tgindex
አብርሆት

አብርሆት

Статистика

የአዳዲስና ወቅታዊ የመረጃ ምንጭ

Последний пост
6 нояб. 2021 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
76
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
279
20 постов
Вовлечённость
367,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 1 month. If it remains inactive in the next 8 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

  • 4 окт. 2021 г.1 1301из Fikreprinting

    መቼ ቢዝነስ ልጀምር❔ ቢዝነሳችንን የምንጀምርበትን ጊዜ እንዴት እንምረጥ? (ወደ ስራ) ብዙ ሰው ቢዝነስን የእድል ያደርገዋል፡፡ “የቢዝነስ ውሳኔዬን ስወስን ጊዜው ጥሩ ይሁን አይሁን እርግጠኛ ሆኜ ማወቅ ስለማልችል በቃ ዝም ብዬ እገባበታለሁ ውጤቱን አብረን እናያለን” የሚል ብዙ ሰው አለ፡፡ በርግጥ ስለ ጊዜ ስናስብ እርግጠኛ ሆነን መቶ በመቶ ይሄ ነው የሚሆነው ማለት ይከብዳል፡፡ ነገር ግን ስንወስን አንዳንድ ነገሮችን ከግምት ውስጥ ብናስገባ ቢዝነሳችንን በተሻለ ሁኔታ ስኬታማ ማድረግ እንችላለን፡፡ 1. ገበያው ወዴት እየሄደ ነው የሚለውን ማጥናት እና ወደ ገበያው አቅጣጫ ለመሄድ ወይም ያንን ለመከተል መሞከር ይመከራል፡፡ ቀድሞ ለመገኘት ማለት ነው፡፡ የእጅ ሰአት እና ሞባይል ስልኮችን ለምሳሌ እንይ፡፡ አሁን ሰአት ማወቅ ስንፈልግ በአብዛኛው ሞባይላችንን ነው የምናየው፡፡ በዚህ ምክንያት የድሮ ሰአቶች ሽያጫቸው ቀንሷል፡፡ በዚህ ምክንያት ደግሞ ስማርት (የተማሩ) የእጅ ሰአቶችን ማምረት ተጀመረ፡፡ እነዚህ ሰአቶች ሰአትን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን፤ ሬዲዮ ልንሰማባቸው እንችላለን፤ ከስልካችን ጋር አገናኝተን አቅጣቻዎች ሊጠቁሙን ይችላሉ፤ ስፖርት በምንሰራበት ጊዜ የአካል ብቃታችንን (ልብ ምታችንን እና የመሳሰሉትን) ይለካሉ፡፡ በተጨማሪ አገልግሎታቸው ምክንያት አዲሶቹ ሰአቶች ተመራጭ ሆነዋል፡፡ ስለዚህ በጣም የተለየ አይነት ካልሆነ በስተቀር ባህላዊውን ሰአት ከማምረት ስማርት ሰአት ማምረት የተሻለ ገበያ ያስገኛል፡፡ 2. ገበያ የምናቀርበው እቃ ሊሆን ይችላል፤ አገልግሎት ሊሆን ይችላል፡፡ አምራች፤ አከፋፋይ፤ ቸርቻሪ፤ አገልግሎት ሰጪ ልንሆን እንችላለን፡፡ መጀመሪያ ማድረግ ያለብን ቁጭ ብለን ብናቅድ ይመረጣል፡፡ አንድ አባባል አለ፡፡ ቢዝነስ ላይ ከማህፀን እስከ መቃብር ነው ማሰብ ያለብን ይባላል፡፡ • ስለዚህ በተቻለ መጠን ምን ሊበላሽ ይችላል? ምን ሊፈጠር ይችላል? የቱ ጋር ችግር ሊነሳ ይችላል? ብለን ማሰብ እና የእርምት እርጃዎችን መውሰድ ጥሩ ነው፡፡ 3. ሌላው ነገር ቢዝነስ ላይ የቆዩ ፤ ከኛ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች እቅዶቻችንን ማማከር ጥሩ ነው፡፡ ይሄ ለማድረግ ታማኝ ሰው ቢኖረን ይመረጣል፡፡ እኛ ካየንበት መንገድ በተለየ መንገድ አይተው የተሻለ አስተያየት ሊሰጡን የሚችሉ ሰዎችን ማማከር፡፡ 4. ሌላ አስፈላጊ ነገር መረጃ መሰብሰብ ነው፡፡ ገበያን ወይም ቢዝነስ ላይ ለውጥ የሚያመጡ ብዙ ነገሮች አሉ የቴክኖሎጂ ለውጦች፤ መንግስት የሚያወጣቸው አዳዲስ ህጎች እና ፖሊሲዎች፤አለም ላይ ያለው ሁኔታ እና የመሳሰሉት፡፡ መረጃዎችን በትክክል ከሰበሰብን ውሳኔዎችን ለመወሰን ብዙም አንቸገርም፡፡ ዜናዎችን መከታተል፤ መፅሃፍትን ማንበብ፤ ላለንበት ኢንደስትሪ የሚጠቅሙ ዌብሳይቶችን እና ብሎጎችን መጎብኘት፤ ኢንደስትሪ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር መወያየት እና መሰል ነገሮች ማድረግ መረጃ እንድናገኝ ይረዱናል፡፡ @goferebusiness

  • 4 окт. 2021 г.740из Fikreprinting

    #የድረገጽ_ጥቆማ በነፃ የቢዝነስ ኮርሶችን መውሰድ ትፈልጋላችሁ❔ አዎ ከሆነ መልሳችሁ፤ እንደሚከተለው ይቀርባል... 🌐 ዛሬ የምናስተዋውቃችሁ ድረገጽ፤ በነፃ የቢዝነስ ኮርሶች የምታገኙበትን ነው፡፡ አለም አቀፍ የንግድ ሴንተር (International Trade Centre)፤ በንግድ ስራ ዙሪያ የተለያዩ ኮርሶችን በኢንተርኔት በነፃ ይሰጣል፡፡ ድርጅቱ አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶችን ለመደገፍ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ ኮርሶችም የሚያተኩሩት:- - በኤክስፖርት ቢዝነስ ላይ - በስራ ፈጠራ (ኢንተርፕረነርሺፕ) ላይ - ዲጂታል ማርኬቲንግ እና የመሳሰሉት ከንግድ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ 🌐 ኮርሶቹ በአብዛኛው ከሁለት እሰከ አራት ሳምንት (በሳምንት 2 ሰአታት) የሚወስዱ ናቸው። 🌐 ለመመዝገብም የሚያስፈልግን የራሳችን የኢ-ሜል አድራሻ ሲሆን ትምህርቱም ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት የሚሰጥ ነው፡፡ 🌐 በዚህ ድረገጽ ላይ የሚገኙ ኮርሶች አብዛኛዎቹ ለንግድ ስራ የሚሆኑ ስለሆነ የራሳችንን ቢዝነስ ለመክፈት የምንፈልግ ከሆነ፣ የቢዝነስ ድርጅቶች ውስጥ የምንሰራ ወይም የቢዝነስ ትምህርት የምንማር ከሆነ በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡ 🌐 ድረገጽ ላይ የሚሰጡትን ኮርሶች ለመውሰድ የሚያስፈልገን ነገሮች:- 1. ድረገጹ ላይ ለመመዝገብ የራሳችን የኢሜል አድራሻ ማዘጋጀት እና 2. ከተመዘገብን በኋላ የምንፈልገውን ኮርስ ከድረገጹ ላይ መርጠን፤ መመዝገብ እና መማር፡፡ 🌐 ኮርሶቹን በራሳችን ፍጥነት እዛው ኢንተርኔት ላይ ማንበብ እና መማር እንችላለን፡፡ ኮርሱን ከጨረስን በኋላ መማራችንን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከድረገጹ ላይ ማውረድ እንችላለን። ከታች ሊንኩን በመንካት ድረገጹን ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡ https://learning.intracen.org ምንጭ:- Wede Sera ወደ ስራ @goferebusiness

  • 4 окт. 2021 г.503из Fikreprinting

    አክሲዮን እና አክሲዮን ማኅበር❗️ (ከትላንቱ የቀጠለ) የአላባ ጥቅም ተቀባዮች በአላባ የተቀበለውን አክሲዮን በእጅ የማስገባት እና የሚስገኘውን ፍሬ ማለትም ትርፍ የመቀበል እና የመጠቀም መብት ( የፍትሐብሄር ህግ አንቀፅ 1311) በጠቅላላ ጉባኤው ድምፅ የመስጠት መብት (የንግድ ህግ አንቀፅ 329 (1) ) አክሲዮኑ የሚያስገኘው ሌላ ጥቅም ቢኖር ለምሳሌ በአክሲዮን ማህበር የተቋቋመ ሆስፒታል ቢሆን እና ባለአክሲዮኖች በቅናሽ ወይም በነፃ የሚታከሙ ቢሆን ይህ መብት ለአላባ ተቀባይ ይተላለፋል የአላባ መብት ጊዜ ሲያልቅ የከፈለው ገንዘብ እንዲመለስለት ያለው መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ለአክሲዮኑ የተጠየቀውን ቀሪ ገንዘብ የመክፈል ግዴታ አለበት( የንግድ ሕግ አንቀፅ 329(4) ሐ. አክሲዮንን በመያዣ የመስጠት መብት አንድ ባለአክሲዮን አክሲዮን በመያዣነት በመስጠት ገንዘብ መበደር ወይም ለሌላ ግዴታ አፈፃፀም እንደዋስትና ማስያዝ እንዲሚችል ከንግድ ህጋችን አንቀጽ 329 እና ከፍትሐብሄር ህጋችን ከአንቀጽ 2863 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መረዳት እንችላልለን፡፡ አክሲዮንን በመያዣነት የተቀበለ ሰው የሚከተሉት መብቶች አሉት ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር በጉባኤዎች ድምፅ የመስጠት መብት (አንቀፅ 329(1)) ከአክሲዮኑ የሚገኘውን ትርፍ የመቀብል መብት ያለው ሆኖ ባለመያዣው ከአክሲዮኑ የሚገኘውን ትርፍ የሚወስደው እንዲያው በነፃ ሳይሆን ደረጃ በደረጃ ከባለአክሲዮኑ የሚጠይቀውን እዳ ለማወራረድ ነው ይህንንም ሲያደርግ መጀመሪያ የዕዳውን ወጪ፣ ቀጥሎ ወለዱን እና በመጨረሻም ዋና እዳውን ያወራርድበታል፡፡(የፍትሐብሄር ህግ አንቀፅ 2868(1-2) ይመለከቷል) ማጠቃለያ! አክሲዮን ማኅበራት በሀገራችን ኢንቨስትመንትን እና ሰፊ የስራ እድል ከመፍጠራቸው በተጨማሪ ዜጎች እንደ አቅማቸው የተለያየ መደብ ያለቸውን አክሲዮኖች በመግዛት፤ ማኅበሩ በዓመት ከሚያስገኘው ትርፍ በመቀበል የተለያየ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ያስችላቸዋል። © Fresenbet Adhanom @goferebusiness

