- Последний пост
- 15 мая
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የባቡሩ ሰራተኞች በአስቸኳይ ተጠርታችኋል‼ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት መልሶ ለመጠገን ወደ ሥራ ሊገባ መሆኑ እየተሰማ ነው። በመሆኑም ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል በስራው ላይ ተሰማርተው ለነበሩ የቀድሞ ሰራተኞች ዳግም የቅጥር ጥሪ አቅርቧል በማለት የኮምቦልቻ ከተማ ሥራና ክህሎት መምሪያ አሳውቋል። መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የሚከተሉትን ነጥቦች በማስተዋል መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል። 📌የምዝገባ ቦታ፦ በየክፍለ ከተማው በሚገኙ የሥራና ክህሎት ጽህፈት ቤቶች ወይም በ6ቱ የገጠር ቀበሌዎች በሚገኙ የሥራ ዕድል ፈጠራ ባለሙያዎች ዘንድ። 📌የምዝገባ ማብቂያ ቀን፦ከግንቦት 7-13/09/2018 ዓ.ም ድረስ 📌 አመልካቾች አስፈላጊውን የሥራ ልምድ ማስረጃ በመያዝ በግንባር ቀርበው መመዝገብ ይኖርባቸዋል ሲል የኮምቦልቻ ከተማ ሥራና ክህሎት መምሪያ ጥሪ አስተላልፏል። Wasu Mohammed - Mereja
видео или голосовое, без подписи
#IOM ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ባለፈው ወር መጨረሻ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እ.ኤ.አ 2025 በአፍሪካ ቀንድ ፍልሰተኞች ላይ ከፍተኛ የሞት አደጋ የተመዘገበበት ዓመት መሆኑን አስታውቋል። በተለይም ከአፍሪካ ቀንድ ተነስቶ በቀይ ባሕር በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ በሚዘልቀውና "ምሥራቃዊ የጉዞ መስመር" ተብሎ በሚጠራው አቅጣጫ የኢትዮጵያውያን ሰለባነት እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ተመልክቷል። እንደ አይኦኤም (IOM) ዘገባ፣ እ.ኤ.አ በ2025 በዚሁ የምሥራቃዊ የጉዞ መስመር 922 የሞት አደጋዎች ተመዝግበዋል። ከእነዚህ አስደንጋጭ የሟቾች ቁጥር ውስጥ 700 ያህሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ይህም አጠቃላይ ከሞቱት ፍልሰተኞች ውስጥ ከ76% በላይ የሚሆኑት ዜጎቻችን ናቸው። ቀሪዎቹ ሟቾች የሶማሊያ እና የኤርትራ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። የአይኦኤም ቃል አቀባይ አንድሪያ ጋርሲያ ቦርሃ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል " ኢትዮጵያውያን ይኼንን የፍልሰት መስመር የሚጠቀሙ ዋነኛቹ ዜጎች ናቸው። ሌሎቹ ዜጎች ሶማሊያዊያን እና ኤርትራዊያን ናቸው " ብለዋል። " በጣም የሚበዙት ግን ኢትዮጵያውያን ናቸው " የሚሉት ቦርሃ " የሚጓዙት መንገድ ደግሞ በጣም፣ በጣም ረጅም ነው። ከኢትዮጵያ ተነስተው በጂቡቲ አቋርጠው ይጓዛሉ። እናም የበለጠ ለአደጋ ተጋላጭ የሚያደርገው የመንገዱ ርዝመት ነው። "በምሥራቁ የጉዞ መስመር በዋነኛነት የሚጓዙት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ናቸው " በማለት አብራርተዋል። ወደ የመን በሚደረገው የባሕር ጉዞ የጀልባዎች መገልበጥ ለሟቾች ቁጥር መጨመር ዋነኛው ምክንያት ነው። ከባሕር አደጋ ተርፈው የመን ከደረሱ በኋላም ወደ ሳዑዲ ድንበር ለመሻገር በሚሞክሩበት ወቅት በሚሰነዘርባቸው ጥቃቶች ሕይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች