ምስለ አድባራት ወገዳማት
Статистика"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" "ስለ ቅዱሳን እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል" ሊቁ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 16
- 1/48двое суток
- 18
- 1/72трое суток
- 19
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? 📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ 📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ 📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ 📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ 📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን 📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው እና የሌሎችንም ........... የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻 👇👇👇 https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
🎉ከ17 ደቂቃ በኃላ ይጠፋል የ 200 ብር ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ! የንኤስ_አንበሳ የተባለው ማን ነው ?
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ✞✞ገብርኤል ስለው ሰምቶ✞✞ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ 👏ገብርኤል ገብርኤል ሰለው ሰምቶ 👏መጣወደኔ ፈጥኖ 👏ሰንሰለቴን በጠሰው የአንበሶቹን አፍ ዘግቶ 👇👇👇1👇👇👇 ገብርኤል ስጋዬ ሳይረግፍ በአናብስቱ ጥፍር '' ''ታድጎኛል ምልጃው የመላኩ ፍቅር '' ''በረሐብ ለነደዱ አናብስት ሲጥሉኝ '' ''አንተ አለኸኝና ክንፎችህ ከለሉኝ 👇👇👇2👇👇👇 ገብርኤል ከአፎቹ ሲመዘዝ የጠላቴ ሰይፍ '' ''አጽንቶ ይዞኛል ፍሬዬ ሳይረግፍ '' ''አደገድጋለሁ አለኝና ፍቅሩ '' ''በእሳት ክንፉ ታጥራል የደጄ ድንበሩ 👇👇👇3👇👇👇 ገብርኤል በሰይፍ ተመትራል የክፉዎች ብክነት '' ''ሐብሉ ተበጣጥሷል ያመጡት ሰንሰለት '' ''ከቅድሱ ድንጋይ ሕይወት ከሚያፈልቀው '' ''እንዳልለይ ረዳኝ ክብሬን ከፍ አረገው 👇👇👇4👇👇👇 ገብርኤል አለው ልዩ ስልጣን በአምላክ የተሰጠው '' ''ይመጣል ወደኛ እሳቱን ሊያጠፋው '' ''እኛም እናምናለን ሰምተናል አይተናል '' ''የመላዕክት አለቃ ከአምላክ ያማልዳል 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን ይዘምሩ #ተዋሕዶ_ለዘለዓለም_ትኑር 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @yemezmurdebiter @yemezmurdebiter @yemezmurdebiter @yemezmurdebiter
አሰርገዋ ለኢትዮጲያ በውብ ቅኔ እያለ ሃሌ ሉያ ክቡር ስሙ የማይረሳ ነው ቅዱስ ያሬድ ዝክሩ ዘላለም ነው/2×/ አዝ አሰርገዋ ተነጥቆ በመንፈስ አሰርገዋ እስካርያም መቅደስ አሰርገዋ የሰማዩን ዜማ አሰርገዋ ለምድሪቱ አሰማ አዝ አሰርገዋ ከመላዕክት እንጀራ አሰርገዋ የሰው ልጅ ተጋራ አሰርገዋ ያሬድ ማህሌታይ አሰርገዋ ሲያወርደው ከሰማይ አዝ አሰርገዋ የደብረ ቅዱሱ አሰርገዋ አብሮን ነው መንፈሱ አሰርገዋ አይሻርም ዜማው አሰርገዋ ያሬድ የዘመረው አዝ አሰርገዋ ከኢትዮጲያ ማህፀን አሰርገዋ የተገኘው ካህን አሰርገዋ እናቱን አስጌጣት አሰርገዋ በዜማ በረከት አዝ አሰርገዋ መአሪረ ቃል አሰርገዋ ጥኡመ ልሳን አሰርገዋ መሰረተ ዜማ አሰርገዋ ሚስጥር የሚያሰማ አሰርገዋ ለኢትዮጲያ በውብ ቅኔ እያለ ሃሌ ሉያ ክቡር ስሙ የማይረሳ ነው ቅዱስ ያሬድ ዝክሩ ዘላለም ነው/2×/ መላከ ፀሃይ መኮንን ፍሥሐ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን ይዘምሩ ፤ ለተዋሕዶ እንጋደል 👇👇👇👇👇👇👇👇 @yemezmurdebiter @yemezmurdebiter @yemezmurdebiter
