tgindex
የቤተክርስታያን ልጆች✞✞✞✞✞✞✞

የቤተክርስታያን ልጆች✞✞✞✞✞✞✞

Статистика

https://t.me/llinkadonay123ቅድስት ድንግል ማርያም

Последний пост
17 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
170
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
60
21 постов
Вовлечённость
35,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 29 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

  • 5 апр.661из Orthodoxtewahdoc

    *©ቡሩክ ዘይመጽእ*        ጥራዝ4. ቁ.48 ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር/፪/ ሆሳዕና/፫/ በአርያም/፪/ ትርጉም:-በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባርከ ነው ሆሣዕና በአርያም።

  • ወልድኪ መድኃኔዓለም ሥጋ ዚኣኪ ዘለብሰ። በዐውደ ጲላጦስ ተወቅሰ (፪) መድኃኔዓላም። እኛን ለማዳን ስለእኛ በዕለተ ዓርብ መጋቢት ፳፯ ቀን የተሰቀለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስሙ ዛሬም ዘወትርም የተመሰገነ ይሁን። 🌷እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ✝

  • የቤተክርስታያን ልጆች✞✞✞✞✞✞✞ pinned «❇ #እለተ_አርብ_የፍቅር_ቀን❤ 📌 እለተ አርብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ ለዓይን የሚዘግንኑ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ከባድ ቀንን ለእኔና ለእናንተ ፍቅር ሲል አሳልፏል፡፡ " ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። "     ኢሳ.…»

  • ❇ #እለተ_አርብ_የፍቅር_ቀን❤ 📌 እለተ አርብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ ለዓይን የሚዘግንኑ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ከባድ ቀንን ለእኔና ለእናንተ ፍቅር ሲል አሳልፏል፡፡ " ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። "     ኢሳ. 53 : 7 🌿🌿13ቱ ህማማተ መስቀል🌿🌿 ➊ እራሱን በዘንግ ተመታ ፦  ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን መቱት ።《ማቴ 27÷30》 ➋ በጥፊ ተመታ ፦ በጥፊም ይመቱት ነበር።《የሀ 19÷4》 ➌ ምራቅ ተፉበት ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን መቱት።《 ማቴ 27÷30》 ➍ የሾክ አክሊል ጎንጉነው በእራሱላይ አቀዳጁት 《ማቴ.27፥29 》 ➎ መራራ ሀሞት አጠጡት  ፦ በሀሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም ።《ማቴ 27÷34 》 ➏ ጀርባውን መገረፉ ፦ በዚያን ጊዜም ጲላጦስ እየሱስን ይዞ ገረፈው ። 《ዩሀ 19÷1》 ➐ ጎኑን በጦር መውጋት፦ ነገር ግን ከጭፈራዎቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ወድያውም ደምና ውሃ ወጣ።《የሀ 19÷34 》 ➑ ወደ ኃላ መታሰሩ ፦ የሾለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሌሎችም እየሱስን ይዘው አሰሩት። 《ዩሀ.18÷12 》 ➒ ሳዶር ➓ አላዶር ➊➊ ዳናት ➊➋ አዴራ ➊➌ ሮዳስ 5ቱ #ቅንዋተ #መስቀል ችንክሮች ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት ፣ አዴራ እና ሮዳስ ይባላሉ። ➊ #ሳዶር ፦ ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት ➋ #አላዶር፦ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት ➌ #ዳናት ፦ ማለት እግሮቹ የተቸነከረበት ➍ #አዴራ ፦ ማለት ደረቱን የተቸነከረበት ➎ #ሮዳስ ፦ ማለት ከወገቡ (እብርቱ) አጣብቆ እንዲይዝ የተቸነከረበት 🍁🍁🍁መከራን ታገሰ🍁🍁🍁 😭 ሁሉን የያዘውን እርሱን ያዙት 😭 ሁሉን የሚገዛውን እርሱን የአምላካችንን እጅ አሰሩት 😭 ሀጥያትን የሚያስተሰርይ እርሱን ሀጢያተኛ አሉት 😭 የማይገረፍ አምላክ እርሱን የሰውን ስጋ በመልበሱ ገረፉት 😭 እንደ መብረቅ የሚያንፀባርቀውን ነጭ ልብስ የሚያለብስውን አምላክ እርሱን ቀይ ግምጃ አለበሱት። 😭 በእሳት በተጋረዱ ዙፋን ላይ የሚቀመጥ እርሱን በመዘባበቻ ወንበር ላይ አስቀመጡት። 😭 እንደ ድንኳን ሰማይን የዘረጋ እርሱን በመስቀል ላይ ሰቀሉት:: 😭 የመላአክት አለቆች በፊቱ በመፍራት የሚቆሙለት እርሱን በጲላጦስ ፊት አቆሙት ፡፡ 😭 በህይዋንና በሙታን ላይ የሚፈርድ እርሱን እንደበደለኛ ተፈረደበት 😭 አለምን ሁሉ በቅፅበት የፈጠረ እርሱ በስጋው ሞተ በመለኮት ህያው ሆነ 📖 ጌታችን_መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ ከ6-9 ስአት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር ቃላት ❤ ኤሉሄ ኤሉሄ ለማስበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ) ማቴ 27÷46 ❤ እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ። ሉቃ.23÷43 ❤ አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ሉቃ 23÷43 ❤ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው። ሉቃ.23÷34 ❤ እናትህ እንኃት እንሆ ልጅሽ::  ዩሀ 19÷26-27 ❤ ተጠማሁ። ዮሀ 19÷28 ❤ ተፈፀመ። ዮሀ 19÷30 #ጌታችን_መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ የተፈፀሙ 7ቱ ተዓምራት 1⃣ ፅሀይ ጨለመች 2⃣ ጨረቃ ደም ለበሰች 3⃣ ከዋከብት ብርሃናቸውን ነሱ 4⃣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተከፈለ 5⃣  አለቶች ተሰነጣጠቁ 6⃣  መቃብራን ተከፈቱ 7⃣  የሞቱት ተነሱ ክብርና ምስጋና አምልኮት ውዳሴ ስግደት ዝማሪ ይድረሰ ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ 🌷አቤቱ  አምላካችን ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበን🤲

