tgindex
(أبو نحلا) Abu Nehla

(أبو نحلا) Abu Nehla

Статистика
@abunehla18арабский

قال الأمام الشافعي رحمه الله من لايحب العلم لاخيرفيه!

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
арабский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 365
0 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
207
24 постов
Вовлечённость
8,8%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
79
1/48двое суток
90
1/72трое суток
97

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.12из 𝐑𝐚𝐟𝐢𝐪𝐮𝐥 𝐈𝐬𝐥𝐚𝐦 𝐏𝐫𝐨𝐦𝐨𝐭𝐢𝐨𝐧

    видео или голосовое, без подписи

  • አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ እህት ወንድሞች አንድ ነገር ላስቸግራቹ ነው ለአላህ ብላቹ ተባበሩኝ አንዲት እህት ስደት ከመጣች ሁለት አመት ሆኗታል ግን በጣም እሚያሳዝነው አሰሪዋ ጠንቋይ ናትና ልጅታን ምንም ነገር እንዳታቅ አድርጋ አፍዝዛታለች እናም ይችህ እህት አላህ ዳኚ ሲላት ዝምብላ ከቤቱ ትወጣለች ከዛም ሲደክማት መንገድ ላይ ቁጭ ትላለች ከዛም አንድ ሱዳናዊ ግለሰብ ያያታል ሲያያት ግን ልጅቷ ላይ ችግር እንዳለ ይረዳና ጠጋ ብሎ ሲጠይቃት ተስፋን የሚያስቆርጡ ንግግሮችን  ትመልስለታለች እሱም ችግር እንዳለ ይረዳና ያለውን ገንዘብ ሰጣትና ሪያድ ኢንባሲ ብላ እንድትሳፈር ተባበራት ከዛም ይችህ እህት ወደ ኢንባሲው ከገባች ቦሀላ ፈዛ ቁጭ ባለችበት አንድ ሀበሻዊ ያገኛታል ከዛም  እነደመጀመሪያው ገለሰብ  ሲጠይቃት ተመሳሳይ መልስ መለሰችለት እና ይችህ እህት ስትጠየቅ ምታቀው ወላሂ ስሟንና የአባቷን ስም ብቻ ነው ምታቀው 2ት አመት ቤተሰብን ሳታወራ ቆይታለች ቤተሰቦቿ ይኑሩ አይኑሩ አንድ ምታቀው ነገር የለም የት እንደነበረችኳን ስንጠይቃት ምታስታውሰው ነገር የለም  እና አስብት እናት የልጇን ድምፅ ሀለት አመት  ሳትሰማ ሞታለች ብላ ቁርጧን አላውቀች ሁሌ ልባ እንደተጠለጠለ  ወላሂ ይከብዳል ልጅቱም እናት አባትን የወንድም እህቶቿን ድምፅ ሳትሰማ  ጭራሽ ስማቸውን እስከመርሳት ድርስ እና ውንድምና እህቶች ሼር በማድረግ ተባበሩኝ በዝች ልጅ ቦታ እራሳችንን አስቀምጠን እናስብ የልጅቷ ስም ሙኒራ አብደላህ ትባላለች የትወልድ ባታ ጉንችሬ  ልዩ ስሙ ኡፍጠሬ ሚባል ቦታ ነው ብላናለች ባረከላሁፊኩም ተባበሩን ወላጆች ልጆቻቹን እያሰባቹ ወደዃላ አትበሉብን  ያገኘ ካለ በዚህ ስልክ ተባበሩን +966550745238 የቻናል ባለቤቶች ተባበሩን

