- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 26
- 1/48двое суток
- 29
- 1/72трое суток
- 32
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ረሱል 🤍 እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَنْ تَشبَّهَ بقومٍ فهوَ مِنهُمْ﴾ “ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እሱ ከነሱ ነው።” 📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል: 4831
ረሱል 📖 እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنَّ اللَّهَ لَيَرْضى عَنِ العَبْدِ أَنْ يَأْكُلَ الأكْلَةَ فَيَحْمَدَهُ عَلَيْها، أَوْ يَشْرَبَ الشَّرْبَةَ فَيَحْمَدَهُ عَلَيْها﴾ “አላህ ከባሪያው ላይ ይወዳል ምግብን ከተመገበ በኃላ በሷ እንዲያመሰግነው። ወይም መጠጥንም ከጠጣ በኋላ በሷ እንዲያመሰግነው።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: (2734)
ቅዱስ ቁርኣን በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 56፥77 እርሱ *የከበረ* ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ ቅዱስ ቁርኣን የምንልበት ምክንያት ቁርኣን "ከሪም" ስለተባለ ነው፤ "ከሪም" كَرِيم የሚለው ቃል "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" የሚል ፍቺ አለው፦ 56፥77 እርሱ *የከበረ* ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ "መጽሐፍ ቅዱስ" ማለት "ቅዱስ መጽሐፍ" ማለት ነው፤ የፈጣሪ ንግግር ብቻ ነው ቅዱስ እንጂ የሰው ንግግር ቅዱስ አይደለም። ባይብል የሰው ንግግር ስላለበት ቅዱስ መጽሐፍ አይባልም። ስለዚህ ባይብልን "መጽሐፍ ቅዱስ" በማለት ፋንታ "ባይብል" በሉት፤ "ባይብል" የሚለው የኢንግሊሹ ቃል "ቢብሊያ" βιβλία ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "ጥቅሎች"scrolls" ማለት ነው፣ በነጠላ ደግሞ "ቢብሊኦን" βιβλίον ሲሆን "ጥቅል"scroll" ማለት ነው። ይህ ቃል ለማንኛውም መጽሐፍ ቃሉ ያገለግላል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ቁርኣን ብቻ ነው፤ ምክንያቱም የቁርኣን ተናጋሪ ፈጣሪ ብቻ ስለሆነ ማለት ነው፤ በእግጥም ቁርኣን "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" ነው። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሰላሙ አለይኩም
ረሱል 📖 እንዲህ ብለዋል፦ ﴿وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ، لَا يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الْأُمَّةِ يَهُودِيٌّ وَلَا نَصْرَانِيٌّ، ثُمَّ يَمُوتُ، وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ إِلَّا كَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ﴾ “የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው እምላለሁ! አንድም ከዚህ ኡመት (ህዝብ) አይሁድም ይሁን ክርስቲያን ስለእኔ መላክ አይሰማም። ከዚያም በእርሱ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት አይኖርም። እርሱ የእሳት ባለቤት የሚሆን ቢሆን እንጅ፡፡” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 153
ረሱል 🤍 እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾ “ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1036
ረሱል 📖 እንዲህ ብለዋል፦ ﴿أَحَدُكُمْ مَا قَعَدَ يَنْتَظِرُ الصَّلَاةَ فِي صَلَاةٍ مَا لَمْ يُحْدِثْ، تَدْعُو لَهُ الْمَلَائِكَةُ : اللَّهُمَّ اغْفِرْ لَهُ، اللَّهُمَّ ارْحَمْهُ﴾ “ከናንተ መካከል አንዳችሁ ሶላት የሰገደበት መስገጃው ላይ እስካለና ውዱእ አስካላጠፋ ድረስ፤ መላእክቶች ለሱ ዱዓእ ያደርጋሉ። አላህ ሆይ! ወንጀሉን ማረው፤ አላህ ሆይ! እዘንለት ይላሉ።” 📚 ቡኻሪ (3229) ሙስሊም (649) ዘግበውታል
የአሏህ መልዕክተኛ (ሶለ ሏሁ አለይሂ ወሠለም) እንዲህ አሉ።በአሏህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር ወይ ዝም ይበል። [ቡሃሪና ሙስሊም ዘግበውታል] @abunejashii
ኢየሱስ ሙስሊም ነው! አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ Telegram ፦ https://t.me/tiriyachen
без подписи