መኖራቸው ተገልጿል። የሞት አደጋው ፍልሰትን ለምን አላስቆመም ? የአይኦኤም ቃል አቀባይ አንድሪያ ጋርሲያ ቦርሃ እንዳሉት፦ - በቀጣናው በተለይም በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ፣ በኤርትራ ያለው ሁኔታ - የኢኮኖሚ ችግር፣ - በድርቅ ምክንያት የሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥ ጫና - እነዚህ ሰዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ አስጊ ያልኾኑ መደበኛ የፍልሰት መንገዶች አለመኖራቸውንም አሁንም ሰዎች ለሞት እየተጋለጡ በዚህ አደገኛ መስመር እንዲጓዙ እያደረጋቸው መሆኑን አመልክተዋል። ምንም እንኳን ሰዎች በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ወይም ደላሎች አማካይነት ከቦታ ቦታ መዘዋወር እንደሌለባቸው ሁሎ ማሳሰቢያ ቢሰጥም መነሻቸውን ከአፍሪካ ቀንድ በማድረግ በየመን በኩል አቋርጠው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚጓዙ ሰዎች ለከፍተኛ አደጋ እየተጋለጡ ይገኛሉ። ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቬለ ሬድዮ ጣቢያ ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
"የአዋሽ-መቀሌ የባቡር መስመር አክሳሪ ኢንቨስትመንት ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክትን በተመለከተ ስንለው እንደነበረው "ባቡር ፕሮጀክቱ መንግስታዊ ደባ ተፈፅሞበታል።በመንግስት አሻጥር የመከነ ባቡር ነው"ነበር።ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስላረጋገጡልን እናመሰግናለን።እርስዎ ያላዩት በዚህ የባቡር ፕሮጀክት የወደፊት ብሩህ ተስፋ ላይ እምነት ጥለው ልጆቻችን ያልፍላቸዋል በሚል የዛሬ መጎዳታችን ችግር የለውም በማለት ስንቶች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ:መሬታቸውን እንደተቀሙና በከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ ነው😥።በቃ ይቅርብኝ ይሄ ጉዳይ ስሜታዊ ያደርገኛል።እናንተ የጀመራችሁት ፅድቅ ቀድሞ የተጀመረው እርግማን እንደሆነ ሰምተናል።ያማል።ጭራሽ ዛሬ አክሳሪ ኢንቨስተመንት መሆኑም ተገልጿል።ልብ በሉ ከአዋሽ ኮምቦልቻ 99% ስራው ተጠናቆ 1%ኤሌክትሪክ ብቻ ነበር የቀረው። 'ባጭሩ የአዋሽ-መቀሌ የባቡር መስመር የሚጓጓዝ ምርት በሌለበት ሁኔታ በ2.6 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ብድር በመገንባቱ አገሪቱን ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነግረውናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ይህ ገንዘብ በአሁኑ ወቅት እየተገነባ ባለው ዓይነት የማዳበሪያ ፋብሪካ ላይ ቢውል ኖሮ፣ ኢንቨስትመንቱ በ6 ዓመታት ውስጥ ተመላሽ ሆኖ ለባቡር መስመር ግንባታ የሚሆን ትርፍ ይገኝ ነበር። መስመሩ መሠረታዊ ቢሆንም "ያለ ጥናትና ያለ ምርት" መገንባቱ ግን አክሳሪ አድርጎታል"ያሉበት ቪዲዬ ተያይዞ ቀርቧል።በጣም ያሳዝናል።ባቡሩ የመከነው በመንግስት መሆኑን የሚያሳይ ነው። #WasuMohammed ==================== አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