  • 11 авг.82из 𝐑𝐚𝐟𝐢𝐪𝐮𝐥 𝐈𝐬𝐥𝐚𝐦 𝐏𝐫𝐨𝐦𝐨𝐭𝐢𝐨𝐧

    🇪🇹የኢትዮጵያ ሰለፊዮችን ትክክለኛ ቻናል በቀላሉ ለማግኘት👉OPEN👈 ምትለዋን ብቻ ይጫኑ

  • ✍ የአላህ ሪዝቅ በሮች ብዙ ናቸው፦ - ሶደቃ ማድረግ - ፀጋን ማመስገን - ልጅ እና ዝርያ - እውቀትን መፈለግ - ኢማን እና አላህን መፍራት - መብቃቃት - አላህን ማውሳት - በጥዋት መውጣት - በምድር ላይ መዟዟር - ሶላትን መስገድ - ስደት (ወደ አላህ) - በአላህ ላይ መመካት - ጥሩ ስራ መስራት - ዝምድና መቀጠል - ሚስኪንን ማብላት - እውነትን መናገር (በንግድ ውስጥ) - ዱአእ ማድረግ - ልብን በአላህ ማንጠልጠል - ትዳርን መያዝ - በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግ - አላህን ለመገዛት ፍሪ መሆን - ኢስቲግፋርን ማብዛት - መቀማመጫን ቦታ ማስፋት - በአላህ መንገድ ላይ መፅናት - ሸሪአን መተግበር 👆በቁርአን እና ሀዲስ ላይ የተጠቀሱልን የሪዝግ በሮች ናቸው። || የቴሌግራም ቻናል⤵️ https://t.me/abuzekeryamuhamed https://t.me/abuzekeryamuhamed

