- Последний пост
- 28 нояб.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Spreading Contagious Diseases — Criminal Liability Under Ethiopian Law Under Article 514 (1–3) of the FDRE Criminal Code, the intentional or negligent transmission of any contagious disease is a criminal offense. 1. Intentional Transmission Any person who intentionally spreads or transmits a contagious disease to another person commits a crime and is punishable with rigorous imprisonment of up to ten years. 2. Aggravated Circumstances The punishment becomes more severe when the perpetrator: Acts out of hatred, cruelty, revenge, or malice; Intends to cause serious bodily injury or death; Actually causes serious harm or death even without such intent; or Spreads a disease classified as an epidemic. In these cases, the penalty may be: Rigorous imprisonment up to twenty years, Life imprisonment, or Death penalty, depending on the gravity of the offense. 3. Negligent Transmission Where the disease is spread through negligence or carelessness, the law provides for simple imprisonment or fine. Conclusion Under Ethiopian criminal law, the transmission of any contagious disease—whether COVID-19, tuberculosis, HIV (where applicable), viral epidemics, or other communicable illnesses—can result in severe criminal penalties. Beyond the legal consequences, individuals have a moral and humanitarian obligation to exercise caution and prevent the spread of disease to others.
@followers share the page #የኢትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ 1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡ 2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡ 3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:- ፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው ፪=በራሱ ፈቃድ ፫=በጤና ጉድለት ፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት ፭=በሞት ናቸው፡፡ 4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:- ፩= በእርጅና ፪=በህመም ፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ ፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡ 5ኛ የጡረታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:- ፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡ ፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም):: 6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:- = ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል። ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡ 7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ.ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡ 8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡ 9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡ 10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:- ፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2) ፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ ፫= የጡረታ መለያ ቁጥር ፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ ፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ ፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ ፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ ናቸው፡፡
