ሀያዕ የሙስሊሞች መገለጫ
Статистика💎እንቁ ናት በሱና ያጌጠች በኢማን ያበበች ከሽርክ ከቢዳአ ፈፅሞ የራቀች በተውሒድ ታንፃ ጌታዋን ያጠራች. رَبَّناَ اجْعَلْ اَعْماَلَناَ خَالِيصَۃً لِوَجْهِكَ الْكَرِيم
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 26
- 1/48двое суток
- 29
- 1/72трое суток
- 32
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ዒልም ሁለት ነው ዒልመ ሰጠር ወዒልመ ሰደር! ዒልመ ሰጠር በግርድፉ ሲተረጎም ከወረቀት፣ ከኪታብ የሚገኘው ነው። ይህ አስፈላጊ ዒልም ሲኾን በስፋት ሰዎች ለፍተው ለማግኘት የሚጥሩበት ነው። ሌላው «ሚን ዱኒይ» የሚባለውና እጅግም የረቀቀው የዒልም ዓይነት ዒልመ ሰደር (የልብ ዕውቀት) የሚባለው ነው። ይህ የዒልም ዐይነት ረቂቅ ነው። አላህ ለባሮቹ በተለያየ መንገድ የሚለግሳቸው ነው። ዘውቅም፣ ኢማንም ያለበት ነው። ኸድርና ሙሳን አስታውሱ። የኸድር ዒልም ዒልመ ሰደር ነው። ይህ በቁርኣን የተላቀው አገላለጽ ነው። የቁርኣንና የሐዲሶች ትምህርቶች፣ የተለያዩ ንባቦች ዓላማው ወደዚህ ረቂቅ ዐለም መሻገር ነው። ይህ መንገድ ግልጹ የሸሪዓ መንገድ ነው። የትኛውም ዒልም በመንፈሳዊነት በሰለዋት፣ በዚክር፣ በቁርኣን ቲላዋ ካልተገራ ዕውቀት በራሱ ብቻውን ድርቀትንና ጥመትን ይፈጥራል። ዒልም ስንጨምር በአምልኮና በመንፈሳዊነት ተግባራት ላይ መጨመርን ካላሳየን በጣም ከባድ የኾነ አውቆ የማጥፋት ስሜት ውስጥ እንዘልቃለን። ለዚህም ነው ዑለሞች በሰለዋትና በዚክር ዊርድ ላይ መቆየት የዒልመ ሰደር በረካን በሕይወት እንደምናገኝ የሚመክሩን።
"ከሰው ሁሉ ይበልጥ ጀግናው ማነው?" — የአሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ምስክርነት ታላቁ ሰሐባ አሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በአንድ ወቅት አብረዋቸው ለነበሩ ሰዎች ጥያቄ አቀረቡ፦ "ከሰው ሁሉ ይበልጥ ጀግናው ማነው?" አሏቸው። ሰዎቹም፦ "ጀግናውማ አንተ ነህ!" ብለው መለሱለት። አሊይም እንዲህ አሉ፦ "እኔማ ከማንም ጋር ለፍልሚያ (ሜዳ ላይ) ወጥቼ እኩል ሳልካካስ የቀረሁበት (ያላሸነፍኩበት) ጊዜ የለም። ነገር ግን እውነተኛውን ጀግና ንገሩኝ?" አሏቸው። ሰዎቹም፦ "አናውቅም፣ ማነው?" ሲሉ ጠየቁ። አሊይ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "እሱማ አቡ በክር ነው አሉ!" ቀጥለውም ምክንያቱን እንዲህ አስረዱ፦ "በበድር ጦርነት ወቅት ለአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጠለያ ሰራንና፦ 'ከአጋሪዎች (ሙሽሪኮች) ጥቃት እንዲከላከልላቸውና ማንም እንዳይደፍራቸው ከመልእክተኛው ጋር የሚቆየው ማነው?' አልን። በአላህ እምላለሁ! ማንም ወደ እሳቸው ሳይቀርብ አቡ በክር ሰይፉን መዝዞ በመልእክተኛው ራስ ላይ ዘብ ቆመ። ሊጠጋቸው የሞከረውን ሁሉ እየተከላከለ ማንም እንዳይቀርባቸው