  • "ባሌን ሌሎች ሴቶች ሲያዩት ዝንጀሮ ያስመስለው" አንድ ሴት ባሏን የግሏ ብቻ ለማድረግ ስትል ባሌን ሌሎች ሴቶች ሲያዩት ዝንጀሮ ያስመስለው ብላለች ይባላል።እናም እቺ ሴት ያስጨነቃት ባሏ የእርሷ ብቻ መሆኑ እንጂ የባሏ ገፅታ ሰዎች ዘንድ መበላሸቱ አላሳሰባትም።ልክ እንደዚሁም አንዳንድ ወንድሞች አላህ ይቅር ይበላቸውና ከደዓዋው መስለሃ ይልቅ የግል መስለሃቸውን ለማስጠበቅ በወንድሞቻቸው ላይ በደልን ይፈፅማሉ።ይህን ፁሁፌን እንድፅፍ ያነሳሳኝ የሚከተለው ክስተት ነው። ሀምሌ 29/2018 ከዓሱር ሰላት በኃላ አንድ ስልክ ከአንድ ወንድሜና የቀድሞ ተማሪዬ በኩል ተደወለልኝ።ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ በመቀጠል እርሱ በሚገኝበት ጀመዓ የደዓዋና የኮርስ ፕሮግራም ለማስኬድ የጋበዟቸው የሱና መሻኢኾችና ኡስታዞች እንደነበሩ ብሎም ማስታወቂያ ጭምር ሰርተው አሰራጭተው እንደነበረ ነገር ግን አንድ ሰው እኔም የማውቀው ወንድሜም የሚያውቀው ወንድም ደውሎለት እገሌ የሚባለው ኡስታዝ ችግር ስላለበት ለምን ጋበዛችሁት ብሎ እንደተቃወመና የተለያዩ ምክንያት የሚላቸውን የትችት ነጥቦችን በመጥቀስ እንዳስጠነቀቀና በዚህ ምክንያት በዚህ ወንድም ማስጠንቀቂያ መሰረት በቦታው ያሉ ወንድሞች ለግዜው በነገሩ በመወዛገብ ፊትና ለመቀነስ በሚል ተወያይተው ያኛውን የሱና ተጋባዥ ኡስታዝ ከፕሮግራሙ እንዲሰረዝ በማድረግ ማስታወቂያውን በአዲስ መልክ ለመቀየር እንደተገደዱ ነግሮኝ ከፕሮግራሙ ስለተወገደው ተጋባዥ ኡስታዝ እውነታ የምታውቀው ነገር አለ ብሎ ጠየቀኝ።እኔም ጉዳዩን ወደ መሻኢኾች በማስጠጋት መረጃ ከእነርሱ እንዲወስድ ከአንዳንድ መንደርደሪያ ምክረሃሰቦች ጋር አቀጣጫ ሰጠውት። በጣም የተደነቁት ከዛም አልፎ ያስደነገጠኝ ነገር ቢኖር ደውሎ አስጠንቃቂውም ማስጠንቀቂያ የተደረገበትም ኡስታዝ የሱና ሰዎች ከመሆናቸውም ጋር በውስጥ መስመር በዚህ ልክ የማስጠንቀቅ እርምጃው ነበር።በእርግጥም ይህ አይነት የሰለፍዬችን አንድነት የሚንድ አካሄዶች ከጀመሩ ሰንበትበት ያለና  በተደጋጋሚ በየቦታው እየተበራከተ ያለ እውነታ ነው።እገሌን በዚህ ቻናል ላይ አትጋብዙት፣ እገሌን ከጋበዛችሁት እኛ አንሳተፍም፣ ለእገሌ መድረክ እንዳትሰጡት እና የመሳሰሉ ግፈኛ ፍርዶች ከተለያየ አቅጣጫ ይሰማሉ ናቅ ተደርገው ታልፈው እንጂ። ውድ ሰለፍይ ወንድምና እህቶች! ሰለፍያ በዚህ ብልሹ አካሄድ እንደማትረዳና ይልቁንም ሰለፍዬችን ወደ ተወገዘው ግሩብተኝነት የሚያደርስ ስለሆነ ከዚህ ተግባር መቆጠብና ከፊላችን ከፊላችንን በዚህ አካሄድ ላይ አላህን ፍራ በማለት ልንተራረም ይገባል። ይህን ዓይነት አካሄድ በግዜ የማንቀርፍ ከሆነ ከባድ ጥፋትን በሰለፍዬች አንድነት ላይ ስለሚያስከትል ከዚህ ብልሹ አካሄድ እንቆጠብ ባይነኝ። ጥፋቶች ካሉም የሸሪዓን ጥቅምና ጉዳት ሚዛንን በጠበቀ መልኩ ወደ ባለቤቶቹ (መሻኢኾች) በመመለስ እንዲታረም ማደረግ አማራጭ የሌለው ሸሪዓዊ መርሆ ነው።ሁሉም እየተነሳ ግልፅ ባልሆነ ምክንያትና ድብቅ በሆነ የአደረጃጀት መዋቅር በንፁሃን ወንድሞች ላይ  ግፈኛ ፍርድ የሚሰጥ ከሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ተጎጂው ባለቤቱ ሲሆን በመቀጠልም የደዓዋውን ጤነኛ ተደራሽነት በማሰናከል ከባድ የሆነ ትርምስና ስርአትአልበኝነትን ያስከትላል። ሰለፍዬች በጥፋት ቡድን ከየቦታው እየታመሱ ባሉበት በዚህ ወቅት ውስጣዊ የሰለፍዬችን የአንድነት እሴታቸውን የሚንድ የጥፋት አካሄድ ማራመድ ከሸሪዓም ከዓቅልም ብሎም ከሞራልም አንፃር የተወገዘ ነው። የሸሪዓችን መርሆ የሚያዘውም አንድ ሙስሊም ሌላን ሙስሊም እንዳይበድለው ብቻ  ሳይሆን ወንድሙም ተበድሎ ያገኘው ግዜ አቅሙ በቻለው ልክ  ከጎኑ ሊቆምና ሃቁን ሊያስመልስለትና በተቃራኒው ደግሞ በዳዩን መታገል ነው። ይህንም በሚመለከት ታላቁ ነብይ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል: "المُسلِمُ أخو المُسلِمِ لا يَظلِمُه ولا يُسلِمُه" (أخرجه البخاري) "አንድ ሙስሊም የሌላኛው ሙስሊም ወንድም ነው።አይበድለውምም፣ (ተበድሎም ሲያገኘው የማይረዳው ሳይሆን)  አሳልፎ  (ለበዳይ) አይሰጠውም።" ይህ ሀዲስ የሚጠቁመን በምንም መልኩ አንድ ሙስሊም ሌላኛውን ሙስሊም እንደማይበድለውና ሌሎች አካላትም ወንድሙን ሲበድሉት አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ የሚተወው እንዳልሆነ ነው። ዛሬ አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ ብዙዎቻችን ከተበደሉት ጎን ልንቆም ቀርቶ በዳይን በማገዝ ላይ በበደል ላይ በደልን እንጨምራለን።በደል አይደለም ሰለፍይ ወንድምህን ይቅርና እንስሳትን መበደልም ቢሆን ነገ ዕለተቂያማ የከፋ ውጤት ያስከትላል።ነብያችን صلى الله عليه وسلم እንደተናገሩት:— (اتَّقُوا الظُّلمَ ؛ فإنَّ الظُّلمَ ظُلُماتٌ يومَ القيامةِ) (أخرجه مسلم) "በደልን ተጠንቀቁ፣ በደል ነገ ዕለተ ቂያማ (ድቅድቅ) ጨለማዎች ነውና።" ውድ ሰለፍይ ወንድም እህቶች ዲን በስሜት፣ በእልክ ብሎም ግፈኛ በሆነች የሴራና የተንኮል አደረጃጀት አይረዳም ይልቁንም ዲን የሚረዳው በማስረጃ፣ በፍትህ፣ አላህን በመፍራትና የአላህን ተጠባባቂነት ብሎም ከመላእክቱም ተጠባባቂዎች እንዳሉብን በማወቅ በምናደርጋቸው እንቅስቃሴ መሆኑን በመገንዘብ አላስፈላጊ ከሆነ የፊትና፣የጥላቻ፣ የቂመኝነትና የእልክ  አካሄዶች አላህን በመፍራት ልንቆጠብና  አጥፊዎችንም ተው ልንላቸው ይገባል።ነገራቶች ስርአታቸውን በዚህ መልክ በግዜ እንዲይዙ ካልተደረገ ማብቂያ ለሌለው ስርአት አልበኝነትና ትርምስ ይዳርጋል። የጀመዓን እንቅስቃሴ በግለሰቦች መስለሃ ላይ ከማንጠልጠል በመቆጥብ እና በጀመዓ የአንድነት እሴት ላይ አሉታዊ የሆኑ የግል አመለካከቶችን በመከላከል የሰለፍዬችን አንድነት ማጠናከር ይገባናል። بارك الله فيكم ✍አቡ ሙዓዝ

