tgindex
አሐቲ ድንግል✝✝✝

አሐቲ ድንግል✝✝✝

Статистика

አንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ~~የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ √ቃሉን የምናገኘው በመጽሐፈ ቅዳሴ ሲሆን “አንቲ ውዕቱ መሶበ ወርቅ ንጹህ እንተ ውስቴታ መና ሕቡዕ ኅብስት ዘወረደ እምሰማያት ወኀቤ ሕይወት ለኩሉ ዓለም።" የተሰወረ መና በውስጧ ያለባት የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ። ከሰማያት የወረደ ኅብስት ለሰው ሁሉ ድኅነት የሚሰጥ” ይላል ትርጉሙ። √ ለሕይወተዎ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ መጽሐፍትን ያገኙበታል።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
41
Всего постов
218
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 283
−10 за 5 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
142
40 постов
Вовлечённость
6,2%
к подписчикам
Постов в день
5,9
всего 218
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
126
1/48двое суток
144
1/72трое суток
155

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • እንኳን ለጽንሰተ ማርያም በሰላም አደረሳችው🙏 " ድንግል ሆይ ከምልጃሽ በቀር ሊጠብቀኝ የሚችል እንደሌለ አወኩኝ ያለ ማህጸንሽም ፍሬ ሊራራልኝ የሚችል እንደሌለ ይህንንም አውቄ ወደ አንቺ ተጠጋሁ በልጅሽም አመንኩ እርሱንም አመለኩ ቸርነቱንም ተስፋ አደረኩ " ❤️ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

  • ፭. የዳዊትና የሜክያስ ትንቢት: ተናግሮ የማያስቀር፣ ምሎ የማይከዳ እግዚአብሔር፦ “ከባሕርይህ የተከፈለ ልጅህ (ክርስቶስን) በዙፋንህ አስቀምጥልሃለሁ” ብሎ ለዳዊት በእውነት ማለለት (መዝ. ፻፴፩፡፲፩)። ዳዊትም ክርስቶስ በሥጋ ከእርሱ እንዲወለድ ባመነ ጊዜ የአካላዊ ቃል ማደሪያውን መርምሮ ያውቅ ዘንድ ወደደ፤ ቀኖናም ገባ። ከዚህም በኋላ “ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም - በኤፍራታ ተወልዶ፤ በጎል ተጥሎ፤ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግዕዘ ሕፃናት ሲያቅስ ሰማነው” አለ (መዝ. ፻፴፩፡፮)። ይህቺውም እኛን ስለማዳን ይወለድባት ዘንድ የመረጣት ቤተ ልሔም፣ ቤተ ኅብስት የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፤ ከሰማይ የወረደው ኅብስት እርሱ ነውና (ዮሐ. ፮፡፶፩)። ከነቢያት አንዱ የሚሆነው ሚክያስም ዳግመኛ እንዲህ አላት፦ “አንቺም የኤፍራታ ዕፃ የምትሆኚ ቤተ ኅብስት ቤተ ልሔም እመቤታችን ሆይ! በይሁዳ ከነገሡ ነገሥታት ብትበልጪ እንጂ አታንሺም። እስራኤል ዘነፍስን የሚጠብቅ ንጉሥ ባንቺ ይወለዳልና እንዲህ እንደሆንሽ አትቀሪም። ንጉሥ ይወለድብሻል፤ ቅዳሴ መላእክት ይሰማብሻል፤ የብርሃን ድንኳን ይተከልብሻል፤ መቶው ነገደ መላእክት ደጅ ይጠኑብሻል፤ አሕዛብ ይገብሩብሻል” ብሏታል (ሚክ. ፡፪)። ጀሮም የተባለ ቅዱስ አባት ይህን አንቀጽ ሲተረጉም፦ “ከሰማይ የወረደ ኅብስት (ዮሐ. ፮፡፶፩) የተወለደብሽ ቤተ ኅብስት