ማነው መጤው? ~ ሙስሊሙ መብቱን በጠየቀ፣ ጭቆናን በተቃወመ፣ እምነቱን ባስተማረ ቁጥር "እናንተ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ስትገቡ አክብረን በተቀበልን እንዴት ውለታችን ይረሳል?" እያሉ በቅጥፈት ለሚመፃደቁ አካላት "እንዴ! እኛ እኮ ኢትዮጵያውያን እንጂ መጤዎች አይደለንም" እያሉ በከንቱ መድከም አያስፈልግም ብዬ በፅኑ አምናለሁ። ሰዎቹ እንዲህ አይነት አመክንዮ የሚገባቸው አይደሉም። ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው። መፍትሔው ማጥቃት እንጂ መከላከል አይመስለኝም። በራሱ ቋንቋ አናግረው። በዚህ ድንቁ ^ ርና ላይ በሰፊው የሚታወቁት በዋናነት የአንድ እምነት ተከታዮች ናቸው። እነሱ ናቸው "የእስላም አገሩ መካ፣ የአሞራ አገሩ ዋርካ" የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ፈጥረው ድንቁርናቸውን ከትውልድ ትውልድ የሚያሻግሩት። እንዴት አድርገው እንደሚጠርቧቸው እንጃ በዚህ ዘመን እንኳ አልተቀየሩም። የለውጥ ተስፋ የሚታይባቸውም አይደሉም። አስቂኙ ነገር ደግሞ ራሳቸውን የአይ^ሁድ ዘር አድርገው መኮፈሳቸው ነው። ሃገሪቱን ለሰባት መቶ ዓመታት በላይ የቦጠቦጠው ራሱን "ሰለሞናዊ መንግስት" ብሎ የሚጠራው መዥገር ስርአትኮ ባህር ተሻግሮ የሰሎሞን ዘር ነኝ የሚል ነው። መጤ ነኝ ማለት አይደል ይሄ? አፄ ምኒልክ "ዳግማዊ" ምኒልክ የተባለው ጥንት ከንጉስ ሰለሞን የተገኘ "ቀዳማዊ" ምኒልክ ነበር ብለው ስለሚያምኑ ነው። "የናዝሬቱ እየሱስ፣ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ቃና ዘገሊላ፣ ቤተልሄም፣ እየሩሳሌም፣ ... " እያለ እምነቱን ከባህር ማዶ ጋር የሚያይዝ አካል እንዴት ሙስሊሞችን መጤ ሊያደርግ ይዳፈራል?! የሙስሊሙን ኢትዮጵያዊነት መቀበል የከበዳቸው ጭንቅላቶች "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" የሚል ያረጀ ያፈጀ ተረት ዛሬም ይተርታሉ። ለመሆኑ እነሱ ዘንድ ኢትዮጵያ ማለት የቷ ናት? ለመሆኑ ኢትዮጵያ ሲሉ አፋርን፣ ሶማሊን፣ ሀረርን፣ ስልጤን፣ ከፊል ጉራጌን፣ ሰፊውን ኦሮሚያን፣ ሀላባን፣ አብዛኛው ወሎን፣ አብዛኛውን በኒሻንጉልን፣ ድሬዳዋን፣ አርጎባን፣ ... ይጨምራል ወይ? እስኪ እነዚህን አካባቢዎች ቆርጠው ያውጡና የደሴቷን ካርታ ይመልከቱ። ካርታው ላይ የሚታየው ቀዩ ክፍል ነው የሚቀራቸው። ከዚያ የቀራችሁን የክርስቲያን ደሴት ተመልከቷት! የምትዘምሩላት ኢትዮጵያ ይቺ ናት? ለማንኛውም "በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል የሰለሞን ዘር ነን"፣ "ነገደ ይሁዳ ነን"፣ "የይሁዳ አንበሳ ነን" የሚለውን የአባቶቻችሁን ተረት የምታምኑበት ከሆነ መጤዎች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ መስክራችኋል። እኛ ሙስሊሞች ዐረቦች ነን አላልንም። ኢትዮጵያውያን ነን። እናንተ "የሁ^ዶች ነን" ካላችሁ እኛ ነን የተቀበልናችሁ። "አይ" ካላችሁ "አይ^ሁድ ነን" የሚለውን የአባቶቻችሁን ተረት ውሸት እንደሆነ አስረግጣችሁ ወርውራችሁ ጣሉ። ከዚያ በኋላ ራሳችሁን የኢትዮጵያዊነት አከፋፋይና ድርጎ ሰፋሪ አድርጋችሁ ማየታችሁን አቁሙ። የነውረኝነታችሁ ዳፋ ለደካሞች ይተርፋልና ጥፍራችሁን ሰብስቡ። በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የከረፋ ሃሳብ ስታንፀባርቁ ታንኩም ባንኩም በእጃችሁ በነበረበት የቀደመው ዘመን ያደረሳችሁትን ማሰብም ይሰቀጥጣል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
без подписи
የሐሰት ትርክት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 22፥30 ከጣዖታት እርኩሰት ተጠንቀቁ! የሐሰትን ቃል ራቁ፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ "ኢትዮጵያ" የምትባል አገር ከሦስት ሺህ ዓመት በላይ ታሪክ ያላት አገር መሆኗን በታሪክ ምሁራን ዘንድ ይተረካል፥ ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ የራሷ ቋንቋ፣ ፊደል፣ ሥነ ጽሑፍ ያላት አገር ናት። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስለ ኦርቶዶክስ ደሴታውያን፦ "ኦርቶዶክስ ፊደል ቀርጻ፣ ብራና ዳምጣ፣ ቀለም በጥብጣ አገር ገንብታለች" በማለት የሐሰት ትርክት ይተርካሉ፥ እውን ኦርቶዶክስ አገር በቀል እሳቤ ነው ወይስ ከሌላ አገር የመጣ እሳቤ ነው? እንደ ጎርጎሮሳውያን በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ከኢትዮጵያ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ወንጌል ሰምቶ እና አምኖ ወደ አገሩ ተመለሰ፥ ያ ሰው ከእርሱ አልፎ ለኢትዮጵያውያን ያስተላለፈው እና ያስፋፋው ነገር እንደሌለ እሙን እና ቅቡል ነው። በአራተኛው ክፍለ ዘመን ሊባኖሳዊ ፍሬምናጥስ በማዕረግ ስሙ "አባ ሰላማ" በንጉሥ ዒዛና ዘመነ መንግሥት ክርስትናን በይፋ አስገብቷል፥ በመቀጠል በ 480 ድኅረ ልደት ተስዓቱ(ዘጠኙ) ቅዱሳን ክርስትናን በጽብሓውያን የአስተሳሰብ ውቅር ወደ ኢትዮጵያ አስገብተዋል። ሙግቱ እስቲ ጠበብ እናርገውና "ክርስትና የገባው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ነው" እንበል "ኢትዮጵያን የሚባሉ ሕዝቦች ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት የሉም" እያላችሁን ነው? ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት ፊደል፣ ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ የለምን? ስለዚህ "ኦርቶዶክስ ፊደል ቀርጻ፣ ብራና ዳምጣ፣ ቀለም በጥብጣ አገር ገንብታለች" የሚለው ትርክት የሐሰት ትርክት ነው። ሌላው ደሴታውያን "ኦርቶዶክስ አገር ናት" የሚል የሐሰት ትርክት አላቸው፥ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድ የክርስትና አንጃ"Sect" እና የክርስትና ሃይማኖት ምድብ እንጂ አገር በፍጹም አይደለችም። አገር ኢትዮጵያ እንደመሆኗ መጠን ኢትዮጵያ ዋቄፈታውን፣ አይሁዳውያንን፣ ሙሥሊሙን፣ እንዲሁ የተለያየ የክርስትና አንጃ እና ጎጥ"Denomination" ያካተተች አገር እንጂ ለኦርቶዶክስ እውነተኛ እናት ለተቀረው የእንጀራ እናት አይደለችም። ዋቄፈታውን፣ አይሁዳውያንን፣ ሙሥሊሙን፣ እንዲሁ የተለያየ የክርስትና አንጃ እና ጎጥ ከጨዋታ ውጪ በማድረግ "ኦርቶዶክስ የአገር ባለቤት ናት" የሚል ትርክርት አሁንም የሐሰት ትርክት ነው፥ አገሪቱ ከሃይማኖት በገለልተኛ አስተሳሰብ"Secularism" መንግሥት እስከተመራች ድረስ አንድ ሰው የአገር ባለቤት ለመሆን ሃይማኖት መስፈርት አይሆንበትም። "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" የሚል የሐሰት ትርክት የተቀበረ እና ደሴታውያን ይህንን የሐሰት ትርክት ሊያንሰራሩ ቢሞክሩም በአገር ግንባታ እና በብሔራዊ መግባባት ትርክቱ እየተደቆሰ ነው። ለማንኛውም እንደ አንድ ሙሥሊም የሐሰት ትርክትን አጋልጠን ትክክለኛውን ንግግር መናገር ይገባናል፦ 33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ትክክለኛውን ንግግር ተናገሩ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا የሐሰት ትርክት ሲተረክ የሐሰትን ቃል ራቁ! እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ! ከእውነተኞቹ ጋር ኹኑ፦ 22፥30 ከጣዖታት እርኩሰት ተጠንቀቁ! የሐሰትን ቃል ራቁ፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ 9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ! ከእውነተኞቹ ጋር ኹኑ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ ከላይ የቀረበው መጣጥፍ "ትክክል አይደለም" የሚል ካለ በማስረጃ መሞገት ይቻላል፥ እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ እና በዕውቀት ንገሩኝ፦ 2፥111 እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ" በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ 6፥143 እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ" በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
ሐሠን እና ሑሠይን ወንድማማቾች በተባሉበት ሒሣብ ኢሥማዒል እና ኢሥሓቅ ወንድማማቾች ተብለዋል፥ ኢብራሂም ለሐሠን እና ለሑሠይን አባት የተባለው በዝርያ ደረጃ እንጂ በመውለድ ደረጃ እንዳለሆነ ሁሉ ኢብራሂም ለየዕቁብ "አባት" የተባለው የልጅ ልጁ ስለሆነ ብቻ ነው። ኢብራሂም ለዩሡፍ አባት ተብሏል፦ 12፥38 የአባቶቼን የኢብራሂምን፣ የኢሥሓቅን እና የየዕቁብን ሃይማኖት ተከትያለሁ"*፡፡ وَاتَّبَعْتُ مِلَّةَ آبَائِي إِبْرَاهِيمَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ ዩሡፍ ወላጁን የዕቁብን፣ አያቱን ኢሥሓቅን እና ቅድመ-አያቱን ኢብራሂምን "አባቶቼ" ብሏል፥ ኢሥሓቅ ለዩሡፍ አያቱ መሆኑ መገለጹ እና የዕቁብ ለኢሥሓቅ ልጅ መሆኑ መገለጹ በራሱ ኢብራሂም የየዕቆብ ወላጅ እንዳልሆነ ማሳያ ነው፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 56 አቢ ዑመር"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የክቡር ልጅ፣ የክቡር ልጅ፣ የክቡር ልጅ ክቡር ነው። ሰላም በእነርሱ ላይ ይሁን! የየዕቆብ ልጅ፣ የኢሥሓቅ ልጅ፣ የኢብራሂም ልጅ ዩሡፍ ነው"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ " الْكَرِيمُ ابْنُ الْكَرِيمِ ابْنِ الْكَرِيمِ ابْنِ الْكَرِيمِ يُوسُفُ ابْنُ يَعْقُوبَ بْنِ إِسْحَاقَ بْنِ إِبْرَاهِيمَ ـ عَلَيْهِمُ السَّلاَمُ ". ይህ ሐዲስ የዕቁብ ለኢሥሓቅ ልጅ መሆኑ ፍትንውና ቁልጭ አድርጎ ካሳየ ከዚህ በላይ ማስረጃ ምን ትፈልጋላችሁ? "ቁርኣን የዕቁብ የኢብራሂም ልጅ እና የኢሥሓቅ ወንድም ይላል" የሚለው ውኃ የማያነሳ እና የማይቋጥር ቅሪላ፣ እንኩቶ፣ አንኮላ ሙግት ነው። ይልቁንስ አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም ኢሥሓቅን ልጅ እንዲሁ የዕቁብን የልጅ ልጅ አርጎ ከመስጠትም ባሻገር ኢብራሂምን፣ ኢሥሓቅን እና የዕቁብን ነቢይ እንዳደረጋቸው ይናገራል፦ 19፥49 *"እነርሱንም ከአላህ ሌላ የሚያመልኩትት በራቀ ጊዜ ለእርሱ ኢሥሓቅ እና የዕቁብን ሰጠነው፥ ሁሉንም ነቢይ አደረግንም"*፡፡ فَلَمَّا اعْتَزَلَهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ وَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا نَبِيًّا "ሁሉንም ነቢይ አደረግንም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! የዕቆብ ወሕይ የሚመጣለት ነቢይ ስለነበረ ከነ ልጆቹ አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት የሚያመልኩ ሙሥሊሞች ነበሩ፦ 2፥133 *"የዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ፦ "ከእኔ በኋላ ማንን ታመልካላችሁ? ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? እነርሱም፦ አምላክህን እና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢሥማዒልን እና የኢሥሓቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለእርሱ ፍፁም ታዛዦች ኾነን እናመልካለን" አሉ"*፡፡ أَمْ كُنتُمْ شُهَدَاءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ الْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِن بَعْدِي قَالُوا نَعْبُدُ إِلَـٰهَكَ وَإِلَـٰهَ آبَائِكَ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ إِلَـٰهًا وَاحِدًا وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ የዕቆብ ልጆች የሚያመልኩት የአባታቸውን የየዕቁብን፣ የኢሥማዒልን፣ የኢሥሓቅን እና የኢብራሂምን አምላክ ነው፥ ይህንን አንድ አምላክ ስለሚያመልኩ እኛ ለአሏህ "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ኾነን እናመልካለን" አሉ። ስለዚህ ቁርኣን ላይ ሕጸጽ እና ግድፈት ከምትፈልጉ ይልቅ የነቢያትን አምላክ በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
ነቢዩ የዕቁብ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 21፥72 *"ለእርሱም ኢሥሓቅን እና የዕቁብን ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው፡፡ ሁሉንም መልካሞች አደረግን"*። وَوَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ نَافِلَةً ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا صَالِحِينَ በቁርኣን ውስጥ ስማቸው ከተጠቀሱት ከሃያ አምስቱ ነቢያት አንዱ የኢሥሓቅ ልጅ የዕቁብ ነው፥ አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም ኢሥሓቅን ልጅ እንዲሁ የዕቁብን የልጅ ልጅ አድርጎ ሰቶታል፦ 29፥27 *"ለእርሱም ኢሥሓቅን እና የዕቆብን ሰጠነው፥ በዘሩም ውስጥ ነብይነትን እና መጽሐፍን አደረግን"*፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَجَعَلْنَا فِي ذُرِّيَّتِهِ النُّبُوَّةَ وَالْكِتَابَ 21፥72 *"ለእርሱም ኢሥሓቅን እና የዕቆብን ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው፡፡ ሁሉንም መልካሞች አደረግን"*። وَوَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ نَافِلَةً ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا صَالِحِينَ ይህ እንዲህ በእንዲህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች፦ "ቁርኣን የዕቁብ የኢብራሂም ልጅ እና የኢሥሓቅ ወንድም በማድረግ ታሪኩን አዛብቷል" በማለት ቁርኣንን ሊያጠለሹ ይሞክራሉ፥ እኛም እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደረሳችሁ የትኛው ኃይለ-ቃል ነው? ስንል እነርሱም፦ "ለኢብራሂም ኢሥሓቅን እና የዕቆብን ሰጠነው" ስለሚል ይላሉ። "ለእርሱም ኢሥሓቅን እና የዕቆብን ሰጠነው" በሚል ኃይለ-ቃል ውስጥ የዕቁብ የኢብራሂም ልጅ እና የኢሥሓቅ ወንድም ስለመሆኑ የሚያሳይ ምንም ሽታው የለም፥ ከዚያ ይልቅ ኢሥሓቅ የየዕቁብ አባት እንደሆነ ተገልጿል፦ 2፥133 *"የዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ፦ "ከእኔ በኋላ ማንን ታመልካላችሁ? ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? እነርሱም፦ አምላክህን እና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልን እና የኢሥሓቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለእርሱ ፍፁም ታዛዦች ኾነን እናመልካለን" አሉ"*፡፡ أَمْ كُنتُمْ شُهَدَاءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ الْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِن بَعْدِي قَالُوا نَعْبُدُ إِلَـٰهَكَ وَإِلَـٰهَ آبَائِكَ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ إِلَـٰهًا وَاحِدًا وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ እዚህ አንቀጽ ላይ የዕቁብ ልጆች ለአባታቸው ኢሥሓቅ አባትህ ብለውታል። እናንተ እንደምትቀጥፉት ኢሥሓቅ ለየዕቁብ ወንድም ከሆነ ወንድም አባት እንዴት ሊባል ይችላል? ኢሥማዒል የየዕቁብ አጎት ስለሆነ አባት ሊባል ይችላል፥ ምክንያቱም ኢሥማዒል እና ኢሥሓቅ ወንድማማቾች ናቸውና፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 45 ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ለሐሠን እና ለሑሠይን ኢሥቲዓዛህ እያረጉ እንዲህ ይሉ ነበር፦ "አባታችሁ ኢብራሂም ለኢሥማዒል እና ለኢሥሓቅ፦ "ፍጹም በሆነው በአሏህ ቃላትን ከሁሉም ሸይጧን፣ ከመርዛማነት እና ከሸረኛ ዓይን ኢሥቲዓዛህ አረጋለው" ይል ነበር*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يُعَوِّذُ الْحَسَنَ وَالْحُسَيْنَ وَيَقُولُ " إِنَّ أَبَاكُمَا كَانَ يُعَوِّذُ بِهَا إِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ، أَعُوذُ بِكَلِمَاتِ اللَّهِ التَّامَّةِ مِنْ كُلِّ شَيْطَانٍ وَهَامَّةٍ، وَمِنْ كُلِّ عَيْنٍ لاَمَّةٍ ".