  • 4 окт. 2021 г.389из Fikreprinting

    አክሲዮን እና አክሲዮን ማኅበር❗️ (ከትላንቱ የቀጠለ) የአክሲዮን አይነቶች በንግድ ህጋችን አንቀፅ 328 (1) እና 715 መሰረት አክሲዮን የማይከፋፈል እና ግዑዝነት የሌለው የሚተላለፍ ሰነድ ነው። አክሲዮኖች ከአንድ ባለቤት ወደ ሌላ ከሚተላለፉበት መንገድ በመነሳት፤ ለአምጪው የሆነ አክሲዮን (To Bearer) እና በባለቤቱ ስም የተመዘገበ አክሲዮን በማለት በሁለት ዓይነት መልክ እንደሚከፈሉ ከንግድ ህጋችን አንቀጽ 325 መረዳት እንችላለን። ላምጪው የሆነ አክሲዮን ላምጪው የሆነ አክሲዮን፤ የባለቤቱን ስም በአክሲዮኑ የምስክር ወረቀት ላይ የሚይዙ ሲሆን ባለቤት ሆኖ የሚገመተው ደግሞ በማንኛውም ጊዜ አክሲዮኑን በእጁ ይዞ የተገኘው መሆኑን እና ይህንኑ በማቅረብ ትርፍ መቀበል፣ መልሶ ገንዘብ መክፈል እና ለጠቅላላው ጉባኤ አባል መሆን የሚያስችሉ መሆኑን ከንግድ ህጋችን አንቀጽ 340 እና 721(1) መሰረት መረዳት ይቻላል። እዚህ ላይ ትኩረት ሊደረግ የሚገባው ምንም እንኳ ላምጪው የሆነ አክሲዮን ላይ የባለቤቱ ስም ባይገለፅም፤ በመጀመሪያ ፈርሞ የወሰደው ባለ አክሲዮን ስም በባለ አክሲዮኖች መዝገብ ውስጥ ስሙ መስፈር እንዳለበት የንግድ ህጉ አንቀጽ 331 ያስገድዳል። በባለቤቱ ስም የተመዘገበ አክሲዮን የንግድ ህጋችን አንቀጽ 722 እና 331 አጣምረን ስናነብ በባለቤቱ ስም የተመዘገበ አክሲዮን፤ በእጁ የያዘ ሰው በአክሲዮኑ ላይ ለተነገረው ግዴታ መብት ተጠቃሚ ለመሆን በአክሲዮኑ ላይና በአውጪው መዝገብ ወይም አክሲዮን ማህበሩ በሚያዘጋጀው መዝገብ ውስጥ ስሙ መፃፍ ይኖርበታል። ከላይ የጠቀስናቸው የአክሲዮን አይነቶች መሠረት ያደረጉት ከአንድ ባለቤት ወደ ሌላ ከሚተላለፉበት መንገድ በመነሳት ሲሆን አሁን ደግሞ ማህበሩ በመመሥረቻ ጽሑፉ ወይም ይህንኑ የሚለውጠው የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ልዩ ልዩ መብቶችና ጥቅሞች የሚያስገኙ የአክሲዮን አይነቶች ማውጣት እንደሚቻል ከንግድ ህጉ አንቀፅ 335፣ 336፣ 337 እና 345 መረዳት እንችላለን። በዚህም መሠረት አክሲዮኖቹን መደበኛ አክሲዮን (Ordinary Share)፣ ቅድሚያ መብት የሚያስገኙ አክሲዮን (Preference Share) እና ትርፍ ብቻ የሚያስገኙ አክሲዮኖች (Dividend Share) በማለት መክፈል ይቻላል። መደበኛ አክሲዮን በንግድ ህጋችን አንቀጽ 345፣ 406 እና 417 መሠረት መደበኛ ወይም ተራ አክሲዮን የገዛ ሰው በአመቱ መጨረሻ ከተጣራ ትርፍ የመካፈል፣ ማህበሩ ሲፈርስ ዕዳው ተከፍሎ ከሚቀረው ገንዘብ የመካፈል፣ በጠቅላላ ጉባኤ ድምጽ የመስጠት፣ በያዙት የአክሲዮን ቁጥር አዳዲስ አክሲዮኖች ሲወጡ ለመግዛት የቀደምትነት መብት እና የማህበሩን የትርፍና ኪሳራ የሂሳብ ሰነዶች እና አስተዳዳሪዎቹንና ተቆጣጣሪዎቹ ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀረቡዋቸውን ሪፖርቶችን የማዎቅ ወይም ቅጂዎችን የመውሰድ መብት ያስገኛሉ። የቅድሚያ መብት የሚያስገኙ አክሲዮን በንግድ ህጋችን አንቀጽ 336 መሠረት የቅድሚያ መብት የሚያስገኝ አክሲዮን የሚያስገኛቸው የቅድሚያ መብቶች የሚከተሉት ናቸው። እነሱም የተለየ ጥቅም ያላቸው ወደፊት የሚወጡ አክሲዮኖችን በቀደምትነት የመግዛት፣ ትርፍ የማግኘት፣ እና ማህበሩ ሲፈርስ ከሚጣራው ሃብ ላይ ቅድሚያ የመከፈል መብትን የሚያስገኝ ሲሆን በድምጽ መስጠት ጉዳይ ላይ ልዮ መብት ወይም ቅድሚያ የሚያሰጡ አክሲዮኖችን ማውጣት የተከለከለ ሲሆን ማህበሩ እነዚህን አክሲዮኖች ለህዝብ የሚሸጥበት ዋና አላማ ብዙ ገንዘብ ለሚያዋጡ ወይም ብዙ አክሲዮን ለሚገዙ አባላት ልዮ መብት በመስጠት የተሻለ ካፒታል ለመሰብሰብ ነው። ሆኖም ግን የቅድሚያ መብት ሲባል ገደብ ያለው መሆኑን ሊጤን ይገባል። ይህም ማለት ከትርፍ የቅድሚያ መብት ሲባል ከሚገኘው የተጣራ ትርፍ ላይ ምን ያህል ገንዘብ ወይም በመቶኛ ምን ያህል የሚለው በመመስረቻ ጽሁፉ ወይም በጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ ላይ በግልፅ መገለፅ አለበት። ትርፍ ብቻ የሚያስገኝ አክሲዮን ይህ አይነቱ አክሲዮን በንግድ ህጋችን በአንቀጽ 337 ላይ የተደነገገ ሲሆን አክሲዮኖቹ ከተገዙ በኋላ ባሉት አመታት ኩባንው ዋጡትን ገንዘብ የመለሰላቸው ባለአክሲዮኖች የሚይዙት አይነት አክሲዮን ነው። እንዲህ አይነነት አክሲዮን ያላቸው አባላት በአመቱ ከሚገኘው ትርፍ የመካፈል መብት ያላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ማህበሩ ሲፈርስ ካፒታል ከተመለሰ በኋላ ከሚጣራው ሃብት ላይ የመካፈል መብት ያገኛሉ። ሆኖም ግን በመተዳደሪያ ደንቡ የተወሰነውን የአክሲዮን ወለድ እንዲሁም ማህበሩ ሲፈርስ ገቢ ያደረጉትን መዋጮ ለመውሰድ የላቸውም። አሁን ደግሞ በአንድ አክሲዮን ማህበር ውስጥ አክሲዮን የገዛ ሰው አክሲዮኖቹ ምን መብት ያስገኙለታል የሚለውን እናያለን። ከላይ የአክሲዮን አይነቶቸን ከሚያስገኙት ልዩ ልዮ ጥቅሞች ወይም መብቶች በመነሳት በመደብ በንግድ ህጉ የተከፋፈሉ ሲሆን እነዚህን አክሲዮኖች የገዛ ሰው በአመቱ መጨረሻ ከተጣራ ትርፍ የመካፈል፣ ማህበሩ ሲፈርስ ዕዳው ተከፍሎ ከሚቀረው ገንዘብ የመካፈል፣ በጠቅላላ ጉባእ ድምፅ የመስጠት፣ በያዙት የአክሲዮን ቁጥር አዳዲስ አክሲዮኖች ሲወጡ ለመግዛት የቀደምትነት መብት እና የማህበሩን ሰነዶች ለማወቅ የመቻል ወ.ዘ.ተረፈ መብት እንዳለው ያየን ሲሆን አክሲዮኖቹን በማዘዋወር ረገድ ባለአክሲዮኑ አክሲዮኑን የማስተላፍ ወይም የመሸጥ፣ በመያዣ የመስጠት እና በአላባ ጥቅም ለሌላ ሰው የመስጠት መብቶች አሉት ( 329 እና 333 ይመለከቷል) እነዚህንም በቅደም ተከተል እናያለን። ሀ. አክሲዮኑን በሽያጭ የማስተላለፍ መብት የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነው የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 40 (1) መሠረት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት የመሆን መብት እና የሌሎችን ዜጎች መብት እስካልተቃረነ ድረስ ንብረቱን የመያዝ፣ የመጠቀም እና የመሸጥ እንዲሁም የማውረስ ወይም በሌላ መንገድ የማስተላለፍ መብት እንዳለው ይደነግጋል። አክሲዮን የማይከፋፈል እና ግዑዝነት የሌለው ንብረት በመሆኑ ባለአክሲዮኖች መብታቸው በዚህ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ውስጥ ጥበቃ የተሰጠው እና አክሲዮናቸውን ለሌላ ሰው በሽያጭ ማስተላለፍ የሚችሉ ቢሆንም ግን ይህ የማስተላለፍ መብት በንግድ ህጉ አንቀጽ 333(1) መሰረት በመተዳደሪያ ደንብ ወይም በድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ የሌሎችን ባለአክሲዮኖች ወይም የኩባንያውን መብት ለማስጠበቅ ሲባል ሊገደብ ይችላል። ለ. አክሲዮንን በአላባ ጥቅም የማስተላለፍ መብት ሌላው አክሲዮን ንብረት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ነጥብ ባለአክሲዮኑ በአክሲዮኑ ላይ ካለው ሙሉ ባለቤትነት በመለስ የአላባ ጥቅሙን ማስተላለፍ እንደሚችል በንግድ ህጉ በአንቀጽ 329 ላይ ተገልጻል። የአላባ መብት ምንነት እና አመሰራረትን እንዲሁም በአላባ ሰጪና ተቀባይ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገዙት መሰረታዊ መርሆች ያሉት በፍትሐብሄር ሕግ ከአንቀጽ 1309 - 1358 ባሉት ድንጋጌ ውስጥ ነው። የአላባ መብት ማለት የሚጠቀሙበትን ነገር ከመጠበቅ ግዴታ ጋር ከዚሁ ነገር ላይ በሚገኙት ፍሬዎች ወይም መብቶች ለመጠቀምና ለመገልገል የሚያስችል መብት ነው (የፍትሐብሄር ህግ አንቀፅ 1309 (1) ይመለከቷል)። እንግዲህ አክሲዮን በአላባ ጥቅም መተላለፍ እንደሚቻል ካየን አክሲዮኑ ለሌላ ሰው የተላለፈ እንደሆነ የባለአክሲዮኑና የአላባ መብት ተቀባዩ መብቶች ምን ምን እንደሆኑ ቀጥለን እናያልን። ክፍል 4 ነገ ምሽት 3:30 ላይ ይቀርባል። ጠብቁን! © Fresenbet Adhanom @goferebusiness