ሆይ! ሰላምታ ይገባሻል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደብሽ ምድረ ፍሬ፣ ምድረ ምውላድ (ኤፍራታ) ሆይ! ሰላምታ ይገባሻል። በዘመነ ብሉይ ሚክያስ ነቢይ ስለ አንቺ ሲናገር እንዲህ ብሎ ተናግሮ ነበርና፦ ‘ወአንቲኒ ቤተ ልሔም ምድረ ኤፍራታ ኢትቴሕቲ እም ነገሥተ ይሁዳ - አንቺም የኤፍራታ ዕፃ የምትሆኚ ቤተ ልሔም ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም (ማቴ. ፪፡፮)። ኢይወጽእ ምስፍና ወምልክና እምአባሉ ለይሁዳ - በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም እንዲል (ዘፍ. ፵፱፡፲) ከባሕርይ አባቱ ከአብ ጋር ቅድመ ዓለም የነበረ፣ ከዲያብሎስ አስቀድሞ ቀዳማዊ የሆነ እስራኤል ዘነፍስን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣል (ይወለዳልና)’” ብሏል (St. Jerome, Letter 108:10)። ወዮ! ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ከአብ ከባሕርይ አባቱ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ ጋራ ክብር ይግባውና በአንድ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸው የክርስቶስን ነገር የተናገሩ ሚክያስና ዳዊት የተናገሩት ነገር ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? አንድም ሚክያስና ዳዊት ለተናገሩት ነገር አንክሮ ይገባል። ከአብ ከባሕርይ አባቱ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ ጋር ክብር ከሚገባው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፣ ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን። ፮. የዳዊት የውኃ ጥምና የሰማዕታት ተጋድሎ ምሳሌነት: ለእስራኤል የነገሠ ዳዊት ኢሎፍላውያን በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ይጠጣ ዘንድ ወደደ። ዳዊት ታመመ፤ ቢታመም ዘመዶቹ ቀሳ አወጡት። ኢሎፍላውያን ይህን ሰምተው ቤተ ልሔምን አልፈው ሰፈሩ። ዳዊትም “ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባመጣልኝ?” አለ። ከእናንተ መካከል፦ “ስለምን ከቤተ ልሔም የተቀዳ ውኃ ይጠጣ ዘንድ ወደደ?” የሚል ሊኖር ይችላል። እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፦ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው ታምሞ ስለነበር የቤተ ልሔም ውኃ ደግሞ ማየ ፈውስ ናትና (፪ኛ ነገ. ፳፫፡፲፭-፲፯)። ስለሆነም የጭፍራ አለቆች አዲኖን፣ ኢያቡስቴ፣ ኤልያና አፋ አፋቸውን ታጥቀው፣ ዘገራቸውን ነጥቀው፣ ራዋታቸውን ጭነው “የማን ጌታ በውኃ ጥም ይሞታል?” ብለው ፈጥነው ተነᠡ። በኢሎፍላውያን ከተማ ተዋጉለት፤ ይጠጣ ዘንድ የወደደውንም ውኃ አመጡለት። ብፁዕ ዳዊት ግን ስለ እርሱ ሰውነታቸውን ለሞት አሳልፈው እንደ ሰጡ በየጊዜው የራዋቱን ውኃ አፈሰሰው፤ በማለፊያው ቀድተው የሰጡትን አልጠጣም፤ “የእናንተን ደም መጠጣት ነው” ብሎ አፍሶታል። አንድም ውኃውን መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አፈሰሰው። ከእናንተ መካከል፦ “ዳዊት ንጉሥ ሲሆን መሥዋዕት የሚሆን ላም፣ በግ አጥቶ ነውን?