"መሀሉ አይነገርም"!!! ዶክተር አብዱ ሁሴን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አብዱ ሁሴን በፌስቡክ የትስስር ገፃቸው "መሀሉ አይነገርም"በሚል ተከታዩን በግልፅ ያልተብራራ ለቅኔ የቀረበ ሃሳብ አጋርተው ተመልክተናል። <<"መሀሉ አይነገርም"!!! የእምነትና የሀቅ ማሳያ አንዱ ገፅ "መሀሉ አይነገርም" ሆኖ እንጅ ስለ ታላቅነት (ታላቁ¡)፣ አርበኝነት (አርበኛው¡)፣ ስለ ዋርካና ዝግባ የዛፍ ዓይነቶች እና ስለ እኛ ልህቀቶች አወራችሁ ነበር...ግን FB...Facebook ነው። ለማንኛውም ደውለናል፤ እየደወልንም ነው። መሀሉ ሲነገር ደሴ ድረስ ስለአጓጓዝኳቸው የዛፍ ዓይነት (ቶች) አወራችኋለሁ።>> ዶ/ር አብዱ ሁሴን
የወሎ ክልል ጉዳይ ምን ደረሰ ይሉኛል። የወሎ ክልልነት ሃሳብን ፈጥሮ ይቻላል ለካ የሚል ትውልድን በመፍጠር እና ጉዳዩን ወደ ፖለቲካ መድረክ እንዲመጣ በማድረግ ወደር የሌለው ድርሻ በመወጣት ግቤን መትቻለሁ። ማን ይተግብረው? መቼ? እንዴት? የሚለው ጊዜ ይፈታዋል። አሁን መሬት ላይ ወርዶ እየሰራ ያለ ወዴፓ የሚባል ፓርቲና የክልል አደራጅ ኮሚቴ አለ!! (የሁለቱም አባል አይደለሁም) የወሎ ጉዳይ፡ ከትችት ወደ አማራጭ (የመፍትሄ ሀሳብ) እንደ አንድ ለወሎ ጉዳይ እንደሚገባው ከልቡ እንደሚጨነቅ፣ ነገር ግን የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ (ወዴፓን ጨምሮ) ወይም የኮሚቴ አባል ያልሆነ ነፃ ወሎየ፤ ጉዳዩን ከወፍ በራር (Bird's-eye view) እና ከእውነታው አንጻር ስመለከተው የሚከተለውን ታዘብኩ። በየሄድኩበት የወሎን ጉዳይ አንገብግቧቸው የሚተቹ፣ የወዴፓንም ሆነ የኮሚቴውን ጉድለቶች የሚዘረዝሩ ወገኖችን እሰማለሁ። ትችቶቹ መሠረታዊ እና እውነት ሊሆኑ ይችላሉ። ሆኖም በፖለቲካ ሳይንስ አንድ የማይታለፍ ሀቅ አለ፡ "ፖለቲካ ባዶ ቦታን ይጠላል" (Power abhors a vacuum)። ይህንን መርህ ተከትለን እውነታውን እንጋፈጠው፡ 1. የመድረክ ባዶነት እና የባለቤትነት ጥያቄ የወሎን አጀንዳ በበላይነት ለመምራት፣ በአዋጭነት ጥናት እና በስትራቴጂ ለመምራት ብቃት ያለው "ትክክለኛ" ልሂቅ በዝምታ፣ በፍርሃት ወይም በዳተኛነት ወደ ኋላ ሲሸሽ፤ መድረኩ ባዶ ሆኖ አይጠብቅም። ክፍተቱን ያገኘው አካል (ብቁም ሆነ ዝቅተኛ አቅም ያለው) ቦታውን ይሞላዋል። ስለዚህ ዛሬ መድረኩ ላይ ላለው አካል (ወዴፓም ሆነ ሌሎች) መኖር ምክንያት፣ የብቁዎች አለመኖር ወይም ዝምታ ነው። "እኔ አውቅልሃለሁ፣ እኔ ባለቤት ነኝ" የሚለው አካል ሜዳውን ለቅቆ፣ ገብቶ የያዘውን አካል ከውጭ ሆኖ መተቸት "የፖለቲካ እሌትነት" (Political Absurdity) ነው። 2. ትችት ብቻውን ፖሊሲ አይሆንም እርግጥ ነው፣ አሁን ያለው እንቅስቃሴ እንከን ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን በእንቅስቃሴ ላይ ያለን አካል ለማረም ሁለት መንገድ ብቻ አለ፡ * አማራጭ መሆን፡ "ይህ አካል አይመጥንም" ከተባለ፣ የሚመጥን እና የተሻለ አደረጃጀት ፈጥሮ፣ የተሻለ ሀሳብ ይዞ ህዝብን ማሳመን። * ተሳትፎ (Engagement)፡ ካለው መዋቅር ጋር በመቀራረብ፣ ክፍተቶችን በመድፈን እና አቅጣጫውን በማስተካከል ጉዳዩን ወደሚፈለገው መስመር ማስገባት። ከዚህ ውጭ፣ የተሻለ አማራጭ ሳያቀርቡ፣ ወይም ገብቶ ለማስተካከል ሳይሞክሩ፤ ከሩቅ ሆኖ ድንጋይ መወርወር እና እንቅፋት መሆን፣ የወሎን ህዝብ ጥያቄ ማፈን እንጂ መብት ማስከበር አይደለም። 