  • 4 окт. 2021 г.274из Fikreprinting

    አክሲዮን እና አክሲዮን ማኅበር❗️ (ከትላንቱ የቀጠለ) ⚖ የህግ ሰውነት በንግድ ህጋችን ውስጥ ከአሽሙር ሽርክና ማኅበር በሥተቀር፤ የንግድ ማህበራት የህግ ሰውነት እንደሚኖራቸው በአንቀጽ 210 (2) በግልፅ ተደንግጓል። የህግ ሰውነት ዋና ዓላማ፤ አንድ ግዑዝነት የሌለው ተቋም ከአባላቱ በተለየ የራሱ ህልውና (ሕይወት) እንዳለው በመቁጠር የራሱ መብት፣ ንብረት፣ ግዴታ...ወዘተ ባለቤት በማድረግ ብዙ ሰዎች አባላት የሆኑበት ማህበር በአንድ ስያሜና በአንድ ውክልና እንዲሠራ ማስቻል ነው። ስለ ህግ ሰውነት ዓላማ ይሄን ያክል ካልን አንድ አክሲዮን ማኅበር መቼ እና የት የህግ ሰውነት እንደሚያገኝ ቀጥለን እናያለን። አንድ አክሲዮን ማኅበር እንደ ማንኛውም ድርጅት ጥንስሱ የሚጀምረው በአንድ ሰው አዕምሮ ነው። ይህ ሰው ሃሳቡን ለሌሎቹ አካፍሎ የሚተባበሩትን ካገኘ በኋላ፤ ለአክሲዮን ማኅበሩ አስፈላጊ የሆኑ የህግ ቅድመ ሁኔታዎች ለማሟላት አብረው ይሰራሉ። ከቅድመ ሁኔታዎቹ ውስጥ የካፒታሉን መጠን ስንት መሆን እንዳለበት፣ የአንድ አክሲዮን አቻ ዋጋ እና ካፒታሉ በስንት አክሲዮን እንደሚከፋፈል ይወስናሉ። ይህ ከተደረገ በኋላ በአባላቱ መካከል አክስዮኖቹ ይከፋፈላሉ። በመስራች አባለቱ ከተወሰነው ካፒታል ላይ ቢያንስ እሩቡ ወይም 25% ከተከፈለ፣ በዝግ ሂሳብ ከተቀመጠ ለማኅበሩ ምስረታ በቂ እንደሆነ እና ምዝገባውም በአንድ ዓመት ውስጥ ካልተፈፀመ በዝግ ሂሳቡ ውስጥ የተቀመጠው ገንዘብ ለአዋጡት ተመላሽ እንደሚደረግ በአንቀፅ 312 በግልፅ ተደንግጓል። አክሲዮን ማኅበሩ እነዚህን ቅደመ ሁኔታዎች ካሟላ የት ነው የሚመዘገበው የሚለውን ጥያቄ ደግሞ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀፅ 9 እና 5 (2) መልስ ይሰጠናል። ይህም አክሲዮን ማኅበሩ ከተመሰረተ በኋላ በንግድ ሚኒስቴር በሚተዳደር ሀገር ዓቀፍ የንግድ መዝገብ ውስጥ መመዝገብ እንዳለበት ይገልፃል። በንግድ መዝገብ ውስጥ ከመመዝገብ በተጨማሪ ማኅበሩ የህግ ሰውነት ለማግኘት ሌላኛው አስፈላጊ ጉዳይ የመተዳደሪያ ደንቡ እና መመሥረቻ ጽሑፉ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ካልተረጋገጡና ካልተመዘገቡ ህጋዊ ውጤት እንደማይኖራቸው የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሐ) ይደነግጋል። ይህ ማረጋገጥ እና ምዝገባ ግን በንግድ ሚኒስቴር ከሚደረገው ምዝገባ በዓላማም በይዘትም የተለየ ነው። የንግድ ሚኒስቴር ምዝገባ ዓላማ ለመንግስት ቁጥጥርና ለሦስተኛ ወገኖች መረጃን አደራጅቶ ማስቀመጥ ነው። ሦስተኛ ወገኖች ሲባል ከንግድ ድርጅቱ ጋር የንግድ ሥራን የሚሰሩ ተገበያዮች፣ አክሲዮን ገዢዎች እና ተመራማሪዎች ድርጅቱ በትክክል የተቋቋመ፣ በቂ ካፒታል ያለው መሆኑን፣ የሃብት መጠኑ (Net Worth)፣ ታሪኩን የቀድሞ የውጤታማነት ደረጃውን፣ የወደፊት ተስፋውን፣ እዳዎቹን ወ.ዘ.ተረፈ የሚያሳይ መዝገብ ነው። በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት በኩል የአክሲዮን ማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንቡ የማረጋገጡና የማስመዝገቡ ዓላማ ደግሞ የሰነዶቹ ይዘት ህግን እና መልካም ጠባይን የማይቃረኑ መሆንን ማረጋገጥ ሲሆን ይህ መዝገብ ለሦስተኛ ወገኖች ክፍት እንደማይደረግ በአዋጅ ቁጥር 334/1995 በእንቀፅ 9(2) ላይ ተደንግጓል። በአጠቃላይ አንድ አክሲዮን ማኅበር የህግ ሰውነት የሚያገኘው በንግድ ሚኒስቴር በሚተዳደር አገር ዓቀፍ የንግድ መዝገብ ውስጥ ከተመዘገበ እና መተዳደሪያ ደንቡና መመስረቻ ጽሑፉ በሰነዶች ማረጋጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ህግን እና መልካም ጠባይን የማይቃረኑ መሆኑ ተረጋግጦ ከተመዘገበ ቡኋላ ነው። 📌 የአክሲዮን ማህበራት አቋቋም በንግድ ህጋችን አንቀጽ 316 እና 317 መሠረት አንድን የአክሲዮን ማኅበር በሁለት አይነት መንገድ ማቋቋም እንደሚቻል መረዳት ይቻላል። እነዚህም፡- *⃣ በመሥራቾች መካከል የሚደረግ መቋቋም የአክሲዮን ማኅበር ለህዝብ አክሲዮን ሳይሸጥ ከአምስት በማያንሱ መስራቾች መካከል ሲቋቋም በአደራጆች መካከል ተቋቋመ ይባላል። በንግድ ህጋችን አንቀጽ 316 መሰረት አንድ አክሲዮን ማኅበር በአደራጆች ወይም በመስራቾች መካከል ለማቋቋም አራት መሠረታዊ ነገሮችን አደራጆች በመመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ ማሳየት ይጠበቅባችኋል፦ 1. ሁሉም አክሲዮኖች የተያዙ መሆናቸውን! 2. በአንቀጽ 312 (1) (ለ) መሠረት የካፒታሉ አንድ አራተኛ ተከፍሎ በዝግ ሂሳብ በባንክ መቀመጡን! 3. በአይነት የተደረገ መዋጮ በባለ አክሲዮኖች ተገምቶ፤ ግምቱ መገለጽ አለበት (አዋጅ ቁጥር 376/2003 አንቀፅ 5 (11) ይመለከቷል)። 4. የተለያዮ የኩባንያው አስተዳደር አካላት፤ ለምሳሌ የማኅበሩ የቦርድ አባላት፣ ኦዲተሮች እና ሥራ አስኪያጅ መሾሙን መገለፅ አለበት። *⃣ አክሲዮን ለህዝብ በመሸጥ የሚቋቋም! በንግድ ህጋችን አንቀጽ 317 መሠረት የንግድ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በመሀከላቸው ማህበሩን ማቋቋም ካልቻሉ ለህዝብ አክሲዮን በመሸጥ ማህበሩን ማቋቋም እንደሚችሉ መረዳት ይችላል። የንግድ ሀሳቡ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቅ ከሆነ ገንዘቡን ትንሽ ሠዎችን በማሣመን መሠብሠብ ስለሚያሥቸግር፤ ለሕዝብ አክሲዮን በመሸጥ አክሲዮን ማህበሩን ማቋቋም ይችላሉ። አደራጆቹ ለህዝብ አክሲዮን በመሸጥ አክሲዮን ማኅበር ሲያቋቁሙ ሊከተሏቸው ወይም መፈፀም ያለባቸውን የድርጊት ቅደም ተከተሎች አሉ (አንቀጽ 318፣ 319 እና 321 ይመለከቷል)። እነዚህም፦ የአክሲዮን ሽያጭ መግለጫ ማውጣት (Prospectus)! የማኅበሩ አደራጆች አክሲዮን የሚገዛው ሕዝብ ስለሚቋቋመው አክሲዮን ማኅበር እና ሥለ አክሲዮኖቹ ትክክለኛ ዋጋ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚያስችል የአክሲዮን ሽያጭ መግለጫ ማውጣት እንዳለባቸው በንግድ ህጉ አንቀጽ 318 ተመልክቷል። ይህን መግለጫ አዘጋጅቶ ለህዝብ መግለፅ እያንዳንዱ አክሲዮን ገዢ ከመግዛቱ በፊት እንዲያነበው መደረጉ ሕዝብን ከስህተት ይጠብቃል ተብሎ ይገመታል። የህዝቡ አክሲዮን መፈረም! የአክሲዮን ሽያጭ መግለጫ ለህዝብ ይፋ ተደርጎ ካበቃ በኋላ፤ አክሲዮኖቹን ለመግዛት የፈለገ ሰው በመግለጫው በተገለፀው ቦታ እና ጊዜ በመቅረብ መግለጫውን በማንበብ መፈረም ይችላል (አንቀጽ 319 ይመለከቷል)። የፈራሚዎች ጉባኤ ማካሄድ! ህዝቡ አክሲዮን ግዢ ፈፅሞ የተፈለገው የካፒታል መጠን ከተሠበሰበ ወይም አደራጆቹ በቂ ካፒታል ተገኝቷል ብለው ካመኑ አሊያም የመፈረሚያው ቀነ ገደብ ካበቃ አክሲዮን ለመግዛት የፈረሙ ሠዎች ወይም የፈራሚዎች ጉባኤ በመሥራቾች እንዲጠራ የንግድ ህጋችን በአንቀፅ 320 እና ተከታዮቹ ይደነግጋል። የፈራሚዎች ጉባኤ ከተደረገ በኋላ የማህበሩ አደራጆች የማኅበሩን የመመሥረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ቤት ማፀደቅ አለባቸው። በተጨማሪም ማኅበሩ በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሚተዳደር ሀገር ዓቀፍ የንግድ መዝገብ ውስጥ በመመዝገብ የህግ ሰውነት ማግኘት አለበት። እንግዲህ የአክሲዮን ማኅበራትን ፋይዳ፣ ባህርያት እና መቋቋም በአጭሩ ከተመለከትን የአክሲዮን አይነቶችን እና አክሲዮን የገዛ ሰው የገዛውን አክሲዮን በተመለከተ ምን መብት አለው የሚለውን ቀጥለን እናያለን። ክፍል 3 ነገ ምሽት 3:30 ላይ ይቀርባል። ጠብቁን! © Fresenbet Adhanom @goferebusiness