ሑሉል በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 87፥1 ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى "ሑሉል" حُلُول ማለት "አምላክ ሁሉ ነገር ነው፥ በሁሉ ነገር ውስጥ ነው" የሚል እሳቤ ነው፥ ይህ እሳቤ በኢሥላም ሺርክ ውስጥ ይመደባል። "ፓንቴይዝም"pantheism" የሚለው ቃል የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ፓን" እና "ቴዎስ" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "አምላክ ሁሉ ነገር ነው"God is all thing" ማለት ነው። "ፓን" πᾶν ወይም "ፓስ" πᾶς ማለት "ሁሉ ነገር" ማለት ነው፥ "ፓን" πᾶν ተሳቢ ቅጽል ገላጭ ሲሆን "ፓስ" πᾶς ደግሞ ባለቤት ቅጽል ገላጭ ነው። "ቴዎን" θεὸν ወይም "ቴዎስ" θεός ማለት "አምላክ" ማለት ነው፥ "ቴዎን" θεὸν ተሳቢ ስም ሲሆን ቴዎስ" θεός ደግሞ ባለቤት ስም ነው። "አምላክ ሁሉ ነገር ነው፥ በሁሉ ነገር ውስጥ ነው" የሚለው እሳቤ በጥንት ጊዜ በሕንድ፣ በግብፅ፣ በባቢሎን፣ በግሪክ እና በሮም የነበረ አሳብ ነው፥ የሚያሳዝነው ጳውሎስ ከእነዚህ ዐረማዊ እሳቤ ወስዶ አምላክ ሁሉ ነገር እንደሚሆን እና በሁሉ ነገር እንደሚሆን ተናግሯል፦ 1 ቆሮንቶስ 15፥28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን አምላክ "ሁሉ" "በሁሉ" ይሆን ዘንድ" በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል። ὅταν δὲ ὑποταγῇ αὐτῷ τὰ πάντα, τότε καὶ αὐτὸς ὁ Υἱὸς ὑποταγήσεται τῷ ὑποτάξαντι αὐτῷ τὰ πάντα, ἵνα ᾖ ὁ Θεὸς πάντα ἐν πᾶσιν. እዚህ አንቀጽ ላይ "ሁሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ፓንታ" πάντα ሲሆን "ሁሉ ነገር"all thing" ማለት ነው፥ "አምላክ ሁሉ ነገር ይሆን ዘንድ" "አምላክ በሁሉ ነገር ይሆን ዘንድ" የሚለው አሳብ ከጥንቱ ፓጋን የተቀዳ ነው። "ፈጣሪ በሁሉ ነገር ውስጥ ይገኛል" የሚለው እሳቤ "ምሉዕ በኲለሄ" ይሉታል፥ እንደ ክርስትናው "ፈጣሪ መንፈስ ነው፥ በመንፈሱ ሁሉን የሞላ ነው" ይላሉ። በመንፈሱ ሁሉም ነገር ውስጥ ካለ "የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ" ስለሚል ጠንቋይ ቤት፣ ድግምት ቤት፣ ሰይጣን ውስጥ እና የሰይጧን ቤት ካለ በእነዚያ ቦታ አርነት አለን? 2 ቆሮንቶስ 3፥17 ጌታ ግን መንፈስ ነው፥ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። አምላክ ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም፥ አምላክ ሁሉም ቦታ ውስጥ ካለ የመንፈሳዊ ጨለማ ሆነ የሌሊት ጨለማ እና ሰይጣን እንዴት ሊኖሩ ቻሉ? 1 ዮሐንስ 1፥5 አምላክ ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም። መዝሙር 139፥12 ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፥ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው። "አምላክ ሁሉ ነገር ውስጥ አለ" ሲባል የሴት ብልት ውስጥ፣ የሴት ማኅፀን ውስጥ፣ የሰው ሆድ ውስጥ፣ ሽንት ቤት እና ሰይጣን ውስጥ አለን? "አምላክ ሁሉ ነገር ውስጥ አለ" ከተባለ ሰው በጥፊ ሲመታ መለኮት በሥጋ ተመታ እንላለልን? አምላክ ሥጋ ሆነ እና በሥጋ ተደበደበ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ሞተ የሚባለው ትምህርት "ኢቲሓድ" اِتِّحَاد ሲባል በክርስትናው ተሠግዎት"incarnation" ይባላል፥ ይህ ትምህርት ከሑሉል የተቀዳ ሲሆን ሺርክ ነው። አምላካችን አሏህ ፈጣሪ ነው፥ ከፍጥረቱ ጋር በባሕርያቱ ግኑኝነት ቢኖረውም ከፍጥረቱ ውጪ የሚኖር ነው። በፍጥረቱ ውስጥ የለም፥ ፍጥረቱን ያካበበ እንጂ በፍጥረቱ ውስጥ የተካበበ አይደለም። እርሱ ከፍጥረቱ መካከል ማንንም አይመስልም፥ እርሱ ሁሉ ነገር ወይም በሁሉ ነገር ውስጥ ሳይሆን ከሁሉ ነገር በላይ ያለ አምላክ ነው፦ 87፥1 ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى "አምላክ ሁሉ ነገር ነው፥ በሁሉ ነገር ውስጥ ነው" የሚሉትን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