  • ♥ መድኃኔዓለም ♥ 💠«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት  ማለት ነው።ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።ምን ዓይነት ፍቅር ነው????? ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው።ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው። በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር። ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን። በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ።አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ። ። መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።

  • ††† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† መድኃኔ ዓለም ††† ††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል:: *ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: *በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: *ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ:: *ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: *በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: (ማቴ. 27:1, ማር. 15:1, ሉቃ. 23:1, ዮሐ. 19:1) ††† ለእኛ ለኀጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኅማማቱ: አምስቱ ቅንዋቱ: ስለ ቅዱስ መስቀሉ: ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን:: ††† ከቅዱሳኑ በዚሕች ዕለት:- ††† ከ80 ዓመታት በላይ በገዳም የኖረ: የገዳማውያን ሞገሳቸው: የመነኮሳትም ሁሉ አለቃ ታላቁ ቅዱስ መቃርስ አርፏል::  ††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ንግሥናን ከሊቅነት: ጽድቅን ከሰማዕትነት ጋር የደረበው ሰማዕቱ ቅዱስ ገላውዴዎስ አንገቱን ተከልሏል:: ቅዱስ ገላውዴዎስ የጻድቁ ዐፄ ልብነ ድንግል ልጅ ነው::  ††† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::  ††† መጋቢት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ (ፍቁረ እግዚእ) 2.ቅዱሳት አንስት (ከእግረ መስቀሉ ያልተለዩ) 3.ቅዱሳን ባልንጀሮች (በጌታ ስቅለት ጊዜ ከሞት የተነሱ) 4.ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ 5.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት አለቃ) 6.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት (የኢትዮዽያ ንጉሥ) 7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል  ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ 2.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት 3.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ 4.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት ††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" ††† (፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ➠✝️ወር በገባ በ 24  ሁሌም የምናስባቸው ሃያ አራቱ  ካሕናተ ሰማይ  የሰውን ልጆች ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይታደጉን🌹 ♨የ24ቱ ካህናተ ሰማይ(ሱራፌል) ስማቸው የሚከተሉት ናቸው።➻ ❶,ቅዱስ አካኤል ❷ ,ቅዱስ ፋኑኤል ❸ ,ቅዱስ ጋኑኤል ❹ ,ቅዱስ ታድኤል ❺ ,ቅዱስ አፍድኤል ❻ ,ቅዱስ ዘራኤል ❼ ,ቅዱስ ኤልኤል ❽ ,ቅዱስ ተዳኤል ❾ ,ቅዱስ ዮካኤል ❿,ቅዱስ  ገርድኤል ❶❶,ቅዱስ  ልፍድኤል ❶❷ ,ቅዱስ መርዋኤል ❶❸,ቅዱስ  ኑራኤል ❶❹,ቅዱስ  ክስልቱኤል ❶❺,ቅዱስ  ዑራኤል ❶❻,ቅዱስ  ባቱኤል ❶❼,ቅዱስ  ሩፋኤል ❶❽,ቅዱስ  ሰላትኤል ❶❾,ቅዱስ  ጣርኤል ❷○ቅዱስ  እምኑኤል ❷❶'ቅዱስ ፔላልኤል ❷❷ ,ቅዱስ ታልዲኤል ❷❸,ቅዱስ ፐሰልዲኤል ❷❹ ,ቅዱስ አሌቲኤል የ ካህናተ ሰማይ በረከት ረድኤት አማላጅነት አይለየን በጸሎታቸው ይማረን

  • 🌹#ወር በገባ በ24 #አባ_ኖብ ሰማዕት📕 ♨••እንኳን ለአባታችን ለአባ ኖብ ሰማዕት ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በምድረ ግብጽ ከታዩ ታላላቅ ከዋክብት አንዱ ቅዱስ ኖብ በሃገረ ንሒሳ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: ወላጆቹ በልጅነቱ ብዙ ሃብት ትተውለት ያርፋሉ:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ካህኑ ስለ ምናኔና ሰማዕትነት ሲሰብክ ይሰማዋል:: ገና በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤቱ የነበረውን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ መስቀለ ክርስቶስን ሊሸከም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምስክርነት አደባባይ -የክርስቲያኖች መገደያ ቦታ) ተጓዘ:: በዚያም በጉባዔ መካከል ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ ምክንያት በሰብዓዊ አካል ሊሸከሙት የማይችሉትን መከራ በልጅ ገላው ተቀብሏል:: በዚያው ልክም ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: በተአምራቱና በጣዕመ ስብከቱም ከመቶ ዘጠና ሺህ በላይ አሕዛብን ወደ ክርስትና መልሶ ሁሉም ተሰይፈዋል:: በእሳት: በስለት: በሰይፍ: በባሕርና በየብስ መከራን ከተቀበለ በኋላ በዚህች ቀን አክሊለ ክብርን ይቀበል ዘንድ አንገቱን ተከልሏል:: ጌታችን የገባለት ቃል ኪዳኑ ግሩም ነውና ዛሬ በግብጽ በድምቀት ይከበራል:: ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች:: የአባኖብ ሰማዕት በረከታቸው ይደርብን፤ጸሎታቸው ይጠብቀን፤ለመንግሥተ ሰማይ መሪ በትር ይሁነን፤ድካማቸው ከጠላት እጅ ያድነን፣የትዕግሥታቸው ሀይል ከእሳት ባሕር ያድነን አሜን አሜን አሜን