አደረገ። ስለዚህ እሱ ከሁሉ በላይ ጀግና ነው።" አሊይ ንግግራቸውን በመቀጠል ሌላም ታሪክ አወሱ፦ "የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቁረይሾች ሲያዳፏቸው፣ ሲያጎሳቁሏቸውና 'አማልክትን ሁሉ አንድ አምላክ ያደረግከው አንተ ነህ?' እያሉ ሲያዋክቧቸው አየሁ። በአላህ እምላለሁ! በዚያ አስፈሪ ሰዓት አቡ በክር ብቻ ነው ወደ መካከላቸው ዘልቆ በመግባት ይህንንም ሲመታ፣ ያንንም ሲገፋና ሲያባርር ያየሁት፦ 'ወዮላችሁ! ጌታዬ አላህ ነው ስላለ ብቻ ሰውን ትገድላላችሁ?' እያለ የተከላከለላቸው።" ከዚህ በኋላ አሊይ የለበሱትን ካባ ከፍ አደረጉና ፂማቸው በዕንባ እስኪረስ ድረስ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ። በመቀጠልም በዚያ ለነበሩት ሰዎች እንዲህ የሚል ጥያቄ ሰነዘሩ፦ "በአላህ ይሁንባችሁ ንገሩኝ፤ በቁርአን የተወደሰው የፈርዖን ቤተሰብ የሆነው አማኝ (ሙእሚን ) ይበልጣል ወይስ አቡ በክር?" ሰዎቹ ሁሉ ዝም አሉ። አሊይም፦ "አትመልሱልኝም?" አሉና ራሳቸው እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "በአላህ እምላለሁ! ከአቡ በክር አንዲት ሰዓት ከፈርዖን ቤተሰብ አማኝ ሺህ ሰዓታት ትበልጣለች። ምክንያቱም ያኛው ሰው (የፈርዖን ዘመድ) እምነቱን ይደብቅ ነበር፤ አቡ በክር ግን (ህይወቱን ለሰይፍ አሳልፎ በመስጠት) እምነቱን ለዓለም ይፋ ያደረገ ጀግና ነው።"በማለት የአቡ በክርን ጀግንነት መሰከሩ። ምንጭ፦ *ሙስነድ አል-በዛር / ታሪኽ አል-ኹለፋእ (ለኢማም አስ-ሱዩጢ)*
ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፡- “የፈለግከውን ያክል ብትኖር ትሞታለህ! የፈለግከውን ብትወድ ትለየዋለህ! የፈለግከውን ስራ ዋጋውን ታገኛለህ! እወቅ! የሙእሚን ክብሩ የሌሊት ሰላት መስገዱ፣ የበላይነቱም ከሰዎች መብቃቃቱ ነው፡፡” (ሐኪም ዘግበውታል፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)
መዲና እንደ ወናፍ ናት! አንድ ሰው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘንድ መጣና እስልምናን በመቀበል ላይ ቃል ገባላቸው፡፡ በነጋታው ደግሞ ተመልሶ መጣ። ወባ ይዞት እየተንዘፈዘፈ ነበር። ለነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ.) “ለርስዎ በገባሁት ቃል የተነሣ ነውና የታመምኩት ቃልኪዳኔን ይመልሱልኝና በፊት እንደነበርኩት ልሁን፡፡” አላቸው። ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ.) ሀሳቡን አልተቀበሉትም። ሰውዬውም መዲናን ለቆ ሄደ። ከዚያም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ አሉ፦ “መዲና እንደ ወናፍ ናት መጥፎነቷን ሁሉ ገፍትራ ታወጣለች፣ ጥሩነቷ ይቀራል።” (መዲና ከነቢዩ ዱዓ በኋላ ወባ ከውስጧ ተጠርጎ ወጣ።) አንዳንድ ሰው እንዲህ ነው፡፡ ... አላህን የሚያመልከው ቋፍ ላይ ሆኖ ነው። ችግር ሲያገኘው ይንሸራተታል፡፡ መልካም ሲገጥመው ይፀናል፡፡ እንደነርሱ አትሁን፡፡ አንዳንዶች በአምልኮ ላይ እያሉ ጭምር መፈተን መኖሩን አያውቁም። ከፍጥረቱ አንፃር የአላህን ፈለግ አይረዱም፡፡ አንዳንዶች አላህን የሚወዱት በሠጣቸው ልክ ነው። እነርሱ በሚጠሉት ነገር የፈተናቸው እንደሆነ ይርቁታል። አንዳንዶች ገንዘብ የተሠጣቸው እንደሆነ አብዝተው ያመሰግናሉ፤ ካጡ ደግሞ አምርረው ይጠላሉ፣ ይነጫነጫሉ፡፡ አንዳንዱ ሰው በወዳጆች መከበብ ደስ ይለዋል፣ በጣም ከሚወዳቸው መካከል አንዳቸውን በሞት ያጣ እንደሆነ ክፉኛ ይራገማል፣ ራሱንም ሆነ አምላኩንም ይጠላል፡፡ አንዳንዶች እኛ የሰው ልጆች የአላህ ባሮች መሆናችንን አይገነዘቡም፣ አገልጋይ ባሮቹ እንደሆንን አያስታውሱም፡፡ ባሮች ጌታቸው እንዳረጋቸው ነው የሚሆኑት፣ ለጌታ መልስ አይሠጠውም፣ ከአለቃ ጋር ክርክር አይገጠምም፡፡ የዱንያ ፈተና እንደሆነ ለአላህ ነቢያት ጭምር አልቀረም፡፡ ነቢዩ ዕቁብ በልጃቸው መጥፋት ምክንያት ለረጅም ዘመን ተክዘዋል፣ ነቢዩ ዩሱፍ ታስረዋል፣ ነቢዩ ዒሳ ደህይተዋል፣ ነቢዩ አዩብ ለዓመታት ታመው ከርመዋል፣ ነቢዩ ዩኑስ ተጨንቀዋል፣ ግራ ተጋብተዋል…. በሁሉም ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይስፈን፡፡ ይህች ዓለም የፈተና ናት። በአላህ ፈቃድ - መገናኛችን ጀነት ነው
без подписи
ከህይወት ተስፋ የምንቀርጥበት ቀን ይመጣል ... ከዛም .. ሞት መጥቶ ልብሳችንን ሌላ ሰው ከኛ ላይ አውልቆት እርቃናችንን ያጥበናል ... ከዛም ጨለማው ቀብር አለ ..... ባለንበት ሁኔታ አሏህን መገናኘት አሳፋሪ ነውና ወደሱ እንመለስ ! https://t.me/MerkezulimamiAhmed
#የኔ እይታ ትናንት ሰወችን ከሀራም ሲከለክል እና ወደ ኸይር ሲ'ያመላክት የነበረ ሰው ዛሬ ወንጀል ላይ ወድቆ ስናየው ለምንድነው የምንደሰተው? ያኔ እየሰራን የነበረውን ወንጀል እንድናቆም ሲያስጠነቅቀን ከኛ የተሻለ እንደሆነ ተሰሞቶን ስለነበር እና አሁን ከፍታውን እኛ ለመውሰድ ስለምንፈልግ ይሆን? ወይስ ኢማን ቋሚ ነገር ስለሚመስለን? ልባችን ውስጥ ያለው ኢማን አንድ ቦታ ላይ ለደቂቃም ቢሆን ያለበት አይቆይም! ከፍ ወይ ዝቅ ይላል። ትናንት በጥሩ የኢማን ከፍታ ላይ ሁኖ ሰወችን ከመጥፎ ሲከለክል እና በኸይር ሲያዝ የነበረ ሰው ዛሬ ከነበረበት ከፍታ ተንሸራቶ ያንኑ አልያም ሌላ ወንጀል ሲሰራ ልታየው ትችላለህ። ያኔ ግን እኔን ሲመክር እንዳልነበረ ዛሬ እሱ ተገኘበት እያልን ከመጠቋቆም ይልቅ ወደነበረበት የኢማን ከፍታ እንዲመለስ ዱአ ማድረግ ግድ ይለናል። አስታውስ እስኪ.. ከአመታት በፊት ይቀፍህ የነበረ እና ዛሬ እንደቀላል የምትሰራው ሀጢያት የለም? ከዚህ በፊት ስትሰራው የነበረ እና ዛሬ በአላህ እገዛ ተውበት አድርገህ የተመለስክበት እና አሁን ስታስበው የሚያንገሸግሽህ ወንጀልስ የለም? ሰወች ከከፍታቸው ተንሸራተው ስናይ አላሁመ ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሰቢት ቀልቢ አላዲኒክ ከማለት ይልቅ መጠቋቆም የቀለለን እንዴት ይሆን?
✍ ተረት የሚመስለው የታቢዒዩ እውነተኛ ታሪክ..... የታሪኩ አስተላላፊ ዐብዱላህ ቢን ሙሐመድ እንዲህ ይተርከዋል፦ የድንበር ጥበቃ ስራ ላይ ሳለሁ ከዕለታት በአንዱ ቀን በግብፅ ድንበር በኩል ተራችን ሆነና ወደዝያ ሄድኩኝ። ወደ ባህር ዳርቻው ስደርስ ሜዳው ላይ አንዲት የድንኳን ጎጆ አየሁኝ። ጎጆዋ ውስጥ እጆቹና እግሮቹ የተቆረጡ፤ ማየትም መስማትም የሚቸግረው፤ ከአካሉ ምላሱን ብቻ ያልተያዘ አንድ ሰው አለባት። ሰውየው ያቺ ድንኳን ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ....... " አላህ ሆይ! ከፈጠርካቸው በርካታ ፍጥረታት አስበልጠህ ላጎናፀፍከኝ በርካታ ፀጋህዎችህን ማወደስ የሚችል ምስጋና እንዳመሰግንህ ወፍቀኝ!!" ሲል ሰማሁት። በውስጤ "ይህ ሰው ስለየትኛው ፀጋው እንደሚያመሰግንማ መጠየቅ አለብኝ" ብዬ ቀርቤው ሰላምታ አቀረብኩለት። " አላህ ሆይ! ከፈጠርካቸው በርካታ ፍጥረታት አስበልጠህ ላጎናፀፍከኝ በርካታ ፀጋህዎችህን ማወደስ የሚችል ምስጋና እንዳመሰግንህ ወፍቀኝ" "ስትል ሰምቼሃለሁ: ስለ የትኛው የተዋለለህ ውለታ ነው እንዲህ አብዝተህ የምታመሰግነው?? ከሌሎቹ አስበልጦ የሰጠህ ፀጋስ ምንድን ነው??" አልኩት። "ጌታዬ ለእኔ ያደረገልኝን አትመለከትምን? ወላሂ! ከሰማይ እሳት ልኮ ብታቃጥለኝ፤ ተራራ ደርምሶብኝ ብታወድመኝ፤ ባህርን አዞ ብታሰምጠኝ፤ መሬትን አዞ ብትውጠኝ እንኳ ጌታዬ ለዋለልኝ ለዚች ምላሴ ውለታ ከምስጋና ሌላ ምጨምርለት አይኖረኝም!!" አለኝ። "እንደው ከመጣህ አይቀር ግን: እንደምታየኝ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለሁት፤ ለራሴ ምንም መጥቀምም ይሁን መጉዳት አልችልም። አንድ ሰላት ሲደርስ ውዱእ የሚያስደርገኝ፤ ሲርበኝ የሚያበላኝ፤ ሲጠማኝ የሚያጠጣኝ ልጄ አብሮኝ ነበር። ወጥቶ ሳይመለስ ከቀረ ሦሥት ቀናት ሆነውታል። እስኪ እሱን አፈላልገህ አምጣልኝ" አለኝ። በአላህ ይሁንብኝ! አንድም ሰው አንድን ሰው ለመርዳት ተንቀሳቅሶ አጅር አያገኝም: የአንተ ዓይነቱ ለመርዳት የሚንቀሳቀስ ሰው የተሻለ አጅር ቢያገኝ እንጂ!! ብዬው ፍለጋ ሄድኩኝ። ከእሱ ወጥቼ ብዙም ሳልጓዝ ያ... የጠቀሰልኝን ልጅ ቋጥኞች መሃል ወድቆ: ስጋው አውሬዎች ተቆራምተውት አገኘሁት። አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ወደ ሰውየው ተመልሼ ይህንን መርዶ እንዴት እንደምነግረው ግራ ገባኝ። በሀሳብ ተውጬ በመመለስ ላይ ሳለሁ.... የነብዩላህ አዩብ ታሪክ እያወሳሁ ሰውየውን ማሳበር እንዳለብኝ ታወሰኝ ስደርስ ሰላምታዬን አቀረብኩለት። ሰላምታውን መለሰልኝ። "ባልደረባዬ አይደለህምን?" አለኝ። "ነኝ" አልኩት። "እና ጉዳዬ ከምን ደረሰ?" አለኝ። "አላህ ዘንድ ከአንተና ከነብዩ አዩብ ማን የተከበረ ይመስልሃል?" አልኩት"በእርግጥም ነብዩ አዩብ ነው" አለኝ። "አላህ ምን እንዳደረገው ታውቃለህን? በልጆቹ: በቤተሰቦቹ: በንብረቱ ሁሉ እንደፈተነው ታውቃለህን?" አልኩት። "አዎን አውቃለሁ" አለኝ። "ታድያ ጌታው እንዴት ነው