  • 4 окт. 2021 г.228из Fikreprinting

    አክሲዮን እና አክሲዮን ማህበር❗️ (ክፍል 1) 📝 መንደርደሪያ ሰሞኑን የቤት አከራዮቼ፤ ከወትሮው በተለየ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እሰጣ አገባ ውስጥ ገብተው ሲነታረኩ እሰማለሁ። እኔም የፀቡ መነሻ ምን እንደሆነ እና በተቻለኝ ለመገላገል ወደ መኖሪያ ቤታቸው ጎራ ብዬ፤ ስለ ተፈጠረው ነገር ስጠይቅ፣ ባል ቀደም በማለት “እንደምታውቀው በከተማ ግብርና ተሰማርተን ውጤታማ ሆነናል። ሆኖም ግን ባለቤቴ እንደዚህ ለፍተን ባንክ ያስቀመጥነውን ገንዘብ አውጥተን ጦማር አግሮ ኢንዱስትሪ አክስዮን ማኅበር በግብርና የንግድ ዘርፍ በታወቁ ሙሁራን በምስረታ ላይ ስለሆነ የአክሲዮን ድርሻ እንግዛ!" እያለች መውጫ መግቢያ አሳጣችኝ። "እኔ ግን ማኅበሩ ወደፊት ቢከስር እና እዳ ከሶስተኛ ወገን ቢኖርበት ያፈራሁትን ንብረት ለእዳ መክፈያ አድርጌ ልጆቼን ሜዳ ላይ አልጥልም ነው የምለው።” እንግዲህ እኔም የህግ ባለሙያ እንደ መሆኔ ይህ አይነት ክርክር በሌሎች ሰዎች ዘንድ በሰፊው ይኖራል የሚል ግምት በመያዝ የአክሲዮን ማኅበር አጠቃላይ ይዘት ጥልቅ እና ውስብስብ ቢሆንም ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ መሰረታዊ ጉዳዮችን በ1952 ዓ/ም ስራ ላይ ከዋለው የሀገራችን የንግድ ህግ አንጻር እንመለከታለን። የንግድ ህጋችን አንዱ ዓላማ ለንግዱ ማኅበረሰብ አማራጭ የንግድ አደረጃጀትን ማቅረብ ሲሆን ግቡም የንግድ ማኅበረሰቡ ወዶ እና ፈቅዶ እንደ ልዩ ፍላጎቱ፣ እንደ ካፒታል አቅሙ፣ የሽሪኮቹን አቀራረብና የሃላፊነት ወሰኑን መሰረት በማድረግ በመደራጀት የንግድ ስራ እንዲከውኑ ለማድረግ ነው። ይህንንም ለማድረግ ይቻል ዘንድ የንግድ ህጉ 6 የተለያዩ የንግድ ማኅበራት አይነቶችን አስቀምጧል። ከእነዚህም ማሀከል የአክሲዮን ካምፓኒ (ማኅበር) አንዱ ነው (የንግድ ህግ አንቀጽ 212 ይመለከቷል)። 💹 የአክሲዮን ማኅበር ፋይዳ! የአክሲዮን ማኅበራት በሀገራችን ብሎም በክልላችን መበራከት ሀገራዊ እና ግለሰባዊ ፋይዳ አለው። ሀገራዊ ፋይዳውን ስናይ፤ አክሲዮን ማኅበር ትልልቅና ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቁ የንግድ ዘርፎች (ለምሳሌ ባንክ፣ መድን ድርጅት፣ በግብርና ዘርፍ፣ በቤቶች ግንባታ ወዘተ) ላይ ለመሰማራት የሚረዳ የማኅበር አይነት በመሆኑ የእነዚህ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች በሀገራችን መፈጠር መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ እያደረገች ያለውን ጥረት በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል። በሌላ በኩል የግለሰቦችን ስራ ፈጣሪነት ያበረታታል። ይህ ሲባል ግለሰቦች የሀገርን ኢኮኖሚ እድገት ሊያፋጥን የሚችል የንግድ ሃሳብ አመንጭተው ካፒታል ከህዝቡ በመሰብሰብ ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ሙያዊ ብቃታቸውን ተጠቅመው የሚሰሩ ስራ ፈጣሪዎች ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያበረታታ ሲሆን ለማህበሩ መፈጠር የደም ስር የሆነውን ካፒታል ያዋጡ ሰዎች ደግሞ ወደ ፊት ማኅበሩ የሚያስገኘውን ትርፍ የድርሻቸውን በመውሰድ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ያስችላል። በተጨማሪም ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እየተመረቁ የሚወጡ ወጣት ሙሁራኖች የእነዚህ ግዙፍ አክሲዮን ማህበራት መመስረት ሰፊ የስራ እድል ይፈጥርላቸዋል። በአጠቃላይ አክሲዮን ማኅበር ባለ ሀብቱን (Capitalist) ከስራ ፈጣሪ (Entrepreneur) ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው። 📖 ትርጉም አክሲዮን ማኅበር ማለት ቢያንስ በአምስት ሰዎች መካከል የሚቋቋም፣ የህግ ሰውነት ያለው፣ ካፒታሉ አስቀድሞ ተወስኖ በአክሲዮኖች የተከፋፈለ እና የአባላቱ ኃላፊነት ለኩባንያው ካፒታል ባዋጡት ወይም በሚያዋጡት መጠን የተወሰነ የንግድ ማህበር ማለት ነው (የንግድ ህግ አንቀጽ 210(2), 304, 307(1) ይመለከቷል)። ከዚህ ትርጉም ውስጥ አክሲዮን ማህበር 4 መሠረታዊ ባህሪያት እንዳሉት መረዳት ይቻላል። እነዚህንም በቅደም ተከተል እናያለን። 1⃣ የአባላቱ ብዛት ከአምስት ሰዎች የማያንስ መሆኑ! አንድ የአክሲዮን ማኅበር ሲመሰረት ዝቅተኛ የመስራች አባላት ብዛት አምስት ሰዎች የሚያስፈልጉት ሲሆን ከፍተኛው የአባላት ብዛት ጣሪያው ያልተገደበ መሆኑን መረዳት ይቻላል። ይህ ባህሪው ደግሞ ከሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ይለየዋል። ምክንያቱም የኋለኛው የአባላቱ ዝቅተኛ ብዛት ከሁለት የማያንስ ሲሆን ከፍተኛው የአባላት ብዛቱም በ50 ሰዎች ብቻ የተገደበ እና የካፒታሉ ዝቅተኛ መነሻ ደግሞ ከ15 ሺህ ብር ማነስ የለበትም (አንቀጽ 510(2) እና 512(1) ይመለከቷል)። 2⃣ ካፒታሉ አስቀድሞ ተወስኖ በአክሲዬኖች የተከፋፈለ መሆኑ! የአክሲዮን ማኅበሩ ካፒታል አስቀድሞ ተወስኖ በአክሲዮን የተከፋፈለ መሆን እንዳለበት ከትርጉሙ መረዳት ይቻላል። ይህም ማለት የአክሲዮን ማኅበሩ ምስረታ ተግባር የሚጀምረው ካፒታሉን፣ የአንድ አክሲዮን አቻ ዋጋ እና ካፒታሉ በስንት አክሲዮን እንደሚከፋፈል በመወሰን ቢሆንም የካፒታሉ መነሻ ደግሞ ከ50 ሺህ ብር ማነስ የለበትም (አንቀጽ 306 ይመለከቷል)።  3⃣ የአባላቱ ሃላፊነት የተወሰነ መሆኑ! የአክሲዮን ማኅበር ሌላኛው ገፅታ ደግሞ ማህበሩ ከሦስተኛ ወገኖች ማለትም ከአበዳሪዎች፣ ከደንበኞቹ እና ከሠራተኞቹ ወ.ዘ.ተረፈ ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ጉዳት ሊያደርሥ ይችላል። በዚህ ወቅት የማህበሩ አባላት (ባለ አክሲዮኖች) ሃላፊነት እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለውን ለመረዳት በንግድ ህጋችን አንቀፅ 304 (2) መሰረት የማህበሩ አባላት ሃላፊነት ለማህበሩ ካፒታል ባዋጡት ወይም በሚያዋጡት መጠን ተጠያቂ እንደሚሆኑ ይደነግጋል። ይህም ማለት አባላቱ ማህበሩ ሲመሠረት ወይም ከተመሰረተ በኋላ ለሽያጭ ከቀረበው የአክሲዮን ድርሻ ውስጥ በገዙት የአክሲዮን መጠን ብቻ ተጠያቂ የሚሆኑ ሲሆን አባሉ የሚጠበቅበትን መዋጮ ያልከፈለ እንደሆነ አክሲዮን ማህበሩ በእዳ ሲያዝ እንዲከፍል ይገደዳል። የአክሲዮን ማህበሩ ሃብት ጉዳቱን ለመካስ በቂ ሆኖ ባይገኝ ወደ ባለ አክሲዮኖቹ ንብረት መሄድ አይቻልም። በተመሳሳይ ሁኔታ የአባላቱ የግል እዳ ከኩባንያው ሃብት አይከፈልም። የአባላቱ ሃላፊነት መወሰን ግለሰባዊ እና ሃገራዊ አላማዎችን ለማሳካት ነው። ግለሰባዊ አላማውን ስናይ ሰዎች ሃላፊነትን ፈርተው ገንዘባቸውን ቀብረው እንዳይቀሩ እና አውጥተው ለንግድ እንዲያውሉት ለማበረታታት ነው። በመሰረቱ ካፒታል መድቦ ወደ ንግድ የሚገባ ሰው ለንግድ የመደበው ገንዘብ እና ጉልበት ትርፍ ማስገኘቱ ቀርቶ ሲከስር ወይም ለእዳ መክፈያነት ሲውል ጉዳቱ ቀላል አይደልም። በተጨማሪም ይህ ሳያንስ እንደገና ከንግድ ስራው ለይቶ ያስቀረውን የግል ሃብቱ ለንግዱ እዳ መክፈያ ይዋል ቢባል ፍተሃዊ ነው ለማለት ያስቸግራል። የሀላፊነት መወሰን ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ሃገራዊ ሲሆን ይህም ሀላፊነት ካልተወሰነ ሰው ወደ ንግድ እንቅስቃሴ ለመግባት ፋቃደኛ ስለማይሆን አገልግሎት አይስፋፋም፣ የስራ እድል አይፈጠርም። እንዲሁም ለመንግስት ግብር የሚሆን ገቢ ይቀንሳል። በመሆኑም ለሀገር ጥቅም ወይም ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ሲባል ማህበሩ አባላት ሀላፊነት በገዙት አክሲዮን ልክ የተወሰነ ይሆናል። ክፍል 2 ነገ ምሽት 3:30 ላይ ይቀርባል። ጠብቁን! © Fresenbet Adhanom @goferebusiness