👉አስቀድሞ በተሸጠ የውርስ ሀብት ላይ ድርሻ አለኝ የሚል ሰው ድርሻውን ሊጠይቅ የሚችለው ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጎ ሀብቱን ገዝቶ በእጁ ካደረገው የቅን ልቦና ገዥ ሳይሆን የውርስ ድርሻውን ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ካስተላለፈው ሰው (ቤተሰብ) ስለመሆኑ። በመሆኑም አስቀድሞ የተደረገ የሽያጭ ውል ፈርሶ የውርስ ሀብት ድርሻዬ ይለቀቅልኝ በሚል የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም። ሰ.መ.ቁ.222435 [ያልታተመ [የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 997፣1195፣2882-2884]
የበርካታ ባለሐብቶች የባንክ ሂሳብ እየታገደ መሆኑ ተሰማ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተሻለ ቢዝነስ ያንቀሳቅሳሉ የሚመባሉ የበርካታ ባለሐብቶች የባንክ ሂሳብ እየታገደ እንደሆነ መሠረት ሚዲያ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። እነዚህ በአብዛኛው የአማራ ተወላጅ የሆኑ ባለሀብቶች እየተመረጡ ተንቀሳቃሽ ሒሳባቸው በህግ እየታገደ ወይም Legal Restriction እየተደረገባቸው እንደሆነ ፐ ተናግረዋል። በአማራ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር በተያያዘ ለታጣቂዎች ድጋፍ ሊያደርጉ ይችላሉ የተባሉ ሁሉ 'ከላይ በመጣ ትእዛዝ) በሚል በጥርጣሬ ባንካቸው እየታገደባቸው ይገኛል። ንግድ ባንክ ላይ ብቻ ቢያንስ 200 የሚሆኑ የእነዚህ ባለሀብቶች አካውንቶች እንደታገዱ ታውቋል ፣ የግል ባንኮች ላይ በተመሳሳይ ቁጥራቸው ያልታወቀ እገዳዎች መደረጋቸው ታውቋል። "አብዛኞቹ የፍርድ ቤት እግድ እንኳን የሌለባቸው ናቸው፣ በጥርጣሬ በሚል በርካታ አካውንቶች ተዘግተዋል" ያሉት ምንጫች ሁኔታው የዛሬ ሶስት እና አራት አመት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት የትግራይ ባለሀብቶች ላይ ከተደረገው ጋር ተመሳሳይነት አለው ብለዋል። በዚህ ዙርያ አካውንታቸው የታገደባቸውን አንድ ነጋዴ "አካውንቱ መታገዱን የሰማሁት ከቢሮዬ ተደውሎ ክፍያ መፈፀም አልቻልንም ሲሉኝ ነው" ብለዋል። እኚህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነጋዴ ወደ ንግድ ባንክ ሄደው ሲያጣሩ "ለግዜው እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እግድ ተጥሎበታል ተባልኩ፣ ሌላው ቀርቶ በወረቀት ላይ የተፃፈ ማብራርያ ወይም ለእግዱ ማረጋገጫ አልሰጡኝም" በማለት አስረድተዋል። በተመሳሳይ እርሳቸው የሚያውቋቸው የአራት የአማራ ተወላጅ የቢዝነስ ባለቤቶች አካውንታቸው እንደታገደባቸው እንደሰሙ ጠቅሰው ወንጀል ባልፈፀሙበት እና ክስ እንኳን ባልቀረበበት ጉዳይ ለ40 አመት የሰሩበትን የንግድ ስራ እንዲያቆሙ እንደተገደዱ ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙርያ ከብሄራዊ ባንክም ሆነ ከሌላ የመንግስት አካል የተሰጠ መግለጫም ሆነ ማብራርያ የለም። መረጃው የመሠረት ሚዲያ ነው Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube https://t.me/ethiotube https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L
без подписи
ተመዝገቡ
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት በማድረስ የተከሰሰው በረከት አለኸኝ ጥፋተኛ ተባለ ***************** (የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ. ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ክስ የቀረበበት በረከት አለኸኝ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈበት። የፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በረከት አለልኝ በተባለ ተከሳሽ ላይ በነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በሀሰተኛ ሰነድ የባንክ ሒሳብ መክፈት፣ በህገወጥ መንገድ ንግድ ፍቃድ ማውጣትና ማደስ፣ የታክስ አዋጁን መተላለፍ፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን መጠቀም፣ የገቢ ደረሰኞችን አትሞ ለተለያዩ ነጋዴዎች ማሰራጨት የሚል ተደራራቢ ሰባት ክስ በዝርዝር ማቅረቡ ይታወሳል። በተለይም በመስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም እና በመስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም ፍቃድ በማሳደስ የተመዘገበዉ በአስመጪነት ንግድ ስራ ዘርፍ ሆኖ ሳለ ምንም አይነት እቃ ከዉጭ ሳያስገባ እና የሀገር ዉስጥ የዕቃ ግዥ ሳይፈጽም ከወሰደው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ደረሰኞችን በማተም ለ339 ግብር ከፋዮች 1 ሺህ 663 ደረሰኞችን በማሰራጨት በ15 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ 25 ቢሊየን 989 ሚሊየን 943 ሺህ 223 ብር ከ83 ሳንቲም ጉዳት ደርሷል በማለት ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ክሶች መካከል ጠቅሶ ነበር። ዐቃቤ ሕግ በክስ ዝርዝሩ ላይ ከ30 ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል በማለት ያቀረበው ዝርዝር ክስ ለተከሳሽ ከደረሰው በኋላ ግለሰቡ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ፤ ዐቃቤ ሕግ 13 የሰው ምስክሮች እና 23 የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም የተሰሙ የሰው ምስክሮችን ቃልና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ብይን ሰጥቶ ነበር። በዚህም ፍርድ ቤቱ በ1ኛና በ2ኛ ክሶች ላይ ማለትም ሰለሞን ሙሉ ከውል በሚል የፈጠራ ስም በወጣ ሀሰተኛ የኗሪነት መታወቂያና ሀሰተኛ ውክልና መሰረት የንግድ ፍቃድ በማውጣትና በማሳደስ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት ተብሎ የቀረበውን ክስ በሚመለከት፣ ንግድ ፍቃድ መውጣቱንና መታደሱን እንጂ ሰለሞን ሙሉ ከውን በተባለው ሰው ወይም በተወካይ ንግድ ቢሮ ቀርቦ ንግድ ፍቃዱን ማን አወጣ ማን አሳደሰ ለሚለው አሳማኝ ማረጋገጫ ያልቀረበ መሆኑን አብራርቷል። በተጨማሪም ከምስክሮች ቃል አሰጣጥ አንጻር በሰነዶች ማረጋጋጫ ተቋም አንድ ሰው በአካል ሳይቀርብ የጣት አሻራ ሳይሰጥና ሳይፈርም ውክልና እንደማይሰጥ መረዳቱን በመጥቀስ ሰለሞን ሙሉ ከውን በሚባል ሰው አሻራ ሰጥቶ ፈርሞ፣ በአካል ቀርቦ ውክልና የሰጠና ንግድ ፍቃድም ያወጣና ያሳደሰ መሆኑን ግምት መያዙን በማብራራት ከ1ኛ እና ከ2ኛ ክስ ነጻ ብሎታል። ፍርድ ቤቱ 3ኛ እና 4ኛ ክስን በሚመለከት በ2010 እና በ2011 ዓ.ም ከውጭ ሀገር እቃ ሳያስገባና ምንም አይነት ሽያጭ ሳያከናውን ሀሰተኛ የተጭበረበሩ ሰነዶችን የአመታዊ የግብር ሪፖርትን ለግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ማስገባቱ መረጋገጡን በመጥቀስ 3ኛ ክስ ከ4ኛ ክስ ጋር ተጠቃሎ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል። በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ለ339 ግብር ከፋዮች 1 ሺህ 663 የገቢ ደረሰኞችን አትሞ በማሰራጨት የንግድ ትርፍ ፣ እና የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በ15 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ 25 ቢሊየን 989 ሚሊየን 943 ሺህ 223 ብር ከ83 ሳንቲም ጉዳት መድረሱን በማስረጃ መረጋገጡን ገልጾ 5ኛ ክስንም ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል። 6ኛ ክስን ደግሞ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በተከራየው ሱቅ ውስጥ ህገወጥ እውቅና የሌለው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያና ኮምፒውተሮች በገቢዎች ሰራተኞች ተገኝቷል ተብሎ የቀረበውን ክስ በሚመለከት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያው ከጁፒተር ንግድ ስራዎች ድርጅት የተገዛና የተገጠመ መሆኑን መረጋገጡን ችሎቱ ጠቅሶ እውቅና የሌለው ህገወጥ መሳሪያ ተገኝቷል በሚል በቀረበው ክስ ላይ ማስረጃ አለመቅረቡን ገልጾ ተከሳሹን ነጻ ነው ብሎታል። 7ኛ ክስን በሚመለከት የታክስ አስተዳደር አዋጅን በመተላለፍ ግብይት ሳይኖር ህገወጥ ደረሰኝ መጠቀም የሚለው ክስ ከ5ኛ ክስ ዝርዝር ጋር የሀሳብ መደራረብ ያለው መሆኑን ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ በዚሁ 7ኛ ክስን በሚመለከት ነጻ በማለት ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል። ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረበውን የመከላከያ ማስረጃ መርምሮና ከዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ጋር አመዛዝኖ ዛሬ በዋለው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል። በዚህም ፍርድ ቤቱ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ማረጋገጡን ተጠቅሶ ጥፋተኛ መባሉን ኤፍቢሲ ዘግቧል። የግራና ቀኝ ቅጣት አስተያየት መርምሮ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጥ ቀጠሮ ሰጥቷል። ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ! #NCRS ሞባይል መተግበሪያ #ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች https://play.google.com/store/apps/details #ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ። የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገ-¬መንግስትና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ታዲዮስ ታንቱን በተከሰሱበትና ጥፋተኝነት በተባሉባቸው 3 ክሶች ነው የጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት የጣለባቸው። አቶ ታዲዮስ ታንቱ በሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል። ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አንደኛው ክስ ላይ እንዳመላክተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/(1)ሀ እና አንቀጽ 257/ሀ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በግንቦት 11 ቀን እና በመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም እና በተለያዩ የዩቲዩብ ቻናሎች ህዝባዊ አመጽ መቀስቀስ ወንጀል የሚል ነው። በ2ኛ ክስ በተመለከተ ደግሞ የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7/4 በመተላለፍ በታሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የዩቱዩብ ቻናል ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦባቸው ነበር። በ3ኛ ክስ ደግሞ የወንጀል ህግ ከንቀጽ 32 /1ሀ ና አንቀጽ 337 በመተላለፍ የመከላከያ ሰራዊትን እቅስቃሴን ለማሰናከልና የመከላከል አደጋ እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ ሀሰተኛ ወሬ በመንዛት ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን በ4ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁ 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ህዝባዊ አመጽ እንዲፈጠር ቀስቃሽ መልዕክት በድምጽና በተቀሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል። በአጠቃላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው አራት ክሶች ላይ የተጠቀሱትን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ገልጸው፤ የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዳሉ ያላቸውን ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል። ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ምስክርን መርምሮ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን መስጠቱ ይታወሳል። አቶ ታዲዮስ እንዲከላከሉ በተሰጠ ብይን መነሻ የተለያዩ የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው አሰምተው የነበሩ ቢሆንም ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ግን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል (ማስተባበል) አለመቻላቸው ተገልጾ በ3 ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን ለመጠባበቅ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም አቶ ታዲዮስ በዚህ እለት የቅጣት ማቅለያ ማቅረብ እንደማይፈልጉና የጥፋተኝነት ፍርዱን እንደማይቀበሉ ለችሎቱ አስታውቀው ነበር። ይሁንና ፍርድ ቤቱ ግን የ6 ልጆች አባት መሆናቸውንና የ70 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ሁለት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 24 መሰረት በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል። የአ/አ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ ላይ የተጣለውን ቅጣት እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ እንዲያስፈጽም ታዟል። በታሪክ አዱኛ
без подписи
ቸርቹ ና ጠጅ ቤቱ ፊት ለፊት ናቸው። ጠጪዎች እየተሳለቁ እየተሳሳቁ ይጠጣሉ: ገበያ ለጉድ ነው። ቸርቹም የዋዛ አይደለም: የመጠጥ ሀጢዓትነት ቢያንስ አንዴ ይሰበካል: ስም ሳይጠቀስ ‘ወጋሁ ይባላል’ ቀስ በቀስ ነገሩ እየተጋጋለ ወደ next level ተሸጋገረ። የ ቸርቹ ፓስተር ‘ጠጅ ቤቱ ብን ብሎ እንዲጠፋ: እንዲከስም በገሀድ መፀለይ ጀመረ። ይባስ ብሎ ትንቢት ተናገረ: እና ትንቢቱ ደረሰና ጠጅ ቤቱ በእሳት ጋየ ወደመ። የጠጅ ቤቱ ባለቤት የዋዛ አይደለም: ብቀጥንም ጠጅ ነኝ አለና በህግ አምላክ’ ብሎ ተነሳ። ቸርቹንና ፓስተሩን ከውል ውጭ ሀላፊነት በአንድነት ና በነጠላ ተጠያቂ ናቸው ሲል ፍርድ ቤት ገተራቸው። ቸርቹ ና ፓስተሩ መቃወሚያ ና በፍሬ ነገሩ መልስ ሰጡ። “ፀሎት ሆነ ትንቢት የእሳቱ መንስዔ ስለመሆኑ ማስረጃ የለም። እኔ ስለፀለይኩና ትንቢት ስለተናገርኩ ጠጅ ቤቱ በእሳት አይወድምም። እንደዚህ ዓይነት ሀይል ና ስልጣንም የለኝም” የጠጅ ቤቱ ባለቤት ግን “ጠጅ ቤቱ በእሳት የወደመው በተከሳሽ ፀሎት የተነሳ ነው። ባይፀልይ ና ትንቢት ባይናገር ኖሮ ስንት ጥሬ ግሬ ያፈራሁት ጥሪት አይወድምም ነበር” ሲል ወጥሮ ተከራከረ። የችሎቱ ዳኛ የግራ ቀኙን ክርክር ና ማስረጃ መርምረው ብይን ሰጡ። ብይን በፀሎት ና ትንቢት በሚያምን የጠጅ ቤት ባለቤት እና በፀሎት ና ትንቢት በማያምን ፓስተር መካከል የሚደረግ ክርክር መፍታት ከፍርድ ቤቱ አቅም በላይ ነው። መዝገቡ ተዘግቷል: ወጪ ና ኪሳራ ይቻቻሉ።