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል። በፍጹም! እግዚአብሔር የወደዱትን ቢተዉለት ስለሚወድ ነው እንጂ (መዝ. ፶፬፡፮)። ዳዊት የወደደውን ውኃ ስለ እግዚአብሔር ብሎ ስላፈሰሰውም ጽድቅ ሆኖ ተነገረለት። አዲኖን፣ ኢያቡስቴ፣ ኤልያና ስለ ዳዊት ብለው ጣዕመ ዓለምን እንደናቁ፤ ዳዊትም ስለእነርሱ (አንድም ስለ እግዚአብሔር) ብሎ ጣዕመ ማይን እንደናቀ ሰማዕታት ጣዕመ ዓለምን ናቁ። አዲኖን፣ ኢያቡስቴ፣ ኤልያና ዳዊትን ብለው «ደማችንን እናፍስ» እንዳሉ፤ ዳዊትም ውኃውን እንዳፈሰሰ፤ ሰማዕታት ስለ እግዚአብሔር ብለው ደማቸውን አፈሰሱ። አዲኖን፣ ኢያቡስቴ፣ ኤልያና ስለ ዳዊት ብለው «መራራ ሞትን እንታገሥ» እንዳሉ፤ ዳዊትም «ጽምዓ ማይን ልታገሥ» እንዳለ ሰማዕታት መራራ ሞትን ታገᡡ። ቸር አባት ሆይ! እኛስ እንደ ሰማዕታት ከዓላውያን ነገሥታት፣ ከዓላውያን መኳንንት ገብተን መከራውን ታግሠን ተቀብለን፤ እንደ ምእመናንም ከፍትወታት፣ ከእኩያት ኃጣውእ ተዋግተን ድል ነሥተን መዳን አይቻለንምና እንደ ቸርነትህ ብዛት ይቅር በለን። ቸርና ይቅር ባይ ከሚባል ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፣ ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣ ለምኚልን። ፯. የሰው ልጅ ድኅነትና የአሕዛብ መቅረብ: ከሦስቱ አካል አንዱ አካል በእግረ አጋንንት መረገጣችንን፣ መጠቅጠቃችንን አየና ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ሰው ሆኖ በድንግል ማኅፀን አደረ (ኢሳ. ፶፱፡፮)። ባሕርየ መላእክትን ባሕርይ አላደረገም፤ ባሕርየ ሰብእን ባሕርይ አድርጎ በድንግል ማኅፀን አደረ እንጂ (ዕብ. ፪፡፲፮)። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀርም እንደ እኛ ሰው ሆነ (ዕብ. ፬፡፲፬)። ሜክያስና ዳዊት «በቤተ ልሔም ይወለዳል» ብለው እንደ ተናገሩ በቤተ ልሔም ተወለደ። “ይሙት ቤዛነ በትስብእቱ ወየሀበነ መድኃኒተ ዘከመ መለኮቱ” እንዲልም እንደ አምላክነቱ አዳነን፤ እንደ ሰውነቱም ቤዛ ሆነን (ኤፌ. ፩፡፯)። ዳግመኛም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ “እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ። አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል” (ኤፌ. ፪፡፲፩-፲፫) እንዲል ወገኖቹ ያልነበርን እኛን ወገኖቹ አደረገን። ወገኖቹ ካደረገን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፣ ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን። ይህን ሲጨርስ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ባርካው ወደ ሰማይ ታርጋለች። እርሱም ተባርኮ እጅ ነሥቶ ይቀራል። አነሣሥቶ ላስጀመረን፣ አስጀምሮም ላስጨረሰን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው፤ አሜን! ወስብሐት  ለእግዚአብሔር!                                 በዲ/ን ይኄይስ ምንጭ፡ ሄላ ሚዲያ የ Telegram ቻናል:- https://t.me/ahatidingil