  • አንድ እርምጃ ወደፊት! ሕይወት እንዳደረጋችሁት ነው፡፡ ስትንቀሳቀሱ ወደፊት ትሄዳላቸሁ፣ ስትቆሙ ወደኋላ ትቀራላችሁ፣ ስትወላውሉ ደግሞ ባላችሁበት ትረግጣላችሁ - ስሌቱ ይኸው ነው! በዙሪያችሁ የሚገኙትን ሰዎችን ተመልከቷቸው፡፡ አንድ ቀን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ አይደለም እዚህ ብዙዎች የሚመኙበት ደረጃ ደርሰው ራሳቸውን ያገኙት፡፡ ተንቀሳቅሰው፣ ሰርተው፣ አጠራቅመው፣ ታግለው . . . ነው፡፡ ነገ ከዛሬው፣ የዛሬ ዓመት ደግሞ ከዘንድሮው የተሻለ ሕይወት ከፈለጋችሁ ያንን የማድረጊያው ብቸኛውና እርግጠኛው መንገድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ ይህ እቅስቃሴ ደግሞ የግድ ትልልቅ መሆን የለበትም፡፡ በየቀኑ የሚደረጉ ትንንሽ እርምጃዎች በዓመት ውስጥ አንድ ግዙፍ ነገር እጃችሁ እንዲገባ ያደርጋል፡፡ ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን የማበረታቻ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ልቦናችሁ ከተነሳሳ የሚከተሉትን ልምምዶች ለመጀመር ሞክሩ፡፡ 1. አሁን ካላችሁበት ደረጃ በተሻለ መልኩ ለማወቅ በምትፈልጉት በአንድ እውቀት ዙሪያ መጽሐፍን የማንበብ ወይም አንድን ስልጠኛ የመውሰድን አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡ 2. ቀረብ ብላችሁ ብትተዋወቁትና ብታውቁት ለሕይወታችሁ እድገት የክህሎ ወይም የስብእና መዋጮ ያደርጋል ብላችሁ የምታስቡትን አንድ ሰው የመቅረብንና የመተዋወቅን አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡ 3. በእጃችሁ ላይ ያለውን ገንዘብ ወይም አንድ ንብረት በማዋል (ኢንቨስት በማድረግ) የተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለመድረሰ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡ መልካም የእድገት ዓመት ይሁንላችሁ! (በDr. Eyob Mamo የቀረበ)

  • [ ደስታ ] ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 350 በጻፈው [Nicomachean Ethics] ሥራው ላይ ግሪካዊው ፈላስፋ እና የሎጅክ አባት አርስቶትል "የሰው ልጅ ለራሱ ሲል የሚፈልገው ደስታ ብቻ ነው" ይለናል ፡፡ 'ሰዎች ሀብትን የሚፈልጉት ሀብታም ለመሆን ሳይሆን ደስተኛ ለመሆን ነው' ፡፡ እንደዚሁም 'ግለሰቦች ዝናን የሚመኙት ዝነኛ ለመሆን ብለው ሳይሆን ዝና ደስታ ያስገኛል ብለው ስለሚያምኑ ነው' እንደማለት መሆኑ ነው ፡፡ አርስቶትል በተጨማሪም "ለእኛ ያለው ትልቁ በጎ ነገር ደስታ ነው ለዚህም ነው የምንመኘው እና የምንፈልገው" በማለት ሃሳቡን ያጠነክረዋል ፡፡ እንደ ልምድ እና እንደ ርዕሰ ጉዳይ ደስታ ከታሪክ ጅማሬ ጀምሮ በስፋት እየተከታተለ እና አስተያየት ሲሰጥበት ቆይቷል ፡፡ ይህ የሰው ልጅ በደስታ ላይ ያስቀመጠውን እና አሁንም ያስቀመጠውን ሁለንተናዊ ጠቀሜታ የሚያንፀባርቅ ነው ፡፡ በእርግጥ የመንፈሳዊ መሪዎች ፣ ፈላስፎች ፣ የሥነ-ልቦና እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ስለደስታ ተፈጥሮ እና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ የተለያዩ አስተያየቶች አሏቸው ፡፡ አንድ ነገር እርግጥ ነው ደስተኛ ለመሆን እና በዙሪያችን ባለው የአለም ውበት ላይ ለመነቃቃት ከፈለግን ህይወታችንን ከጥልቅ እሴቶቻችን እና እምነቶቻችን ጋር በሚስማማ ሁኔታ ማኖር አለብን ፡፡ ሌሎች እንድንፈልገው ( እንድንሆነው) የሚፈልጉትን ሳይሆን ከህይወታችን የምንፈልገውን ማሳደድ አለብን። ይህ ነገር በጣም ቀላል አይደለም ፣ በተለይም በአሁን ዘመን ህብረተሰብ ውስጥ ፣ እኛ ለብዙ የውጭ ተጽኖዎች ተገዥዎች ነንና ፡፡] Erich Fromm [Escape from Freedom] በተባለው መጽሐፉ ላይ "Modern man lives under the illusion that he knows what he wants, while he actually wants what he is supposed to want." ሲል ፅፎልናል ፡፡ በእርግጥ ፣ በዛሬው የሸማቾች ማኅበረሰብ ውስጥ አድቬርት የሚሰሩና እና የሚዲያዎች ሰዎች ላይ እነሱ የሚፈልጉትን ለመጫን ይሰራሉ በማርኬቲንጉ 'the selling concept' እና 'mass marketing' የሚሉት Marketing Concept/ Philosophy ዘርፎች ናቼው፡፡ ብዙ ሰዎችም ደስተኛ የሚያደርጋቸውን ነገር ራሳቼውን ጠይቆ ከማቆም ይልቅ ይህንን ፕሮግራም በስግብግብነት ይጠቀማሉ ፡፡ ለነገሩ አብዛኛው ሰው ምን እያደረገ ነው ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ከብዙዎች ጋር ለመስማማት መሞከሩ በጣም ቀላል ነው ፡፡ ሆኖም ግን በተሳሳተ ስፍራ ደስታን ፍለጋ አብዛኞቹን መከተል እብደት ነው። ደስታ የደረሳችሁበት ነገር ግድ እንደማይለው አስተውሉ ፣ ምንም ያህል ብትሰሩ ግድ የለውም ፡፡ እንዲሁም የዲዛይነር ልብሶችን መልበስ ወይም መኪናችሁ ምን ያህል ቆንጆ እንደሆነ ወይም ምን ያህል ንብረት እንዳላችሁ ግድ የለውም ፡፡ በተጨማሪም ደስታ ምን ያህል ቆንጆ ፣ የተዋጣልህ ባለሙያ ወይም ብልህ መሆንህ ሁሉ ግድ የለውም ፡፡ ምናልባት እነዚህ እብድ ግምቶች ናቸው ትሉኝ ይሆናል፡፡ በተቃራኒው እነዚህን መግለጫዎች የሚደግፉ ብዙ ምሁራዊ መረጃዎች አሉ ፡፡ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ያደረጉት ጥናት እንደሚያመለክተው ብዙ ሰዎች ሕይወትን የተሻለ ያደርጉታል ብለው የሚገምቷቸው ነገሮች - ገንዘብን ፣ ደስታን ፣ ትልቅ ደረጃን ፣ ውበትን ፣ ወይም ማህበራዊ ታዋቂነትን - ያን ያህል አስፈላጊ አይመስሉም ። ለምሳሌ ፣ አንድ የምርምር ጽሑፍ አካላዊ ማራኪነት ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ምን ያህል ይዘት እንዳላቸው ሲያሳይ በጣም አነስተኛ ውጤት እንዳለው ዘግቧል ፡፡ ሌላ ጥናት ግለሰቦች ትልቅ ሎተሪ ካሸነፉ በኋላ ለአንድ ወይም ለሁለት ወር ሊደሰቱ ይችላሉ ፣ ግን ከአንድ ዓመት በኋላ በገንዘብ እና በመጨረሻው ደስታ መካከል ምንም ግንኙነት የለም ፡፡ አሁንም ቢሆን ሌሎች ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማህበራዊ አቋም ፣ ዕድሜ ፣ ብልህነት እና ትምህርት በእውነተኛ ደስታ ላይ ምንም ተጽዕኖ የላቸውም ፡፡ ደስተኛ ለመሆን መጀመሪያ፥ ደስተኛ ለመሆን ፈቃደኛ መሆንን ይወሰናል። ቀጥለን ለራሳችን መልካምና ክፉውን ራሳችንን በመጠየቅ ማወቅ ይኖርብናል ። እጣ ፈንታ ወይም ሌሎች መንገዱን እንዲሰጧችሁ ከጠበቃችሁ በጭራሽ እውነተኛ ደስታን እንደማታገኙት እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ፡፡ ጥቁርም ይሁን ነጭ ፣ ወንድ ወይም ሴት ፣ ፊደል ያልቆጠረ ወይም የትምህርት ሊቅነት ላይ የደረሰ ፣ ያላገባም ሆነ ባለትዳሮች ፣ ረዥምም ይሁን አጭር ፣ ወይም ሀብታም ወይም ድሃ ፣ ቢሆን ደስታ ማን ስለመሆንህ አይጨነቅም ፡፡ የቲቤታዊያን ቡዲስት ላማ Dalai Lama ሲናገር "Happiness is not something ready-made that Buddha can give you.It comes from your own actions." ይላል ጠቃሚ ምክርም ይመስለኛል ስለዚህም keep it within your heart !

