው ልጅ ማን ይሉታል?" ክፍል -1 የባለፈው ሳምንት ትምህርታችን በ ዲ/ን ዳንኤል ታደለ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

  • 11 авг.92из weldwahid

    ​✨ የረቡዕ ጉባኤ ✨ ​ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በሌሎች እምነቶች ያለው አስተምህሮ በስፋትና በጠለቀ ሁኔታ የሚዳሰስበት ትምህርት ተዘጋጅቷል። ​ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት የሚሰጠው የዚህ ትምህርት ክፍል ፩ በዚህ ሳምንት ረቡዕ ይጀምራል! ​✨ መምህር፦ ዲ/ን ዳንኤል ታደሰ 📅 ቀን፦ ነሀሴ 6 ቀን  2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:30 - 1:30 📍 ቦታ፦ ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ​📖 “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” (ማቴ 16፥13)

  • 🎓የተማሪዎች ምርቃት🎓 “በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው። ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችኹ።”መዝ 118፡26 እንኳን ደስ አላችኹ። የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስትያን ወልድ ዋህድ ሰንበት ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም በመደበኛ እና በርቀት መርሐ ግብር  ያስተማረቻቸውን ተማሪዎች በደማቅ መርሐግብር ለማስመረቅ ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች ። ሁላችንም ነጭ ልብስ ለብሰን እንድንገኝ #ነሐሴ 17 🕰 7፡00 አራት ኪሎ በቅድስት ሥላሴ ዮኒቨርስቲ አዳራሽ 4ኛ ፎቅ 🎓🎓🎓  ነሐሴ 17 🎓🎓🎓

  • 10 авг.1061из weldwahid

    “ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን ለአምላክነቱ እንደሚገባ አምልከህ ከዚያ በኋላ ወደ ሥራህ ብትሔድ የምትሠራው ሥራ የተባረከና የሰመረ እንደሚሆንልህ አታውቅምን?" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

  • 8 авг.1441из weldwahid

    🔔ቅዳሴ🔔 "ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ"       መጽ ኢያሱ 3÷5 🔔ምስባክ ዘነሐሴ ፫🔔 የዕለቱ ምንባባት 1ኛ ቆሮ 8÷1-ፍ 1ኛ ጴጥ 4÷1-6 ሐዋ 26÷1-29 የዕለቱ ወንጌል ማቴ 12÷38-ፍ ቅዳሴ፦ ዘእግዝትእነ የዕለቱ ምስባክ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአሞኃ፤ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን።መዝ ፵፬÷፩፪-፩፫ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ #ቅዳሴ ወደ ጌታ ደስታ የመግባት ምሥጢር #እንዳላስቀድስ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

  • 8 авг.14121из weldwahid

    "ኃጢአት ለመሥራት ቀጠሮ ትይዛለህ፤ ጽድቅ ለመሥራት ግን ጊዜ የለኝም ትላለህ፡፡ ጓደኛህን ለማግኘት ጊዜ አለህ፤ ንስሐ አባትህን ለማግኘት ግን ጊዜ የለህም፡፡ በሥጋ ስትራብ ከየትም አምጥተህ (ለምነህም ቢኾን) ትበላለህ፤ ነፍስህ የክርስቶስ ሥጋ ከራባት ግን ዘመናት ተቆጠሩ፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባብ አሳተኝ ያለችውንና፥ ከፍርድ ያላመለጠችውን ሔዋን ታስታውሳለህን? እንግዲያውስ፥ አንተም እንደ እርሷ ምክንያት በመደርደር ራስህን ለማጽደቅ አትሞክር፡፡ ይህ ሲነገርህም በተግባር እንጂ በከንፈርህ መልስ ለመስጠት አትጣር፡፡" (መቅረዝ ዘተዋሕዶ የተወሰደ)

  • “​​የምታደርገውን ጸሎት ብዛት አትቁጠር፤ ይልቁንም በጸሎትህ ውስጥ ያለውን ትኩረትና እንባ መዝነው።እግዚአብሔርም የቃላትን ብዛት ሳይሆን የልብን ስብራት ያዳምጣልና።’’          ✍️ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

  • 6 авг.203101

    እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ "የምግባራት ኹሉ እናታቸው ጾም ደረሰች፤ ጸሎትና ምጽዋትም ልጆችዋ ናቸው፤ ሦስቱም ሀገራቸው አንድ ነው። እናት እና አባታቸውም አንድ ናቸው።"     🌹የርቱዓ ሃይማኖት ደራሲ 🌹 ፍልሰታ 1)በሰዓታት ፣ቅዳሴ ፣በኪዳን በቻልነው መሳተፍ 2)መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ 3) በቻልነው ለነዳያን መርዳት ( 1ብር መመጽወት) 4) በቻልነው ጠዋት እና ማታ መስገድ 5)በዚህ ጾም ከጌታ ዘንድ ምን መቀበል እንደምንፈልግ እናስቀምጥ 6)ማስወገድ የምንፈልጋቸውን ልማዶች/ኃጢአቶችን ለይቶ በማውጣት እግዚአብሔር ድል መንሳትን እንዲሰጠን መለመን 7)በ7ቱ የጸሎት ሰዓታት መጸለይ የበረከት ጾም ያድርግልን🙏

  • እንዴት አደራችሁ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ ደብራችን በጾመ ፍልሰታ ለምዕመናን ንፍሮ ከቅዳሴ በኋላ ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል ስለሆነም ለዚህ አገልግሎት ጊዜው ያላችሁ እህቶች ከዛሬ 9:00 ጀምሮ ንፍሮ ማዘጋጀት ስለሚጀመር በሚከተለው የቴሌግራም user @kirube11 ስማችሁን እና ስልካችሁን በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ።

  • 5 авг.173из weldwahid

    ዕቅበተ እምነት ክፍል-፩ ዛሬ

  • 4 авг.1852из weldwahid

    ​✨ የረቡዕ ጉባኤ ✨ ​ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በሌሎች እምነቶች ያለው አስተምህሮ በስፋትና በጠለቀ ሁኔታ የሚዳሰስበት ትምህርት ተዘጋጅቷል። ​ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት የሚሰጠው የዚህ ትምህርት ክፍል ፩ በዚህ ሳምንት ረቡዕ ይጀምራል! ​✨ መምህር፦ ዲ/ን ዳንኤል ታደሰ 📅 ቀን፦ ሐምሌ 29 ቀን  2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:30 - 1:30 📍 ቦታ፦ ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ​📖 “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” (ማቴ 16፥13)

  • ሰላምን ለእናንተ ዛሬ 10:30 ላይ ትምህርት የለንም

  • ሰላም እንዴት አመሻችሁ ለ8ኛ ክፍሎች ነገ ጠዋት 1:30 በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ እንገኝ የዕለቱ ይህን አገልግሎት የሚያስተባብረው መምህር ሀብታሙ ይሆናል።መልካም ፈተና ✅መታወቂያ እና እርሳስ እንዳትረሱ መልካም ምሸት

  • ሰላም ለእናንተ የ2018 ዓ.ም የሀገረ ስብከት አቀፍ ምዘና ዝግጅት ለማድረግ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዝግጅቱን አጠናቆል ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከ 231 ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅት ስታደርግ ቆይታለች በዘንድሮ  4፣8 እና 10 ክፍል ተማሪዎች በዚህ ዓመት የምታስፈትን ይሆናል። ስለሆነም የተወደዳችሁ ከላይ ስም ዝርዝራችሁ የተገለፀ  ተማሪዎች  እነዚህን ማሳሰቢያ እንድትተገብሩ እናሳስባለን 1.የመፈተኛ ጣቢያ ኮተቤ ኪዳነ ምህረት ትምህርት ቤት ነው። 2.መታወቂያ እና እርሳስ ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ። 3.ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መኪና ማቅረብ አልተቻለም ስለሆነም በዕለቱ 1:30 ሰንበት ትምህርት ቤት በመገኘት በዕለቱ ለዚህ አገልግሎት ከተመደቡ አባላት ጋር ወደ መፈተኛ ጣቢያ እንድትሄድ እናሳስባለን። ለኮተቤ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ቅርብ የሆናችሁ አባላት በዛው መሄድ ትችላላችሁ። ⚠️የድጋሚ ፈተና ስለሌለው በዕለቱ ፈተና በመገኘት ፈተናውን እንድትፈተኑ እናሳስባለን መልካም ዕድል እንመኝላችኋለን።     ትምህርት ክፍሉ

  • 31 июл.217из weldwahid

    ዛሬ

  • 30 июл.203из weldwahid

    ነገ አይቀርም