ዕሩቅ ብእሲ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 3፥47 ፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ "ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ ٱللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ ۚ إِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًۭا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ በግዕዝ "ዕሩቅ" ማለት "ብቻ" ማለት ነው፥ "ብእሲ" ማለት "ተባዕት ሰው" "ወንድ" "ጎልማሳ" ማለት ሲሆን "ብእሲት" ማለት ደግሞ "አንስታይ ሰው" "ሴት" "ጎልማሲት" ማለት ነው። በጥቅሉ "ዕሩቅ ብእሲ" ማለት "ሰው ብቻ" ማለት ሲሆን በዐበይት ክርስትና ኢየሱስ የመለኮት ማንነት እና ምንነት ከመዋሐዱ በፊት የነበረው የሰው ማንነት እና ምንነት "ዕሩቅ ብእሲ" ይባላል፦ ሉቃስ 1፥31 እነሆም ትፀንሻለሽ "ወንድ ልጅም" ትወልጃለሽ፥ ስሙንም "ኢየሱስ" ትዪዋለሽ። "ወንድ" የሥጋ መደብ እና የአንስታይ አንቀጽ ሲሆን የሚገረዝ ወንድ ነው፥ "ትፀንሻለሽ" የሚለው በራሱ ፅንስ ፍጡር መሆኑን አመላካች ነው። ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ኢየሱስ "ፍጡር" እንደሚባል ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 19 “ከሴት በሥጋ ስለተወለደ "ፍጡር" እንላለን”። ዐማርኛ ላይ "ሰው" ብለው ቢያስቀምጥም ግዕዙ “ንብሎ "ፍጡረ" እስመ ውእቱ ተወልደ በሥጋ እምብእሲት” በማለት አስቀምጦታል፥ "ፍጡረ" ማለት "ፍጡር" ማለት ነው። በአንድ ወቅት "ኢየሱስ ፍጡር ነው" ብዬ ይህንን ጥቅስ ስጠቅስ "ፍጡር አይልም፥ ወሒድ ዋሽቷል" በማለት የኦርቶዶክስ መምህራን ሲወርፉኝ ከርመው በኃላ ላይ ሃማኖተ አበውን በግዕዝ ሲመረምሩ ብዙ ቦታ ኢየሱስ ፍጡር መሆኑን ሲረዱ "ፍጡር ነው" የሚሉ የኦርቶዶክስ መምህራን "ፍጡር አይባልም" ከሚሉ የኦርቶዶክስ መምህራን እስከ ዛሬ እየተወዛገቡ ነው። አል ሐምዱ ሊላህ የሙሥሊም ዐቃቢያን የኦርቶዶክስ መምህራንን ዓይናቸውን ገለጡላቸው፥ ይህ ውዝግብ ለብዙዎች መሥለም ምክንያት እየሆነ ነው። ኤጲፋኒዮስ ዘቆጵሮስ ኢየሱስ የተፈጠረ ሰው መሆኑን ፍንትው አርጎ ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 56 ቁጥር 20 "ተፈጠረ" መባሉ ሰው በመሆኑ ምሥጢር ይፈጸማል"። ኤጲፋኒዮስ ዘቆጵሮስ በተጨማሪም ኢየሱስ የተፈጠረ ሰው እንደሆነ ቁልጭ አርጎ ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 56 ቁጥር 21 "ሰው ስለሆነ "ፍጡር" ቢባል ወዲህ በር ተባለ"። ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በተመሳሳይ “ሥጋ ስለሆነ ፍጡር ይባላል” ብሏል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 35 ቁጥር 6 “ሥጋ ስለሆነ ፍጡር ይባላል”። ግዕዙ “ወዓዲመ ይትበሀል ፍጡረ በእንተ ዘኮነ ሥጋ” በማለት አስቀምጦታል። ኢየሱስ በትንቢት መነጽር "ከማኅፀን ጀምሮ "የሠራኝ" በማለት እግዚአብሔር እርሱን እንደፈጠረው ይናገራል፦ ኢሳይያስ 49፥5 ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ "የሠራኝ" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡— ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ኢሳይያስ 49፥5 ያለውን ጥቅስ ይዞ የኢየሱስ ፍጡርነት እንቅጩን ፍርጥ አርጎ ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 76 ቁጥር 19 “ዳግመኛም መድኅን ክርስቶስ ከድንግል ስለመወለዱ በኢሳይያስ አፍ “ብዙ ሥራ እሠራ ዘንድ የያዕቆብንም ወገን አጸና ዘንድ አስራኤልንም አንድ አደርግ ዘንድ "በድንግል ማኅፀን ተፈጠርኩ" አለ”። ዐማርኛው ላይ "ተፀነስኩ" ቢሉትም ግዕዙ ግን "ተፈጥረ" ይለዋል፥ "ተፈጥረ" ማለት "ተፈጠርኩኝ" ማለት ነው። ነገሩ ፅንስ ፍጡር ነውና ቄርሎስ ዘእስክንድርያ በመቀጠል ኢየሱስ "በማሕጸን "የፈጠረኝ" እግዚአብሔር" ማለቱን አጽንዖት ሰጥቶ ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ ምዕራፍ 76 ቁጥር 21 “ዳግመኛም የያዕቆብን ወገን አንድ ለማድረግ፤ እስራኤልን ለማዳን አገልጋይ እሆነው ዘንድ "በማሕጸን "የፈጠረኝ" እግዚአብሔር" እርሱ ይወደኛልና”። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 25 "በእውነት ሰው እንደመሆኑ "እግዚአብሔር ፈጠረኝ" ይላል"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 26 "ሰው ፍጡር ነውና ስለዚህ እርሱ ሰው ስለሆነ "እግዚአብሔር ፈጠረኝ" ይላል"። እንግዲህ ኢየሱስ "እግዚአብሔር ፈጠረኝ" ካለ ማኅፀን ውስጥ የተሠራ ነገር አምላክ ካልሆነ የተሠራውን ሰው ማምለክ ባዕድ አምልኮ ነው፦ ኢሳይያስ 43፥10 ከእኔ በፊት "አምላክ አልተሠራም" ከእኔም በኋላ አይሆንም። ፈጣሪ "አምላክ አልተሠራም" እያለ "ፈጣሪ ፍጡር ሆነ" "ፈጣሪ ተፈጠረ" "ማኅፀን ውስጥ ከተፈጠረው ዕሩቅ ብእሲ ጋር ፈጣሪ አንድ ሆነ" የሚል ትምህርት ምንኛ ክፉ ትምህርት ነው? ሳውርዮስ ዘአንጾኪያ "ፍጡር ከፈጣሪ ጋር አንድ ሆነ" የሚል ተስተምህሮት አለው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 112 ቁጥር 32 "ፍጡር ከፈጣሪው ጋር አንድ ሆነ"። "ፈጣሪ እና ፍጡር አንድ ሆነ" የሚል ትምህርት "ወሕደቱል ዉጁድ" وَحْدَة الوُجُود ሲባል በኢሥላም ኢንካር የተደረገ ነው። ከዚያ ይልቅ ዒሣ መሢሑ መርየም ማኅፀን ውስጥ የተፈጠረ ፍጡር እና በምንነቱ ሰው ብቻ ነው፦ 3፥47 ፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ "ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ ٱللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَآءُ ۚ إِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًۭا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ ይህንን ዕሩቅ ብእሲ የምታመልኩ በንስሓ ወደ አሏህ እንድትመጡ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
ወደ ፊት ብቻ! ~ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሁሉም አይነት ሰው አለ። ሞቅ ያለ ተሳትፎ ካለን በተለያዩ አካላት እንገመታለን። እንገመገማለን። እንተመናለን። በአቋም የሚመስለን እንዳለ ሁሉ የሚቃረነንም ብዙ ነውና ዋጋችንና ቦታችን ከሰው ሰው ይለያያል። * ከፊሉ የምትፅፈው/ የምትናገረው ነገር አይጥመውም። ከፊሎቹ ጋር ደግሞ እውነታው ይለያል። * ከፊሉ ቀድሞ በጥላቻ ስለተሞላ የኔ የሚለው ሰው ቢናገረው የሚደግፈውን ብትናገር እንኳ ሰበብ ፈልጎ ያብጠለጥልሃል። * ከፊሉ ዘንድ ሚዛናዊ ነህ። ሌላው ዘንድ ደግሞ ፅንፈኛ፣ ፍርደ ገምድል ነህ። * ከፊሉ ዘንድ አስተዋይና በሳል ነህ። ሌላው ዘንድ የሃገርና የወቅት ተጨባጭ ያልገባህ ጥሬ ነህ። * ከፊሉ ዘንድ አዛኝ ነህ። ከፊሉ ዘንድ ጨካኝ ነህ። * ከፊሉ ዘንድ እየበሰልክ ነው። ሌላው ዘንድ እየባሰብህ ነው። * ከፊሉ ዘንድ ቡድንተኛ ነህ። ሌላው ዘንድ ውግንናህ ለሐቅ ብቻ ነው። የሚርቅህ ብቻ ሳይሆን የተሻለ የሚቀርብህ ራሱ የበለጠ ሊጠላህ እና ንግግርህንም ዝምታህንም ያላሰብከውን ትርጉም