  • 👂👂ሕይወት አዙሪት ናት👂👂 ሕይወት አዙሪት ናት፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሠው ከጀመርክበት ነው፡፡ ራቁትክን ትወለዳለህ፤ እርቃንህን ወደመቃብር ትወርዳለህ ፡፡ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ ። የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ፤ አጎንብሠህ ትጨርሳለህ፡፡ ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡ መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል፡፡ ሠኞ ማክሠኞ ብለህ ተጉዘህ፤ እንደገና ሠኞ ትላለህ ፡፡ ሕይወት አዙሪት ናት! መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው፡፡ ልብ በል! ባለማወቅ ትጀምራለህ፤ በመዘንጋት ትጨርሳህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም፡፡ በለቅሶ ትጀምራለህ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡ በሠው እቅፍ ትጀምራለህ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል? ሕይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ ልብ በል! የዓለም ከንቱነት ግን ውበትዋ ነው፡፡ ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን፤ ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!! ‹‹ርቀህ የሄድክ ቢመስልህም፤ ትልቅ ክብ ሠርተህ ተመልሠህ እዚህ ትመጣለህ፡፡ ዋናውን ተግባርክን ግን እስካሁን አልጀመርከውም፡፡››👣👣 ፧ ምንጭ ፦ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ (መርበብት - ከገጽ 314 - 315) #Share

  • 28 сент. 2021 г.1531из Doctoralle8809

    ✍#የሰዉነት #የበሽታ #መከላከል #አቅም 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የሰዉነት የበሽታ መከላከል አቅም ማለት አንድ ሰዉ በህመም እንዳይያዝ ወይም ህመም አምጪ በሆኑ ነፍሳት እንዳይጠቃ ወይም ከተጠቃ በኋላ እንዳይራቡ የሚዋጋልን የሰዉነታችን ስርዓት ነዉ። ⏩ #አንድ ሰው የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅሙ ሙሉ በሙሉ መሥራት በማይችልበት ጊዜ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ችግር እንዳለበት ይነገረዋል፡፡ በሽታ ተከላካይ ህዋሶች ለሰው ልጅ በህይወት ለመኖር በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ያለ በሽታ መከላከያ ሰውነት በቀላሉ ለባክቴሪያ ፣ለቫይረስ እንዲሁም ለጥገኛ ተዋሲያን የመጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ ⏩ #በዋነኝነት #በሽታ #ተከላካይ #የሚባሉት #ደግሞ #የሚከተሉት #ናቸው፡፡ 🔺 ነጭ የደም ህዋስ 🔺 በደም ውስጥ የሚፈጠሩ ፀረ-ባክቴሪያዎች (Antibodies) 🔺 በሰውነት ውስጥ ፀረ-ባክቴሪያዎች እና ተዋሲያን ለመግደል የሚያገለግሉ ስርአቶች (Complement System) 🔺 የደም ህዋሶች (Lymphatic System) 🔺 ጣፊያ (Spleen) 🔺 መቅኔ (Bone marrow) 🔺 ደረት ላይ የሚገኙ ዕጢዎች (thymus) ⏩ #የተዳከመ #የበሽታ #መከላከልን #አቅምን #የሚፈጥሩ #ሁኔታዎች 🔺 ኤች አይቪ ኤድስ 🔺 ዕድሜ እየጨመረ መሔድ 🔺 ካንሰር 🔺 ራስን ጤንነት የሚያጠቃ በሽታ (Autoimmune disease) 🔺 መድሃኒቶች እንደ (Corticosteroids) ያሉ መድሀኒቶች በተደጋጋሚ መውሰድ 🔺 የስኳር በሽታ፣ የኩላሊት በሽታ፣ ሄፓታይተስ ከተጠቃን 🔺 የአልኮል ሱሰኝነት የበሽታ መከላከያ አቅምን ያሳጣል 🔺 የልብ ሕመም ⏩ #በሽታ #የመከላከል #አቅምን #ለማሳደግ #የሚረዱ #ቀላል #ልማዶች 🔺 የሰውነት ንፅህናን መጠበቅ፣ እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ 🔺 በርከት ያለ ውሃ መጠጣት 🔺 ጮክ ብሎ መሳቅ 🔺 ፀሀይ መሞቅ 🔺 አዎንታዊ አስተሳሰብ መላበስ፤ ተስፈኛ መሆን 🔺 ቁርስ መመገብ 🔺 ለራስ ጊዜ መስጠት (ተመስጦ) 🔺 በየቀኑ የእግር ጉዞ ማድረግ 🔺 የሚያነቃቁ ሙዚቃዎችን መስማት 🔺 የስኳር አጠቃቀምን መቀነስ ⏩ #ስለማንኛው የጤና ጉዳይ ላይ ለመወያየት ካሻዎ 8809 ይደውሉ ስለችግሮ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ይማከሩ !!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)

  • ሰዎችን እርዷቸው ወይም ተረዷቸው! ሰዎች የሚያንጸባርቁት አጉል ባህሪይ በሙሉ እርዳታ ፈላጊነታቸውን ጠቋሚ መሆኑን አትርሱ፡፡ በአጠገባችሁ የሚገኙ በማንኛውም አይነት መልኩ የምትገናኟቸው የቅርብም ሆኑ የሩቅ ሰዎች ከእነሱ ጋር በሚያነካካችሁ ጉዳይ አማካኝነት ስትቀርቧቸውና ተግባቦትን ስትፈጥሩ ቁጣና ስሜታዊነት፣ ክፋትና ኃይለኛነት፣ ክስና ወቀሳ . . . የሚመልሱላችሁ ከሆነ እነዚህን ሰዎች እንደጠላት ለመቁጠር አትቸኩሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች እርዳታ የሚያስፈልገው የስነ-ልቦና ጫና ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ሰዎች ከአስተዳደጋቸው፣ ካሳለፉት አጉል ልምምድ ወይም ከምልከታ ቀውስ የተነሳ በስነ-ልቦና ጫና ውስጥ ሲሆኑ ውስጣቸው እርዳታን ይፈልጋል፡፡ ይህንን የእርዳታ ጥሪና ጩኸት ግን በተለያየ መልኩ ነው የሚገልጹት፡፡ አንዳንዶች መደበኛ በሆነ መልኩ ከጓደኛ ወይም ደግሞ ከአማካሪ እርዳታን በግልጽ ይጠይቃሉ፡፡ ሌሎቹ ግን ቀደም ሲል በጠቀስነው መልክ የተለያዩ ወጣ ያሉና አስደንጋጭ ስሜቶች አማካኝነት ያንን የእርዳታን ጩኸት ይጮሃሉ፡፡ ሰዎች ውስጣቸው ካለው ቀውስ የተነሳ “ወጣ” ያሉ ሲሆኑ እኛም በእነሱ ምክንያት “ወጣ” ያለ ምላሽና ባህሪይ ካንጸባረቅን ሁለታችንም እርዳታ ፈላጊዎች መሆናችንን አትዘንጉ፡፡ እነሱ ከተለያዩ ጫናዎችና ግፊቶች የተነሳ ያንን ባህሪ በመግለጣቸው፣ እኛም ብንሆን የእነሱ ባህሪይ ካስከተለብን ጫና እና ግፊት የተነሳ ያንን ባህሪይ በመግለጣችን ተመሳሳይ ያደርገናል፡፡ በስሜትና በስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ከቻልን እንርዳቸው፣ ካልቻልን ደግሞ ሌላ ሰው እስከሚረዳቸው ድረስ እኛ ቢያንስ እንረዳቸውና ተሽለን እንገኝ፡፡ በማሕበራዊ ብልህነት ልቆ የመገኛው አንዱ መንገድ ይህ ነውና!

  • በፌስቡክ ስሟ Maki ye ወይንም በፔጇ ማኪ ቡና በሚል የምናውቃት ማኪ ይሄን ብላለች፣ "በማለዳ ንባብ፣ ፀሎትና ስፖርት ለሰው ልጅ አስፈላጊ ናቸው። ንባብ ለአእምሮ ምግብ፣ ስፖርት ለአካል ጥንካሬ፣ ፀሎት ለመንፈሳዊ ህይወት ጠቃሚ ናቸው። የዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ "መርበብት" መጻፍ ትናንት ሰው ጋብዞኝ ዛሬ ወደ ሥራ እስክገባ እያነበብኩት ነበር። እንዲህ የሚል ቁምነገር አግኝቻለሁ፣ ".... ሕይወት አዙሪት ናት! መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው፡፡ ልብ በል! ባለማወቅ ትጀምራለህ፤ በመዘንጋት ትጨርሳህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም፡፡ በለቅሶ ትጀምራለህ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡ በሠው እቅፍ ትጀምራለህ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡....." በነገራችን ላይ የማኪ አድራሻ ባህርዳር ከተማ ገበያ፣ አዝዋ ሆቴል ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ከዋናው ንግድ ባንክ ፊት ለፊት "አሩሰል ባህር የገበያ ማዕከል አንደኛ ፎቅ ላይ ነው። ጎብኟት!

  • ቀና ብላችሁ ኑሩ! ያላገባችሁና ግራ የተጋባችሁ . . . ሳላገባ ሌላ ዓመት መጣ፣ እድሜዬም ሊያልፍ ነው ብላችሁ ከመፍራትና ትክክለኛ ባልሆነ ሰው ላይ ከመውደቅ ይልቅ፣ ትክክለኛውን ሰው እስከምታገኙ ድረስ ራሳችሁን እያሳደጋችሁ፣ የወቅቱን ሁኔታችሁን ተቀብላችሁ፣ እንደገና የማይመለሰውን ይህንን “የብቸኝነት” ኑሮ እያጣጣማችሁና ተረጋግታችሁ እያንዳንዷን ቀን ቀና ብላችሁ ብትኖሩ ይሻላችኋል፡፡ እድሜ ማለፉ ላይቀር ከማይሆን ሰው ጋር እየተነታረካችሁ ከሚያልፍ ይልቅ ከራሳችሁ ጋር ተስማምታችሁ ቢያልፍ ይሻላል፡፡ ራሱን የሚቀበል፣ ራሱን የሚያከብር፣ ራሱን የሚያሳድግና ራሱን የሚመራ ሰው በፍጹም ብቸኝነት ተሰምቶት አያውቅም፡፡ መልካምና የተረጋጋ “የብቸኝነት” ዓመት ይሁንላችሁ!

  • የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዘመን አቆጣጠር (ባሕረ- ሐሳብ ) የዘመነ ማርቆስ/ የ2014 ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት “በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” መዝ. 64(65)፥11 ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምህረት + ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) = 2014+ 5500 =7514 ወንጌላዊ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡ ዓመተ ዓለም፥4 7514 ÷ 4 = 1878 1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡ 7514 - 4×1878 = 2 ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ቀሪው ' 0 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል። ስለዚህ ቀሪው '2' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ማርቆስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ ይባላል። ••• ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡ ዕለተ ቀመር= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7 = 7514 + 1878 =9392 = 9392 ÷ 7 = 1341 ቀሪ 5 ቀሪው '0 'ከሆነ ሰኞ ቀሪው '1' ከሆነ ማክሰኞ ቀሪው '2 'ከሆነ ረቡዕ ቀሪው '3 'ከሆነ ሐሙስ ቀሪው '4 'ከሆነ ዓርብ ቀሪው '5 'ከሆነ ቅዳሜ ቀሪው '6 'ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው '5'ስለሆነ ዕለተ ቀመር ቅዳሜ ይሆናል። ••• መደብ = ዓመተ ዓለምን በ19 በመግደፍ እናገኛለን። = 7514፥19=395 ደርሶ 9 ይቀራል። ስለዚህ መደብ 9 ይሆናል፡፡ ••• • ወንበር = ከመደብ አንድን ለዘመን በመተው ወንበርን እናገኛለን። ወንበር =9 - 1= 8 ይሆናል። • አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በወንበር አባዝተን በ30 ገድፈን እናገኛለን። አበቅቴ =11*8=88 88፥30= '2' ደርሶ ቀሪው '28' ሲሆን ዘንድሮ አበቅቴ '28'ይሆናል። አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ጥንተ አበቅቴ ላይ 11 በመጨመር ነው። ይህም ማለት የ2013 ዓ.ም አበቅቴ 17 ነበር፤ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም አበቅቴን ለማግኘት 17+11=28 ይሆናል ማለት ነው። • መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በወንበር አባዝተን ለ30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን። መጥቅዕ = 19×8 = 152 152 ÷ 30= 5 ቀሪው '2 'ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ '2 'ይሆናል። መጥቅዕንን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ጥንተ መጥቅዕ ላይ 19 በመጨመር ነው። ይህም ማለት የ2013 ዓ.ም መጥቅዕ 13 ነበር፤ ስለዚህ የ2014 ዓ.ም መጥቅዕን ለማግኘት 13+19=32 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 2 ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ የ2014 መጥቅዕ 2 ይሆናል ማለት ነው። “አበቅቴ ወመጥቅ ክሌሆሙ ኢይበዝሁ እም30 ወኢይኅዱ እም 30 ወትረ ይከዉኑ 30 ፤ አበቅቴ ቢበዛ መጥቅ ቢያንስ መጥቅ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከ30 አይበዙም አያንሱም” ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አብቅቴ ተደምረዉ ዉጤቱ ከ30 መብለጥና ማነስ የለበትም፤ ሁሌ 30 ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ የ2013 ዓ.ም = 28+2= 30 መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ይዉላል፤ መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይዉላል፤ መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ በየካቲት ይብታል። ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 2 ሲሆን ከ14 ያንሳል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በጥቅምት ይዉላል፤ ••• ስለዚህ የ2014 መጥቅዕ ጥቅምት 2 ነው ሲሆን ዕለተ መጥቅዕ ማግሰኞ ይሆናል፡፡ ••• መባጃ ሐመር፦ መጥቅዕንና የባለመጥቅዕን ተውሳክ በመደመር በ30 በመግደፍ እናገኛለን፡፡ ከዕለተ መጥቅዕ ጀምረን እስከ ነነዌ ጾም መግቢያ ስንቆጥር 128 ቀን ይሆናል፡፡ በ30 ብንገድፈዉ 4 ቀሪ 8 ይሆናል፡፡ ይህም የቅዳሜ ተውሳክ ነው። ልብ ይበሉ የዕለት ተውሳክ ከቅዳሜ ይጀምራል፡፡ • ቅዳሜ፡ 128፥30= 4 ቀሪ 8 • እሁድ፡127፥30= 4 ቀሪ 7 • ሰኞ፡ 126፥30=4 ቀሪ 6 • ማግሰኞ፡ 125 ፥30= 3 ቀሪ 5 • ረቡዕ፡124 ፥30= 2 ቀሪ 4 • ሐሙስ፡ 123፥ 30= 2 ቀሪ 3 • ዓርብ፡122፥ 30= 2 ቀሪ 2 ስለዚህ የዕለታት ተውሳክ ቀሪዎቹን በመያዝ ይታወቃል። ይህም የቅዳሜ 8፣ የእሁድ 7፣ የሰኞ 6፣ የማግሰኞ 5፣ የረቡዕ 4፣ የሐሙስ 3 እንዲሁም የዓርብ 2 ይሆናል ማለት ነው። መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ መደመር ነው። መባጃ ሐመር= 2+5=7 መባጃ ሐመር ከ30 ስለሚያንስ ራሱ 7 ይያዝና መጥቅዕ በጥቅምት ስለዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት 7 በዕለተ ሰኞ ይውላል ማለት ነው። • ጾመ ነነዌ፦ መጥቅዕና የዕለቱን ተውሳክ በመደመር በ30 ገድፈን እናገኛለን፡፡ይህ ጾም ሕጸፅ የለውም፡፡ ሌሎችን አጽዋማት ተውሳኩን ከነነዌ ደምረን ከ30 ከበለጠ ለ30 እያካፈልን እናገኛለን። ••• ፩፥ ከነነዌ ጾም እስከ ዐቢይ ጾም 14 ቀናት አሉ። ስለዚህ የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ይሆናል፡፡ ፪፥ ከነነዌ እስከ ደብረዘይት 41 ቀኖች አሉ፡፡ 41 ÷ 30 = 1 ደርሶ ቀሪው 11 የደብረዘይት ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፫፥ ከነነዌ እስከ ሆሣዕና 62 ቀኖች አሉ፡፡ 62 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 2 የሆሣዕና ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፬፥ ከነነዌ እስከ እስከ ስቅለት 67 ቀኖች አሉ፡፡ 67 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 7 የስቅለት ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፭፥ ከነነዌ እስከ ትንሣኤ 69 ቀኖች አሉ፡፡ 69 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 9 የትንሣኤ ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፮፥ ከነነዌ እስከ ርክበ ካህናት 93 ቀኖች አሉ፡፡ 93 ÷ 30=3 ደርሶ ቀሪው 3 የርክበ ካህናት ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፯፥ ከነነዌ እስከ ዕርገት 108 ቀኖች አሉ፡፡ 108 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀሪው 18 የዕርገት ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፰፥ ከነነዌ እስከ ጰራቅሊጦስ 118 ቀኖች አሉ፡፡ 118 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀርው 28 የጰራቅሊጦስ ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፱፥ ከነነዌ እስከ ጾመ ሐዋርያት 119 ቀኖች አሉ፡፡ 119 ÷ 30 =3 ደርሶ ቀሪው 29 የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ ነው፡፡ ፲፥ ከነነዌ እስከ ጾመ ድኅነት 121 ቀኖች አሉ፡፡ 121 ÷ 30 = 4 ደርሶ ቀሪው 1 ሲሆን የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ይሆናል፡፡ ••• ከዚህ ተነስተን አጽዋማትንና በዓላትን ተውሳኮቻቸውን ከነነዌ ጋር እየደመርን እናገኛለን፡፡ ስለዚህ የ2014 የነነዌ ጾም መግቢያ የካቲት 7 ይሆናል፡፡ 2+7= 9 ስለሆነ ነው፡፡ ★ ዓብይ ጾም ተውሳኩ 14 ነው = 14 +7= 21 ሲሆን ስለዚህ ዘንድሮ በዘመነ ማርቆስ ዓብይ ጾም በየካቲት 21 ይገባል ማለት ነው፡፡ * ደብረ ዘይት፡ ተውሳኩ 11 ነው፡፡ 11+7 =18 ይሆናል፡፡ 18 ከ 30 ስለሚያንስና በየካቲት ስላለፍን ቀጣዩን በመጋቢት እናገኛለን። ስለዚህ በመጋቢት 18 እሁድ ደብረዘይት ይሆናል። ★ ሆሣዕና ተውሳኩ 2 ነው፡፡ = 2+7 =9 ሲሆን ከ30 ስለሚያንስና በመጋቢት ስላለፍን ቀጣዩን ሚያዚያን እናገኛለን፡፡ ስለዚህ ሚያዚያ 9 እሁድ ይሆናል፡፡ ★ ስቅለት ተውሳኩ 7 ነው፡፡ 7+7= 14 ሲሆን ዘንድሮ በሚያዝያ 14 ዓርብ ስቅለት ይሆናል፡፡ ★ ትንሣኤ ተውሳኩ 9 ነው፡፡

  • #ቀጣይ አመት ስኬታማ ለመሆን ልትተዋቸው የሚገቡ ልምዶች! ▸ በሌሎች ለመወደድ ያለህን ፍላጎት አስወግድ፦ ምንም ስራህ ምን ሁሌም ድርጊትህን የሚቃወሙ ሰዎች መኖራቸው አይቀርም። ▸ መርዘኛ ባህሪ ያላቸው ሰዎችን አስወግድ፦ መልካም አመለካከት የሌላቸውን ሰዎች በዙሪያ ይዞ ስኬታማ መሆን አይቻልም። ▸ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ያለህን ፍላጎት አስወግድ፦ የተወሰኑ ነገሮች ለኛ አብዛኞቹ ደሞ ለኛ እንዳልሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ▸ ሁሌም ፍፁም ለመሆን ያለህን ፍላጎት አስወግድ፦ ፍፁም ለመሆን ማሰብ ባንተ ላይ ከፍተኛ ግፊት ያሳድራል ስለሆነም በተግባርህ ጥሩ ከሆንክ ይበቃል። ▸ በፍጥነት ስኬት ላይ ለመድረስ ያለህን እምነት አስወግድ (Overnight Success)፦ ስቲቭ ጆንስን ጨምሮ ማንም በአንዴ ስኬታማ የሆነ የለም። ▸ ትንንሽ ህልሞችን አስወግድ፦ ራዕይህ ትልቅ ካልሆነ መቼም ትልቅ ነገር አታሳካም። ▸ ጤናማ ያልሆኑ የህይወት መንገዶችን አስወግድ፦ አካልህ ቤትህ ነው ስለሆነም ስኬትህ ላይ ለመድረስ ጤናማ መሆን አለብህ።