3. የማያወላዳው እውነት የወሎ ጉዳይ "ውጤቱ የከፋ ይሆናል" ብሎ የሚያስብ አካል ካለ፣ ይህንን አደጋ ሊቀለብስ የሚችለው ሜዳው ውስጥ ገብቶ ሲታገል ብቻ ነው። "አደጋ አለው" እያሉ ዳር ቆሞ ማየት፣ አደጋው ሲመጣ "እኔ ቀድሜ ተናግሬ ነበር" ለማለት ካልሆነ በቀር፣ ህዝብን አይታደግም። እኔ የማንኛውም ቡድን ጠበቃ አይደለሁም፤ የህዝብ ጉዳይ ጠበቃ እንጂ! መልእክቴም ግልጽ ነው!! የወሎ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ልሂቃን፣ ወይ የተሻለ አማራጭ ይዛችሁ ወደ ሜዳ ኑ፤ ወይ ያለውን እንቅስቃሴ ገብታችሁ አርሙት። አለበለዚያ "ወይም አይሰሩ ወይም አያሰሩ" ሆኖ መንገድ መዝጋት ታሪክም ትውልድም ይቅር የማይለው ስህተት ነው። የፖለቲካ ብስለት የሚለካው በትችት ብዛት ሳይሆን፣ በተጨባጭ አማራጭነት ነው! Abdujelil Sheh Ali Kassa
ከደሴ ወደ ባህርዳር‼ አማራ ክልል የት አካባቢ ህዝብን ባስቆጣ ይሻላል በማለት በሃሳብ ቆሞ የሚያድር አመራር ያለ ይመስላል።ከሰሞኑ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ሰበር ችሎትን ከደሴ ከተማ አንስተው ወደ ባህር ዳር ከተማ ለማዘዋወር ሂደቶች እያለቁ ይገኛሉ።ህዝቡ በቅርበት የፍትህ አገልግሎት እንዳያገኝ በማድረግ ምን ታተርፋላችሁ? ይህ ሲሆን የደሴና የደቡብ ወሎ ፍትህ መምሪያ የስራ ኃላፊዎች እጃቸውን አጣጥፈው ተቀምጠዋል።ለምን ብሎ መጠየቅ የለም።ኧረ በህግ አምላክ። ከዚህ በፊት ተጠራርገው የተወሰዱት ተቋማት ይሄው ህዝቡን ባህርዳር እያመላለሱት።ምን ለውጥ መጣ? አንዳንዶች"ወሎ ክልል መሆን አለበት" የሚለውን ሃሳብ የሚያቀነቅኑ ሰዎች ወደ አደባባይ እንዲወጡ የሚያበረታቱ ተግባራትን ራሳቸው እየፈፀሙ በጎን ሃሳቡን ያወግዛሉ። በየአካባቢው መገፋቶችን እየሰበኩ መከፋፈሎች እንዲበረቱ የምታደርጉ አመራሮች ተረጋጉ።አማራ ክልልን ፈረካክሶ ትንንሽ ክልሎችን ለመፍጠር በዚህ ልክ አሻጥር መስራት አያስፈልግም። ከዚህ በፊት:- 📌 የአማራ መስኖ ዲዛይን የምስራቅ አማራ ማስተባበሪያ ቢሮ 📌የኦዲት ቢሮ የምስራቅ አማራ ደሴ ቅርንጫፍን ሌሎችም እንዲነሱ ተደርጓል።ህዝቡ ይሁን ብሎ ዝም አለ።ዝም ካላችሁማ በዋናው ጉዳይ እንመጣለን ብላችሁ ይሄው ሌላ አጀንዳ አመጣችሁ።አይጠቅምም።ህዝቡ የሌሎችን መንገድ እንዲከተል አትገፋፉ።አይጠቅምም‼ የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ቤቱ ደሴ ምድብ ባለበት ይቀጥል።ወደ ባህርዳር ለመውሰድ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተገቢ አይደለም።አርሙት‼ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ሰበር ችሎትን ከደሴ ከተማ ወደ ባህር ዳር ከተማ ለማዘዋወር ፋይሎቸን ይዤ እሄዳለሁ በማለት መዝገቦችን በካርቶን አሽጎ እየጨረሰ ነው።ይሄ የሚመለከተው ማንን ነው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ብቻ ነው።ሌላው ከደሴ ከተማ እና ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደሮች ጋር የሚገናኝ አይደለም። ፖለቲካዊ አስተዳደሩ ከቻለ አገልግሎቱ ለሚመራው ህዝብ የሚሰጥ በመሆኑ ለምን? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።ከዛ ውጭ የታሸገ ካርቶን ትወስዳለህ አትወስድም የልጅ ጨዋታ ውስጥ የሚያስገባ አይደለም። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ ሀሰት ነው ብሎ የለም እኛም መጨረሻውን እናየዋለን።ጩኸታችን ተሰምቶ ሀሰት ሆኖ ከተገኘ እኛ ስለተገልጋዩ ህዝብ ስንል ሀፍረቱንም ውርደቱንም ውሸታምነቱንም ብንወስድ አይከፋንም። #ዋሱመሐመድ