  • 👉 የኣደም ልጅ ነፍስ በሶስት ፀፀት እንጂ ከዱንያ አትወጣም ! قال الحسن البصري – رحمه الله – " لا تخرج نفس ابن آدم إلا بحسرات ثلاثة :– 1 – أنه لم يشبع مما جمع 2 – ولم يدرك ما أمل 3 – ولم يحسن الزاد لما قدم عليه " موسوعة ابن أبي الدنيا (5/132) አል ሐሰኑል በስርይ የተባለ ታላቅ ሊቅ እንዲህ ይላል : – " የኣደም ልጅ ነፍስ በሶስት ፀፀት እንጂ ከዱንያ አትወጣም ! 1– ከሰበሰበው ነገር አልጠገበም ። 2 – የተመኘውን አላገኘም ( አልደረሰበትም) ። 3 – ለሚሄድበት ሀገር በቂ ስንቅ አላዘጋጀም "። http://t.me/bahruteka

  • ሱረቱል ዩሱፍ ካስተማረኝ ህመም የታሪኩ መጨረሻ እንዳልሆነ የአዲስ ህይወት ማሳወቂያ እንጂ ምናልባት ዛሬ ላይ ራስህን እንደ ዩሱፍ ልታይ ትችላለህ የህመም ጉድጎድ አልያም በበዳዬች ስር ወይንም ውስጥህን በሚፈትኑ ከባባድ ፈተናወች ውስጥ ራስህን ልታገኝ ትችላለህ ። እናልህ ጉድጎዱ ወደ ቤተመንግስቱ መሄጃ መንገድ እንደሆነ እስር ቤቱም ወደ ዙፍኑ መሄጃ ድልድይ እንደሚሆን አስታውስ ። በህይወትህ  የሚያጋጥሙህ እያንዳንዱ እርምጃወችህ  ምንም ያህል ጨለማ መስለው ቢታዩህ አላህ አንተ በማታቀው መልኩ በጥበብ ወዳንተ እየመራህ ነው ። አንተ ያላሰብከው ያልጠበከው መልካም ነገር መጨረሻው ላይ ይጠብቅሀል ። @Abu Nehla

  • ሰው ሞልቶ ሰው ጠፋ ወዳጅ የተባለው እንደ ጠላት ከፋ ሁሉም ይሯሯጣል የውስጡን አምቆ ለገሀዱ ዓለም ቢታይ እንኳን ስቆ ከፈገግታው ጀርባ ጥቁር ድንኳን ጥሎ መኖርን ይዳዳል ይህም ያልፋል ብሎ ይህም ያልፋል ብሎ በሰላ ጉልበቱ ዐለትን ይገፋል ሞቱ እየናፈቀው ለመኖር ይለፋል!

  • አሰላሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ የተወደዳችሁ ውድ ሰለፍዮች በያላችሁበት የአሏህ ሰላም በናንተ ላይ ይሁን ማስታወቂያውን በማሰራቸት ላይ ወድ ሰለፍዮች የበኩላችሁን ተወጡ ባረከሏህ ፊኩም ወደ ግሩፑ ለመቀላቀል ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/haraselefi

  • ከስራ ቤትህን ስትገባ  ሚስትህ ቁርኣን ይዛ ስትቀራ እንደ ማየት ምን የምያስደስት ነገር ኣለ? ሚስቶቻችሁን ቁርኣን አስቀሩ።ሴቶች በቲክቶክ ቫይረስ በተለከፉበት ዘመን የቁርኣን አፍቃሪ ሚስት ማግኘት እጅግ መታደል ነው። منقول

  • 🔷 ከጥበብ ሶዎች አባባል ! — ከተብቃቃህ ትንሹ ብዙ ነው ። — ከከጀልክ ጎተራው ቢሞላ ትንሽ ነው ። — ከወደድክ ሩቁ ቅርብ ነው ። — ከጠላኸው የቅርቡም ሩቅ ነው ። — ከታገስክ መከራው ደስታ ነው ። — ትእግስት ካጣህ ግን ደስታው መከራ ነው ። — ከተገነዘብክ ነገሩ ሁሉ ካንተው ነው ። http://t.me/bahruteka

  • አንዳንድ ቀናት ...‼️ አንዳንድ ቀናት እንደ ንፋስ ሽውታ ናቸው። በትላትናው እና በዛሬው ቀን መሀል ቢገኙም  ያልነበርንባቸው ያህል ምስልና ድምፅ አልባ ናቸው። ብቻ እድሜን ይሰራሉ። አልኖርንም እንዳንል ዘመኑ ይራመዳል ኖረናል እንዳንል ለወግ የሚበቃ ትውስታ እንኳ አላበጀንባቸውም። ምናልባት እነዚህ ቀናት ናቸው በልጅነት እና በማደግ መሀል ያለውን ልዩነት የሚቀምሩት። እይታን ማደብዘዝ ያውቁበታል።