ያገኘው" አልኩት "ታጋሽና አመስጋኝ ሆኖ አግኝቶታል" አለኝ። "በዚህም አላበቃለትም: ከዘመዶቹ ከወዳጆቹ ሁሉ ነጥሎ ብቸኛ እስከሚያደርገው ድረስ" አልኩት። "በእርግጥም አው" አለኝ። "እና ጌታው እንዴት ነበር ያገኘው?" አልኩት። "ታጋሽ እና አመስጋኝ ሆኖ አግኝቶታል!! አላህ ይዘንልህ ጉዳዩን አሳጥረህ ንገረኝ" አለኝ "እንግዲያውስ... ያ እንድፈልግልህ የላከኝ ልጅህ ቋጥኞች መሃል ወድቆ ስጋውን አውሬዎች ተቆራምተውት አግኝቼዋለሁ። አላህ ምንዳህን ያተልቅልህ ሰብሩም ይወፍቅህ!!" አልኩት። "ከልጆቼ አንድም እሱን አምፆ በጀሀነም የሚቀጣ ያልፈጠረብኝ አላህ ሙሉ ምስጋና ይድረሰው!! ኢናሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!" አለ። በዝያው ቅፅበት ትንፋሹ ተናንቆት ሲቅ...ሲቅ አለውና ላይመለስ አሸለበ!! "ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" ካልኩኝ በኋላ የሰውየው ሁኔታ እኔም ላይ ከባድ ሙሲባ ሆነብኝ። ይህንን ሰው ትቼው ብሄድ ጀናዛው አውሬ ሊበላው ነው። አብሬው ብቆይ አልጠቅመው አልጎዳው፤ እንዲው ግራ ገብቶኝ በአንዲት ጨርቅ ሰውነቱን ሸፍኜለት ራስጌው ጋ ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ። በዚሁ መልኩ ተቀምጬ ሳለሁ ከየት እንደመጡ ሳላውቅ አራት ሰዎች ከበቡኝ። "ዐብደላህ ሆይ! ምን ሆነህ ነው?? ምን ገጥሞህ ነው??" አሉኝ። የሆነውን ሁሉ ዘረዘርኩላቸው። "እስኪ ፊቱን ክፈትልን ድንገት ካወቅነው" አሉኝ ከፈትኩላቸው። ልክ ፊቱን ስከፍትላቸው.... ሁሉም ጀናዛው ላይ ተደፍተው ማልቀስ ጀመሩ። አንዱ ዓይኖቹ ይስማል፤ አንዱ እጁ ይስመዋል፤ "አላህ ዕርም ካደረጋቸው ነገሮች ተሰብራ የኖረች ዓይን: ሰዎች በተኙበት እየሰገደ ያደረ አካሉ....." እያሉ ይላቀሳሉ። " እንደው አላህ ይዘንላችሁና ይህ ሰው ማን ነው??" አልኳቸው። " ይህ እኮ.... የኢብኑ አባስ ባልደረባ : አላህንና መልእክተኛውን አብዝቶ ይወድ የነበረው; 👇 👉አቡ ቂላባ አል_ጁርሚ ነው!!" አሉኝ። አጥበን፤ እኛጋ በነበረ ልብስ ከፍነን፤ ሰግደንበት ቀበርነው። እነርሱም ወደ ሐጃቸው ሄዱ: እኔም ወደ ጥበቃዬ ሄድኩኝ። ምሽቱ በጨላለመ ጊዜ ለማረፍ ጋደም ባልኩበት ያንን ሰው በህልሜ አየሁት። ከጀነት ጨፌዎች አንዱ ጨፌ ላይ ሆኖ፤ ከጀነት አልባሳት ለብሶ....... {سَلَٰمٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى ٱلدَّارِ} {"ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን: (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ሀገር ምንኛ ታምራለች" (ይሏቸዋል)፡፡} የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ ሲቀራ ሰማሁት። "ያ.... ባልደረባዬ አይደለህምን?" አልኩት። "አዎ ራሱ ነኝ" አለኝ። "ይህንን እንዴት ሆነልህ?" አልኩት;...... "ለአንድ ባሪያ አላህ ዘንድ የተፃፈለት ደረጃ አለው። ያንን ደረጃ የሚገኘው ግን፦ በሙሲባ ሰዓት በሚደረግ ሰብር፤ በድሎት ሰዓት በሚደረግ ምስጋና እና በድብቅም ይሁን በግልፅ ለአላህ በሚኖር ፍራቻ ነው" አለኝ። ታሪኩ በበርካታ የታሪክ መዛግብት ላይ በስፋት ተዘግቦ የሚገኝ ነው። የአቡ ቂላባ እዝያ ዳርቻ ላይ ተነጥሎ የመኖር ምክንያት በሌሎች ዘገባዎች ላይ እንደመጣው፦ አቡ ቂላባ በዘመኑ በስራ ከነበሩ ትላልቅ ዑለማዎች፤ ዙሃዶችና ዑባዶች ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነበር። ለየት ባለ መልኩ ስለ አሕካምና ስለ ሸሪዐ ህግ የበለጠ ዐዋቂ ነበር። ስለሆነም በዘመኑ የነበሩ መሪዎች በዳኝነት ሊሾሙት ሲፈልጉ እሱ ግን ሹመት ላይ ከመቀመጥ ይልቅ ተነጥሎ አላህን መገዛት መርጦ ወደ ሻም በድብቅ ተሰደደ። በመጨረሻም በዛ መልኩ እዝያው ሞቶ እዝያው ተቀበረ።
" ቀልብህን 3 ቦታዎች ላይ ፈልግ .... " " እነዚህ 3 ቦታዎች ላይ ቀልብህን ካላገኘህ አንተ ቀልብ የለህምና አላህ ቀልብ እንዲሰጥህ ለምነው " https://t.me/MerkezulimamiAhmed
#የኔ እይታ ኢማን ቋሚ ነገር ቢሆን ጥሩ ነበር? ወይስ አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ ማለቱ ነው ኸይሩ? ስገዱ፣መድረሳ ሂዱ የምንባልበት የልጅነት ጊዚያችን አልፎ ለራሳችን ሀላፊነት መውሰድ ስንጀምር እና ኢማናችን መጨመር ሲጀምር እራሳችንን ከፈርድ አልፎ በሱና ኢባዳወች ቻሌንጅ ማድረግ ጀመርን፣ ሱና ሰላቶች ላይ ተጋን፣ ለይል ሰላትን አጣጣምን፣ ብዙ ቲላዋወች ከኛ ተሰሙ ፣ ደርስ ባለበት ቦታ ተገኝተን ዲናችንን በትንሹም ቢሆን ለማወቅ ሞከርን፣ እኩያወቻችን ካሉበት ዝንጋቴ እርቀን ወደአላህ ቀረብን ፣ ትንንሽ የሚባሉ ወንጀሎች ሳይቀሩ ዘገነኑን ፣ሰወች እንዴት አላህን ይዳፈራሉ ፣ሀያዕ እንዴት ጠፋ ስንል ተደመጥን። ልክ እንደ ልጅነታችን ጊዜ ይሄም አለፈና.... ከአመታት በኋላ እራሳችንን በብዙ ዱንያዊ ጉዳዮች ውስጥ ሰምጦ አገኘነው። ከአመታት በፊት የነበረው ጁህድ ተረስቶ እንደልጅነት ጊዚያችን ፈርድ ሰላትን በሰአቱ ለመስገድ ስንታገል ተገኘን፣ ቁርአን ጁመአ አልያም ረመዳን ላይ የምናነሳው የሩቅ ዘመድ ሆነብን፣ ዉሏችን ለዱንያም ለአሄራም በማይጠቅም ጉዳይ ከመባከኑ ባሻገር ድካም አዝሎት የተኛ ሰውነታችን ለይል ሰላት ቀርቶ ለፈጅር መነሳት ከብዶት በተኛንበት ፀሀይ ትወጣብን ጀመር። ይቺማ ትንሽ ወንጀል ናት አዛኝ የሆነው አላህ ይምረኛል እያልን ልባችንን በትናንሽ ጥቋቁር ወንጀሎች ብዛት አደነደነው፣ ትናንት ጉድ ያስባለን ወንጀል ላይ ተገኘን፣ ወንጀልን የማጣጣም ደረጃ እስክንደርስ ኢማናችን ተሟጠጠ። በዚህ ሁሉ መሀል ግን ልባችን አላህን ፍሩ፣ ኧረ አላህ እያያችሁ ነው ፣ ኧረ ከአላህ ራቃችሁ እያለ ይወቅሰን ነበር። ከዛም ተመለስን ፊታችን በእምባ እርሶ ምህረትን ተማፀንን ፣ ወደቀድሞ አቋማችን ለመመለስ ብዙ ታገልን፣ ፈርድ ነገሮች ላይ ብቻ ላንገደብ አቋም ያዝን፣ ቁርአን ጋር አዲስ የወዳጅነት ስምምነት ፈፀምን ፣ ካለንበት ዝንጋቴ ወጥተን እራሳችንን እዚህ ነኝ ብንል የማናፍርበት ቦታ ላይ ለመሆን ወሰንን ፣ የወንጀሉን ትንሽነት ሳይሆን የጌታችንን ትልቅነት አስበን ከወንጀል ለመራቅ ተጋን። በዚህ ሁኔታ ጥቂት የማይባሉ ጊዜያትን አሳለፍን ከዛ...