  • (ሃይ. አበ. ፷፯፡፫-፭)። ከባሕርያችን መርገመ ሥጋን፣ መርገመ ነፍስን የሚያጠፋልንን ጌታን ዘር ምክንያት ሳይሆንላት ወለደችው። ስለዚህ ነገር “ሰውን የምትወድ፣ ሰው የሚወድህ አቤቱ ክብር ላንተ ይገባል” እያልን እናመስግነው። “ኄር ዘበህላዌሁ ዘልማዱ ኂሩት - በባሕርይው ቸር የሆነ፤ ቸርነትን ማድረግም ልማዱ የሆነ” እያልን እናመስግነው። ኄር ዘበህላዌሁ ዘልማዱ ኂሩት ከሚባል ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፣ ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን። ፫. ድንግልናዊ ልደትና የሰብአ ሰገል እጅ መንሻ: ዘር ምክንያት ሳይሆንላት አምላክን የወለደች ድንግል፣ የማኅፀንዋ ሥራ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? አንድም ለድንግል ለማኅፀኗ ሥራ አንክሮ ይገባል። ለዮሴፍ የነገረው መልአክ ሳይለወጥ ሰው የሆነ አካላዊ ቃል ከእርሷ የሚወለድ በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ መስክሯልና (ማቴ. ፩፡፳)። ማርያም የዚህ ደስታ ዕጥፍ ድርብ የሚሆን ጌታን ወለደችው። ሴቶች ልጅ ትወልዳላችሁ ሲባሉ ደስ ይላቸዋል፤ ይልቁንም ወንድ ትወልዳላችሁ ሲሏቸው ደስ ይላቸዋል። እመቤታችን ግን ከዚሁ ሁሉ ያለፈ አምላክን ወልዳለችና ደስታዋ ዕጥፍ ድርብ ሆነላት። መልአኩ፦ “ልጅ ትወልጃለሽ፤ ስሙም አማኑኤል ይባላል” አላት። አማኑኤልም ማለት እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋ፣ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ ከእኛ ጋራ አንድ ባሕርይ ሆነ ማለት ነው። ዳግመኛም ወገኖቹን ከኃጢአታቸው ፍዳ የሚያድናቸው መድኃኒት ይባላል አላት (ማቴ. ፩፡፳፩)። በመሆኑም በክሂሎቱ (በከሃሊነቱ) ያድነን ዘንድ፣ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ (እስከ ዕለተ ምፅአት ድረስ ክብር ይግባውና) ሰው የሆነ እርሱ አምላክ እንደሆነ በተረዳ ነገር አወቅነው። አምላክ ብቻ ቢሆን ባልታመመ ነበርና፤ ሰውም ብቻ ቢሆን ባላደነን ነበርና። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ከዚህ ጋር አያይዞ፦ “ፍቁራን ሆይ! ምንም እንኳን ለዚህ ክብር የተገባን ሆነን ባንገኝም አባታችን በከሃሊነቱ እንዲሁ ከኃጢአታችን አድኖናልና ይህን ክብር፣ ይህን ጸጋ በፍጹም ልናክፋፋው (ልናቆሽሸው) አይገባንም። ልጅነት እንዲሁ ሳይሰጠን ለምረረ ገሃነም የተገባን የቁጣ ልጆች ከነበርን፤ ይህ ከኅሊናት በላይ የሆነ ጸጋ ከተቀበልን በኋላማ ፍዳችን እንደምን የበዛ አይሆን? ልጆቼ! ይህን የምለው እንዲሁ ለመናገር ያህል አይደለም፤ ዳግም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ከተወለዱ በኋላ ብዙ ክርስቲያኖች በኃጢአት፣ በስንፍና፣ ለምግባርና ለትሩፋት ሳይሽቀዳደሙ ታክተው ስለምመለከት ነው እንጂ” ሲል ይመክረናል (St. John Chrysostom, Homily IV on St. Matthew)። ወዮ! ንዕድ ክብርት ከምትሆን ከእመቤታችን ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? ቃልን ወሰነችው፤ ለልደቱም ዘርዕ ምክንያት አልሆነውም፤ በመወለዱም ማኅተመ ድንግልናዋን አልለወጠውም። ከአብ አካል ዘእምአካል፣ ባሕርይ ዘእምባሕርይ ድካም ሳይሰማው የተወለደ እርሱ ፭ ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን ሲፈጸምም ከድንግል ሕማም ሴቶች የሚሰማቸውን ሕማም ሳይሰማት፣ እርሱን ሕፃናትን የሚሰማቸው ሕማም ሳይሰማው ተወለደ እንጂ። ሰብአ ሰገል ሰገዱለት፦ ዕጣን፦ አምላክ ነውና አምላክ እንደሆነ ለማጠየቅ ዕጣን አመጡለት። ወርቅ፦ ንጉሥ ነውና ንጉሥ እንደሆነ ለማጠየቅ ወርቅ አመጡለት። ከርቤ፦ ማኅየዊ የሚሆን የሞቱ ምሳሌ ከርቤንም አመጡለት። አንድም፦ “ይህን ወርቅ እንገብርላቸው የነበሩ ነገሥታት ቀድሞም ፍጡራን፣ ኋላም ኃላፊያን ናቸው፤ አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ፣ ኋላም የማታልፍ ነህ” ሲሉ ወርቅ አመጡለት። “ይህን ዕጣን እናጥናቸው የነበሩ ጣዖታት ቀድሞም ፍጡራን፣ ኋላም ኃላፊያን ናቸው፤ አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ፣ ኋላም የማታልፍ ነህ” ሲሉ ዕጣን አመጡለት። “ምንም ቀድሞ ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ብትሆን በሰውነትህ መራራ ሞትን ትቀምሳለህ” ሲሉ ከርቤ አመጡለት። አንድም፦ ወርቅ ጽሩይ ነውና “ጽሩየ ባሕርይ ነህ” ሲሉ ወርቅ አመጡለት። ዕጣን ምዑዝ ነውና “አንተም ምዑዘ ባሕርይ ነህ” ሲሉ ዕጣን አመጡለት። ዳግመኛም “ከርቤ የተሰበረውን ይጠግናል፤ የተለያየውን አንድ ያደርጋል። አንተም ከማኅበረ መላእክት የተለየ አዳምን አንድ ታደርገዋለህ፤ ጽንዓ ነፍስ ሰጥተህ ታጸናዋለህ” ሲሉ ከርቤ አመጡለት። አንድም፦ ወርቅ ጽሩይ ነውና “ባንተ ያመኑ ምእመናን ጽሩያነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው” ሲሉ ወርቅ አመጡለት። ዕጣን ምዑዝ ነውና “ባንተ ያመኑ ምእመናንም ምዑዛነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው” ሲሉ ዕጣን አመጡለት። ዳግመኛም በዕለተ ሞቱ ያቀምሱታልና ከርቤ አመጡለት። ቸርና ሰው ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው። ቸርና ሰው ወዳጅ ከሆነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፣ ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን። ፬. የሰው አፈጣጠርና የእመቤታችን አማላጅነት: ከአዳም ጎን አንድ ዓፅም መንሣቱ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? “በእምነት ዓይን ከማየት በቀር ይህ ከኅሊናት በላይ የሆነውን ድንቅ ነገር በቋንቋ መናገር አይቻለንም” (St. John Chrysostom, Homily 15 on Genesis)። ከእርሱ (ከአዳም) ሔዋንን ፈጠረ፤ ፍጥረትንም ሁሉ ከአዳምና ከሔዋን ፈጠረ። እንዲህም አድርጎ የአብ አካላዊ ቃል ለኵነተ ሥጋ (ለሕማም ለሞት) ተሰጠ። ከልዩ ድንግልም ሰው ሆነና አማኑኤልም ተባለ። “ኦ ለዝንቱ መንክር ልዑል ላዕለ ኵሉ ሕሊናት ብእሲት ምድራዊት ወለደቶ ለእግዚአብሔር ቃል ዘኮነ ሰብአ… - ከኅሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል፤ ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው። ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው፤ እርሱም እናቱን ፈጠረ። ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ” (ሃይ. አበ. ፵፯፡፪)። ስለዚህ ነገር ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን ዘንድ ሁል ጊዜ እርሷን እንለምን። በቅዱሳን ዘንድ ቸር ናትና እርሷን እንለምን፦ ለሊቃነ ጳጳሳት «አስበ ጵጵስናችንን (የጵጵስናችን ዋጋ) ይሰጠናል» ብለው ደጅ የሚጠኑትን ወልዳላቸዋለችና ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን ዘንድ ሁል ጊዜ እርሷን እንለምን። ነቢያት «አስበ ትንቢታችንን ይሰጠናል» ብለው “ይወርዳል፤ ይወለዳል” ብለው ትንቢት የተናገሩለትን ወልዳላቸዋለችና ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን ዘንድ ሁል ጊዜ እርሷን እንለምን። ሐዋርያት «አስበ ሰብከታችንን ይሰጠናል» ብለው “ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ - መምህራነ ሐዲስ ሐዋርያት ለምእመናነ ሐዲስ ወረደ ተወለደ ብለው አስተማሩ” እንዲል (መዝ. ፲፰፡፬) ጽንፍ እስከ ጽንፍ ዙረው ወረደ ተወለደ ብለው ያስተማሩለትን ወልዳላቸዋለችና ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን ዘንድ ሁል ጊዜ እርሷን እንለምን። ሰማዕታት ከዓላውያን ነገሥታት፣ ከዓላውያን መኳንንት ገብተው «አስበ ትዕግሥታችንን ይሰጠናል» ብለው መከራውን ታግሠው የተቀበሉለትን፣ ምእመናን «አስበ ተጋድሏቸውን ይሰጠናል» ብለው ከፍትወታት ከእኩያት ኃጣውእ የተዋጉለት ኢየሱስ ክርስቶስን ወልዳላቸዋለችና ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን ዘንድ ሁል ጊዜ እርሷን እንለምን። ሰው ሆኖ አድኖናልና በጥበቡ እየሰፈረ የሚሰጠው፣ ዳግመኛም የጸጋው ብዛት የማይታወቅ የቸርነቱን ብዛት መርምረን እንወቅ። ሰው ሆኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፣ ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን።

  • ሄላ ሚዲያ Hela media: 🌺የሐሙስ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ🌺 ሄላ ሚዲያ (ነሐሴ ፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.) ይህ ዕለት ለምስጋና አራተኛ፤ ለፍጥረት አምስተኛ ቀን ነው። በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጸፋል። ከዚያ ላይ ሆናም ሊቁን ባርካው ምስጋናውን ጀምሯል። ከወትሮ ይልቅም ነቢያትንና ሐዋርያትን አስከትላ መጥታለች። ፩. የዕፀ ጳጦስ ምሳሌነ: ነደ እሳት ሰፍሮባት፣ በነደ እሳት ተከባ፣ ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ ድንግል ማርያምን ትመስላለች (ዘጸ. ፫፡፩-፫)። አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ሆኗልና፤ ባሕርየ (እሳተ) መለኮቱም አልለወጣትምና (አላቃጠላትምና) ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች። ዳግመኛም እርሱን ከወለደችው በኋላ ማኅተመ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች። እርሱም ምንም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ፍጹም ሰው ቢሆንም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና እሳቱን ይመስላል። ሰውም ቢሆን ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሰው ሆኖ ያዳነን የባሕርይ አምላክ ነው። ሰው ሆኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፣ ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን። ፪. የቀደመችው