ሊታረም ይገባል‼ ዛሬ ዝም ከተባለ ነገሩ መልኩን እየቀየረ ሊመጣ ይችላል።ህዳር 20/2018 ቅዳሜ ምሽት 2:00 ሰዓት ላይ በኮምቦልቻ ከተማ በቢራሮ ክፍለ ከተማ የፖሊስና የሚኒሻ አባላት 3 ወጣቶችን ይይዛሉ።ሁለቱ ባልና ሚስት ሌላው አንድ ወጣት ነው። ከያዙ በኋላ ወጣቶቹ ጥፋተኛ ከሆኑ ጣቢያ ወስዶ ማሰር ሲገባቸው ከህዝብ የተሰጣቸው ህግ የማስከበር ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ወንዶቹን ከባድ ድብደባ እንዳደረሱባቸው ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። የተላከልኝ ምስል ከቀናት በፊት ደሴ ከተማ 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ የተፈፀመ ድብደባ ነው በሚል ሲስተጋባ ቢቆይም ጉዳዩ የተፈፀመው ኮምቦልቻ ከተማ ሆኖ ተገኝቷል።በርግጥ የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እነ ኮማንደር ጥላሁን ጉዳዩን በጊዜው አስተባብለዋል። እንደዚህ አይነት ከህግ ያፈነገጠ አስነዋሪ ተግባር እንድታረም የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መስራት ቢኖርበት መልካም ነው።አጥፊዎችን ተጠያቂ ካላደረጋችሁ ነገ ከህዝብ ጋር አለመተማመን ውስጥ ያስገባል።በዚህ የሚከፋው ሰው ቢኖር የድርጊቱ ፈፃሚ ብቻ ነው። #ዋሱመሐመድ
የወሎ ነዳጅ ውሳኔ ለመስጠት ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው የተውጣጣ የባለድርሻ አካላት ቡድን አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ ገብቷል። ለገሂዳና ወረኢሉ ወረዳዎችን በሚያዋስነው መቸላ ወንዝ በአለት ስንጥቅ ወጥቶ የሚታየው ነዳጅ ለሀገር ልማት ይውል ዘንድ ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ከዞን ዘርፉ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፤ ከወሎ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች ዛሬ ታህሳስ 1/2018 ዓ.ም በቦታው ተገኝተዋል፡፡ ለእንግዶቹም በወረዳ አስተባባሪ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አካባቢውን ተመልክተው፤ በአለት ላይ ከሚታየው ፈሳሽ ናሙና ወስደው፤ በ2005 ዓ.ም ነዳጅ ሲያፈላልግ የነበረው ድርጅት ከፍተኛ ክምችት እንደሚገኝ አመላክቶት የነበረውን ጎራና ት/ቤት አካባቢ ከነዋሪዎች በተሰጣቸው ማብራሪያ በመነሳት በጂፒኤስ መረጃ ወስደዋል። መንግስት ለማዕድን ዘርፍ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ የገለጹት ባለሙያዎቹ ዛሬ ያዩትን ሀብትም ክትትል እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡
видео или голосовое, без подписи
" ነዳጁ በትክክል ወጥቶ መሬት ላይ እየታየ ነው ፣ በተሰነጠቁ መሬቶች አማካኝነት የወጣው ነዳጅ በአካባቢው የሚገኙ ውሃዎችን እየበከለ ነው " - የደቡብ ወሎ ዞን የማዕድን ሀብት ልማት መምሪያ በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ የነዳጅ ክምችት በተፈጥሮ አስገዳጅነት ከከርሰ ምድር በላይ መውጣት ከጀመረ ከ7 አመታት በላይ ቢያስቆጥርም እስካሁን ጥቅም ላይ እንዲውል ባለመሰራቱ አሁንም የነዳጅ ድፍድፉ መሬቱን ሰንጥቆ እየወጣ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ማዕድን ሀብት ልማት መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። በመምሪያው የማዕድን ስራዎች እና ፍቃድ አስተዳደር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጀማል እንዲሪስ ይህን የነዳጅ ክምችት አዋጪነቱ ተጠንቶ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ በተደጋጋሚ ለማዕድን ሚኒስቴር ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግረዋል። አቶ ጀማል እንዲሪስ በዝርዝር ምን አሉ ? " ከዚህ በፊት በወረዳው ያለውን የነዳጅ ክምችት ጥቅም ላይ ለማዋል የተለያዩ ፕሮጀክቶች በግል ተቋማት እና በመንግስት ተቋማት ሲሞካከሩ ነበር። እኛም በየጊዜው ጉዳዩ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ስናደርግ ቆይተናል። እኛ ማድረግ የምንችለው ጥናት እንዲካሔድበት ግፊት ማድረግ ነው፣ በዚህም መሰረት በ 2011 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ውይይት አካሒዶ ነበር። በሰአቱም ሀብቱ እንዳለ ከመሬት በላይ በምልክት ተጋልጦ እየታየ ስለሆነ ሀገራችን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ እንዲጠቀም ለማድረግ ጥናት እንዲካሔድ ጥያቄ አቅርበንላቸው ተቀብለውን ነበር። ጥናት ለማካሔድም እቅድ መያዙን ነግረውናል፣ ከዛን በሗላ ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ እየተደረገ አይደለም። እንደዞን አሁን ያለን ሃሳብ ጉዳዩ በተለያዩ ሚዲያዎች ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ እና ከላይ ያሉት የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው ጥናት እንዲያደርጉ ጫና ማሳደር ነው። እኛ አቅደን የማንሰራው ጉዳይ ስለሆነ ፍላጎት እና ሀሳብ ነው ያለን። ምክንያቱም ይህን የመስራት ስልጣን የተሰጠው ማዕድን ሚኒስቴር ብቻ ነው። ነዳጁ በትክክል ወጥቶ መሬት ላይ እየታየ ነው፣ በተሰነጠቁ መሬቶች አማካኝነት የወጣው ነዳጅ በአካባቢው የሚገኙ ውሃዎችን እየበከለ ነው። በዚህ የነዳጅ ክምችት ላይ ክልሉም፣ ዞናችንም፣ ወረዳውም ፍላጎታችን ተመሳሳይ ነው። የለገሂዳ ወረዳ ኮሚኒኬሽን በተደጋጋሚ ትኩረት እንዲሰጠው እየጠየቀ ነው፣ አመራሮችም በየጊዜው በተገኙበት መድረክ ሁሉ ስለ ጉዳዩ ሳያነሱ አያልፉም፣ ነገር ግን የሚመለከተው አካል ' ጥናት እናደርጋለን ' ብሎ ቃል ከመግባት የዘለለ ነገር አያደርግም። አሁንም ጥያቄውን እያቀረብን ነው። በመሆኑም አሁን ላይ በተሰነጠቀው መሬት ከላይ የሚፈሰውን ድፍድፉን የአካባቢው ማህበረሰብ በመውሰድ ለምሽት መብራትነት በኩራዝ በባህላዊ መንገድ እየተጠቀመበት ነው። ይህ ማዕድን ለሀገር ትልቅ ገቢ ቢሆንም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ባለመሆኑ ነዳጁ እየባከነ ነው። ከመሬት በላይ ያለው ወይም የሚታየው ድፍድፉ በጣም ቀጭን አይደለም፣ ግን በጣም ይሸታል፣ ተቀጣጣይ ነው፣ ለናሙና ቢሮ ያመጣነው አለ፣ ስናቀጣጥለው በጣም ይቀጣጠላል። ይህን የተፈጥሮ ሀብት ጥቅም ላይ ለማዋል መስራት የሚችለው እና በአዋጅ መብት የተሰጠው ማዕድን ሚኒስቴር ነው፣ በአቅም ደረጃም ቢታይ ወረዳው አይችልም። ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት የተለያዩ ባለሙያዎችን እና ተማሪዎቹን በስፍራው በመውሰድ ምልከታ አድርጎ ነዳጅ መሆኑን አረጋግጧል። በወቅቱ ባለሙያዎቹ አካባቢው በተዳከመ የመሬት Fault ነዳጁ ወደ ውጪ እንደወጣ ነው ያስረዱት። ነዳጅ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ነገር የለም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
የወሎ ለገሂዳ የነዳጅ ክምችት!!!