ከቀድሞ ኢማናችን ከፍ ብለን እንደበረርን አስበን ከሰወች የተሻለ አቢድ እንደሆንን ማሰብ ስንጀምር እና ሰወችን ማሳነስ ስንጀምር የኢባዳ ጥፍጥና ተነሳብን። የልብ እረፍት እና የኢማን ስክነት አጣን። የሰጋጅ ባህሪ አልታይብን አለ፣ ከቁርአን ከማነብነብ ያለፈ ጥቅም አጣን ፣ ይህን ጊዜ ያቺ ፈርድ ሰላት አሳልፋ የምታለቅስ፣ ቁርአን ከቀራሁ ቆየሁ ብላ እራሷን የምትወቅስ፣ ለለውጥ ጥልቅ ፍላጎት የነበራትን ነፍሳችንን ተመኘን። ከዛ ደሞ ጥሩ የኢማን ከፍታ ላይ ሆንን ከዛ ደሞ ወደቅን። #በነዚህ የኢማን ከፍታ እና ዝቅታ ውስጥ ዛሬም እንዋልላለን። ምክንያቱም ኢማን በየሰከንዱ ከፍ ወይ ዝቅ የምትል ፣ባለችበት ለሰከንድ የማትቆይ ናት። ሂወታችን ውስጥ የኢማን ዝቅታው ወይስ ከፍታው ነው እያመዘነ ያለው? ጥያቄው ያ ነው።
ኢብኑል ቀይም አል-ጀውዚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ > "በልብ ውስጥ መበታተን (ትርምስ) አለ....ወደ አላህ በመዞር እንጂ አይሰበሰብም። በልብ ውስጥ የብቸኝነት ስሜት አለ....በአላህ መቃረብ እንጂ አይወገድም። በልብ ውስጥ ሀዘን አለ... አላህን በማወቅና ለእርሱ እውነተኛ በመሆን በሚገኝ ደስታ እንጂ አይጠፋም። በልብ ውስጥ ጭንቀት አለ...ወደ አላህ በመሸሽ እንጂ እርካታን አያገኝም።
ٰ • ○ ° 🌹🌹🌹• ○ °• ○ °• ○ ° • ○ 🌹🌹🌹🌹 • ○ ° 👈አበባውን • ○ °🌹🌹🌹🌹🌹 በመንካት• ○ ° • 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ብቻ ምርጥ ○ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 የሱና 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡 ° :. 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ያገኛሉ📡 • 🌹🌹🌹🌹🌹 ° :. * • ○ • ○ 🌿🌹🌹🌿 • ○ ° 🌿🌿 👈 • 🌿 • ○ ° 🌿🌿 • ○ ° 🌿 • ○ ° 🌿🌿🌿 • ○ ° 🌿 🌿🌿🌿🌿 • ○ ° 🌿 🌿🌿🌿🌿🌿 • ○ ° 🌿 🌿🌿🌿🌿 • ○ ° 🌿 🌿🌿🌿 • ○ ° 🌿 🌿° :. * • ○ °• ○ ° 🌿° :. * • ○ 🌿° . °☆ . * ● ¸ . ★ 🌿° :. * • ○ ° ° . 🌿. * ● ¸ 🌿 በቀላሉ ይቀላቀላሉ ። ☆ . * ● ¸ . ★ ° . * ° . °☆ . * ● ¸ . ★ ° :. * • ○
ከሚከተሉት መካከል በአረበኛ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናል የትኛውን ጠቃሚ ትምህርት መማር ይፈልጋሉ ✍የአረበኛ የእጅ ፅሁፍ ትምህርት ✍የአረበኛ ፊደላቶች አነባበብ ትምህርት ✍ሶርፍ/متن البناء في علم التصريف / ✍ነህው/متن الآجرومية/ ✍አረበኛ ቋንቋ/دروس اللغة العربية / ✍ተጅዊድ/تيسير أحكام التجويد / ✍ቁረአን / القرآن الكريم / ✍ሁሉንም በደረጃ ለመማር ወደ ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል https://t.me/arabicmedia1