ሔዋን እና የሁለተኛዋ ሔዋን (ድንግል ማርያም) ንጽጽር: ይቅርታሽ (ምልጃሽ) ለሁላችን ይሆን ዘንድ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ! ሁላችን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለን። ሔዋን ባደረገችው ዓመፅ በባሕርያችን ጸንቶ የነበረ መርገመ ሥጋ፣ መርገመ ነፍስ በእርሷ ምክንያት የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የሁላችን መመኪያ ናት። “ሔዋን ምን አደረገች?” ትለኝ እንደሆነም ዕፀ በለስን በልታለች እልሃለሁ። “ወአዘዞሙ ለኪሩቤል ወሱራፌል ዘውስተ እደዊሆሙ ሰይፈ እሳት እንተ ትትመያየጥ ከመ ይዕቀቡ ፍኖተ ዕፀ ሕይወት - ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ” እንዲል (ዘፍ. ፫፡፳፬)፤ በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ። “ወአግኃሦ ለሱራፊ ዘየዐቅብ ፍና ዕፀ ሕይወት፤ ወአእተተ እምእዴሁ ኵናተ እሳት” እንዲልም በድንግል ማርያም ምክንያት ዳግመኛ ተከፈተልን። ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግም እንዲህ ሲል አስተምሯል፦ “አዳምን እንዲሞት ያደረገች ያቺ ቀን ተለወጠች። እርሱም ከሞት የሚድንባት ሌላ ቀን መጣች። እባቧ ሳትሆን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይናገር ዘንድ ተነሣ። ሔዋን ሳትሆን ድንግል ማርያምም ቃሉን ትቀበል ዘንድ ተዘጋጀች። በተንኰል የሚያስተው ሳይሆን ሕይወትን የሚያውጀው ቃል ወጣ። በሞት ዛፍ መካከል የሞት ዕዳዋን በጻፈችው ሔዋን ፈንታ ልጇ (ማርያም) የአባቷን ዕዳ ሁሉ ከፈለች። ሔዋንና እባቡ በቅድስት ድንግል ማርያምና በቅዱስ ገብርኤል ተተኩ። ያ ከመጀመሪያው የተበላሸው ነገር አሁን ተስተካከለ። የሔዋን ጆሮና ቀልብ አታላዩ በሚናገርበት ጊዜ እንደምን እንዳዘነበለ አስተውሉ፤ ያ በገነት ሲመለከታቸው የነበረው መልአክ አሁን በድንግል ማርያም ጆሮ የድኅነትን ተስፋ ሲያሰርጽና የእባቡን ክፉና መርዛማ ቃል ሲያጠፋ ደግሞ አስተውሉ፤ ሔዋን ያፈረሰችውን ሕንፃ ገብርኤል ገነባው። በዔደን ገነት ውስጥ ሆና ሔዋን ያፈረሰችውን መሠረት ዳግሚት ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ሆና ገነባችው። ከሁለት መልእክተኞች መልእክት የተቀበሉ ሁለት ደናግላን ሁለት ትውልድን ቀጠሉ፤ አንዱም የአንዱ ተቃራኒ ሆነ። በእባብ ምክንያት ሰይጣን ምሥጢርን ለሔዋን ላከ፤ በሌላ ቅዱስ መልአክ አማካኝነት ደግሞ ጌታ የምሥራቹን ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ላከ። እባብ ለሔዋን የሐሰትን ቃል ሲናገር ቅዱስ ገብርኤል ግን የእውነትን ቃል ለቅድስት ድንግል ማርያም ተናገረ። እውነትን በሚናገር አንደበቱ የቀደመውን የእባብ ቃል አደሰው፤ እውነትን ተናገረና ሐሰቱን አስወገደው። አስቀድሞ ሐሰትን ከራሱ አንቅቶ ሰይጣን ሔዋንን በዔደን ገነት አታለላት፤ ይህንንም ታላቅ ስሕተት በጆሮዋ አልፎ እንዲሰማት ፈቀደች። አሁን ግን በመጀመሪያዋ ድንግል ፈንታ ሌላ ድንግል ተመረጠች፤ በዚህች ድንግል ጆሮም ከአርያም የተላከ የእውነት ቃል ገባ። ሞት በገባበት በዚያ በር (ጆሮ) ሕይወት ገባ፤ ክፉው (ዲያብሎስ) ያጠበቀው ጽኑ የሞት ማሰሪያም ተፈታ። ኃጢአትና ሞት ሠልጥነውበት በነበረ ቦታ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በዝቶ ታየ... እባብ የስሕተትን ዜማ ለሔዋን ዘመረላት፤ ሐሰትንም ረጨባት። በተፈጥሮዋ ገና ድንግል በምትሆን በሔዋን ላይ ክፉ ምክርና ስሕተት አፈሰሰባት። በመርዝ የተለወሰና ደምን የተጠማ ክፉ ምክር በአዳም ቤት ውስጥ አስገባ። ኃይለ ልዑል የላከው መልአክ ግን እነዚህን የክፋት ሰይፎች ለመቆራረጥ ክንፉን እያማታ እየበረረ መጣ። ለሰው ሁሉ የሚሆን የድኅነት ሰነድ ይዞ መጥቶም ለድንግሊቱ (ለማርያም) አበሠራት፤ ሰገደላት፤ ሕይወትን በውስጧ አሰረጸ፤ ሰላም ዐወጀ፤ በፍቅር ቀረባት፤ የቀድሞውን የሞት ዳባ በጣጠሰው። እባብ የገነባውን የማታለል ግንብ ዳግም ላይገነባ በወልደ እግዚአብሔር እንደሚናድ ነገራት። በእባብ የታጠረው የሞት ቅጽር በወልድ መውረድ እንደሚሰባበር ቀጠሮው እንደደረሰ ነግሮ የምሥራች አላት” በማለት ከማር የጣፈጠ ትምህርቱን እያነጻጸረ አስተምሯል። ከዕፀ ሕይወትም እንበላ ዘንድ አደለን፤ ይኸውም እኛን ስለ መውደድ ሰው ሆኖ ያዳነን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው። ወዮ! ሰውን የሚወድ፣ ሰውም የሚወደው እግዚአብሔር፣ ማኅደርም ኅዳሪም ያይደለ አካላዊ ቃል፣ ሳይለወጥ ቅድመ ዓለም የነበረ እግዚአብሔር ወልድ፣ ከአብ አንድነት ሳይለይ መጥቶ ንዕድ ክብርት ከምትሆን ከእመቤታችን ሰው ሆኗልና፤ እርሱንም ከወለደችው በኋላ እንደ ቀድሞ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ኑራለችና፤ ስለዚህም ነገር አምላክን የወለደች እንደሆነች በጎላ በተረዳ ነገር ታውቃለችና ለእርሷ ድንቅ ሆኖ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? መስማትስ የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? ማወቅስ የሚቻለው ምን አእምሮ ነው? የእግዚአብሔር የጥበቡ ምላት ስፋትስ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? አንድም ለእግዚአብሔር ለጥበቡ ምላት ስፋት አንክሮ ይገባል። “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል” (ዘፍ. ፫፡፲፮) ብሎ የፈረደባት ማኅፀን የሕይወት፣ የድኅነት መገኛ ሆነች። ዕንቆ ጳዝዮን የተባለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም፦ “እስመ ቀዳሚኒ ሔዋን ኮነት ድንግል ወአስሐታ ዲያብሎስ ለማርያምሂ ድንግል አብሠራ ገብርኤል ወባሕቱ ለሔዋንሰ አስሐታ ዲያብሎስ ወወለደት ቃየልሀ ዘውእቱ ምክንያተ ሞት ወማርያምሰ ሶበ አብሠራ መልአክ ወለደት ቃለ በሥጋ ዘውእቱ መራሔ ኵሉ ኀበ ሕይወት ዘለዓለም - ቀድሞም ሔዋን ድንግል ነበረችና ዲያብሎስ አሳታት እንጂ፤ ድንግል ማርያም ግን ገብርኤል አበሠራት። ነገር ግን ሔዋንን አሳታት፤ የሞት ምክንያት የሚሆን ቃየልን ወለደች፤ ማርያም ግን መልአክ ባበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች። የሔዋንን ልብላ ልብላ ማለቷ ዕፀ በለስ የሞት ምክንያት እንደሆነ አስረዳ፤ በዚያም አዳም ተድላ ደስታ ካለበት ከገነት ወጣ። ከድንግል የተወለደ አካላዊ ቃል ግን ዕፀ መስቀል የድኅነት ምክንያት እንደሆነ ገለጠ፤ በዚያም መስቀል ቀማኛ ወንበዴ የነበረው ሰው ከአባቱ ከአዳምና ከቀደሙ አባቶች ሁሉ ጋር ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት ገባ” ብሏል

  • ✝ ፅንሰትሽ የድኅነታችን መሠረት ነው!!! ✝

  • ✝ ፅንሰትሽ የድኅነታችን መሠረት ነው!!! ✝