tgindex
የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ. ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ዋና ገጽ Wulude Brhan SS

የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ. ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ዋና ገጽ Wulude Brhan SS

Статистика

ይህ የእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዉለደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ዋናው ገፅ ነው በዚህ የሰንበት ት/ቤት ዋና ገፅ ላይ በሰንበት ቤት ስም የሚለቀቁ ትምህርቶች፣ መዝሙሮች፣ ኪነ ጥበባዊ በጽሑፎች እና የሰንበት ት/ቤቱ መልእክቶች የሚተላለፍበት ነው። ስለሆነም ወደ ዋናው ገፅ እንድትቀላቀሉ ይሁን የሰ/ት/ቤቱ ሥራ አመራር ጽ/ቤት

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
8
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
321
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
253
22 постов
Вовлечённость
78,8%
к подписчикам
Постов в день
1,1
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
127
1/48двое суток
145
1/72трое суток
156

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 12 авг.1131из ema26kiya

    видео или голосовое, без подписи

  • ✝✝የሐዘን መግለጫ✝✝ የደብራችን አገልጋይ የነበሩት የመምሬ አሥራት ልጅ ከዚዓለም ድካም ስላረፈች ዛሬ ማለትም ዕሮቡ በ 6/12/2018 ዓ/ም የማጽናኛ መርሐግብር በቤታቸው በ12:00 ሠዓት ላይ በመገኝት መርሐግብሩን እናደርጋለን ላልሰሙት በማሰማት መረጃውን እናድርስ። አድራሻ 02 መጣት ማዕከል ከፍ ብሎ

  • 11 авг.2088из ema26kiya

    https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScL0A9keNRzo2QYFWsK4SoF1cm9BwXB11v_N7Pqc2k8vpekFw/viewform?usp=publish-editor

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • አመራሩ ይህን ድልድል ካደረገ በኋላ በተሰጠው ኃላፊነትና ስልጠን መሰረት የየስራ አባላት ለ7ቱም የአገልግሎት ክፍሎች በመምረጥ በሚከተለው መልክ ድልድል አድርጓል። ጽ/ቤት ዋና ሰብሳቢ ሶስና ፋንታሁን ም/ሰብሳቢ ፌቨን ፍስሐ ፀሐፊ ሲ/ር ቤተልሔም ተስፋዬ የአገልግሎት ክፍሎች መሪዎች 1. ትምህርት እና ስልጠና ያሬድ ጌታቸው 2. መርሃ ግብርና ጉባኤያት ቤተልሔም አሰፋ 3. መረጃና የውስጥ ግንኙነት ተሾመ ወ/ሰንበት 4. መዝሙርና ሥነ ጥበብ ጌታቸው ገ/ሥላሴ 5. የሰው ሃብት አስተዳደር ርብቃ ወርቅነህ 6. ልማትና በጎ አድራጎት ዮርዳኖስ አንዱአለም 7. በጀትና ንብረት አስተዳደር ኑሃሚን ጌታሁን ናቸው

  • አዲስ የተመረጡ አመራሮች እና የማስተባበሪያ ክፍል ድልድል ተደርጓል። በዚህ መሰረት ጽ/ቤት 1. ዋና ሰብሳቢ ታዬ ደንቦላ 2. ምትክል ሰብሳቢ ሶስና ፋንታሁን 3. ዋና ፀሐፊ ዲን ሮቤል ነቢዩ አመራርና የማስተባበሪያ ክፍሎች ተጠሪዎች 1. ዕቅድ ጥናትና ምርምር ማስተባበሪያ ሙሉእመቤት ፍቃዱ 2. ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ተካልኝ ፃራ 3. ትምህርት እና ዕቅብተ እምነት ማስተባበሪያ አብርሃም አስፋው 4. አባላትና ተቋም አደረጃጀት ማስተባበሪያ ወንድወሰን ፋንታሁን 5. መረጃና ወቅታዊ ጉዳይ ማስተባበሪያ ሰናይት አሻግሬ 6. ምጣኔ ሃብትና ማህበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ካሳሁን ጉማታው 7. ሒሳብና ንብረት አስተዳደር ማስተባበሪያ አዜብ ታፈሰ

  • ✨ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በሙሉ ✨ 🔴 አስቸኳይ መልእክት 🔴 ቀን፡ 04/12/2018 ዓ.ም 🕊️ *«ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁም ጋር ይሁን!»* 🕊️ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ለቀጣይ 3 ዓመታት የሚያገለግሉ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አመራሮች መመረጣቸው ይታወቃል። በቀጣይ ዓመታት በተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎች ተመድበው የሚያገለግሉ አባላትን ለመደልደል እንዲመች እስከ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም ድረስ ምሽት ከጸሎት በኋላ መመደብ የምትፈልጉበትን የአገልግሎት ክፍል ምርጫ እንድታሳውቁ በአክብሮት እናሳውቃለን። 📌 ማሳሰቢያ፡ * ⏳ የመጨረሻ ቀን፡ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም (ከምሽት ጸሎት በኋላ) * 📍 ቦታ፡ በሰንበት ትምህርት ቤት

  • ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!!የተደራረቡ መርሀግብሮችን በመኖራቸው ምክንያት በ3የሚኖረን መርሀግብር ላይ የነሀሴ ጽዋ የሚካተት ሲሆን በዕለቱ ከስልጠናው በተጨማሪ ስራ አስፈጻሚ አባላት ይፋ ይደረጋሉ በተጨማሪም አባላት በቀጣይ ማገልገል የሚፈልጉትን የአልግሎት ክፍል የሚሞሉ ይሆናል!

  • 6 авг.188из mkpublicrelation

    የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል። ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን አስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ አድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ አላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በአጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብር አዞናል ከቅዱሳን ፍጥረታት መካከል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም አብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብራት እዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በአጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢአታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት አውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር አባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ነው።

  • видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.132из mkpublicrelation

    ቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ምክንያት አድርገው መልእክት አስተላለፉ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፣ አሜን በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺህ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን አካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ አካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን አካላት ግንኙነት በአካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ አይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከአካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ አንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር አምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ. ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ዋና ገጽ Wulude Brhan SS — tgindex