السلام عليكم
ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ አሏህ ያስችለው
ልብህን በሰው ላይ አታንጠልጥል። ልብ የተፈጠረው አላህን ለመውደድ ነው። ከ አላህ ውጪ ባለ ነገር ላይ ውዴታንና እርጋታን አገኛለሁ ብለህ አትድከም።በፍጹም አታገኝም። ሰው ከሆነ ልብህን ሁሌም እንዳስከፋ ነው ሚኖረው። ሰዎች ሁሉ ደካማና ጎዶሎ በመሆናቸው ኡዝር ተሰጧቸዋል።ልብህ ያለ አላህ ሊረጋ፣ ደህንነት ሊሰማው፣ እንደማይችል እስክታረጋግጥ ድረስ ስትዋልል፣ ስትታመም ትኖራለህ። እሱን ስታገኝ ለሱ ብለህ ትወዳለህ። አላህ የወደደውን ሰው ደግሞ ሌሎቹም እንዲወዱት ያደርገዋል። ኢብኑ ተይሚያህ رحمه الله መጅሙእ ፈታዋ 10/134
ለካ ብዙ ስብራቶችን ምናስተናግደው...ዱንያን በጣም ስለምንወድ...የሷ መሙላትና መጉደል ለልባችን ጉዳይ ስለሆነ ነው::. ጭንቅ ላይ ስንሆን አሏህን እንለምነውና ከዛ ነጃ ሲለን እናምፀዋለን...ልክ መርከቧ ላይ እንደነበሩት ሰዎች...አሏህ ግን ከዛ ሁሉ ወንጀላችን ጋር አዋርዶናል?? ወሏሂ አንዴም አላወረደንም... ተመልሰን ወደ እርሱ በመጣን ቁጥር በእዝነቱ ይጠግነናል...አቤት!! አሏህ ግን ለባሪያዎቹ ያለው ፍቅር!!... ደጋግመን በጠየቅነው ቁጥር..በጨቀጨቅነው ቁጥር...በጠራነው ቁጥር...ይሰማናል!!.... በእርምጃ በቀረብነው ጊዜ በሩጫ ይቀርበናል::.. እሱኮ ሱጁድ ላይ የነገርነውን የማይረሳ ጌታ ነው::........እና ለ ዱንያ መጨነቃችን ለምን ነው? ዱንያ ምንድን ናት??....ከአሏህ ጋር ያለንን ነገር ብቻ ማሳመር ነው...እሱ ነገሮችን ባለሰብነውና ለኛ በተሻለ ሁኔታ ያደርግልናል:: ከልክ ያለፈ ማዘንና ጭንቀት የኢማን ድክመትም ነው... በቃ በቀዷ እና በቀድር ማመን ግድ ነው::.. ስለምንም ነገር ከልክ በላይ ማዘን አያስፈልግም:: በጌታውም የሚያምን ሰው መጎደልንም መጨመርንም አይፈራም፡፡ የሰዎችን ውዴታ...የዱንያን ውዴታ መፈለግ ትተን..የሚወደንን አሏህ ውዴታ እንፈልግ::...
без подписи
ሞት ሀቅ ሁኖ ሳለ ውሸት ነው የተባልን ይመስል ምን ይሆን ያዘናጋን! ኢላሂ ኻቲማችንን አሳምርልን
ከሚከተሉት መካከል በአረበኛ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናል የትኛውን ጠቃሚ ትምህርት መማር ይፈልጋሉ ✍የአረበኛ የእጅ ፅሁፍ ትምህርት ✍የአረበኛ ፊደላቶች አነባበብ ትምህርት ✍ሶርፍ/متن البناء في علم التصريف / ✍ነህው/متن الآجرومية/ ✍አረበኛ ቋንቋ/دروس اللغة العربية / ✍ተጅዊድ/تيسير أحكام التجويد / ✍ቁረአን / القرآن الكريم / ✍ሁሉንም በደረጃ ለመማር ወደ ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል https://t.me/arabicmedia1