እየሰጠ ሊያጣጥልህ ይችላል። ቢሆንም ታገስ። ሞራልህ ሳይጎዳ ወደፊት ገስግስ። የተራራቁ አመልካከቶች በበዙበት፣ ከዒልምና ተርቢያ የራቀ ትውልድ እንደ አሸን በፈላበት፣ በሺርክና መልከ ብዙ ቢድዐዎች ላይ የተዘፈቀው ወገን በበዛበት፣ ይሄ ሁሉ ወፈ ሰማይ በነፃነት የሚናገርበት መድረክ አግኝቶ ከየትኛውም አካል ጉንተላ ሳያገኘኝ ሰላም እጓዛለሁ ማለት ዘበት ነው፣ አጉል ምኞት። ስለዚህ ደዕዋ ላይ ያለኸው ወገኔ ሆይ! በደዕዋህ ላይ ትችትና ዘለፋ አያስደንብርህ። ቲፎዞና ጭብጨባም አያቅልጥህ። ሰዎች የሚሰጡህ ደረጃም አይድነቅህ። ሁሉም አላፊ ነው። ይልቅ አላህን ብቻ አስብ። በኢኽላስ ተጓዝ። በኢኽላስ ለካ! በኢኽላስ ቁረጥ። ጫጫታ ሳይበግርህ ወደፊት ብቻ። እልህ እንዳይሾፍርህም ሚዛንህን ጠብቅ። ዝቅ ብለህ ጀምር። ወርደህ ስራ። ተግተህ ጣር። መስመር ይዘህ፣ አላህን እያሰብክ እስከተጓዝክ ድረስ መንናቅ አያሳምምህ። ዝናም አያንጠባርህ። በየትኛውም ሁኔታ ከደዕዋ እንዳትርቅ። እንዳትርረታ። * ያያያዝኩት ግጥም የኔ አይደለም። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
አንድ ሰው በሰዎች ፊት ልክ እንደ ጀነት ሰዎች ሥራ ይሠራል ከእሳት ሰዎች ነው፥ አንድ ሰው በሰዎች ፊት ልክ እንደ እሳት ሰዎች ሥራ ይሠራል ከጀነት ሰዎች ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 19 ሠህል ኢብኑ ሠዕድ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንድ ሰው በሰዎች ፊት ልክ እንደ ጀነት ሰዎች ሥራ ይሠራል ከእሳት ሰዎች ነው፥ አንድ ሰው በሰዎች ፊት ልክ እንደ እሳት ሰዎች ሥራ ይሠራል ከጀነት ሰዎች ነው"። عَنْ سَهْلِ بْنِ سَعْدٍ السَّاعِدِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ الرَّجُلَ لَيَعْمَلُ عَمَلَ أَهْلِ الْجَنَّةِ فِيمَا يَبْدُو لِلنَّاسِ وَهُوَ مِنْ أَهْلِ النَّارِ . وَإِنَّ الرَّجُلَ لَيَعْمَلُ عَمَلَ أَهْلِ النَّارِ فِيمَا يَبْدُو لِلنَّاسِ وَهُوَ مِنْ أَهْلِ الْجَنَّةِ " . በእርግጥ አንድ ሰው የጀነት ሰዎችን ሥራ ለረጅም ጊዜ ይሠራ እና ከዚያም ኢማን ስለሌለው ሥራው በእሳት ሰዎች ሥራ ይደመደማል፥ በተቃራኒው አንድ ሰው የእሳት ሰዎችን ሥራ ለረጅም ጊዜ ይሠራ እና ከዚያም ኢማን ስላለው ሥራው በጀነት ሰዎችን ሥራ ይደመደማል፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 18 አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በእርግጥ አንድ ሰው የጀነት ሰዎችን ሥራ ለረጅም ጊዜ ይሠራ እና ከዚያም ሥራው በእሳት ሰዎች ሥራ ይደመደማል፥ አንድ ሰው የእሳት ሰዎችን ሥራ ለረጅም ጊዜ ይሠራ እና ከዚያም ሥራው በጀነት ሰዎችን ሥራ ይደመደማል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ الرَّجُلَ لَيَعْمَلُ الزَّمَنَ الطَّوِيلَ بِعَمَلِ أَهْلِ الْجَنَّةِ ثُمَّ يُخْتَمُ لَهُ عَمَلُهُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ وَإِنَّ الرَّجُلَ لَيَعْمَلُ الزَّمَنَ الطَّوِيلَ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ ثُمَّ يُخْتَمُ لَهُ عَمَلُهُ بِعَمَلِ أَهْلِ الْجَنَّةِ " .
◇ ከሴቶች ከፊት ሀፍረ-ገላ የሚወጣ ንፋስ ከሴቶች ከፊት ሀፍረተ-ገላ የሚወጣ ንፋስ ከዑለማኦች ትክክለኛው አቋም ውዱእ አያስፈታም (አያፈርስም)። ففرق بين الريح الذي يخرج من الدبر وبين يخرج من القبل. ከኋላ መቀመጫ የሚወጣው ንፋስ እና ከፊት ሀፍረተ-ገላ የሚወጣው ፍርዱ ይለያያል። ሴት ልጅ በመትቀመጥ ጊዜ ማህፀኖ ይሰበሰባል በምትቆም ጊዜ ይለጠጣል የዚህን ጊዜ አየር (ንፋስ)…