  • ♦️| ሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ ኢኽዋን ነበሩን⁉️ — በተደጋጋሚ ከኢንተርኔት ሞኞች ከምናየው ግፍ  ሚዛን ከጎደለው ወንጀል አንዱ ሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድን ታርጌት ያደረጉበት ከንቶ ክሳቸው ነው። በዚህ ክሳቸው ላይ በጣም የሚገርመው ተመሳሳይ እንኳን ፍርድ የላቸውም እዚህ ሌላ አቋም እዛ ጋር ሌላ!። — ሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ ከኢኸዋኖች ጋር ነበር ስለዚህ እኽዋን ነበር & ኢሊያስ አህመድ ከኢኽዋን ጋር ነው  ኢኽዋን ግን አይደለም¡ ሰዎች በምን ቋንቋ አውርተን እንግባባ⁉️ — ሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ ኢኽዋንን ያወድስ ነበር ስለዚህ እኽዋን ነበር ኢሊያስ ኢኽዋንን ያወድሳል አይ ያወድስ ግዴለም እሱ ሰለፊይ ነው¡ — ሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ ከኢኽዋን ተከላክሎ ነበር ስለዚህ ኢኽዋን ነበር ኢልያስና መሰሎቹ ለኢኽዋን እየተካላከሉ ነው ሲባል አይ ግድ የለም ሰለፊይ ነው ቆይ ግን ይሄ ስሌት ኬት የበቀለ እውቀት ቢሆን ነው⁉️ እውር እውርን ቢከተል ተያይዘው ገደል! — እንዲህ የሚቀባዥሩ ወንድምና እህቶች ቢረጋጉና ቢያስተውሉ የንግግራቸውን ውጤት በተረዱት ነበር ሙመዪዓ ለዘመናት የሚያራግቡት የማይቆም ታሪክ  ይሄ ጉዳይ ነው። በነገራችን ላይ ልጅን አሳዳጊ እሳትን ውሃ ያጠፋዋል አሳዳጊ የበደለው ለአፉ ለከት የለውም። ሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድን በድሮ አቋማቸው በዚህ ልክ እየከሰሳችሁ ምንም እንኳ ፍትህ ባይሆንም ሁሉም ላይ ለምን አታደርጉትም⁉️ — ሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ ከኢኽዋኖች ጋር ይገናኙ ስለነበር ወይም ይከላከላሉ ስለነበረ ብቻ ኢኽዋን ነበሩ ማለት ነው? — ያ ማለት አንድ ዓሊም ለኢኽዋን ቢከላከል ወይም ከኢኽዋን ጋር ቢታይ ያለምንም ቅድመሁኔታና ደንብ ማሟላት ኢኽዋን ነው ተብሎ ይፈረጃል ማለት ነው? የማሚቴን እጅ ያላየ በእሳት ይጫወታል!። እነዚህስ ላይ ምን ትሉ ይሁን⁉️ 1.ኛ ሸይኽ አል-አልባኒይ -ረሒመሁ'ሏህ- እንዲህ ይላሉ፦ "እኔ በኢኽዋኖች በእጅጉ አዋቂ ነኝ ምክንያቱም ዲመሽቅ ላይ ዳዒ ሆኜ 10 አመታቶችን ከነሱ ኑሬያለሁ" ይላሉ። 🎙ድምፁን ለመስማት ከስር ሊንኩን ይጫኑ https://youtu.be/9s4hLrhCv04?si=pgw-fmYc97iwmSCx የሸይኻችን ግልጽ አቋምና ራስን ማጥራት 🎙የመጨረሻ የሸይኽ ዐብዱል-ሐሚድ አቋም ይሄንን የመስላል በሊንኩ ያገኙታል፦ https://t.me/abuabdurahmen/81 — ሸይኽ አብዱል ሐሚድ ከኢኸዋኖች ኖሬያለው ኢኽዋን ግን አልነበርኩም ማለታቸው በጣም ለገረማችሁ አሁንም በድጋሚ ወደ ሸይኽ አል-አልባኒይ ንግግር ልመልሳችሁ። 2.ኛ ጠያቂ እንዲህ ይላሉ፦ "ከኢኽዋን ጋር እንዴት ነበር  ስትኖሩ የነበራችሁት ከዛስ እንዴት ኢኽዋንን ትታታችህ ወጣችሁ? ሸይኽ (አል-አልባኒይእንዲህ አሉ፦) በመጀመሪያ እንዴት ተውካቸው ለመባል ኢኽዋን አልነበርኩም። ሶሪያ ላይ አብሬያቸው ነበርኩኝ ሙሓደራቸውን እሳተፍ ነበር እኔም ሙሓደራ አደርግ ነበር" ይላሉ በንግግራቸው ሓሲል። 🎙ድምጻቸውን ለመስማት ሊንኩን ይጫኑ፦ https://youtu.be/ECy_BBhr0CY?si=5qxp89f1Avt4Jpz8 3.ኛ  ምንም በማያሻማ መልኩ ሸይኽ አል-አልባኒይ  - رحمه الله - እነ ሐሰን አልበናን እና ኢኽዋንን ሰለፊያ ናቸው ከሰለፊያ አላስወጣሁም ሲሉ ነበር። ምንም እንኳን በመጨረሻ ትክክለኛውን አቋማቸውን ቢገልፁም የመጀመሪያ አቋማቸው ይሄ ነበር። ታዲያ ኢኽዋን ነበሩ⁉️ እሳቸው አልነበርኩም እያሉ ነው። 🎙የመጀመሪያ አቋማቸውን በዚህ ሊንክ ገብተን እንስማ፦ https://youtu.be/nwlOTjtethw?si=8L8TDHN6_B8mbm4h 4.ኛ በግልጽ ኢኽዋንን ከሱና ያስወጡበት የመጨረሻ አቋም እንዲህ ይላሉ፦ ليس صوابا أن يقال أن الإخوان المسلمين هم من أهل السنة لأنهم يحاربون السنة. "ኢኽዋን አ'ል ሙስሊሚን ከአህሉሱና ናቸው ማለት ትክክል አይደለም። ምክንያቱም አህሉሀሱናን ስለሚዋጉ።" ድምጻቸውን ለመስማት ሊንኩ ላይ ይግቡ ፦ https://youtube.com/shorts/BQORjrP1Bzo?si=13bwTFrtLTReWZKD ጹሁፉ ረዘም ስላለብኝ በክፍል ክፍል አድርጌዋለሁ ይቀጥላል.. ✍ ኡስታዝ ዐብዱል-ቃዲር አዳማ -ሐፊዞሁ'ሏህ- || የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/abuabdurahmen https://t.me/abuabdurahmen