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ☞ ወር በገባ በ 24 ቀን የሙሴ ጸሌም ወርሐዊ መታሰቢያ ነው፡፡ ☞ብዙ መነኮሳት ወደ አቡነ ሙሴ እየመጡ የሕይወት ትምህርትን ይማሩ ነበር፡ ከነዚህ የሕይወት ትምሕርታቸው መካከል በጥቂቱ እንመልከት፡፡ ☞1ኛ☞አባ ሙሴ በገዳመ አስቄጠስ እያለ ከገዳማውያን አንዱ ጥፋት ሠራና ማኅበሩ ለፍርድ ተሰበሰበ፡፡ አባ ሙሴ ግን በጉባኤ ላይ አልነበረም፡፡ ስለዚህ ካህኑ ተልኮ ና ሁላችንም አንተን እየጠበቅን ነው አለወ፡፡ አባ ሙሴም በሚያፈስስ ከረጢት አሸዋ ሞልቶ ያንንም በጀርባው ተሸክሞ ከኀላው እያፈሰሰ ወደ ጉባኤው አመራ፡፡ ጉባኤተኞቹ ተገርመው ለምን እንደዚህ እንዳደረገ ጠየቁት፡፡ እርሱም የእኔ ኃጢአቶች በኀላዬ እንደዚህ አሸዋ በዝተው ይፈሳሉ ነገር ግን ላያቸው አልቻልኩም ዛሬ ግን በሌላው ላይ ለመፍረድ መጥቻለሁ አላቸው፡፡ ይህን ሲሰሙ ዝም አሉ፡፡ ያን ወንድምም በይቅርታ አለፋት፡፡ ☞2ኛ☞በሌላ ጊዜ በገዳመ አስቄጠስ ያሉ መነኮሳት ተሰብስበው የአባ ሙሴን ትዕግሥት ለመፈተን ሲሉ ይህ ጥቁር መነኩሴ ለምን እዚህ መጣ ብለው ተናገሩት፡፡ እርሱም ዝም አለ፡፡ ጉባኤው ሲበተን አባ ክፋ ስንናገርህ ምንም ሐዘን አልተሰማህም ነበርን? ሱሉ ጠየቁት፡፡ እሱም ተሰምቶኝ ነበር ግን እንዳልናገረው አንደበቴን ተቆጣጠርኩት አላቸው፡፡ ☞3ኛ☞አንድ ጊዜ የአካባቢው ገዥ ሰለ አባ ሙሴ ዝና ሰምቶ ያየው ዘንድ ወደ ገዳመአስቄጠስ መጣ፡፡ ይህን የሰማው አባ ሙሴ ሸሽቶ ወደ ጫካ ገባ፡፡ በመንገድም ላይ የገዥው መልእክተኞች አገኙትና እባክህን አባ ሙሴ የት እንዳለ በኣቱን አሳየን አሉት፡፡ ከርሱ ምን ትሻላችሁ እርሱ ኮ ቂላቅል ነው አላቸው፡፡ ☞ይህን የሰማው የአካባቢው ገዥ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጣና የሆነውን ሁሉ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፡፡ ብዙ ሰዎች ስለ አባ ሙሴ ሲያወሩ ሰምቼ ለማግኘት መጥቼ ነበር በመንገድ ላይ ያገኘነው አንድ አረጋዊ ሰው ግን የአባ ሙሴ በኣት የት እንደሆነ ስንጠይቀው ከእርሱ ምን ትሻለችሁ እርሱ ኮ ቂላቅል ነው አለን ብለው ነገራቸው፡፡ ☞አገልጋዮቹም በጣም ተናደዱና ምን ዓይነት ሰው ነው ስለ ቅዱሱ ይህን የሚናገር ብለው ጠየቁት፡፡ ☞ትልቅ ጠቆር ያለ አሮጌ ልብስ የለበሰ ነው፡፡ አላቸው፡፡ አገልጋዮቹም ተገርመው ይህማ ራሱ አባ ሙሴ ነው ይህን ያለህ ሊያገኝህ ስላልፈለገ ነው አሉት፡፡ የአካባቢው ገዥም ከአባ ሙሴ ሁኔታ ከንቱ ውዳሴን ስለ መሸሽ ትልቅ ትምህርት ተምር ተመለሰ፡፡ ☞4ኛአባ ሙሴ በኣት