እግዚአብሔርን በንጹሕ ልቤ አመልካለሁ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እወዳለሁ የምትል እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ወንድሜ/እኅቴ ሆይ! ራስህን፣ ቤተ ክርስቲያንህንና ሀገርህን ማዳን ከፈለግህ የእነዚኽን ሰዎች እንቅስቃሴ በደንብ ተከታተልና ለመፍትሔው ምከር፦ 1. አቡነ አብርሃምና አቡነ ኤርምያስ ሌሎችም... 2. ጵጵስናን ለመቀበልና ቤተ ክህነቱን ለመቆጣጠር ሲል በዓላማ የመነኰሰው ቴዎድሮስ በለጠ (አሁን ላይ በየገዳማቱ እየዞረ ምን እየሠራ እንደኾነ ጠይቅ)፤ 3. ሄኖክ ኀይሌ (ከዳንኤል ክብረት የከፋ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ ትልቅ አጀንዳ የተሰጠው)፤ 4. "ሊቀ ሊቃውንት" የሚል ማዕረግ አስቀድመው በዓላማ የተቀበሉ እነ ስምዐ ኮነ (ወልድ አብን አምልኳል" (ሎቱ ስብሐት) ብለው የሚያምኑትን እነ አክሊልን አትናገሩ ካለ በኋላ ነው የተጋለጠው)፤ 5. የጉባኤ ቤት መምህራን መስለው የተማሩ ሊቅ መስለው በየሶሺያል ሚዲያው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች፤ 6. 7. 8. . . . ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንንም ሀገራችንን አሁን ላይ ከውጭ ኾነው የሚዋጓቸው የሉም። ምክንያቱም ውስጥ ድረስ ሰርስረው ገብተዋል። የቤተ ክህነቱንና የቤተ መንግሥቱን መዋቅር ጠርንፈው ይዘዋል። በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን "ታዋቂ" የሚባሉ ሰዎችን መልምለው ለእኩይ ዓላማ አሰማርተዋል። አሁን ላይ እያንዳንዱ ምልምል ኹሉ የየራሱ እኩይ ዓላማ አለው። ዋነኛዎቹ የ"one world order" ሥራ አስፈጻሚ መንግሥታት የኢትዮጵያ ትንሣኤ መቼ እንደኾነ ጠንቅቀው ያውቁታል። አሁን ያለው የዓለም ሥርዐት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል። ያ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ልዑላቸውን አንግሠው መላውን ዓለም ለልዑላቸው ለማስገዛት ከፍተኛ እርብርብ ላይ ናቸው። ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ግን የዚኽ ዓላማቸው እንቅፋት ናት። ስለዚኽ ቤተ ክርስቲያኒቱም ኾነኝ ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ትንሣኤ በፊት ቀድሞው መመታት አለባቸው። በትግራይና በአማራ ክልል የታወጀው ጦርነት አንዱ የዚኽ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ነው። እደግመዋለሁ በቅርቡ አሁን ያለው የዓለም ሥርዐት ሙሉ በሙሉ ይለወጣል። ስለዚኽ ያ ከመኾኑ በፊት የቻሉትን ኹሉ የጥፋት ጦራቸውን ይወረውራሉ። ከእነዚኽ የጥፋት ጦሮቻቸው ውስጥ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን "ታዋቂ" የሚባሉ ሰዎችን መልምለው ለእኩይ ዓላማ ያሰማሩ መኾኑን ሕዝቡ ሊገባው አልቻለም። የእኛ ነገሮችን መረዳት አለመቻል በራሱ አንድ ፈተና ኾኗል። ይመጣ ዘንድ ያለው አስከፊ ጥፋት ተረድቶ ራሱን፣ ሃይማኖቱንና ሀገሩን እንዳይጠብቅ ወጣቱን በ"ታዋቂ" ሰዎች አማካኝነት አስቀድመው አጀዝበውታል። ሞራሉ ላሽቋል፤ የሀገር ፍቅር እንዳይኖረው አድርገውታል፤ የዲያብሎስና የአጋንንቱ ስም እየተደገመበት የተፈጨ የሞቱ ሰዎች ዐፅም በሀገሪቱ ላይ አስቀድሞ የተበተነ አፍዝ አደንግዝ መላውን ሕዝብ ያደነዘዘው ቢኾንም የአሁኑ ወጣት በተለይ የኦርቶዶክሳዊው ወጣት ድንዛዜ ግን እጅግ የከፋ ነው። ከሚመጣው የጥፋት ወጀብ በመጀመሪያ ራስህን ማዳን፤ ቀጥሎ ቤተ ክርስቲያንህንና ሀገርህን ማዳን የምትፈልግ እውነተኛው ኦርቶዶክሳዊ እኅት ወንድሜ ሆይ! የግለሰብ ተከታይና አድናቂ መኾንህን ትተህ ከሚተርፉት ወገን ለመኾን ተዘጋጅ!!! የእግዚአብሔር መቅሠፍት (አስከፊ ወረርሽኝ፣ በሽታ፣ ረኀብ) እና የአሕዛብ ሰይፍ በቅርቡ የጥርጊያ ወጀብ ኾኖ ይመጣልሃልና ከተራፊዎች ወገን ትኾን ዘንድ የምትሻ ወገኔ ኹሉ በጊዜ ንቃ!!!
ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ መብዓ ጽዮን (ተክለማርያም) ትውልዳቸው በሰሜን ሸዋ ተጉለት ውስጥ እንደገብጣን በሚባል ቦታ አባታቸው ንቡረእድ ሀብተ ጽዮን እና ከእናታቸው ጽዮን ትኩና (ሒሩት) በ14ኛው መቶ ክፍለዘመን ተወለዱ። ደገኛ ጻድቅ ሲሆን ከታወቁበት ግብራቸው በሳምንት አርብ አርብ ኮሶ ይጠጡ ነበር። ጌታችንን ሀሞት እንዳጠጡት እያሰቡ፣ የደረሰበትን መከራ እና ሞቱን እያሰቡ የአንድ ሰው ክብደት ያህል ድንጋይ በጀርባቸው አዝለው እልፍ እልፍ ይሰግዱ ነበር። ከጽድቃቸው ብዛት የተነሳ መቋሚያቸውን ቢተክሉት ሎሚና ትርንጎ አፍርቷል። በየወሩ የመድኃኔዓለምን ዝክር አላፊና አግዳሚውን፣ ወጪ ወራጁን፣ የገበያውን ሰው ሁሉ ያበሉ እና ያጠጡ ነበር። አባታችን አባ መብዓጽዮን እጅግ አብዝተው በሚወዱትና በሚያከብሩት በዕለተ መድኃኔዓለም በጥቅምት 27 ያረፉ ሲሆን እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ሁልጊዜ ከመድኃኔዓለም ጋር ይታሰባሉ። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጻድቁ አባታችን አቡነ መብዓ ጽዮን በሰጣቸው ቃልኪዳን መሰረት ሁልጊዜ በዕለተ አርብ አርብ፣ በ21 በእመቤታችን ፣ በ27 በመድኃኔዓለም ቀናት ወደ ሲኦል እየወረዱ እልፍ እልፍ ነፍሳትን ያወጣሉ። ዓመታዊ በዓላቸው ጥቅምት 27 እረፍታቸው፣ ሐምሌ 12 (ፍልሰታቸው) በገዳማቸው ደብረ ማጢቆስ ይከበራል። ሌላኛው ገዳማቸው በትግራይ ሽረ አካባቢ ይገኛል። በመ/ር ወርቅዬ ታደለ የጻድቁ ገድል ያልታተመና በገዳማቸው የሌለ ሲሆን በዋሊስ ባጅ ታትሞ በእንግሊዝ ሀገር እንደሚገኝ ቀሲስ ዶክተር አምሳሉ በነቅእ መጽሐፋቸው ጠቅሰውታል። በሀገረ እንግሊዝ የምትገኙ ምዕመናን ከጻድቁ በረከት እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
3. ከድንጋይ ላይ ሁኖ ወርቅ ዘንግ ወርውሮ ያፈለቀው ማየ ጸሎት ማየ ዮርዳኖስ ብሎ የሰየመው 4. ቁመት ጨምራ ከመሬት ተነስታ እንደ ሰው አፍ አውጥታ የመሰከረችው ዋንጫ 5. ጻድቃኑ ይወቅጡበት የነበረ የድንጋይ ሙቀጫ 6. በማኅበራቸው ጊዜ ሲደግሱባቸው የነበሩ የድንጋይ ገበታዎች 7. ከሀገራቸው ከሮም ያመጡት ባለመስታወት ቋሚ ዕፀ መስቀል፡፡ 8. ርዕሰ ዮሐንስ የሚባል ነገሥታት ከነዘውዳቸው፥ ጳጳሳት ከነአክሊላቸውና ከነመስቀላቸው በዚያን ጊዜ የተሳሉበት ስዕል፡፡ 9. ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ በማህበረ ፃድቃን ዴጌውን ሆኖ ያስተማረበትና የጠመቀበትን በስዕል የሚያሳይ፡፡ 10. ይህ ገዳም በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት እንደተገደመና ገዳሙ ራሳቸው የገደሙት የራሳቸው መሆኑን በአክሱም መጽሐፍ ክብረ ነገሥት ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ መልክኦሙ ለጻድቃን ዘዴጎ፤ ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ዘሐዋዝ ጥቀ፤ ለዘይሰምእ በእዝኑ ወበኅሊናሁ ጥንቁቀ:: ጻድቃን ዘዴጎ እበይክሙ ተአውቀ፤ እመ በትህትና ማእከሌክሙ ረፈቀ፤ ሊቀ ጠቢባን ክርስቶስ ዘይሜህር ጽድቀ፡፡