  • ♦️| የለተሞ ሸይኽ ማን ናቸው⁉️ (2)  🎙ኡስታዝ ዐብዱል-ቃዲር ከአዳማ 🗓 ከ «አርበዑን አል-ለተሚየህ» ደርስ! || የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abu_Hessan https://t.me/Abu_Hessan

  • ይድረስ ሼኽ አብደልሀሚድንም ሆነ ሌሎች የሱና ዑለሞችን በመሳደብ ለተጠመዱ በሙሉ‼️ https://t.me/abunehla18

  • 👌 ወሳኝ ፈትዋ በተለይ ለሴቶችና ለወጣቶች ከተዳሰሱት ነጥቦች ውስጥ ✔️ እጅጌው ላይ ዚፕ ያለው ወይም እጅጌው ሽብሽብ የሆነ ጂልባብ መልበስ እንዴት ይታያል? ✔️ በአንድ ሴት ሌላ ወንድ አጅነብይ የሚሆንባት የልጁ እድሜው ስንት ሲደርስ ነው? ✔️ ሴት ልጅ ለመህረሞቿ ክፍት ማድረግ የሚፈቀድላት አካላቶቿ የትኞቹ ናቸው ? ✔️ አጅ ነብይ ወንድ በሌለበት ሴቶች ፀጉራቸውን መክፈት ይችላሉ ? ✔️ ቤተ ሰብ አውቆ ቃል ተጋብቶ መኖር ይቻላል ? ቃል ከተጋቡስ ከኒካህ በፊት ስጦታ መሰጣጠት ይቻላል ? ✔️ ኒቃብ ዋጂብ ነው ? እሺ ትምህርት ቤት ውስጥስ ? 👍 ሴት ልጅ ጅልባብ ለብሳ ፊቷን ከከፈተች የቱ ላይ ነው ውበቷ ?? 👌 ደሞ አንድ ሴት የህብረተ ሰብ አይደለችም የአንድ ባል ናት !! 🎤 ፈዲለቱ ሸይኽ አብድል ሃሚድ ለተሚይ ሃፊዘሁሏህ ✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!! https://t.me/Abumuseab

  • 26 июн.272из 𝐑𝐚𝐟𝐢𝐪𝐮𝐥 𝐈𝐬𝐥𝐚𝐦 𝐏𝐫𝐨𝐦𝐨𝐭𝐢𝐨𝐧

    አል ኢስራእ ወል ሚዕራጅ የሚባለው ጉዞ ከየት ወደ የት ነበር? ትክክለኛውን መልስ በመንካት የሚመጣላቹን የሰለፊዮች ቻናሉ ይቀላቀሉ።

  • 25 июн.281из 𝐑𝐚𝐟𝐢𝐪𝐮𝐥 𝐈𝐬𝐥𝐚𝐦 𝐏𝐫𝐨𝐦𝐨𝐭𝐢𝐨𝐧

    🇸🇦ሰለፊዮች ሆይ የምርጥ የሰለፊይ መሻይኮች ኡስታዞች እንዲሁም ወንድሞች ቻናል እያለላቹ በየሙብተዲእ ቻናል ምን ትሰራላቹህ? አሁን ጉዳዬ ላሳጥርላቹህ እና ከታች ጆይን የምትለዋን ምልክት ስትፈልጉ በአውራ ጣታቹ ስትፈልጉ በቀለበት ጣታቹ ብቻ በፈለጋቹት ጣታቹ ጆይን(JOIN) የምትለዋን ምልክት በመንካት ወደ ኢትዮጵያ የሰለፊዮች ቻናል ተቀላቀሉ🇸🇦

  • 24 июн.254из 𝐑𝐚𝐟𝐢𝐪𝐮𝐥 𝐈𝐬𝐥𝐚𝐦 𝐏𝐫𝐨𝐦𝐨𝐭𝐢𝐨𝐧

    የነገውን የአሹራ ቀን መፆም የአንድ አመትን ወንጀል ያስምራል። ትክክለኛውን መልስ በመንካት ወደ ሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ።

(أبو نحلا) Abu Nehla — tgindex