  • 7 ነገሮችን እናስታውስ❗ 1. ብቸኛው ወሳኙ ራሳችሁ ናችሁ! 2. ሕይወት ከመቅፅበት ትጠፋለች! 3. የማድነቅ ስሜታችሁን ፍጹም አትተው! 4. ከሕልማችሁ እንጂ ከሰዎች ኋላ አትሂዱ! 5. እራሳችሁን ከምታውቁ በላይ ትችላላችሁ! 6. ራሳችሁን ስትወዱ፤ ሌሎችም ይከተላችኋል! 7. በሕይወት መጸጸት የለባችሁም፤ ትምህርት መውሰድ እንጂ! ስለሆነም ሕይወትን ኑሩ! (የኔ ትውልድ ሳይኮሎጂ)

  • ግሩም አባባሎች 😍😍ለመልካም ቀን 😍😍😍😍 "እያንዳንዱ ሰው ልክ እንደጨረቃ ነው፡፡ ለማንም የማያሳየው ግማሽ ጎን አለው።" ማርክ ትዌይን "የወደፊቱን የእርካታ ጊዜ የምታገኝበት የተሻለ መንገድ ያለህበትን ዕለት በሳቅና በፈገግታ ስታሳልፈው ነው።" ቻርለስ ደብሊው "የጅረቶች ብዛትና የዝናብ መዓት የውቅያኖስ ጣዕም እንደማይበርዙት ሁሉ የመከራ ውርጅብኝም የቆራጥ ሰው ህሊናን በድን አያደርገውም እንዲህ ያለ ሰው የህያውነት ሚዛኑን ይጠብቃልና።" ሴኒካ "አንድን ነገር መቼም ላላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው፤ስታውቅ ደግሞ መቼም ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው!!" ኮንፊሽየስ " ንግግር ከማድረግህ በፊት ንግግርህን በነዚህ ሶስት በሮች ፈትሸህ አሳልፈው... ትክክል ነው ወይ? አስፈላጊ ነው ወይ? በጎ ነገር ነው ወይ? " ሩሚ "ሁሉም ሰው ሞትን ይቀምሳል ህይወትን የሚቀምሰው ግን በጣም ጥቂቱ ነው።" ሩሚ " ፍቅር ያልነካው እሱ በጨለማ ውስጥ እንደሚጓዝ ፍጡር ነው " ፕሉቶ "በአለም ላይ ከብዙ ሰው ጋር ትገናኛላችሁ ግን በጭራሽ ከራሳችሁ ጋር ተገናኝታችሁ አታውቁም።" ኦሾ “አንድን ነገር ካልወደድከው ለውጠው፤ ለመለወጥ ካልቻልክ ደግሞ በነገሩ ላይ ያለህን አመለካከት ለውጥ” – ማያ አንግሎ በአብርሆት(Enlightenment) ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ

  • አብርሆት pinned «❗ቢያውቋቸው ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ወሳኝ #ድረገፆች ኢንተርኔት እንደዓለም ዳርቻ እጅግ ጥልቅ በሆነበት በአሁን ሰዓት ሁሉንም የድረገፅ አይነት አውቆ መጠቀም ምናልባትም በዓለማችን በሚገኙ እያንዳንዱ ቦታዎች ተዘዋውሮ እንደመጎብኘት እጅግ ሊከብድ ይችላል፡፡ ታዲያ እነዚህ ጥበብን፣ እውቀትን፣ ልምድን እና በጠቅላላውም ህይወትን ለመቀየር የሚያስችሉትን፤ ወሳኝ ድረገፆች አውቆ ለመጠቀም የሌሎች ጠቋሚነት እጅግ…»

  • ❗ቢያውቋቸው ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ወሳኝ #ድረገፆች ኢንተርኔት እንደዓለም ዳርቻ እጅግ ጥልቅ በሆነበት በአሁን ሰዓት ሁሉንም የድረገፅ አይነት አውቆ መጠቀም ምናልባትም በዓለማችን በሚገኙ እያንዳንዱ ቦታዎች ተዘዋውሮ እንደመጎብኘት እጅግ ሊከብድ ይችላል፡፡ ታዲያ እነዚህ ጥበብን፣ እውቀትን፣ ልምድን እና በጠቅላላውም ህይወትን ለመቀየር የሚያስችሉትን፤ ወሳኝ ድረገፆች አውቆ ለመጠቀም የሌሎች ጠቋሚነት እጅግ ወሳኝ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ በመሆኑም ለዛሬ ከዚህ በፊት የማያውቋቸው ነገር ግን ከዚህ በኋላ ቢያውቋቸው እጅግ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ድረ ገፆችን ከተለያዩ ምንጮች አሰባስበናል፡፡ ያወቁትን ሌሎች እንዲያውቁት ብታደርጉ የበለጠ ያተርፋሉ!!! 1. ከሌላው ዓለም ህዝብ ጋር ጥበብን፣ አውቀትን እና ልምድን ለማጋራትና ለማንሸራሸር • MentalFloss.com • Lifehacker.com • https://www.quora.com/ • https://medium.com/ • Lumosity.com 2. አዲስ ነገር መማር ሲፈልጉ • Make code (Microsoft MakeCode) {Must visit!} • Guitar ( https://www.justinguitar.com/ ) {you can thank} • Duolingo (Learn a language for free) • Tutorials Point (Tutorials) • Experiments with Google 3. ለግራፊክስ ዲዛይነሮች ከphotoshop ውጭ ሌላ አማራጭ ሲፈልጉ • Free Pik ( https://www.freepik.com/ ) • Flaticon ( https://www.flaticon.com/ ) • Adobe colour picker (Adobe Color CC) • Pexels ( https://www.pexels.com/ ) • Video Pexels (Free stock videos - Pexels Videos) • Canva (Amazingly Simple Graphic Design Software 4. ከEmail ውጭ ሌላ አማራጭ ይኖር ይሆን ካሉ • www.bluebottle.com • http://mail.yahoo.com • http://gmail.google.com • www.hotmail.com • www.walla.com 5. የጤናዬ ጉዳይ ያሳስበኛል ካሉ • www.nelh.nhs.uk • www.hpa.org.uk • www.food.gov.uk • www.bmj.com • www.avert.org 6. ሲደብሮትና እና ራሶን ለማንቃት ሲፈልጉ • Ted ( https://www.ted.com/ • www.7billionworld.com • www.beesbeesbees.com • www.sanger.dk ✳️ ጠቃሚ የመጽሐፍ ድረ ገጾችን እንጠቁማችሁ ◽️ http://gen.lib.rus.ec/ ይህ ድረ-ገጽ ማንኛው አይነት መፅሀፍ ማውረድ የሚያስችሎት ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠር መፅሀፎች አሉት በዉስጡ ከሚግኙ መፅሀፎች መካከል 🔺የትምህርት መፅሀፎች፤ 🔺የሳይኮሎጂ መፅሀፎች፤ 🔺ፍልስፍና መፅሀፎች ፤ 🔺የታሪክ መፅሀፎች ይገኙበታል፡፡ ◽️ http://sci-hub.org/ ይህ ድህረ-ገጽ ከ64 ሚሊዮን በላይ የጥናት ወረቀት የሚገኝ ሰለሆነ በቀላሉ ማዉረድ ይቻለሉ፡፡ በዚህ ድረ- ገጽ የተለያዩ መጻፎች በተለያ ምርጫ እና አይነት ያገኛሉ። ◽️ https://bookboon.com/ ይህ ድረገጽ ማንኛው አይነት የነጻ መጻፍ የሚያገኝበት ሲሆን በየትኛዉም የክፍል ደረጃ ላሉ ተማሪዎች አንዲዉም በማንኛው የስራ ሁኔታ ላይ ላሉ ሰዎች ጠቃሚ ድርገጽ ነው፡፡ ◽️ http://bookzz.org/ ቡክዚ አለማችን ለይ ትልቅ የመጻሀፍ ላይብረሪ ያለው ሲሆን በአማካኝ 2.6 ሚሊዮን መጻሀፍ በ ድረገጹ ይገኛል። ይህ ድረገጽ ብዙ የቴክኖሎጂ መጽሀፍት ያሉት ሲሆን የፕሮግራሚንግ፤ ግራፊክስ፤ የኮምፒተር አጠቃቀም እና የተለዩ የትምህርት መጻሃፎች ያገኛ የተለያዩ ኮርሶችን መማር እና ማወቅ ለምትፈልጉ በሙሉ ማለትም ለምሳሌ #Programming , #Web_Development , #Networking እና ሌሎችም...(ከታች ያሉትን ሳይቶች ይጠቀሙ) 1. www.codecademy.com 2. www.lynda.com 3. www.udemy.com 4. www.udacity.com 5. www.coursera.org 6. www.w3schools.com 7. www.thenewboston.org 8. www.programmr.com 9. www.codeavengers.com 10. www.codeschool.com 11. www.learnstreet.com 12. www.teamtreehouse.com 13. www.sqlzoo.net 14. www.codehs.com 15. www.teamtreehouse.com 16. www.html5rocks.com 17. www.codepen.io 18. www.sitepoint.com 19. www.tutorialspoint.com 20. www.javatpoint.com 21. www.cplusplus.com 22. www.learncpp.com 23. www.tutorialspoint.com 24. www.cprogramming.com 25. www.stackoverflow.com 26. www.learncodethehardway.org 27. www.bloc.io 28. www.howtocode.io 29. www.edx.org 30. www.instructables.com 31. www.developer.apple.com 32. www.developer.android.com 33. www.developers.google.com 34. www.developer.mozilla.org 35. www.msdn.microsoft.com 36. www.decompera.com 37. www.www.developphp.com 38. www.quackit.com 39. www.htmlite.com 40. www.siteduzero.com 41. www.dreamincode.net 42. www.phpbuddy.com 43. www.php.net 44. www.microsoftvirtualacademy.com 45. www.professormesser.com ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው #Share #Share