Amhara Regional State <<...ሴት ልጆቻቸውን አናስደፍርም ያሉ እናቶች በጥይት ተደብድበው እየተገደሉ ይገኛሉ....ተው የሚል ሽማግሌ፣ በቃ የሚል ምሁር፣ እርቅ አውርዱ የሚል የኃይማኖት አባት የለም....>>አቶ ጋሻው መርሻ <<ህዝባችን መሸከም ከሚችለው በላይ ግፍ እያረፈበት ሁለት ዓመታት እንደ ቀልድ ተቆጥረዋል። ህጻናት ከትምህርት ከተራራቁ፣ መምህራን ከብላክ ቦርድ እና ጠመኔ ከተለያዩ፣ ነጋዴ የባንክ ብድር መክፈል ዳገት ከሆነበት፣ እምቦቃቅላ እህቶቻችን እንደ በግ ተነድተው መደፈር ከጀመሩ፣ ሾፌሮች ምድር ሲኦል ከሆነባቸው፣ በላባቸው አደሮች ተንቀሳቅሰው መስራት የሊማሊሞን ገደል ያክል ከባድ ከሆነባቸው እንደ ዘበት ዓመታት ነጎዱ። የእናት አገር ልጆች በግራና በቀኝ ጣለው ጣለው በሚል የYoutube ገደል ማሚቶ ታጅበው መገዳደል ስራዬ ብለው ከያዙት ይኸው ሶስተኛ ዓመታችን ደፈንን። ተው የሚል ሽማግሌ፣ በቃ የሚል ምሁር፣ እርቅ አውርዱ የሚል የኃይማኖት አባት የለም። ገሚሱ ግፋ በለው ሲል ገሚሱ ፀጥ ብሏል። በመካከል ህዝብ አሳሩን እየበላ ይገኛል። ያሳዝናል...! እንደ አማራ ህዝብ የወላድ መካን የሆነ የወዴት ይገኛል...! ሴት ልጆቻቸውን አናስደፍርም ያሉ እናቶች በጥይት ተደብድበው እየተገደሉ ይገኛሉ። ይኸ ከሰው በታች የሆነ ድርጊት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ የተከሰተ አይደለም። ከመደጋገሙ የተነሳ ዜናውን ሁሉ የለመድነው የአዘቦት ተግባር እንጅ። እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ከጥቂት ዓመታት በፊት በፊልም ብንመለከተው ኖሮ ደራሲውን ቀሽም እንደሆነ እና የማይታመን ነገር እንደጻፈ ልናስብ እንችል ነበር። በአሁኑ ወቅት የእለት ተዕለት ትዕይንት ሆኗል። በትውልድ ሰፈራችን መከራ እንደ ሐምሌ ጎርፍ እየወረደ ይገኛል። ድኃው ህዝባችን ወጥቶ መግባት፣ አርሶ መብላት፣ ነግዶ ማደር ባይችል በመከራ ያሳደጋቸውን ልጆቹ እንኳን ሊተርፉለት አልቻለም። ሴት ልጅን ከእናቷ እቅፍ ነጥቆ መድፈር፣ ወንድ ልጇን በጥይት አረር መቁላት የጀብድ ያክል የሚያኮራ ሆኗል። ቀስ በቀስ ወደ ጥልቁ ጉድጓድ እየተምዘገዘግን እንገኛለን። ዓለም የት በደረሰበት የAI ዘመን ላይ ብንገኝም ድንቁርናን አንቱ ብለን የምንከባከብ ጉዶች ሆነናል። በእውነቱ ለመጻፍ አይደለም ለመስማት የሚቀፉ እነዚህን ጭካኔዎች እንዴት በአጠረ ጊዜ ተለማመድናቸው? ብለን መልስ አልባ ጥያቄ እንጠይቃለን። መንግስት፣ ተዋጊ አካላት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የድንጋይ ዘመን ድርጊት በተቻለ ፍጥነት እንዲቆም ከመቸውም በላይ ሊሰሩ ይገባል። ይኸ ጉዳይ የግድ መቋጨት አለበት። ህዝባችን ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ሆኖበታል። ከአሁን በኋላ የሚቀጥል ግጭት ፈረንጆቹ "the last straw that broke the camel's back" እንደሚሉት ነው።>> አቶ ጋሻው መርሻ
ደሴ ከተማ ምን ተፈጠረ? ዛሬ ጥቅምት 26/2018 ደሴ ከተማ ሸርፍ ተራ የሸቀጣ ሸቀጥ :የህንፃ መሳሪያ አከፋፋዮችና ሌሎች አካባቢ የንግድ ድርጅቶች መዘጋታቸውን የሚያመለክቱ በርከት ያሉ ጥቆማዎች ደርሰውኛል።ምክንያቱን አንዳንዶች ከክልል በመጡ ተቆጣጣሪዎች ናቸው ተብሏል እንደት? ለሚለው ከነጋዴዎች የመጡት አስተያየትና ጥቆማዎች:- 📌<<በደሴ የሚደረገው ጫና አንዳንድ የመንግስት ሰራተኛ ሁነው መንግስትን የሚቃወሙ የክልልና የከተማ አስተዳደር አሉ እና የሚሰሩት ስራ የፌደራል መንግስቱን ለማስጠላት ነው የሚመስለው የፌደራል መንግስቱ እንደዚህ አደረገ ተብሎ እንዲታሰብ ይመስላል ስራቸው አሁን ላይ ነጋዴው ከክልል በሚመጣ ህግ ምርር ብሎት ሱቁን ዘግቶ ቢጠፋ ደስታው ነው ደግሞ ጫናው ደሴ ብቻ ነው አሁን ላይ መስራት አልቻለም>> 📌<<ደሴን ለማዳከም ክልሉ የሚጥለዉ ግብር እጅግ የሚገርም ነዉ>> 📌<<ነጋዴው አዳዲስ ህጎችን ሌላ አገር የሌሉ ደሴ ላይ እያመጡ አስመርረውት አሁን ሰርቶ መለወጥ ሳይሆን አንዳንዶቹ ነጋዴወች ከከተማው እየወጡ ነው።>> 📌<<ግብር ላይ በፊት ሲከፍሉት የነበረው 30% አሁን ወደ 60% ተጥሎባቸው እንደሆነና አሁን ካለው የሰላም ሁኔታ እንኳን ግብር የቤት ኪራይም ከወረታቸው ይከፍላሉ>> 📌<<ደሴና አካባቢው ለምን ሰላም ሆነ ብለው የክልል ሰዎች የፈፀሙት ሴራ ነው ሱቅ አንከፍትም በሩን ሰብረው ጭነውት ይሂዱ>> 📌<<የደሴን ከንቲባ ቢሮ የሰራነው እኛ ኮሪደሩን የሰራነው እኛ ሁሉንም ከንቲባችን ያውቃል የክልል ሌቦች ደሴን ለማዳከም የሸረቡት ሴራ ነው>> የሚሉና ሌሎችም በጣም በርካታ አስተያየትና ጥቆማዎች መጥተዋል።የደሴ ከተማ አስተዳደር የሚነሱትን ሃሳቦች ከግንዛቤውስጥ በማስገባት ጉዳዩ በውይይት እንዲፈታ ቢያደርግ መልካም ነው።ከከተማ አስተዳደሩ የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ አስተናግዳለሁ። Wasu Mohammed
ይህ ግፍ የተፈፀመው በአዋሽ ኮምቦልቻ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት ላይ ነው።የሀዲዱ ሙሉ ቡለን እና የኤሌክትሪክ መስመሩ ተዘርፎ አልቋል።ሀዲዱን ነቅሎ ለመውሰድ እየተደረገ ያለውን ጥረት በጣም ያሳፍራል። ላም አለኝ በሰማይ ነው እና ብሂሉ የምድር ባቡር የሚሰጠው ተስፋ እና መሬት ላይ ያለው እውነታ እርቀቱ ይሄ ነው።
"ወላሂ ወሎ ሲባል ስሰማ አንጀቴ ይላወሳል" ሼህ በሽር አሊ ቦንጋ ለስራ በሄድኩበት ነው። ቦንጋ መምህራን ኮሌጅ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት ቡና ከሚሸጡ የኮንቲነር ቤቶች በአንዷ ቁጭ ብያለሁ። እኚህ የምትመለከቷቸው አዛውንት ሰላም ነህ ልጄ? ና እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ" ብለው ጠሩኝ። እኔም ሳላመነታ የአባት ጥሪ ተቀብዬ ተጠግቼ ሰላም አልኳቸው። "ምን ልታዘዝ አባቴ?" ስል በቻልኩት መጠን በትህትና ጠየኳቸው። "ምን መሰለህ ወሎዬ ነኝ፣ የሰው ሀገር ሲመጣ ሁሉም ወሎዬ ይመስለኛል" አሉና አንገታቸውን ለጥቂት ሰከንዶች በትካዜ አቀርቅረው መሬት መሬቱን ማየት ጀመሩ። ቀጠሉና "እና ለዛ ነው የጠራሁህ፣ ደቡብ ወሎ "ከወረኢሉ-ካቤ" በቅርብ ርቀት በምትገኘው ደኙ- (7 ወንዝ ተሻግሮ) በምትባል ሰፊ ሜዳ ያላት አካባቢ እንደተወለዱ ነገሩኝ።ገና ታዳጊ እያሉ አንድ ሰው አዲስ አበባ ልውሰድህ ብሎ አባብሎ እንደወሰዳቸው አጫወቱኝ። 👉ይመር አሊ 👉ያሲን አሊ 👉መሀመድ አሊ የሚባሉ ሶስት ታላላቅ ወንድሞች እንዳሏቸውም አወጉኝ። እና ከዛ ሰውዬ ጋር እንደወጡ እንደቀሩ፣ አሁን ቦንጋ ልጆችና የልጅልጆች አፍርተው እየኖሩ እንደሆነም ነገሩኝ። ሼህ በሽር በግምት ከ8 እስከ 10 ዓመት እድሜአቸው ወሎንና ቤተሰቦቻቸውን ጥለው አሁንም በግምት 81 ዓመታቸው ድረስ ከዘመዶቻቸውና ከወሎ እንዳልተያዩ በቁጭት፣ እንባ እየተናነቃቸው ገለፁልኝ። "ዘመዶቼ ከእናንተ ምንም ፈልጌ አይደለም፣ ከኔም ምንም ታገኛላችሁ ብዬ አይደለም ሳልሞት እንተያይ" ሲሉ እርጅና የተጫጫናቸው አይኖቻቸው እንባ እየተናነቃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። "ወላሂ ወሎ ሲባል ስሰማ አንጀቴ ይላወሳል" ሼህ በሽር አሊ- የወሎው- የቦንጋው አዛውንት‼ዘመዶቻቸውን እናገናኛቸው! 👉0917898090- ሩቆያ በሽር 👉0917255153- ይመር በሽር ✍️ጌራ ጌታቸው @wasulife