# ማኅበረ_ዴጎ (ዶጌ) # ማኅበረ_ጻድቃናት )፤ # ጥር_29 #ቃል_ኪዳን_የተቀበሉበት፤ # ጥር_30 # ምስዋሮን_በተባለ_ቦታ_የተሰወሩበት_ዕለት_ነው ፡፡ ፠ማኅበረ ዴጎ ማለት የደጋጎች ሀገር ማለት ሲሆን የተባለበት ምክንያትም ቅዱሳን ስላሉበት ነው፡፡ በ365 ዓ.ም በአስፍሕ ወልደ አብርሃም ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ‹‹ ሮምያ›› ከምትባል መንደር የቅዱስ መጽሐፍ ቃል የሆነውን መሠረት አድርገው፤ 1ኛ ‹‹ ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት የነርሱ ናትና›› ያለውን 2ኛ ‹‹ አባቱንና እናቱን ሚስቱንና ልጆቹን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ብሎ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን አንብበው የዚህን ዓለም ጣዕም ጥቅም ንቀው ሃገራቸውን ትተው መንነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡ ፠ እነዚህም በአኵሱም ከተማ በስተሰሜን በሐውልቱ ጀርባ ቤተ ቀጢን በሚባል ስፍራ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህል እንደ ተቀመጡ በዚያም ምቾትና ድሎት ስለተሰማባቸው ለዚሁ ለዚሁማ ከሀገራችን ለምን ትተን መጣን? ስለዚህ ሱባዔ ገብተን በጾም በጸሎት ተወስነን የምንሄድበትን ቦታ በረከተ ነፍስ የምናገኝበትን ስፍራ እግዚአብሔር እንዲያሳየን እናመልክት ብለው ሱባዔ ገቡ ጾም ያዙ፡፡ ከሱባዔው በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልፃ ግማሾቹን እያንዳንዳቸው የሚኖሩበትን በዓት አመልክታቸው በዚያም በጾምና በጸሎት ፀንተው እንዲኖሩ ነገረቻቸው፡፡ ፠ ሦስት ሺህ/3000/ ያህሉ ደግሞ ከላይ ወደጠቀስነው ሄዱ፡፡ ከነርሱ የተቀሩት ደግሞ ወደ ቆየፃ ሓባር፣ ተድባ፣ አኮርየን፣ ተንስሓ፣ ደብረ አንሳ ወደ ተባሉ ቦታዎች ሄደዋል፡፡ ፠ ተጨማሪ ሦስት ሺ ደግሞ እዚያ ከነበሩት ጋርም ተደመሩ፡፡ ከዚያም የቅዱስ ጳውሎስና የቅዱስ ዮሐንስ መመሪያ ተከትለው ማለት ‹‹ከሁሉ ፍቅር ይበልጣል›› የሚለውን ጠብቀው በእምነት በፍቅር በአንድነት ፀንተው በየሳምንቱ እሑድ እሑድ ተዝካረ ሰንበትን ጠብቀው ማኅበር መጠጣት ጀመሩ፡፡ የማኅበረ ዴጎ ታሪክም ተቀየረ ፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በአምሳለ ነዳይ ድሀ መስሎ በመካከላቸው ተገኘ፡፡ ከእነርሱ ጋርም አንድ ማኅበርተኛ ሁኖ እንዲታወቅ ጠየቃችው፣ እነርሱም ፈቀዱለት እና አንዱ የማኅበሩ አባል ሆነ፤ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህልም ከነርሱ ጋር ሳይለይ ቆየ፡፡ በዚሁ ጊዜ ‹‹እስቲ ለኔም ተራ ስጡኝ እንደአቅሜ ዝክር ላውጣ፡፡›› አላቸው፡፡ በዚህ ግዜ ግን ድህነቱን አይተው ‹‹አይሆንም አንተ ድሀ ነህ ከኛ ጋር ሁነህ በዓሉን አክብር እንጂ ምን አለህና ነው የምትደግሰው ይቅርብህ›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹አይሆንም ስጡኝ እንጂ›› አላቸው እነርሱም ካልክማ ብለው ቀን ወስነው ሰጡት፡፡ ቀኑም ጥር 29 ነበር፡ ፠ ከማኅበርተኞቹ መካከል አሳላፊ ወይም ሙሴ ‹‹ሣይዳ ›› የሚባል ሰው ነበር፡፡ ይህም ሰው እንግዳና ድሀ ሰው ፈጽሞ አይወድም ነበርና ጌታችንም ከማኅበርተኞቹ መካከል ሲገኝ ደሀ መስሎ ስለነበር በጣም ይጠላው ነበር፡፡ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከነርሱ ጋር ሲቀመጥም አንድ ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፡፡ የሆኖ ሆኖ የጌታችን ማኅበር መድረሱ አልቀረም ደረሰ፡፡ እንደማኅበሩ ሥርዐት የወይን ጠጅ የሚጠመቅባቸውን ጋኖች የሚያጥበው ሙሴው /አሳላፊው/ ነው፡፡ ስለሆነም በሥርዐቱ መሠረት ጌታችን ሙሴውን ጠርቶ ጋኖችን እጠብልኝ አለው፡፡ አሳላፊውም በቁጣ ‹‹አንተ ቤትህ የማይታወቅ፤ ከየት አምጥተህ ማኅበር ልታደርግ ነው አንተ ብሎ›› በማለት አናንቆ አልታዘዝህም ብሎ ሄደ፡፡ ይህን የተመለከተው ጌታም አንድ እረኛ ጠርቶ ‹‹አንተ ልጅ ከብቶችህን እኔ እጠብቅልሃለሁና በዚህ ውሀ አምጣልኝ›› አለው፡፡ ትንሹ እረኛ ልጅ ገምቦውን ይዞ ትንሽ ወጣ እንዳለ ጌታ ዘወትር በሚቀመጥበት ድንጋይ ላይ ሆኖ ዘንጉን ወደ ልጁ አቅጣጫ ወረወረው፣ ዘንጉንም ከልጁ ፊት ሂዶ ተተከለ፡፡ ልጁንም ጠርቶ ዘንጉንም እንዲነቅለው አዘዘው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ዘንጉንም ቢነቅለው ውሀ ፈለቀ፡፡ ከርሱ ቀድተህ አምጣልኝ አለው፡፡ ልጁም ከዚህ ውሀ ቀድቶ አመጣለት ጋኖቹን አጠባቸው፡፡ ፠ በበዓሉ ቀን ማህበርተኞቹ ምን ሊያበላን ነው፣ ምን ሊያጠጣን ነው ሳይሉ ኹሉም ተሰበሰቡ፡፡ ጌታችንም በፊታቸው ጋኖቹን ቢባርካቸው የወይን ጠጅ ሞልተው ተገኙ፡፡ ፠ ቀድቶ ቢሰጣቸውና ቢቀምሱትም በጣም ግሩም ጣፋጭ ስለነበር እጅግ አደነቁ፡፡ እነርሱም ጌታን ከጻድቃን አንዱ ስለመሰላቸው ከእግሩ ላይ ወድቀው እስካሁን ድረስ ሳንበድልህ አልቀረንምና ይቅር በለን ብለው ለመኑት፡፡ ተነሱ ብሎ ካስነሳቸው በኋላ እናንተ ምንም አልበደላችሁም የጠየኳችን እድርጋችኋል የበደለኝ ግን አሳላፊው ነው በማለትና አንድም ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ አልሰጠኝምና አፈራርዱኝ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሙሴው/አሳላፊው/ የማያፍር ደፋርና ርጉም ስለነበር ‹‹ይህ ሰው ጌታችን በልቶ አልበላሁም ፣ ጠጥቶ አልጠጣሁም የሚል ስለሆነና ስለማይጠግብ ነው እንጂ እንዲያውም ለናንተ አንድ አንድ ዋንጫ ሲሰጣችሁ ለእርሱ ሁለት ሁለት ነበር የሚሰጠው ብሎ የሐሰት ቃል መለሰ፡፡ ፠ ጌታችንም እንግድያስ እኔ የጠጣሁበት ዋንጫ ትቅረብና ትመስክርብኝ አለው፡፡ በዚሁ ተስማምተው አሳላፊው/ሙሴው/ ሄዶ አንድ ሸራፋ ዋንጫ አምጥቶ በዚህ ነበር የሚሰጠውና የሚጠጣው ብሎ አቀረበ፡፡ ዋንጫዋም ከተቀመጠችበት አንድ ክንድ ከስንዝር ተነስታ ጽዋይቱን ስትመሰክር ‹‹ዓለማትን የፈጠረ አምላክ ምስክሬ ነው እኔ የያዝኩትን የወይን ጠጅ ዕቃ ሙሴም በእጆቹ አልያዝኩትም በከንፈሩ አልነካኝም በሌሎቹ ሰዎች እጅ ግን ተይዤ ያየን ነበር›› አለች ያን ጊዜ እንደ ዳታን እና አቤሮን ምድር ተከፈተችና ሙሴውን ከነልጁ ዋጠቻቸው፡፡ ፠ ማኅበረ ጻድቃንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ ተረድተው እንደገና ከእግሩ ወድቀው ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ለመኑት፡፡ ቀኑም ጥር 29 ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታ ካደረገላቸው በኋላ ስማችሁ የጠራ በስማችሁ ተዝካር ያወጣ በስማችሁ ድሆችን የረዳ፣ ያለበሰ፣ ያጎረሰ፣ የሰጠ፣ የመጸወተ፣ ቤተ ክርስትያናችሁን የሠራ፥ ያሠራ፣ እሰከ 14 ትውልድ ደረስ ምሬላችኋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው፡፡ ይህችን ቦታችሁ መጥቶ የሳመ እየሩሳሌም እንደሳመ አድርጌላችኋሁ አላቸው፡፡ ፠ በኦሪት ሔኖክ፣ ዕዝራ፣ ኤልያስ፤ በሐዲስ ኪዳንም እነ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድና በየጊዜውም እንደሚሰወሩ ቅዱሳን እንደዚሁም ጌታችን እነዚህን የማኀበረ ዴጎ ጻድቃንንም ከሞት ተሰወሩ ብሎ በበነጋታው ጥር 30 ቀን ሠውሯቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ይህ ታላቅ በዓል ሆኖ ዛሬም በየዓመቱ ጥር 30 ቀን በደማቅ ሁኔታ ሲከበር ይኖራል፣ ይከበራልም፡፡ ፠ በገዳመ ዴጎ በዓይን የሚታዩ፥ በእጅ የሚዳሰሱ ተአምራት የታየባቸውና የተደረገባቸው ንዋያት እስካሁንም አሉ፡፡ ወደ አኵሱም ስትሄዱ ታዩት ዘንድ እንጠቁማችሁ፡፡ 1. ጌታችን የተቀመጠበትንና የቆመበትን ድንጋይ ከነምልክቱ 2. ምስዋሮም የሚባል ጻድቃኑ የተሰወሩበትን ስፍራ
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️ 💁♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️ 👨🦱🧑🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️ ⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️ 🤵♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️ በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት 👇👇👇 @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel
⛪️📚🙏 1, እመጓ 2, ዝጎራ 3, መርበብት 4, ዴርቶጋዳ 5, ዮራቶራድ 6, ዣንቶዣራ 7,መጽሐፈ ሄኖክ 8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ 9, ፍኖተ አእምሮ 9, አዳም እና ጥበቡ 10, ዝክረ መስቀል 11, ሰይፈ ሥላሴ 12, ፍትሐ ነገስት 13, መጽሐፈ መነኮሳት 14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና 16, ህግጋተ ወንጌል 17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን 18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል 19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ 20, ግድለ ተክለሃይማኖት 21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ 22, የወጣቶች ህይወት 23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት 24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት 25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ 📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖 ✝ ይቀላቀሉን ✝
без подписи
без подписи
★★★አቡነ ደንቆሮ ዘጎረጎር ማርያም★★★ ★★★"አባ ደንቆሮ" የሚባሉ በሞት ፈንታ የተሠወሩ ጻድቅ እንዳሉ እናውቅ ይሆን? የገዳመ ጎረጎር ቅዱሳን በዚኽች ዕለት 21ቀን ወርሀዊ በዓላቸው ስታስበው ይውላሉ። እግዚአብሔር እንደ እነ ሄኖክና ኤልያስ በሞት ፈንታ የሠወራቸው ታላላቅ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ከሀብታሞች ቤት የማዕድ ፍርፋሪ እየሰበሰበ የሚያመጣና በጾም በጸሎት ላሉ ባሕታውያን የሚሰጥ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ የውስጥና የውጭ ቅድስናውን ንጽሕናውን ሰው እንዳያውቅበት ዕብድ መስሎ የሚኖር አለ፤ መራራ የሆነ የበረሓ ቅጠልና ሣርን የሚመገብ አለ፤ ለዚህ ዓለም ሰዎች ፊቱንና መልኩን እንዳያሳይ በገዳም ውስጥ ዘግቶ የሚኖር አለ፤ ከተራራ ሥር የተሠወረ አለ፤ ችግረኛና ድኃ መስሎ የሚኖር አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ በኋለኛው ዘመን የሚሆነውን ነገር በትንቢት የሚናገር አለ፤ በነፋስ ክንፍ ረቂቅ በሆነ በደመና ጀርባ የሚጓዝ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ ስለ ተሠወሩ ምሥጢራት ሁሉ ከቅዱሳን መላእክት ጋር የሚነጋገር አለ፤ በሕይወት በብሔረ ሕያዋን የሚኖሩትን ተመልክቶና በእነርሱም ተባርኮ የሚመጣ አለ፤ በሌሊት ራእይ የገነትን ቦታዎችና ውበቷን የሚያይ አለ፤ የኀጥአንን ኑሯቸውን የጩኸታቸውን ድምፅ የሚሰማ አለ፡፡ የእዚኽም እጅግ የከበሩ ቅዱሳን ስማቸው አቡነ መርዓዊ፣ አቡነ ምሰሶ፣ አቡነ ደንቆሮ፣ አቡነ ሞአብራ፣ አቡነ ሙሴ፣ አቡነ አላሽኝ ይባላሉ፡፡ በዝምታ በተደሞ የማይሰማ በመምሰል እንደ ደንቆሮ ሆኖ መላ ዘመኑን ለዓለም ሙት ሆኖ ስለኖረ ‹‹አቡነ ደንቆሮ›› የተባለ አለ፤ መርዓዊ ማለትም መርዓዊ ዘክርስቶስ (የክርስቶስ ሙሽራ) ማለት ነው፣ እርሱም በታላቁ በዋልድባ አብረንታት ገዳም አበ ምኔት ሆኖ መነኰሳቱን የመራ ነው፤ ምሰሶ ማለትም ዐምደ ሃይማኖት (የሃይማኖት ምሰሶ) ማለት ነው፤ ሞአብራ ማለትም ሞዐ ሐራሁ ለክርስቶስ (አሸናፊ የሆነ የክርስቶስ ሠራዊት) ማለት ነው፤ ሙሴ ማለትም በልቡ ሽንገላን የማያውቅ ሩኅሩኅ የዋህ ማለት ነው፤ አላሽኝ ማለትም በጸሎቱ ኀይል በደልን አበሳን ይቅር የሚያስብል፣ ምሕረትን የሚያሰጥ ማለት ነው፡፡ የእነዚኽም ክቡራን ቅዱሳን የትውልዳቸው ሀገር ምድረ አግዓዚት የተባለች ኢትዮጵያ ናት፡፡ የተወለዱበት አውራጃም ላኮመልዛ ትባላለች፣ በኋላ ላይ ወሎ ተባለች፤ ዳግመኛም የደላንታ ቦታ የዋድላ ሜዳ ይሏታል፡፡ ሌሎችም መጠሪያ ስሞች አሏት፡፡ እነዚኽም ቅዱሳን በዚኽች ሀገር ሲወለዱ ከሕፃንነታቸው ጀምረው ተጋድሏቸውን አብረው የጀመሩ ናቸው፡፡ ሰባት ዓመት ሲሞላቸው ወደ ትምህርት ቤት ገብተው አውሎጊስ ወደተባለ ደገኛ መምህር ዘንድ ሔደው የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ተማሩ፣ መምህራቸውም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እነርሱ ታላላቅ ቅዱሳን እንደሚሆኑና በዘመናቸውም ግራኝ አህመድ እንደሚነሣ ትንቢት ተናገረ፡፡ ★★★ዐፄ ሱስንዮስም በ1616 ዓ.ም የካቶሊክን ሃይማኖት ካልተቀበላችሁ ብሎ ጎንደር ደንቀዝ ላይ ከ8ሺህ በላይ የሚሆኑ ክርስቲያኖችን ከሰየፋቸው በኋላ በመቅሠፍት ተመቶ ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ በዚኽም ወቅት መኳንንቱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲያማክሩ አንዲት ፍኖቲ የምትባል ከቤታቸው የምትኖር ደግ ባልቴት ‹‹ከጨጨሆ በላይ ያለ ጻድቅ ስሙ አቡነ መርዓዊ የሚባል ካህን ቢባርከው ምላሱ ይመለሳል፣ እርሱም ከመንግሥቱ ይፈልሳል፣ ፋሲል ይነግሣል›› በማለት መከረቻቸው፡፡ የንጉሡም ጭፍሮች አቡነ መርዓዊ ያሉበትን አፈላልገው አግኝተው ነገሯቸው፣ እርሳቸውም በሠረገላ ብርሃን ተጭነው በመሔድ በመስቀላቸው ባርከው ምላሱን መልሰውለት ፈውሰውታል፡፡ ንጉሡም ከዳነ በኋላ ዐዋጁን በዐዋጅ ሽሮ ‹‹ተዋሕዶ ሃይማኖት ትመለስ ፋሲል ይንገሥ›› ብሎ ዐርፏል፡፡ ዐፄ ሱስንዮስ የካቶሊክን እምነት ካልተቀበላችሁ ብሎ ሊቃውንቱን በአንድ ቀን ባሳረደ ጊዜ ንጉሡ ወዲያው ‹‹ኦርቶዶክስ ይርከስ ካቶሊክ ይንገሥ›› ብሎ ያወጀበት ምላሱ ተጎልጉሎ ከወጣ በኋላ በተኣምራት ተጎልጉሎ የወጣውን ምላሱን በመስቀላቸው ባርከው ወደነበረበት በመመለስ የፈወሱት ሌሎችም ቅዱሳን እንዳሉ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ለምሳሌ፡- የማኅበረ ሥላሴው አቡነ ዓምደ ሥላሴ፣ የጩጊ ማርያሙ አቡነ ምእመነ ድንግል ይጠቀሳሉ፡፡ ይኽም ማለት አቡነ ዓምደ ሥላሴ፣ አቡነ ምእመነ ድንግል፣ አቡነ መርዓዊ ወይም ሌላ ጻድቅም ቢሆን እንዲሁ ዐፄ ሱስንዮስን ምላሱን ወደነበረበት መልሰው አዳኑት ተብሎ ለሁሉም ቅዱሳን ቢነገር ታሪኩ እርስ በእርሱ የሚጋጭ አይደለም፡፡ የእነዚኽንም እጅግ የከበሩ ስድስት ቅዱሳንን ገድላቸውን ከሌሎቹ ቅዱሳን ገድል ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን በቱርኮች አጋዥነት በሀገራችን ላይ ተነሥቶ ለ15 ዓመት ቤተ ክርስቲያንን ሲያቃጥል ካህናትን ሲያርድ ስለኖረው ስለ ግራኝ አህመድ መነሻ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ዘርዝሮ ስለሚያስረዳ ነው፡፡ ገድለ ስድስቱ ቅዱሳን ዘገዳመ ጎረጎር እንደሚናገረው ቅዱሳኑ ጽኑ የሆነውን ተጋድሏቸውን ከፈጸሙ በኋላ ጌታችን መስከረም 21 ቀን በክብር ተገልጦላቸው እንዲህ የሚል ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡- ‹‹ስማችሁን የጠራና የዘከረ ሰው ዕድል ፈንታው ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ወደ ገዳማችሁ የሚመጣውን ሰው እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እምረዋለሁ፤ ወደዚኽች ገዳም በልቡ ሊመጣ አስቦ መምጣት ያልቻለውን ሰው መጥቶ ሰግዶ እንደተሳለመ ይቆጠርለታል፣ እርሱ ይድናል፣ ልጆቹንና ሚስቱንም ያድናል፤ ለቤተ ክርስቲያን መባዐ የሰጠ ዋጋውን በሰማያት ያገኛል፣ መባዐ መስጠት ያልቻለ ሰው ገድላቸውን ያለምንም ጥርጣሬ ያድምጥ በፍጹም ልቡናው ለተከታተለ ሰው መባዐ እንደሰጠ ይቆጠርለታል፤ ቦታችሁ እንደ ኢየሩሳሌም ትሁን፣ ይኽችን ቦታ ያየ ሰው ኢየሩሳሌምን አላየሁም አይበል ይኽች ቦታ ኢየሩሳሌም ናትና፤ ወንዞቿ እንደ ገነት ወንዝ እንደ ግዮንና እንደ ጤግሮስ ናቸው፤ በገዳሙ ጠበል በንጹሕ ልብ አምኖ ንስሓ ገብቶ የተጠመቀ ሰው እንደ አርባና ሰማንያ ቀን ሕፃን ይሆናል የሠራው ኀጢአቱ ሁሉ ይደመሰስለታል፤ መታሰቢያችሁን ለማድረግ የሚደክመውን ሰው በቤቱ ውስጥ የእንስሳት ሞትም ቢሆን ቸነፈር አይገባም እስከ ልጅ ልጁ ድረስ የሥራው ፍሬ ይባረካል፡፡›› ጌታችን በገባላቸው ቃልኪዳን መሠረት ቅዱሳኑ የተሠወሩባትን ምድር ጎረጎር ገዳምን እንደ መሶም አንሥተው አስባርከዋታል፣ ቅዱሳኑ እንደ ሄኖክና ኤልያስ ከሞት የተሠወሩባት ናት። የእኚህ እጅግ የከበሩ ቅዱሳን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን። ምዕራፈ ቅዱሳን ጎርጎር ቅድስት ድንግል ማርያም አንድነት ገዳም የምትገኘው በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቄት ወረዳ ከባህርዳር ወደ ወልድያ የሚወስደው መንገድ ላይ የምትገኘው ደብረ ዚጥ ከተማ በስተደቡብ ምዕራባዊ አቅጣጫ 12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሲሆን ከደብረ ዚጥ ከተማ የ3 ሰዓት የእግር ጉዞ #አርከ ስሉሥ ቅዱስ #ቅዱሳንና ቅዱሳት መካናት እንወቅ
без подписи