ሠርቶ ወደ ጴጥራ ሲሔድ በአካባቢው ውኃ ሰላልነበረ ተጨንቆ ነበር፡፡ አንድ ድምፅ ሒድ ስለምን ነገር አትጨነቅ አለው፡፡ ሰለዚህም በዚያ መኖር ጀመረ፡፡ አንድ ቀን በጴጥራ እያለ አበው ሊጎበኙት መጡ የነበራቸውን ውኃ ጥቂት ነበረችና በርሷ ምግባቸውን አበሰለ፡፡ የሚያጠጣቸው ግን አላገኘም፡፡ ስለዚህ ወደ ውጭ እየወጣ ውኃ ይሰጠው ዘንድ እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በመጨረሻም ዝናብ ዘነበና የውኃ ማጠራቀሚያዎቹን ሁሉ ሞላ፡፡ ☞እነዚያም አባቶች ትወጣና ትገባ የነበረው ለምን እንደሆነ እባክህ ንገረን አሉት፡፡ እናንተ በእግድነት ስትመጡ ውኃ አልነበረኝም ስለዚህ ያንተን አገልጋዮች ወደ እኔ ልከሃቸዋል ነገር ግን ውኃ የለኝም ስለዚህ እባክህ ውኃ ስጠኝ እያልኩ እግዚአብሔርን ለመለመን ነበር አላቸው፡፡ ☞5ኛ☞በአንድ ወቅት በገዳመ አስቄጠስ ጾም ታወጀ፡፡ በዚያም ሳምንት አባ ሙሴን ለማየት ከግብፅ ወንድሞቹ መጡ፡፡ አባ ሙሴም በእንግድነት ተቀበላቸውና ምግብ ያበስልላቸው ጀመር፡፡ የእሳቱን ጢስ የተመለከቱ ጉረቤቶቹ አባ ሙሴ ትእዛዝ አፍርሶ ምግብ ያበስላል ብለው ለገዳሙ ሓላፊዎች ተናገሩት፡፡ ሓላፊዎችም አሁን ተውት ሲመጣ እኛው ራሳችን እናናግረዋለን አሏቸው፡፡ ☞ሓላፊዎችም አባ ሙሴን ጠርተው ለምን ምግብን እንዳበሰለ ተረዱ፡፡ በቀዳሚ ሰንበት ማኅበሩ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን ሲጣ በዐደባባይ አባ ሙሴ ሆይ የሰውን ትእዛዝ አልጠበቅም የእግዚአብሔር ትእዛዝ /እንግዳ ሆኜ መጥቼ ተቀብላችሁኛል የሚለውን ግን ጠብቀሃል ብለው አመሰገኑት፡፡ ☞የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሙሴ ጸሊም የሕይወት ትምህርቶች ከብዙ በጥቂቱ በእኔ በሀጥያተኛው ለበረከት ያክል ይቺን ጻፍኩላችሁ፡፡ ☞የጹሁፍ ምንጭ(በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከተጻፈው "በበረሓ ጉያ ውስጥ"ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ) ☞ከጻድቁ አባታችን ከአባ ሙሴ ጸሊም የሕይወት ትምህርት ተምረን ፍሬ ለማፍራት ፈጣሪ ማስተዋሉን ያድለን፡፡ ☞የጻድቁ አባ ሙሴ ጸሊም በረከታቸው ይደርብን፡፡ ☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

  • #ጌታ #ሆይ #ብትወድስ #ልታነጻኝ-#ትችላለህ? 🌼 #መምህር #ሳሙኤል #አስረስ " እነሆም፥ #ለምጻም #ቀርቦ። #ጌታ #ሆይ፥ #ብትወድስ #ልታነጻኝ #ትችላለህ እያለ #ሰገደለት።"♥️ (የማቴዎስ ወንጌል 8:2)